1. ሰላምታ፡- ሰላም ላንተ(ቺ) ይሁን– አስ-ሰላም አሌይኩም
ምላሽ፡- ላንተም (ቺም) ሰላም ይሁን– ዋ አሌይኩም አስ-ሰላም
2. እግዚአብሔር – አላህ (አል-ኢላህ)፣ አል (መስተዋድድ) ሲሆን ኢላህ (አምላክ) ማለት ነው፡፡
3. ታላቁ አምላክ – አላህ ታአላ (Ta’ala)
4. የከበረውና የተወደሰው እግዚአብሔር– አላህ ሱብሃናሁ ዋ ታአላ ወይም አላህ (SWT)
5. እግዚአብሔር (ከማናቸውም ነገሮች በላይ) ታላቅ ነው – አላህ -ኡ አክበር
6. በእግዚአብሔር ስም – ቢስሚላህ
7. እጅግ በጣም ሩህሩህ፣ በጣም አዛኝ በሆነው በእግዚአብሔር ስም – ቢስሚላህ – ኢር ራህማን – ኢር ራሂም
8. እግዚአብሔር ይመስገን (ሃሌሉያ) – አል-ሃምዱሊላህ
9. የሰማይና የምድር (አፅናፈ ዓለም) ጌታ – ራብ-አል አለሚን
10. መሲሁ ኢየሱስ — ዒሳ አል-መሲህ
11. አብርሃም (ሰላም ለእርሱ ይሁን ወይም በምህፃረ ቃል Pbuh) – ኢብራሂም (አላኢሂ አስ- ሰላም ወይም [ኤ፡])
12. ይስሃቅና ያዕቆብ – ኢሻቅ [ኤ፡] እና ያቁብ [a፡]
13. እስማኤል – ኢሽማኤል [a፡]
14. ሙሴና አሮን – ሙሳ [a፡] እና ሀሩን [a፡]
15. ዳዊትና ሰለሞን – ዳውድ [a፡] እና ሱለይማን [a፡]
16. መጥምቁ ዮሐንስ – ያሀ [a፡]
17. ነቢይ – ናቢ
18 ማሪያም – መርያም [a፡]
19. ገብርኤል (የመንፈስ ቅዱስ መልዕክተኛ) – ጂብሪል ወይም ሩህ -ኡል ቁዳስ
20. ሙሐመድ (ሰላምና በረከት በእርሱ ላይ ይሁን) — ሙሐመድ (ሳላላሁ አላኢ ዋ አስ – ሰላም) ወይም ሙሐመድ [s፡]
21. መጽሐፍ ቅዱስ – አል-ኪታብ- አል ሙቃዳስ
22. የሙሴ መጻሕፍት (ቶራ) – አል-ታውራት
23. የዳዊት መዝሙሮች – አል-ዛቡር
24. አዲስ ኪዳን (ወንጌል) – ኢንጂል (ሻሪፍ)
25. የነቢያት መጻሕፍት – ሱሁፍ – ኡን ነቢይን
26. ኢየሩሳሌም – አል ቃዳስ
27. የእስልምና ሃማኖታዊ ሕግ – ሸሪአ