በመንፈስ ቅዱስ ለመሞላት የሚቀርቡ ቅድመ ሁኔታዎች

ጥያቄ፡- የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብብ። ኤፌ. 5፡18፤ 4፡30፤ 1ኛ ተሰ. 5፡19። ሀ) ስለ መንፈስ ቅዱስ የተሰጡ የተላያዩ ትእዛዛትን ዘርዝር። ለ) እያንዳንዱ ትእዛዝ የመንፈስ ቅዱስ ሙላትን እንዴት ሊነካ እንደሚችል አንዳንድ ምሳሌዎችን ጥቀሰ። 

ስለ መንፈስ ቅዱስ የተሰጠን የመጀመሪያ ትእዛዝ «በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ» የሚል ነው። ዋናው ጥያቄ በመንፈስ ቅዱስ እንዴት እንሞላለን? የሚል ነው። ከመንፈስ ቅዱስ ሙላት በምንጐድልበት ወቅት ያንን ሙላት ተመልሰን የምናገኘው እንዴት ነው? መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ ስላመሞላት ምንም ዓይነት ግልጽ ቀመር አይሰጠንም። ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ይሞላን ዘንድ መሟላት ያለባቸው ሁኔታዎች አሉ። መንፈስ ቅዱስ ይሞላብንና በሕይወታችን በአስደናቂ መንገዶች ይሠራ ዘንድ የሚያስችሉ አንዳንድ ሁኔታዎች ቀጥሎ ቀርበዋል። 

1. መንፈስ ቅዱስ የሚሞላን ለሕይወታችን ላለው መመሪያ ስንገዛና እራሳችንን ሕያው መሥዋዕት አድርገን ለእርሱ ልናቀርብ ነው (ሮሜ 12፡1)። 

መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን ዙፋን ላይ ነግሦ ምን እንደሚሆን እንወስን ዘንድ አይፈቅድም። ይልቁኑ ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ እንዲቆጣጠረው ለእርሱ እንድናስረክብ ይገፋፋናል። የራሳችንን ዕቅዶች፥ አሳቦችና ሕልሞች ለመፈጸም ያለንን መብት ላእርሱ መተው አለብን። ሕይወታችንን በሙሉ እግዚአብሔር ለእኛ ለወሰነው ነገር ማስገዛት አለብን። መንፈስ ቅዱስ የሚሞላን በዚያን ጊዜ ብቻ ነው። በሕይወታችን ማንኛውም ወቅት የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምንቃወም ከሆነ፥ እራሳችንን አሳልፎ ለመስጠት ወይም ለማስገዛት እምቢ የማላት ዝንባሌ ካለን በዚያን ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ መሞላታችን ይቀራል ማለት ነው። 

አዲስ ኪዳን በመንፈስ ቅዱስ እንሞላ ዘንድ መጾም እንዳለብን አይናገርም። ለመንፈስ ቅዱስ ሙላት መጸለይ እንዳለብን እንኳ አልተነገረንም። ይልቁኑ ሕይወታችንን ሕያው መሥዋዕት አድርገን ስናቀርብ በመንፈስ ቅዱስ ወዲያውኑ እንሞላለን። 

2. በሕይወታችን ከማናቸውም ነገሮች በላይ መንፈስ ቅዱስ እንዲቆጣጠረንና እንዲጠቀምብን መፈለግ አለብን። 

ስስታሞች ሆነን ለራሳችን ክብርን ብንፈልግ ወይም ከእግዚአብሔር ይልቅ ሌላ ነገርን ብንወድ መንፈስ ቅዱስ አይሞላብንም። እግዚአብሔር ከእኛ በኩል የሚፈልገው ሙሉ ለሙሉ የሆነ መሰጠትን እንጂ ከፊል መሰጠትን አይደለም። ከሁሉ በላይ የቅድሚያን ስፍራ ይፈልጋል። በሕይወታችን ድርሻ ያላቸው ሌሎች ነገሮች ቤተሰብ፥ ሥራ +ዕቅድ፥ ወዘተ… ከኋላ መምጣት አለባቸው። ኢየሱስ እንዳለው የእርሱ ለመሆን የምንገባው ሌሎችን ነገሮች ሁሉ «ስንጣላ» ነው (ማቴ. 10፡32-39)። ሕይወታችንን በራሳችን ለመቆጣጠር ከመሞከር ፍጹም ነፃ የማንሆንበት ጊዜ አይኖር ይሆናል። በመንፈሳዊ ሕይወት ሰብለለት ማደግ የሕይወታችንን ክፍሎች ለእግዚአብሔር በመተው ከዕለት ወደ ዕለት የበለጠ በእርሱ ቁጥጥር ሥር የመሆን ተቀዳሚ ችሎታ ነው። እግዚአብሔር ጸጋን የተሞላ አምላክ ስለሆነ የመንፈስ ቅዱስ ሙላትን ፍጹሞ እስክምንሆን ድረስ አይቆጥብብንም። 

ነገር ግን በሕይወታችን አስቀድሞ ባሳየን ነገሮች እየታዘዝን መኖር አለብን። መንፈስ ቅዱስ ያላስገዛንላትን የሕይወት ክፍላችንን ያሳየናል። ያንን የሕይወት ክፍላችንን እንድናስገዛለት ይረዳናል። ከዚያ በኋላ ማስገዛት ያለብንን ሌላ የሕይወት ክፍላችንን ያሳየናል። መንፈስ ቅዱስ በእርሱ ቁጥጥር ሥር እንዳልሆኑ የሚያሳየንን የሕይወታችንን ክፍሎች በማስገዛት እስከኖርን ድረስ እግዚአብሔር በቸርነቱ በመንፈስ ቅዱስ ሊሞላን ይችላል። 

የሕይወታችን የትኩረት አቅጣጫ «ከመንፈስ ቅዱስ ሙላት» ላይ ሊሆን አይገባም። ይህን ካደረግን ግን ምክንያቶቻችን ከራስ ወዳድነት የመነጨ ፍላጐት ይሆናል። ከዚህ ይልቅ በእግዚአብሔር ላይ በማተኮር ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የቀረበና የሞቀ ኅብረት እንዲኖረን መትጋት ያስፈልጋል። እግዚእብሔርን በምንፈልግበት ጊዜ ለእርሱ እንገኝለታለን። በእግዚአብሔር በተገኘን ጊዜ ቀንኙነታችን እውነተኛና ጥብቅ ይሆናል። ይህ በሚሆንበት ወቅት እኛ ምንም ዓይነት ጥረት መሻት ሳናደርግ መንፈስ ቅዱስ ይሞላናል። 

3. መንፈስ ቅዱስ እኛን እንዲሞላን ከተፈለገ ለእግዚአብሔርና ለፈቃዱ ታዝዘን መኖራችን ሌላው መሠረታዊ ሁኔታ ነው። ሕይወታችንን ከኃጢአት ሁሉ ማንጻት አለብን። 

በአዲስ ኪዳን ስለ መንፈስ ቅዱስ ከተሰጡን ትእዛዛት ሁለተኛው «መንፈስን አታሳዝኑ» (ኤፌ. 4፡30) የሚል ነው። [የመጀመሪያው ትእዛዝ በመንፈስ ተሞሉ] የሚል ነው። መንፈስ ቅዱስን የሚያሳዝነው ምንድን ነው? 

ጥያቄ፡– ኤፌ. 4፡29-32 አንብብ። ሀ) አታድርጉ የተባልናቸውን ነገሮች ዘርዝር። ለ) አድርጉ የተባሉትን ነገሮች ዘርዝር። 

በኤፌ.4 የሚገኙት እነዚህ ጥቅሶች ማድረግ ያለብንና የሌለብንን ነገሮች ይዘረዝራሉ። በአንድ በኩል ማድረግ የሌለብን ነገሮች እንዳሉ ተነግሮናል። ክፉ ንግግር ከአፋችን መውጣት እንዲወጣ መፍቀድ የለብንም። ከልባችን መራርነት፥ ቁጣ፥ ስድብ፥ ክፋትና ንዴት መወገድ አለባቸው። ጳውሎስ የሚናገረው ከሌሎች ጋር ያሉንን ግንኙነቶች የሚያጠፉ ነገሮች ሁሉ መወገድ እንዳለባቸው ነው። የተሳሳቱ የልብ ዝንባሌዎች ወደተሳሳቱ ንግግሮች ያመሩና የተበላሸ ቀንኙነት ይፈጥራሉ። በሌላ በኩል ከሌሎች ጋር ያላንን ግንኙነት የሚያመቻቹ ነገሮችን እንድናደርግ ታዝዘናል። በተለይ ቶርና ርኅሩኖች በመሆን ሌሎችን ማነጽ መቻል አለብን። በደል በሚደርስበት ጊዜ እንኳ እርስ በርስ ይቅር መባባል አለብን። 

በእነዚህ ሁለት የትእዛዛት ዝርዝሮች መካከል «የእግዚአብሔርን መንፈስ እታሳዝኑ» (ኤፌ.4፡30) የሚል ትእዛዝ እናገኛለን። መንፈስ ቅዱስን ማሳዘን ማለት ምን ማለት ነው? ከክፍሉ አጠቃላይ ይዘት አንጻር ስናየው ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር ያለንን ግንኙነት የሚያበላሽ የተሳሳተ ዝንባሌ በማንኛውም ጊዜ በልባችን ሲኖር ነው። በመሠረቱ ይህ በሕይወታችን ኃጢአት የሚኖርበት ማንኛውም ጊዜ ነው። ኃጢአት ከእግዚአብሔር እብ ጋር ያለንን ግንኙነት ያቋርጠዋል። ከእግዚአብሔር እብ ጋር ያለን ግንኙነታችን ሲበላሽ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያላን ግንኙነትም ይነካል። የመንፈስ ቅዱስ ሙላትና ኃይል ይታቀባል። ይህ ግን በዚህ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን መኖሩን ያቋርጣል ማለት አይደለም። ሆኖም ቀን ሙላቱንና ሕይወታችንን የመቆጣጠሩ ጉዳይ ይነካል» 

ብዙ ጊዜ ኃጢአታችን ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት ይረጋገጣል። ወደ ቁጣ፥ ትክክል ወዳልሆኑ ንግግሮች፥ ብሎም ወደተበላሸ ቀንኙነት የሚመራ ትዕቢት በሕይወታችን ካለ መንፈስ ቅዱስን አሳዝነናል ማለት ነው። ይህ አካሄድ በድል ሊሰበር የሚችለው እራሳችንን ትሑት በማድረግ ደግና ርኅሩህ ስንሆን እርስ በርስ ይቅር ስንባባልና አንዱ ሌላውን ሲያንጽ ነው። ከሌሎች ሁሉ ጋር በሰላም ለመኖር የምንችለውና ግንኙነታችን የሚስተካከላው ያኔ ብቻ ነው። 

ይህ ክፍል የሚያስተምረን የመንፈስ ቅዱስ ሙላት የሚወሰነው በሕይወታችን በምንኖረው ኑሮ መንፈስ ቅዱስን በማሳዘናችን ወይም ባለማሳዘናችን ላይ እንደሆነ ነው። ያልተናዘዝነው ኃጢአት በሕይወታችን ካለ መንፈስ ቅዱስን እያሳዘንነው ነው ማለት ነው። ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር ያለን ግንኙነት የሻከረ ከሆነ መንፈስ ቅዱስን እያሳዘንነው ነው ማለት ነው። ውጤቱም በሕይወታችን የመንፈስ ቅዱስን ኃይል ማጣት ይሆናል። የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ይመለስልን ዘንድ ኃጢአታችንን ለእግዚአብሔር መናዘዝና የለዴልናቸውን ሰዎች ይቅርታ መጠየቅ አለብን። ግንኙነታችንን ማስተካክል ይኖርብናል ማለት ነው። ከእግዚአብሔርና ከሌሎች ጋር ያለንን ግንኙነቶች እስካላስተካከልን ድረስ በመንፈስ ቅዱስ እንደገና ልንሞላ እንችልም። 

ጥያቄ፡- ልብህን መርምር። ሀ) ያልተናዘዝክው ኃጢአት ካለ መንፈስ ቅዱስ እንዲያሳይህ ጠይቀው። (መዝ[39]23-24) ለ) ከባለቤትህ, ከልጆችህ፥ ከቤተሰቦችህና በቤተክርስቲያን ካሉ ከሌሎች ሰዎች ጋር ስላለህ ግንኙነት አስብ። የተቋረጡ ወይም የተበላሹ ግንኙነቶች አሉህን? የመንፈስ ቅዱስ ኃይልን እንደገና ትለማመድ ዘንድ እነዚህን የተቋረጡ ወይም የተበላሹ ግንኙነቶች ለማስተካክል ምን ማድረግ አለብህ? 

የመንፈስ ቅዱስን ሥራ መቃወም፥ መገደብ፥ ወይም ጥያቄ ውስጥ መጣል የለብንም። መንፈስን ማጥፋት የለብንም (1ኛ ተሰ 5፡19)። ይህ መንፈስ ቅዱስ ከእኛ ጋር ስላለው ግንኙነት በአዲስ ኪዳን ውስጥ የተሰጠ ሦስተኛ ትእዛዝ ነው። 

ጥያቄ፡– 1ኛ ተሰ5፡12-22 አንብብ። ሀ) እንዴት መኖር እንዳለብን መመሪያ የሚሰጡንን በእነዚህ ቁጥሮች ያሉ ነገሮችን ዘርዝር። ለ) የመንፈስ ቅዱስን እሳት በማጥፋትና ትንቢቶችን በማጥፋት መካከል ያለው ግንኙነት ምን ይመስልሃል? 

በ1ኛ ተሰ. ጳውሎስ የመንፈስ ቅዱስን እሳት ያጠፋል ብሎ ያምን የነበረው ምን እንደሆነ ለማወቅ አስቸጋሪ ነው። «መንፈስን ማጥፋት» የሚለው ሐረግ ጳ ውሎስ የሚያመላክተው መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያንን ጥሎ እንዲሄድ የማስገደድን ጉዳይ ሳይሆን ክርስቲያኖችና ቤተ ከርስቲያን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያላቸውን ቅርብ ግንኙነት የማጣታቸውን ጉዳይ ነው። በአንድ ጎጆ ውስጥ መካከል ላይ የሚነደው እሳት ላቤቱ ሙቀትን እንደሚያመጣው ሁሉ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የሚደረግ ሕያው የሆነ የቅርብ ግንኙነት ለክርስቲያን ልብና ለቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ሙቀትን ያመጣል። 

ጳውሎስ የመንፈስ ቅዱስን እሳት ላለማጥፋት በሚያስጠነቅቅበት ጊዜ ስለ ሁለት ነገሮች ማመልከቱ ሳይሆን አይቀርም። እግዚአብሔርን በማያስከብር ማንኛውም መንገድ ስንኖር መንፈስን ማጥፋታችን ነው ማለቱ ሊሆን ይችላል። ተግተው የሚያገለግሉ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችን ሳናከብር ስንቀር፥ ሰነፎች ሆነን እግዚአብሔርን በሚያስከብር መንገድ ሳንሠራ ስንቀር፥ ወይም አንዳችን ሌላችንን መታገሥና መርዳት ሲያቅተን፥ ወዘተ… የመንፈስ ቅዱስ እሳት በመካከላችን እየቀነሰ እንዲሄድ በዚሁም ከቀጠልን እንዲሞት እናደርጋለን። በሌላ አነጋገር በሕይወታችን በማንኛውም ጊዜ ያልተናዘዝነው ኃጢአት ሲኖርና ለወንጌል የማይገባ ኑሮ ስንኖር በእግዚአብሔር ላይ ግልጽ የሆነ ያለ መታዘዝ እያሳየን በመሆኑ የመንፈስ ቅዱስ እሳትን ወይም ሙላቱን እናጣለን። ይህ ማለት ይኽኛው ትእዛዝ መንፈስን አታሳዝኑ ከሚለው ትእዛዝ ጋር ተመሳሳይ ነው ማለት ነው። 

«መንፈስን አታጥፉ» የሚለው ሐረግ ሊተረጎም የሚችልበት ሌላኛው ወመንገድ ጳውሎስ ወዲያውኑ ከሚጠቅሰው ትንቢት ጋር ማዛመድ ነው። የተሰሎንቁ ክርስቲያኖች በመካከላቸው የነበረውን የትንቢት ስጦታ ባልታወቀ ምክንያት አልተቀበሉትም ነበር። ይህ ስጦታ አገልግሎት ላይ እንዳይውል በማድረጋቸው የመንፈስ ቅዱስን ሥራ እየገደቡት ነበር። በውጤቱም መንፈስ ቅቶስ በመካከላቸው ያለመከላከል እንዳይሠራ በመገደብ፥ እነርሱንም እንሳይናገራቸው በመከልከል፥ ያለመታዘዝ ሕይወትን ይኖሩ ስለነበር የመንፈስ ቅዱስ እሳት ከመካክላቸው የመጥፋት አደጋ ነበረበት። ጳውሎስ የሚያስጠነቅቃቸው መንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊ ስጦታዎችን ለሰዎች እንዲሰጥና የተሰጣቸውም ሰዎች በነፃነት በቤተክርስቲያን ውስጥ እንዲጠቀሙበት መፍቀድ እንዳለባቸው ነው። መንፈስ ቅዱስ እንዲናገራቸው እራሳቸውን አዘጋጅተው መቆየት ነበረባቸው። 

የመንፈሳዊ ስጦታዎች አገልግሎት ላይ መዋል የሚገደብበት ማናቸውም ዝንባሌ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሊኖር የሚገባ ሞቅ ያለውን ግንኙነት የማጥፋት አደጋ ሊያመጣ ስለሚችል መጠንቀቅ ያስፈልጋል። እጅግ የተላመደው የዚህ ትእዛዝ አመዛኝ ተላምዶአዊው አተረጓጎም መንገድ ይህ ነው። 

ሆኖም ቀን ጳውሎስ ወደሌላው ጽንፍ በመሄድ ትንቢቶች ሁሉ ከመንፈስ ቅዱስ እንደሆኑ አድርገው እንዳይቀበሉ ፍላጎቱ ነበር። ሊፈትኑአቸው ይገባ ነበር። መልካም የሆነውን በመቀበል ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የማይሄደውንና ለቤተ ክርስቲያን ጥቅም የማይሆነውን ደግ መለየት ነበረባቸው። 

ካሪዝማቲክ ካልሆኑ አብያተ ክርስቲያናት የሆንን ሰዎች ላላ መንፈስ ቅዱስ አንዳንድ ስጦታዎች አስቀድሞ በነበሩን አሳቦች ምክንያት «የመንፈስን እሳት የማጥፉት» አዴጋ ያንዣብብብናል። አዎን መጠንቀቅ ያስፈልጋል። የሚሰጠውን ትምህርት መፈተንና እውነትን ከሐሰት ማበጠር ያስፈልጋል። ነገር ግን አንዳንድ ከሪዝማቲኮች ሚዛናዊ አመለካከት ባለመያዛቸው ምክንያት ብቻ ካሪዝማቲኮችን ሁሉ ማጣጣል የለብንም። ግልጽ በሆኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ምክንያት ካልሆነ በቀር በምንም ዓይነት ሁኔታ በየቤተ ክርስቲያናችን በመንፈስ ቅዱስ ሥራ ላይ ገደብ ማድረጋችን ሥራውን ማቀባችን ብቻ ሳይሆን የመንፈስ ቅዱስን እሳት አደጋ ላይ እንጥላለን። እሳቱ ከሞተ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንም ትሞታለች። ምክንያቱም ያለ እሳቱ ሕይወት የለም። ያለ ሕይወት ደግሞ ቤተ ክርስቲያን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጣት የሚፈጅባት ጊዜ አጭር ነው። መንፈስ ቅዱስ የቤተ ክርስቲያንን መቅረዝ ከሥፍራው ሊወስድ እንደሚችል አስጠንቅቋል። ይህም በእግዚአብሔር መንግሥት ያላት ሥፍራ ማለት ነው (ራእ. 2፡5)። 

ጥያቄ፡- ሀ) በአንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የመንፈስ ቅዱስን ሥራ በመገደባቸው መዘዝ የተነሣ ቤተ ክርስቲያንን አደጋ ላይ በመጣል መንፈሳዊ እሳትን ሊያጠፉ እንዳዘነበሉ ያየኸው እንዴት ነው? ለ) የቤተ ክርስቲያን መሪዎችም ሆኑ እባላት ይህ ሲፈጸም ሲያዩ ምን ማድረግ እለባቸው? ሐ) በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚመጡ ትምህርቶችን ሁሉ በቂ ማጣሪያ ሳያደርጉ መቀበል ምን ክፋት አለው? 

5. በመንፈስ ቅዱስ ላይ ሙሉ በሙሉ በመደገፍ የመመላለስ ሕይወት መኖር አለብን (ገላ5፡16)። 

በመንፈስ መመላላስ አለብን። ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ስላለን ግንኙነት የተሰጠ አራተኛ ትእዛዝ ይህ ነው። ቀደም እንዳሉት ትእዛዛት አታድርጉ የሚል ሳይሆን ይህ እንድናደርገው የሚጠበቅ ነገር ነው። በሕይወታችን ያለውን ኃጢአት ለማሸነፍ ኃይል የምናገኘው ከየት ነው? 

ጳውሎስ የሚናገረው ይህን ኃይል የምናገኘው በመንፈስ የምንኖር ወይም በመንፈስ የምንመላላስ እንደሆነ ነው። ሰው በራሱ ተፈጥሮአዊ ችሎታ በሕይወቱ ያለውን የኃጢአት ኃይል ለማሸነፍ አይችልም። ለጊዜው ለኃጢአት እምቢ ማለት ይችል ይሆናል፥ በመጨረሻ ግን አንኮታኩቶ ይጥላዋል። ነገር ግን ለሚሰጠን ኃይል መንፈስ ቅዱስን ተደግፈን ከተመላለስን እጅግ ጠንካራ የሆነውን ኃጢአትን ማሸነፍ እንችላለን። 

ብዙ ጊዜ ይህ የመደገፍ ወይም የመታመን ሕይወት ሁለት ደረጃዎች አሉት። በመጀመሪያ፥ ብዙ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር በሕይወታቸው እንደሚሠራ ቢያዩም እንኳ ደካማና ጎስቋላ ናቸው። ሁልጊዜ በኃጢአት የሚወድቁ ይመስላሉ። አገልግሎታቸውም ኃይል የሌለው ውጤትንም የማያስገኝ ነው። አንድ ቀን እግዚአብሔርን ባልተላመደ መንገድ ይገናኙታል። ሙሉ ለሙሉ እራሳቸውን ለእግዚአብሔር ለመስጠት ትልቅ ውሳኔ ያደርጋሉ። ፈቃዳቸውን ለእግዚአብሔር በማስገዛት እግዚእብሔር በሕይወታቸው በበላይነት እንዲነግሥ ይጠይቁታል። እግዚአብሔር የወደደውን ያደርግባቸው ዘንድ ሙሉ ለሙሉ እራሳቸውን ለእግዚአብሔር ለመስጠት ይወስናሉ። በዚህ አስቸጋሪ ልምምድ ሕይወታቸው በከፍተኛ ደረጃ ይለወጣል። 

ጥያቄ፡- ሀ) የሕይወትህን አቅጣጫ በሙሉ የቀየረ እንደዚህ ዓይነት ጠንካራ ልምምድ አሳልፈህ ታውቃለህን? መልስህ እዎ ከሆነ ስለ ልምምዱ በአጭሩ ግለጽ። መልስህ አሳልፌ አላውቅም ከሆነ በሕይወትህ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል መኖሩን፥ በየዕለቱም የምታደርገውን ድርጊት እየተቆጣጠረ ለመሆኑ በትጋት እራስህን መርምር። ይህ ኃይል በሕይወትህ ከሌለ እግዚአብሔር በታላቅ ኃይሉ እንዲገናኝህ ለመጸለይ በቂ ጊዜ ውሰድ። ለ) ከእግዚአብሔር ጋር ልዩ የሆነ ግንኙነት እንዳለው የተረጋገጠለት ሌላ ክርስቲያን አነጋግር። እንደዚህ ዓይነት አስቸጋሪ ሁኔታ ተለማምዶ ያውቅ እንደሆነ ጠይቀው። ተለማምዶ ከሆነና ሊገልጥልህ ፈቃደኛ ከሆነ ስለ ልምምዱ ይመስክርልህ። 

በሁለተኛ ደረጃ ፥ ሕይወትህን ለእግዚአብሔር ያለማቋረጥ በየዕለቱ ልትሰጥ ያስፈልጋል። በየዕለቱ ሕይወትህን ለእግዚአብሔር በማስረከብ ፈቃድህንና መንገድህን ለእርሱ አሳልፈህ ስጠው። ይህ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በሕይወትህ እንዲፈስስ ያደርጋል። 

በመንፈስ ቅዱስ መኖር ወይም መመላለስ ማለት ምን ማለት ነው? ይህ ለጥቂት ሰዎች ብቻ ግልጽ የሆነ ምሥጢራዊ መርህ አይደለም። ይልቁኑ መንፈስ ቅዱስ ወደ ክርስቲያን ሕይወት ሲመጣ ለክርስቲያን ኃይሉን ይሰጠዋል። ይህ ክርስቲያን ከሚታወቅ ኃጢአት እራሱን አንጽቶ ከሆነና ለእግዚአብሔር ፈቃድ እራሱን አስገዝቶ የሚኖር ከሆነ መንፈስ ቅዱስ ለዚያ ግለሰብ እዚአብሔርን ደስ በማሰኘት ለመኖር የሚያስፈልገውን ኃይል እንደሚሰጠው ልጽ ነው። የሚጠይቀን የተሰጠ ሕይወት፥ በእግዚአብሔር ላይ መደገፋችንን የምንገልጽበትን ሕይወት ብቻ ነው። አንድን ነገር በራሳችን ብርታት ለማድረግ ስንሞክር የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ወይም ሙላት አይኖረንም። ነገር ግን እግዚአብሔርን በሚያስከብር መንገድ አንድን ነገር ለመሥራት በመንፈስ ቅዱስ ብርታት ላይ መደገፍ እንዳለብን ስንነዘብ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ኑሮ የምንኖርበትን ኃይል ይሰጠናል። 

