የሕይወት እንጀራ

ሁሉም ሰው የኃጢአት ተግባርን ፈጽሟል 

ባለፈው ሳምንት ትምህርት፥ ሁሉም ሰዎች ከአዳም ኃጢአት የተነሣ በእግዚአብሔር ፊት በደለኞች መሆናቸውን ተመልክተናል። ትናንትና ደግሞ በአዳም ኃጢአት ምክንያት ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኞች ሆነውና የኃጢአትን ተፈጥር ተላብሰው የተወለዱ መሆናቸውን ተገንዝበናል። ከዚሁ ከእቶም ኃጢአት የተነሣ ሰዎች በደለኛች እንደ ሆኑ ወይም ከኃጢአት ጋር እንደ ተወለዱ አንዳንድ ሰዎች አምነው አይቀበሉም። ለምሳሌ ያህል፥ ሙስሊሞች ኃጢአተኞች ሆነን መወለዳችንን ወይም መበደላችንን አምነው አይቀበሉም። ሌሎች ሰዎች ደግሞ አዳም በበደለ የእኛ ሥቃይን መቀበል ተገቢ አይደለም ባይ ናቸው። እንዲሁም አዳም በፈጸመው ኃጢአት ምክንያት እኛ የኃጢአት በደለኞች ወይም የኃጢአት ተፈጥሮ ለብሳችሁ ከኃጢአት ጋር የተወለዳችሁ ናችሁ መባላችን አግባብ አይደለም ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስገነዝበው ከሆነ ግን የኃጢአት በደለኞች ሆነንና በኃጢአት መወለዳችን ብቻ ሳይሆን፥ ሁላችንም ኃጢአተኞች እንደሆንን ያስተምራል። በእግዚአብሔር ፊት በደለኞች፣ የኃጢአት ባለዕዳዎችና የኃጢአት ባሪያዎች ሊያደርጉን የሚችሉ ብዙ የኃጢአት ተግባራትን ፈጽመናል። በዛሬው ትምህርታችን ሰዎች ሁሉ የኃጢአት ተግባራትን ስለ መፈጸማቸው እንማራለን። 

1. ሰዎች ሁሉ ኃጢአትን የፈጸሙ መሆናቸውን ብሉይ ኪዳን ያስተምራል። 

ጥያቄ፡– 1ኛ ነገሥት 8፡46 አንብብ። እንደ ንጉሥ ሰሎሞን አባባል ስንት ሰዎች ኃጢአትን ይሠራሉ? 

ጥያቄ፡- መጽሐፈ መክብብ 7፡20 አንብብ። ስንት ሰዎች ኃጢአትን ላይሠሩ ሁልጊዜ መልካም ተግባርን ይፈጽማሉ። 

ጥያቄ፡- መዝሙር (143)፡2 አንብብ። በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ማን ነው? 

ጥያቄ፡- መዝሙር 14፡1-3 አንብብ። ሀ) በጎ ነገርን ማን ያደርጋል? ለህ እግዚአብሔርንስ ማን ይሻል? ሐ) ማን ዐመፀ፥ ማንስ ረከሰ? 

ጥያቄ፡- መዝሙር (3)፡1-3 እንብብ፡ እግዚአብሔር ከመዝሙር 4፡1-3 ጋር ተመሳሳይ የሆነ ቃል በምን ምክንያት የደገመ ይ«መስልሃል? 

ብሉይ ኪዳን በግልጽ እንደሚያስረዳው ሰዎች ሁሉ ኃጢአት በመሥራታቸው ምክንያት በእግዚአብሔር ፊት ራሳቸውን ክፉዎች አድርገዋል። በ1ኛ ነገሥት 8 ላይ ንጉሥ ሰሎሞን የኢየሩሳሌምን ቤተ መቅደስ ሲመርቅ ባሰማው ታላቅ አሉት ሰዎች ሁሉ ኃጢአት መሥራታቸውን ተናግሯል። በተጨማሪም በመክብብ 7፡20 ላይ ንጉሥ ሰሎሞን በምድር ላይ ሁልጊዜ መልካምን የሚሠራ ኃጢአትንም የማያደርግ ጻድቅ አይገኝም ይላል። እንዲሁም ዳዊት በመዝሙር (148)፡2፥ አንድም ጻድቅ የለም ይላል። በመዝሙር 14፡1-3 ሲናገር መልካም ነገርን የሚያደርግ የለም ይላል። ለመሆኑ ዳዊት ይህን ሲል ምን ማለቱ ነበር? ይህን ሊል ማንም ሰው ሌሎች መልካም የሚሉትን ተግባር ሊፈጽም አይችልም ማለቱ ነበር? አይደለም፥ እንዲህ አላለም። ሰዎች ብዙውን ጊዜ የሚወዱዋቸውንና ሌሎችንም ሰዎች የሚረዱ መልካም ተግባራትን ያከናውናሉ። ዳዊት ለመናገር የፈለገው አሳብ ከቁጥር 2-3 ተገልጾአል። እግዚአብሔርን የሚሻ ሰው የለም። ሰዎች ሁሉ ከእግዚአብሔር ፊታቸውን አዙረዋል፥ ከዚህም የተነሣ ራሳቸውን አርክሰዋል። በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር በጎ ነው ብሎ የተቀበለውን ተግባር የፈጸመ ማንም የለም። በእግዚአብሔር ፊት ሊያቀርበው የሚችል በጎ ተግባር የፈጸመ ማንም አይገኝም። መዝሙር (53)፡1-3 ከመዝሙር 14፡1-3 የቃል በቃል ድግግሞሽ ያህል በጣም የተቀራረበ መልእክት ነው። እግዚአብሔር እነዚህን ቃላት የደጋገመበት ምክንያት ሰዎች የእግዚአብሔርን ዒላማ በመሳታቸው፥ ራሳቸውን በእግዚአብሔር ፊት እንዳረከሱና በደለኞች እንደሆኑ በግልጽ እንድንገነዘብ ለማድረግ ነው። 

ምናልባትም ሰዎች ሁሉ በግላቸው ኃጢአት ስለ መሥራታቸው የሚያስረዳ እጅግ በጣም ኃይል ያለው ጥቅስ በሮሜ 3፡9-20 ያለው ነው። 

ጥያቄ፡- ሮሜ 3፡9 እንብብ። ቀደም ባሉት በሮማ መልእክት ምዕራፎች ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ለተናገረው ቃል ማጠቃለያ ምንድን ነው? 

ጥያቄ፡- ሮሜ 3፡10–20 አንብብ። ጳውሎስ በእነዚህ ከብሉይ ኪዳን በተጠቀሱ ቁጥሮች ላይ የተናገራቸውን ሁሉ በአንድ ዓረፍተ ነገር አጠቃልለህ ጻፍ። 

ጥያቄ፡– ሮሜ 3፡10-12 አንብብ። ሀ) በሥራው በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛ ሆኖ ሊቆም የሚችል ማን ነው? ለ) እግዚአብሔርን ለማወቅና ደስ ለማሰኘት ከልብ የሚሻ ማን አለ? ሐ) እግዚአብሔርን ለማስደሰት በቂ መልካም ሥራ የሠራ ማን አለ? 

ጥያቄ፡– ሮሜ 3፡13-14 አንብብ። ሐዋርያው ጳውሎስ እዚህ ላይ የገለጻቸውን የአፍ ኃጢአቶችን በዝርዝር ጻፍ። 

ጥያቄ፡- መዝሙር 5፡4-10 አንብብ። ሮሜ 3፡13 ከዚህ ምንባብ ላይ የተወሰደ ነው። ሐሰትን በሚናገሩ በክፉዎች ላይ ምን ይደርሳል? 

ጥያቄ፡– መዝሙር (140)፡1–3 አንብብ። እንደዚህ ጥቅስ አገላለጽ ሰዎች «ምላሳቸው እንደ መርዛም እባብ ነው» ሊባል ምን ማለት ነው? 

ጥያቄ፡- ሮሜ 3፡15-18 አንብብ። እነዚህ ጥቅሶች በምን በምን ኃጢአቶች በደለኞች ያደርጉናል? 

በሮሜ 3፡9 ላይ ጳውሎስ በሮሜ ውስጥ በሌሎች ምዕራፎች ላይ የተናገረውን ሁሉም ሰው አይሁድ ይሁን አሕዛብ ኃጢአት በመሥራታቸው በኃጢአት ኃይልና ቅጣት ሥር ናቸው በማለት ያጠቃልላል። አሕዛብ በልባቸውና በሕሊናቸው የእግዚአብሔርን እውነት ያወቁ ቢሆንም ግን ችላ ብለውት ወደ ኃጢአት ገብተዋል። አይሁዶች ምንም እንኳን የእግዚአብሔርን ቃል የመልማት ዕድል ቢኖራቸውም፥ እነርሱም ቃሉን ችላ በማለታቸውና ባለመታዘዛቸው ምክንያት ወደ ኃጢአት ገብተዋል። 

ጳውሎስ ሰዎች ሁሉ በየግላቸው ኃጢአተኞች መሆናቸውን ለማረጋገጥ ወደ ብሉይ ኪዳን ያመራል። ሁሉም ሰው ኃጢአት ለመሥራቱ ማስረጃ ለማቅረብ የተለያዩ ጥቅሶችን ያቀርባል። እነዚህ ጥቅሶች 2 ነጥቦችን ያስተጋባሉ፡- ሀ ሁሉም ኃጢአት ሠርተዋል 2) ኃጢአት ገዳይ የሆነ ክፉ ውጤትን ያመጣል። 

ጳውሎስ፥ በሮሜ 3፡10-12 ባለው ክፍል መዝሙር 14፡1-3 እና መዝሙር (53)፡1-3 ያለውን ይጠቅሳል። ቀደም ሲል እነዚህን ጥቅሶች በመጀመሪያው በብሉይ ኪዳን ጽንሰ አሳባቸው አኳያ ተመልክተናቸዋል። እነርሱም ማንም ሰው በእግዚአብሔር ፊት ፍጹም እንዳልሆነ፥ በእውነት እርሱን የሚፈልግ እንደሌለ ያስገነዝቡናል። በብሉይ ኪዳን ውስጥ እንዳነበብነው፥ እነዚህ ጥቅሶች ሰዎች መልካም የተባለ ሥራ ከቶ አይሠሩም አይሉም፡ የሚሉት ሰዎች የሚሠሩት መልካም ሥራ በእግዚአብሔር ፊት እነርሱን መልካም ለማድረግ ብቁ ሆነው አይገኙም ነው። ብዙ ሰዎች መልካም ሥራዎችን እንደሚፈጽሙ የታወቀ ነው። ግን እነዚያ መልካም ሥራዎች በእግዚአብሔር ፊት ቀርበው ሊመዘኑ ጻድቃን ሊያደርጓቸው አይችሉም። እነዚህን መልካም ነገሮች ቢሠሩም ከኃጢአታቸው የተነሣ በእግዚአብሔር ፊት የረከሱና በደለኞች ናቸው። እኛም ብንሆን መልካም ነገርችን ብንሠራም እንኳ ከኃጢአታችን የተነሣ አሁንም ቢሆን መጥፎ ሰዎች ነን። አሁንም ኃጢአተኛች ነን ማለት በእግዚአብሔር ፊት በደለኞች ነን ማለት ነው። 

በቁጥር 13 ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ መዝሙር 5፡9 እና መዝሙር (140)3ን ይጠቅሳል። እንዲሁም በቁጥር 14፥ መዝሙር 10፡7ን ይጠቅሳል። በእነዚህ ቁጥሮች ውስጥ ከአፍ ኃጢአት የተነሣ ሁሉም በደለኞች ናቸው ይላል። «ጉርርአቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው» ሲል፣ ይህን ማለቱ ነው። ሰዎች ሁሉ ወደ ሞት የሚያደርሷቸው ኃጢአቶች በአፋቸው አማካይነት ይፈጽማሉ። እዚህ ላይ ስለ ምን ዓይነት ኃጢአቶች ይናገራል? የሚናገረው ስለ ውሸት ስለ መራገምና ስለ ምሬት ነው። ውሸት ማለት እውነት ያልሆነ ነገር መናገር ወይም ማድረግ ነው። እንዲሁም ትንሽም ቢሆን እውነቱን ነገር ለእኛ በሚጠቅመን ዘዴ ለውጥ አድርገን መገኘት ራሱ መዋሸት ነው። መዝሙር 5፡9 የሚዋሹና የሚያጭበረብሩ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት በደለኛች ስለሆኑ በፊቱ ሊቆሙ አይችሉም ይላል። ስለዚህ እንዲህ ያሉ ሰዎች ይጠፋሉ፥ ይወገዳሉም። መራገም፥ ንጹሕ ያልሆኑ ነገርችን መናገር፥ ወይም የእግዚአብሔርን ለም ክብር በሌለበትና በግድየለሽነት ሁኔታ ማንግት ነው። ምሬት ደሞ ሌላውን ሰው የሚጎዳ ነገር በቀጥታ ለራሱ ወይም ከበስተኋላው መናገር ወይም ማድረግ ነው። በመዝሙር (140)፡1-3 ላይ መዝሙረኛው ሲናገር፥ የእባብ መርዝ በከንፈሩ ያለው ሰሙነ በሌሎች ላይ ዓመፅንና ጉዳትን የሚያስከትሉ ነገሮችን የሚናገር ሰው መሆኑን ይገልጻል። 

ብዙ ሰዎች፥ ከአፍ የሚወጡ እንደ መዋሸት፥ መራገምና ስለ ሌሎች ሰዎች የምራት ታላን መናገር ያሉ ነገሮችን ማድረሳ መጥፎ ኃጢአቶች እንዳልሆኑ አድርገው ያስባሉ። እንዲያውም ብዙ ክርስቲያኖች እነዚህን 5 የመሳሰሉ ኃጢአቶችን እየፈጸሙ፥ ምንም የከፋ ነገር እንዳላደረጉ ያስባሉ። ጳውሎስ ቀን እኛ ሁላችን ኃጢአተኞች ነን፥ ኃጢአታችንም በእግዚአብሔር ፊት በደለኞች አድርጎናል ሲል የጠቀሰው እነዚህን የመጀመሪያ ኃጢአተች አድርጎ ነው። 

ከቁጥር 5-7 ባለው ክፍል ጳውሎስ ኢሳይያስ 5፡7-8ን ይጠቅሳል። በዚህም የሰዎች ኃጢአት የሌሎችን ሰላም እንደሚያናውጥ ይናገራል። በጣም ጥቂት ሰዎች ሌላውን ሰው ይገድሉ ይሆናል፥ ግን ሌሎችን ያልጠላ አንድም ሰው አይገኝም። በሌሎች ላይ ክፉ ተግባራትን በመፈጸም ወይም በመናገር ሕይወታቸው እንዲጎሳቆል ያላደረገ ማንም ሰው የለም። እንዲሁም ሁሉም ሰው የሌሎች ሰዎችን ሰላም አደፍርሷል። እነዚህም ጥቅሶች ሰዎች ከኃጢአታቸው የተነሣ በከፋ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን ከሚገልጸው የኢሳይያስ የትንቢት መጽሐፍ አጠቃላይ ምዕራፍ አንዱ ክፍል ናቸው። ስለሆነም ሰዎች ከኃጢአተኝነታቸው የተነሣ ነፍሰ ገዳዮች፣ ውሸታሞች፥ የታወሩ፥ ሙታን፥ ጠበኞች፥ ከእግዚአብሔርም የተለዩና የእግዚአብሔር ቁጣ የሚጠብቃቸው ተብለዋል። ቁጥር 18 ከመዝሙር (36)፡1 የተወሰደ ነው። «እግዚአብሔርን ከተ አለመፍራት» ማለት፥ ሰዎች እግዚአብሔር ስለ እንድ ነገር ምን ማድረግ እንዳለባቸው የሚነግራቸውን እያወቁ አለማድረጋቸውን ይጠቁማል። እንደዚሁ ሁሉ ሰዎች የሚፈጽሙት መጥፎ ተግባር ኃጢአት መሆኑን ሙሉ በሙሉ እያወቁ ያደርጉታል። 

እንደገናም፥ ብዙ ሰዎች በሚናገሩት ወይም በሚያደርጉት ሌሎች ሰዎችን በጥላቻ ሲያጎሳቁሉአቸው የከፋ ኃጢአት የሠሩ መስሎ አይታያቸውም፡ እንዲሁም ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ እንዲፈጽሙ የሚያዛቸውን ተግባር ባያደርጉ እንደ ከባድ ኃጢአት አይቆጥሩትም። በዚህም የእግዚአብሔርን ሕፃ ስለ ጣሰን የእግዚአብሔርን ቅጣት እንቀበላለን ይላል። 

ጥያቄ፡- በቅርቡ በአፋችሁ ኃጢአት የሠራችሁበትን ወቅት አስታውሱና አፉት። ለ) ደሞም በቅርቡ የማትወዱትን ሰው የሚጎዳ ነገር አድርጋችሁበት ከሆነ፥ እለታውሳችሁ 4ሩት፡ ሐህ መጽሐፍ ቅዱስ እንድታደርጉት ያዛችሁንና እናንተ ደግሞ ለላላደረጋችሁት የቅርብ ጊዜ ተባር አስታውሳችሁ ጻፉ። 

ጥያቄ፡- ሀ) እነዚህን ነገሮች ባደረጋችሁ ጊዜ ከባዶች አይደሉም ብላችሁ ነበር፥ ወይስ የእግዚአብሔርን ሕቀ በጽኑ መጣላችሁ ተሰነ+እችሁ ነበር? ስለ እነዚህ ኃጢአተች አሁን ምን ይሰማችኋል? የምታስቡትን በማለታወሻ ደርቻችሁ ውስጥ አፉ ለ) እዚህን ብዙ ሰዎች ችላ የሚሉአቸውን ኃጢአቶች በተመለከተ ጊዜ ወስዳችሁ ልባችሁን በመመርመር ወደ እዚአብሐር በንስሐ ቅረቡ። 

ሁላችንም ኃጢአትን ሠርተናል። ብዙ ጊዜ እነዚህ ኃጢአቶች በጣም መጥፎዎች መሆናቸውን አናስብም። ታዲያ ከእነዚህ ለእኛ ከባድ መስለው ከማይታዩ ኃጢአቶች ውስጥ አንዳንዶቹ እግዚአብሔር ሕጉን በመጣሳችን ቅጣት እንደሚገባን የተናገራቸው ናቸው። ነገር ቀን እኛ በኢየሱስ ክርስቶስ የምናምንና የሕይወታችን ጌታ ልናደርገው የምንሻ ከሆነ እግዚአብሔር ስለ ኃጢአታችን የሚነግረንን መቀበል እንችላለን። ይህን ስናደርግ እነዚህ ኃጢአቶች በእርግጥ የከፉ መሆናቸውንና በእግዚአብሔር ፊትም በደለኞች እንደሚያደርጉን እንገነዘባለን። ስለዚህም ንስሐ በመግባት ልናስወግዳቸው እንጥራለን። 

