ለክርስቲያኖች የተዘጋጀ ሽልማት የማግኘት ወይም ሽልማት የማጣት ክብረ በዓል

(ይህ ሥነ ሥርዓት ፣ የክርስቶስ የፍርድ ወንበር ወይም የቤማ//Bema መቀመጫ በመባል በስፋት ይታወቃል)

ለክርስቲያኖች ብቻ የተዘጋጀው ይህ የፍርድ ሥነ ሥርዓት ፈፅሞ ከድነት ጉዳይ ጋር የተገናኘ አይደለምከቅጣት ጋርም አይገናኝም፡፡ ፍርድም ሆነ ቅጣት በመስቀሉ አማካኝነት ምልሽ አግኝተዋል፡፡ ይህ ሽልማት እኔ ለእግዚአብሔር ካደረኩት ተግባር ጋርም አይገናኝም፡፡ እግዚአብሔር እኔ በራሴ ማድረግ የምችለውን ነገር አይፈልገውም፡፡ ይህ ሽልማት የሚያያዘው በምድር የሕይወት ዘመኔ፣ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ባለኝ ሕብረት አማካኝነት በእምነት እርሱ በእኔ ሕይወት ውስጥ ፍሬ እንዲያፈራ ከፈቀድኩለት ጉዳይ ጋር ብቻ ነው፡፡ ይህ ሰማያዊ ሽልማት ከምድራዊ ሽልማት ጋር ሊነጻጸር አይችልም፡፡ ሽልማቱ በሰማይ ባለኝ የሕይወት ሁኔታ/quality ላይ በሆነ መልክ ተፅዕኖ የሚያሳድር መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ሽልማትን ከቅጣት ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር አለመኖሩ ክርስቲያኖች ጉዳዩን በቸልታ እንዲያዩት ሊያደርጋቸው አይገባም፡፡ እግዚአብሔር ይህንን ጉዳይ ታላቅ ነው ካለ፣ በእርግጥ ታላቅ ነውና!

1. እያንዳንዱ ክርስቲያን በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት ይቀርባል፡፡

ሮሜ. 14፡10-12 አንተም በወንድምህ ላይ ስለ ምን ትፈርዳለህ? ወይስ አንተ ደግሞ ወንድምህን ስለ ምን ትንቃለህ? ሁላችን በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለንና፡፡ እኔ ሕያው ነኝ፣ ይላል ጌታ፣ ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል መላስም ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናል ተብሎ ተጽፎአልና፡፡ እንግዲያስ እያንዳንዳችን ስለ ራሳችን ለእግዚአብሔር መልስ እንሰጣለን፡፡

2ቆሮ. 5፡9-10 ስለዚህ ደግሞ ብናድር ወይም ተለይተን ብንሆን እርሱን ደስ የምናሰኝ ልንሆን እንቀናለን፡፡ መልካም ቢሆን ወይም ክፉ እንዳደረገ፣ እያንዳንዱ በሥጋው የተሠራውን በብድራት ይቀበል ዘንድ ሁላችን በክርስቶስ በፍርድ ወንበር ፊት ልንገለጥ ይገባናልና፡፡

2ጢሞ. 4፡7-8 መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፣ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፣ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፣ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፣ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም፡፡

ራዕ. 22፡12 እነሆ፣ በቶሎ እመጣለሁ፣ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ፡፡

2. የክርስቶስ የፍርድ ወንበር ባሕሪ ምን ይመስላል?

1ቆሮ. 3፡8-15 የሚተክልና የሚያጠጣ አንድ ናቸው፣ ነገር ግን እያንዳንዱ እንደ ራሱ ድካም መጠን የራሱን ደመወዝ ይቀበላል፡፡ የእግዚአብሔር እርሻ ናችሁ፤ የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ፤ ከእርሱ ጋር አብረን የምንሠራ ነንና፡፡ የእግዚአብሔር ጸጋ እንደ ተሰጠኝ መጠን እንደ ብልሃተኛ የአናጺ አለቃ መሠረትን መሠረትሁ፣ ሌላውም በላዩ ያንጻል፡፡ እያንዳንዱ ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንዲያንጽ ይጠንቀቅ፡፡ ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፣ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ማንም ግን በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ ቢሆን በብርም በከበረ ድንጋይም በእንጨትም በሣርም ወይም በአገዳ ቢያንጽ፣ የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል፤ በእሳት ስለሚገለጥ ያ ቀን ያሳያልና፣ የእያንዳንዱም ሥራ እንዴት መሆኑን እሳቱ ይፈትነዋል፡፡ ማንም በእርሱ ላይ ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ደመወዙን ይቀበላል፤ የማንም ሥራ የተቃጠለበት ቢሆን ይጎዳበታል፣ እርሱ ራሱ ግን ይድናል ነገር ግን በእሳት እንደሚድን ይሆናል፡፡

1ቆሮ. 4፡5 ስለዚህም በጨለማ የተሰወረውን ደግሞ ወደ ብርሃን የሚያወጣ የልብንም ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ በዚያን ጊዜም ለእያንዳንዱ ምስጋናው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል፡፡

3. የክርስቶስ የፍርድ ወንበር መቼ ተግባራዊ ይሆናል?

ማቴ. 16፡27 የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ሥራው ያስረክበዋል፡፡

ሉቃስ 14፡13-14 ነገር ግን ግብዣ ባደረግህ ጊዜ ድሆችንና ጕንድሾችን አንካሶችንም ዕውሮችንም ጥራ፤ የሚመልሱት ብድራት የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ፤ በጻድቃን ትንሣኤ ይመለስልሃልና፡፡

1ጴጥ. 5፡1-4 እንግዲህ እኔ፥ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤ በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤ ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ፤ የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ፡፡

ራዕ. 11፡18 አሕዛብም ተቈጡ፣ ቍጣህም መጣ፣ በሙታንም ትፈርድ ዘንድ ዘመን መጣ፣ ለባሪያዎችህም ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚፈሩት ለታናናሾችና ለታላላቆችም ዋጋቸውን ትሰጥ ዘንድ፣ ምድርንም የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ፡፡

4. ለአማኝ የተዘጋጀ ቅጣት የለም፡፡

ዮሐ. 5፡24 እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፣ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም፡፡

ሮሜ. 4፡8 ጌታ ኃጢአቱን የማይቆጥርበት ሰው ብፁዕ ነው፡፡

ሮሜ. 8፡1 እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም፡፡

ዕብ. 10፡14 አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋልና፡፡

ዕብ. 10፡17-18 … ኃጢአታቸውንና ዓመጻቸውንም ደግሜ አላስብም ይላል፡፡ የእነዚህም ስርየት ባለበት ዘንድ፣ ከዚህ ወዲህ ስለ ኃጢአት ማቅረብ የለም፡፡

ራዕ. 21፡4 እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፣ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንምኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፣ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ፡፡

5. ነገር ግን እያንዳንዳችን በዚህ ወቅት ሽልማት ‹‹የማጣት›› አደጋ እንዳለብን መዘንጋት የለብንም፡፡ (ሽልማት ማጣት ቅጣት አይደለም፡፡

ዮሐ. 15፡16 እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ አብም በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንዲሰጣችሁ፣ ልትሄዱና ፍሬ ልታፈሩ ፍሬአችሁም ሊኖር ሾምኋችሁ፡፡

1ቆሮ. 3፡14-15 ማንም በእርሱ ላይ ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ደመወዙን ይቀበላል፤ የማንም ሥራ የተቃጠለበት ቢሆን ይጎዳበታል፣ እርሱ ራሱ ግን ይድናል ነገር ግን በእሳት እንደሚድን ይሆናል፡፡

1ቆሮ. 9፡24-27 በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት፣ ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ፡፡ የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤ እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው፣ እኛ ግን የማይጠፋውን፡፡ ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም፣ ነፋስን እንደሚጎስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም፤ ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ፡፡

ገላ. 6፡9 (አ.መ.ት.) በጎ ነገር ከማድረግ አንታክት፤ ተስፋ ካልቆረጥን ጊዜው ሲደርስ መከሩን እናጭዳለን፡፡

2ጢሞ. 2፡5 ደግሞም በጨዋታ የሚታገል ማንም ቢሆን፣ እንደሚገባ አድርጎ ባይታገል፣ የድሉን አክሊል አያገኝም፡፡

2ዮሐ. 1፡8 ሙሉ ደመወዝን እንድትቀበሉ እንጂ የሠራችሁትን እንዳታጠፉ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፡፡

ራዕ. 3፡11-12 እነሆ፣ ቶሎ ብዬ እመጣለሁ፤ ማንም አክሊልህን እንዳይወስድብህ ያለህን አጽንተህ ያዝ፡፡ …

6. አማኞች የሚሸለሙት ስለ የትኞቹ ነገሮች ነው? መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ እንዲሰራ በፈቀድንለት መጠን ከዚህ በታች የተገለፁትን እና ሌሎች የሚያሸለሙ ፍሬዎችን በእኛ ውስጥ ያፈራል፡፡

1ሳሙ. 26፡23 ዛሬም እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ ሰጥቶህ ሳለ እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጄን እዘረጋ ዘንድ አልወደድሁምና ለሁሉ እያንዳንዱ እግዚአብሔር እንደ ጽድቁና እንደ እምነቱ ፍዳውን ይክፈለው፡፡

ምሳሌ 19፡17 ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፣ በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል፡፡

ማቴ. 5፡11-12 ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ፡፡ ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፣ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና፡፡

ማቴ. 5፡44-46 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፣ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፣ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፣ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፣ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና፡፡ የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? 

ሉቃስ 6፡35 ነገር ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካም አድርጉ፤ ምንም ተስፋ ሳታደርጉም አበድሩ፣ ዋጋችሁም ታላቅ ይሆናል፣ የልዑልም ልጆች ትሆናላችሁ፣ እርሱ ለማያመሰግኑ ለክፉዎችም ቸር ነውና፡፡

ማቴ. 19፡27-30 በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መልሶ፣ እነሆ፣ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ፤ እንኪያስ ምን እናገኝ ይሆን? አለው፡፡ ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፣ … ስለ ስሜም ቤቶችን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል፡፡ ነገር ግን ብዙዎቹ ፊተኞች ኋለኞች፣ ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ፡፡

ሮሜ. 8፡17-18 ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፣ አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን፡፡ ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ፡፡

ኤፌ. 6፡5-8 ባሪያዎች (ሠራተኞች) ሆይ፣ ለክርስቶስ እንደምትታዘዙ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ በልባችሁ ቅንነት በሥጋ ጌቶቻችሁ ለሆኑ ታዘዙ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንደሚያደርጉ እንደ ክርስቶስ ባሪያዎች እንጂ ለሰው ደስ እንደምታሰኙ ለታይታ የምትገዙ አትሁኑ፡፡ ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምትገዙ በትጋትና በበጎ ፈቃድ ተገዙ፤ ባሪያ ቢሆን ወይም ጨዋ ሰው፣ እያንዳንዱ የሚያደርገውን መልካም ነገር ሁሉ ከጌታ በብድራት እንዲቀበለው ታውቃላችሁና፡፡

ቆላ. 3፡22-24 ባሪያዎች (ሠራተኞች) ሆይ፣ በቅን ልብ ጌታን እየፈራችሁ እንጂ፣ ለሰው ደስ እንደምታሰኙ ለታይታ የምትገዙ ሳትሆኑ፣ በሥጋ ጌቶቻችሁ ለሆኑ በሁሉ ታዘዙ፡፡ ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ፣ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉት፣ ከጌታ የርስትን ብድራት እንድትቀበሉ ታውቃላችሁና፡፡ የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስ ነውና፡፡

ፊሊ. 4፡1 ስለዚህ፣ የምወዳችሁና የምናፍቃችሁ፣ ደስታዬና አክሊሌ የምትሆኑ ወንድሞቼ ሆይ፣ እንዲሁ በጌታ ቁሙ፣ ወዳጆች ሆይ፡፡

1ተሰ. 2፡19-20 ተስፋችን ወይስ ደስታችን ወይስ የትምክህታችን አክሊል ማን ነው? በጌታችን በኢየሱስ ፊት በመምጣቱ እናንተ አይደላችሁምን? እናንተ ክብራችን ደስታችንም ናችሁና፡፡

ያዕ. 1፡12 በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና፡፡

ራዕ. 2፡10 ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ፡፡ እነሆ፣ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው፣ አሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ፡፡ እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ፡፡

‹‹ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ›› (ማቴዎስ 6፡20) 

ይህ ትዕዛዝ እንጂ አስተያየት አይደለም፡፡

7. ምድራዊ ባህሪ ያለውን ሽልማት ሳይሆን ዘላለማዊውን ሽልማት ልንሻ ያስፈልጋል፡፡

ማቴ. 6፡1-6 ለሰዎች ትታዩ ዘንድ ምጽዋታችሁን በፊታቸው እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ ያለዚያ በሰማያት ባለው አባታችሁ ዘንድ ዋጋ የላችሁም፡፡ እንግዲህ ምጽዋት ስታደርግ፣ ግብዞች በሰው ዘንድ ሊከበሩ በምኩራብ በመንገድም እንደሚያደርጉ በፊትህ መለከት አታስነፋ፤ እውነት እላችኋለሁ፣ ዋጋቸውን ተቀብለዋል፡፡ አንተ ግን ምጽዋት ስታደርግ ምጽዋትህ በስውር እንዲሆን ቀኝህ የምትሠራውን ግራህ አትወቅ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል፡፡ ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፣ ዋጋቸውን ተቀብለዋል፡፡ አንተ ግን ስትጸልይ፣ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል፡፡

ማቴ. 6፡16-21 … ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤ ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና፡፡

ሉቃስ 14፡12-14 … ምሳ ወይም እራት ባደረግህ ጊዜ፣ እነርሱ ደግሞ በተራቸው ምናልባት እንዳይጠሩህ ብድራትም እንዳይመልሱልህ፣ ወዳጆችህንና ወንድሞችህን ዘመዶችህንም ባለ ጠጎች ጎረቤቶችህንም አትጥራ፡፡ ነገር ግን ግብዣ ባደረግህ ጊዜ ድሆችንና ጕንድሾችን አንካሶችንም ዕውሮችንም ጥራ፤ የሚመልሱት ብድራት የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ፤ በጻድቃን ትንሣኤ ይመለስልሃልና፡፡

ዮሐ. 5፡44 እናንተ እርስ በርሳችሁ ክብር የምትቀባበሉ ከአንዱም ከእግዚአብሔር ያለውን ክብር የማትፈልጉ፣ እንዴት ልታምኑ ትችላላችሁ?

ዮሐ. 12፡42-43 (አ.መ.ት.) ይህም ቢሆን፣ ከአለቆች መካከል እንኳ ሳይቀር ብዙዎች በእርሱ አመኑ፤ ይሁን እንጂ ከምኩራብ እንዳያስወጧቸው ስለ ፈሩ ማመናቸውን አይገልጡም ነበር፡፡ ይህም የሆነው በእግዚአብሔር ከመመስገን ይልቅ በሰው መመስገን ስለ ወደዱ ነው፡፡

2ቆሮ. 4፡17-18 የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፣ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፣ የማይታየው ግን የዘላለም ነው፡፡

ፊሊ. 3፡7-16 ነገር ግን ለእኔ ረብ የነበረውን ሁሉ ስለ ክርስቶስ እንደ ጉዳት ቈጥሬዋለሁ፡፡ አዎን፣ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቈጥራለሁ፤ … ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍ ከፍ ያለውን የእግዚአብሔርን መጥራት ዋጋ እንዳገኝ ምልክትን እፈጥናለሁ፡፡ እንግዲህ ፍጹማን የሆንን ሁላችን ይህን እናስብ፤ …

ቆላ. 3፡1-3 እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፣ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ፡፡ በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም፡፡ …

1ጢሞ. 4፡8 ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው፣ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል፡፡

1ጢሞ. 6፡17-19 በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ፣ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ በሚያልፍ ባለ ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው፡፡ እውነተኛውን ሕይወት ይይዙ ዘንድ፣ ለሚመጣው ዘመን ለራሳቸው መልካም መሠረት የሚሆንላቸውን መዝገብ እየሰበሰቡ፣ መልካምን እንዲያደርጉ በበጎም ሥራ

ባለ ጠጎች እንዲሆኑ፣ ሊረዱና ሊያካፍሉም የተዘጋጁ እንዲሆኑ ምከራቸው፡፡

1ጴጥ. 1፡17 ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ ብትጠሩ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ፡፡

‹‹መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናል፡፡›› (ማቴ 6፡21)

8. የእርሱ ሽልማቶች ዘላለማዊ ናቸው፡፡ (ማሳሰቢያ፡- ከዳንኤል መጽሐፍ የተጠቀሰው ሃሳብ የበብሉይ ኪዳን ቅዱሳንን ብቻ የሚመለከት ሊሆን ይችል ይሆናል፡፡)

ዳን. 7፡18 ነገር ግን የልዑሉ ቅዱሳን መንግሥቱን ይወስዳሉ፣ እስከ ዘላለም ዓለምም መንግሥቱን ይወርሳሉ፡፡

ዳን. 7፡27 መንግሥትም ግዛትም ከሰማይም ሁሉ በታች ያሉ የመንግሥታት ታላቅነት ለልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ ይሰጣል፤ መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፣ ግዛቶችም ሁሉ ይገዙለታል ይታዘዙለትማል፡፡

1ቆሮ. 9፡24-27 በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት፣ ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ፡፡ የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤ እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው፣ እኛ ግን የማይጠፋውን፡፡ …

2ቆሮ. 4፡17-18 የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፣ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፣ የማይታየው ግን የዘላለም ነው፡፡

1ጴጥ. 1፡3-7 ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፣ እድፈትም ለሌለበት፣ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል፡፡

በዚህም እጅግ ደስ ይላችኋል፣ ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፣ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል፡፡

9. ምንም እንኳ በርካታ ሐይማኖታዊ ተግባራት መንፈሳዊ ቢመስሉም ለሽልማት የሚያበቃን ግን በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት የተሰሩቱ ብቻ ይሆናሉ፡፡ (የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፣ ደስታ፣ ትዕግስት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ እምነት፣ የውሀት፣ ራስን መግዛት ነው፡፡ እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም፡፡ ገላ 5፡22-23

መክ. 3፡14 እግዚአብሔር ያደረገው ሁሉ ለዘላለም እንዲኖር አወቅሁ፤ ሊጨመርበት ወይም ከእርሱ ሊጐድል አይቻልም፤ 

ዮሐ. 15፡5 እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ፡፡ ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፣ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል፡፡

1ቆሮ. 13፡1-3 በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ፡፡ ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ፡፡ ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም፡፡

ገላ. 6፡7-10 ቨአትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም፡፡ ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና፤ በገዛ ሥጋው የሚዘራ ከሥጋ መበስበስን ያጭዳልና፣ በመንፈስ ግን የሚዘራው ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል፡፡ ባንዝልም በጊዜው እናጭዳለንና መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት፡፡ እንግዲያስ ጊዜ ካገኘን ዘንድ ለሰው ሁሉ ይልቁንም ለሃይማኖት ቤተ ሰዎች መልካም እናድርግ፡፡

1ዮሐ. 4፡16-17 እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል፡፡ እግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል፡፡ በፍርድ ቀን ድፍረት ይሆንልን ዘንድ ፍቅር በዚህ ከእኛ ጋር ተፈጽሞአል፤ እርሱ እንዳለ እኛ ደግሞ እንዲሁ በዚህ ዓለም ነንና፡፡

10. የብሉይ ኪዳን አማኞች ጭምር ይሸለማሉ፡፡

ዕብራዊያን 11

11፡1-2 እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፣ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው፡፡ ለሽማግሌዎች የተመሰከረላቸው በዚህ ነውና፡፡

11፡8-11 አብርሃም የተባለው ርስት አድርጎ ሊቀበለው ወዳለው ስፍራ ለመውጣት በእምነት ታዘዘ፣ ወዴትም እንደሚሄድ ሳያውቅ ወጣ፡፡ ለእንግዶች እንደሚሆን በተስፋ ቃል በተሰጠው አገር በድንኳን ኖሮ፣ ያን የተስፋ ቃል አብረውት ከሚወርሱ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር፣ እንደ መጻተኛ በእምነት ተቀመጠ፤ መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠብቅ ነበርና፡፡ ተስፋ የሰጠው የታመነ እንደ ሆነ ስለ ቈጠረች፥ ሣራ ራስዋ ደግሞ ዕድሜዋ እንኳ ካለፈ በኋላ ዘርን ለመፅነስ ኃይልን በእምነት አገኘች፡፡

11፡13-16 እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ፣ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል አላገኙምና፤ ዳሩ ግን ከሩቅ ሆነው አዩትና ተሳለሙት፣ በምድሪቱም እንግዶችና መጻተኞች እንዲሆኑ ታመኑ፡፡ እንዲህ የሚሉት ለእነርሱ የሚሆነውን አገር እንዲፈልጉ ያመለክታሉና፡፡ ያን የወጡበትን አገር አስበው ቢሆኑ፣ ሊመለሱ ጊዜ በሆነላቸው ነበር፤ አሁን ግን የሚበልጠውን እርሱም ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ በእነርሱ አያፍርም፣ ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና፡፡

11፡24-27 ሙሴ ካደገ በኋላ የፈርዖን የልጅ ልጅ እንዳይባል በእምነት እምቢ አለ፤ ከግብፅም ብዙ ገንዘብ ይልቅ ስለ ክርስቶስ መነቀፍ እጅግ የሚበልጥ ባለ ጠግነት እንዲሆን አስቦአልና ለጊዜው በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ፤ ብድራቱን ትኵር ብሎ ተመልክቶአልና፡፡ የንጉሡን ቍጣ ሳይፈራ የግብፅን አገር የተወ በእምነት ነበር፤ የማይታየውን እንደሚያየው አድርጎ ጸንቶአልና፡፡

11፡32-40 … ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤ ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ፤ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ፣ ተፈተኑ፣ በመጋዝ ተሰነጠቁ፣ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ፣ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፣ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ፡፡ እነዚህም ሁሉ በእምነታቸው ተመስክሮላቸው ሳሉ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አላገኙም፣ ያለ እኛ ፍጹማን እንዳይሆኑ እግዚአብሔር ስለ እኛ አንዳች የሚበልጥ ነገርን አስቀድሞ አይቶ ነበርና፡፡ 

“ደግሞም ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ምክንያቱም ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ሁሉ እግዚአብሔር መኖሩንና ከልብ ለሚሹትም ዋጋ እንደሚሰጥ ማመን አለበት፡፡” 

(አ.መ.ት.) ዕብ. 11፡6
እያንዳንዳችን ሦስት ሐብቶች አሉን፡- ጊዜ፣ ጉልበትና ያለን ሃብት/ንብረት፡፡ መንፈስ ቅዱስ እነዚህን ሃብቶቼን እንዲጠቀም በሕይወቴ ውስጥ ስፈቅድለት ከወርቅ፣ ብርና የከበረ ድንጋይ ዘላለማዊ ሽልማት ያለውን ፍሬ ለእኔ ይሰራል፡፡ እነዚህ ሃብቶቼን መንፈስ ቅዱስ እንዳይጠቀም እንቅፋት ስሆንበት ደግሞ ከእንጨት ከገለባና አገዳ ጊዚያዊ የሆነና ለሽልማት የማያበቃ ሕንፃ ራሴ ለራሴው እሰራለሁ፡፡

Leave a Reply

Discover more from

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading