እግዚአብሔር ወልድ – የኢየሱስ መለኮታዊነት

በርካታ ሰዎች ኢየሱስ በስጋ የተገለጠ አምላክ መሆኑን በመካድ ሃሰተኛ ሃይማኖትን መስርተው ከእዉነት መንገድ ሸሽተዋል። በተጨማሪ ሃሰተኛ ወንጌሎች የሚለውን ይመልቱ።

ሀ) ኢየሱስ ስለራሱ ምን ይላል?

– ከሰማይ መጥቷል በሰማይም ይኖራል – ዮሐ 3፡13

– በሁሉም ስፍራ ይኖራል – ማቴ 18፡20

– የሰንበት ጌታ እንኳ ሳይቀር እንደሆነ ተናግሯል – ማር 2፡27-28 ይህ በእግዚአብሔር ነገር ሁሉ ላይ ስልጣኑን ያሳያል

– እግዚአብሔርን አባቴ ብሎ ይጠራል – ዮሐ 5፡17-18 ትርጓሜውም ከእግዚአብሔር ጋር እኩል እንደሆነ ያሳያል – ዮሐ 5፡ 17-18

– ከአባቱ ጋር አንድ ነው፣ ስለዚህም እግዚአብሔር ነው – ዮሐ 5፡30-33

– ኢየሱስ በአባቱ ስም መምጣቱን ተናገሯል – ዮሐ 5፡43

– እርሱን ማየትና መወቅ አብን ማየትና ማወቅ ነው – ዮሐ 14፡7-11

– በመጽሐፍ ቅዱስ ስልጣን ያወራል – ማቴ 5፡21-22፣ 27-28

– “እኔ ነኝ” የሚል ስያሜን ለራሱ ይጠቀማል – ዮሐ 18፡5-8። “እኔ ነኝ” የሚለው ስያሜ የእግዚአብሔር ስያሜ ነው – ዘጻ 3፡ 14

– ከአብርሃም በፊት መኖሩን ተናግሯል – ዮሐ 8፡58

– ንጉስና ፈራጅ እንደሆነ ተናግሯል – ማቴ 25፡31-46። ብሉይ ኪዳን ያህዊን እንደፈራጅ ያሳየናል – ዘፍ 18፡25፤ ኢዮ 3፡18

– ስልጣን በሰማይና በምድር የእርሱ መሆኑን ይናገራል – ማቴ 28፡18-20

ለ) ሌሎች ስለ ኢየሱስ ምን አሉ?

– ‹‹ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው›› ብሎ ጳውሎስ ፅፏል – ሮሜ 9፡5

– የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ብሏል ብለው አይሁድ ተናግረዋል – ዮሐ 19፡7

– ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሏል ብሎ ዮሐንስ ተናግራል – ዮሐ 5፡18

– ጻፎች እግዚአብሔር ብቻ የሚያደርገውን ያደርጋል ብለውታል – ማር 2፡5-7

– ዘላለማዊ፣ ፈጣሪ፣ እግዚአብሔር መሆኑ ተፅፎለታል – ዮሐ 1፡1-5 – ቶማስ ‹‹ጌታዬና አምላኬ›› ብሎታል – ዮሐ 20፡28

– አለማት በእርሱ ተፈጠሩ – ዕብ 1፡2፤ ዮሐ 1፡3፤ ቆላ 1፡16

– ኢየሱስ የእግዚአብሔር ፍፁም ምሳሌ ነው – ዕብ 1፡3

– ፍጥረት ሁሉ በኢየሱስ ተጋጥሟል – ዕብ 1፡3፤ ቆላ 1፡17

– ኢየሱስ በመላዕክት አምልኮ ቀርቦለታል – ዕብ 1፡6

– ወልድ “እግዚአብሔር” ተብሏል – ዕብ 1፡8 – ዘላለማዊ ነው – ዕብ 1፡12

– እርሱ መልአክ ሳይሆን ከመላዕክት በላይነው – ዕብ 1፡4፤ 1ጴጥ 3፡22

– ከሙሴ በላይ ነው – ዕብ 3፡1-6

– ከብሉይ ኪዳን ሊቀካህናት በላይ ነው – ዕብ 4፡14-5፡10

– የእግዚአብሔር ባሕሪይ ባሕሪዩ ነው – ፊል 2፡6-11

– የማይታየው አምላክ አምሳል ነው – ቆላ 1፡15-20

– የመለኮት ሙላት በክርስቶስ አካል ውስጥ ይኖራል – ቆላ 1፡15-20

-‹‹ጌታ›› የሚለው ስያሜ ለአብና ወልድ ጥቅም ላይ ውሏል

አብ – ማቴ 1፡20፤ 9፡38፤ 11፡25፤ ሐዋ 17፡24፤ ራዕ 4፡11

ወልድ – ሉቃስ 2፡11፤ ዮሐ 20፡28፤ ሐዋ 10፡36፤ 1ቆሮ 2፡8፤ ራዕ 19፡16

ሐ) አምላካዊ አምልኮን ተቀብሏል

– የጥበብ ሰዎች አምልከውታል – ማቴ 2፡11

– ደቀ መዛሙርት አምልከውታል – ማቴ 14፡3

– ከነናዊቷ ሴት አምልካዋለች – ማቴ 15፡25

– የተፈወሰው ሰው አምልኮታል – ዮሐ 9፡38

– ሁለቱ ማርያሞች አምልከውታል – ማቴ 28፡9

– ከእርገቱ በኋላ ደቀ መዛሙርት አምልከውታል – ሉቃስ 24፡52

– የእግዚአብሔር መላእክት አምልከውታል – ዕብ 1፡6

– አራቱ ሕያዋን ፍጡራን እና ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች አምልከውታል – ራዕ 5፡8

መ) እግዚአብሔር አብ ስለእርሱ ምን ይላል?

– የአባትና – ልጅ ግንኙነት – ማቴ 3፡17፤ ማቴ 17፡5፤ ዮሐ 8፡16-19፤ 1ዮሐ 5፡9

ይህ ግንኙነት ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን እኩልነት ያመለክታል – ዮሐ 5፡17-18

Leave a Reply

Discover more from

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading