“ኢየሱስ ተራ ነቢይ ብቻ ነው፡፡”

ኢየሱስ በቁርአን ውስጥ ያለውን ልዩ ስፍራ ለመሸፈን በርካታ ሙስሊሞች የሚከተለውን ከቁርአን ይጠቅሳሉ፡-

  • የመርየም ልጅ አልመሲሕ፣ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፣ እናቱም በጣም እዉነተኛ ናት፤ (ሁለቱም) ምግብን የሚበሉ ነበሩ፤ አንቀጾችን ለነርሱ (ለከሓዲዎች) እንዴት እንደምናብራራ ተመልከተ፣ ከዚያም (ከዉነት) እንዴት እንደሚመለሱ ተመልከት፡፡ 

ሱረቱ አል-ማኢዳህ (5)፡75

O people of the Book (Jews and Christians)! Commit no excesses in your religion; nor say for God aught by the truth. Christ Jesus the son of Mary was (no more than) an apostle of God, and His Word, which He bestowed on Mary, and a Sprit proceeding from Him.

እርግጥ ነው ኢየሱስ በሰውነቱ እንደ ሌሎቹ ነቢያት ከሰው ዘር ሥጋን የነሳ/የወሰደ/የተዋሃደ ነው፡፡ ነገር ግን በዚህ የሰው ሥጋ ውስጥ መለኮታዊ የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ማደሩን የሚናገሩትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ትምህርት ልንዘነጋቸው አንችልም፡፡ (ዮሐንስ 1፡14፣ ቃል ሥጋ ሆነ በመካከላችንም አደረ፡፡) ምንም እንኳን ይህንን የኢየሱስን ሰውነትና መለኮታዊነት ምስጢር እዚህ ላይ ለማብራራት ባንሞክርም እውነታውን ግን ቅዱሳት መጻሕፍቱ ያረጋግጣሉ፡፡ ቁርአን ሳይቀር የኢየሱስን ሰውነትና መለኮታዊነት ያሳያል፡፡ ለአብነት የሚከተለውን ከቁርአን እናንብብ፡-

  • እላንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፣ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ፣ የመርየም [የማሪያም] ልጅ አልመሲሕ ዒሳ [መሲሁ ኢየሱስ] የአላህ መልክተኛ ወደ መርየም የጣላት (የኹን) ቃሉም ከርሱ የኾነ መንፈስም ብቻ ነዉ፤ ነዉ …

ሱረቱ አል-ኒሳእ (4)፡171

O people of the Book (Jews and Christians)! Commit no excesses in your religion; nor say for God aught by the truth. Christ Jesus the son of Mary was (no more than) an apostle of God, and His Word, which He bestowed on 

Mary, and a Sprit proceeding from Him.

ይህ ክፍል – እግዚአብሔርን፣ ማርያምን እና ኢየሱስን እንደ ሶስት አማልክት በመቁጠር ኢየሱስን ከሦስቱ አማልክት አንዱ ነው ይሉ የነበሩ በዘመኑ ይኖሩ የነበሩ አንዳንድ መናፍቅ ‹‹ክርስቲኖች›› ያስተምሩ የነበሩትን የኑፋቄ ትምህርት ( የኑፋቄ ትምህርት፡- ከትክክለኛ እምነት ጋር የማይስማማ ትምህርት ማለት ነው) ለመቃወም ከሚያስተላልፈው የግሳጼ መልዕክት ውጪ ቁርአን ለኢየሱስ ልዩ ስፍራ የሚሰጥና መለኮትነቱንም፣ (ኢየሱስ ‹‹የእሱ (የእግዚአብሔር) ቃል›› በማለትና ‹‹መንፈስም ብቻ ነው››) በማለት የሚያረጋግጥ መሆኑንም ያሳያል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስም በአዲስ ኪዳን ላይ ኢየሱስን ‹‹የእግዚአብሔር ቃል›› በማለት ይጠራዋል፡- 

  • በደምም የተረጨ ልብስ ተጐናጽፎአል፣ ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ተብሎአል።› 

ራዕይ 19፡13

ይህ ስያሜ በቀላሉ መታየት የለበትም፡፡ በርካታ ሙስሊሞች የእግዚአብሔር ቃል የማይፈጠርና የማይሞት እንደሆነ ይቀበላሉ፡፡ እርሱ፣ ማለት ቃሉ፤ ‹ከዘላለም ለዘላለም የሚኖር ዘላለማዊ ነው› ይላሉ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ አይነት ባሕሪ እንዳለው ካላደናገረ፣ እንግዲያው መለኮታዊ ባሕሪውም ግር ሊያሰኝ አይገባም!

ከላይ በሰፈረው ጥቅስ ውስጥ ‹‹መንፈስም ብቻ ነው›› የሚለው ሃረግ አረቢኛ ቅጂው ruh-un min hu የሚል ሲሆን፣ ይህው ሃረግ በሌላ የቁርአን ክፍል ላይ ጥቅም ላይ ውሎ እናገኛለን፡-

  • በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑትን ሕዝቦች አላህንና መልክተኛውን የሚከራከሩትን ሰዎች፣ አባቶቻቸዉ ወይም ልጆቻቸዉ፣ ወይም ወንድሞቻቸዉ ወይም ዘመዶቻቸዉ ቢኾኑም እንኳ የሚወዳጁ ኾነው አታገኛቸዉም፤ እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ እምነትን ጽፏል፤ ከርሱም በኾነ መንፈስ ደግፏቸዋል፤ ከሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸዉ ዘውታሪዎች ሲኾኑ ያገባቸዋል፣ አላህ ከነርሱ ወዷል፡፡ ከርሱም ወደዋል፣ እነዚያ የአላህ ሕዝቦች ናቸው፣ ንቁ የአላህ ሕዝቦች እነሱ ምኞታቸውን የሚያገኙ ናቸው፡፡

ሱረቱ አል-ሙጃደላህ (58)፡22

He (God) has written faith in their hearts, and strengthened them with a spirit from Himself.

በ ኤ. ዩሱፍ አሊ የተጻፈው፣ የቅዱስ ቁርአን ትርጉምና ማብራሪያ የግርጌ ማስታወሻ ቅጥር 5365 ‹‹ከእርሱም በሆነ መንፈስ›› ስለሚለው ሀረግ ሲያብራራ ይህንን መንፈስ ‹‹በሰው ቋንቋ የአላህን ማንነትና ባሕርይ በበቂ ሁኔታ ለመበየን እንደማንችለው አይነት መለኮታዊ መንፈስ›› በማለት ይገልጸዋል፡፡ 

ካላይ በተገለጸው መሠረት ቁርአን ኢየሱስን ለመግለጥ በሱረቱ አል ኒሳእ (4)፡171 ላይ የተጠቀመው አጠቃቀም፣ ኢየሱስ አንድ ተራ ነቢይ ሳይሆን ከዛ በላይ ስለመሆኑ በግልጽ ያሳየናል፡፡

ስለ ኢየሱስ ልዩ መሆን ቁርአን የሚያመለክታቸው ሌሎች በርካታ ጥቅሶች በመኖራቸው እነዚህን ቸል ልንላቸው አይገባም፡፡ እስቲ ከዚህ በታች የሰፈሩትን ጥቅሶች በአንክሮ እንመርምራቸው፡-

ሀ. በተአምራት ከድንግል ተወለደ

  • (በጋብቻ) ሰው ያልነካኝ ኾኜ አመንዝራም ሳልኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል! አለች [ማሪያም]፡፡ አላት፡- (ነገሩ) እንደዚህ ነዉ፣ ጌታሽ፡- እርሱ በእኔ ላይ ገር ነዉ፣ ለሰዎችም ታምር ከኛም ችሮታ ልናደርገዉ (ይህንን ሠራን) የተፈረደም ነገር ነው አለ፣ (ነፋባትም)፡፡ ወዲያውኑም አረገዘችው፤ በርሱም (በሆድዋ ይዛው) ወደ ሩቅ ስፍራ ገለል አለች፡፡

ሱረቱ- መርየም (19)፡20፣21፣22

She (Mary) said: “How shall have a son, seeing that no man has touched me, and I am not unchaste”

He (Gabriel) said: “So (it will be): Thy Lord saith, ‘That is easy for Me.”

‹አዳምም (አደም) እኮ ተፈጥራዊ አባት የለውም› በማለት በዚህ ጥቅስ መነሻነት ብቻ ኢየሱስ እንደ ልዩ ሰው መወሰድ የለበትም የሚሉ አይጠፉም፡፡ እውነት ነው አዳም ምድራዊ አባት የለውም፤ ነገር ግን ይህ እንግዳ ነገር ሳይሆን የሚጠበቅ ጉዳይ ነው! ራሱ የመጀመሪያው የሰው ፍጥረት ከሆነ እንዴት አባት ሊኖረው ይችላል እዚህ ላይ ኢየሱስን በተመለከተ ያለው ጉዳይ ግን ከዚህ ፈፅሞ የተለየ ነው፡፡ ኢየሱስ ተራ ነቢይ ብቻ ቢሆን ኖሮ እንደማንኛውም ነቢይ ሊወልዱት የሚችሉ በመቶና በሺዎች የሚቆጠሩ ወላጆች በምድር ላይ በጊዜው ነበሩ፡፡ ነገር ግን ይህ ጉዳይ ለሰው ልጆች ሁሉ ልዩ ምልክት ነበረና እንደዚያ አልሆነም፡፡ እግዚአብሔር አለሙ በሞላ ኢየሱስ ከወንድ ዘር ያልተገኘ መሆኑን እንዲያቁ ወዷል፡፡ እርሱ ከላይ፣ ከመለኮታዊ ዘር ነውና፡፡ 

ለ. የተቀደሰ ሕይወት ኖረ

  • እኔ ንጹሕን ልጅ [ቅዱስ ልጅ] ለአንቺ ልሰጥሽ የጌታሽ መልክተኛ ነኝ አላት፡፡

ሱረቱ- መርየም (19)፡19

He (Gabriel) said: “Nay, I am only a messenger from thy Lord, (to announce) to thee the gift of a holy son.” 

ኢየሱስ በእርግጥ ቅዱስ ልጅ ነበር፡፡ አመጣጡ ከሰው ዘር ሳይሆን ከእግዚአብሔር ስለነበር በልደቱ ጊዜ ኢየሱስን ሰይጣን ፈፅሞ ሊያገኘው አልቻለም፡፡ በምድር ላይ የነበረውን የሕይወቱን ዘመን በሞላ ያለ ምንም እንከን በፍፁም ንፅህና አሳልፏል፡፡ በርካታ ሙስሊሞች፣ ‹ሌሎች ነቢያትም በምድር ላይ ያለምንም ነቀፋ ይኖሩ ስለነበር የኢየሱስ ሕይወት ከእዚህ አንጻር ልዩ ተደርጎ ሊታይ አይችልም› ብለው ይከራከራሉ፡፡ ነገር ግን ቁርአንን በወጉ ብንመረምር ይህ ክርክር ትክክል እንዳልሆነ ማወቅ እንችላለን፡፡ ታላላቅ ነቢያት የሚባሉት ሳይቀሩ ፈጣሪን ስለበደሉ ምህረትን ከእርሱ ለምነዋል፡፡ የመበደላቸውና ይቅርታ የመጠየቃቸው ምክንያት ደግሞ ከኢየሱስ በቀር ነቢያት ሁሉ ከወንድ ዘር የተወለዱ የሰው ልጆች ብቻ በመሆናቸውና በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ኃጢአትን የሚሰሩ መሆናቸው ነው፡፡ 

የሚከተሉትን ምሳሌዎች ይመለከቱ፡-

  • [አደም/አዳምና ሔዋን]፡- ጌታችን ሆይ! ነፍሶቻችንን በደልን፣ ለኛ ባትምር ባታዝንልንም በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንኾናለን አሉ፡፡

ሱረቱ አል-አዕራፍ (7)፡23 

Adam (and Eve): They said: “Our Lord, we have wronged our own souls. If Thou forgive us not and bestow not upon us Thy mercy, we shall certainly be lost.”

  • [ኢብራሂም/አብርሃም]፡- ያም በፍርዱ ቀን ኀጢአቴን ለኔ ሊምር 

የምከጅለው ነው፡፡

ሱረቱ አል-ሹዐራ (26)፡82

Abraham: And who (God) I hope will forgive me my faults on the Day of Judgment.

  • [ሙሳ/ሙሴ]፡- ጌታዬ ሆይ! እኔ ለፍሴን በደልኩ፣ ለኔም ማር አለ፣ ለርሱም ምሕረት አደረገለት፣ እርሱ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡

ሱረቱ አል-ቀሶስ (28)፡16

Moses: He prayed: “O my Lord! I have indeed wronged my soul! Do Thou then forgive me!”

  • [ዳውድ/ዳዊት]፡- ሴት በግህን ወደ በጎቹ (ለመቀላቀል) በመጠየቁ በእርግጥ በደለህ፣ ከተጋሪዎችም ብዙዎቹ ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ወሰን ያልፋሉ፣ እነዚያ ያመሉትና መልካሞችን የሠሩት ብቻ ሲቀሩ፣ እነሱም በጣም ጥቂቶች ናቸው አለ፣ ዳውድም [ዳዊትም] የፈተንነው መኾኑን ዐወቀ፤ ጌታውንም ምሕረትን ለመነ፤ ሰጋጅ ኾኖ ወደቀም፣ በመጸጸት ተመለሰም፡፡

ሱረቱ ሷድ (38)፡24

David: and David gathered that We had tried him; he asked forgiveness of his Lord.

  • [ሱለይማን/ሰሎሞን]፡- ጌታዬ ሆይ! ለኔ ማር፣ ከኔ በኋላ ለአንድም የማይገባንም ንግሥና ስጠኝ፣ አንተ ለጋሱ አንተ ብቻ ነህና አለ፡፡

ሱረቱ ሷድ (38)፡35

Solomon: He said, “O my Lord! Forgive me…”

  • [ዩኑስ/ዮናስ]፡- እርሱም ተወቃሽ ሲኾን ዐሣዉ ዋጠዉ፣ እርሱ ለጌታዉ ከአወዳሾቹ ባልኾነም ኖሮ፣ እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ በሆዱ ዉስጥ በቆዬ ነበር፡፡

ሱረቱ አል-ሷፍፋት (37)፡142-144

Jonah: And he had done acts worthy of blame. Had it not been that he (repented and) glorified God, he would certainly have remained inside the fish…

  • [ሙሐመድ]፡- እኛ ላንተ ግልጽ የኾነን መክፈት ከፈትንልህ፡፡ አላህ ከኃጢአትህ ያለፈውንና የሚመጣውን ላንተ ሊምር ጸጋውንም ባንተ ላይ ሊሞላ ቀጥተኛውንም መንገድ ሊመራህ (ከፈተልህ)፡፡

ሱረቱ አል-ፈትሕ (48)፡1፣2

Muhammad: Verily We have granted thee (Muhammad) a manifest victory; that God may forgive thee thy faults of the past and those to follow.

  • እነሆ ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩንም ዕወቅ፤ ስለ ስሕተትህም ለምእምናንም ምሕረትን ለምን፣ አላህም መዘዋወርያችሁን መርጊያችሁንም ያውቃል፡፡

ሱረቱ ሙሐመድ (47)፡19

Know therefore that there is no god but God, and ask forgiveness for thy fault, and for the men and women who believe. 

ማንም ሰው ቁርአኑን በአግባቡ ቢመረምር በየትም ስፍራ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ለኀጢአቱ ይቅርታን ሲለምን አይመለከትም፡፡ የዚህ ምስጢር አሁን ግልፅ ሊሆንልን ይገባል፡፡ ኢየሱስ ቅዱስ፣ የማይሳሳት፣ ፍፁምና ንፁህ ነበር፡፡ የዚህ ምክንያት ደግሞ ምድራዊ ሳይሆን ሰማያዊ ስለነበረ ነው፡፡

ሐ. አስደናቂ ተአምራትን አድርጓል

  • ወደ እሥራኤልም ልጆች መልክተኛ ያደርገዋል፤ (ይላልም)፡- እኔ ከጌታዬ ዘንድ በታምር መጣኋችሁ፡፡ እኔ ለናንተ ከጭቃ እንደ ወፍ ቅርጽ እፈጥራለሁ፤ በርሱም እተነፍስበታለሁ፤ በአላህም ፈቃድ ወፍ ይኾናል፡፡ በአላህም ፈቃድ ዕዉር ኾኖ የተወለደን ለምጸኛንም አድናለሁ፤ ሙታንንም አስነሳለሁ፡፡ የምትበሉትንና በቤታችሁ የምታደልቡትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፤ የምታምኑ እንደኾናችኁ ለእናንተ በዚህ ውስጥ በእርግጥ ታምር አለበት፡፡

ሱረቱ አሊ-ዒምራን (3)፡49

I have come to you with a sign form your Lord, in that I (Jesus) make for you out of clay, as it were, the figure of a bird, and breathe into it, and it becomes a bird by God’s leave; and I heal those born blind, and the lepers, and I quicken the dead, by God’s leave…

ታላላቅ ተአምራትን ያደረገ፣ ፈውስን ያከናወነና ሙታንን ያስነሳ ኢየሱስ ብቻ አልነበረም፡፡ ነገር ግን ከእርሱ በፊት ከኖሩትም ሆነ ከእርሱ በኃላ ከመጡት ነቢያት በተለየ መልኩ እርግብን ከጭቃ እንዳበጀ፣ እስትንፋስም እንደዘራባትና ሕያው እንድትሆን እንዳደረጋት ግን ቁርአን በግልጽ ይመሰክርለታል፡፡

መ. ወደ እግዚአብሔር ተመልሷል

  • አላህም ባለ ጊዜ (አስታውስ)፣ ዒሳ [ኢየሱስ] ሆይ! እኔ ወዳጂህ ወደ እኔም አንሺህ ነኝ[raise thee to Myself] ከነዚያም ከካዱት ሰዎች አጥሪህ ነኝ፤ እነዚያንም የተከተሉህን እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ ከእነዚያ ከካዱት በላይ አድራጊ ነኝ፤ ከዚያም መመለሻችሁ ወደኔ ነዉ፣ በርሱ ትለያዩበትም በነበራችሁት ነገር በመካከላችሁ እፈርዳለሁ፡፡

ሱረቱ አሊ-ዒምራን (3)፡55

Behold! God said: “O Jesus! I will take thee and raise thee to Myself…

አፈር ስለሆኑ ወደ አፈር እነደ ተመለሱት እንደ ሌሎች ነቢያት ሳይሆን ኢየሱስ ወደ ሰማይ ተወስዷል፤ መሲሁ ኢየሱስ ወደ እግዚአብሔር ተወስዷል! መጻሕፍት እንደዚህ አይነት ክብር የተቀበለ ሌላ ነብይ ስለመኖሩ አይናገሩም፣ የለምና፡፡ ኢየሱስ ግን ከላይ ስለነበረ፣ ከራሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስለነበር፣ በቁርአን መሠረት ኢየሱስ ወደ እግዚአብሔር ዘንደ ተመልሷል፡፡

ሠ. ዳግመኛም ወደ ዓለም ይመለሳል

  • እርሱም (ዒሳ) [ኢየሱስ] ለሰዓቲቱ (ማወቂያ) በእርግጥ ምልክት ነው፡፡ በርሷም አትጠራጠሩ፡፡ ተከተሉኝም፣ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው፣(በላቸው)፡፡

ሱረቱ አል-ዙኸሩፍ (43)፡61

And (Jesus) shall be a Sign (for the coming of) the Hour (of Judgment).

ምንም እንኳን ቁርአን ኢየሱስ ከሰማይ እንደሚመለስ በግልፅ ባይናገርም፣ በርካታ የሙስሊም ምሁራን ‹ኢየሱስ በመጨረሻው ዘመን የሰይጣንን ኃይላት ለማጥፋትና ለአለማቀፋዊው ሰላም መንገድን ለማበጀት ይመለሳል›፣ የሚለውን የሙስሊም ወግ ለማጠናከር ከላይ የሰፈረውን ጥቅስ ይጠቀማሉ፡፡ ይህንን ጥቅስ በተመለከተ በግርጌ ማስታወሻው ላይ የቅዱስ ቁርአን፡- ትርጉምና ማብራሪያ፣ (በ ኤ. ዩሱፍ አሊ)፣ የሚከተለውን ያስነብበናል፡- ‹‹ይህ ከትንሳኤ በፊት በመጨርሻው ዘመን ስለሚሆነው የኢየሱስ ዳግም ምጽአት የሚያወሳ መሆኑ ግልፅ ነው…፡፡››

ለማጠቃለል፣ ከላይ የተመለከትናቸው የቁርአን ጥቅሶች ኢየሱስ ከወንድ ዘር ውጪ ተአምራዊ በሆነ መንገድ ስለመወለዱ ይጠቁሙናል፤ ከዚህ በተጨማሪ ኢየሱስ ከኃጢአት የፀዳ ፍፁም ሕይወት እንደነበረው፣ መፍጠርን ጨምሮ ታላላቅ ተአምራት መሥራቱን፣ ወደ እግዚአብሔር ዘንድ እንደ ተወሰደ፣ የዓለምን ሰላም ለመመለስ ዳግመኛ ወደ ዓለም እንደሚመለስ በግልጽ የበስሩናል፡፡ በዚህ አይነት ክብርና ሁኔታ በማናቸውም ቅዱሳት መጻሕፍት የተገለፀ ከኢየሱስ ሌላ ማንም ነቢይ የለም! አንዳንድ ሙስሊሞች ምንም ይበሉ ምን፣ ቁርአን ኢየሱስ ተራ ነቢይ እነዳልሆነ አስረግጦ ይናገራል!!!

Leave a Reply

%d bloggers like this: