በኢየሱስ ሕይወት ውስጥ አንዱና አስደናቂው ነገር ፍጹም ሰው በመሆኑ ሁሉም ሰብአዊ ስሜቶች ነበሩት። አብዛኛዎቹ አማኞች ስለ ኢየሱስ ስሜቶች መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ሁሉ ልብ አይሉትም። ስለ ኢየሱስ ስሜታዊ ሕይወት ማጥናት ያለብን ለምንድን ነው? በመጀመሪያ፥ ኢየሱስን ይሰሙት የነበሩትን ልዩ ልዩ ስሜቶችን ማጥናት እውነተኛውን ሰብአዊነቱን በጥልቀት ተገንዝበን እንድናመሰግነው ይረዳናል። እርሱ እንደ እኛው ሙሉ በሙሉ ሰብአዊነት ከሰብአዊ ስሜቶች ጋር ነበሩት። ሁለተኛ፥ የኢየሱስን ስሜታዊ ሕይወት ማጥናት የእኛ ስሜታዊ ሕይወት እንዴት መሆን እንደሚገባው ለመገንዘብ ይረዳናል። ኢየሱስ ፍጹም ሰው ሆኖ የኖረ ብቸኛው ሰው ነበር። የእርሱ ስሜቶች እንዴት እንደነበረ ተገንዝበን ቢሆን ኖሮ፥ የእኛ ስሜታዊ ሕይወት እንዴት መሆን እንዳለበት መረዳት እንችል ነበር። ስለዚህ በሕይወታችን ልክ እንደ ኢየሱስ መሆን ከፈለግን እና በሕይወታችን እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት ካለብን፥ ኢየሱስ የነበረውን ፍጹማዊ ስሜት እንዲኖረን መጣር አለብን።
ምሕረት
ጥያቄ- ማቴዎስ 9:6፤ 5፡32፤ 20።4፤ ማርቆስ 1፡4፤ ሉቃስ 7፡13 አንብቡ። ኢየሱስ ዕለራራላቸው ሰዎችና ለለነበሩት ሁኔታ ዝርዝር ጻፉ። የእያንዳንዳቸውን ችግር ለማሟላት ኢየሱስ ምን እንዳደረገ ልምራችሁ በዝርዝሩ ውስጥ ያዙ።
መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ስለተሰማው ስሜት ብዙ ጊዜ የሚነግረን ምሕረቱንና ርኅራኄውን ነው። ስለ ኢየሱስ ምሕረትና ርኅራኄ የሚገልጹ ቃላት የሚያመለክቱት ለሰዎች ውጫዊ (አካላዊ) ችግር ውጤት አዘል ውስጣዊ የአዘኔታና ጥልቅ የኃላፊነት ስሜትን ነው። ኢየሱስ የሰዎችን ሥጋዊና መንፈሳዊ ችግር በተመለከተ ጊዜ፥ የተሰማው ይኸው ነበር። በማቴዎስ 9፡36 ላይ የሰዎችን አጠቃላይ የማኅበራዊ ሁኔታ በተመለከተ ጊዜ ራራ። የተመለከታቸውም ሰዎች ለሥጋዊ ሕይወታቸው የሚፈልጉት ነገር ነበረ፤ በየአካባቢአቸው በሚገኙ ሌሎች ሰዎች ተጨቁነዋል፥ በመንፈሳዊ ነገር ጠፍተዋል፥ እንደዚሁም የሚረዳቸውና የሚንከባከቧቸው መሪዎች አልነበሯቸውም።
እርሱም ይህን እንደ ተመለከተ ለሕዝቡ ችግርና ፍላጎት እገዛ የሚያደርጉ ሰዎችን እግዚአብሔር ይልክ ዘንድ፥ ደቀ መዛሙርቱ እንዲጸልዩ አላሰባቸው። ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ሕዝቡን እንዲያገለግሉ ላካቸው። በማቴዎስ 5፡32 ከሩቅ ስፍራ መጥተው ቃሉን ሲሰሙ ለነበሩና ተርበው ለነበሩ ሰዎች መራራቱን ይነግረናል። እርሱም ያንን ሁሉ ሕዝብ መገበ። እንደዚሁም በማቴዎስ 20፡34 ውስጥ ሁለት ዓይነ ሥውራን ጌታ እንዲፈውሳቸው በሁ ጊዜ፥ እንደ ራራላቸው ተጽፎአል። እርሱም በርኅራኄው ፈውሷቸዋል። በእነዚህ ሁኔታዎች ሁሉ የምንገነዘው ኢየሱስ ስለ እነርሱ ተሰምቶት ፍላጎታቸውን ለሟሟላት እንደ ችግራቸው ሁኔታ እንደ ረዳቸው ነው። በማርቆስ 1፡4ህ ላይ አንድ ለምፃም ሰው ኢየሱስ እንዲፈውሰው ለመነው። ኢየሱስም ራራለትና ፈወሰው። በመጨረሻም በሉቃስ 7፡13 አንድ ልጇ ለሞተባት መበለት መራራቱ ተጽፎአል። ጌታም ራርቶ የሞተውን ልጅዋን አስነሥቶላታል።
ጥያቄ፡- ሀ) በጎረቤቶቻችሁና በከተሞቻችሁ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ችግር ምንድን ነው? በአጭሩ ሦስት መሠረታዊ ችግሮቻቸውን ጻፉ። ለ) ስለ እነርሱ ምን ይሰማችኋል? ሐ) በ ጻፋችኋቸው ችግሮች በእያንዳንዳቸው አቅጣጫ እናንተ ልትረዷቸው የምትችሉባቸውን ሁለት ሁለት መንገዶች ጻፉ።
በአካባቢአችን ስላሉ ሰዎች ችግርም ሆነ ፍላጎት ቀዝቃዛ ስሜት ይኖረን ይሆናል። ለምሳሌም ያህል፥ ብዙ ጊዜ ድሆችን፥ በሽተኞችን አካላቸው የጎደለ ሰዎችን ወይም የሚወዷቸውን ዘመዶቻቸውን በሞት ያጡ ሰዎችን እንደዚሁም በራሳቸው ኅብረተሰብ የተጨቆኑ ሰዎችን እንመለከት ይሆናል። የእነዚህን ሰዎች ችግር ሁልጊዜ ማየታችን አንዳንድ ጊዜ ለእነርሱ የሚኖረንን ርኅራኄ ያጠፋዋል። ኢየሱስ ግን በዚህ ሁኔታ የተቸገሩትን ሰዎች እንደየችግራቸው ለይቶ በመቀበል በጥልቅ ምሕረትና ርኅራኄ ተመልክቶአቸዋል። ለችግሮቻቸውም መፍትሄውን ሰጥቶአቸዋል። የኢየሱስም ደቀ መዛሙርት ልክ እንደ እርሱ ለመኖር በመፈለግ ችግረኞችን ሰሚመለከቱበት ጊዜ ርኅራኄ ሳይርቃቸው ለችግሮቻቸው መፍትሄ በመስጠት የእርሱን ዱካ መከተል ይገባቸዋል።
ፍቅር
ጥያቄ፡- ዮሐንስ 3፡1 እና ማርቆስ 10፡21 አንብቡ። ሀ) በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ እንደተጻፈው ኢየሱስ ምን ዓይነት ስሜት ነበር ያላየው? ለ) የእያንዳንዳቸው ፍላጎት ምን ነበር? ሐ) ኢየሱስ ለፍላጎታቸው እንዴት ያለ መፍትሄዎችን ለጠ?
ከኢየሱስ የርኅራኄ ስሜት ጋር የቅርብ ትስስር ያለው የፍቅር ስሜቱ ነው። ከርኅራኄው ለየት ባለ መልኩ የኢየሱስ የፍቅር ስሜት የሚገለጸው አሳሳቢ ችግር ላልነበረባቸው ሰዎች ነበር። ለምሳሌም ያህል፥ በማርቆስ 10፡21 ኢየሱስ ያንን ወጣት እንደ ወደደው ይገልጻል። ይህ ወጣት ሕይወቱ ፍጹም እንደሆነ ያስብ ነበር። ማርቆስ 10፡22 ይህ ሰው ሀብታም እንደ ነበረ ያስረዳል። ሉቃስ 18፡18 ደግሞ ወጣቱ ገዢ እንደነበርና አንድ ዓይነት ሥልጣን እንደ ነበረው ያወሳል። ማቴዎስ 19፡20 ደግሞ ወጣት እንደ ነበረ ይናገራል። ታዲያ ይህ ወጣት የብሉይ ኪዳን ሕጎችን ሁሉ የጠበቀ ይመስለው ነበር (ማርቆስ 10፡20)፡፡ ይህ ሰው በዓለም ምርጥ የተባለ ነገር ሁሉ የነበረውና ታዋቂ ሰው ነበር። ሀብት፥ ሥልጣን፥ ጉብዝና ያለውና የሞራል ሕይወቱም ጥሩ የሆነ ነበር። ይህ ሰው የሚቸግረው ነገር አልነበረም። ነገር ግን ኢየሱስ በእርግጥ ምን እንደሚያስፈልገው ደህና አድርጎ ያውቅ ነበር። ያም በነበረው ሁሉ ማለትም ባሀብት፥ በሥልጣን፥ በወጣትነት አቋምና በተሟላ ኑሮ መታበዩን ትቶ ራሱን አሳልፎ ለኢየሱስ እንክብካቤ እንዲሰጥና በእርሱ እንዲታመን ነበር። ሰውዬው ምን እንደሚያስፈልገው ባያስተውልም፥ ኢየሱስ ግን ምን እንደሚያስፈልገው አውቆአል። እናም ወደደው። በተመሳሳይ ሁኔታ በዮሐንስ 13፡1 ላይ እንደተጻፈው ከጌታ ራት ቀደም ብሎ ደቀ መዛሙርቱ ለእርስ በርሳቸው አገልጋዮች መሆን እጅግ እንደሚያስፈልጋቸው አልተገነዘቡም ነበር። ስለ ሥልጣናቸው አስፈላጊነትና ማን ከማን እንደሚበልጥ ይከራከሩ ነበር (ሉቃስ 22፡24)። ፍላጎታቸውን ስለማያውቁ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች አይመስሉም ነበር፥ እነርሱ ባያዩም ኢየሱስ ፍላጎታቸውን አይቶ ነበር። እናም ወደዳቸው።
ርኅራኄን በተመለከተ እንዳደረገው ሁሉ ኢየሱስ ፍቅር በተሰማው ወቅት ወዲያው ያላሰበውን ይፈጽም ነበር። ፍላጎታቸውን ለማሟላት አስፈላጊውን አድርጓል። ያ ሀብታም ጎበዝ በራሱና በሀብቱ ላይ የነበረውን ትምክህት በመረዳቱ ሊገዳደረው እንደሚገባ ያውቃል። ስለዚህ ሀብቱን ሁሉ ትቶ፥ በእርሱ እንዲታመንና ለዕለት ምግቡም እርሱን ተስፋ እንዲያደርግ አላሰበው። ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አገልጋይነት ውስጥ ፍቅሩን አይተው ከግለኝነት በመላቀቅ በእርስ በርስ ፍቅር አንዱ ሌላውን እንዲያገለግል አሳስቦአቸዋል።
ጥያቄ፡- ሀ) የተለየ ችግር ወይም ፍላጎት ያላቸው ስለማይመስሏችሁ አንዳንድ ሰዎች አስቡና የሁለት ወይም የሦስት ሰዎችን ስም በማስታወሻ ደብተርቻችሁ ላይ ጻፉ። ለ) እነዚህ ሰዎች ምን እውነተኛ ፍላጎቶች አሏቸው? ሐ) እነዚህን ችግሮች ቀርባችሁ በማቃለልና መፍትሄ በመስጠት የክርስቶስ ምሳሌነታችሁንና ፍቅራችሁን እንዴት ትገልጻላችሁ?
አንዳንድ ጊዜ የምናውቃቸው ሰዎች ራሳቸውን በጣም ከፍ አድርገው ስለሚመለከቱ፥ የሚጎድላቸው ነገር መኖሩ አይከሰትላቸውም። እንዲህ ያሉት ሰዎች ኃጢአታቸው በበጎ ሥራቸው ይቅር ሊባል እንደማይችል ያልተገነዘቡ በጣም ሃይማኖተኛች ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ። ኢየሱስ ብቻ ሊያድናቸው እንደሚችል ያላስተዋሉ ሊሆኑ ይችላሉ። የሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ የተሟላላቸው በጣም ሀብታም ሰዎችም ይሆኑ ይሆናል። ያላቸው ቁሳዊ ንብረታቸው ደስታ እንደማይሰጣቸው አይረዱም። ወይም ጤነኞችና ጠንካራ ሰዎች ጤናማ የሆኑ ቤተሰቦች ያሏቸው ሆነው፥ ይህ ሙሉ ጤንነት ድንገት ቶሉ እንደሚከዳ ላያስተውሉ ይችላሉ። እነዚህን ሰዎች ልንወዳቸውና ወዳጆቻችን ልናደርጋቸው ይገባናል። እግዚአብሔር ዕድል በሚሰጠን ጊዘ ክርስቶስ ለእነዚህ ሰዎች ሊያደርግላቸው ስለሚችለው ነገርና በምን ረገድ እንደሚያስፈልጋቸው አብረናቸው ልንወያይ ደግሞም የችግራቸው ተካፋይ ልንሆን ይገባናል።
ቁጣ
ጥያቄ፡ ማርቆስ 3፡51 10፡14፤ ዮሐንስ 11፡33፥ 38 አንብቡ። ሀ) በእነዚህ ክፍለ ምንባቦች ውስጥ ኢየሱስን የተሰማው ስሜት ምን ነበር? ላ) ኢየሱስን ይህ ስሜት እንዲሰማው ያደረጉ ሁኔታዎች ምን ነበሩ? ስለ እያንዳንዱ ሁኔታ ጻፉ።
ኢየሱስ በአንዳንድ ሁኔታ ይቆጣና ይገሥጽ እንደነበረ ሰዎች በሚሰሙበት ጊዜ ይገረማሉ። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ቁጣ ኃጢአት ነው (ኤፌሶን 4፡30) ነገር ግን ኃጢአት ያልሆነ የጽድቅ ቁጣ መኖሩ ግልጽ ሊሆን ይገባል (ኤፌሶን 4፡26)። ኢየሱስን ይሰማው የነበረው ይህን የመሰለ የጽድቅ ቁጣ ነበር። ኢየሱስ ይቆጣ የነበረው መች ነበር? በማርቆስ 10፡14 ውስጥ እንደተጻፈው ደቀ መዛሙርቱ ሕፃናት ወደ እርሱ እንዳይመጡ በከለከሏቸው ጊዜ ኢየሱስ ተቆጥቷል። በማርቆስ 3፡5 ውስጥ ደግሞ የሃይማኖት መሪዎች እጁ ከሰለለው ሰው ፈውስ ይልቅ የሰንበትን ቀን ስለመጠበቅ ሕጋቸው ትርጉም ትኩረት በመስጠታቸው ኢየሱስ ተቆጥቷል። በተለይ የሃይማኖታቸውን ሁኔታ ከፍ ለማድረግ በእግዚአብሔር ቃል አላግባብ በመጠቀማቸው ተቆጥቷል። ስለ ሥልጣናቸው ያስቡ ስለነበር ስለ ሌሎች ሰዎች ጥቅም ግድም አልነበራቸው። በኩራታቸው የእግዚአብሔርን ቃል አላግባብ በመጠቀማቸውና ስለ ሌሎች ሰዎች አለማሰባቸው ኢየሱስን አስቆጥቶታል።
ጥያቄ፡- ሀ) ወደ ኢየሱስ በሚመጡ ሰዎች ላይ ስር የሚዘጋ ሰው መቼ ነው ያያችሁት? እንዲህ ያለውን ሁኔታ ስታዩ ምን ተሰማችሁ? ለ) እናንተም ራሳችሁ ብትሆኑ ወደ ኢየሱስ በሚመጡ ሰዎች ላይ መች በር እንደ ዘጋችሁ አስቡና ስለ ሁኔታው በማስታወሻ ደብተራችሁ ላይ ጻፉ። ሐ) ስለ ሃይማኖታችሁ ክንዋኔዎች በሕይወታችሁ ውስጥ ለመታበይ የተፈተናችሁበት ሁኔታ አለ? በማስታወሻ ደብተራችሁ ውስጥ ጻፉት። መ) አንድ የተቸገረ ሰውን ችግር ከማቃለል ይልቅ የራሳችሁን ጉዳይ አብልጣችሁ የተመለከታችሁበትን ጊዜ አስቡ። ይህን ጊዜ በማስታወሻ ደብተራችሁ ላይ ጻፉት። ሠ) ይህን ሁሉ ኃጢአታችሁን ለጌታ ለመናዘዝ ጊዜ ይኑራችሁ።
በዮሐንስ 11 ላይ ኢየሱስ ሁለት ጊዜ እንደ ተቆጣ ተነግሮናል። በቁጥር 33 በአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ማርያምና አይሁዶች ሲያለቅሱ ባየ ጊዜ «በመንፈሱ አዝኖ ታወከ» ይላል። ስለዚህ የተጻፈው የግሪክ ቃል በጣም ጠንከር ያለ ቃል ሲሆን የሚለውም፥ ተቆጣ ከዚያም በጥልቅ አዘነ ማለት ነው። ይህ ከኀዘን በላይ ነው። ከቁጣ ጋር የተደባለቀ ኀዘን ነው። በቁጥር 38 ውስጥ ከመቃብሩ ውጭ ቁሞ ሳለ፥ የአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው «ኢየሱስ እንደ ገና አዘነ» ይላል። የግሪኩ ቃል በቁጥር 33 ውስጥ እንዳለው ነው። እንደገና ኢየሱስ ተቆጣ እናም አዘነ ይላል። ኢየሱስ ከአልዓዛር መቃብር ውጭ ሆኖ የሰዎችን ኅዘን በመካፈል ላይ እያለ በምን ምክንያት ተቆጣ? ኢየሱስ በሁለት ምክንያቶች የተቆጣ ይመስላል። በመጀመሪያ፥ ያዘነውና የተቆጣው በሞት በራሱ ላይ ነበር። እንዲሁም ኃጢአት ወደ ዓለም መጥቶ ሞትንም በዓለም ላይ በማስከተሉ ተቆጥቷል፥ ደግሞም አዝኖአል። ኀዘንን ባስከተለው በሞት ላይ ተቆጥቶአል። ሁለተኛ፥ ሞት ባስከተለው ተስፋ- ቢስነት ላይ ኢየሱስ ተቆጥቷል። በኀዘን ላይ የነበሩት ብዙዎቹ አይሁዶች ተስፋ እንደሌላቸው ሰዎች ያዝኑ ነበር (1ኛ ተሰሎንቄ 4፡13)። ሞት አሰቃቂ ነገር ነው፥ ን የትንሣኤ ዋስትና ላላቸው ደግሞ ሞት መለያየት ብቻ ነው። በምንም ሁኔታ ወደ ተስፋ መቁረጥ ሊያደርሰን እይገባም። ኢየሱስ በዙሪያው በነበሩ እምነት ባልነበራቸው አይሁዶች ላይ ተቆጣ፥ ደግሞም አዘነ።
ጥያቄ- ሀ) የምትወዱት ሰው በሚሞትባችሁ ጊዜ ምን ይሰማችኋል? ለ) በአካባቢአችሁ የሚኖሩ የማያምኑ አብዛኛዎቹ ሰዎችስ የሚወዱት ሰው ሲሞትባቸው ምን ይሰማቸዋል?
በእርግጥ አንድ አማኝ የሆነ ሰው በሚሞትበት ጊዜ ማዘን ስሕተት አይደለም። ምንም እንኳን ሟቹ አማኝ ቢሆንም፥ ያ ምእመን ስለተለየ ኀዘን ይሰማናል። ኀዘናችን ብስጭት የተቀላቀለው ቢሆን እንደ ስሕተት ሊቆጠር አይችልም። እኛን ሊያስቆጣን ወይም ሊያበሳጨን የሚችለው ኃጢአት ወደ ዓለም መጥቶ ሞትን በማስከተሉ ነው። ስለሆነም ሞት መለያየትን ስለሚያመጣብን ልንቆጣ እንችላለን። ሆኖም ተስፋ እንደሌላቸው የማያምኑ ሰዎች ልናዝን አይገባም። እኛ የትንሣኤ ዋስትና ያለን አማኞች ኀዘናችንን ከተስፋ ጋር አድርገን በማሳየት እምነታችንን መግለጽ አለብን።
ኢየሱስ በመቆጣት ሙሉ በሙሉ ሰው መሆኑን ገለጸ። ነገር ግን ሰው በሚበድለው ጊዜ በፍጹም አይቆጣም ነበር። አንድ ሰው ሲያስቸግረው በፍጹም አይቆጣም ነበር። እርሱ ይቆጣ የነበረው ሰዎች ወደ እርሱ ሲመጡ ሌሎች እንዳይመጡ ሲያደርጓቸው ነው። ይቆጣ የነበረው በሃይማኖት የሚታበዩትንና ስለ ሌሎች ሰዎች ችግር ግድ ያልነበራቸውን ሲመለከት ነው። በኃጢአትና የኃጢአት ውጤት በሆነው በሞት ላይ ይቆጣ ነበር። እኛም ሌሎች በሚያስቸግሩን ጊዜ መቆጣት የለብንም። ነገር ግን በኃጢአት ላይና ወደ ኢየሱስ የሚመጡትን በሚያሰናክሉ ሰዎች እንደዚሁም እርዳታ ለሚሹ ሰዎች ርኅራኄ የሌላቸውን ግድየለሾች ስንመለከት ልንቆጣ እንችላለን።
ደስታ
ጥያቄ፡- ሉቃስ 10፡17-2፤ ዮሐንስ 15፡9-11 17፡13 አንብቡ። ሀ) በእነዚህ ክፍለ ምንባቦች ውስጥ ኢየሱስ የሚያሳየው ስሜት ምንድን ነው? ለ) በእያንዳንዱ ሁኔታ ላይ ኢየሱስ የዚህ ዓይነት ስሜት እንዲኖረው ያደረገው ምን ነበር?
ኢየሱስ በዚህ ምድር ሕይወት ዘመኑ ታላቅ የደስታ ሰው የነበረባቸው ብዙ ጊዜያት ነበሩ። በሉቃስ 10 ላይ የተጻፈው ታሪክ ሰባ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ለአገልግሎት ስለ መላክ ነበር። እነርሱም ወደ ተላኩበት ሄደው ተልዕኮአቸውን ፈጽመው በተመለሱ ጊዜ በጣም ደስ ብሏቸው ነበር። ደስታቸውም በመንፈስ ኃይል ተልዕኮአቸው በሚገባ መከናወኑን ስለተገነዘቡ ነበር። በተልዕኮአቸው ጊዜም ወንጌልን ሰብከዋል፥ አጋንንትንም አውጥተዋል። እግዚአብሔር በአገልግሎት ጠብቆአቸዋል፤ እግዚአብሔርም በኃይል በውስጣቸው እንደ ሠራ ተገንዝበዋል። ኢየሱስም በአከናወኑት አገልግሎት ደስ ብሎታል። ነገር ግን በሉቃስ 10፡20 ውስጥ አጋንንት ስለታዘዙላቸው ሳይሆን የበለጠ ሊደሰቱ የሚገባቸው በደኅንነታቸው መሆኑን ኢየሱስ ነግሮአቸዋል። በሉቃስ 10፡21 ውስጥ እንደተነገረ ሰባ ሁለት ልዑካን እግዚአብሔርን በበለጠ ስላወቁት መደሰቱን ይነግረናል። በእርግጥም በአገልግሎታቸው ጊዜ የእርሱ ኃይል ሲሠራ ደህና አድርገው ስለተመለከቱ ሊያውቁት ችለዋል። እንደዚሁም የደኅንነታቸውን ሙላት በአገልግሎቱ ወቅት ስለተነዘቡ ይበልጥ አውቀውታል። ጌታ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ጠለቀ መንፈሳዊ እውነታ ስለደረሱ ይህ ሁኔታ ታላቅ ደስታ ሊሰጠው ችሏል።
በዮሐንስ 5፡11 እና በዮሐንስ 7፡13 ውስጥ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ እርሱ ያለው ደስታ ዓይነት እነርሱም ሊኖራቸው እንደሚችል ይነግራቸዋል። በዮሐንስ 5፡1 ያ ደስታ የሚገኘው የክርስቶስን ትእዛዝ በመታዘዝና እግዚአብሔር አብን በማወቅ፥ እንደዚሁም ክርስቶስ እንደሚወዳቸው በመገንዘብ እንደሆነ ይናገራል። በዮሐንስ 15፡11 ውስጥ እንዳለው የክርስቶስ ደስታ ለደቀ መዛሙርቱ የመጣው እርሱ ተለይቶአቸው ከሄደ በኋላ አብ እንዲጠብቃቸው መጸለዩን ሲሰሙ ነው።
ጥያቄ፡= ) በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎች ደስታንና እርካታን ለማግኘት ጥረት የሚያደርጉባቸው መንገዶች ምንድን ናቸው? ለ) ባለፈው ወር ደስታና እርካታን ለማግኘት ጥረት ያደረጋችሁባቸው አንዳንድ መንገዶች ምንድን ናቸው? ሐህ እንዳንድ ክርስቲያኖች ደስታ የሌላቸው የሚመስሉት ለምንድን ነው? ምንን ረስተው ይሆን?
በዛሬው ዓለም ሰዎች በተለያዩ ነገሮች ደስታንና እርካታን ለማግኘት ይፈልጋሉ። አንዳንድ ሰዎችም ከገንዘብና ከንብረት ደስታን ለማግኘት ይሞክራሉ። ሌሎች ደስታን ክትምህርት፥ ከሥልጣንና ከዝና ለማግኘት ይፈልጋሉ። ሌሎችም ወደ መዝናኛ ስፍራዎች ሄደው በመዝናናት ደስታ የሚያገኙ ይመስላቸዋል። ነገር ግን የኢየሱስ ደስታ ለደቀ መዛሙርቱ የእውነተኛ ደስታን መገኛና የእርካታን መንገድ አሳይቶአቸዋል። እውነተኛ ደስታና እርካታ የሚገኘው እግዚአብሔርን ደህና አድርገን ስናውቀው፥ በአገልግሎታችንም ውስጥ ኃይሉን ስንገነዘብና ስንታዘዘው፥ እንዲሁም በሕይወታችን ውስጥ ያለውን ጥበቃውንና እንክብካቤውን ስንለማመድ ነው። የዛሬዎቹ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት በዚህ መንገድ እውነተኛውን ደስታ ለማግኘት የሚጥሩ ለመሆናቸው እርግጠኞች መሆን አለባቸው እንጂ የማያምኑ ሰዎች ደስታን ለማግኘት የሚፈልጉበትን መንገድ ሊከተሉ አይገባም። የዓለም ደስታ በመጨረሻው ላይ ባዶነትን ያመጣል፣ ክርስቶስ የሚሰጠው ደስታ ግን እውነተኛ እርካታን ይሰጣል። አማኞች በአካባቢአቸው ላሉ ያላመኑ ሰዎች የክርስቶስን ደስታ የሚያንጸባርቁ ለመሆናቸው እርግጠኞች ሊሆኑ ይገባል። እግዚአብሔርን በማወቅና ለእርሱም በመታዘዝ ሊኖር የሚችለውን እርካታና ደስታ ልናሳያቸው ይገባል።
ጥያቄ፡– በዚህ ሳምንት የክርስቶስን ደስታ ልትገልጹለት የምትፈልጉትን አንድ ያላመነ ሰው ስም በማስታወሻ ደብተራችሁ ላይ ጻፉ። ለዚህ ሰው ይህን ደስታ ለመግለጽስ ምን ታደርጋላችሁ?
ኀዘን
ጥያቄ፡- ኢሳይያስ 5፡3፤ ማቴዎስ 26፡37-38፤ ሉቃስ 12፡50፤ 22፡41-44 ዮሐንስ 12፡27 13፡21 አንብቡ። ሀ) በእነዚህ ክፍለ ምንባቦች ውስጥ ኢየሱስ ምን ዓይነት ስሜትን ያሳያል? ለ) ይህ ስሜት እንዲሰማው ያደረጉት ሁኔታዎች ምን ነበሩ?
ምንም እንኳን ኢየሱስ የደስታ ሰው የሆነባቸው ጊዜያት ቢኖሩም፥ በአንጻሩ ደግሞ የኀዘን ሰው የሆነባቸው ጊዜያትም ነበሩ። በእርግጥ ኢሳይያስ እርሱ የሥቃይና የኀዘን ሰው እንደሚሆን ተንብዮአል። ሆኖም ወንጌሎች ኢየሱስ ያዘነባቸውን ሁኔታዎች በስቅላቱ ጊዜ በተከሰቱ ድርጊቶች ዙሪያ የተፈጸሙ አድርገው አቅርበዋል። ኢየሱስ ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጠው በማሰብ አዝኖአል። በመጨረሻው እራት ላይም የመስቀሉ ሁኔታ ይታየው ስለነበረ ያዝን ነበር። በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራም ይጸልይ በነበረበት ጊዜ በዋነኝነት ይጨነቅ ነበር። ኢየሱስ በእነዚህ ጊዜያት ያዝንና ይጨነቅ የነበረበትን ምክንያት ለመገንዘብ ቀላል ነው። በመስቀል ላይ ተሰቅሎ መሞት እጅግ በጣም ጭካኔ የሞላበትና የሚያሠቃይ ሞት ነው። ስለሆነም ኢየሱስ ትልቅ ሥቃይና ሕማም እንደሚደርስበት ያውቅ ስለነበረ አዝኖአል። ይሁን እንጂ በቅድሚያ ኢየሱስን ያስጨንቀው የነበረው ሥጋዊ ሥቃይና ሕማም አልነበረም። ኢየሱስን ከሁሉም በላይ እንዲጨነቅ ያደረገው፥ የዓለምን በደልና ኃጢአትን የያዘውና ከእርሱ እንዲያልፍ የፈለገው ጽዋ ነበር (ሉቃስ 22፡42)። ኢየሱስ ለዓለም ኃጢአት ሲል በመስቀል ላይ መሥዋዕት ሆኖ ሲቀርብ ከአባቱ ጋር የነበረው ግንኙነት እንደሚቋረጥ ያውቅ ነበር (ማቴዎስ 27፡46)። ልጁ ለዘላለም ከአብ ጋር ልዩ ጣዕም ያለው ግንኙነትና ኅብረት አሳልፎአል። ነገር ግን አሁን ኢየሱስ ለዓለም ኃጢአት ሲል የነበረው አንድነት መቋረጡ ነበር (2ኛ ቆሮንቶስ 5፡2)። እንግዲህ ይህ ከአባቱ ጋር የአንድነቱ መቋረጥ ነበር ኢየሱስን ያስጨነቀው።
ሚያ ቋንም አይትና የግል ነሽ። ጊዜ ይጸልይ ነታ
ጥያቄ፡– በአብዛኛው የሚያስጨንቃችሁ ችግር ምንድን ነው?
ብዙ ጊዜ ጭንቀት ኃጢአት ነው (ፊልጵስዩስ 4፡6)። በምንጨነቅበት ጊዜ እግዚአብሔር እንደሚንከባከበን ስለማንታመንበት ኃጢአት እናደርጋለን። ከእግዚአብሔር በመለየታችን የሚሰማን ጭንቀት ኃጢአት ሊሆን አይችልም። ኃጢአት ሠርተን ከእግዚአብሔር ጋር የነበረን ግንኙነት ሲቋረጥ መጨነቃችን የተገባ ነው። ለዘላለም ከእግዚአብሔር ስለሚለዩት በምናስብበት ጊዜ መጨነቃችን ስሕተት ሊሆን አይችልም። የክርስቶስ ተከታዮች ከክርስቶስ ሊማሩ ይችላሉ፡- መጨነቅ ያለብን እኛንና በእኛ ዙሪያ ያሉትን ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለሚለየው ኃጢአት ነው።
ዛሬ ኢየሱስ ማንኛውም ሰብዓዊ ፍጡር የሚሰማው ዓይነት ስሜት እንዳለው ተገንዝበናል። ይህ ሁኔታ ስለ ኢየሱስ ስሜት ስናስተውል እርሱ እንደ እኛው ሰው እንደነበረ ለመገንዘብ ይረዳናል። ኀዘን፥ ደስታ ወይም ፍቅር ሲሰማን ኢየሱስ እንደ እኛው ሰው ሆኖ እነዚህን ሁሉ ስሜቶች ፍጹም በሆነ መንገድ ስላለፈባቸው የእኛም ስሜት ሁኔታ ይገባዋል። ስለ ኢየሱስ ስሜት ስናስብ፥ ንጹሕና ኃጢአት የሌለበት ስሜት ምን እንደሆነ ለመገንዘብ ይረዳናል። ኢየሱስ ፍጹም ሰው ነበር። ይሁን እንጂ ኃጢአትን በፍጹም አላደረገም (ዕብራውያን 4፡5)። በዚህ በስሜታዊ ሕይወታችን ውስጥ ክርስቶስን ልንመስል ይገባናል። እርሱ በኖረበት ስሜት እኛም በመኖር እግዚአብሔርን የምንፈራና እግዚአብሔር እንድንሆን የሚፈልገን ዓይነት ሰዎች ለመሆን እንችላለን።
ጥያቄ፡- በስሜታዊ ሕይወታችሁ ውስጥ እንደ ክርስቶስ ለመሆን የምትመኙባቸውን ሦስት መንገዶች በማስታወሻ ደብተራችሁ ውስጥ ጻፉ። በዚህ ሳምንት ውስጥ በስሜቶቻችሁ የበለጠ ኢየሱስን ለመምሰል ምን ታደርጋላችሁ?
ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ
God bless you all.