ማቴዎስ 21፡1-27

  1. ኢየሱስ እንደ ሰላም ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ (ማቴ. 21፡1-11)

በዚህን ጊዜ ከዳዊት የዘር ሐረግ የወጣ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን ከገዛ ከ600 ዓመታት በላይ አልፎ ነበር። እነዚህ ዓመታት አይሁዶች መሢሑን ሲናፍቁና ሲጠብቁ የቆዩባቸው ጊዜያት ነበሩ። ኢየሱስ ይፋዊ አገልግሎቱን በጀመረ ጊዜ፥ ሰዎች ደጋግመው የሚያነሡት ጥያቄ፥ «ይህ የዳዊት ንጉሥ ነውን?» የሚል ነበር። አንድ ቀን ንጉሣቸው በአህያ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ። ለምን በሰጋር በቅሎ ላይ ሳይሆን በአህያ ላይ ተቀመጠ? ክርስቶስ ሌላ የመጓጓዣ እንስሳ ለማግኘት የሚያስችል ገንዘብ አልነበረውም? በጥንት ዘመን አንድ ንጉሥ የሚቀመጥበት የመጓጓዣ እንስሳ ማንነቱን ያሳይ ነበር። በፈረስ ላይ ከተቀመጠ ይህ ኃይልና ሥልጣን ያለው ድል ነሺ ንጉሥ እንደሆነ ያሳይ ነበር። ነገር ግን በአህያ ላይ ተቀምጦ ከመጣ በትሕትና ሕዝቡን የሚያገለግል ሰላማዊ ንጉሥ መሆኑን ያሳይ ነበር። (ከመሳ. 10፡4፤ 2ኛ ሳሙ. 16፡1-2 ሉሎች የአይሁድ መሪዎች በአህያ ላይ ተቀምጠው መጓዛቸውን የሚያመለክቱ ምሳሌዎችን ተመልከት። ይህ ትንቢት ስለመፈጸሙ ዘካ 9፡9ን አንብብ።) ኢየሱስ በአህያ ላይ ተቀምጦ ሲመጣ አይሁዶች ከዳዊት የዘር ሐረግ የወጣ መሢሕ መሆኑን እየገለጸ እንደሆነ ተረድተዋል። በዚህ ጊዜ እጅግ ደስ ተሰኝተው እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ጀመር። ኢየሱስ ሰዎች መሢሕነቱን እንዳይናገሩ ሲያስጠነቅቅ የቆየ ሲሆን (ማቴ. 1፡9)፥ በዚህ ጊዜ ግን የተሰጠውን ክብር ተቀብሏል።

የክርስቶስ የሕይወት ፍጻሜ እየተቃረበ ሲመጣ፥ ማቴዎስ አሁንም ክርስቶስ ባደረጋቸውና ጥንታዊ ትንቢቶችን በመፈጸሙ ላይ ትኩረት አድርጓል። ስለ መሢሑ መምጣት የሚናገር የብሉይ ኪዳን የተስፋ ቃል ሁሉ፥ በክርስቶስ እንደ ተፈጸመ፥ ለአይሁዶች በድጋሚ አሳይቷል። ክርስቶስን ካልተቀበሉ ሌላ መሢሕ ሊኖራቸው አይችልም ነበር።

  1. ኢየሱስ ቤተ መቅደሱን አፅዳው (ማቴ. 21፡12-17)

ኢየሱስ ይናደዳል ብለን አንገምትም። ስለዚህ እርሱ የዋህ፥ ታጋሽና ደግ እንደሆነ እናስባለን። በእርግጥም ኢየሱስ በተለይ ለኃጢአተኞች እንዲህ ዓይነት ባሕርይ ያሳይ ነበር። ነገር ግን ክርስቶስ ሰዎች የእግዚአብሔርን አምልኮ ሲያበላሹ በመመልከቱ በጣም ተቆጣ። ፈሪሳውያን ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር እንዳይቀራረቡ የተሳሳተ መንገድ በማሳየታችው ተቆጣቸው። በቤተ መቅደሱ ሕዝቡ እግዚአብሔርን እንዳያማልክ ባደረጉትም ወገኖች ላይ ተቆጣ።

[ማስታወሻ:- ክርስቲያኖች ሊቆጡ ይችላሉ? መልሱ፥ አዎን የሚል ነው፡፡ (ኤፌ 4፡26 አንብብ፡፡) መቆጣት ያለብን ግን ኃጢአተኛችን ሳይሆን፥ በሰዎችና በማኀበረሰቡ ኃጢአት ላይ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ክብር በሚያጎድፉ ነገሮች ላይ ሊሆን ይገባል። ብዙውን ጊዜ ግን ኃጢአትን እታገሥ በሆነ መንገድ የሚጎዱንን ሰዎች እንቆጣለን፡ ይህ ኃጢአት ስለሆነ መናዘዙ ተገቢ ነው።]

የውይይት ጥያቄ:- ሀ) ብዙ ሰዎች በተሳሳተ መንገድ የሚቆጡባቸውን ጉዳዮች ዘርዝር። ለ) እግዚአብሔር ክርስቲያኖች እንዲቆጡ የሚፈልባቸውን ነገሮች ዘርዝር፡፡ ሐ) የተቆጣህነትን የመጨረሻ ጊዜ አስታውስና ይህ የጽድቅ ቁጣ ነበር ወይስ የኃጢአት? በእነዙህ በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

ሄሮድስ የሠራው ቤተ መቅደስ አራት የተለያዩ ክፍሎች ነበሩት፡፡ በውስጠኛው ክፍል የካህናት አደባባይ ይገኛል። በዚህ አደባባይ ውስጥ ቆመው ሊያመልኩ የሚችሉት ካህናት ብቻ ነበሩ፡፡ ከዚያ ቀጥሉ አይሁዳውያን ወንዶች የሚያመልኩበት የወንዶች አደባባይ ይገኛል። ሦስተኛው አይሁዳውያን ሌቶች የሚያመልኩበት የሴቶች አደባባይ ነበር፡፡ በመጨረሻም፥ ለአሕዛብ አምልኮ የተፈቀደ የአሕዛብ አደባባይ ተዘጋጅቷል። ለኣሕዛብ ከዚህ ውጫዊ አደባባይ በቀር ወደሌሎቹ አደባባዮች ለመቅረብ መሞከር ራስን ለሞት መጋበዝ ነበር፡ በዚሁ የአሕዛብ አደባባይ ነበር ነጋዴዎች ንግዳቸውን የሚያጧጡፉት። ሰዎች የአሕዛብ ገንዘቦቻቸውን ወደ ተቢው የቤተ መቅደስ ገንዘብ እንዲለውጡ የሚያስችል ገንዘብ ለዋጮች ነበሩ። እንዲሁም፥ ለመሥዋዕት እንስሳትን የሚሸጡ ሰዎች ነበሩ፡፡ የሚያሳዝነው እነዚህ ነጋዴዎች ብዙውን ጊዜ ከካህናት ጋር በመተባበርና ሕዝቡ የተፈለጉትን እንስሳት በውድ ዋጋ እንዲገዙ በማስገደድ ከፍተኛ ገንዘብ ለማትረፍ ይሞክሩ ነበር፡፡ (ይህ በፋሲካ ሰሞን ዶሮ እንደሚወደድ ማለት ነው፡፡) ኢየሱስ ነጋዴዎችን ያስወጣው ከዚህ የአሕዛብ አደባባይ ነበር፡፡ ማርቆስ ነጋዴዎቹ የአሕዛብን አምልኮ በማደናቀፋቸው ኢየሱስ በመቆጣቱ ላይ ሲያተኩር፥ ማቴዎስ የአምልኮው አካል በነበረው ሙስናና ስግብግብነት ላይ አጽንኦት ሰጥቷል፡፡

በቤተ መቅደሱ ውስጥ ቢቆጣም፥ ኢየሱስ ሕዝቡን በመፈወስ ርኅራኄውን አሳይቷል። ልጆች ቀደም ሲል ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም በአህያ ላይ ተቀምጦ ሲገባ ከተደረለት አቀባበል የሰሟቸውን ቃላት በመደጋገም፣ “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ” ይሉ ጀመር፡፡ ኢየሱስ ይህ የትንቢት ፍጻሜ መሆኑ ገብቶታል። ምንም እኳ የሃይማኖት መሪዎች ባያመሰኙትም፣ ልጆች ሳያውቁ ለይተው ሊያመሰኙት ቻሉ፡፡

  1. ኢየሱስ የበለስ ዛፍን ረገመ (ማቴ. 21:18-22)።

አንድ ቀን ኢየሱስ፣ የፍሪ ምልክት በምታሳይ ዛፍ አጠገብ አለ፡፡ ነገር ግን ፍሪ ስላልነበራት ረግሞ እንድትደርቅ አደረጋት፡፡ ኢየሱስ ለምን ይህን አደረገ? ኢየሱስ በለሲቱ የእስራኤል ሕዝብ ተምሳሌት እንደሆነች ገልጾአል፡፡ እግዚአብሔር እስራኤል ለስሙ ክብርን እንድታመጣ በማሰብ ነበር የመረጣትና የፈጠራት። እንደ በለሲቱ ሁሉ፥ እስራኤልም ከርቀት ስትታይ ፍሪያማ ትመስል ነበር። በቅርብ ሲታዩ ግን አይሁዶች ፍሬ (ጽድቅ፥ ፍቅር፥ ፍትሕ) እንደሌላቸው ይታወቅ ነበር። በለሲቱ እንደ ተረገመች ሁሉ፥ አይሁዶችም ለእግዚአብሔር ፍርድ ራሳቸውን አመቻችተው ነበር። ከዚያን ጊዜ በኋላ ኢየሩሳሌም ለአርባ ዓመታት ቆይታ በሮማውያን እጅ ትደምስሳለች። ለቀጣይ 1900 ዓመታት አይሁዶች አገር አልነበራቸውም።

  1. የሃይማኖት መሪዎች የኢየሱስን ሥልጣን ተጠራጠሩ (ማቴ. 21፡23-27)

ፈሪሳውያንና የሃይማኖት መሪዎች በኢየሱስ ላይ የሚሰነዝሩት የቃላት ጦርነት ቀጥሏል። መሪዎቹ ኢየሱስን በሕዝብ ፊት ለማሳጣት የሚችሉትን ጥረት ሁሉ ያደርጉ ነበር፡፡ ኢየሱስን ለማሳጣት የታሰበው የመጀመሪያው ጥያቄ የተነሣው ከሰዱቃውያን ነበር፡፡ ዋንኞቹ ካህናትና ሽማግሌዎች ለአብዛኞቹ የአገሪቱ ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ኃላፊነቶች ነበረባቸው። ዋንኛው አጀንዳቸው ሥልጣን ነበር። የእነርሱ ሥልጣን የመነጨው በአይሁዶች ላይ እንዲገዙ ከሾሟቸው ሮማውያን ነበር፡፡ ኢየሱስን ሰዎችን ከቤተ መቅደሱ ለማስወጣትና ለመፈወስ የሚያስችል ሥልጣን ከየት አገኘ? እነዚህ ነገሮች ስለ ኢየሱስ ምን እንደሚያሳዩ የመገንዘብ ፍላጎት አልነበራቸውም። የሚያሳስባቸው ጉዳይ ቢኖር፥ የእርሱ ሥልጣን የእነርሱን ሥልጣን እያደበዘዘ መሄዱ ወይም ሰዎች በሮም ላይ ቢያምፁ የሚደርስባቸው ችግር ብቻ ነበር። የክርስቶስ ሥልጣን ከሰማይ መምጣቱን ለማረጋገጥ የፈጸማቸው ተአምራትና ያስተማራቸው እውነቶች ይበቁ ነበር፡፡ እነርሱ ግን የዚህ ዓይነቱን ሥልጣን ለመቀበል አልፈለጉም።

ኢየሱስ ግን የጥያቄያቸውን አፈሙዝ ወደ ራሳቸው አዞረ። በዚህ ጊዜ መጥምቁ ዮሐንስ እንደ ነቢይና ለእምነቱ እንደ ተሠዋ ጻድቅ ይታሰብ ነበር። ነገር ገን እነዚህ የሃይማኖት መሪዎች ዮሐንስ በሚያገለግልበት ጊዜ ሊቀበሉት አልፈለጉም ነበር። የሃይማኖት መሪዎቹ የዮሐንስ ሥልጣን ከሰማይ ወይ ከምድር መሆኑን ለመናገር አልፈለጉም ነበር። ሕዝቡ ዮሐንስ የእግዚአብሔር ነቢይ እንደሆነ ያምኑ ስለነበር፥ ችግር እንዳይፈጠርባቸው በመስጋት አገልግሎቱ ሰብአዊ ሥልጣን ብቻ ነበር ለማለት አልደፈሩም። ከእግዚአብሔር ነበር ካሉ ደግሞ ለምን አልሰማችሁትም? የሚል ጥያቄ ስለሚከተል፥ እንደዚያ ለማለት አልፈለጉም። ኢየሱስም ጥያቄያቸውን ለመመለስ ባለመፈለጉ ትተውት ሄዱ።

(ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ.አይ.ኤም ከታተመውና የአዲስ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ ስለዚህ አስደናቂ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡)

Leave a Reply

%d