የሕይወት እንጀራ

“አብርሃም ለመሥዋዕት ያቀረበው እስማኤልን ነው፡፡”

እስልምናን ዋጋ ለማሳጣት ሲባል ሆን ተብሎ መጽሐፍ ቅዱስ ተለውጧል ለሚለው ክስ ሙስሊሞች እንደ ማስረጃነት ከሚቆጥሯቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች መካከል አንዱ አብርሃም ልጁን እንዲሰዋ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠው መለኮታዊ ትዕዛዝን የተመለከተ እንደሆነ በርካታ ሙስሊሞችን ያስማማል፡፡ በርካታዎቹ ሙስሊሞች አብርሃም እንዲሰዋ የተጠየቀው ልጅ እስማኤል እንደሆነ አጥብቀው ይናገራሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ ይህ ልጅ ይስሃቅ እንደሆነ ይናገራል፣ (ዘፍጥረት 22፡9፣ ዕብራዊያን 11፡17 እና ያዕቆብ 2፡21)፡፡ 

ይህ ታሪክ በቁርአን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ የተጠቀሰ ሲሆን ይህም ክፍል አብርሃም በጠየቀው በሚከተለው ጥያቄ እንዲህ ብሎ ይጀምራል፡-

  • ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን ልጅ ስጠኝ፡፡ ታጋሽ በሆነ ልጅም አበሰርነው [So we gave him the good news]፡፡ ከርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ፣ ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፤ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ? አለው፤ አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፤ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ፣ አለ፡፡ ሁለቱም ትዕዛዙን በተቀበሉና በግንባሩም ጎን ላይ በጣለው ጊዜ (የሆነው ሆነ)፡፡ ጠራነውም፤ (አልነው)፡- ኢብራሂም [አብርሃም] ሆይ! ራእዩን በእውነት አረጋገጥክ፤ እኛ እንደዚሁ መልካም ሰሪዎችን እንመነዳለን፡፡ ይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፡፡ በታላቅ እርድም (መሥዋዕት) ተቤዠነው፡፡ 

ሱረቱ-አል-ሷፍፋት (37)፡100-107

“O my Lord, grant me a righteous (son)!” So We gave him the good news of a boy ready to suffer and forbear. Then when (the son) reached (the age of) (serious) work with him, he said, “O my son, I see in a vision that I offer thee in sacrifice. Now see what is thy view!” (The son) said, “O my father! Do as thou art commanded. Thou will find me if God so wills one practicing patience and constancy!” So when they had both submitted their wills (to God) and he had laid him prostrate on his forehead (for sacrifice), We called out to him, “O Abraham, thou hast already fulfilled the vision!” Thus indeed do We reward those who do right. For this was obviously a trial-and We ransomed him with a momentous sacrifice.

በቁርአን ውስጥ ስለምናወራው መሥዋዕት በማውሳት ብቸኛ የሆነውን ይህን ጥቅስ ልብ ብለን እንመልከት፡፡ በዚህ ጥቅስ ውስጥ የልጁ ስም አልተጠቀሰም! የልጁ የልደት ዜና ‹‹መልካም ዜና›› ተብሎ አስቀድሞ የተነገረለት ልጅ እንደሆነ ግን በእርግጠኝነት ፍንጭ ይሰጣል፡፡ አንድ ሰው ቁርአንን ከዳር እስከ ዳር አገላብጦ ቢያነብ (ቢቀራ) የትም ቦታ ላይ ስለ እስማኤል ልደት ተጠቅሶ አይመለከትም፡፡ ስለ እስማኤል ጥቂት የተባለ ነገር ቢኖርም ስለ እናቱ ማንነትም ሆነ ስለልጆቹ ቁርአን ምንም አይናገርም፡፡ እስማኤል አጋር የምትባል እናት እንዳለውና 12 ልጆችም እንደነበሩት መረጃ የምናገኘው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነው (ዘፍጥረት 25፡12-17)፡፡ ከላይ በቀረበው የቁርአን ጥቅስ ውስጥ ስለ ሰፈረው ‹‹መልካም ዜና›› ጉዳይ በቁርአን ውስጥ ሌላ ምእራፍ ላይ ሰፍሮ የምናገኘውን ጥቅስ እስቲ አብረን እንመልከት፡፡ ይህ ክፍል ስለ ይስሃቅና ስለ እናቱ ሳራ የሚከተለውን ያስነብበናል፡-

  • የተከበሩት የኢብራሂም [አብርሃም] እንግዶች ወሬ መጥቶሃልን? በእርሱ ላይ በገቡና ሰላም ባሉ ጊዜ (አስታውስ)፤ ሰላም፤ ያልታወቃችሁ ሕዝቦች ናችሁ፤ አላቸው፡፡ ከእነረሱ መፍራትንም በልቡ አሳደረ፡፡ አትፍራ አሉት፤ በዐዋቂ ወጣት ልጅም አበሰሩት፡፡ ሚስቱም እየጮኸች መጣች፤ ፊቷንም መታች፤ መካን አሮጊት ነኝ አለችም፡፡ እንደዚህስ ጌታሽ ብሏል እነሆ እርሱ ጥበበኛ ዐዋቂ ነውና አሏት፡፡

ሱረቱ አል-ዛሪያት (51)፡24፣25፣28-30

Has the story reached thee of the honored guests of Abraham? Behold, they entered his presence and said “peace!” He said “Peace…” They said, “Fear not,” and they gave him glad tidings of a son endowed with knowledge. But his wife came forward (laughing) aloud; she smote her forehead and said, “A barren old woman!” They said, “Even so has thy Lord spoken; and He is full of wisdom and knowledge.”

ከዚህ በተጨማሪ፣ ስለ አብርሃምና ይስሃቅ ማጠቃለያ የሚሆንና ስለ መሥዋዕቱ የሚያወራ ከቁርአን አንድ አንቀጽ እንደሚከተለው እናነባለን፡-

  • ሰላም በኢብራሂም [በአብርሃም] ላይ ይሁን፡፡ እንደዚሁ መልካም ሰሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን [እንሸልማለን]፡፡ እርሱ በእርግጥ ካመኑት ባሮቻችን ነው፡፡ በኢስሐቅም [በይስሃቅም] አበሰርነው፤ ከመልካሞቹ ነቢይ ሲሆን፡፡ በእርሱና በኢስሐቅ ላይም ባረክን፤ ከሁለቱም ዘሮች በጎ ሠሪ አለ፤ ለነፍሱ ግልጽ በዳይም አለ፡፡ 

ሱረቱ አል-ሷፍፋት (37)፡109-113

Peace and salutation to Abraham! Thus indeed do We reward those who do right. For he was one of Our believing Servants. And We gave him the good news of Isaac-a prophet-one of the righteous. We blessed him and Isaac.

‹‹በአዋቂ ወጣት ልጅም አበሰሩት›› የሚለውንና ‹‹በይስሃቅም አበሰርነው›› የሚሉትን ዐረፍተ-ነገሮች ያስተውሉ፡፡ በቁርአን ውስጥ እንዲህ የመሰሉት አገላለጾች ለእስማኤል ተሰጥተው በየትም ቦታ ላይ አናነብም፡፡ እንግዲያውስ፣ በሱራ 37፡100-107 ውስጥ እንደተገለጠው የመልካም ዜና ብሥራት የተባለለት ልጅና ለመሥዋዕት ሊቀረብ የተዘጋጀው ይስሃቅ እንጂ እስማኤል እንዳልነበረ አሁን ግልፅ ሊሆን ይገባል፡፡ ይህንኑ እውነት ነው መጽሐፍ ቅዱስ በማያሻማ መልኩ የሚናገረው፡፡በዚህ ርስሰ-ጉዳይ መነሻ ላይ፣ በርካታ ሙስሊሞች ለመሥዋዕት የቀረበው ልጅ እስማኤል ነው ብለው እንደሚያምኑ ተገልጿል፡፡ ይህንን የሚያምኑት ግን ሁሉም ሙስሊሞች እንዳልሆኑ ልብ ይሉዋል! ቁርአንን በጥንቃቄ ያጠኑ ሙስሊሞች መረጃዎቹ ሁሉ ወደ ይስሃቅ እንደሚጠቁሙ ይገነዘባሉ፡፡ ዮሱፍ አሊ፣ በዓለም ታዋቂ በሆነው የቅዱስ ቁርአን ትርጉምና ማብራሪያ፣ ገጽ 1204፣ ማስታወሻ 4096 ላይ የሚከተለውን አስፍሯል፡- ‹‹…በሙስሊሞች ወግ መሠረት (ምንም እንኳን በአንድ ድምጽ ተቀባይነት ያገኘ ባይሆንም) … ይህ ልጅ የአብርሃም የበኩር ልጅ የሆነው እስማኤል ነበር፡፡›› ‹‹በሙስሊሞች ወግ መሠረት›› የሚለውንና ‹‹በአንድ ድምጽ ተቀባይነት ያገኘ ባይሆንም›› የሚሉትን ሐረጎች ልብ ይሏል፡፡ ለመሥዋዕት የቀረበው ልጅ እስማኤል ስለ መሆኑ በማስረጃነት የቀረበው፣ ቁርአን ስላለመሆኑ ግንዛቤ የተወሰደ ይመስለናል! ከዚህ በተጨማሪ ቁርአን የመጣው ከእርሱ ቀድሞ የመጡትን ቅዱሳት መጻሕፍቶች ለማስረገጥ (ለማረጋገጥ) እንጂ ሊቃረናቸው አለመሆኑን ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡ ቁርአን ይህን ክፍል በተመለከተ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይስማማል፡፡ የዚህ ክፍል አሳብ የሚጋጨው ከቁርአኑ ሃሳብ ጋር ሳይሆን ከሙስሊሞች ወግ ጋር መሆኑን ልብ ልንል ይገባል፡፡

የጌታ ጸጋ ከእርስዎ ጋር ይሁን፤ ሀሳብዎን ለመስማት ዝግጁ ነን።

Discover more from የሕይወት እንጀራ

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading