በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና ልሳን በመናገር መካከል ያሉ ግንኙነቶች

ጥያቄ፡- «በልሳናት ካልተናገርክ በስተቀር የመንፈስ ቅዱስ ኃይልና ሙሉ ህልውና የለህም። በልሳናት ካልተናገርህ በስተቀር በመንፈስ ቅዱስ እልተጠመቅህም።» ሀ) እነዚህንና የመሳሰሉትን አባባሎች እንዴት እንደሰማህ ግለጽ። ለ) ስለ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀት እስካሁን ካጠናኽው ጥናትህ እነዚህን አባባሎች እንዴት ትመልሳቸዋለህ? 

የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ስልሳናት መናገርን ማስከተል አላበት የሚለውን አሳብ ሁሉም ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች የሚያጠብቁት ባይሆንም እንኳ በብዙ ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች አእምሮ ውስጥ ለመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ተቀዳሚ ማረጋገጫው በልሳን መናገር መሆኑ የጸና ነው። ይህ እሳብ የመጣው ከየት ነው? ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚያቀርቡት ማረጋገጫ ምንድን ነው? ለዚህ ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች ወደ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ፊታቸውን ይመልሳሉ። ስላ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ያላቸው መረዳት፥ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት በክርስቲያኖች ላይ ሲወርድ የመንፈስ ቅዱስ ህልውናው እንዲረጋገጥ ተአምራዊ በሆነው በልሳናት የመናገር ምልክት መታጀብ እንዳለበት ያስተምራል የሚል ነው። ብዙ ክርስቲያኖች ዛሬ በሚለወጡበት ጊዜ በልሳናት ስለማይናገሩ መንፈስ ቅዱስ በኃይል በመምጣት በልሳን ንግግር የሚረጋገጥበት ግልጽ የሆነ የመንፈስ ቅዱስ «ሁለተኛ ሥራ» መኖር አለበት በማለት ይከራከራሉ። 

ጥያቄው የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ በእርግጥ በልሳናት መናገርን የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አስፈላጊ ምልክት አድርጐ ያቀርበዋልን ? በክርስቲያኖችን ሕይወት መታየት ያለበት ነገር ነውን? በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ በልሳናት መናገር ከመንፈስ ቅዱስ ህልውና ጋር ተያይዞ የቀረበባቸው ሦስት ቦታዎች ብቻ አሉ። በሐዋርያት ሥራ 2፡4 ላይ መንፈስ ቅዱስ በ120 አማኞች ወይም የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ላይ ካመኑ በኋላ እንደወረደ እንመለከታለን። በሐዋርያት ሥራ 10ና 19 ላይ መንፈስ ቅዱስ በአሕዛብ ክርስቲያኖችና በመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ላይ ባመኑ ጊዜ እንደወረደ እንመለከታለን። በሦስቱም ቦታዎች ላይ በልሳናት መናገር የመንፈስ ቅዱስ ህልውና የተረጋገጠበት መንገድ ነው። 

ጥያቄ፡- የሐዋርያት ሥራ 2፡1-4፤ 10፡44-47፤ 19፡1-7 አንብብ። ሀ) [በእነዚህ ሦስት ስፍራዎች በልሳናት መናገር የቻሉት እነማን ነበሩ? ላ) በትናንትናው ትምህርት ላይ በመመሥረት መንፈስ ቅዱስ እነዚህን ሰዎች በልሳናት እንዲናገሩ ያስቻለበትን ምክንያት ዘርዝር። መንፈስ ቅዱስ በክርስቲያን ውስጥ ስለመገኘቱና ከድነት (ደኅንነት) በኋላ የመንፈስ ቅዱስ «ዳግሞ ሥራ» ሆኖ ስለመገለጡ ያለማወላወል እንድናምን እነዚህ ሦስት ሁኔታዎች በቂ ማረጋገጫ የሚሰጡን ይመስልሃልን? መልስህን አብራራ። 

ክርስቲያኖች ከደኅንነታቸው በኋላ ለሚቀበሉት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ማረጋገጫው በልሳናት መናገራቸው ነው ለሚለው የሥነ መለኮት ትምህርታቸው የጰንጠቆስጤ ክርስቲያኖች ማስረጃ አድርገው ለማቅረብ የሚጠቀሙባቸው በልሳን ስለመናገር የሚያወሱትን እነዚህን ሦስት ሁኔታዎች ነው። ሉቃስ እነዚህን ታሪኮች የጻፈው መንፈስ ቅዱስ በታሪክ ሁሉ ውስጥ ለሚሠራው ሦስቱ ሁኔታዎች ምሳሌ መሆናቸውን ለማሳየት ነው የሚል መረዳት አላቸው። ነገር ግን ሁኔታው እንደዚህ ነውን? መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ ሁሉ በልሳናት የተናገሩበትን እነዚህን ሦስት ታሪኮች ስንመለከት በልሳናት የመናገር ችሎታ ያረጋግጥ የነበረው የመንፈስ ቅዱስ ህልውናን ነበር? በሥነ መለኮታቸው ካሪዝማቲክ ባልሆኑ ክርስቲያኖች አመለካከት እግዚአብሔር በእነዚህ ሦስት ሁኔታዎች በልሳናት መናገርን እንደ ምልክት አድርጐ የሰጠበት አንድ ልዩ ነገር እየተካሄደ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው። ቀጥለን እያንዳንዱን ታሪክ ለየብቻ እንመለከታለን። 

1) የሐዋርያት ሥራ 2፡— በሐዋ. 2 ላይ 120 ደቀመዛሙርት (ያመኑት 3000 ሳይሆኑ) በመንፈስ ቅዱስ በተጠመቁና በተሞሉ ጊዜ ሁሉም በልሳናት መናገር ጀመሩ። ጴጥሮስ እየተፈጸመ የነበረው ምን እንደሆነ ለማያምኑት እይሁድ በሚናገርበት ጊዜ ወደ ብሉይ ኪዳን አመለከታቸው። ጴጥሮስ በልሳን በመናገራቸው ህልውናው የሚረጋገጥበት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ፥ እግዚአብሔር በኢዩ. 2 የተናገረውን ትንቢት መፈጸም ለመጀመሩ ለእስራኤል ማረጋገጫ ነው ይላቸዋል። የሰቀሉት ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት የሚያመጣው መሢሕ እንደሆነ ይገልጽላቸዋል። ሕፃን የነበረችው ቤተ ክርስቲያን የብሉይ ኪዳን ተስፋ የተፈጸመባት የእግዚአብሔር ሕዝብ ሆነች። አይሁዳውያን በብሉይ ኪዳን ሥርዓት ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡበት ጊዜ እከተመ። ይልቁኑ የአይሁድ ሕዝብም እንዲድኑና በብሉይ ኪዳን ቃል የተገቡላቸውን በረከቶች በሙሉ እንዲቀበሉ ከተፈለገ፥ ወደ እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መምጣት አለባቸው። 

ጴጥሮስ የሚሰብከው ነገር በእርግጥ እውነት መሆኑን እይሁዶች እንዴት ይወቁ? እግዚአብሔር ኢየሱስን ከተከተለ ከዚህ ትንሽ ቡድን ጋር እንደነበረ እንዴት ይወቁ? ምንም የማያወዛግቡና ግልጽ ምልክቶች ካላዩ በስተቀር አይሁዳውያን ይህን ናዝራውያን» በመባል የሚታወቀውን የተናቀ እፈንጋጭ የሰሜነኞች አናሳ ቡድን፥ እግዚአብሔር ለገባላቸው የብሉይ ኪዳን ተስፋዎች መፈጸሚያ ነው ብላው ለማመን ያዳግታቸው ነበር። ስለዚህ እግዚአብሔር ከዚህ ቡድን ጋር እንደነበረ፥ የሚናገሩትም መልእክት እውነት እንደሆነ በግልጽ ለማረጋገጥ እግዚአብሔር በልሳናት የመናገር ስጦታ ለደቀ መዛሙርት ሰጠ። ምልክቱ ትንቢት ወይም ሌላ ልዩ ተአምራት ያልሆነው በልሳናት መናገር የሆነው ለምን ነበር? እርግጠኛ ሆነን በዚህ ምክንያት ነው ለማለት አንችልም። ምክንያቱም ኢዩኤል እራሱም የጠቀሰው ትንቢት እንጂ በልሳናት መናገርን አልነበረም። በዚህ ጊዜ ከዓለም ዙሪያ የመጡ እግዚአብሔር ከደቀ መዛሙርት ጋር ስለመሆኑ የሚታይ ማረጋገጫ የሚሹ አይሁዳውያን ስለነበሩ በልሳን መናገርን እግዚአብሔር እንደ ምልክት ተጠቅሞ ይሆንን? በሚታወቁ ልሳናት መናገር፥ ወንጌልና መንፈስ ቅዱስ፥ ለአይሁድ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ሕዝቦች የተሰጡ ዓለም አቀፍ ስጦታዎች መሆናቸውን ለአይሁድና ለደቀ መዛሙርት የሚያሳይ ስለሆነ ይሆንን? የምንችለው መገመት ብቻ ነው። ግልጽ የሆነው ነገር በልሳናት መናገር የሚያረጋግጠው በኢዩ. 2 ላይ የተሰጡት የተስፋ ቃል ኪዳኖች በመጀመሪያይቱ ቤተ ክርስቲያን በሚገኙ በእነዚህ ጥቂት ክርስቲያኖች አማካኝነት መፈጻም መጀመራቸውን ነው። ቤተ ክርስቲያን እሁን የእግዚአብሔር ሕዝብ እንጂ የእስራኤል ሕዝብ ወይም በብሉይ ኪዳን እንደ ነበረው የአይሁድ ሕዝብ አልነበረችም። 

2. የሐዋርያት ሥራ 10፡- እግዚአብሔር በአይሁድ ሕዝብ እጅግ የተጠሉ ለነበሩት ለአሕዛብ መንፈስ ቅዱስን የመስጠቱ ጉዳይና ህልውናውንም ለአይሁድ ክርስቲያኖች መጀመሪያ በሰጠበት መንገድ ማረጋገጡ ለመጀመሪያይቱ ቤተ ክርስቲያን እጅግ ጠቃሚ የሆነ እውነት ነበር። እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነታቸው ምክንያት ብቻ ወደ ክርስቶስ አካል እንደ ጨመራቸው ይህ ምልክት ሆኗል። አሕዛብ ላመዳንም ሆነ የቤተ ክርስቲያን አባል ለመሆን አስቀድመው አይሁድ መሆን አይጠበቅባቸውም ነበር። በሐዋርያት ሥራ 11፡1-3 ላይ እይሁድ ሐዋርያው ጴጥሮስ ወደ አንድ አሕዛብ ሰው ዘንድ እንደ ሄደና ወንጌልን እንደ ሰበከላት በሰሙ ጊዜ ያሳዩትን ምላሽ አስታውስ። ጴጥሮስ ለዚህ ጉዳይ የሰጠውን መግለጫ የተቀበሉት መንፈስ ቅዱስ በአሕዛብ ላይ እንደ ወረደ በሰሙ ጊዜ ብቻ ነበር። በሐርያት ሥራ 15 ላይ የተጻፈውን በኢየሩሳሌም ጉባኤ ላይ የተደረገውን ኃይለኛ ክርክር ታስታውሳለህን? ከብዙ ዓመታት በኋላ በርካታ አይሁዳውያን ክርስቲያኖች አሕዛብ ኢየሱስን እንደ መሢሐቸውና አዳኛቸው አድርገው ለመቀበል አስቀድመው አይሁድ መሆን አለባቸው እያሉ ይከራከሩ ነበር። አሕዛብ ወደ ይሁዲነት የሚመጡት በመገረዝና የአይሁድን ሕግ በመጠበቅ ነበር። እግዚአብሔር አሕዛብን እንደ ተቀበላ ለአይሁዳውያን ክርስቲያኖች የሚያረጋግጥበትን ብቸኛ መንገድ መጠበቅ ሳያስፈልግ እግዚአብሔር ለእነርሱም መንፈስ ቅዱስን መስጠቱና ሙሉ ክርስቲያኖች መሆናቸውን ማሳየቱ ነበር። አይሁዳውያን አሕዛብ መንፈስ ቅዱስን እንደ ተቀበሉ እርግጠኞች የሚሆኑበት መንገድ ደግሞ አንድ ልዕለ ተፈጥሮአዊ የሆነ ምልክትን ማየት ነበር። ስለሆነም እግዚአብሔር በፍጹም የእኩልነት ደረጃ መቀበሉን ላማሳየት ከዚህ ቀደም ለአይሁድ የሰጠውን ያንኑ ምልክት ተጠቀመ። ሰው የሚድነው በእምነት ብቻ እንደ ሆነ በግልጽ ለማሳየት እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ለአሕዛብ ባወረደ ጊዜ በልሳናት መናገርን ሰጣቸው። ለአሕዛብ ሙሉና ፍጹም ክርስቲያን ለመሆን መገረዝም ሆነ የአይሁድን ሕግ መጠበቅ አላስፈለጋቸውም። እግዚአብሔር ሌላ ምልክት ተጠቅሞ ቢሆን ኖሮ ምልክቶችን በማወዳደር የእኔ ይበልጣል የሚል ክርክር ይነሣ ነበር። 

