ዳንኤል 7-12
የትንቢተ ዳንኤል የመጀመሪያ ክፍል የሆነው ምዕራፍ 1-6፥ በዳንኤል የሕይወት ዘመን በተፈጸሙ ታሪካዊ ድርጊቶች ላይ ያተኩራል። ራእዮቹም ስለ አሕዛብ ነገሥታት እንጂ ስለ ዳንኤል አልነበሩም። ከምዕራፍ 7-12 ያለው የመጽሐፉ ሁለተኛ ክፍል እግዚአብሔር የአሕዛብ መንግሥታትንና የእስራኤልን ሕዝብ የወደፊት ሁኔታ ለዳንኤል በገለጣቸው ልዩ ራእዮች ላይ ያተኩራል። የመጀመሪያዎቹ ስድስት ምዕራፎች በቅድሚያ አሕዛብን የሚመለከቱ ከመሆናቸው የተነሣ የተጻፉት በአራማይክ ቋንቋ ሲሆን፥ የመጨረሻዎቹ […]