የሐዋርያት ሥራ አወቃቀር እና አስተዋጽኦ

የሐዋርያት ሥራ አወቃቀር እና አስተዋጽኦ

፩. የሐዋርያት ሥራ አወቃቀር ከመልክዐ ምድር አቀማመጥ አንጻር

የውይትት ጥያቄ:- የሐዋርያት ሥራ 1፡8 እንብብና፥ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱ ወንጌሉን ወደ አራት የተለያዩ መልክዐ ምድራዊ ስፍራዎች እንዲወስዱ ያዘዛቸውን ዘርዝር።

ክርስቶስ ወደ ሰማይ ከመመለሱ በፊት፥ ስለ እርሱ ሲመሰክሩ ወንጌሉን ወደ ኢየሩሳሌም፥ ይሁዳ፥ ለማርያና ወደ ሌሎች የዓለም ክፍሎች እንዲያደርሱ ገልጾላቸዋል፡፡ ሉቃስ እነዚህን ክፍፍሎች ከመጽሐፉ ጋር አድርጎ ይጠቀማል። የሐዋርያት ሥራን አስተዋጽኦ ለማዘጋጀት አንዱ መንገድ እነዚህን መልክዐ ምድራዊ ክፍፍሎች መከተል ነው።

ሀ. ወንጌሉ ኢየሩሳሌም ደረሰ (የሐዋ. 1፡1-8፡3)

ለ. ወንጌሉ ሰማርያና ይሁዳ ደረሰ (የሐዋ. 8፡4-11፡8)

ሐ. ወንጌሉ ወደ ምድር ዳርቻ ደረሰ (ሐዋ. 11፡9-28-31፡፡)። (ሮም የዓለም ማዕከልና የሮም ግዛተ ዐጼ መዲና ስለነበረች፥ ሉቃስ ወንጌሉ እንዴት ወደ ሮም እንደ ተሰራጨ በአጽንኦት ገልጾአል። ሉቃስ ወንጌሉ በምሥራቅ ወደ ሕንድ፥ በደቡብ ወደ አፍሪካ ወይም በሰሜን ወደ ሩሲያ መስፋፋቱን አልጠቀሰም።)

፪. የሐዋርያት ሥራ አወቃቀር ከአገልጋዮቹ አንጻር።

ሌላው ሉቃስ ታሪኩን ያዋቀረበት መንገድ እግዚአብሔር ዋነኛ መሣሪያ አድርጎ የተጠቀመባቸውን አገልጋዮች በመከተል ነው።

ሀ. ጴጥሮስ፥ የአይሁድ ሐዋርያ (የሐዋ. 1-5)

ለ እስጢፋኖስ፥ የመጀመሪያው ሰማዕት (የሐዋ. 6-7)

ሐ. ሌሎች ቁልፍ የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች በኢየሩሳሌምና አንጾኪያ (የሐዋ. 6-12)

መ. ጳውሎስ፥ የአሕዛብ ሐዋርያ (የሐዋ. 13-28)

፫. የሐዋርያት ሥራ አስተዋጽኦ

  1. በኢየሩሳሌም የደቀ መዛሙርት ምስክርነት (የሐዋ. 1-7)

ሀ. መግቢያ፥ ክርስቶስ ተከታዮቹ ምስክሮቹ እንዲሆኑ ካዘዘ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ (የሐዋ. 1፡1-11)

ለ. ማትያስ 12ኛ ደቀ መዝሙር ሆኖ የአስቆሮቱ ይሁዳን ተካ (የሐዋ. 1፡12-26)

ሐ. የቤተ ክርስቲያን ልደት፡- በበዓለ ኀምሳ ቀን የመንፈስ ቅዱስ መውረድ (የሐዋ. 2)

መ. በሐዋርያትና በአይሁድ ሃይማኖት መሪዎች መካከል የተካሄደው የመጀመሪያው ፍጥጫ (የሐዋ. 3፡1-4፡35)

ሠ. ሐናንያና ሰጲራ:- እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን ስለ ንጽሕና አስተማረ (የሐዋ. 4፡36-5፡16)።

ረ. በሐዋርያትና በአይሁድ ሃይማኖት መሪዎች መካከል የተደረገ ሁለተኛው ፍጥጫ (የሐዋ. 5፡17-42)

ሰ. የሰባቱ ዲያቆናት መመረጥ (የሐዋ. 6፡1-7)

ሸ. እስጢፋኖስ የመጀመሪያው የቤተ ክርስቲያን ሰማዕት (የሐዋ. 6፡8-7፡60)

  1. የክርስቶስ ተከታዮች ምስክርነት በይሁዳና ሰማርያ (የሐዋ. 8-12)።

ሀ. ፊልጶስ በሰማርያና ለኢትዮጵያዊው ጃንደረባ የሰጠው አገልግሎት (የሐዋ. 8)

ለ. የአሕዛብ ሐዋርያ የሆነው የጳውሎስ መለወጥ (የሐዋ. 9፡1-31)

ሐ. የጴጥሮስ አገልግሎት በይሁዳ (የሐዋ. 9፡32-11፡18)

መ. በአንጾኪያ የአሕዛብ ቤተ ክርስቲያን መጀመር (የሐዋ. 11፡19-30)

ሠ. የጴጥሮስ ከእስራትና ሞት ነፃ መውጣት (የሐዋ. 11፡19-30)

  1. ምስክርነቱ እስከ ዓለም ዳርቻ መድረሱ (የሐዋ. 13-28)

ሀ. የጳውሎስ የመጀመሪያው ሚሲዮናዊ ጉዞ (የሐዋ. 13፡1-14፡28)

ለ. የኢየሩሳሌሙ ጉባኤ (የሐዋ. 5፡1-35)

ሐ የጳውሎስ ሁለተኛው የወንጌል ተልዕኮ ጉዞ (የሐዋ. 5፡36-18፡22)

መ. የጳውሎስ ሦስተኛው የወንጌል ተልዕኮ ጉዞ (የሐዋ. 18፡23-21፡15)

ሠ. የጳውሎስ በኢየሩሳሌም መያዝና በቂሣርያ መታሰር (የሐዋ.21፡15-26፡32)

ረ. የጳውሎስ ጉዞ ወደ ሮም (የሐዋ. 27፡1-28፡10)

ሰ. የጳውሎስ አገልግሎት በሮም (የሐዋ. 28፡11-31)

(ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ.አይ.ኤም ከታተመውና የአዲስ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ እግዚአብሔር አገልግሎታቸውን ይባርክ፡፡)

 

Leave a Reply

Discover more from

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading