2ኛ ዮሐ 1:1-13
፩. ሰላምታ (2ኛ ዮሐ 1-3) ሐዋርያው ዮሐንስ ለረጅም ዘመን የኖረ አገልጋይ ነው። ከክርስቶስ ጋር በመኖር እውነትን ሲያስተምር ሰምቷል (ዮሐ. 8፡31-32፤ 45)። ቤተ ክርስቲያን እያደገች ከመጀመሪያው ትውልድ አማኞች ወደ ሁለተኛ ትውልድ አማኞች (የአማኞች ልጆች) ስትሄድ ተመልክቷል። የክርስትናን ዕድገት ሲመለከት ንጹሕ እውነተኛ ወንጌል በሁለት መንገዶች መበከሉ አሳሰበው። ወንጌሉ የተሳሳቱ ትምህርቶች በቤተ ክርስቲያን ላይ በሚያሳድሩት ተጽዕኖ ምክንያት እየተበከለ […]