የሕይወት እንጀራ

ወደ ፊልሞና

ፊልሞና 1-25

መግቢያና ሰላምታ (ፊልሞና 1-7) ከቀድሞይቱ ቤተ ክርስቲያን አስገራሚ ባሕርያት አንዱ በአማኞች መካከል የነበረው ፍቅርና መተሳሰብ ነበር። በተራራቁ ስፍራዎች የነበሩት ብዙም የማይታወቁ አማኞች ሳይቀር ከልባቸው ይዋደዱ ነበር። ጳውሎስ የሚኖረው ሮም ውስጥ ሲሆን ፊልሞና ደግሞ በቆላስይስ ውስጥ ይኖር ነበር። ይህም በመካከላቸው ከ1200 ኪሎ ሜትሮች በላይ ርቀት መኖሩን ያመለክታል። ጳውሎስ ቀደም ብሎም ከፊልሞና ጋር አብሮ ያሳለፈ አይመስልም። ይሁንና […]

ፊልሞና 1-25 Read More »

የፊልሞና ዓላማ፣ ልዩ ባሕሪያት እና አስተዋጽኦ

የፊልሞና ዓላማ የመጀመሪያ ዓላማ፡- ፊልሞና የኮበለለ ባሪያውን አናሲሞስን እንዲቀበል ለማግባባት። በሆነ ምክንያት ባሪያው አናሲሞስ ከፊልሞና ኮብልሎ ነበር። ምናልባትም የሆነ ነገር ሰርቆ ሊሆን ይችላል የኮበለለው። አናሲሞስ ነጻነቱን ፍለጋ ብዙ ርቀት ተጉዞ ወደ ሮም ሄደ። ሮም ከአንድ ሚሊዮን የሚበዛ ሕዝብ የነበረባት በመሆኗ በቀላሉ ሊደበቅባት ይችል ነበር። በጥንት ዘመን፥ ከጌቶቻቸው የኮበለሉ ባሮች በጭካኔ ይቀጡ ነበር። ድንገት ቢያዙ በጋለ

የፊልሞና ዓላማ፣ ልዩ ባሕሪያት እና አስተዋጽኦ Read More »

የፊልሞና መግቢያ

ቤተልሔም ያደገችው ክርስቲያን ባልሆኑ ቤተሰቦች ዘንድ ነበር። አባቷ ሰካራም በመሆናቸውና እናቷም ቅስም ሰባሪ ቃላት ስለሚሰነዝሩባት፥ በ14 ዓመቷ የተሻለ ሕይወት ፍለጋ ወደ አዲስ አበባ ጠፍታ መጣች። አዲስ አበባ ደርሳ ከአውቶቡስ ስትወርድ ዙሪያዋን የከበቡትን ጸጉረ ልውጥ ሰዎች ተመልክታ ፈራች። ለአያሌ ቀናት በጎዳናዎች ላይ ላይ ታች እያለች ሥራ ስትፈልግ ቆየች። የኋላ ኋላ አንዲት አሮጊት ሴትዮ ከሆቴላቸው ውስጥ እንድትሠራ

የፊልሞና መግቢያ Read More »