የደኅንነት አስፈላጊነት- ሰዎች ኃጢአተኛ በሆነ ባሕርይ ተወለዱ ማለት ምን ማለት ነው?

ባለፈው ሳምንት ለለ ኃጢአትና በክርስቶስ የሚሰጠው ደኅንነት በምን ምክንያት እንደሚያስፈልገን የሁለት ሳምንት ትምህርት መጀመራችን ትዝ ይላችኋል። በዚሁ ጊዜ ኃጢአት ማንኛውንም ነገር ከእግዚአብሔር ማስቀደም እንደሆነ ለመመልከት ችለናል። በመሆኑም ማንኛውንም ነገር ከእግዚአብሔር በምናስቀድምበት ጊዜ የእግዚአብሔርን ባሕርይና ሕግ በተግባራችንና በአመለካከታችን ወይም በፍጥረታችን እንጥላለን። ባለፈው ሳምንት የራሳችን ፍላጎት ከእግዚአብሔር ፍላጎት እንዲቀድም ስናደርግ ያኔ ኃጢአት እንደምንሠራ ተገንዝበናል። እንደዚሁም የኃጢአት ውጤት ሥጋዊ፥ መንፈሳዊና ዘላለማዊ ሞት ወይም ከእግዚአብሔር መለየት መሆኑን አስተውለናል። በመጨረሻውም ከአዳምና ከሔዋን ኃጢአት የተነሣ ሰዎች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት በደለኞች መሆናቸውን ተምረናል። በዚህ ሳምንት ስለ ኃጢአት የጀመርነውን ጥናት እንቀጥላለን። በአዳምና በሔዋን ኃጢአት ምክንያት ወደ ሰዎች ሁሉ ስለሚተላለፈው የኃጢአት ተፈጥሮና የአማኞችንም ሆነ የማያምኑ ሰዎችን ኃጢአት ጨምሮ ግላዊ ኃጢአትም እናጠናለን። 

መጀመሪያ ቀን- ሁላችንም የኃጢአትን ተፈጥሮ ከአዳም ኃጢአት ወርሰናል። 

ኃጢአተኛች ስለ መሆናችን ሰዎች የተለያየ አስተሳሰብ አላቸው። ሙስሊሞችም ሆኑ ብዙ ምዕራባውያን ማንም ኃጢአተኛ ሆኖ አይወለድም ይላሉ። የአዳምና የሔዋን ኃጢአት በምንም ዓይነት አይነካንም ብለው ያምናሉ። ሰዎች በመሠረቱ መልካሞች ሆነው ይወለዳሉ፥ ግን አንዳንድ ጊዜ በሕይወታቸው ውስጥ ስሕተት ሊያደርጉ ይችላሉ ይላሉ። 

ጥያቄ፡- ሰዎች በተፈጥሮአቸው እንዴት ኃጢአተኞች ስለ መሆናቸው፥ የምታውቋቸው ሰዎች የሚያምኑት ምንድን ነው? እናንተ የምታስቡትንም በጽሑፍ አስፍሩ። በኋላም ሦስት ሰዎችን ማለትም አንድ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን፥ አንድ ወንጌላዊ ክርስቲያንና አንድ ሙስሊምን ለማነጋገር ሞክሩ። ይህን ጥያቄም ጠይቋቸው፡= ሰዎች ከኃጢአት ተፈጥሮ ጋር ተወልደዋል ወይስ ንጹሕ ሆነው ወይስ ከሁለቱም ላይሆኑ? ተመልሳችሁ ኑና መልሶቻቸውን በማስታወሻ ደብተሮቻችሁ ውስጥ አስፍሯቸው። 

ምንም እንኳን ብዙ ሰዎች ኃጢአተኞች ሆነን መወለዳችንን ባያምኑና፡ ሰዎች በመሠረቱ መልካም ሆነው ተወልደዋል ሲሉም፥ ከአዳምና ከሔዋን ኃጢአት የተነሣ ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኞች ሆነው እንደሚወለዱ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል። ሰዎች ሁሉ በኃጢአት ተበክለው ይወለዳሉ። በዛሬው ትምህርታችንም ኃጢአተኞች ሆነን ስለ መወለዳችን ወይም በተፈጥር ኃጢአተኞች ስለ መሆናችን የሚናገሩትን ብዙዎቹን ቅዱሳት መጻሕፍት እናጠናለን። 

1. ሰዎች ሁሉ በኃጢአት ተፈጥሮ ተወልደዋል። 

ጥያቄ፡– መዝሙር (51)፡5 አንብብ። ዳዊት ከመቼ ጀምሮ ነው ኃጢአተኛ የነበረው? 

ጥያቄ፡- መዝሙር (58)፡3 አንብብ። ክፉዎች የተለዩት፥ የሳቱትና ውሸትን መናገር የጀመሩት ከመቼ ጀምሮ ነው? 

ጥያቄ፡– ኤርምያስ 17፡9 አንብብ። ኤርምያስ ልብን እንዴት ይገልጸዋል? 

ብሉይ ኪዳን ሰዎች ኃጢአትን እንደሚፈጽሙ ብቻ ሳይሆን፥ ነገር ግን በተፈጥሮአቸውም ኃጢአተኛች መሆናቸውን ያስተምረናል። መዝሙር (5) ዳዊት ከቤርሳቤህ ጋር ኃጢአት ከሠራ በኋላ የጸለየው የንስሐ መዝሙር ነው። ነገር ግን ዳዊት በመዝሙር (505 ውስጥ ከቤርሳቤህ ጋር ያደረገውን ኃጢአት ብቻ አልተናዘዘም። ጨምሮም ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ ኃጢአተኛ መሆኑን ተናዝዟል። እንዲያውም በእናቱ ማሕፀን ከተረገዘበት ጊዜ ጀምሮ ኃጢአተኛ እንደ ነበረ ተናዝዛል። እንዲህ ማለትም እናቱ በምንዝርና አርግዛዋለች ማለት አይደለም። ማለት የተፈለገው ዳዊት ከተረገዘበት ቅጽበት ጀምሮ ፍጥረቱ ኃጢአትን ተላብሷል ማለት ነው። በመዝሙር (58)3 ደግሞ ዳዊት ስለ ሌሎች ሰዎች ይህንኑ የመሰለ ቃል ይናገራል። ከእናታቸው ማሕፀን ጀምሮና ከተወለዱበት ጊዜ ጀምሮም ኃጢአተኞች ናቸው። ኤርምያስ 17፡9 የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኮለኛና ክፉ ነው ይላል። እንዲህ ማለትም ሰዎች ኃጢአትን መሥራትን የእግዚአብሔርንም ሕግ መተላለፍን ባለማስተዋል ይመርጣሉ፥ ምክንያቱም ልባቸው ኃጢአት ክፉ አለመሆኑን እየነገረ ስለሚያታልላቸው ነው። አሳባቸውና ተግባራቸው እግዚአብሔርን ደስ አያሰኘውም፥ ራሳቸውንም ለማረም የሚያደርጉት ነገር የለም። የሰዎችን ልብ ክፉና አሳች ተፈጥሮ የሚያድን መድኃኒት የለም። ብሉይ ኪዳን ሰዎች ተወልደው ኃጢአት ከመሥራታቸው በፊት ሳይቀር ኃጢአተኞች መሆናቸውን ይገልጻል። እንዲህም ማለት የሰው ልጆች ከተፈጥሮአቸው ጀምሮ ኃጢአተኞች መሆናቸውን ያሳያል። 

ጥያቄ፡– ኤፌሶን 2፡3 አንብብ። ጳውሎስ ሁላችንም በተፈጥሮ ምንድን ነን ይላል? 

ጥያቄ፡- ሮሜ 7፡18 አንብብ። ጳውሎስ በሥጋዩ ውለጥ ምን ይኖራል ይላል? 

ጥያቄ፡– ቲቶ 1፡15 አንብብ። ጳውሎስ ለርኩሳን ምን የለም አለ? 

አዲስ ኪዳንም በበኩሉ ሰዎች በተፈጥሮ ኃጢአተኞች ስለ መሆናቸው ያስተምረናል። ኤፌሶን 2፡3 እኛ ሁላችን «ከፍጥረታችን» የቁጣ ልጆች ነበርን ይላል። እንዲህም በተፈጥሮአቸው ኃጢአተኘች ስለነበሩ የእግዚአብሔር የጽድቅ ቁጣ በላያቸው ላይ ነበር ማለት ነው። የሰው ልጆች በተግባር ከፈጸሙት ኃጢአት ውጭ የእግዚአብሔር ቁጣ በሰው ሁሉ ላይ ነው። ሰዎች ሁሉ ከተፈጥሮአቸውና ከውልደታቸው ኃጢአተኞች በመሆናቸው በማንነታቸው የተነሣ የእግዚአብሔር ቁጣ ሰፍኖባቸዋል። ጳውሎስ በሮሜ 7፡18 ውስጥ በሥጋው ውስጥ ምንም መልካም ነገር እንደሌለ ይናገራል። «በሥጋዩ» ሲል ጳውሎስ ስለ ኃጢአተኛ መግለጹ ነው። እንደዚሁም ከክርስቶስ ውጭ ስላለው እርሱነቱ ሁሉ መናገሩ ነው። ምንም እንኳን እርሱ የዳነ ሰው ቢሆንም፥ አሮጌው ተፈጥሮ አሁንም አብሮት እንዳለ ሲጠቁም ነው። እናም በዚያ አርጌ ተፈጥሮ ውስጥ ምንም መልካም ነገር ሊኖር አይችልም አለ። የሰው ልጆች ሁሉ ከክርስቶስ ውጭ እና ከመወለጻቸው ጀምሮ ያላቸው ማንነት ሁሉ ክፉ ነው። ከክርስቶስ ውጭ በተፈጥሮአችን ማንኛውም ነገር መልካምነት የለውም። በቲቶ 15 ርኩሶች «አእምሮአቸውም ሆነ ሕሊናቸው የረከሰ ነው» ይላል። «ርኩሶች» ከክርስቶስ የተለዩ ሰዎች ናቸው። ስንወለድ ርኩሶች ነበርን ማለት እእምሮአችንም ሆነ ሕሊናችንም ርኩስ ነው ማለት ነው። 

መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች በተፈጥሮአቸው ኃጢአተኞች መሆናቸውን ብቻ አያስተምርም። ስለሆነም መጽሐፍ ቅዱስ በዝርዝር ሲያስተምር ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኛች ሆነው እንደ ተወለዱና በተፈጥሮአቸውም (በባሕሪያቸውም) ኃጢአተኞች እንደሆኑ ያስነዝባል። 

2. ሰዎች ኃጢአተኛ በሆነ ባሕርይ ተወለዱ ማለት ምን ማለት ነው? 

2.1 በራላችን የምናደርገው ነገር ሁሉ እግዚአብሔርን አያስደስተውም። 

ጥያቄ፡– ሮሜ 8፡7-8 አንብብ። ሀ) ስለ ሥጋዊ ነገር የሚያስብ እእምር የሚታወቅበት እውነት ምንድን ነው? ለ) በሥጋ ስላሉትስ እውነቱ ምንድን ነው? 

ጥያቄ፡- ኢሳይያስ 64፡6 አንብብ። እንደ እግዚአብሔር አስተሳሰብ፥ የጽድቅ ሥራችን ምንድን ነው? 

ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኛ ሆነው ተወለዱ፥ በባሕርያቸው ኃጢአተኞች ናቸው ስንል ምን ማለት ነው? የመጀመሪያው የተፈጥሮ ኃጢአት ስላለን በራሳችን የምናደርገው እግዚአብሔርን የሚያስደስተው ነገር የለም ማለት ነው። ምክንያቱም ሰዎች ኃጢአተኞች ሆነው ስለ ተወለዱ በእግዚአብሔር ፊት ራሳቸውን መልካም አድርገው ማቅረብ አይችሉም። ሮሜ 8፡7-8 ስለ ሥጋ የሚያስብ አእምሮ የእግዚአብሔር ጠላት ነው ካለ በኋላ፥ እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ እግዚአብሔርን ደስ አያሰኙም ይላል። እንግዲህ ሥጋ ሁላችንም የተወለድንበት ኃጢአተኛው ተፈጥሮአችን ነው። ማንም የሥጋን ፈቃድ የሚከተል እግዚአብሔርን ማስደሰት አይችልም። እንደዚሁም በሥጋ ፈቃድ ቁጥጥር ሥር የሆኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላቶች ናቸው። ኢሳይያስ 646 ጽድቃችን ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው ይላል። እንዲህ ማለት ደኅንነትን ያላገኘ ሰው ምንም ያህል መልካም ምግባሮች ይኑረው፥ ምግባርቑ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አይኖራቸውም፤ እግዚአብሔርንም ደስ አያሰኙትም። ሥራዎቹ ያን ሰው ከእግዚአብሔር ጋር አያቀራርቡትም። እግዚአብሔር በሕይወታቸው ውስጥ ጣልቃ ገብተ ካላዳናቸውና እርሱን ደስ እንዲያሰኙ ካሳደረጋቸው በስተቀር፥ ሰዎች በዛ ፍላጎታቸው ተነሣሥተው እግዚአብሔርን ሊያስደስቱት አይችሉም። እግዚአብሔር በመጀመሪያ ሰሕይወታቸው ውስጥ ጣልቃ ገብቶ ከራሱ በማለታረቅ ወዳጆቹ እስካላደረጋቸው ድረስ ሰዎች ጠላቶቹ ሆነው ይኖራሉ። እንዲሁም ኃጢአተኞች ሆነን ከመወለዳችን የተነሣ በዛ ኃይላችን ተነሥተን እግዚአብሔርን ልናስደስተውም ሆነ በፊቱ ራሳችንን ብቁዎች አድርገን ማቅረብ አንችልም፡፡ 

2.2 መንፈሳዊ ነገሮችን መገንዘብ አንችልም። 

ጥያቄ፡– ኤፌሶን 4፡18 አንብብ። አማኞች ስላልሆኑ አረማውያን እውነት የሆኑ ምን ሁለት ነገሮች አሉ? 

ጥያቄ፡- 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡14 አንብቡ። የእግዚአብሔር መንፈስ ስለሌለበት ሰው እውነት የሆነው ምንድን ነው? 

ሁለተኛው ነገር ሁላችንም ኃጢአታዊ ባሕርይ አለን ሲባል ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ ነገርን አንነዘብም ማለት ነው። ኤፈሶን 18 የማያምኑ «አእምሮአቸው ጨልሞአል» ይላል። እንዲህ ማለት አእምሮአቸው ስለታወረ የእግዚአብሔርን ነገር መገንዘብ ተሳነው ማለት ነው። 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡14 የእግዚአብሔር መንፈስ ስለሌለበት ሰው ይናገራል። ይህ እንግዲህ ስለማያምን ሰው ነው ሮሜ 8፡9 ተመልከቱ)። የእግዚአብሔር መንፈስ የሌለባቸው ሰዎች የእግዚአብሔር መንፈስ ሊገልጥላቸው የሚፈልገውን ማንኛውንም ነገር ሊነዘቡ አይችሉም። የእግዚአብሔርን እውነት ከሞኝነት ይቆጥሩታል። ስለዚህ አይቀበሉትም። እነዚህ ጥቅሶች ስንወለድ ከኃጢአት ጋር መወለዳችንንና ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር በሕይወታችን ውስጥ ጣልቃ ገብቶ እስካልገለጠልን ድረስ መንፈሳዊ ነገሮችን የማይነዘብ ተፈጥሮ እንደ ነበረን ያስረዳናል። እኛ በራሳችን ኃጢአተኞች ነን። በኃጢአት ተወለድን ማለት ደግሞ እግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ እስካልገለጠልን ድረስ መንፈሳዊ እውነታን ለመገንዘብ የማንችል ነበርን ማለት ነው። 

2.3. እግዚአብሔር ዓይኖቻችንን እስካልከፈተልን ድረስ ለእርሱ የምንሰጠው መልስ አይኖርም። 

ጥያቄ፡– ኤፈሶን 2፡1 አንብብ። ጳውሎስ ስለ ሰዎች ሁሉ እውነቱ ምንድን ነበር ይላል? 

ጥያቄ፡- ዮሐንስ 8፡34 አንብብ። ሀ) ኃጢአትን ስለሚያደርጉ ሰዎች እውነቱ ምንድን ነው? ለ) ሮማ 6፡17 አንብብ። ቀድሞ ምን ነበርን?

ጥያቄ፡- ዮሐንስ 6፡44 አንብብ። አንድ ሰው ወደ ክርስቶስ መምጣት የሚችለው ምን ሲሆን ነው? 

ሦስተኛው በተፈጥሮአችን ኃጢአተኞች ነን ማለት እግዚአብሔር በሕይወታችን ውስጥ ጣልቃ ገብቶ እንድናዳምጠውና መልስም እንድንሰጠው ካላደረገን በስተቀር እኛ በዛ ኃይላችን ይህን ማድረግ አንችልም ማለት ነው። በኤፌሶን 2፡1 ውስጥ ጳውሎስ ለኤፈሶን አማኞች ሲጽፍ፥ እነርሱም ሆኑ ሁሉም ሰው ወደ ክርስቶስ ከመምጣታቸው በፊት በመተላለፉና በኃጢአታቸው ምክንያት ሙታን እንደ ነበሩ ይነራቸዋል። ለቀች ሁሉ በመተላለፉቸውና በኃጢአታቸው ሰበብ ስለ ሞቱ ጳውሎስ አየርን የሚገዛ ብሎ የተናገረለትንና በማይታዘዙት ውስጥ የሚሠራውን የሰይጣንን መንገድ ይከተላሉ። ስለዚህ ክርስቶስ የተላዩ ሰዎች ሁሉ በመንፈሳቸው የሞቱ ናቸው፡ ልክ በአካል የሞቱ ሰዎች ማንም ሰው ቢናገራቸው መልስ መስጠት እንደማይችሉ ሁሉ፥ በመንፈሳቸውም የሞቱ ላት ለእግዚአብሔር ድምፅ መልስ ሊሰጡ አይችሉም። በመሆኑም መንፈሳዊ መልስ ለመለስ ብቁዎች አይደሉም። ለለዚህም የሰይጣንን መንገድ ይከተላሉ። እኛም ከኃጢአት ጋር ስለ ተወለድንና በመንፈስም የሞትን ስለሆነ ለእግዚአብሒር ምላሽ መስጠት ያጻተናል። በዮሐንስ 34 ሁላችንም የኃጢአት ባሪያዎች ነን ይላል። እንዲሁም ሮሜ 6፡17 አሁን በክርስቶስ የሚያምኑቱ እስቀድሞ ን የኃጢአት ባሪያዎች እንደ ነበሩ ያስረዳል። እንዲህ ማለትም ሰዎች ሁሉ የኃጢአት ባሪያዎች ሆነው ተወልደዋል ማለት ነው። ባሪያዎች የሆኑ ሁሉ ደግሞ የፈለጉትን መሥራት አይችሉም። ስለዚህ የጌቶቻቸውን ፈቃድ ብቻ ይፈጽማሉ፡ ከኃጢአት ጋር ስለ ተፈጠርን ከኃጢአት በስተቀር ሌላ መሥራት አንችልም። በኃጢአት ቀንበር የታሰርን በመሆናችንም እዚእብሔር ፈቃዱ ሆኖ በሕይወታችን ውስጥ ጣልቃ ገብቶ ነፃ ካላወጣንና ወደ እርሱ እንድንመጣ ካላደረገን በስተቀር በገዛ ራሳችን ኃይልና ችሎታ ወደ እርሱ ልንመጣ ከቶ አንችልም። በዮሐንስ 6፡44 አብ የሳበው ካልሆነ በስተቀር፥ ማንም ሰው ወደ ኢየሱስ ሊመጣ እንደማይችል ይናገራል። በተፈጥር ከኃጢአት ጋር ከመወለዳችን የተነሣ በገዛ ራሳችን ኃይልና ችሎታ ወደ ኢየሱስ ልንመጣ አንችልም። ስለሆነም እግዚአብሔር በቅድሚያ ጣልቃ ገብቶ ወደ ራሱ ሊስበን ይገባል። 

2.4 ማጠቃለያ- ሙሉ ለሙሉ ተበላሽተናል 

ሰዎች በኃጢአት ተወልደዋል፥ በባሕሪያቸው ኃጢአተኞች ናቸው ሲባል ምን ማለት ነው? እንዲህ ማለት በምጀመሪያ፥ እግዚአብሔርን ለማስደሰት በራሳቸው ምንም ሊያደርጉ አይችሉም፥ ወይም ከእግዚአብሔር ጋር ራሳቸውን ሊያስታርቁ አቅም የላቸውም ማለት ነው። ሁለተኛው ደግሞ መንፈሳዊ የሆኑ ነገሮችን ሊገነዘቡ አይችሉም ማለት ነው። ሦስተኛው ደሞ፥ የኃጢአት ባሪያዎች ሆነው፥ በኃጢአት የሞቱ ስለሆኑ እግዚአብሔር ራሱ ካልፈቀደላቸውና ለእርሱ ምላሽ እንዲሰጡ ካልፈለገ በስተቀር በራሳቸው ኃይልና ፈቃድ ይህን ሊያደርጉ አይችሉም።  

«ምሉዕ ብልሽት» ሲባል ሰዎች በኃጢአት መወለዳቸውንና የለበሱት የኃጢአት ተፈጥሮ የመሆኑን እውነታ ለማብራራትም ይሆናል። ስለዚህ «ምሉዕ ብልሽት» ማለት፥ ሰዎች እዚእብሔር ወደ ራሱ ክለሳባቸው በስተቀር፥ እርሱን ሊያስደስቱ፥ የእርሱ የሆነውን ሁሉ ሊነዘቡ እንደዚሁም ለጥሪው መልስ ሊሰጡ ይሳናቸዋል ማለት ነው። «ምሉ ብልሽት» ሊባል፥ ያልዳኑ ሰዎች መልካምና ክፉ ስለሆኑ ነገሮች ምን፡ አይሰማቸውም ማለት አይደለም፡ ባለፈው ሳምንት 7 215 ባጠናንበ ጊዜ ያልዳኑ ሰዎች እንኳን ክፉ ነገር ሲሠሩ ሕሊናቸው እንደሚወቅሳቸው መልካም በሚያደርጉበት ጊዜ ደግሞ ይኸው ሕሊናቸው እንደሚፈርድ አይተናል። ያልዳኑ ሰዎች መልካም ሆነ ክፉ ነገር የሚሰማቸውም ናቸው። «ምሉዕ ብልሽት» ማለት ያልዳኑ ሰዎች እንደፈለጋቸው ኃጢአተኞች ናቸው ማለት አይደለም። ብዙ ያላመኑ ሰዎች ለሌሎችም የሚተርፍ አያለ በጎ ተግባራትን የሚያከናውኑ ደጋግ ሰዎች ናቸው። ሆኖም እነዚህ መልካም ተግባርቻቸው እግዚአብሔርን የሚያስደንቁና ከእግዚአብሔር ጋር የሚያቀራርቧቸው አይደሉም። ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች አሁንም ኃጢአተኞች ሲሆኑ፥ ብዙ ኃጢአትም ይሠራሉ። መልካም ምግባሮቻቸውም ሁሉ በእግዚአብሔር ዓይን ፊት እንደ መርገም ጨርቅ ናቸው፡ በመዉረሻውም «ምሉዕ ብልሽት» ሊባል ያላመኑ ሰዎች ያገኙትን ኃጢአት ሁሉ ይፈጽማሉ ማለትም አይደለም። ብዙ ያልዳኑ ሰዎች በርካታ አሰቃቂ ኃጢአታችን ከመሥራት ይቆጠባሉ። ለምሳሌ ያህል፥ አይገድሉም፥ አያመነዝሩም፥ ታዲያ እነዚህን የክፉ ኃጢአተችን ባይፈጽሙም በኃጢአት ከመወለዳቸውም በላይ አሁንም ቢሆን ኃጢአተኞች ናቸው። «ምሉዕ ብልሽት» ማለት፡ ሁሉም ሰው በኃጢአት የተወለደ የኃጢአት ባሕርይ ያለው ማለት ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር በሕይወታቸው ጣልቃ ገብቶ ካልለወጣቸው በስተቀር እግዚአብሔርን ሊገነዘቡት፥ ሊያስደስቱትና መልስ ሊሰጡ ወይም ራሳቸውን በፍላጎታቸው ከእግዚአብሔር ጋር ሊያቀራርቡ 

አይችሉም። 

ጥያቄ፡- ሀ) በአካባቢአችሁ የሚኖሩ ሰዎች ጥያቄዎች መልሳቸው ምንድን ነው? እግዚአብሔርን እንዴት ታለደስቱታላችሁ? ከእርሱስ ጋር እንዴት በትክክል ትቀራረባላችሁ? እንዴትስ ልታውቁት ትችላላችሁ? እንዴትስ መልስ ትሰጣላችሁ? ላ) ስለ «ምሉዕ ብልሽት» የተማርነውን ትምህርት መሠረት ካደረግን ሁሉም ሰው ምን ዓይነት እጻኝ የሚሻ ይመስላችኋል? 

ዛሬ አብዛኛዎቹ ሰዎች በመልካም ሥራቸው እግዚአብሔርን የሚያስደስቱ ይመስላቸዋል። እግዚአብሔርንም ሊገልጥላቸው የሚችል በቂ ንዛቤ በውስጣቸው ያላቸው ይመስላቸዋል። ከዚህም በስተቀር ለእግዚአብሔር ቢታዘዙ ጥሪውን ሰምተው ወደ እርሱ ሊመጡና ለጥሪውም ምላሽ ሊሰጡ የሚችሉ ሆኖ ይታያቸዋል። እነዚህንም ሁሉ በሥርዓት ለመፈጸም የሚያስችላቸው መድኅን እንደሚያስፈልጋቸው አያምኑም። ነገር ግን ኃጢአተኞች ሆነን በመወለዳችን፥ በራሳችን ተነሣሥተን እግዚአብሔርን ማስደሰት፥ እንዲሁም መንፈሳዊ እውነትን መገንዘብና ለእግዚአብሔርም ጥሪ መልስ መስጠት እንደሚያቅተን ቀደም ሲል ተመልክተናል። ማንም ቢሆን እግዚአብሔር አስቀድሞ ወደ እርሱ ዘንድ ካልመጣ በስተቀር ወደ እግዚአብሔር አይመጣም። ሰዎች ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲታረቁና ደስ እንዲያሰኙት ማድረግ የሚችል አዳኝ ያስፈልጋቸዋል። በተጨማሪም ሁሉም ሰው መንፈሳዊ እውነት እንዲገዘብና ለእግዚአብሔርም ጥሪ መልስ እንዲሰጥ ማድረብ የሚችል አዳኝ ያስፈልገዋል። እንዲሁም ሰዎች ሁሉ ሕያው የሚያደርጋቸውንና ከኃጢአት ነፃ የሚያወጣቸውን ለእግዚአብሔር ጥሪ ምላሽ ይሰጡ ዘንድ አዳኝ ይላሉ። ነገር ን በዓለማችን ውስጥ አብዛኛዎቹ ሰዎች ኃጢአተኞች ሆነው መወለዳቸውንም ሆነ በተፈጥሮ ኃጢአተኞች እንደሆኑ አያምኑም። ከዚህ የተነሣ አዳኝ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን አይገነዘቡም ወይም አያምኑም። 

ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

Leave a Reply

Discover more from

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading