የእውነተኛና ሐሰተኛ ነቢያት ንጽጽር

ጥያቄ፡- ሀ) ኤር. 14፡13-16፤ 23፡9-40 አንብብ። ኤርምያስ ከሐሰተ ነቢያት ጋር ያሳለፈውን ችግር ግለጽ። ለ) ዘዳ 13፡3-5፤ 18፡17-22 አንብብ። ) አንድ ሐሰተኛ ነቢይ ከእውነተኛ ነቢይ የሚለይባቸው መንገዶች ምንድን ናቸው? 2) ሐሰተኛ ነቢይ የሚቀጣው በምን ነበር? 

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የእግዚአብሔርን ቃል ለሕዝብ የሚናገሩ እውነተኛ ነቢያት እንደነበሩ ሁሉ እውነተኛ ነቢያትን በመቃወም የሚሠሩ ሐሰተኛ ነቢያትም ነበሩ። የመጀመሪያዎቹ የእግዚአብሔርን ቃል ይናገሩ የነበሩ ሲሆን ሌሎች ደግሞ በእግዚአብሔር ስም ቢናገሩም እንኳ የሚናገሩት የእግዚአብሔርን ቃል አልነበረም። እውነተኞች ከእግዚአብሔር ስለነበሩ የእግዚአብሔር ሰዎች ሊሰሟቸው ይገባ ነበር። ሐሰተኞቹ ግን በሰይጣን ኃይል ቁጥጥር ሥር ሆነው የሚናገሩ ወይም እራሳቸው የፈጠሩትን ነገር የሚናገሩ ነበሩ። እነዚህን ማንም ሊቀበላቸው አይገባም ነበር። እግዚአብሔር ሐሰተኛ ነቢያትን እጅግ ከመጥላቱ የተነሣ ማንኛውም ነቢይ ሐሰተኛነቱ በሚረጋገጥበት ጊዜ መገደል ነበረበት። 

እስራኤላውያን አንድ ነቢይ፥ እውነተኛ ወይም ሐሰተኛ መሆኑን የሚያውቁት እንዴት ነበር? መጽሐፍ ቅዱስ ሐሰተኛ ነቢያት የሚለዩባቸውን የሚከተሉትን ባሕርያት ይሰጣል። 

1) ሐሰተኛ ነቢያት የእግዚአብሔርን ቃል በቀጥታ የሚቃወም መልእክቶችን ያመጣሉ። እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን በሚናገርበት ወቅት አንድ ነቢይ ወደ እናንተ ቢመጣና ከሙሴ ሕግጋት ጋር በቀጥታ የሚቃረን መልእክት ቢያመጣላችሁ ሐሰተኛ ነቢይ መሆኑን አውቃችሁ ልትገድሉት ይገባል ያላቸው ለዚህ ነበር። ነቢያት ያመጡትን መልእክት የምንመዝንበት የመጨረሻው ሥልጣን ያለው መጽሐፍ ቅዱስ የመሆኑን እውነታ ይህ እንደገና ያስረግጣል። መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ከሚያስተምራቸው ትምህርቶች ከእኛ አተረጓጐም ሳይሆን) አብሮ የማይሄድ ማንኛውም መላእክት ሐሰተኛ ነውና ሊኮነን ይገባዋል። 

2) ሐሰተኛ ነቢያት የተናገሩት መልእክት ልክ እንደተናገሩት አይፈጸምም። እግዚአብሔር የወደፊቱንም የሚያውቅ አምላክ ነው። ስለዚህ ወደፊት የሚፈጸመውን ነገር ለሕዝቡ ማሳወቅ እያስቸግረውም። ስለዚህ እንድ ሰው የወደፊቱን ጉዳይ በዝርዝር ቢያመለክትና ባመለከተው መንገድ ነገሮች ባይከናወኑ ሰውዬው ያመጣው መልእክት የእግዚአብሔር ቃል (ፈቃድ) አልነበረም ማለት ነው። ይህንንም ያለማቋረጥ ካደረገ እርሱ ሐሰተኛ ነቢይ ነው። ከዚህ ቀደም «ጌታ ኢየሱስ በዚህና በዚህ ቀን በዚህና በዚህ ስፍራ ይመጣል» ብለው የተናገሩ ብዙ ሰዎች ነበሩ። ብዙዎች ስላመኗቸው ሥራቸውን ሁሉ ትተው የኢየሱስን መመለስ ተጠባበቁ። ነገር ግን ቀኑ ቢደርስም እንኳ ኢየሱስ እልተመለሰም። ስለዚህ ሰው የምንረዳው ነገር ምንድን ነው? እግዚአብሔር ስለማይሳሳት ከእግዚአብሔር አለመሆኑን ነው። እውነተኛ ነቢያት የሚናገሩት መልእክት በሙሉ በትክክል ይፈጸማል። (ማስታወሻ፡— አንዳንዶች እግዚአብሔር ስለ ወደፊት የሚናገረው ነገር በሙሉ ትክክል ቢሆንም መልእክቱን የሚቀበላው ነቢይ ያለአግባብ ሊረጻውና ያለ አግባብ ሊተገብረው ይችላል የሚሉ አሉ፡፡) 

የአንድን ነቢይ መልእክት ለመመዘን መፈጸሙን ብቻ ማየት በቂ አይደለም። ሰይጣን እንደ ጠንቋዮች ያሉ ተከታዮቹን ስለ ወደፊቱ ጉዳይ እንዲናገሩ ሊረዳቸው ይችላል። የሚናገሩትም መልእክት ብዙ ጊዜ ትክክል ሊሆን ይችላል። ነገር ግን የሚናገሩአቸውን መልእክት ትክክለኛነት ላማረጋገጥ ለረጅም ጊዜ ብንከታተል ከትንቢቶቻቸው ብዙዎቹ አይፈጸሙም። እነዚህ የሐሰተኛ ነቢያት ባሕርያት አብዛኛው እርስ በርስ የተያያዙ ስለሆኑ አንድ ትንቢት መፈጸሙን ለማረጋገጥ አንዱን ዘርፍ ብቻ መመልክት የለብንም በቂ አይደለም። 

3) የሐሰተኛ ነቢያት ባሕርይ ብዙ ጊዜ መልካም አይደለም። አንድ ሰው ነቢይ ነኝ እያላ የእግዚአብሔርን ቅድስና በማያንፀባርቅ መንገድ የሚኖር ከሆነ እውነተኛ ነቢይ መሆኑን ወይም መሆኗን መጠራጠር ተገቢ ነው። አውነተኛ ነቢያት በትሕትና ይመላለሳሉ። አገልግሎታቸውም በሌሎች ሕይወት ውስጥ ትሕትናን ይፈጥራል። 

4) የሐሰተኛ ነቢያት አገልግሎት ለእግዚአብሔር ክብርን አያመጣም። እንድ ሰው ነቢይ ነኝ እያለ ለራሱ ጥቅም፥ ሀብት፥ ክብር ወይም ኃይል ለማግኘት ከሠራ ወይም የአገልግሎቱ ክብር ወደ እግዚአብሔር ሳይሆን ወደ ራሱ የሚሄድ ከሆነ ሰውዩውን መጠራጠር ተገቢ ነው። እግዚአብሔር «ክብሬን ለሌላ አልሰጥም» (ኢሳ. 42፡8) ብሏል። ስለዚህ ከእግዚአብሔር ያልሆነ ማንኛውም ትንቢት ክብርን ለሰው እንጂ ለእግዚአብሔር አያመጣም። እውነተኛ ነቢይ ለኢየሱስ ክብርን ያመጣል፤ ሌሎችም ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲያከብሩ ያደርጋል። 

5) የእውነተኛ ነቢይ ትንቢት የመንፈስ ቅዱስ ፍሬን ያፈራል። በክርስቶስ አካል ውስጥ መክፋፈልን አያመጣም። 

ጥያቄ፡- እነዚህ መመሪያዎች አንድ ሰባኪን ወይም ነቢይን ለመመዘን የሚጠቅሙት እንዴት ነው? 

ጥያቄ፡- 1ኛ ቆሮ. 14፡26-40 አንብብ። ትንቢት ለመናገር የሚጠቅሙ የተላያዩ መመሪያዎችን ዘርዝር።

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.