መጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ አምላክ መሆኑን ያሳየናልን?

መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ሥላሴ እንደሆነ በአንድ አምላክ ውስጥ ሦስት አካላት መኖራቸውን እንደሚያስተምር ተመልክተናል። እውን መጽሐፍ ቅዱስ የመንፈስ ቅዱስን አምላክነት በእርግጥ ያስተምራል? 

ጥያቄ፡– የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከት፡- መዝ 139፡7-10፤ ሉቃስ 35 ዮሐ 14፡26፤ 16፡3የሐዋ. 5፡3-4 ሮሜ 8፡2፤ 5፡30፣ ዕብ 9፡14። መንፈስ ቅዱስ አምላክ መሆኑን እነዚህ ጥቅሶች እንዴት ያሳዩናል? 

መንፈስ ቅዱስ መለኮት ለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ በርካታ ማረጋገጫዎች አሉት። 

1. መንፈስ ቅዱስ መለኮት መሆኑን የሚያመለክቱ ስሞች አሉት። 

ለምሳሌ «የእግዚአብሔር መንፈስ» ተብሎ ተጠርቷል (ታብሷል) (2ኛ ቆር. 3፡3)። እንዲያውም «እግዚአብሔር» እንኳ ተብሎ ተጠርቷል። ሐናንያ መሬቱን ሽጦ ከሚስቱ ጋር ተስማምቶ ለቤተ ክርስቲያን ሊሰጥ ስላመጣው ገንዘብ በዋሹ ጊዜ ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስን እንደዋሹ በዚህም እግዚአብሔርን መዋሸታቸውን ያለአንዳች ልዩነት ተናግሯል (የሐዋ. 5፡3 4)። «የሕይወት መንፈስ» (ሮሜ 8፡2) ተብሎም ተጠርቷል። ሕይወት የሚሰጥ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ተቀዳሚ ስሙ የሆነው «ቅዱስ» የሚለው ቃለ እግዚአብሔር ብቻ ልዩ መሆኑንና ፍጹም ንጹሕናውን ያመለክታል (ያስረግጣል)። ይህም እውነት የሚሆነው ለእግዚአብሔር(ለእርሱ ብቻ ነው)። 2. መንፈስ ቅዱስ አምላክ መሆኑን የሚያሳዩ ባሕርያት አሉት። 

ሀ. መንፈስ ቅዱስ «የዘላለም» መንፈስ ነው «ዕብ. 9፡14)። እንደ እግዚአብሔር አብና እንደ እግዚአብሔር ወልድ መንፈስ ቅዱስ ከዘላለም ነበር። መንፈስ ቅዱስ ያልነበረበት ጊዜ አልነበረም። ደግሞም እርሱ እልተፈጠረም። ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሳይለወጥ ይኖራል። ይህ የሚባለው ለእግዚአብሔር ብቻ ነው። እግዚአብሔር በስተቀር ነገሮች ሁሉ ጅማሬ አላቸው። ዘላለማዊ አይደሉም። 

ለ. መንፈስ ቅዱስ በአንድ ጊዜ በሁሉም ስፍራ ይገኛል (መዝ. 139. 7 10)። ከሌሎች ፍጥረታት በተለየ መልኩ እግዚአብሔር በአንድ ጊዜ በእንድ ቦታ ብቻ የሚወሰን አይደለም። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስንም ጨምሮ በእኩልነት በአንድ ጊዜ በሁሉም ስፍራ ይገኛል። በኢትዮጵያም ሆነ በእንግሊዝ በአንድ ጊዜ ይገኛል። በአንድ ጊዜ በሰማይም በምድርም ይገኛል። መንፈስ ቅዱስ በሁሉም ስፍራ ይገኛል። የምናውቃቸው ነገሮች በሙሉ በአንድ ጊዜ የሚገኙት በአንድ ስፍራ ብቻ ነው። በመሆኑም ይህንን እውነት ለመረዳት እንቸገራለን። 

ሐ. መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን አሳብ በሙላት ያውቃል (1ኛ ቆሮ. 2፡10-10። ሁሉን ነገር ያውቃል። ልክ እንደ እግዚአብሔር አብ ምንም ነገር መማር አያስፈልገውም። እውቀቱ ሙሉና ፍጹም ነው። ሁሉን ነገር የሚያውቅ እግዚአብሔር ብቻ ስለሆነና መንፈስ ቅዱስ ደግሞ የእግዚአብሔርን አሳብ በሙሉ ማወቁ ከእግዚአብሔር አብ የተለየ አካል መሆኑን ብቻ ሳይሆን አምላክ መሆኑንም ያሳያል። 

መ. ኢየሱላ «እውነት» እንደተባለ መንፈስ ቅዱስም «እውነት» ተብሎ ተጠርቷል (ዮሐ 14፡6፤ 1ኛ ዮሐ 5፡6)። ዮሐንስ በዚህ ቦታ የሚናገረው መንፈስ ቅዱስ ወይም ኢየሱስ እውነት እንደሚያውቁ ወይም እውነትን እንደሚናገሩ አይደለም። ለነገሩ ይህም እውነት ነው። ዮሐንስ የሚናገረው ግን ኢየሱስም መንፈስ ቅዱስም እውነት እንደሆኑ ነው። በኑባሬአቸው እውነት ሁለንተናቸው ትክክልና ልክ የሆኑ ነገሮች ሁሉ የሚመነጩት ከእነርሱ ውስጥ ነው። 

3. መንፈስ ቅዱስ የመለኮት ተግባራትን ይፈጽማል። 

ሀ. መንፈስ ቅዱስ በፍጥረት ሥራ ውስጥ ተካፍሏል (ዘፍ 1፡2፤ መዝ. [33]፡6፤ [14]፡30)። እግዚአብሔር አብ የፍጥረትን ሥራ እንደሚያቅድ መሐንዲስ እግዚአብሔር ወልድ ደግሞ ሥራውን በኃላፊነት ወስዶ እንደሚሠራ ተቋራጭ ሲሆኑ፥ ዋናው ሠራተኛ ግን መንፈስ ቅዱስ ነበር። 

ለ. የእግዚአብሔርን ቃል ሲጽፉ ሰዎችን የመራቸው መንፈስ ቅዱስ የመጽሐፍ ቅዱስ ደራሲ ነው (2ኛ ጴጥ. 1፡21፤ 2ኛ ጢሞ. 3፡16)። መንፈስ ቅዱስ የጥንት ሰዎች ምን መጻፍ እንዳለባቸው እና እንደሌለባቸው ቃል በቃል አልነገራቸውም። ነገር ግን የጥንት ሰዎች በሚጽፉበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ የሚጽፉትን ቃላት እንኳ በመቆጣጠር ጽሑፋቸው ሲጠናቀቅ እያንዳንዱ የጻፉት ነገር የእግዚአብሔር ቃል ተብሎ እንዲጠራ አድርጓል። ለዚህም ነው ኢየሱስ በእርግጠኛነት የዓለም ፍጻሜ እስኪሆን ድረስ አንድም ነቁጥ (ነጥብ) እንኳ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሊወድቅ እንደማይችል የተናገረው (ማቴ. 5፡17-18)። 

ሐ. መንፈስ ቅዱስ ሕይወትን ይሰጣል (ኢዮብ 33፡4፤ ሮሜ 8፡2፥10። ይህ ሁለት እውነታዎችን ይዟል። በመጀመሪያ ደረጃ ላሥጋዊ ሕይወት እንኳ ምንጩ መንፈስ ቅዱስ ነው። በሴት ማኅፀን ውስጥ ፅንሱን ሕይወት የሚያስጀምረው መንፈስ ቅዱላ ነው። የራሱን ባሕርይ፥ ተሰጥኦዎችና ችሎታዎች በመስጠት የማንኛውንም ሰው እድገት የሚቆጣጠር እርሱ ነው። በሁለተኛ ደረጃ መንፈሳዊ ሕይወትንም የሚሰጥ እርሱ ነው። በኃጢአት የሞተን ነፍስ የሚያቀናና ለእግዚአብሔር ሕያው የሚያደርገው እርሱ ነው። ለመንፈሳዊ ነገር እውር ለሆነ ሰው የመንፈስ ዓይኖቹን የሚከፍት እርሱ ነው። 

መ. ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል እንዲወለድ ያደረገው መንፈስ ቅዱስ ነው (ሉቃስ 1፡35)። ይህ እንዴት እንደሆነ አሁን ላናውቅ እንችላለን። ዘላለማዊ የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ሥጋ እንዴት እንዴላበሰ እንደ ሕናን ለመወለድ በማኅፀን እንዴት እንደተዋሰበ (ማኅፀን እንዴት እንደበቃው) ምስጢር ነው። ይህን ሁሉ ያከናወነው መንፈስ ቅዱስ ነበር። 

ጥያቄ፡- ሀ) መንፈስ ቅዱስ መለኮት ስለመሆኑ የተሰጡ ማረጋገጫዎችን እንደገና ተመልክት። ለ) መንፈስ ቅዱስ በልብህ እንደሚኖር መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል። (1ኛ ቆሮ. 6፡19 ተመልከት።) በመንፈስ ቅዱስ ባሕርይ እማካኝነት እግዚአብሔር በልብህ የመኖሩን እውነታ ስትመለከት ምን ያህል ትበረታታለህ? ሐ) እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን የጸሎት ጊዜ ወስደህ አመስግነው። 

የእግዚአብሔርን አንድነትና ሦስትነት መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያረጋግጥ ለማስረዳት ይህን ያህል ጊዜ መውሰድ እስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ብዙዎቻችን ይህን ክፍል ስናጠና ስለ ሥላሴ እውነታ ጥያቄ አንስተንም፥ ተጠራጥረንም እናውቅምና ምን ያስፈልጋል እንል ይሆናል? እስኪ የሚከተሉትን ምክንያቶች እናስተውል። 

በመጀመሪያ፥ በኢትዮጵያ ውስጥ እግዚአብሔር በአካል ሦስት መሆኑን የማይቀበሉና በርካታ ክርስቲያኖችን የሚያስቱ የሃይማኖት ቡድኖች ስላሉ ነው። ብዙ ክርስቲያኖች ስላልተማሩና መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚያስተምር ስለማያውቁ በሐሰተኛ አስተማሪዎች አሳብ ይማረካሉ። የሚያሳዝነው ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር የሚያስተምረውን ቆም ብለው የሚጠይቁት አልፎ አልፎ ብቻ መሆኑ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን ስለማያጠኑና የብያኔ መሣሪያቸው አድርገው ስለማይጠቀሙበት ለሰው የመከራከሪያ አሳብ ይሸነፋሉ። እርግጥ ነው የሥላሴን እውነት መረዳት እጅግ ከባድ ነው። እግዚአብሔር ከአስተሳሰባችን በላይ ነው። ባይሆንማ ኖሮ እርሱ አምላክ አይሆንም ነበር። እግዚአብሔር ራሱን በአንድነትና በሦስትነት የገላጻውን በማመን ልንደገፍበት ይገባል። 

በሁለተኛ ደረጃ ፥ አንድ ሰው የእግዚአብሔርን ሥራ አገልግሎት እስካልተረዳና ከእያንዳንዱ የሥላሴ አካል ጋር ያለውን ግንኙነት እስካላሳደገ በእምነቱና እግዚአብሔርን በማወቅ ለማደግ አይችልም። ስለ እግዚአብሔር አብና ስለ እግዚአብሔር ወልድ ማሰብ ነገር ግን የመንፈስ ቅዱስንና አካላዊ ህልውናና አገልግሎት ያላመረዳት በመንፈሳዊ ሕይወታችን ልፍስፍስና ውጤት አልባ ያደርገናል በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፥ በእግዚአብሔር አብና በእግዚአብሔር ወልድ መካከል ያለው ግንኙነት። 

በክርስቲያኖች መካከል ለዘመናት ሲያከራክር የቆየ በመንፈስ ቅዱስ መለኮትነት ላይ ያተኮረ አንድ የሥነ መለኮት ርእሰ ጉዳይ አለ። ይህም መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር አብና ከእግዚአብሔር ወልድ ጋር ያለው ግንኙነት ነው። መንፈስ ቅዱስ የመጣው ከእግዚአብሔር አብ ዘንድ ብቻ ነው? ወይስ ከእግዚአብሔር አብና ከእግዚአብሔር ወልድ? ይህ ርእስ በቀድሞዪቱ ቤተ ክርስቲያን እከራካሪ ሆኖ የቆየና በመጨረሻም ቤተ ክርስቲያንን የካቶሊክና የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናት በመባል እንዲከፈሉ እድርጓል። ይህ የመከራከሪያ አሳብ በዕለታዊ ሕይወታችን ላይ ብዙ ተጽዕኖ ስለሌለው በዝርዝር ለማጥናት ጊዜ አንወስድም። የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መንፈስ ቅዱስ የሚወጣው ከእግዚአብሔር አብ ብቻ ነው በማለት ስታስተምር፥ የቀረው የክርስቲያን ኅብረተሰብ ግን መንፈስ ቅዱስ በእኩል ደረጃ ከአብና ከወልድ ይመጣል በማለት ያስተምራሉ (ዮሐ 14፡26፥ 16፡7 ተመልከት)። 

የበታችነት ሳይኖር የአንዱ ለሌላው መገዛት 

የሥላሴ አካላትን የእርስ በርስ ግንኙነት በጥንቃቄ ስንመለከት በርካታ እውነተች ግልጽ እየሆኑ ይመጣሉ። በመጀመሪያ፥ ግፃዌ መለኮት እያንዳንዳቸው በባሕርይ ሙሉ በሙሉ እኩል ናቸው። ሁሉም ምሉዕ አምላክ ናቸው ኃይላቸው፥ እውቀታቸው፥ ዘላለማዊነታቸው፥ ፍቅራቸው፥ ወዘተ… ሁሉም እኩልና አንድ ዓይነት ነው። አካላዊ ህልውናቸውን በተመለከተ አንዳቸው ከሌላቸው የሚያንሱበት ምንም ሁኔታ የለም። 

በሁለተኛ ደረጃ ፥ በግንኙነትና በተግባር ተደጋጋፊነት አለ። እያንዳንዱ የሥላሴ አካል በባሕርይ እኩል ቢሆንም የግንኙነት ሥርዓት እንዳለና ይህም በአንዳንድ መንገዶች እርስ በርስ ያላቸውን ግንኙነቶች ለማሳየት እንጂ የበታችነትን ለማንፀባረቅ እንዳልሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል። መጽሐፍ ቅዱስ ሁል ጊዜ የሚያሳየን የመጨረሻው ባለሥልጣን እግዚአብሔር አብ እንደሆነ ነው። ይህንን በበርካታ መንገዶች እናየዋለን። ኢየሱስ የዓለም አዳኝ እንዲሆን የላከው እግዚአብሔር አብ ነው (ዮሐ 3፡16)። ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ዘመን ሁሉ አሳቱን እንደታዘዘ ተናግሯል። ያደረጋቸው ሥራዎች በሙሉ አባቱ እንዲያከናውን የሰጠውን ነበር (ዮሐ 5፡36፤ 5፡10)። እንዲያውም በዘመነ ፍጻሜ ታሪክ ሲደመድም ኢየሱስን ሥልጣኑን ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ እንደሚያስረክብ ተነግሮናል (1ኛ ቆሮ. 5፡24-28)። 

መንፈስ ቅዱስ በምግባሩ ለእግዚአብሔር አብና ለእግዚአብሔር ወልድ ሁልጊዜ ጥገኛ ነው። መንፈስ ቅዱስን ወደ ክርስቲያን ሕይወት የሚልኩት እግዚአብሔር አብና እግዚአብሔር ወልድ እንደሆኑ ተምረናል (ዮሐ 14፡26፤ 15፡26፤ 16፡7)። መንፈስ ቅዱስ በሰዎች መካከል ባለው አገልግሎቱ ተቀዳሚ ሚናው ሰዎችን ወደ ራሱ ሳይሆን ወደ ኢየሱስ መምራት ነው። ኢየሱስ ያስተማረውን ያስተምራል (ዮሐ 14፡26፤ 16፡2-5)+ አዲስ ክርስቲያኖችን ወደ ክርስቶስ አካል ይመራቸዋል (1ኛ ቆሮ. 1፡13)። ሰዎች ክርስቶስን እንዲመስሉ አድርጐ ይለውጣቸዋል (2ኛ ቆሮ. 3፡18)። 

ጥያቄ፡- የዚህን ምዕራፍ ትምህርቶች በመጠቀም እኔ የተከራከርኩትንና ክርስቲያን ስለ ሥላሴ ትምህርት የተረጻውን በመቃረን የሚያስተምረውን «የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን እምነት አስተማሪን ለእግዚአብሔር ቃል የምትገጻደረው እንዴት ነው? የመላላህን ዋና ዋና ነጥቦች ዘርዝር። 

የሥላሴ አካላት በአስተሳሰብና በዓላማ ሁልጊዜ አንድ ቢሆኑም እንኳ እያንዳንዱ አካል የየራሱ ልዩ ሚና እንዳለው መገንዘብ በጣም አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ በመስቀል ላይ የሞቱት እግዚአብሔር አብና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አይደሉም። ይህ የወልድ ልዩ አገልግሎት ነበር። በሌላ አባባል አንድ ክርስቲያን እግዚአብሔር አብን በመስቀል ላይ ስለሞትክልኝ አመሰግንሃለሁ ቢል መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም። በተመሳሳይ መንገድ መጽሐፍ ቅዱስ የክርስቲያንን ሕይወት እግዚአብሔር አብ ወይም ወልድ እንደሚሞሉት ፈጽሞ አይናገርም። ይህ የመንፈስ ቅዱስ ልዩ አገልግሎት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር ትክክለኛ እንሆን ዘንድ የመንፈስ ቅዱስን ማንነትና በሕይወታችን የሚያከናውናቸውን አገልግሎቶች በሚገባ ማስተዋል አለብን።

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

%d bloggers like this: