“ሙሐመድ እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ ነው፡፡”

  • ከወንድሞቻቸው መካከል እንደ አንተ ያለ ነቢይ አስነሣላቸዋለሁ፤ ቃሌንም በአፉ አደርጋለሁ፣ ያዘዝሁትንም ቃል ሁሉ ይነግራቸዋል፤

ዘዳግም 18፡18 

ይህንን ጥቅስ በተመለከተ በርካታ ሙስሊሞች እንዲህ ይላሉ፡- እዚህ ላይ እግዚአብሔር የይስሃቅ ዘር ለሆኑት እስራኤላውያን እየተናገረ ስለሆነ፣ ‹‹ከወንድሞቻቸው መካከል›› የሚለው ሐረግ ስለ እስማኤል ትውልድ/ዘር ነው የሚያወራው ምክንያቱም እስማኤል የይስሃቅ ወንድም ነውና ይላሉ፡፡ ስለዚህ፣ ይላሉ የክርክሩን ምክንያታዊነት ሲያስረዱ፣ ስለዚህ ሊመጣ የተተነበየለት ‹‹እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ›› ሊያመለክት የሚችለው ሙሐመድን ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም ከይስሃቅ ወንድም ከእስማኤል ዘር የተገኘ ታላቅ ነቢይ እሱ ብቻ ነውና፣ እንደ ሙሴ ሁሉ ሙሐመድ የእግዚአብሔርን ሕግ መስርቷል ተአምራትንም አድርጓልና ይላሉ፡፡

በመጀመሪያ፣ እስቲ ‹‹ከወንድሞቻቸው መካከል›› ስለ ሚለው ሀረግ እንመልከት፡፡ እስራኤላውያን ንጉሥ ለመምረጥ ሲያስቡ የአነጋገሱን ደንብ እግዚአብሔር ካሳወቀበትና ከላይ የተጠቀሰው ሀረግ ጥቅም ላይ ከዋለበት የሚከተለው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የሀረጉን ትርጉም ይበልጥ መረዳት እንችላለን፡፡

  • አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በገባህ፣ በወረስሃትም ጊዜ፣ በተቀመጥህባትም ጊዜ። በዙሪያዬ እንዳሉት አሕዛብ ሁሉ በላዬ ንጉሥ አነግሣለሁ ስትል፣ አምላክህ እግዚአብሔር የመረጠውን በላይህ ታነግሣለህ፤ ከወንድሞችህ መካከል የሆነውን በአንተ ላይ ንጉሥ ታነግሣለህ፤ ወንድምህ ያልሆነውን ከሌላ ወገን ሰው በላይህ ንጉሥ ታደርግ ዘንድ አይገባህም። 

ዘዳግም 17፡14፣15

በመካከለኛው ምሥራቅ ጥንታዊ ልማድ ውስጥ የነበረውን ሁኔታ በቅጡ የሚያውቅ ማንኛውም ሙስሊም፣ እስራኤላውያን ንጉሣቸውን ከእስማኤል ዘር መካከል ይፈልጋሉ ብሎ እንደማያስብ እርግጠኞች ነን፡፡ ስለዚህ ‹‹ከወንድሞቻቸው መካከል›› የሚለው ሀረግ ትርጉም እሥራኤላዊ የሆነ ወንድም ማለት ነው፡፡

በሁለተኛ ደረጃ፣ ሙሐመድን ከሙሴ ጋር ለማነጻጸር የተደረገውን በተመለከተ ዘዳግም 34፡10-12 ላይ የተገለጸውን በጥንቃቄ ማንበብ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ ክፍል ስለ ነቢዩ ሙሴ ማንነት አጭርና ግልጽ ማስረጃ የሚሰጥና ወደፊት ከሚመጣው ነቢይ የሚጠበቀውን የሚያወሳ ነው፡፡

  • እግዚአብሔርን ፊት ለፊት እንዳወቀው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ ከዚያ ወዲህ በእሥራኤል ዘንድ አልተነሣም፤ በግብፅ ምድር በፈርዖንና በባሪያዎቹ ሁሉ ላይ በምድሪቱም ሁሉ ላይ ምልክትንና ድንቅን ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ላከው ያለ፣ በእሥራኤል ሁሉ ፊት በጸናች እጅ ሁሉና በታላቅ ማስደንገጥ ሁሉ እንዳደረገው እንደ ሙሴ ያለ አልተነሣም። 

ዘዳግም 34፣10-12

ከዚህ የመጽሐፍ ክፍል የምንረዳቸው ነገሮች 1) ሙሴ እሥራኤላዊ ነበር፣ 2) እግዚአብሔርን ፊት ለፊት ያወቀ ነበር፣ ይህም ማለት ያለማንም መካከለኛ እግዚአብሔር በቀጥታ የተናገረው ሰው ነበር፣ እና 3) አስደናቂ ተአምራትን ያደረገ ሰው ነበር፡፡ 

ሙስሊሞች ሙሐመድ የዘዳግም 18፡18 ፍጻሜ ነው ይላሉ፡፡ ክርስቲያኖች ደግሞ ‹‹እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ›› ከመሲሁ ኢየሱስ በቀር ሌላ ሊሆን አይችልም ሲሉ የሚከተለውን ንጽጽር በማስረጃነት ያቀርባሉ፡-

ሙሴኢየሱስሙሐመድ

ከእስራኤላውያን መካከል የተገኘ ነቢይ

ከእስራኤላውያን መካከል የተገኘ ነቢይከይሁዳ ነገድ (ማቴዎስ 1፡3፣ ሉቃስ 3፡33)

ከአረቦች መካከል የተገኘ ነቢይ(ሱራ 46፡12፣ 36፡6፣34፡43፣44

ከእግዚአብሔር መገለጥን በቀጥታ የተቀበለ (ሱራ 4፡164፣ ዘፀአት 33፡11

ከእግዚአብሔር መገለጥን በቀጥታ የተቀበለ (ዮሐንስ 12፡49-50፣ 14፡10)

መገለጥን ከመላኩ ገብርኤል (በሁለተኛ ወገን) የተቀበለ (ሱራ 2፡97)

ተአምራትን ያደረገ (ሱራ 2፡50 ባሕር፣ ሱራ 2፡57 መና)

ተአምራትን ያደረገ (ሱራ 3፡49) ማቴዎስ 8፡27 ባሕር፣ ዮሐንስ 6፡11-14 መና

ተአምራት አላደረገም(ሱራ 6፡37፣ ሱራ 28፡48)

ከለይ ከተገለጠው በተጨማሪ፣ አዲስ ኪዳን የዘዳግም 18፡8 ትንቢት በመሲሁ ኢየሱስ ተፈፃሚነት ማግኘቱን ያረጋግጣል፡፡ ሐዋሪያት ሥራ 3፡17-26 በተለይም ቁጥር 22 ያንብቡ፡- ‹‹ሙሴም ለአባቶች፡- ጌታ አምላክ እኔን እንዳስነሳኝ ነቢይን ከወንድሞቻችሁ ያስነሣላችኃል፣…››፡፡

በመጨረሻም ሱረቱ አል-ቀሶስ (28፡48) የሚለውን ልብ እንበል፡-

  • እውነቱም ከእኛ ዘንድ በመጣላቸው ጊዜ ለሙሳ [ለሙሴ] የተሰጠው [ምልክት] ብጤ [ለሙሐመድ] አይሰጠውም ኖሯልን? አሉ፤ …

But (now) when the Truth has come to them from Ourselves, they say, “why are not (signs) sent to him (Muhammed) like those which were sent to Moses?”

ከዚህ ጥቅስ የምንረዳው፣ ሙሐመድ ራሱን እንደ ሙሴ ያለ አድርጎ አለመቁጠሩን ቁርአን ራሱ ማስረጃ ሊሆን እንደሚችል ነው!

Leave a Reply

Discover more from

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading