ከዚህ በታች ያለው የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያ መተግበሪያን ማውረድ እና መጠቀም የሚችሉት የአንድሮይድ ሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎች ብቻ መሆናቸውን አስቀድመን ማሳወቅ እንፈልጋለን፡፡ መተግበሪያውን በስልክዎ ላይ ለማውረድ የሚከተለውን ቅደም ተከተል ተግባራዊ ያድርጉ፡፡
- በመጀመሪያ፣ ከዚሀ በታች ያለውን “የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያ መተግበሪያውን ያውርዱ” የሚለውን ሊንክ ተጭነው ለአንድ ሰከንድ ይቆዩ፤
- በመቀጠል ከቀረቡት አማራጮች መካከል “Download link ” የሚለውን በመምረጥ መተግበሪያውን ያውርዱ (download ያድርጉ)፤
- ያወረዱትን መተግበሪያ ለመክፈት ሲሞክሩ፣ በቅድሚያ “Setting” ላይ በመሄድ ለመተግበሪያው የይለፍ ፈቃድ እንዲሰጡ ይጠየቃሉ፡፡ ይህን ለማድረግ “Setting” የሚለውን በመጫን “Allow from this source” የሚለውን ይምረጡ፡፡ ይህን ሲያደርጉ “Installing apps from this source may put your phone and data at rick.” የሚል መልእክት የሚመጣ ቢሆንም፣ ወደኋላ በመመለስ ሳይሰጉ መተገበሪያውን ይጫኑ፡፡ መተግበሪያውን ከጫኑ በኋላ ለአጠቃቀሙ ከዚህ በታች የቀረበውን ባብራሪያ ይመልከቱ፡፡ መልካም ጥናት!!!
በምስሉ ራስጌ በቢጫ ቀለም የተከበበበትን ስፍራ አንዴ በመጫን የ66ቱን ቅዱሳት መጻሕፍት ዝርዝር ማግኘት ይችላሉ፡፡
በምስሉ ግርጌ በቀይ የተከበበውን አካባቢ በመጫን ደግሞ የመጽሐፉን ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡ጽሑፉን ማጋራትን ጨምሮ ሌሎች አማራጮችን ለማግኝት በሰማያዊ የተከበበውን ስፍራ አንዴ ይጫኑ፡፡
በጣም ጠቃሚ አስፈላጊ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ማጥኛ ነው። ለአቅራቢው ከልብ ማመስገን እፈልጋለሁ። ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በረከት የሆነ ድህረ ገጽ ነው። በተለይ ክርስቲያኖች በተለይ በተለይ ደሞ አገልጋዬችን የሚጠቅም የሚረዳ ነው። እግዚአብሄር እንደነዚህ ያሉትን ሥራ የሚሰሩትን ሁሉ ይባርክ ያስፋቸው።
ከዚህ በፊት በሞባያሌ አውርጄ ጭኜ ነበር ነገር ግን አብዛኞቹ ማብራርያ አይከፍትም፡፡ ስለ አንዴርድ ነው፡፡ ስለ አገልግሎታችሁ አመስግናለሁ፡፡
ለምንአይሠራም በጣም ጠቃሚ ነበር
Haw we dounlod it?
ወንድሜ፣ ለጊዜው አፑን ማውረድ የማይቻል መሆኑን ከይቅርታ ጋር እንገልጻለን፡፡