በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የተሠገዎ ታሪክ፣ ኢቢዮናውያን 

ዛሬ ስለ ኢየሱስ ተሠገዎ ማጥናታችንን እንቀጥላለን፥ ነገር ግን ሆኖም ጥናታችን ከሌላ አቅጣጫ ይሆናል። የዛሬው ጥናታችንም የሚጀምረው የተሠዎ አስተምህሮ በጥንታዊትዋ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዴት እንደ ተስፋፋ ነው። በሚመጣው ሳምንትም የተሠገዎ አስተምህር በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዴት እንደ ተስፋፋ የምናጠና ሲሆን፥ ይህ ኣስተምህሮ በኢትዮጵያም ውስጥ እንዴት እንደ ተስፋፋ እንማራለን። 

የእምነት አስተምህሮን ታሪክ መማራችን ለምን ይጠቅመናል? ከክርስቶስ ጊዜ ጀምሮ ለሁለት ሺህ ዓመታት ብዙ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ወንዶችና ለቶች መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት በታማኝነት ሊነዘቡትና ሊታዘዙትም ሞክረዋል። በእነዚህ ጥንታውያን ክርስቲያኖች ትምህርት ሁለት ከመሥመር የወጡ ወይም ጽንፍ ዘለል አመለካከቶች እንዳንይዝ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል። በአንድ በኩል ትምህርታቸው ዋጋ የለውም ብለን ጨርሰን ልናጣጥለው አይገባም። ተሞክሮአቸውንና የአሳቦቻቸውን መደምደሚያ በማጥናት፥ መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት መገንዘብ እንዳለብን ከትምህርቶቻቸው ላይ ብዙ ልንማር እንችላለን። በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ አስቸጋሪ ሁኔታ በተፈጠረ ጊዜ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በመፍትሔነት በአዘጋጁት የእምነት አቋም ልዩ ትኩረት መስጠት አለብን። ነገር ግን በሌላ በኩል የእነርሱን የትምህርት ድምዳሜ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር እኩል አድርገን ማስቀመጥ የለብንም። የእነዚህ የጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ኣባቶች የእምነት አንቀጾችና ትምህርቶቻቸው በጊዜው ለአጋጠሟቸው ጉዳዮችና ችግሮች በመፍትሔነት የተጠቀሙባቸው ናቸው። እነዚህ ንጥረ ድምዳሜዎች ጠቃሚዎች ናቸው፥ ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ከተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ጋር በእኩልነት ደረጃ ሊታዩ አይገባም። ስለሆነም ድምጻሜዎቻቸውን በማጥናት ልንማርባቸው እንችላለን። ይሁን እንጂ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ በመመለስ ላለንበት ባሕል፥ ለቋንቋችንና ለትውልዳችን ምን ዓይነት ትምህርት እንደሚሰጡ ማብራራት አለብን። ዛሬ ክርስቲያኖች በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተመሥርተው የእምነት አንቀጾቻቸውንና የአስተምህሮ መሠረታቸውን ሊጽፉ ያስፈልጋል። እነዚህ የእምነት አንቀጾች ከጥንቶቹ ጋር የማይቃረኑ ሊሆኑ ይችላሉ፤ ነገር ግን ያንኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት በአዲስና ወቅታዊ ኣገላለጽ ሊያሰፍሩ ይችላሉ። 

ለሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት የእምነት አስተምህሮን ታሪክ የምናጠና ስለሆነ የተለመደውን መንገድ በመከተል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችን በመመለስ በመልሶቻቸው ላይ አንወያይም። በዚህ ፈንታ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስለሆነው ነገር በማጥናት በአጠናነው ትምህርት ላይ ለተመሠረቱት ጥያቄዎች መልስ እንሰጣለን። የጥንቷን ቤተ ክርስቲያን ታሪክን በተመለከተ በምንጭነት ብዙ መጻሕፍትን እጠቀማለሁ። ነገር ግን በተለይ «The Word Became Flesh» (ቃል ሥጋ ሆነ) ከሚለው የሚላርድ ኤሪክስን መጽሐፍ ውስጥ ለዚህ ትምህርት የሚጠቅመውን ልወስድ እወዳለሁ። 

ጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን በዓመታት መካከል ስለ ኢየሱስ ማንነት ትክክለኛ ጥርት ያለ ግንዛቤን አዳብራ ቆይታለች። ታዲያ ይህ ግንዛቤ በአመዛኙ ሊዳብር የበቃው በክርስቶስ ማንነት ላይ የተነሡትን የሐሰት ትምህርቶች ለመቋቋም በተወሰደ ምላሽ ነው። የሆኑ ቡድኖች ብድግ ብለው ስለ ክርስቶስ የተሰማቸውን ማስተማር ይጀምሩ ነበር። የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ደግሞ እነዚህን ትምህርቶች አጥንተው ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ያስተያዩ ነበር። ከዚያም መጽሐፍ ቅዱስ በትክክል የሚያስተምረውን በመግለጽ መልስ ይሰጡ ነበር። ከዚህ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ቃል አዲስ ትምህርት ስሕተቱና ትክክለኝነቱ ምኑ ላይ እንደሆነ ለይተው በደንብ ያብራሩ 

ነበር። 

ኢቢዮናውያን 

የጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን መልስ መስጠት የነበረባት በጊዜው ከተነሡት ቡድኖች መካከል አንደኛ ለሆነው ለኢቢዮናውያን ቡድን ነበር። ኢቢዮናውያን ከብዙዎቹ የቀድሞ የአይሁድ ክርስቲያኖች ሲወርድ ሲዋረድ የመጡ ናቸው። እነዚህ ሰዎች አይሁዳውያን ሲሆኑ፥ ኢየሱስንም እንደ አይሁድ መሢሕ አድርገው ይቀበሉት ነበር። እነርሱም አንድ አምላክ እንደነበርና እርሱም አይሁዶች እንደ መመሪያ አድርገው ለምን ጊዜውም የሚታዘዙበትን ሕግ እንደ ሰጣቸው አጥብቀው ያምኑ ነበር። ስለዚህ ኢስዮናውያን ሰዎች ሊድኑ ከፈለጉ ለሕጉ ተገዢ መሆን እንዳለባቸው ያምኑ ነበር። አቢዮናውያን ኢየሱስን የአይሁዶች መሢሕ አድርገው ይቀበሉት እንጂ እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን አያምኑም ነበር። አንድ አምላክ ብቻ አለ፥ ታዲያ በምን አኳኋን ሰው የሆነው ኢየሱስ እግዚአብሔር ሊሆን ይችላል የሚል ክርክር ነበራቸው። በምትኩ ኢየሱስ በተጠመቀ ጊዜ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ ወርዶ በተለየ ሁኔታ እንደ ማደጎ ልጁ አድርጎ ተቀበለው ብለው ያምናሉ። እግዚአብሔር በእርሱ ውስጥ አድሮ የመሢህን ተልዕኮ ለማሟላት ሠራ ይላሉ። ያ የተባለው ሥራ ምንድን ነበር? ኢቢዮናውያን እንደሚሉት፥ የኢየሱስ ዋነኛ ሥራ፥ ሰዎች ሕገ እግዚአብሔርን እንዲታዘዙ ማስተማር ነው ብለው ያምኑ ነበር። እኛ ከእግዚአብሔር ጋር ስምምነት ያለው ሕይወት እንድንመራ ልንከተለው የሚገባ ምሳሌያችን ሆኖ ኖረ ይላሉ። የጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን መሪዎች በዚህ በኢቢዮናውያን አስተምህሮ ላይ ሁለት ችግሮች ታይተዋቸው ነበር። በመጀመሪያ፥ ኢየሱስ ራሱ አምላክ መሆኑን መካዳቸው ሲሆን፤ ሁለተኛ፥ ሰዎች ለመዳን የእግዚአብሔርን ሕግ መጠበቅ ይገባቸዋል የሚሉት ናቸው። የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ኢሲዮናውያንን በአስተማሩት በዚህ ትምህርት አውግዛቸዋለች። ነገር ግን ይህ የተሳሳተ ትምህርታቸው ቤተ ክርስቲያን ስለ ክርስቶስ ማንነት ያልተበረዘና ጥርት ያለ ትyህርታዊ ግንዛቤን እንድታዳብር ረድቷታል። አባቶች መጽሐፍ ቅዱስን በመመርመር፥ ኢየሱስ ከመወለዱ በፊት እንኳን አምላክ እንደነበረ አረጋገጡ፥ እንደዚሁም እርሱ ለእኛ ምሳሌ ሲሆን፥ ዋና ተግባሩ ግን ስለ ኃጢአታችን መሞት መሆኑን በጥልቅ ተመለከቱ። 

ጥያቄ፡- ሀ) ኢቢዮናውያን ኢየሱስ ማን መሆኑን አመኑ? ላ) ኢቢዮናውያን እግዚአብሔር በኢየሱስ ውስጥ አደረ ብለው የሚያምኑት መቼ ነው? ሐ) ኢቢዮናውያን የኢየሱስ ዋነኛ ሥራ ምን ነበር ብለው ኣመኑ? መ) ኢቢዮናውያን ያስተማሩትን ትምህርት ብንከተል ኖሮ ዛሬ እምነታችን ምንኛ ይለወጥ ነበር? 40ኛ ጥያቄ፡- ኢየሱስ እግዚአብሔር የተጠቀመበት መልካም ሰው ነበር እንጂ አምላክ አልነበረም ብለው የሚያምኑ የምታውቋቸው ሰዎች ይኖሩ ይሆን? ከእነርሱ ያገኛችሁትን የምታውቁትን ጻፉ። ለ) ቀደም ሲል ከኣጠናችኋቸውና ስለ ክርስቶስ ማንነት ከሚናገሩ ጥቅሶች የትኞቹን አብራችኋቸው ትካፈላላችሁ? 41ኛ ጥያቄ፡- የኢየሱስ ዋና ተግባር ለእግዚአብሔር ታማኝ የመሆን ምሳሌነት ነው ብለው የሚያምኑ የምታውቋቸው ሰዎች አሉ? ስለ እነዚህ ሰዎች ያላችሁን ተሞክሮ ጻፉት። 

ከዚህ ቀደም እንደተመለከትነው ሁሉ፥ ዮሐንስ ምዕራፍ 1 እና ፊልጵስዩስ ምዕራፍ 2 ክርስቶስ ወደዚህ ምድር ሰው ሆኖ ከመምጣቱ በፊትም እንኳ ፍጹም አምላክ እንደነበረ በግልጽ ያስረዳሉ። አንዳንድ የሐሰት ትምህርቶች እንዲሁም ክርስቲያኖች ነን ብለው ራሳቸውን የሚጠሩ ሰዎች ሳይቀሩ ኢየሱስ እግዚአብሔር በውስጡ ያደረበትና የተገለገለበት ቅን ሰው ነበር ብለው ዛሬም ያስተምራሉ። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ጥርት ባለ ሁኔታ ኢየሱስ ሰው ሆኖ ከመወለዱ በፊትም ራሱ እግዚአብሔር መሆኑን ይመሰክራል። ሌላው አንዳንድ ክርስቲያኖች ደግሞ ኢየሱስ ለእኛ ምሳሌ ሊሆን የኖረውን ሕይወት ትኩረት በማድረግ የመጀመሪያውን ስፍራ ይሰጡታል። ምንም እንኳን ኢየሱስ ምሳሌያችን ቢሆንም፥ ቆየት ብለን በሚቀጥለው ትምህርታችን ውስጥ እንደምናየው እርሱ ለእኛ የኃጢአትን ይቅርታ ለመስጠት ሲል የሞተው ሞት ከሁሉም የላቀ ተግባር ነው።

ምንጭ፡- “አስተምህሮ ክርስቶስና ደኅንነት”፤ ጽሑፍ፣ በዶ/ር ስቲቭ ስራውስ፤ ትርጉም በኃይሉ ልመንህ

Leave a Reply

Discover more from

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading