የሕይወት እንጀራ

ትንቢተ ኤርምያስ

ሰቆቃወ ኤርምያስ መግቢያ

ክርስቲያኖች ነገሮች ሁሉ ለእነርሱ የጨለሙ በሚመስሉበት ጊዜ ምን ማድረግ አለባቸው? አገራቸው በእርስ በርስ ጦርነት በምትጠፋበትና ምንም ተስፋ የሌለ በሚመስልበት ጊዜ ምን ማድረግ አለባቸው? ከቤተሰቦቻቸው መካከል አንዳንዶች በበሽታ፥ በራብ ወይም በሌላ አሳዛኝ መንገድ በሚሞቱበት ጊዜ ምን ማድረግ ይገባቸዋልን? ተስፋ መቁረጥ አለባቸውን? እግዚአብሔርን መውቀስ ይገባቸዋልን? እምነታቸውን መተው አለባቸው? ችግሩን ሸሽተው ለማምለጥ ወደ ሌላ አገር መሰደድ ይገባቸዋል? ቀኖቹ […]

ሰቆቃወ ኤርምያስ መግቢያ Read More »

ኤርምያስ 46-52

የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) የመንግሥታት መሪዎች በጽድቅና በቅን ፍርድ ይመሩ ዘንድ የሚያበረታታቸውና ሊገነዘቡት የሚገባቸው ነገር ምንድን ነው? ይህ ነገር ብዙ ጊዜ ይሆናልን? ለ) እግዚአብሔር ለሚፈጽሙት ተግባር ሕዝቦችን ተጠያቂ ሲያደርግ ያየኸው እንዴት ነው? ሐ) እግዚአብሔር ሕዝቦችን ሲቆጣጠር ያየኸው እንዴት ነው? የብዙ መንግሥታት መሪዎች የተሳሳተ ስሜት ወይም እምነት በእግዚአብሔር ተጠያቂ እንደማይሆኑ ማሰባቸው ነው። ስለ ራሳቸው ኃይል ብቻ ያስባሉ።

ኤርምያስ 46-52 Read More »

ኤርምያስ 37-45

አንድ ሰው በእግዚአብሔር ፊት የተቀደሰ ሕይወት በመኖሩ ሌሎች ሰዎች ከሚቀበሉት መከራ ያመልጣል ማለት አይደለም። ይልቁንም ድርቅ ወይም ወረርሽኝ ሲኖር የእግዚአብሔር ሕዝብም ብዙ ጊዜ መከራ ይቀበላሉ፤ ደግሞም ይሞታሉ። ኤርምያስ የእግዚአብሔር ነቢይ ቢሆንም እንኳ የኖረው የእግዚአብሔር ፍርድ በይሁዳ ላይ በተፈጸመ ጊዜ በመሆኑ፥ ሌሎች አይሁድ የተቀበሉትን መከራ ተቀብሏል። የምግብ ዕጥረት ሲከሠት ተርቧል፤ አንዳንድ ዘመዶቹ ሞተውበታል፤ ወዘተ። እግዚአብሔር ሌሎች

ኤርምያስ 37-45 Read More »

ኤርምያስ 26-36

የእውነትና የወንጌል ጠላቶች ብዙ ጊዜ በሕዝቡ መካከል የሚገኙ የሃይኖት መሪዎች መሆናቸው አሳዛኝ የሆነ እውነታ ነው። ይህ ኢየሱስ በኖረበት ዘመንም እውነት ነበር። ተራ የሆኑ ሰዎችና ኃጢአተኞች ኢየሱስን ሲወዱ፥ ለእግዚአብሔር ቅርብ ነን ይሉ የነበሩ የአይሁድ ሃይማኖታዊ መሪዎች ግን ኢየሱስን በመጥላት ሰቅለው ገደሉት። ይህ በኤርምያስ ሕይወትም እውነት ነበር። ኤርምያስ የእግዚአብሔርን ቃል፥ ሊመጣባቸው ስላለው ፍርድ ለሕዝቡ በድፍረት በተናገረ ጊዜ

ኤርምያስ 26-36 Read More »

ኤርምያስ 18-25

እግዚአብሔር ከግለሰቦች ጋር እንደሚሠራ ሁሉ፥ በቡድን ከሰዎች ጋር ወይም ከአብያተ ክርስቲያናት ጋርም ይሠራል፤ በሁለቱም ረገድ የራሱ ዓላማዎች አሉ። በግለሰብ ደረጃ፥ ለሁላችንም ያለው ዓላማ ኢየሱስ ክርስቶስን እስክንመስል ድረስ እያንዳንዳችንን መቅረጽ ነው (2ኛ ቆሮንቶስ 3፡18)። በአብያተ ክርስቲያናት ደረጃ ደግሞ የእግዚአብሔር ፍላጎት ለኢየሱስ ክርስቶስ ብቁ የሆነች ቅድስትና ንጽሕት ሙሽራ እንድትሆን ነው (2ኛ ቆሮንቶስ 11፡2)። በግለሰብ ወይም በአብያተ ክርስቲያናት

ኤርምያስ 18-25 Read More »

ኤርምያስ 7-17

በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚመጣው ከፍተኛ አደጋ ስደት አይደለም። የሐሰት ትምህርትም አይደለም። ትልቁ አደጋ ግን ቤተ ክርስቲያን የሃይማኖትን ቅርጽ ወይም ሥርዓታዊ አምልኮ ብቻ ይዛ መጓዟን፥ መቀበሏንና የሰዎችን ሕይወት የሚለውጥና በሰዎች አኗኗር ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድር ሃይማኖት አለመኖሩ ነው። በኤርምያስ ዘመን የነበሩ አይሁድ ወደ ቤተ መቅደስ እየሄዱ ማምለካቸውን አልተዉም ነበር። ለእግዚአብሔር የእንስሳ መሥዋዕት ማቅረባቸውን አልተዉም ነበር፤ ነገር

ኤርምያስ 7-17 Read More »

ኤርምያስ 1-6

የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) አንተ ባለህበት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንድ ሰው መሪ የሚሆነው እንዴት ነው? የሚመረጠውስ እንዴት ነው? ለ) አንድ ሰው የቤተ ክርስቲያን መጋቢ፥ ሽማግሌ ወይም ወንጌላዊ ለመሆን ሊኖሩት የሚገቡ የተለያዩ መመዘኛዎችን ዘርዝር። አንድ የቤተ ክርስቲያን መሪ ሊኖረው ከሚገባ እጅግ ጠቃሚ ነገሮች አንዱ፡- የሚሠራው ሥራ እግዚአብሔር ሊያደርገው የሚፈልገው ነገር ለመሆኑ ማረጋገጥ አለበት። ይህን ማረጋገጥ ብዙ ጊዜ

ኤርምያስ 1-6 Read More »

የትንቢተ ኤርምያስ ዓላማ፣ ዋና ዋና ትምሕርቶች እና ከአዲስ ኪዳን ጋር ያለው ግንኙነት

የትንቢተ ኤርምያስ ዓላማ ትንቢተ ኤርምያስ የተጻፈው ስለ ሁለት ዋና ዋና ዓላማዎች ነበር፤ አንደኛ፡- የይሁዳ ሕዝብ ለምን እንደተማረኩ ለመግለጽ ነበር። ይህ ክፍል እግዚአብሔር ለሕዝቡ የነበረውን የመጨረሻ መልእክት የሚነግረን ነው። እግዚአብሔር ሕዝቡን ወደ ራሱ ለመመለስ የሞከረበት፥ ሕዝቡ በእግዚአብሔርና በሕጉ ላይ በማመፃቸው ምክንያት የሚደርስባቸውን ነገር በማሳየት የሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ ሁሉ የምናይበት ነው። ሕዝቡ የነበረበትን መንፈሳዊ ሁኔታ፥ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ

የትንቢተ ኤርምያስ ዓላማ፣ ዋና ዋና ትምሕርቶች እና ከአዲስ ኪዳን ጋር ያለው ግንኙነት Read More »

የትንቢተ ኤርምያስ መግቢያ

የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) ታላቅ ክርስቲያን፥ የተዋጣለት ወንጌላዊ ወይም ሰባኪ፥ በአገልግሎቱና በግል ሕይወቱ ሁልጊዜ የሚከናወንለት ይመስልሃልን? መልስህን አብራራ። ለ) ክርስቲያኖች ከሆኑ ሕይወት እጅግ ቀላል እንደሚሆንላቸው፥ እግዚአብሔር ከበሽታ እንደሚጠብቃቸው፥ ሥራ እንደሚያገኙና ሀብታሞች እንደሚሆኑ አድርገው የሚያስቡ የምታውቃቸው ሰዎች አሉን? ይህ ነገር ሁልጊዜ እውን የሚሆን ይመስልሃል? ሐ) በመንፈሳዊ ሕይወቱ የበሰለ ክርስቲያን ተስፋ አይቆርጥም ወይም እግዚአብሔርን አይጠራጠርም ብለህ ታስባለህን? መልስህን

የትንቢተ ኤርምያስ መግቢያ Read More »