የሕይወት እንጀራ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የትንቢተ ኢሳይያስ ዓላማ

የትንቢተ ኢሳይያስ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከሚገኙ ጥልቅ የሥነ-መለኮት ትምህርቶች መካከል አንዳንዶቹን የያዘ ነው። መጽሐፉ የይሁዳ ሕዝብ በባቢሎን መንግሥት የሚማረክበትን ምክንያትና የይሁዳ ሕዝብ ቅሬታ ደግሞ በመጨረሻ ከምርኮ እንደሚመለስ ቢናገርም፥ የመጽሐፉ ተቀዳሚ ትኩረት ግን ይህ አይደለም። የኢሳይያስ ትኩረት በእግዚአብሔር ባሕርይ ላይ ነው። የቀሩት ትምህርቶች በሙሉ ኢሳይያስ ስለ እግዚአብሔር የነበረው ግንዛቤ ውጤቶች ናቸው። እግዚአብሔር በይሁዳ ሕዝብ ላይ እንደሚፈርድ […]

የትንቢተ ኢሳይያስ ዓላማ Read More »

የትንቢተ ኢሳይያስ አስተዋጽኦ

እንደ አብዛኛዎቹ የትንቢት መጻሕፍት ሁሉ የትንቢተ ኢሳይያስንም አስተዋጽኦ ማዘጋጀት አስቸጋሪ ነው። ምክንያቱም አብዛኛዎቹ የትንቢተ ኢሳይያስ ክፍሎች ዝርዝር ጉዳዮችን ያላካተቱ ተከታታይ መልእክቶችና ትንቢተች ናቸው። ኢሳይያስ ከፍርድ መልእክት አጽናኝና ተስፋ ሰጭ ወደሆነ መልእክት፥ እንደገና ደግሞ ወደ ፍርድ መልእክት የሚመላለስ ይመስላል፡፡ ይህ ዑደት በመጽሐፉ ውስጥ በተደጋጋሚ ሲፈጸም የሚታይ ነው። ከዚህ ቀጥሉ ያለው ከመጽሐፉ አስተዋጽኦ ውስጥ አንዱ ሊሆን ይችላል።

የትንቢተ ኢሳይያስ አስተዋጽኦ Read More »

ኢሳይያስ የኖረበት ዘመን ታሪካዊ ሥረ-መሥረት እና የነቢዪ ኢሳይያስ ሥረ-መሠረት

I. ኢሳይያስ የኖረበት ዘመን ታሪካዊ ሥረ-መሥረት፡- የውይይት ጥያቄ፥ ኢሳይያስ 1፡1 እና 2ኛ ነገሥት 15-20 አንብብ። ሀ) ኢሳይያስ ባገለገለባቸው ዘመናት የነበሩትን ነገሥታት ስም ዘርዝር። ለ) የእነዚህ ነገሥታት ባሕርይ ምን ይመስል ነበር? ሐ) በእነዚህ ዓመታት ውስጥ በእስራኤልና በይሁዳ የተከናወኑ ዋና ዋና ድርጊቶች ምን ነበሩ? ነቢዪ ኢሳይያስ የኖረውና የሠራው ለብዙ ዓመታት ነበር። መቼ እንደተወለደ ባናውቅም እንኳ የነቢይነት አገልግሉቱን

ኢሳይያስ የኖረበት ዘመን ታሪካዊ ሥረ-መሥረት እና የነቢዪ ኢሳይያስ ሥረ-መሠረት Read More »

የትንቢተ ኢሳይያስ መግቢያ

የውይይት ጥያቄ፥ እግዚአብሔር የነገሮች ሁሉ የበላይ ተቈጣጣሪ ነው፡- እርሱም በሕዝብ መሪዎች ላይ፥ ወደ ክርስቲያን ሕይወት በሚመጣ በረከት ላይ፥ በምድር በሚመጡ ፍርዶች ላይ፥ በምድር በሚፈጸሙ ነገሮች ሁሉ ላይ የበላይ ተቆጣጣሪ ነው። አንድ ክርስቲያን ይህን እውነት ከተረዳ በክርስትና ሕይወቱ የሚያበረታታው እንዴት ነው? በብሉይ ኪዳን ከሚገኙ ታላላቅ የትንቢት መጻሕፍት አንዱ ትንቢተ ኢሳይያስ ነው። ታላቅ የተባለባቸው በርካታ ምክንያቶች አሉ፤

የትንቢተ ኢሳይያስ መግቢያ Read More »

ስለ ትንቢት የሚቀርቡና በአተረጓጐሙ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ የተለያዩ አመለካከቶች

ትንቢትን ማጥናት ቀላል አይደለም። ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና ሌሎች የሰጡትን ትርጕም ለመመርመር ረጃጅም ሰዓታትን የሚጠይቅ ነው። በትንቢት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙትን አብዛኛዎቹን የነቢያት መልእክቶች ለመተርጐም በምሁራን ዘንድ አጠቃላይ ስምምነት ቢኖርም፥ ሆኖም ግን በአይሁድ ታሪክ ወይም በኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት ተፈጻሚነት ያላገኙትን ትንበያዎች ለመተርጎም ትልቅ ልዩነት ታይቶአል። ምሁራን፡- እነዚህ ትንበያዎች ተምሳሌታዊ በሆነ መንገድ ቀደም ሲል በአይሁዳውያን ተፈጽመዋል ወይስ በቤተ

ስለ ትንቢት የሚቀርቡና በአተረጓጐሙ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ የተለያዩ አመለካከቶች Read More »

ትንቢትን ለመተርጐም የሚጠቅሙ መመሪያዎች

በብሉይ ኪዳን ውስጥ 17 የትንቢት መጻሕፍት እንዳሉ ተመልክተናል። ይህ ማለት ከብሉይ ኪዳን መካከል ብዙዎቹ መጻሕፍት የተጻፉት በነቢያት ነው ማለት ነው። እነዚህ ነቢያት እኛ በምናስተውለው በተለመደው መንገድ አልነበረም ነቢይነታቸው፤ ነገር ግን ለነበሩበት ትውልድ የእግዚአብሔር ቃል አቀባዮች ነበሩ። የትንቢት መጻሕፍት ስለ ወደፊት ሁኔታዎች እንደሚናገሩ ከማሰብ ይልቅ መልእክቶች (ስብከቶች) እንደሆኑ መቊጠሩ ይመረጣል። ብዙውን ጊዜ ነቢያት የእስራኤልን ሕዝብ በሚመለከት

ትንቢትን ለመተርጐም የሚጠቅሙ መመሪያዎች Read More »

ነቢያትና ትንቢቶች

የውይይት ጥያቄ፥ «ነቢይ» ማለት ምን ማለት ነው? ይህንን ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ በመመልከት ነቢይ ምን እንደሆነና ምን እንደሚሠራ የሚያመለክት አጭር መግለጫ ጻፍ።  የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) ዛሬ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነቢያት አሉን? ለ) ካሉ፥ የሚሠሩት ምንድን ነው? ነቢያት እንዳሉ የምናውቀውስ እንዴት ነው? ሐ) ከብሉይና ከአዲስ ኪዳን ነቢያት የሚለዩት ወይም የሚመሳሰሉት በምንድን ነው? የትንቢት መጻሕፍት

ነቢያትና ትንቢቶች Read More »

የትንቢት መጻሕፍት አጠቃላይ ገጽታ

በብሉይ ኪዳን ጥናታችን እስካሁን ሦስት ዋና ክፍሎችን ተመልክተናል። በመጀመሪያ፥ ፔንታቱክ በመባል የሚታወቁትን አምስቱን የመጀመሪያ መጻሕፍት ተመልክተናል። እነዚህ አምስት መጻሕፍት በይበልጥ ስለተመረጠው የእግዚአብሔር ሕዝብ ጅማሬ ማለትም ስለ አይሁድ የሚናገሩ ናቸው። እግዚአብሔር ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በሲና ተራራ ስላደረገው ቃል ኪዳን ይናገራሉ። ይህ ቃል ኪዳን የቀሩትን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ሁሉ ለመረዳት መሠረት የሚጥል ነው። በሁለተኛ ደረጃ፥ የእስራኤል ሕዝብ

የትንቢት መጻሕፍት አጠቃላይ ገጽታ Read More »

የመኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን መጽሐፍ ዓላማ

ቀደም ሲል እንደተጠቀሰው፥ መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞንን ልንረዳባቸው የምንችልባቸው በርካታ መንገዶች አሉ። የመጽሐፉ ዓላማ የሚወሰነው መጽሐፉ በሚተረጐምበት መንገድ ነው። ይህን መጽሐፍ በምንተረጕምበት ጊዜ ልንጠነቀቅባቸው የሚገቡ ሁለት ከፍተኛ ደረጃዎች ይኖራሉ። የመጀመሪያው መጽሐፉ ሙሉ በሙሉ ዓለማዊ የሆነና ስለ ፍቅር አሳፋሪ በሆነ መንገድ የሚናገር ነው በለሚል ብዙ ክርስቲያኖች ሐፍረት ስለሚሰማቸው ይህንን መጽሐፍ ከማጥናት ይቈጠባሉ። እንዴት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተካተተ

የመኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን መጽሐፍ ዓላማ Read More »

የመኃልየ መኃልይ ትርጕም እና አስተዋጽኦ

የመኃልየ መኃልይ ትርጕም ምሁራን ይህ መኃልየ መኃልይ እንዴት መተርጐም እንዳለበት ለመወሰን ሞክረዋል። ይሁን እንጂ መጽሐፉን መረዳት ስለሚችሉበት መንገድ ለመስማማት አልቻሉም። በዚህም ምክንያት መጽሐፉ ሲተረጐም የቆየባቸው አያሌ የተለያዩ መንገዶች አሉ። እንዲሁም ይህን መጽሐፍ መተርጐም እጅግ አስቸጋሪ የሆነበት ሦስት ምክንያቶች አሉ፡- 1. የመጽሐፉ ርእሰ-ጉዳይ የሆነው የሁለት ግለ ሰቦች ፍቅርና በመጽሐፉ ውስጥ የምናየው የቋንቋ አጠቃቀም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ

የመኃልየ መኃልይ ትርጕም እና አስተዋጽኦ Read More »