መንፈሳዊ ስጦታ ምንድን ነው?

ጥያቄ፡- ሀ) መንፈሳዊ ስጦታ ምንድን ነው? የሚለውን ጥያቄ እንዴት ትመልሰዋለህ? ለ) መንፈሳዊ ስጦታ ከተፈጥሮአዊ ችሎታ የሚለየው እንዴት ነው? 

ዛሬ በቤተ ክርስቲያን በመንፈሳዊ ስጦታ ምንነት ላይ በርካታ የተላያዩና የተምታቱ አሳቦች አሉ። አንዳንዶች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ጥሩ ዘማሪ ይሰውና የመዘመር መንፈሳዊ ስጦታ አለው ይላሉ። የመዘመር ችሎታ ስጦታ ሲሆን ይህን ስጦታ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሰዎችን ለማገልገል ልንጠቀምበት እንችላለን። ነገር ግን ክርስቲያን ያልሆኑ በርካታ ሰዎች የማከም ችሎታ አላቸው። ብዙ ጊዜ ጌታን የማያከብር ዜማ ያዜማሉ። ስለዚህ ዜማ ከእግዚአብሔር የሚገኝ ስጦታ ቢሆንም ለክርስቲያኖችና ክርስቲያን ላልሆኑም የሚሰጥ ተፈጥሮአዊ ችሎታ ነው። ስለዚህ የመዘመር ችሎታ በራሱ መንፈሳዊ ስጦታ አይደለም። ሌሎች ደግሞ አንዳንድ ሰዎች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚያደርጉትን እንደ ተአምራትና ፈውስ የመሳሰሉ አስደናቂ ሁኔታዎችን ብቻ መንፈሳዊ ስጦታዎች ናቸው ብለው ያስባሉ። ሆኖም ቀን ብዙ ጊዜ መንፈሳዊ ስጦታዎች ሌሎችን እንደ መርዳት ሳሉ ቀላል ነገሮች የሚገለጡም ናቸው (ሮሜ 12፡6-8)። 

አንድ ሰው መንፈሳዊ ስጦታ «የክርስቶስን አካል የምናገለግልበት የጸጋ ስጦታ ነው» ብሏል። መንፈሳዊ ስጦታ፥ «ቤተ ክርስቲያንን ማለትም የክርስቶስን እካላ እንዲያገለግልበት እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ለእያንዳንዱ ክርስቲያን የሚያድላው ነፃ ስጦታ» ሲሆን አገልጋዩ የክርስቶስ አካል ለሆነችው ለቤተ ክርስቲያን ሰዎችን በማዝ አገልግሎቱን ይሰጥ ዘንድ የሚያስችላውን ሁኔታ የሚፈጥር ነፃ ስጦታ ነው። 

ይኸውም፡- 

የቤተ ክርስቲያን ጌታ የሆነውን ክርስቶስን ማምልከ እንዲችሉ፥ 

ክርስቶስን ወክለው ለቤተ ክርስቲያን ይናገሩ ዘንድ፥ 

ክርስቶስን እየመሰሉ ያድጉ ዘንድ ሌሎችን እንዲረዱ፥ 

ክርስቶስን ወክለው የሌሎችንም ክርስቲያኖች ፍላጎት እንዲያገለግሉ። 

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በዓለም ፊት እንዲወክሉ የሚያስችልበት መንገድ ነው። 

ቀጥሎ መንፈሳዊ ስጦታዎችን በተመለከተ ዋና የሚባሉ ትምህርቶችን በአጭሩ እንመለከታለን። 

1 እግዚአብሔር ለክርስቲያኖች እንደ ስጦታ የሚሰጣቸው ነገር ነው። ከእግዚአብሔር ጸጋ የሚመጣ ስለሆነ ሠርተን ወይም በጣም መንፈሳዊ በመሆናችን የምናገኘው አይደለም። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ከራሱ ፍላጐት በነፃ ለክርስቲያኖች የሚሰጠው ነገር ነው። 

2. የሚሰጠው ለክርስቲያኖች ብቻ እንጂ ክርስቲያን ላልሆኑት አይደለም። ስለዚህ አንድ ሰው ከመዳኑ በፊት ሳይሆን ከዳነ በኋላ ብቻ የሚያገኘው ነው። ይህ ማለት ተፈጥሮአዊ ችሎታዎች በራሳቸው መንፈሳዊ ስጦታ ፧ አይደሉም ማለት ነው። ከተፈጥሮ ችሎታ ጋር ሊያያዙ ቢችሉም እንኳ መንፈሳዊ ስጦታዎች ከእግዚአብሔር የሚሰጡ ልዩ ስጦታ ስለሆኑ ከተፈጥር ችሎታ የላቁ ናቸው። 

3. የመንፈሳዊ ስጦታዎች ዓላማ ኢየሱስን ወክሎ ሌሎችን ማገልገል ነው (ኤፌ. 4፡1-13፤ 1ኛ ጴጥ. 4፡10-11፤ 1ኛ ቆሮ. 12፡7፥ 21-26፥ 14፡26፤ ሮሜ 12፡4-5)። ስለዚህ ትኩረቱ የክርስቶስ አካል የሆነችው ቤተ ክርስቲያን ናት። ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን ይናገር ዘንድ ይረዳል። ሰዎች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ኢየሱስን እየመሰሉ እንዲያድጉ ይረዳል። ቤተ ክርስቲያን በውስጧ ያሉት ሰዎች እርስ በርሳቸውም ሆነ በዓለም ያሉትን ያገላሉ ዘንድ ይረዳቸዋል። የእግዚአብሔርን ጸጋ ለሌሎች የምናገለግልበት መንገድ ነው (1ኛ ጴጥ. 4፡10)። 

4 መንፈሳዊ ስጦታዎች በርካታ ዓይነት ናቸው። እያንዳንዱ ክርስቲያን ቢያንስ አንድ ስጦታ ማለትም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግልበት አንድ ችሎታ አለው (1ኛ ቆሮ. 12፡7፥1፥ 27፤ ሮሜ 12፡6)። ስጦታዎችን በሙሉ አጠቃሎ የያዘ ክርስቲያን የለም (ሮሜ 12፡4-5፤ 1ኛ ቆሮ. 12፡29-30)። 

በዚህ ክፍል የተዘረዘሩት ስጦታዎች ስጦታዎችን በሙሉ ያጠቃለሉ እንደሆነ አናውቅም። ሁሉም ዝርዝሮች የተላያዩ መሆናቸው የሚያሳየው፥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱት ስጦታዎች ናሙናዎች መሆናቸውንና ሌሎችም መንፈሳዊ ስጦታዎች ተብለው መጠቀስ የሚችሉ ነገሮች መኖራቸውንም ይመስላል። ስለዚህ በአዲስ ኪዳን ከተጠቀሱት ከአሥራ ሰባት ወይም ከአሥራ ስምንት የሚበልጡ መንፈሳዊ ስጦታዎች እንዳሉ ማመን የበለጠ ትክክለኛ ነው። 

5. መንፈሳዊ ስጦታ የአገልግሎት ቦታ አይደለም። አንድ ሰው የማስተማር ስጦታ ሳይኖረው ‹መምህር› ተብሎ ሊጠራ ይችላል። መንፈሳዊ ስጦታ የሚለካው አንድ ሰው በአገልግሎቱ በሚያስገኘው ፍሬ እንጂ ለሥራው በመቀጠሩ አይደለም። 

6. መንፈሳዊ ስጦታን በማግኘትና በመንፈሳዊ ሕይወት በመብሰል መካከል ቀጥተኛ ግንኙነት የለም። በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ያልበሰሉ ክርስቲያኖች ሁሉ እንኳ መንፈሳዊ ስጦታ አላቸው። አንድ ክርስቲያን መንፈሳዊ ስጦታዎችን በሚገባ እየተጠቀመ (ለምሳሌ በልሳን ሊናገር ይችላል) መንፈሳዊነት ግን ላይኖረው ይችላል። የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በመካከላቸው በነበረው መከፋፈልና የሥነ ምግባር ጉድለት የተነሣ ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮ. 3፡1-4 ቤተ ክርስቲያናቸውን ዓለማዊ ብሎ ጠርቷታል (1ኛ ቆሮ. 3፡5)። ነገር ግን መንፈሳዊ ስጦታዎች በሙሉ እንደነበራቸው ደግሞ ተናግሯል (1ኛ ቆሮ. 1፡7)። እነዚህ ክርስቲያኖች ስልሳናት እየተናገሩ በመንፈስ ቅዱስ ኃይልና ቁጥጥር ሥር ግን አይኖሩም ነበር። 

7. ማንም ሰው መንፈሳዊ ስጦታዎችን በሥራው ሊያገኛቸው ባይችልም ከእግዚአብሔር መጠየቅ እንደሚቻል ቀን ተጽፏል (1ኛ ቆሮ. 12፡31፤ 14፡1። መንፈሳዊ ስጦታዎቻችንን ቶል ብለን ልንተዋቸው ወይም በልምምድና በሥልጠና ልናነሣሣቸው እንደምንችል የሚያመለክቱ ማስረጃ ዎች አሉ። በአዲስ ኪዳን ውስጥ የእግዚአብሔር ሰዎች የሆኑ መሪዎች በመንፈስ ቅዱስ መሪነት መንፈሳዊ ስጦታዎችን ለሌሎች ክርስቲያኖች ለማስተላለፍ እንደቻሉ በበርካታ ስፍራዎች እንመለከታለን (1ኛ ጢሞ. 4፡14፤ 2ኛ ጢሞ. 16)። 

ጥያቄ፡- ከላይ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች በአጭሩ የተመለከትነው አሳብ የምታውቃቸው በርካታ ክርስቲያኖች ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ካላቸው አመለካከት ጋር የሚነጻጸሩት እንዴት ነው? 

በአዲስ ኪዳን ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች የሚነግሩን አራት ክፍሎች አሉ። ሮሜ. 12፡1-8፤ 1ኛ ቆሮ. 12-14፤ ኤፌ. 4፡7-13፤ 1ኛ ጴጥ. 4፡7-11። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች የሚያስተምራቸውን ነገሮች በግልጽ ለመረዳት እነዚህን ክፍሎች በጥንቃቄ መመርመር አለብን። በመጀመሪያ አግግርቹን ክፍሎች እናጠናና ቀጥሎ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ክሚያስተምሩት ክፍሎች ዋነኛው የሆነውን 1ኛ ቆሮ. 12-14 እናጠናለን።

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.