3. የሐዋርያት ሥራ 19፡- መጥምቁ ዮሐንስ ከታላላቅ ነቢያት አንዱ እንደ ነበር ኢየሱስ እራሱ ተናግሯል (ማቴ. 11፡11)። በአገልግሎቱ ጥቂት ዓመታት ዮሐንስ በርካታ ደቀ መዛሙርትን በማፍራቱ ሮም በምትገዛበት ዓለም ሁሉ ተሰራጭተው ነበር። ብዙዎቹ ዮሐንስ በተገደለበት ጊዜ ፍልስጥኤምን ትተው ስለወጡ ለኢየሱስ ሞት፥ ቀብርና ትንሣኤ ምክንያት የሆኑትን ሁኔታዎች አልተመላከቱም ነበር። መጥምቁ ዮሐንስን በምታከብረው ቤተ ክርስቲያን ዓይንስ የሚታዩት እንዴት ነበር? የዮሐንስ ጥምቀት (የደቀ መዛሙርቱን ንስሐ መግባት ያስከተላ) በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሊያደርጋቸው ይችል ነበርን? እግዚአብሔር በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ለመጨረሻ ጊዜ በልሳናት መናገርን ለቤተ ክርስቲያን ትልቅ ጠቃሚ ትምህርት ለማስተማር እንደ ምልክት ተጠቀመበት። የዮሐንስ ጥምቀት ማዳን የሚችል አልነበረም። አንድ ሰው የሚድነው በኢየሱስ ሲያምን ብቻ ነው። እነዚህ ሰዎች መቼ በትክክል እንደ ዳኑ እንዴት መናገር ይቻል ነበር? የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርት እርሱን ይከተሉ ሰነበረ ጊዜ ያልተደረገ፥ ነገር ግን የኢየሱስን የተጠናቀቀ የመስቀል ሥራ ባመኑ ጊዜ በትክክል የሆነላቸው ምን እንደ ሆነ እንዴት ማወቅ ይችላሉ? ይህ የዮሐንስ ጥምቀት ለሰው ድነት (ደኅንነት) በቂ አለመሆኑን እንዴት ማወቅ ይቻላል? በኢየሱስ ስም እስኪጠመቁ ድረስ መንፈስ ቅዱስን እንዳልተቀበሉ የሚያሳይ አንድ ልዕለ-ተፈጥሮአዊ ምልክት ከተገኘ ብቻ ይሆናል። በልሳናት የመናገር ምልክት የዮሐንስ ጥምቀት በቂ እንዳልነበር እግዚአብሔር ለሁሉም ያሳየበት መንገድ ነው። 

እንግዲህ አንዳንዶች በልሳናት መናገር የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ምልክት ነው ወደሚል ማጠቃለያ እንዴት እንደ ደረሱ መመልከትና መረዳት ቀላል ነው። በሦስቱ ጊዜያት እንደዚህ ነበር። ነገር ግን እነዚህ ሦስት ጊዜያት ድነት (ደኅንነት) በኢየሱስ ብቻ መሆኑን ለመመስከር የመንፈስ ቅዱስ ህልውና ልዩ ማረጋገጫ የተፈለገባቸው ጊዜያት ነበሩ። ሰዎች መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው በልሳን መናገራቸው ያልተጠቀሰበት ሌሎች ጊዜያት እንደ ነበሩም ተመልክተናል። ይህ የሚያሳየው በልሳናት መናገር ሰው መንፈስ ቅዱስ በሕይወቱ የማደሩ ቋሚ ምልክትና ማስረጃ እንዳልነበረ ነው። 

በተጨማሪ ሰዎች በልሳናት መናገርን የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ልማዳዊ ምልክት አድርገው እንዳልጠበቁት የሚያሳይ ቢያንስ አንድ ፍንጭ ከሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ እናገኛለን። በሐዋ. 11፡13-18 ጴጥሮስ በቆርኔሌዎስ ቤት የነበረውን ልምምዱን ሲያካፍል መንፈስ ቅዱስ በሁሉም ላይ በወርደበት ዓይነት በአሕዛብ ላይ ይመጣል አላለም። ሰዎች ሁሉ መንፈስ ቅዱስን ሊቀበሉ እንደሚያደርጉት በልሳናት ተናገሩ አላላዎ። በዚያ ምትክ በቆሮኔሌዎስ ቤት የሆነው ነገር በመጀመሪያው እንደ ሆነው ዓይነት መሆኑን ተናገረ። ጴጥሮስ «ሰመጀመሪያ ጊዜ» ያለበት ምክንያት፥ ለመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና መውረድ የመጀመሪያው ማረጋገጫ በልሳን መናገር ስለመሆኑ የሚያውቀው ብቸኛ ልምምድ የጰንጠቆስጤ ዕለት ስለነበር ሊሆን ይችላል። 

በመንፈስ ቅዱስ የተጠመቁ ክርስቲያኖች ሁሉ በልሳናት እንደማይናገሩ የተሰጠ የመጨረሻ ማረጋገጫ የምናገኘው 1ኛ ቆሮ. 12 ላይ ነው። እያንዳንዱ ክርስቲያን በመንፈስ የተጠመቀ ቢሆንም እንኳ (1ኛ ቆሮ. 12፡13)። ጳውሎስ ሁሉም ግን በልሳናት አይናገሩም አለ (1ኛ ቆሮ. 12፡30)። [ማስታወሻ፦ በግሪክ ይህ ጥያቄ የቀረበበት መንገድ አሉታዊ መልስን የሚጋብዝ መሆኑ ግልጽ ነው። በተሻለ መንገድ መተርጐም ቢፈለግ ‹ሁሉም በልሳን አይናገሩም። ይናገራሉ እንዴ?› የሚል ይሆናል።] 

አንዳንድ ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች በ1ኛ ቆሮ. ላይ የምናገኘው በልሳናት የመናገር ጉዳይ ለአንዳንድ ክርስቲያኖች ብቻ የተሰጠ ስጦታ ነው ይላሉ። ሆኖም ግን የሐዋርያት ሥራ 2 እና 10 ልሳናት የተለያዩ ናቸው። በዚህ ስፍራ የተጠቀሰው ልሳን ግን በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አማካኝነት የሚመጣ፥ ሁሉም ክርስቲያኖች በመንፈስ ለመጠመቃቸው ማረጋገጥነት የሚሹት መሆን አለበት ይላሉ። ይህ ክፍል 1ኛ ቆሮ. 12፡30 ስለ መንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች እንደሚናገር እውነት ነው። ነገር ግን ስለ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ይናገራል። በዚህ ላይ ያለው በልሳን መናገር ሰው በመንፈስ ቅዱስ ሲጠመቅ ከሚለማመደው የልሳን ንግግር የተለየ ነው ማለት ወጥነት የሌለው የራስን አመለካከት መጽሐፍ ቅዱስ እንዲደግፍ የማስገደድ ያህል ይሆናል። 1ኛ ቆሮ. በግልጽ የሚያስተምረን በልሳናት መናገር ለሁሉም ክርስቲያኖች ሳይሆን ለአንዳንዶች የተሰጠ ስጦታ መሆኑን ነው። 

በእኔ እምነት ልሳን ለመንፈስ ቅዱስ መውረድ ምልክት መሆኑን በሚገባ የተረዳነው ከሆነ ለአንዳንዶች መንፈስ ቅዱስ በሕይወታቸው ለመሥራቱ ቢሆንም የግድ የሚያስፈልግ አለመሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል። መንፈስ ቅዱስ ያላቸው ብዙ ክርስቲያኖች በልሳን አይናገሩም። 

ጥያቄ፡- የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከት፡- የሐዋ. 1፡4-5፥ 8፤ 2፡33፤ 38-39፤ 5፡32፤ 8፡17፥ 20-21፤ 10፡43-45፤ 11፡17-18፤ 19፡2-4። በክርስቲያን ላይ መንፈስ ቅዱስ እንዲወርድ መሟላት ያለባቸው ነገሮች ምንድን ናቸው? 

ከሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ጥናት የምንመለከተው አንድ ተጨማሪ ነጥብ ከድነት (ደኅንነት) በኋላ ለመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ወይም ለመንፈስ ቅዱስ መውረድ ምንም ዓይነት ቅድመ-ሁኔታ ያለመቀመጡ ነው። የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ከድነት (ደኅንነት) በኋላ የሚመጣ ከሆነ በክርስቲያን ላይ በኃይል እንዲወርድ (በሁለተኛ በረከት) የሚያስችሉ ሁኔታዎችን መጽሐፍ ቅዱስ ያስቀምጥልን ነበር። ብዙ የጰንጠቆስጤ ሥነ መለኮት ትምህርት አስተማሪዎች ክርስቲያኖች መንፈስ ቅዱስን ከመቀበላቸው ወይም በመንፈስ ቅዱስ ከመጠመቃቸው በፊት ማድረግ ያለባቸው አንዳንድ ነገሮች እንዳሉ ይናገራሉ። ጸሎት፡ መታዘዝና እምነትና አንዳንድ ጊዜ እንደ እጅ መጫን ያሉትን ድርጊቶች ይዘረዝራሉ። ከእነዚህ ጥቂቱቹ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ መንፈስ ቅዱስ በወረደባቸው አንዳንድ ጊዜያት ላይ የነበሩ ቢሆንም በሁሉም ጊዜያት ቀን አልነበሩም። 

በአዲስ ኪዳን ውስጥ እነዚህ ነገሮች ለመንፈስ ቅዱስ መውረድ እንደ ቅድመ-ሁኔታ የተሰጡበት ቦታ ፈጽሞ የለም። በሐዋ. 1፡4-5፥ 8 (ሉቃስ 3፡15-17)፣ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት የተገለጸው እንደ ተስፋ ቃል ነው። በግሪክ «ትቀበላላችሁ» የሚለው ግሥ የሚያመለክተው ተቀባዮቹ የሚያደርጉት ምንም ነገር ሳይኖር ወደፊት እንደሚፈጸም ተስሩ ነው። ኢየሱስ በሚናገርበት ጊዜም የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ይቀበሉ ዘንድ ማድረ ስላላባቸው ምንም ነገር አልተናገረም። መጸለይቶ እራስን መስጠትና መታዘዝም በቅድመ-ሁኔታነት አልቀረቡም። ይልቁኑ ተስሩ የተሰጠው ስጦታ እስኪመጣ ድረስ እንዲጠብቁ ብቻ ነገራቸው። ሊያሟሉት የሚገባ ቅድመ ሁኔታ በኢየሩሳሌም ለመቆየት ብቻ ነበር። መንፈስ ቅዱስ አዲስ እማኞችን ባጠመቀበት በመጀመሪያው ወቅት ለመቀበል ሲሉ ስላደረጉት እንደ መጸለይ፥ እራስን መስጠት መሻት የመሳሰሉ አንዳችም ነገር አልተናገረም። ወመንፈስ ቅዱስ በመጣ ጊዜ የነበሩበትን ሁኔታ ለመግለጽ ሉቃስ የተጠቀመበት ቃል ቁ 2 ላይ ተቀምጠው ነበር የሚል ነው። በመጨረሻ፡- የመንፈስ ቅዱስን መምጣት ለመግለጽ አገልግሎት ላይ የዋሉት አራት ቃሎች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መምጣቱን ያረጋግጣሉ። እነዚህ አራት ቃሎች፡- 1) ተስፋ (የሐዋ. 1፡4፤ 2፡33-39፤ ሉቃስ 24፡49)፤ 2) ሰጦታ (የሐዋ. 2፡38፤ 8፡20፤ 10፡45፤ 11፡17)፤ 3) የሰጠው (የሐዋ. 5፡32፤ 11፡17-18) እና 4) ትቀበላላችሁ (የሐዋ. 1፡8፤ 2፡38፤ 8፡17፤ 10፡47፤ 19፡2) የሚሉ ናቸው። 

የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ለመሆንና በመንፈስ ቅዱስ ለመጠመቅ የተሰጠ ብቸኛ ቅድመ-ሁኔታ ንስሐ መግባትና በክርስቶስ ማመን ነው። (የሐዋ 2፡38፤ 10፡43 እና 19፡4ን ከሐዋ. 9፡17ና ከ22፡16 ጋር አወዳድር)። በሐዋርያት ሥራና በቀረው የአዲስ ኪዳን ክፍል ሁልጊዜ የምንመለከተው በኢየሱስ ከማመን በቀር በእነርሱ በኩል ምንም ዓይነት ድርጊት ወይም ሁኔታ ሳይፈለግ መንፈስ ቅዱስ በክርስቶስ ባመኑት ሁሉ ላይ እንደ ወረደባቸውና እንዳጠመቃቸው ነው። ይህ የሚያጠናክረው የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ መሆንና መጠመቅ ሰው በሚለወጥበት ጊዜ በሕይወቱ የሚፈጸም መሆኑን ነው። 

እንዳንድ የጰንጠቆስጠ ክርስቲያኖች የሐዋ. 5፡32 መታዘዝ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ቅድመ-ሁኔታ መሆኑን ያስተምራል ይላሉ። የሚያስተምረው ይህን ነውን? ከዚህ ጥቅስ የሚከተሉትን ነገሮች ልብ በል፤ 

1- ክፍሉ የሚናገረው መንፈስ ቅዱስ በድነት (ደኅንነት) ጊዜ ስለ መምጣቱ ነው። ይህ የመንፈስ ቅዱስ ሁለተኛ መምጣት ማለትም የማጥመቅ ሥራው ከሆነ ሉቃስ በቃላት አጠቃቀሙ ግልጽነት ጐድሎታል ማለት ይሆናል። 

2. መንፈስ ቅዱስ በአንድ ሰው ላይ የሚወርደው ወይም የሚያጠምቀው ሰውዩው ስለሚታዘዝ ከሆነ፥ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ በተሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት ነህ ስጦታ መሆኑ ቀርቶ የሥራ ውጤት ይሆናል (ሮሜ. 4፡4 ተመልከት።)። 

3. ጴጥሮስ ለወንጌል ትእዛዛት የእምነት ምላሽ በመሆን ስለሚገለጸው ታዛዥነት እንደሚናገር ክፍለ-ምንባቡ በግልጽ ያስቀምጣል። ( የሐዋ. 5፡31 ና 6፡7 ላይ ያለውን አሳብ ተመልከት)። ይህ ሰዎች ለእምነት ወይም በክርስቶስ እንዲያምኑ ለተደረገ ጥሪ የመታዘዛቸው ምሳሌ ነው። እውነተኛ እምነት ሁልጊዜ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ የመኖር ውሳኔንም ይጨምራል። 

4. መንፈስ ቅዱስ እንዲወርድ ሙሉ በሙሉ መታዘዝ አስፈላጊ ከሆነ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል የሚበቃ አላ ብለን መናገር እንችላለን? ከሚታወቁ ኃጢአቶች ሁሉ ነጽተን ሙሉ በሙሉ የታዘዝንበት ጊዜ ኖሮ ያውቃል? 

ጥያቄ፡- ሀ) አንዳንድ ሰዎች መንፈስ ቅድስን ለመቀበል አስፈላጊ ሁኔታዎች ናቸው ብለው የሚያስተምሩት ምን ምን ናቸው? ለ) መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል የሚያስፈልጉ ቅድመ–ሁኔታዎች ናቸው ብለህ የምታምነው ምን ምንን ያካትታል? 

ጥምቀትና መጎል ላልሆኑ፥ ክርስቲኛል። ይህን የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና ሙላት እንደዚሁም በልሳን መናገርን በተመለከተ ጴንጠቆስጤና ጴንጠቆስጤ ሳልሆኑ፥ ክርስቲያኖች መካከል በሚታየው የማያቋርጥ ውዝግብ ላይ ከፍተኛ ትኩረት አድርገናል። ይህን ያደረግንበት ምክንያት በአብያተ ክርስቲያናት መካከል በአሁኑ ጊዜ መከፋፈልን ከሚያስከትሉ ነገሮች አንዱ ይህ ስለሆነ ነው። በጥናታችን ሁሉ ይህ ክርክር ክርስቲያን መሆን አለመሆናችንን የሚወስን እንዳይደለ ለማስተማር በቂ ጥንቃቄ አድርገናል። ይህ ክርክር የትኛው ቡድን ጌታን ይወዳል፥ መንፈሳዊውስ የትኛው ነው የሚልም አይደለም። በአጠቃላይ ስንመለከተው ሁለቱም ቡድኖች በቅንነት ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተልና ለእርሱ ለመኖር የሚፈልጉ ናቸው። ነገር ግን ጥያቄያችን አዲስ ኪዳን ከሚያስተምረው ትምህርት ጋር የበለጠ ቅርብ የሆነው የትኛው አመለካከት ነው? የሚል ነው። የጰንጤቆስጤ ክርስቲያኖች መንፈስ ቅዱስ ለዳግመኛ መባረክ ወደ ክርስቲያን ሕይወት በመምጣት በልዩ ኃይል መሙላቱ የማንኛውም ክርስቲያን ልምምድ መሆን እንዳለበት የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ያስተምራል ብለው ያምናሉ። ነገር ግን የአዲስ ኪዳን ማስረጃ ዎች ክርስቲያኖች ሁሉ ከዳኑበት ቅጽበት ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ እብሮአቸው እንደሚኖር የሚያስተምር መሆኑን ተመልክተናል። ካሪዝማቲክ ያልሆኑ ክርስቲያኖች መንፈስ ቅዱስ በክርስቲያኖች ላይ ልዩ በሆነ መንገድ ይመጣል ቢሉም ግን ይህን አመጣጥ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ይሉታል። በተጨማሪ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ልዩ የሆነ ሁለተኛ በረክትን አንድ ጊዜ ብቻ በመፈጸም የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎትን የሚያጠቃልል ሳይሆን በክርስቲያን ዘመን ሁሉ በተደጋጋሚ ያለማቋረጥ ክርስቲያኖችን የሚያድስበት ነው ይላሉ። 

ልናስታውሰው የሚገባን ዋና ነገር ስለ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ሙላት ምን እናምናለን? የሚለው አይደላም። ቁም ነገሩ አሁን የምንኖረው በመንፈስ ቅዱስ ምሪትና ቁጥጥር ሥር መሆኑ ነው። አሁን በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተናል ወይ? መንፈሳዊ ሕይወታችን ዕለት በዕለት እያደገ ነው ወይ? ሕይወታችን የተለየ መሆኑን ሰዎች ያያሉ ወይ? በምናገላግላው ማኅበረሰብ ላይ በጐ ተጽእኖ አድርገናልን? በአገልግሎታችን ውስጥ ኃይል አለ? በሐዋ. 1፡4፥ 8 ላይ የምንመለከተው ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስን እኛ የሰጠበት ዋና ምክንያት በታላቅ ኃይል የመመስከር ችሎታን እንዲሰጠን ነው። ይህ እየሆነ ነውን? ስለ እነዚህ ሁለት የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች ልንናገርና ልንከራከርም እንችላለን። ነገር ግን እግዚአብሔር የሚገደው ነገር በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር የመኖራችን ጉዳይ ነው። ዛሬ በቤተ ክርስቲያን በጣም የሚያስፈልጉት ስለ መንፈስ ቅዱስ ሙላትና ጥምቀት በትክክል የሚረዱ የሥነ መለኮት መምህራን አይደሉም። ነገር ግን በትምህርት ቤት፥ በቤተ ክርስቲያን፥ በሥራ ቦታ ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር የሚኖሩና ክፉ ነገሮችን ሁሉ በመሸሽ እግዚአብሔር ይጠቀምባቸው ዘንድ ሕይወታቸውን የሚሰጡ ክርስቲያኖችን ነው። መንፈስ ቅዱስ ለመጀመሪያይቱ ቤተ ክርስቲያን የሰጠውን ኃይል በሕይወታችንና በቤተ ክርስቲያናችን የምናየው ይህ ሲሆን ብቻ ነው። 

ጥያቄ፡– ሀ) የመንፈስ ቅዱስን የማጥመቅና የሙላት ተግባርን በትክክል “ከመረዳት ይልቅ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ሥር መኖር አስፈላጊ የሚሆነው በምን መንገድ ነው? ለ) በቤተ ክርስቲያናችሁ ብዙ ሰዎች ሙሉ በሙሉ በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር ስለ መኖር ቢያስቡ ኖሮ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ትለወጥ ነበር ብለህ ታስባለህ? ) መንፈሳዊ ስለ መሆን ወይም በመንፈስ ቅዱስ ስለ መጠመቅ ያሉ አሳቦችን በዝግታ ማረም የሚያስፈልገው ለምን ይመስልሃል? በመንፈሳዊነት ጉዳይ የሚነሡ የተሳሳቱ እመለካከቶች ምን ምን ናቸው? 

ስለ መንፈስ ቅዱስ የፈለግነውን ማናቸውንም ነገሮች ማመን እንችላለን ከሚል ሌላኛው አክራሪ ጽንፍ መጠንቀቅ አለብን። ለምን? በመጀመሪያ፥ «የእውነትን ቃል በቅንነት የምንናገር» የማያሳፍር ሠራተኛ እንሆን ዘንድ (2ኛ ጢሞ. 2፡15) በእግዚአብሔር ፊት ኃላፊነት አለብን። በሁለተኛ ደረጃ ፥ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አሳብ ለመኖሮ አጥብቀን ካልተጋን የሐሰት ትምህርት የሚያስተምሩ ሰዎች እኛንና ጉባኤያችንን ወደ ስሕተት አዝቅት በመምራት በመጨረሻ መንፈሳዊ ሕይወታችንንና ምስክርነታችንን ይደመስሱታል። በሦስተኛ ደረጃ ፥ ላላ መንፈሳዊነትና ስለ መንፈስ ቅዱስ ህልውና ማረጋገጫ መንገዶች በሚሰጡ የተሳሳቱ አመለካከቶች የተነሣ በአብያተ ክርስቲያናት መካከል እየሰፋ ያለውን መከፋፈል መግታት አለብን። እግዚአብሔር የሚከበረው በአንድነት እንጂ በመከፋፋል አይደለም። 

ስለ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ለተደረገው ጥናት የማጠቃለያ አሳቦች 

ጥያቄ፡- ሀ) ጴንጠቆስጤ ያልሆኑ ክርስቲያኖች መንፈስ ቅዱስ አላን ነበማለት እየፎከሩ፥ ነገር ግን ኃይልን ሳይሹ በእምነታቸው ላይ የሚያንዣብብ ምን አድጋ ታያለህ? ለ) እነርሱ በሚያመልኩበት መንገድ (ካላመለካችሁ ወይም በልሳን ካልተናገራችሁ በእውነት በመንፈስ ቅዱስ አልተሞላችሁም በሚሉ የጰንጠቆስጤ ክርስቲያኖች እምነት ላይ ምን አደጋ ታያለህ? ሐ) ሁለቱ ቡድኖች አንዳቸው ለሌላቸው ሊኖራቸው የሚገባ በጣም የላቀ አመለካከት ነው ብለህ የምታምነው ምንድን ነው? 

1) ጰንጠቆስጤ ያልሆኑት፡- ጴንጠቆስጤ ያልሆኑት የሥነ መለኮት ትምህርታቸው «የሚያስፈልገኝን ሁሉ አግኝቻለሁ» ወደ ሚል አስተሳሰብ እንዳይመራቸው መጠንቀቅ አለባቸው። ምክንያቱም ይህ ወደ መንፈሳዊ ሞትና ቅዝቃዜ የሚመራ ነው። ክርስቲያኖች መንፈስ ቅዱስን በምንድንበት ጊዜ አግኝተን ይሆናል። ግን ያገኘነውን ልንጠቀም መቻል አለብን። የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ወደ ክርስቶስ አካል ጨምሮናል ሊል የሚያስፈልገንን ያህል ኃይል በሙሉ ሰጥቶናል ማለት አይደለም። የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን በዳንንበት ቅጽበት አግኝተናል የሚለው አሳብ በራስ ወደ መተማመን በማምራት ወደ ሕይወታችን የመንፈስ ቅዱስን ሥራ በሙላት እንጻንሻ ያግደናል። ይህም ደግሞ በራሷ ላይ የምትደገፍና በኃይሏ የምታገለግለውን ቤተ ክርስቲያን ይፈጥራል። በክርስትና ሕይወታችንና አገልግሎታችን በራሳችን ላይ የምንመካ እንዳንሆን መጠንቀቅ አለብን። እግዚአብሔር የጰንጠቆስጤ እብያተ ክርስቲያናትን የባረከው በመንፈስ ቅዱስ ሥራ ላይ በማተኮራቸውና ራሳቸውን ዝቅ በማድረግ ኃይልን እንዲሰጣቸው በእርሱ ላይ በመታመናቸው ነው። 

ጰንጠቆስጤ ያልሆኑ ክርስቲያኖች በዛሬይቱ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የእግዚአብሔር ተአምራዊ ኃይል አያስፈልግም ላማላት ምክንያት ከመፈላለግ መጠንቀቅ አለባቸው። ብዙ ምዕራባውያን ክርስቲያኖች በዚህ ጉዳይ ጥፋተኞች ናቸው። የምናመልከው አምላክ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ታላላቅ ተአምራት ያደረገውን ያንኑ አምላክ ነው። እግዚአብሔር ሁልጊዜ ተአምራትን የማያደርግ ቢሆንም እንኳ በዚያ መንገድ ለመሥራትም ይችላል። ይህን ኃይል የማናየው ጴንጠቆስጤ የሆኑ ወንድሞችና እህቶች እንደሚያደርጉት በተስፋ ስለማንጸልይበት ይሆን? 

2) ጰንጠቆስጤዎች፡- ጴንጠቆስጤ ወይም ካሪዝማቲክ ወንድሞችና እህቶች ለተሟላ ድነት (ደኅንነት) ያስፈልጋል በማለት በክርስቶስ እምነት ላይ የሆነ ነገር ከመጨመር መጠንቀቅ አለባቸው። እንደምታስታውሱት በገላትያ ቤተ ክርስቲያን አንዳንድ አይሁዳውያን ወንድሞች ለመጀመሪያ ድነት (ደኅንነት) በክርስቶስ ማመን በቂ ሲሆን ፍጹም ክርስቲያን ለመሆን አንድ ክርስቲያን መገረዝ ግዴታው ነው በማለት ያስተምሩ ነበር። ጳውሎስ የድነት (ደኅንነት) ልምምዳችንን ፍጹም ለማድረግ በክርስቶስ ባለን እምነት ላይ አንዳችም ነገር እንዳንጨምር ያስጠነቅቀናል (ገላ. 1፡6-7)። ጴንጠቆስጤ ያልሆኑ ወንድሞችና እህቶች ፍጹም እንዳይደሉ የሚያመለክት ማንኛውንም ድርጊት ከማድረግ መጠንቀቅ* አለብን። ኤፌ. 1፡3ን ተመልከት። በዚህ ስፍራ መንፈሳዊ በረከቶችን በሙሉ በደኅንነታችን ውስጥ እንደተቀበልን ተጽፏል። ይህ መንፈስ ቅዱስንም ይጨምራል (ኤፌ. 1፡13-14)። 

ጴንጠቆስጤዎች መጽሐፍ ቅዱስ ደጋግሞ እንዳናደርገው የሚያዘውን የእግዚአብሔርን ምልክቶች ከመፈለግ መጠንቀቅ አለባቸው (1ኛ ቆሮ. 1፡22-23፤ ሉቃስ 4፡12፡11፡29-32)። እግዚአብሔር ህልውናውን ለማስረገጥ በልሳናት መናገርን የመሰሉ ልዕለ-ተፈጥሮአዊ ምልክቶችን ሊያደርግ ይችላል። ነገር ግን ሁልጊዜ ማድረግ አለበት ማለት በአደገኛ ሁኔታ መንፈሳዊ ሥርዓተ-አልበኛ መሆን ነው። 

ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች የመንፈስ ቅዱስን ህልውና ለማረጋገጥ በየጊዜው እየመጠቁ የሚሄዱ ልምምዶችን ከመሻት መጠንቀቅ አለባቸው። መንፈስ ቅዱስ ህልውናውንና ኃይሉን ለማረጋገጥ አንዳንድ አስደናቂ፥ አስገራሚና አንዳንድ ጊዜም አሳፋሪ በሆኑ መገዶች እንዲሠራ ይፈልጋሉ። በሕይወታቸው በጽኑ ተመሥርተው ያላመናወጥ ማደጋቸውን በማየት አይረኩበትም። ነገር ግን እግዚአብሔር ታላላቅ ነገሮችን እንዲያደርግ ሁልጊዜ ይፈልጋሉ። መንፈስ ቅዱስ የተሰጠን በአስደናቂ ነገሮች እንዲያዝናናን ወይም ራስ-ወዳድነት የሚያጠቃውን ፍላጐታችንን እንዲያገለግል እይደለም። መንፈስ ቅዱስ የተሰጠን እግዚአብሔርን እንድናመልክ፥ በሕይወታችንና ከሌሎች ጋር በሚኖረን ኅብረት እርሱን እያስከበርን እንድንኖር ይረዳን ዘንድ ነው። 

ጴንጠቆስጤዎች ከእግዚአብሔር እንደሆነና የመንፈሳዊነት ማረጋገጫ እንደሆነ የሚመሰክሩለትን ማንኛውንም ልምምድ ያላ ጥያቄ ከመቀበል መጠንቀቅ አለባቸው። ሰይጣን የእግዚአብሔርን ልጆች ለማታላል ተአምራትን ማድረግ ይችላል። ማንኛውም ልምምድ መጽሐፍ ቅዱስ ከሚያስተምረው ጋር አብሮ የሚሄድ መሆኑን በቀጥታ በቃሎቹም ሆነ በመንፈስ መመርመር አለበት። 

ሁለቱም ክፍሎች እበልጣለሁና እሻላለሁ ከሚል ዝንባሌ መጠንቀቅ አለባቸው። ጴንጠቆስጤ ያልሆኑት ክፍሎች ብዙ ጊዜ እኛ የሰለጠ ‹መጽሐፍ ቅዱሳዊ› ነን በማለት መኩራራት ይታይባቸዋል። ጰንጠቆስጤዎችን ከወንጌላውያን የሥነ መለኮት ትምህርት ቋፍ ላይ እንዳሉ አድርገው ይመለከቷቸዋል። እንዲያውም አንዳንድ ሰዎች ጴንጠቆስጤ ክርስቲያኖች መናፍቃን ናቸው ሲሉ ሰምቼ አውቃለሁ። ይህ ብዙ ጰንጠቆስጤዎች በእግዚአብሔር ቃል ላይ ያላቸውን ጠንካራ አትኩሮትና ልምምዳቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እንዲሆን የሚያደርጉትን ጥረት ዋጋ የሚያሳጣ ነው። (ይህ በተለይ ለተወሰነ ጊዜ ጴንጠቆስጤ በነበሩ አማኞች የሚሠራ እውነት ነው)። 

ጴንጤቆስጤዎች አንዳንድ ጊዜ በልሳን የማይናገሩ ወይም እነርሱ በሚያመልኩበት አኳኋን የማያመልኩ ሌሎች ሰዎች በክርስትና ልምምድ ውስጥ እጅግ አስፈላጊ የሆነውን ክፍል እንዳጡና በዚሁ ምክንያት «የቀረባቸው» እንደሆኑ ይናገራሉ። አንዳንዶች እንዲያውም በልሳን የማይናገሩ ሁሉ እውነተኛውን የመንፈሳዊ ኃይል ልምምድ አላገኙም ብለው ሲናገሩ ሰምቻለሁ። ይህ ክርስቲያኖችን በሁለት ደረጃ ወደ መመደብ ያደርሳቸዋል። ይኸውም የተሻለ መንፈሳዊ ሕይወት ያላቸው ማለትም መንፈስ ቅዱስ ያላቸውና ስልሳናት የሚናገሩትን በአንድ ወገን ሊያስቀምጡ፥ ዝቅተኛ መንፈሳዊ ሕይወት ያላቸው ማለትም መንፈሱ ስሙላት የሌላቸውን በሌላ ወገን ያስቀምጣሉ። አዲስ ኪዳን ክርስቲያኖችን ‹ያላቸው› ና ‹የሌላቸው) ብሎ ክፋፍሎ አያውቅም። ይልቁኑ ሁላችንም በቅድስናና በፍጹምነት መንገድ ያለን ዘላለማዊውን ሕይወት እስከምንቀዳጅ ድረስ ምን ጊዜም ልንደርስበት የማንችል ኃጢአተኞች እንደሆንን ብቻ ያስተምራል (ፊልጵ. 3)። «እኔ እሻላለሁ» የሚለው ይህ የሁለቱ ዝንባሌ በክርስቶስ እካል መካከል መከፋፈልን ያመጣል። 

አንድ ተማፅኖ ላቅርብ። ሁላችንም የሌላውን ልምምድ እውነተኛነትና ቅንነት ከመካድ እንጠንቀቅ። ጴንጠቆስጤ ያልሆናችሁ፥ የአንዳንድ ጰንጠቆስጢዎችን ልምምድ እውነተኛነት አትካዱ አብዛኛዎቹ ልምምዶቻቸው በእውነት ከእግዚአብሔር ናቸው። ጴንጠቆስጤ የሆናችሁ ደግሞ ለመንፈስ ሙላት ማረጋገጫ እናንተ የምትለማመዱትን ሁሉ ሌሎች እንዲለማመዱ እትጠብቁ። ሌሎች የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን መቀበላቸውንና በልባቸው መንፈስ ቅዱስ መኖሩን አትካዱ። በእውነት ዳግም የተወለዱ እማኞች የመንፈስ ጥምቀትንና የመንፈስ ማደርያነትን አግኝተዋል። አብዛኛዎቹ በኃይሉ ሙላት በደስታ ይኖራሉ። በእርግጥ በዚህ ሙላት ሐሤት እያደረጉ መኖርን መማር የሚገባቸው ሌሎች ብዙዎች አሉ። ስለዚህ ሁላችንም የመንፈስ ቅዱስን ህልውናና ኃይል የበለጠ በሕይወታችን እንዲሠራ ሁልጊዜ አጥብቀን እንፈልግ። ለእምነታችንና ለልምምጻችን ሁልጊዜ መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርገን እንጠቀም። ሌላ መመዘኛ የሚያስቀምጥ ሰው ቤቱን የሕይወትን ማዕበል በማይቋቋም አሸዋ ላይ እንደሚመሠርት ነው (ማቴ. 7፡24-27)። 

ጥያቄ፡- ሀ) መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ በሰው ልብ ማደር፥ ጥምቀትና ሙላት ያስተምራል ብለህ የምታምነውን በአጭሩ ጻፍ። ለ) በየትኛው ክፍል ትመደባለህ? ለምን? ሐ) ጴንጠቆስጤዎችም ሆኑ ጴንጠቆስጤ ላልሆኑት ክርስቲያኖች የተሰጡትን ማስጠንቀቂያዎችና ምክሮች ማስታወስና መተግበር አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድን ነው? መ) ሰኢትዮጵያ በሚገኙ ቤተ ክርስቲያኖች በካሪዝማቲኮችም ሆነ ካሪዝማቲክ ባልሆኑት የሚያንዣብበውን አደጋ እንዴት ትመለከተዋለህ? ሠ) የእግዚአብሔርን ቃል ያለማቋረጥ በማጥናት እምነታችንን በየጊዜው መሞረድ የሚያስፈልገው ለምንድን ነው?

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.