ከካሪዝማቲክ ትምህርት ለቤተ ክርስቲያን የተረፉ መልካም ውጤቶች

የካሪዝማቲክ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ላሉ የእምነት ክፍሎች በሙሉ የተጫወተው ሚና በመልካምነቱ እጅግ የሚበዛ እንደሆነ ጥርጥር ሊኖር አይችልም። ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን ካሪዝማቲክ ከሆኑት ክርስቲያኖች ላገኘችው ጥቅም የምስጋና ባለ ዕዳ ናት። በዓለም ዙሪያ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ያደረጉት በጎ ተጽእኖ ቀጥሎ ተዘርዝሮአል። 

1. ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ንቁ የሆነ ሕያው ግንኙነት እንድናደርግ አትኩሮታችንን አድሰውልናል። ለቤተ ክርስቲያንና ለግላሰብ ክርስቲያኖች አደገኛ ከሆኑ አዝማሚያዎች ዋናው በመንፈሳዊ ሕይወት እየቀዘቀዙ መሄድ ነው። በቅዝቃዜያችን እያደግን በሄድን ቁጥር የክርስትና ማዕከል የምናውቀውና የምናምነው ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት መሆኑን እንዘነጋለን። ትውፊታችንን፥ የቤተ ክርስቲያን ልምምዶቻችን ወይም ኢኮኖሚያዊ እድገታችንን በመሳሰሉት ላይ እናተኩራለን። ከእነዚህ ነገሮች የትኞቹም በራሳቸው መጥፎ አይደሉም ነገር ግን የእምነታችን ማዕከል አይደሉም፤ የካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች ኢየሱሳን በሙሉ ልባችን እንዴት መውደድ እንዳለብንና ከኢየሱስ ጋር ባለን ኅብረት በየቀኑ እንዴት መመላለስ እንዳለብንና ጥሩ ምሳሌ ሆነውናል። በልባችንና በቤተ ክርስቲያናችን የኢየሱስ ህልውና እንዲሰማንና እንደ እንግዶች ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ወዳጆች መመላለስ እንዳለብን ያስተምሩናል። 

2. የሕይወት ንጽሕና በመፈለግ ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች መልካም ምሳሌዎቻችን ናቸው። ብዙ ጊዜ ከክርስቲያኖች ብዙዎቻችን እግዚአብሔርን የኃጢአት ባሕርያችንን አሸንፈን እንድንኖር እንደሚያስችለን አንተማመንበትም። መንፈስ ቅዱስ እነዚህን የኃጢአት ልማዶቻችንን እሸንፈን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ኑሮ እንድንኖር ኃይል እንደሚሰጠን ከመተማመን ይልቅ ለባሕሪዎቻችን ምክንያት ሰጪዎች እንሆናለን። ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች ግን መንፈስ ቅዱስ በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ህልውናውን የሚያሳውቀው ኃይልን በመስጠት ነው ብለው ያስተምራሉ። መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ስለሚኖር የእግዚአብሔር ኃይል በውስጣችን አለ ማለት ነው። ይህ ኃይል መኖሩ የሚረጋገጥበት እንድ መንገድ የኃጢአትን ኃይል በማሸነፋችን ነው። ይህ ኃይል ኃጢአትን ለማሸነፍ ብቻ ሳይሆን ለመመስከርና ለማምለክም ያግዘናል። 

3. ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች በአምልኮአቸው ስሜታቸውን ለመግለጥ አይፈሩም። እግዚአብሔር የአእምሮ ብቻ ሳይሆን የስሜት ሰዎች አድርጎ እንደፈጠረን ያምናሉ። በአምልኮአቸው ወቅት ሳይነኩ ማለፍን እይፈልጉም። ለእግዚአብሔር ያላቸውን አምልኮ ለማነሣሣት ስሜቶችን እንደ መሣሪያ ይጠቀማል። ደስታቸውን በነፃነት ይገልጣሉ። ይህም የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን በምንም ዓይነት መንገድ እስከማንገልጽ ድረስ፥ ለሜቶቻችንን ይህ ነው በማይባል ቁጥጥር ሥር አምቀን ከምንይዝ ከብዙዎቻችን ሁኔታ የሚቃረን ነው። 

4 ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች ትኩረታችንን በጸሎት አስፈላጊነት ላይ እንድናደርግ አድርገዋል። ስለ ጸሎት ዓይነትና መልክ እጅግ አይገዳቸውም፤ ይልቁኑ ጸሎት የክርስትና እምብርት መሆኑን ይገነዘባሉ። ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት የምናደርግበት መንገድ ነው። የኃይል ምንጭ ነው። ለብዙዎች በልሳናት መናገር ይህን ያህል የመንፈስ ቅዱስ ህልውና ማረጋገጥ አይደለም። ይልቁኑ የአምልኮና የጸሎት ሕይወታቸውን ለማጠናከር መሣሪያ አድርገው ይጠቀሙበታል። ምስጋናቸውንና ለእግዚአብሔር ያላቸውን አምልኮ ለመግለጽ ከሁሉ የተሻለ መንገድ እንደሆነ ያምናሉ። 

5. ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች አምልኮን አድሰውታል። አብያተ ክርስቲያናት ትርጉማቸውን ወዲያው የሚያጡ የአምልኮ ዘይቤዎችን በመፍጠር ሥርዓት አድርገው ይከተሉአቸዋል። በዚህም አምልኮ ከመድረቁ የተነሣ ሕይወትና ትርጉም ያጣል። እነርሱ ግን አዳዲስ፥ ሕይወት የሞላባቸውን ዝማሬዎች በማከል፥ በተላይ ስሜቶቻቸውን ጨምሮ ሁለመናቸውን ለአምልኮ በመስጠት የእሑድ የእምልኮ ፕሮግራሞች መሆን እንደሚገባቸው አድርገው ከሥረ መሠረታቸው እድሰዋቸዋል። ስለ እግዚአብሔር በርካታ እውነቶችን በመማር አንኳር ፍሬ ነገሮችን ከማየት ይልቅ መሆን እንደሚገባው እሑድ ጠዋት የምንሰበሰብበት ዋና ዓላማ እግዚአብሔርን ለማመስገን መሆኑን በትክክል ይጠቀሙበታል። 

6. እያንዳንዱ ክርስቲያን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መሳተፍ ያለበት መሆኑን በማጉላት የአትኩሮት አቅጣጫችንን እንደገና እንድናስተካክል እድርገዋል። ብዙ አብያተ ክርስቲያናት የቤተ ክርስቲያንን ሥራ በሙሉ የመሥራት ኃላፊነት የሰባኪው፥ የወንጌላዊውና የመዘምራኑ ነው በሚል ወጥመድ ውስጥ ይወድቃሉ። እነርሱ ግን መንፈስ ቅዱስ ለእያንዳንዱ ክርስቲያን የሰጠው ስጦታ እንዳለ ስለሚያምኑ ይህን ስጦታውን በንቃት ተግባራዊ ለማድረግ እያንዳንዱ ክርስቲያን በአገልግሎት መሳተፍ እንዳለበት አጥብቀው ያስተምራሉ። 

7. ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች በመስጠት ቸርነትን አጐልብተዋል። ብዙ ባሕላዊ ክርስቲያኖች ለእግዚአብሔር ለመስጠት የሚያቅማሙ ሲሆኑ ቢሰጡም እንኳ ለሥርዓት ያህል እጅግ ከፍተኛ በሆነ ጥንቃቄ በማስላት የገቢያቸውን አንድ እሥረኛ (እሥራት) በማቅረብ ብቻ ነው። ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች ግን ታላቅ ደስታቸውንና ምስጋናቸውን ለመግለጽ በጸጋ ስትልቅ ቸርነት ይሰጣሉ። 

8. ስለ ሰይጣንና አጋንንት ህልውና እውነታና ከእነርሱም ጋር ስለምናደርገው መንፈሳዊ ጦርነት አብያተ ክርስቲያናት በንቃት እንድንገነዘብ የካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች ረድተውናል። እነዚህን ኃይላት ለማሸነፍ በሚችለው በክርስቶስ ኃይል ላይ አትኩሮት ያደርጋሉ። 

9. ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች ሁሉም የእምነት ክፍሎች መንፈስ ቅዱስ ማን እንደ ሆነና በክርስቲያን ሕይወት ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንደሚያደርግ እንዲመረምሩ አስገድደዋል። የካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች የመንፈስ ቅዱስን ጉዳይ ሰአትኩሮት እንድንመለከት በሕይወታችንና በአገልግሎታችን የሚሠራውን ሥራ እንደንመረምር እስኪነግሩን ድረስ ብዙ ክርስቲያኖች ይህ የሥላሴ አካል በሕይወታችን ላይ ስላለው ሚና ግድ አልነበረንም። ሆኖም ግን በትምህርታቸው ምክንያት ሁላችንም «መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ምን ይላል? ሕይወት የሞላበትና ኃይል ያለው እምነት ይዤ ለመኖር የመንፈስ ቅዱስን ህልውና በምን ላረጋግጥ እችላለሁ?» የሚሉ ጥያቄዎች ለመጠየቅ ተገደድን። 

ጥያቄ፡- ሀ) እነዚህ ዘጠኝ ነገሮች እንዴት የአንተ ሕይወትና የቤተ ክርስቲያንህ አምልኮ አካል እንደሆኑ ግለጥ።

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.