በብሉይ ኪዳን ውስጥ የሚገኙ ጥቅሶች ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኞች መሆናቸውን ጥርት አድርገው ይናገራሉ። እግዚአብሔርን የሚፈልግ ማንም የለም። ሰዎች ሁሉ በአፍ አማካይነት የሚፈጸም ኃጢአትን አድርገዋል። ሰዎች ሁሉ ለሌሎች የጥላቻ ሁኔታን በማሳየት በድለዋል። ሁሉም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ችላ በማለት ያላቸውን አድርገዋል። በዚህም ምክንያት ሁሉም ኃጢእት አድርገዋል። ስለዚህ ሁሉም ኃጢአትን ስለ ፈጸሙ፥ ሕግን ባለ መጠበቃቸው ጻድቃን ሊባሉ አልቻሉም። ጳውሎስም በሮሜ 3፡20 እና 23 ውስጥ የሚናገረው ይህንኑ ነው። 

2. ሰዎች ሁሉ ኃጢአትን በመሥራት የበደሉ ስለሆኑ፥ ማንም ሕግን ከመጠበቅ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሊሆን አይችልም። 

ጥያቄ፡– ሮሜ 3፡20 አንብብ። ሀ) ሕግን በመጠበቅ ማን ጻድቅ ሊባል ይችላል? | ለ) የሕግ እውነተኛው ዓላማ ምንድን ነው? (ቁጥር 20) 

ጥያቄ፡- ሮሜ 3፡23 አንብብ። ሀ) ኃጢአትን ማን ሠራ? ላ) የዚህ ኃጢአት ውጠት ምንድን ነው? 

ጳውሎስ በሮሜ 3፡20 ውስጥ በሮሜ ምዕራፍ 1-3 ያለውን መልእክቱን ያጠቃልላል። ሁሉም ኃጢአትን ስለ ሠሩ፥ ሁሉም በእግዚአብሔር ፊት በደለኞች ናቸው። በቂ የሆነ መልካም ሥራ በመሥራት ደኅንነትን ሊያገኙ የሚችሉ የሉም። በየትም ስፍራ ያሉ ሰዎች ሁሉ ምንም ያህል መልካሞች ሊሆኑ ቢጥሩም፥ በእግዚአብሔር ፍርድ ፊት ይቆማሉ። ለምን? ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ሕግ በፍጹምነት ሊጠብቅ የሚችል ማንም ስለማይገኝ ነው። ታዲያ ሕግ በምን ምክንያት ተሰጠ? ሕግ የደኅንነት መንገድ በመሆን ፈንታ እውነተኛ ዓላማው ሰዎች ኃጢአተኞች መሆናቸውን ማሳየት ነው። ስለዚህ ሕግ ማንም ሰው እግዚአብሔር ያስቀመጠውን ፍጹምና የጽድቅ ሚዛን ሊሞላ እንደማይችል ይገልጻል። ማንም ሰው በንጽሕናው ወይም በመልካምነቱ ከእግዚአብሔር ፍርድ ሊያመልጥ አይችልም። እግዚአብሔር ሕን የደኅንነት መገኛ መንገድ እንዲሆን አልሰጠም። ሕግን የሰጠው ሰዎች ራሳቸውን ማዳን እንደማይችሉ ለማሳየት ነው። ሕን የሰጠው ሰዎች በንስሐ ተመልሰው እግዚአብሔር በምሕረቱና በጸጋ ብቻ እንዲያድናቸው መማጻን እንዲችሉ ነው፡፡ 

እንደገናም ጳውሎስ ይህንኑ አሳብ በሮሜ 3፡4 ውስጥ ያጠቃልለዋል። በዓለም ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ በድለዋል። በአይሁድና በአረማውያን መካከል ልዩነት የለም። በዓለም ያሉ ሁሉ የእግዚአብሔርን ሕግና የሕሊናቸውን ሕግ ጥሰዋል። ከዚህ ኃጢአት የተነሣ ሰዎች የእግዚአብሔርን ክብር አጥተዋል። ይህም ማለት ሁላችንም የተፈጠርንለትንና በሰማይ ብቻ እንደገና ልናገኘው የምንችለውን ከእግዚአብሔር ጋር የነበረንን ግንኙነት አጥተናል ማለት ነው። ብዙ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት ይህን ያህል ክፉዎች ሆነው እንደማይገመቱ አድርገው ያስባሉ። ጥቂት ስሕተቶችን መፈጸማቸውን ቢረዱም የሠሩት ኃጢአት የከፋ ሆኖ አይታያቸውም። 

ብዙ ሰዎች የሠሩትን ጥቂት ኃጢአት የሚሸፍንላቸው መልካም ሕይወት ሊኖሩ እንደሚችሉና እግዚአብሔርም ይህን መዝኖ እንደሚያድናቸው አድርገው ይገምታሉ። ጳውሎስ ግን በግልጥ ሁሉም በድለዋል፥ ስለዚህ የሁሉም ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት በደለኞች ያደርጋቸዋል ይላል። ማንም ሰው ቢሆን በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሆኖ ለመገኘት ብቁ የሆነ ሕይወትን ሊኖር አይችልም። ኃጢአትን ባለመሥራቱ ማንም ቢሆን የእግዚአብሔርን ደኅንነት ሊያገኝ አይችልም። በበጎ ሥራው የእግዚአብሔርን ጽድቅ የሚቀበል አንድም አይኖርም። 

ጥያቄ፡- ሀ) በእግዚአብሔር ፊት በመልካም ሥራቸው ለመጽደቅ እንደሚችሉ የሚያምኑ የምታውቋቸው ሰዎች አሉ? ለ) ኃጢአታቸው የከፋ ሆኖ ሳለ የከበደ ኃጢአት እንዳልሠሩና በእግዚአብሔር ፊትም ትክክለኞች እንደሆኑ የሚሰማቸው የምታውቋቸው ሰዎች አሉ? ሐ) ለእነዚህ ሰዎች መልካም ሥራቸው እነርሱን ለማዳን በቂ አለመሆኑን ምን ጥቅላ ትነግሯቸዋላችሁ? ብዙ ሰዎች ኃጢአታቸው እጅግ የከፋ ሆኖ አይታያቸውም፡ ስለዚህ በቂ የሆነ መልካም ሥራ ከፈጸሙ፥ እግዚአብሔር ወደ መንግሥተ ሰማይ እንዲገቡ የሚፈቅድላቸው ይመስላቸዋል። ነገር ግን ርማ 3 በግልጽ እንደሚያስተምረን፥ ሰዎች ሁሉ ኃጢአትን ስለሠሩ ማንም ሰው ቢሆን የእግዚአብሔርን ክብር እንዲያገኝና ወደ መንግሥተ ሰማይ እንዲገባ የሚያደርግ መልካም ሥራ ሊፈጽም አይችልም። ሰዎች ሁሉ ኃጢአት ስለሠሩ ማንም ሰው ሕግን በመጠበቅ ወይም በበጎ ሥራው በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ ሊያገኝ አይችልም። ስለዚህ ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኞች የመሆናቸውን እውነታ ለሌሎች ማካፈልና ኃጢአታችንም በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን አድርጎ ሊያቀርበን የሚያስችል በጎ ተግባር ሊያስፈጽመን እንደማይችል ማስገንዘብ አለብን።

ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

የጌታ ጸጋ ከእርስዎ ጋር ይሁን፤ ሀሳብዎን ለመስማት ዝግጁ ነን።

Discover more from የሕይወት እንጀራ

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading