“የተበረዘውንና ያፈጀውን” የአይሁድና ክርስቲያኖች ሃይማኖታዊ ሥርዐት በአዲስ ሃይማኖትና በአዲስ ሕግ መተካት የነቢያቸው የሙሐመድ ተልዕኮ እንደ ነበረ አንዳንድ ሙስሊሞች ይናገራሉ፡፡ በዚህ ምክንያት በርካታ ሙስሊሞች ለክርስትና መልዕክት ትኩረት የመሰጠት አስፈላጊነት አይታያቸውም፡፡ እንደ እነዚህ ሰዎች እምነት፣ ከክርስቶስ ልደት 600 አመታት በኃላ በመጣዉ ሙሐመድ የተዋወቁት ‹‹አዲሱና የተሻለው›› የእስልምና ሃይማኖት ክርስትናን ተክቷል፡፡ ምንም እንኳ ይህ አስተሳሰብ በእስልምና ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ የተስፋፋ ቢሆንም ከእስልምናው ቅዱስ መጽሐፍ፣ ቁርአን ትምህርት ጋር ግን ፍጹም የሚጋጭ አስተሳሰብ ነው፡፡
በቁርአኑ መሰረት የሙሐመድ ተልዕኮ ፍፁም አዲስ የሆነ ሃይማኖትን መትከል ሳይሆን የአብርሃም ሃይማኖትን ማስቀጠል ነው፡፡
- ከዚያም ወደ አንተ [ሙሐመድ] የኢብራሂምን [የአብርሃምን] ሃይማኖት ቀጥተኛ ሲኾን ተከተል፣ [የአብርሃምን ሃይማኖት ተከተል] ከአጋሪዎቹም አልነበረም ማለትን አወረድን፡፡
ሱረቱ አል-ነሕል (16)፡123
So We have taught thee (Muhammad) the inspired message, “Follow the ways of Abraham the true in faith, and he joined not gods with God.”
- እኔ ጌታዬ ወደ ቀጥተኛዉ መንገድ ትክክለኛን ሃይማኖት ወደ እውነት አዘንባይ ሲኾን የኢብራሂምን [የአብርሃምን] መንገድ፣ መራኝ፣ እርሱም ከአጋሪዎቹ አልነበረም በል፡፡
ሱረቱ አል-አንዓም (6)፡161
Say: “Verily, my Lord hath guided me to a way that is straight,-a religion of right,-the path (trod) by Abraham the true in faith, and he (certainly) joined not gods with God.”
- አላህ ውነትን ተናገረ፣ የኢብራሂምንም [የአብርሃምንም] መንገድ ወደ እውነት ያዘነበለ ሲኾን ተከተሉ፣ [የአብርሃምን ሃይማኖት ተከተሉ] ከአጋሪዎቹም አልነበረም በላቸው፡፡
ሱረቱ አሊ-ዒምራን (3)፡95
Say: “God speaketh the truth: follow the religion of Abraham, the sane in faith; he was not of the pagans.”
- አይሁድን ወይም ክርስቲያኖችን ኹኑ፣ (ቅኑን መንገድ) ትመራላችሁና አሉም፣ አይደለም፣ የኢብራሂምን [የአብርሃምን] ሃይማኖት ቀጥተኛ ሲኾን እንከተላለን፣ ከአጋሪዎችም አልነበረም በላቸዉ፡፡
ሱረቱ አል-በቀራህ (2)፡135
They say: “Become Jews or Christians if ye would be guided (to salvation).” Say thou: “Nay! (I would rather) the religion of Abraham the true, and he joined not gods with God.”
- እርሱ መልካም ሠሪ ኾኖ ፊቱን ለአላህ ከሰጠና የኢብራሂምንም መንገድ ቀጥተኛ ሲኾን፣ ከተከተለ ሰው ይበልጥ ሃይማኖቱ ያማረ ማን ነዉ? አላህም ኢብራሂምን ፍጹም ወዳጅ አድርጎ ያዘዉ፡፡
ሱረቱ አል-ኒሳእ (4)፡125
Who can be better in religion than one who submits his whole self to God, does good, and follows the way of Abraham the true in faith? For God did take Abraham for a friend.
እላይ ከተገለጡት አሳቦች በተጨማሪ፣ ቁርአን ራሱ ሙሐመድ አዲስና እንግዳ ነገር ሊያስተምር እንዳልመጣ ይናገራል፡፡ ቁርአኑ፣ ሙሐመድ የተቀበለው መገለጥ የቀድሞዎቹን መገለጦች ትክክለኛነት ለማረጋገጥ እንደመጣ በግልጽ ይናገራል፡፡ የሙሐመድ መገለጥ የመጣው የቀድሞዎቹን ሊያርም፣ ሊተካ፣ በእነርሱ ላይ ሊጨምር ወይም ለመሻር ሳይሆን ለማረጋገጥ ብቻ ነው!
- ከበፊቱም የሙሳ [የሙሴ] መጽሐፍ መሪና ጸጋ ሲኾን አልለ፤ ይህም እነዚያን የበደሉትን ሊያስፈራራ በዐረብኛ ቋንቋ ሲኾን (የፊቶቹን መጻሕፍት) አረጋጋጭ መጽሐፍ ነው፡፡ ለበጎ አድራጊዎችም ብሥራት ነው፡፡ [ቁርአን፣ በአረብኛ ቋንቋ፣ ቀድሞ አላህ የገለጣቸውን የሙሴን መጻሕፍት ትክክለኛነት ሊያረጋግጥ ነው የመጣው፡፡]
ሱረቱ አል-አሕቃፍ (46)፡12
And before this was the Book of Moses as a guide and a mercy; and this Book (Qur’an) confirms (it, the book of Moses) in the Arabic tongue.
- ካንተ በፊት [ከሙሐመድ በፊት] ለነበሩት መልክተኞች የተባለዉ ብጤ እንጅ ለአንተ ሌላ አይባልም፤ ጌታህ የምሕረት ባለቤትና የአሳማሚ ቅጣት ባለቤት ነዉ፡፡ [ሙሐመድ፣ ከአንተ በፊት በነበሩ መልእክተኞች እጅ አላህ የላከውን መልእክቶች አይነት (ብጤ) እንጂ ልዩ መልእክት አልተነገረህም፡፡]
ሱረቱ ሓ፡ሚም፡ አል-ሰጅዳህ (41)፡43
Nothing is said to thee (Muhammad) that was not said to the apostles before thee, that thy Lord has at His command (all) forgiveness as well as a most grievous penalty.
- ለናንተ ከሃይማኖት ያንን [The same religion] በርሱ ኑሕን [ኖህን] ያዘዘበትን ደነገገላችሁ፤ ያንንም ወዳንተ ያወረድነውን ያንንም በርሱ ኢብራሂምን [አብርሃምን]፣ ሙሳንና ዒሳንም [ሙሴንና ኢየሱስን] ያዘዝንበትን ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ በርሱም አትለያዩ ማለትን (ደነገግን)፤ በአጋሪዎቹ ላይ ያ ወደርሱ የምትጠራቸው ነገር ከበዳቸው፤ አላህ የሚሻውን ሰው ወደርሱ (እምነት) ይመርጣል፤ የሚመለስንም ሰው ወደርሱ ይመራል፡፡
ሱረቱ አል-ሹራ (42)፡13
The same religion has He (God) established for you as that which He enjoined on Noah…and that which We enjoined on Abraham, Moses, and Jesus: namely, that ye should remain steadfast in Religion, and make no divisions therein.
እዚህ ላይ፣ የአብርሃም ሃይማኖት በነቢዩ ሙሴ አማካኝነት ለእግዚአብሔር ሕዝብ በቀረቡ ሞራላዊና ማሕበራዊ ሕጎች መሰጠት ጋር ተያይዞ የተስፋፋ ሃይማኖት መሆኑን ማስታወስ ጠቃሚ ነጥብ ነው፡፡ ይህ ሃይማኖት በእስልምና ሃይማኖት ላይ ካሳደረው ተጽእኖ የተነሳ የእስልምና ሃይማኖት፣ ከሙሐመድ መምጣት አስቀድሞ ከመቶ አመታት በፊት በአይሁድ ይዘወተሩ የነበሩ በርካታ ልማዶችን እንዲወስድ አስገድዶታል፡፡ የሚከተሉት ጥቂት ዝርዝሮች በአሁን ሰአት የሙስሊም ልማዶች የሆኑ፣ ነገር ግን ከረጅም ዘመናት በፊት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰፍረው የምናገኛቸው ናቸው፡፡ እነዚህ ልማዶች አንዳንድ ሙስሊሞች ክርስቲያኖች እንዲያምኑላቸው እንደ ሚፈልጉት የአዲስ ሃይማኖት አዲስ ልማዶች አይደሉም፤ ቀድሞዉኑም ቢሆን የነበሩ እንጂ፡-
- ሰላም ለአንተ (ለአንቺ) ይሁን ብሎ ሰላምታ መስጠት (ሉቃስ 10፡5)
- ከፀሎት በፊት መታጠብ (ዘጸአት 40፡31፣ 32)
- በእግዚአብሔር መገኛ ስፍራ ጫማ ማውለቅ (ዘጸአት 3፡5)
- በፀሎት ወቅት መስገድ (መዝሙር 95፡6)
- የእንስሳት መስዋዕቶችን ማቅረብ (ዘዳግም 16፡1-6)
- መንፈሳዊ ጉዞ ማድረግ (የሐዋሪያት ሥራ 8፡26-28)
- ሴቶች ራሳቸውን በልብስ መሸፈን (1ቆሮንቶስ 11፡56)
- ግዝረት (ሉቃስ 2፡21)
- በሕፃን ልጅ ልደት ወቅት የእንስሳ መሥዋዕትን ማቅረብ (ሉቃስ 2፡24)
- ረጅም ፆም መፆም (ዘጸአት 34፡28 ፣ 1ነገሥት 19፡8 ፣ ማቴዎስ 4፡2)
- የሴቶች ጨዋነትና ዝምታ (1ቆሮንቶስ 14፡34)
- የአሳማ ሥጋን ከመብላት መቆጠብ (ዘሌዋዊያን 11፡7)