ኦሪት ዘኍልቍ

ዘኁልቁ 22-36

እግዚአብሔር አንድን ሰው ለመባረክ ከወሰነ፥ ያንን ሰው መርገም አንዳች ፋይዳ ይኖረዋልን? የበለዓምና የሞዓብ ንጉሥ ታሪክ እግዚአብሔር የሚወዳቸውን ሰዎች፥ የእግዚአብሔር ሕዝብ ጠላቶች በምንም ዓይነት ብርታት ሊረግሟቸው ቢሞክሩም፥ እርግማናቸውን እግዚአብሔር እንደሚያከሽፍ ያሳያል፤ ሙከራቸውም ከንቱ ልፋት ብቻ ይሆናል። በተጨማሪ ይህ የበለዓምና የሞዓብ ንጉሥ ታሪክ የሚያስተምረን የእግዚአብሔርን ሕዝብ የሚያጠፋቸው ውጫዊ ስደት ሳይሆን፥ ከዓለም ጋር ጓደኝነት መግጠማቸውና ዓለምን መምሰላቸው እንደሆነ […]

ዘኁልቁ 22-36 Read More »

ዘኍልቁ 13-21

በሕይወታችን የምናደርገው ምርጫ ለሚያጋጥመን በጎም ይሁን ክፉ ነገር ሁሉ ወሳኝ ሚና አለው። በኢየሱስ ማመንን በመረጥን ጊዜ፥ የወደፊት ሁኔታችን ሁሉ ይለወጣል። ኢያሱና ካሌብ በእግዚአብሖር ለመታመንና ከነዓናውያንን ለመውጋት ሲወስኑ፥ ከዚያ ትውልድ መካከል ወደ ተስፋይቱ ምድር የሚገቡ ብቸኛዎቹ ሰዎች እነርሱ መሆናቸውን አላወቁም ነበር። የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ላለመከተል በምንወስንበት ጊዜ፥ ለጊዜው የቱንም ያህል ትንሽ ቢመስለንም፥ በሕይወት ዘመናችን ሁሉ የሚታይ መጥፎ

ዘኍልቁ 13-21 Read More »

ዘኍልቁ 1-12

የእግዚአብሔርን ሕዝብ በጥሩ ሁኔታ ለመምራት ጥሩ አደረጃጀት ያስፈልጋል። ጥሩ አደረጃጀት ከሌለ መምራት በጣም አስቸጋሪ ይሆናል፤ ሕዝቡም ስለሚምታታበት፥ የእግዚአብሔር ሥራ እንደሚጠበቀው ስኬታማ አይሆንም። ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ የሲና ተራራን ለቆ ወደ ቃዴስ በርኔ፥ ከዚያም ወደ ተስፋይቱ ምድር ከመሄዱ በፊት ሕዝቡን ለማደራጀት ይረዳው ዘንድ እግዚአብሔር ግልጥ ትእዛዛትን ሰጠ። ይህም ግራ መጋባትንና ውጤት አልባነትን ተከላከለ። የውይይት ጥያቄ ሀ) ደካማ

ዘኍልቁ 1-12 Read More »

የኦሪት ዘኁልቁ ዓላማና መልእክት

፩. በመሠረቱ የኦሪት ዘኁልቁ ታሪክ፥ የእስራኤል ሕዝብ ከሲና ተራራ ጀምሮ እስከ ከነዓን ምድር ያደረገውን ጉዞ በአጭሩ የሚያቀርብ ነው። እስራኤላውያን በእግዚአብሔር ባለማመናቸው ምክንያት ወደ ከነዓን ምድር ለመግባት አለመቻላቸውንና በእነርሱ ላይ ስለ ተሠጠው የእግዚአብሔር ፍርድ የሚናገር ታሪክ ነው። በኦሪት ዘፍጥረት ተጀምሮ በዘጸአትና በዘሌዋውያንም የቀጠለው የእስራኤል ሕዝብ ታሪክ አካል ነው። ፪. እንደቀረው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ኦሪት ዘኁልቁም ስለ

የኦሪት ዘኁልቁ ዓላማና መልእክት Read More »

የኦሪት ዘኁልቁ መግቢያ

እስካሁን ድረስ ከፔንታቱክ መጻሕፍት መካከል የመጀመሪያዎቹ ሦስቱን ማለት ዘፍጥረት፥ ዘጸአትና ዘሌዋውያንን አጥንተናል። በዘፍጥረት እግዚአብሔር፥ አይሁድ የራሱ የተለዩ ሕዝብ እንዲሆኑና እንዲያገለግሉት እንዴት እንደመረጣቸው ተመልክተናል። በዘጸአት ደግሞ እግዚአብሔር ሕዝቡን ከባርነት እንዴት እንደተቤዣቸው አይተናል። ዘሌዋውያን የተዋጁ የእግዚአብሔር ቅዱስ ሕዝብ ሆነው መኖር ይችሉ ዘንድ፥ እግዚአብሔር ለአይሁድ ሕዝብ ስለሰጣቸው ሕግጋት ይናገራል። ዛሬ ደግሞ የእስራኤል ሕዝብ እምነትን በማጣቱ ምክንያት በእግዚአብሔር ተቀጥቶ

የኦሪት ዘኁልቁ መግቢያ Read More »