የገላትያ ክርስቲያኖች እንደ ብዙዎቻችን በሰይጣን ወጥመድ ውስጥ ወድቀው ነበር። ድነት (ደኅንነት) እንደሚያስፈልጋቸው ተገንዝበው ነበር። ኢየሱስን በማመናቸው የራሳቸውን ድነት (ደኅንነት) ለማግኘት እንደማይችሉ ያወቁ በመሆናቸው ለእነርሱ ሲል በሞተው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ተደግፈው ነበር። ስለሆነም ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ የእግዚአብሔርን ነፃ ስጦታ ለመቀበል ችለው ነበር። መንፈሳዊ ሕይወታቸውን የጀመሩት በእግዚአብሔር ስጦታና ችሮታ ላይ በመደገፍ ነበር። ነገር ግን ካመኑ በኋላ መልካም ክርስቲያኖች ለመሆን በአይሁድ ሕግጋት ውስጥ የሚገኙትን በርካታ አታድርግና አድርግ የሚሉ ትእዛዛትን መከተል እንዳለባቸው ገመቱ። የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች ሁሉ የሚያደርገው እግዚአብሔር መሆኑን ዘነጉ። ይልቁኑ ሕግጋትን በመጠበቅ መንፈሳዊ መስሎ ለመገኘት በራሳቸው ችሎታዎች ተደገፉ። በእዚእብሔር ላይ የመደገፍ ሕይወታቸውን በመተው በራሳቸው ላይ መደገፍ ጀመሩ። ይህን በማድረጋቸው ከመንፈስ ቅዱስ ጋር መኖራቸው ወይም በመንፈስ ቅዱስ መመራታቸው አከተመ። 

እኛም ዛሬ በቤተ ክርስቲያን የራሳችን አድርግና አታድርግ ሞልተውናል። አትጠጣ፥ አታጭስ፥ ወደ ፊልም ቤት እትሂድ፤ የሕፃንነት ጥምቀትህ ስለማይሠራ እንደገና ተጠመቅ፥ በቤተ ክርስቲያን ስብሰባዎች ሁሉና በምትዘምርበት ጊዜ እጅህን ወደ ላይ አንሣ። እነዚህ እንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ያሏቸው ጥቂት ልምምዶች ብቻ ናቸው። በራሳቸው ስሕተት አይደሉም፤ ነገር ግን እነዚህን ልምምዶች በራሳችን ብርታት የምንፈጽማቸው ይመስለ መንፈሳዊ መሆናችን ለማሳየት እንደ ማስረጃ አድርጎ ማቅረቡ ቀላል ነው። መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን ፈቃዱን እንዲሠራ በእርሱ ከመደገፍ ይልቅ ሁሉንም በራሳችን ብርታት ላማድረግ እንሞክራለን። በእርሱ ላይ የመደገፍ ሕይውትን ትተን በራሳችን ብቃት ወደ መተማመን ደረጃ እንመጣለን። በውጤቱም የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ከብዙዎቻችን ዘንድ ሳይገኝ ይቀራል። 

ጥያቄ፡- ዮሐ 5፡1-10 አንብብ። ሀ) እዚህ ቁጥሮች አንድ አማኝ ከኢየሱስ ጋር ስላለው ቀንኙነት ምን ይገልጻሉ? ለ) በኢየሱስ የማይኖሩ ምን ይደርስባቸዋል? ሐ) በኢየሱስ የሚኖሩ በሕይወታቸው የሚያገኙት ውጤት ምንድን ነው? 

በመንፈስ መመላለስ ላምናደርገው ነገር ሁሉ መሠረት የሆነ ዝንባሌ ነው። ዝንባሌያችን «እችላለሁ» ከሆነ በመንፈስ ቅዱስ እየተመላለስን አይደለም። ነገር ግን ዝንባሌያችን «እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ካልሆነ በስተቀር እርሱን ደስ በሚያሰኝ መንገድ ላደርገው አልችልም።» ከሆነ በመንፈስ እየተመላለስን ነው ማለት ነው። ኢየሱስ ይህንን ተደግፎ የመኖር ሕይወት «በቀንቶ መኖር» (ዮሐ5፡5) ብሎ ይጠራዋል። ግንኙነታችንን ከኢየሱስ ጋር ስናደርግ፥ ከእርሱ እንማርና ለእርሱ ፍላጎቶች እየታዘዝን ስንኖር ብቻ በእርሱ እየኖርን ነው ማለት እንችላለን። ለደኅንነታችን ብቻ ሳይሆን በእምነት ላምናደርገው ጉዞም በኢየሱስ ላይ በመደገፍ ስንኖር ሰኢየሱስ ላይ የማረፍ ግንኙነት ውስጥ እንገባለን። ውጤቱስ? ብዙ ፍሬ ማፍራት እንደሆነ ኢየሱስ ተናግሯል። በዮሔቱ ላይ ለክርስቲያኖች የተሰጠ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ አለ። በመንፈስ ካልኖሩ ወይም በኢየሱስ ካልኖሩ በስተቀር በኢየሱስ ላይ መደገፍን ይማሩ ዘንድ እግዚአብሔር አብ በሕመም በችግር ወይም በስቃይ ያስተምራቶዋል። 

ባለፈው ወር በበላነው እንጀራ ልንኖር አንችልም። እንደዚሁም ከዚህ ቀደም ከኢየሱስ ጋር ጥብቅ ግንኙነት ስላልነበረንና በመንፈስ ቅዱስ ስለተመላለስን ብቻ አሁን ያለውን ጉዞአችንን ልንቀጥል አንችልም። ከመንፈስ ቅዱስ ጋር መመላለስና ብርታቱን መቀበል የየዕለት ተግባር ወይም ሂደት ነው። በየዕለቱ መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን እንዳይሠራ የሚያድ ኃጢአት እንዳለን እግዚአብሔር እንዲያሳየን መጠየቅ አለብን። ለሁሉም ነገር የምንደገፈው በእርሱ እንደሆነ መናዘዝ አለብን። ቀኑን በሙሉ መንፈስ ቅዱስን ለመስማት፥ ከእርሱ ጋር ለመመላለስና እርሱን ለመታዘዝ ደግሞም የሚሰጠንን ኃይል ለመጠቀም በጥንቃቄ መሥራት አለብን። 

የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በሆንን ሰዎች ላይ የተደቀነ ልዩ አደጋዎ አለ። በመጀመሪያ እግዚአብሔርን ማገልገል ስንጀምር በራሳችን ኃይል ልናደርገው እንደማንችል እናውቀው ነበር። ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲረዳን ያለማቋረጥ እንጠይቅ ነበር። በእርሱ ላይ በመደገፍ እንኖር ነበር። እግዚአብሔር አገልግሎታችንን መባረክ ሲጀምር ግን ብዙ ጊዜ አንድ ነገር ይፈጸማል። እግዚአብሔር በረከቱን ፡ ያመጣበት ምክንያት እኛ እንደሆንን ማሰብ እንጀምራለን። ጥሩ ወንጌላውያን ወይም አስተማሪዎች ስለሆንን ነው ብለን ማሰብ እንጀምራለን። ውጤቶቹን ማምጣት የሚችል ችሎታ ያላን ይመስለናል። በእግዚአብሔር ላይ የመደገፍ ልምምዳችንን በማቆም በራሳችን ኃይል መሥራት እንጀምራለን። በአገልግሎት በቀጠልን ቁጥር እንደ ልማድ ይሆንብንና በእግዚአብሔር ላይ መታመናችንን እናቆማለን። ከጌታ ጋር በቆየን መጠን በሌሎች ፊት በአገልግሎት በቆየን መጠን በመንፈስ ቅዱስ ላይ ለመደገፍ የበለጠ ጠንቃቃ እየሆንን መሄድ አለብን። ጳውሎስ ያላሟቋረጥ «ሥጋዩን እቀስማለሁ» ያለው ለዚህ ነበር ሰኛ ቆሮ. 9፡27)። እግዚአብሔር በኃይል ከተጠቀመበት በኋላ በእግዚአብሔር መደገፉን አቁሞ በራሱ ላይ በመደገፍ በኃጢአት በመውደቅ ለእግዚአብሔር የሚጠቅም መሣሪያ መሆኑ እንዳይቀር ሰግቶ ነበር። 

ጥያቄ፡- ሀ) ይህ ችግር በብዙ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ላይ እንዴት እንደተፈጸመ ግለጽ። ላ) የመጨረሻ እስትንፋስህን እስክታጣ ድረስ በመንፈስ ቅዱስ ላይ እየተደገፍክ ትኖር ዘንድ እግዚአብሔር እንዲረዳህ ተማጸነው። 

እንድ ሰው እንዳለው የክርስቲያን ሕይወት ቁልፍ ጉዳይ መንፈስ ቅዱስን የበለጠ እናገኝ ዘንድ መሥራት አይደለም። ይልቁኑ ሕይወታችንን ለመንፈስ ቅዱስ በመስጠት እርሱ የበለጠ እንዲቆጣጠርን ማድረግ ነው። ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ባለን ግንኙነት ሊሠራቸው በሚችላቸው ወይም በሚሠራቸው ተአምራት ላይ እናተኩር። ይልቁኑ ሕይወታችንን ንጹሕና ቅዱስ በማድረግ ላይ እናተኩር። በእግዚአብሔር ላይ ተደግፈን ለመኖር ጥረት እናድርግ። ቀጥሎ በመንፈስ ቅዱስ መሞላት በራሱ ይከተላል። የመንፈስ ቅዱስ ፍሬና ስኬታማ አገልግሎት የሆኑት ውጤቶቹም ተስፋ ልናደርግ ከምንችላቸው ማናቸውም ተአምራት የበለጠ የሚያስደስቱ ዘላቂነት ያላቸው ይሆናሉ።

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

%d bloggers like this: