መጽሐፈ አስቴር

የታሪክ መጻሕፍት ክለሳ

እስካሁን ድረስ ባካሄድነው ጥናታችን ሁለት ዋና ዋና የብሉይ ኪዳን ክፍሎችን ተመልክተናል። በመጀመሪያ ፔንታቱክ በሚል ስም የታወቁትን በሙሴ የተጻፉትን አምስቱን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትን ተመልክተናል። በሁለተኛ ደረጃ፣ አሥራ ሁለቱን የታሪክ መጻሕፍትን ተመልክተናል። እነዚህ የታሪክ መጻሕፍት የተጻፉት በተለያዩ ያልታወቁ ጸሐፊዎች ነበር። የሚናገሩትም በብሉይ ኪዳን ያሉትን የቀሩትን የእግዚአብሔር ሕዝብ ታሪክ ነው። ታሪኩም ከ1400 እስከ 400 ዓ.ዓ. ድረስ ያለውን ዘመን […]

የታሪክ መጻሕፍት ክለሳ Read More »

የመጽሐፈ አስቴር ዋና ትምህርት

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ የግለሰቦች ታሪክ ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔርና በሰይጣን መካከል የሚካሄድ ጦርነት ታሪክ ነው። ከኦሪት ዘፍጥረት ጀምሮ እስከ ዮሐንስ ራእይ ድረስ የዚህን ጦርነት ፍንጮች እናያለን። ሰይጣን በጦርነቱ ለመዋጋት የተለያዩ መንገዶችን ቢጠቀምም ዓላማው ሁልጊዜ አንድ ነው። የእግዚአብሔርን ዕቅድና የእግዚአብሔርን ሕዝብ ለማጥፋት ይፈልጋል።  በእግዚአብሔር ሕዝብ ታሪክ ውስጥ ሁሉ ሰይጣን የደኅንነት መስመር እንዲቋረጥ ለማድረግ በመሞከር የእግዚአብሔርን ዕቅድ ለማበላሸት

የመጽሐፈ አስቴር ዋና ትምህርት Read More »

አስቴር 7-12

የውይይት ጥያቄ፡ ምሳሌ 21፡1 አንብብ። ሀ) እግዚአብሔር በምድር መሪዎች ላይ ስላለው ቁጥጥር ይህ ጥቅስ ምን ያስተምረናል? ለ) ክርስቲያኖች ከመንግሥት ጋር በሚሠሩበት ጊዜ ይህ ነገር እንዴት ማበረታቻ ይሆናቸዋል? ሐ) ይህ ነገር ሲፈጸም እንዴት እንዳየህ ምሳሌዎችን ስጥ። እግዚአብሔር ስለ ሕዝቡ ብሎ ሁልጊዜ የሚሠራ መሆኑን አይተናል። ተአምራትን ባናይም እንኳ እግዚአብሔር በሥራ ላይ አይደለም ማለት አይደለም። እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ

አስቴር 7-12 Read More »

አስቴር 1-6

ብዙ ጊዜ እግዚአብሔር በዓለም ላይ ለሕዝቡ ያለውን ዕቅድ ለመፈጸም የሚሠራው እንዴት ነው? ብዙ ጊዜ ቀይ ባሕርን እንደመክፈል ያሉ ታላላቅ ተአምራትን ይሠራልን? ብዙ ጊዜ እኛ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር ይህንን የመሳሰሉ ታላላቅ ተአምራትን እንዲሠራ እንፈልጋለን። በመሆኑም በልሳን መናገርና ፈውስን ወደ መሳሰሉ አስደናቂ ተግባራት እንሳባለን። አዎን እግዚአብሔር ዛሬም ቢሆን በመካከላችን በታላላቅ መንገዶች ይሠራል፤ ነገር ግን ለአስደናቂ ነገሮች ብቻ ትኩረት

አስቴር 1-6 Read More »

የመጽሐፈ አስቴር ዓላማዎች እና አስተዋጽኦ

የመጽሐፈ አስቴር ዓላማዎች መጽሐፈ አስቴር የእግዚአብሔርን ታላቅነትና በዓለም ሕዝብ ሁሉ ላይ ያለውን የበላይ ተቆጣጣሪነት ለአይሁድ ለማስተማር የተጻፈ ታሪክ ነው። ጸሐፊው አይሁድን ለማስተማር የፈለገው ነገር፥ ሕዝቡ የሚኖሩት በተስፋይቱ ምድር ሳይሆን በምርኮ ምድር ቢሆንም እንኳ፥ እግዚአብሔር ለቃል ኪዳኑ አሁንም ቢሆን ታማኝ መሆኑን ነው፤ ነገር ግን ይህንን እውነት ለማስተማር ጸሐፊው የተጠቀመው የመጽሐፍ ቅዱስን የተለመደ መንገድ አይደለም። በብሉይ ኪዳን

የመጽሐፈ አስቴር ዓላማዎች እና አስተዋጽኦ Read More »

የመጽሐፈ አስቴር መግቢያ 

የውይይት ጥያቄ፥ ባለፉት 20 ዓመታት ስለ ተፈጸመው የኢትዮጵያ ታሪክ አስብ። መንግሥትን፥ ቤተ ክርስቲያንንና የግል ሕይወትህን በመቆጣጠር ረገድ የእግዚአብሔርን ሉዓላዊነት እንዴት አየህ? ምሳሌዎችን ስጥ። መጽሐፈ አስቴር እግዚአብሔር በማይታይ መንገድ በሉዓላዊነቱ ሕዝቡን እንደሚጠብቅ የሚያሳይ መጽሐፍ ነው። የእግዚአብሔር ሰዎች የእግዚአብሔር እጅ በሥራ ላይ ሆኖ ባያዩም እንኳ እግዚአብሔር በብዙ በማይታዩ መንገዶች ለራሳቸው ጥቅምና ለመንግሥቱ መስፋፋት በመሥራት ላይ ነው። ክርስቲያን

የመጽሐፈ አስቴር መግቢያ  Read More »