እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ማን ነው?

ጥያቄ፡- ሀ) «መንፈስ ቅዱስ ማን ነው?» እንዴት ታብራራዋለህ? ተብለህ ብትጠየቅ ምን ትል ነበር? ከምን ጋር ታወዳድረዋለህ? ለ) በመጀመሪያው ቀን «የኢየሱስ ብቻ » ተከታዮች ደግሞም የኦርቶዶክስ ቀሳውስት የሰጡህን መልሶች ከልስ። እነርሱ ስለ መንፈስ ቅዱስ የገለጡበት [መንገድ አንተ ከተረዳህበት መንገድ በምን ይለያል? 

ብዙዎቻችን እግዚአብሔር አብንና እግዚአብሔር ወልድን ለመረዳት አንቸገርም። ይህ የሆነበት ምክንያት ምናልባት በምድር ላይ የምናየውም የአባትና ልጅ ዛንኙነት እግዚአብሔር አብና እግዚአብሔር ወልድን ለመረዳት ስለሚያግዘን ይሆናል። በተጨማሪ አብዛኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የሚያተኩረው በእግዚአብሔር አብና በእግዚአብሔር ወልድ ላይ ነው። መንፈስ ቅዱስ ማን እንደሆነ ለመረዳት እንሞክር ግን መንፈስ ቅዱስን በምድር የሚመስለው ስለሌለ በቀላሉ ለመገንዘብ ያስቸግረናል። ስሙ የተገኘው «ነፋስ» ከሚለው ቃል የሆነበት ምክንያት አለመታየቱንና ነገር ግን በእርግጥ መኖሩን ለማመልከት ነው። 

ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ እንደ ነፋስ የማይታይ ኃይል ያለውና ግን ሕይወት የሌለው ነውን? ወይስ በቤታችን ውስጥ በሽቦ ገመዶች ተደብቆ እንዳለና ማብሪያና ማጥፊያውን ስንነካ እንደሚሠራ ኤሌክትሪክ ነውን? እግዚአብሔር የፈጠራቸው ሆነው ታላቅ ኃይል እያላቸው ግን ሕይወት የሌላቸው ኑባሬዎች አሉ? እሳት ትላልቅ ጫካዎችን ማውደም ይችላል። ነፋስ ትላልቅ መኪናዎችንም ሆነ ቤቶችን መገልበጥ ይችላል። ነገር ግን እነዚህ ነገሮች በራሳቸው ሕይወት የላቸውም። አያስቡም፥ አያቅዱም፥ በፈቃዳቸው አያደርጉም። መንፈስ ቅዱስ ይህን የሚመስል ነውን? 

እግዚአብሔር የፈጠራቸውና ሕያው የሆኑ ነገር ግን ሰብአዊ ህልውና የሌላቸው ብዙ ነገሮች አሉ። እንደ ውሻ ያሉ እንስሳት ሕይወት አላቸው፥ ፈቃድ እላቸው የተወሰነ ደረጃ ም ቢሆን የማሰብ ኃይል አላቸው። ነገር ግን የእነርሱ ሕይወት ሰዎች ካላቸው ሕይወት የተለየ መሆኑ ግልጽ ነው። መንፈስ ቅዱስ ያላው እንደዚህ ዓይነት የእንስሳት ሕይወት ነውን? 

የሕይወት ከፍተኛ ደረጃ ው ሰብአዊ ህልውና ሲኖር ነው። ሰዎች መኖርና መተንፈስ ብቻ ሳይሆን ላማሰብ፥ ለማቀድና አንድ ነገር ለመፍጠር የሚችሉ ናቸው። እንደዚህ ዓይነቱ ሕይወት በእግዚአብሔርና በአምሳያው በተፈጠረው በሰው ሕይወት ውስጥ ብቻ ያለ ነው። መንፈስ ቅዱስ ያለው እንደዚህ ዓይነቱ ሕይወት ነውን? 

በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ዛሬም ቢሆን እንኳ መንፈስ ቅዱስ እንደ እግዚአብሔር ዓይነት እውነተኛ ሕይወት የለውም በማለት የሚያስተምሩ እሉ። ይልቁኑ ሴቶችን ለማፈራረስ ከፍተኛ ኃይል እንዳለው ነፋስ መንፈስ ቅዱስም ሕይወት የሌለው እግዚአብሔር ፈቃዱን ለመፈጸም የሚጠቀምበት ኃይል ነው ይላሉ። የራሱ ፈቃድ የለውም፥ ሕይወት ያለው አይደለም። እግዚአብሔርም እይደለም። እግዚአብሔር አብ የራሱ አካላዊ ህልውና ቢኖረውም መንፈስ ቅዱስ ግን በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር የሆነ እንደ እሳትና ነፋስ ያለ ነገር ነው። እካላዊ ህልውና ስለሌለው አያስብም፥ አያቅድም፥ አይሠራም ወይም እካላዊ ህልውና ያላቸው ሌሎች ካላቸው ባሕርይ እንድም የለውም ይላሉ። (ማስታወሻ፡ አንድ ነገር አካላዊ ህልውና አለው ስንል ለማሰብ፥ ለማቀድ፥ ለመንደፍ፥ ለመፍጠር ስሜት ሊኖረው የሚችለውን የሰውን ክፍል መናገራችን ነው።) 

አንዳንድ የሐሰት ትምህርቶችና ለዘብተኛ-ክርስቲያኖች ካላቸው አሳቦች ጥቂቶቹ ቀጥለው ተዘርዝረዋል። 

1. የይሖዋ ምስክሮች፡- ይህ የሐሰት ትምህርት መንፈስ ቅዱስ አገልጋዮቹ ፈቃዱን እንዲያደርጉ የሚያንቀሳቅሳቸው የማይታይ ገቢራዊ የሆነ የሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ኃይል ነው ብለው ያስተምራሉ። በእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱሳቸው መንፈስ ቅዱስ አምላክ እንደሆነ የሚያመለክት የቃላት አጠቃቀም እንዳያደርጉ ይጠነቀቃሉ። (ይኽውም፥ Holy የሚለውን holy, Spirit የሚለውን spirit በማለት ነው።) የመንፈስ ቅዱስን አምላክነት ይክዳሉ። 

2. የዓለም አቀፍ መንገድና ኢየሱስ ብቻ “The Way International and Jesus Only”፡- እነዚህ መናፍቃን እንደሚከተለው ያስተምራሉ። መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር አብ ጋር አንድ ነው። በሥላሴ ውስጥ ያሉ የተለያዩ አካላት አይደሉም። የእግዚአብሔር ኃይል የሆነው መንፈስ ቅዱስ ለእግዚአብሔር ልጆች ሊሰጥ ይችላል። 

3. ዓለም አቀፍ የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን “The Word wide Church of God” ስታስተምር መንፈስ ቅዱስ አካላዊ ህልውና ያለው አይደለም። እኛ የኤሌክትሪክ ኃይልን ብርሃን ለማግኘትና ሌሎች እቃዎችን ለመጠቀም እንደምንገለገልበት ሁሉ እግዚአብሔር እብም መንፈስ ቅዱስን እንዲሁ ይጠቀምበታል። ለእግዚአብሔር መንፈሱ፥ አሳቡ፥ ኃይሉ፥ ባሕርዩ ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር አብና እንደ ክርስቶስ ራሱን የቻለ አካላዊ ሕልውና የለውም። 

4 አንዳንድ ለዘብተኛ ክርስቲያኖች እና ራሳቸውን “Unitarians” ብለው የሚጠሩና የሥላሴን ጽንሰ አሳብ የሚክዱ የክርስቶስን መለኮታዊነት የሚጠራጠሩ፤ የመንፈስ ቅዱስን መላኮታዊነትና አካላዊ ህልውና ይክዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ሲጠቅስ፥ እግዚአብሔር አብ በዓለም ውስጥ ስላለው ተግባር መናገሩ ነው ይላሉ። 

ብዙዎቻችን መንፈስ ቅዱስ ግዑዝ ኃይል ነው ብለን ብናምንም በተግባር ግን ዓላማችንን በማስፈጸም እንዲያገለግላን እንደፈለግን የምንናቆረቁረውና የምንቆጣጠረው ኃይል አድርገን እንቆጥረዋለን። አንዳንድ ኦርቶዶክሶችና ሙስሊሞች ከክፉ የሚጠብቀን ኃይል ነው በማለት የአስማት ክታብ በአንገታቸው እንደሚያስሩ፥ አንዳንዶቻችንም መንፈስ ቅዱስን በዚህ መልክ እናስተናግደዋለን። መንፈስ ቅዱስን መቆጣጠርና እንደፈለግነው መጠቀም የምንችል ይመስለናል። ልናውቀው የምንችለው የራሱ አካላዊ ህልውና እንዳለው ከእርሱ ጋር ግንኙነት መመሥረትና ማዳበር እንደሚገባን አድርገን እንቆጥረውም። ይህ ዝንባሌ በተለያየ መንገድ ይታያል። አንዳንድ ሰዎች መንፈስ ቅዱስን አንድ ነገር እንጠይቀውና በኢየሱስ ስም በመጸለያችን ብቻ ክፍላጐታችን ጋር እንዲስማማ የምናስገድደው ይመስለናል። መንፈስ ቅዱስን የአምልኮ መንፈስ እንዲፈጥር ለማስገደድ የጉባኤን ስሜት በሚፈልገው አቅጣጫ ለመጠቀም ሙከራ ይደረጋል። ላሰዎች ለመጻላይ ብቻ መንፈስ ቅዱስ እንዲፈውሳቸው ለማስገደድ ይሞክራሉ። 

ጥያቄ፡- ሀ) ክርስቲያኖች እግዚአብሔርን በተለይም ደግሞ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ለመቆጣጠር የሚሞክሩባቸውን ሌሎች መንገዶች ጥቀስ? ለ) ይህ ስሕተት ይመስልሃልን? ለምን? 15ኛ ጥያቄ፡– ሕይወት ባለውና ሕይወት በሌለው ነገር ግን ኃይል ባለው ነገር መካከል የሚታየው ልዩነት ምንድን ነው። 

ሥጋዊ አካል ያለን ፍጡራን በመሆናችን እውነተኛ ሕይወትና አካላዊ ህልውና ሥጋዊ አካል ሊኖረው ያስፈልጋል ብለን እናስባለን። ብዙውን ጊዜ እካላዊ ህልውናና ሕይወት ያላን ሥጋዊ አካል ስላለን ነው ብለን እናስባለን። ነገር ግን ሥጋዊ አካል ሕይወት ወይም ነፍስ የሚኖርበት ቤት ነው። አንድ ሰው በሥጋው ሲሞት ህልውናው እያከትምም። አካላዊው ሕልውና ወይም ነፍሱ ትኖራለች። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው አንድ ክርስቲያን ሊሞት አካላዊ ህልውናው ሕያው ሆኖ በመቀጠል ከጌታው ጋር ይሆናል (ፊልጵ. 1፡20-24)። ስለዚህ እራሳችንን፤ መንፈስ ቅዱስ አካላዊ ህልውና አለው ወይስ ቁስ ነው የሚለውን ጥያቄ ስንጠይቅ አካላዊ ህልውና ምን ማለት እንደሆነ ቀደም ብሎ የነበረንን አሳብ መለወጥ አለብን። መንፈስ ቅዱስ ሥጋዊ አካል ባይኖረውም እንኳ አካላዊ ህልውና ሊኖረው እንደሚችል ልብ ልንል ይገባል። 

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል? መንፈስ ቅዱስና አካላዊ ሕልውና፥ ፈቃድ፥ እእምሮና ስሜት እንደሌላቸው ነፋስና እሳት ነውን? ወይስ አካላዊ ህልውና ያለው ለማሰብ ለማቀድ የሚችልና ስሜት ያለው ወዘተ… ነውን? 

ጥያቄ፡– የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከት 1ኛ ቆሮ. 2፡10-13፤ ኤፌ. 4፡30፤ 1ኛ ቆሮ. 12፡7-11፤ ዮሐ 14፡26፤ ሮሜ 8፡14፤ የሐዋ. 8፡29፤ የሐዋ. 10፡19-21፤ የሐዋ. 5፡3፤ የሐዋ. 7፡51፤ ማቴ. 12፡31። ሀ) ስለ መንፈስ ቅዱስ ከአካላዊ ህልውናው ጋር በተዛመደ እነዚህ ጥቅሶች የሚያስረዱበትን ነጥቦች ዘርዝር። ለ) እነዚህ ጥቅሶች ስለ መንፈስ ቅዱስ ዓይነት ሕይወት ምን ያስተምሩናል? 

1. መንፈስ ቅዱስ ማንኛውም አካላዊ ህልውና ያለውን ባሕርይ በሙሉ ይዟል። 

እንደ ሰውና እንደ እግዚአብሔር አካላዊ ህልውና ያለው ሆኖ ለመገኘት መሟላት ያለባቸው ብዙ ነገሮች አሉ። አእምሮ መኖር እለበት፥ የማሰብ፥ የማቀድና የመወሰን ችሎታ ማለት ነው። ፈቃድ መኖር አለበት፥ ለመወሰንና እቅዶቹን ለመተግበር የሚያግዘው ውስጣዊ ዓላማ ማለት ነው። ስሜቶች መኖር አለባቸው፥ ከአእምሮና ከፈቃዱ ጋር በጥምረት የሚሠሩ ስሜቶች ባለቤት የመሆን ችሎታ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ የሚናገረውን ስናጠና እርሱ ሕያው ጭብጥ እንጂ ሕይወት የለሽ ኃይል ብቻ እንዳልሆነ እንገነዘባለን። ከላይ በተዘረዘሩት ጥቅሶች ስለ መንፈስ ቅዱስ የሚከተሉትን ነገሮች መመልከት እንችላለን። 

ሀ) መንፈስ ቅዱስ አእምሮ አለው፡- ነገሮችን የማወቅ፥ የእግዚአብሔር የሆኑትን ነገሮች የመፈለግና ውሳኔ የማድረግ ችሎታ አለው። የሚያውቀውን እውነት ለሰዎች ማስተማር ይችላል (1ኛ ቆሮ. 2፡10-13፤ ኤፌ. 1፡17፤ ሮሜ 8፡2)። 

ለ) መንፈስ ቅዱስ ልማቶች አሉት፡- አማኞች ኃጢአትን ሲያደርጉ ያዝናል (ኤፌ 4፡30)። በከፍተኛ ችግሮች ውስጥ ስንሆን ከእኛ ጋር ያዝናል፥ ይቃትትልናልን (ሮሜ 8፡26)። ደግሞም ይወደናል (ሮሜ 5፡30)። 

ሐ) መንፈስ ቅዱስ ፈቃድ አለው፡- አንድ ነገር ወስኖ ዕቅዶቹን መፈጸም ይችላል። ለተለዩ ሰዎች የትኞቹን ስጦታዎች መስጠት እንዳለበት ይወስናል። እንደ ምርጫውም ያከፋፍላቸዋል (1ኛ ቆሮ. 12፡7-11)፡፡ 

2. መንፈስ ቅዱስ አካላዊ ህልውና እንዳለው የሚያሳዩ ተግባራትን ይፈጽማል። 

መንፈስ ቅዱስ የማሰብ ውስጣዊ ችሎታ ያለው ብቻ ሳይሆን አንድ አካላዊ ህልውና ያለው ነገር ብቻ ሊያደርግ የሚችለውን ያደርጋል። (ለምሳሌ ያስተምራል፥ ትእዛዝ ይሰጣል፥ ወዘተ…) መንፈስ ቅዱስ ተራ ግዑዝ ኃይል ባለመሆኑና አካላዊ ህልውና ያለው አካል በመሆኑ ብቻ የሚያከናውናቸውን የሚከተሉትን ተግባራቱን ልብ በል። 

ሀ) ለአማኞች የእግዚአብሔርን እውነት የሚያስተምራቸው መንፈስ ቅዱስ ነው (ዮሐ 14፡26)። 

ለ) ስለ እግዚአብሔር እንዳንድ እውነቶችን ለዓለምና ለመንፈሳችን የሚነግርና የሚመሰክር መንፈስ ቅዱስ ነው (ዮሐ 5፡26፤ ሮሜ 8፡16)። 

ሐ) መንፈስ ቅዱስ ሰዎች በእግዚአብሔር ፈቃድ እንዴት መራመድ እንዳለባቸው ይመራቸዋል (ሮሜ 8፡14)። 

መ) መንፈስ ቅዱስ ሰዎች አንዳንድ ነገሮችን እንዲያደርጉ ያዝዛችዋል። (የሐዋ. 8፡29) 

3. ሌሎች እካላዊ ህልውና ያላቸው መንፈስ ቅዱስን አካላዊ ህልውና እንዳለው ይቀበላሉ። 

በመጨረሻም መጽሐፍ ቅዱስን ስናጠና መንፈስ ቅዱስ በቁጥጥር ሥር የሚሆን አንድ ኃይል እንዳልሆነ እናያለን። ይልቁኑ እንደ እግዚአብሔር አብ ወይም እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ አካላዊ ህልውና እንዳለው እውነተኛ ጭብጥ እንደሆነ እንመለከታለን። 

ሀ) ልንታዘዘው ወይም ላንታዘዘው እንችላለን (የሐዋ. 10፡19-2)። 

ለ) ልንዋሸው እንችላለን (የሐዋ. 5፡3)። 

ሐ) ልንቋቋመው እንችላለን (የሐዋ. 1፡5)። 

መ) ልንሰድበው እንችላለን (ማቴ. 12፡31)። 

አካላዊ ህልውና ሳይሆን አንድ ታላቅ ኃይል ያለው ነገር አድርጎን ነፍስን በምሳሌነት ብንጠቀም ካላይ የተዘረዘሩት ጥቅሶች መንፈስ ቅዱስ ሕያው ጭብጥ እንጂ አካላዊ ህልውና የለሽ ኃይል እንዳይደለ ያሳዩናል። ነፋስ ከፍተኛ የማጥፋት ኃይል አለው። ሆኖም ግን ነፋስ ምን እንደሚያደርግ አስቀድሞ አያስብም። አያቅድም። እራሱን ለመቆጣጠር አይችልም። ሰዎች አንድ ነገር እንዲያደርጉ ማዘዝ አይችልም። አንድ አካላዊ ስብዕና ላለው ነገር አንታዘዝም እንደምንል ለእርሱ አንለውም። 

በሌላ አንጻር ስንመለከት መንፈስ ቅዱስ እንደ ማንኛውም ሌላ ህልውና (ሰውም ሆነ መላኮት) በራሱም ሆነ በተግባሩ ላይ ቁጥጥር አለው። ማሰብ፥ ማቀድና ያቀዳቸውን ጉዳዮች ተግባራዊ ማድረግ ይችላል። ከሌሎች ጋር መነጋገር፥ ሌሎችን መምራትና ማዘዝ ይችላል። ሌሎች ሊዋሹት፥ ላይታዘዙት፥ ሊቋቋሙትና ሊሰድቡትም እንኳ ይችላሉ። እውቀት፥ ልማቶችና ተግባራት አሉት። መንፈስ ቅዱስ እንደ እኛ ዓይነት ሥጋዊ አካል ሳይኖረው ቀርቶ ልንረዳው አስቸጋሪ ቢሆንብንም እንኳ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚፈልገው መንገድ ማሰብ ካለብን መንፈስ ቅዱስን መረዳት ያለብን እንደ እካላዊ ህልውና እንጂ እንደ ዕቃ እይደለም። እካላዊ ህልውና እንዳለው አውቀን ዝምድና ልንመሠርት፥ ጓደኞቹ ልንሆንና እንደሚረዳን፥ እንደሚወደንና ከእኛ ጋር እንደሚሠራ ልንገነዘብ ይገባል። 

የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች መንፈስ ቅዱስን የተገነዘቡት እንደ አንድ አካላዊ ህልውና እንጂ እንደ ኃይል አለመሆኑን የሚያመለክትን አንድ ተጨማሪ የአዲስ ኪዳን ማረጋገጥ አለ። የመንፈስ ቅዱስ መጠሪያ ስም «ነፋስ» ከሚለው የግሪክ ቃል መወሰዱን ታስታውሳለህ። ከአማርኛ በተለየ መንገድ በግሪክ ቋንቋ ውስጥ ስለ አንድ ነገር ሲናገሩ የሚጠቀሙበት ሁለት የተለያዩ ተውላጠ ስሞች አሉ። አንደኛው ለግል ብቻ ያልሆነ ሕይወት ላሌላቸው ግዑዝ አካላት የሚውል ሊሆን ይህ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ለዕቃዎች የወል መጠሪያ ይውላል። ሌላው ተውላጠ ስም ግን ሕይወት ላላቸው ብቻ የሚውል ነው። ለምሳሌ አንድን ሰው አንድ ዕቃ ወይም ነገር ብለን አንጠራውም። ለአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች ስለ ቅዱስ «ነፋስ» ወይም መንፈስ ሲናገሩ በመጀመሪያ ተውላጠ ስም ላነገሮች (ለዕቃዎች) በሚውለው መጠቀም በሰዋሰው ሕግ ትክክለኛ ያደርጋቸው ነበር። ነገር ግን የሰዋሰው ሕጐችን በሙሉ በማፍረስ መንፈስ ቅዱስን «እርሱ» እያሉ በአካላዊ ህልውና መጠሪያነት ተጠቅመውበታል። ይህንን ያደረጉት መንፈስ ቅዱስ አካላዊ ህልውና እንጂ እርሱ ህልውና የሌለው ኃይል እንዳልነበረ ስላወቁ ነው፡፡

ጥያቄ፡- የኢየሱስ ብቻ እምነት፥ ተከታዮች ስለ መንፈስ ቅዱስ ስላላቸው አመላካከት የተነጋገራችሁትን እንደገና ከልሱት። ከላይ በተዘረዘሩት ጥቅሶች አማካኝነት መንፈስ ቅዱስ በሥራ ላይ ያለ የእግዚአብሔር ኃይል ብቻ ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር የራሱ አካላዊ ህልውና ያለው መሆኑን የምታረጋግጥላቸው እንዴት ነው? 

ስለ መንፈስ ቅዱስ በአእምሮአችን ያላው ሥዕለ-ሕሊና ምን እንደሆነ መመርመር እጅግ ጠቃሚ ነው። አካላዊ ህልውና ያለው ሳይሆን «የእግዚአብሔር ኃይል ብቻ እንደሆነ የማሰብ ዝንባሌ ካለን እርሱን ወደ መቆጣጠርና ለእኛ እንዲሠራላን ወደ ማድረግ እናጋድላላን። ነገር ግን እርሱ አምላክና ሕያው አካላዊ ህልውና ያለው መሆኑን ከተገነዘብን ከአንድ አካላዊ ህልውና ካለው አካል ጋር ግንኙነት እንደምናደርግ ከእርሱም ይህን ግንኙነት ለመፍጠር እንፈልጋለን። ከእርሱ ጋር ግንኙነት እናደርጋለን፤ የበለጠ እርሱን ለማወቅ እንፈልጋለን። 

የሚያሳዝነው ነገር ብዙ ክርስቲያኖች ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያላቸው ግንኙነት ከሚከተሉት ሁለት መንገዶች በእንቶ የሚገለጽ ነው። እንደኛ አንዳንዶች ምንም አስፈላጊ እንዳልሆነ ዓይነት ሙሉ በሙሉ ቸል ይሉታል። እግዚአብሔር አብን ወይም ወልድን ያመልካሉ። ስለ መንፈስ ቅዱስ ግን ፈጽሞ አያስቡም። እርሱን ለማወቅ ምንም ጥረት አያደርጉም። በሕይወታቸው መንፈስ ቅዱስ መኖር አለመኖሩን፥ በሕይወታቸው ይሥራ አይሥራ ምንም የሚያውቁት ነገር የለም። አንድ ክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስን ሥራ የማይለማመድ ከሆነ ይህ ሰው የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ እንደሆነ እንኳ በእርግጠኛነት ለመናገር አስቸጋሪ ነው። መንፈስ ቅዱስ ወደ ክርስቲያን ሕይወት ሲገባ የሚያመጣው ልዩነት በግልጽ የሚታወቅ ነው። የክርስቲያንን ሕይወት የሚለውጥበት መንገድ አለው (2ኛ ቆሮ. 5፡17 ተመልከት)። 

በሁለተኛ ደረጃ ሌሎች ደግሞ መንፈስ ቅዱስን በፈቃዳቸው ሊቆጣጠሩት እንደሚችሉ ያስባሉ። ልክ እኛ በግድግዳችን ላይ ባለው ማብሪያና ማጥፊያ ኮረንቲን እንደምንቆጣጠር ሁሉ መንፈስ ቅዱስን እንደ ግዑዝ ዕቃ፥ እንደሚቆጣጠሩት አንድ ኃይል አድርገው ይቆጥሩታል። ጠንቋዩ ስምዖን እጆችን በመጣን መንፈስ ቅዱስን ሊቆጣጠረው እንደሞከረው ዓይነት አንዳንድ ነገሮችን በማድረግ መንፈስ ቅዱስን የሚቆጣጠሩት ይመስላቸዋል ( የሐዋ. 8፡18-23)። 

ጥያቄ፡- ሀ) ክርስቲያኖች ከላይ ከጠቀስናቸው ሁለት ዝንባሌዎች አንዱን ሊይዙ እንዴት ተመለከትክ? ለ) መንፈስ ቅዱስ ከሰዎች ጋር የሚመሳሰለው እንዴት ነው? ሐ) የሚለየውስ? መ) አንተ ከመንፈስ ቅዱስ |ጋር ስላለህ ግንኙነት አስብ። አካል እንዳለው ከማሰብ ይልቅ እንደ ግዑዝ ዕቃ ነው የምታየው? ምሳሌዎችን ስጥ። ሠ) መንፈስ ቅዱስ አካል ያለው የመሆኑን እውነታ ለማንፀባረቅ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለህን ግንኙነት እንዴት ትለውጠዋለህ? 

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.