መዝሙረ ዳዊት 1-75

መዝሙረ ዳዊት 1-25 

የውይይት ጥያቄ፥ መዝሙር 1-25 አንብብ። ሀ) እነዚህ መዝሙራት እያንዳንዳቸው በየትኛው የመዝሙራት ዓይነት ውስጥ እንደሚመደቡ ጥቀስ። (ምሳሌ፡- የግል ምስጋና፥ ሰቆቃ፥ ጥበብ ወዘተ)። ለ) እያንዳንዱ መዝሙር እግዚአብሔርን በተሻለ ሁኔታ ለመረዳትና በሙላት እርሱን ለማምለክ እንዴት ይረዳናል? ሐ) አንድ መዝሙር ምረጥና በልብ ውስጥ ያለውን ስሜት እንዴት እንደሚገልጥ ተናገር። መ) ሌላ መዝሙር ምረጥና ያ መዝሙር ለራስህ ሕይወት የምታደርገውን ጸሎት እንዴት እንደሚገልጥ ተናገር። ሠ) በሚከተሉት መንገዶች አገልግሎት ላይ ሊውሉ የሚችሉትን መዝሙራት ዝርዝር አዘጋጅ፡- 

1) በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እግዚአብሔርን በጋራ ለማምለክ 

2) በግል የጥሞና ጊዚህ እግዚአብሔርን ለማምለክ፥ 

3) እራስህንም ሆነ ሌላን ሰው በብቸኝነት ጊዜ ለማበረታታት፡ 

4) በስደት ላይ የሚገኝን ሰው ለማበረታታት፥ 

5) በጣም የታመመ ወይም ለመሞት የተቀረበ ሰው ለመርዳት የሚያስችል። 

ለእግዚአብሔር የሚቀርብ አምልኮን የሚገልጥ ሌላ መዝሙር ምረጥ። በዚህ መዝሙር ስለ እግዚአብሔር ባሕርያት የተዘረዘሩትን ነገሮች ሁሉ ጻፍ። ስለ እነዚህ ባሕርያት በጸሎትና በመዝሙር እግዚአብሔርን ለ15 ደቂቃዎች ያህል አምልከው። 

መዝሙራት የተጻፉት ለልባችን እንዲናገሩ መሆኑን አስታውስ። ስሜታችንን ለመቀስቀስ የተጻፉ ናቸው። መዝሙራትን በምታነብበት ጊዜ ጸሐፊው በግጥም ለመግለጥ የፈለገው ነገር በስሜትህ እንዲሠርፅ አድርግ። 

መዝሙር 26 – 50 

የውይይት ጥያቄ፥ መዝሙር 26-50 አንብብ። ሀ) እነዚህ መዝሙራት እያንዳንዳችው በየትኛው የመዝሙራት ዓይነት ውስጥ እንደሚመደቡ ጥቀስ። ለ) ጸሐፊው በመዝሙሩ ለመግለጽ የፈለገው ስሜት ምን ነበር? ሐ) እያንዳንዱ መዝሙር እግዚአብሔርን በተሻለ ሁኔታ ለመረዳትና በሙላት እርሱን ለማምለክ እንዴት ይረዳናል? መ) አንድ መዝሙር ምረጥና በልብህ ውስጥ ያለውን ስሜት እንዴት እንደሚገልጥ አስረዳ። ሠ) ሌላ መዝሙር ምረጥና ይህ መዝሙር ለራስህ ሕይወት የምታደርገውን ጸሎት እንዴት እንደሚገልጥ አስረዳ። ረ) በሚከተሉት መንገዶች ሊያገለግሉ የሚችሉ መዝሙራትን ዝርዝር አዘጋጀ፡- 

1) በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እግዚአብሔርን በኅብረት ለማምለክ፣ 

2) በግል የጥሞና ጊዜህ እግዚአብሔርን ለማምለክ፣ 

3) ራስህንም ሆነ ሌላውን ሰው በብቸኝነት ጊዜ ለማበረታታት፣ 

4) በስደት ላይ የሚገኝ ሌላ ሰው ለማበረታታት፣ 

5) በጣም የታመመ ወይም ወደ ሞት የተቃረበ ሰው ለመርዳት። 

ለእግዚአብሔር የሚቀርብ አምልኮ የሚገልጥ ሌላ መዝሙር ምረጥ። በዚህ መዝሙር ስለ እግዚአብሔር ባሕርያት የተዘረዘሩትን ነገሮች ሁሉ ጻፍ። ስለ እነዚህ ባሕርያት እግዚአብሔርን በጸሎትና በመዝሙር ለ15 ደቂቃዎች ያህል አምልከው። መዝሙራት የተጻፉት ለልባችን ለመናገር እንደሆነ አስታውስ። ስሜታችንን ለመቀስቀስ የተጻፉ ናቸው። መዝሙራትን በምታነብበት ጊዜ ጸሐፊው በግጥም ለመግለጥ የፈለገው ነገር በስሜትህ እንዲሠርጽ ፍቀድ። 

መዝሙር 51-75 

የውይይት ጥያቄ፥ መዝሙር 51-75 አንብብ። ሀ) እነዚህ መዝሙራት እያንዳንዳቸው በየትኛው የመዝሙራት ዓይነት እንደሚመደቡ ዘርዝር። ለ) ጸሐፊው በመዝሙሩ ለመግለጽ የፈለገው ስሜት ምን ነበር? ሐ) እያንዳንዱ መዝሙር እግዚአብሔርን በተሻለ ሁኔታ ለመርዳትና በሙላት ለማምለክ እንዴት ይረዳናል? መ) አንድ መዝሙር ምረጥና በልብህ ውስጥ ያለውን ስሜት እንዴት እንደሚገልጥ አስረዳ። ሠ) ሌላ መዝሙር ምረጥና ለራስህ ሕይወት የምታደርገውን ጸሎት እንዴት እንደሚገልጥ አስረዳ። ረ) በሚከተሉት መንገዶች ሊያገለግሉ የሚችሉ መዝሙራትን ዝርዝር አዘጋጅ፡- 

1) በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እግዚአብሔርን በኅብረት ለማምላክ፥ 

2) በግል የጥሞና ጊዜህ እግዚአብሔርን ለማምለክ፥ 

3) ራስህንም ሆነ ሌላውን ሰው በብቸኝነት ወቅት ለማበረታታት፥ 

4) በስደት ላይ የሚገኝን ሰው ለማበረታታት፥ 

5) በጽኑ የታመመ ወይም ሊሞት የተቃረበ ሰውን ለመርዳት። 

ለእግዚአብሔር የሚቀርብ አምልኮ የሚገልጥ ሌላ መዝሙር ምረጥ። በዚህ መዝሙር ስለ እግዚአብሔር ባሕርያት የተዘረዘሩትን ነገሮች ሁሉ ጻፍ። ስለ እነዚህ ባሕርያት እግዚአብሔርን በጸሎትና በመዝሙር ለ15 ደቂቃዎች ያህል አምልከው። መዝሙራት የተጻፉት ለልባችን ለመናገር እንደሆነ አስታውስ። ስሜታችንን ለመቀስቀስ የተጻፉ ናቸው። መዝሙራትን በምታነብበት ጊዜ ጸሐፊው በግጥም ለመግለጥ የፈለገው ነገር በስሜትህ እንዲሠርጽ ፍቀድ። 

(ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ.አይ.ኤም ከታተመውና የብሉይ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ እግዚአብሔር አገልግሎታቸውን ይባርክ፡፡)

1 thought on “መዝሙረ ዳዊት 1-75”

Leave a Reply

Discover more from

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading