የሕይወት እንጀራ

የሐዋርያት ሥራ

የኢየሩሳሌሙ ጉባኤ ስለ ብሉይ ኪዳን ሕግ ሚናና ስለ አሕዛብ ተወያየ (የሐዋ. 15፡1-35)

በአስተምህሮ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ የአሳብ ልዩነት በሚከሰትበት ጊዜ፥ ቤተ ክርስቲያን ምን ልታደርግ ይገባል? መሪዎች ችግሩ በራሱ ጊዜ ይፈታል ብለው ዝም በማለት መጠባበቅ አለባቸው ወይስ ጥቂት መሪዎች ብቻቸውን በጉዳዩ ላይ ውሳኔ መስጠት አለባቸው? የውሳኔው መሠረት ምን መሆን አለበት? የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ጉዳይ ላይ ያደረገችው ምንድን ነው? በአሁኑ ጊዜ ተሰሚነት ያላቸው ሰዎች የሚሰጡት አስተያየት ምንድን ነው? […]

የኢየሩሳሌሙ ጉባኤ ስለ ብሉይ ኪዳን ሕግ ሚናና ስለ አሕዛብ ተወያየ (የሐዋ. 15፡1-35) Read More »

የጳውሎስ አገልግሎት በኢቆንዮን፥ በልስጥራንና በደርቤን እና የጳውሎስና በርናባስ ወደ አንጾኪያ መመለስ (ሐዋ. 14፡1-28)

የጳውሎስ አገልግሎት በኢቆንዮን፥ በልስጥራንና በደርቤን (ሐዋ. 14፡1-20) ሉቃስ ለሦስት ዓመት ያህል የዘለቀውን የጳውሎስንና የበርናባስን አገልግሎት ያቀረበው አጠር ባለ ዘገባ ነው። ኢቆንዮን ከአንጾኪያ 100 ኪሎ ሜትር ርቃ የምትገኝ ከተማ ናት። ጳውሎስ በምኩራብ ለአሕዛብ ወንጌልን ከሰበከ በኋላ፥ ብዙ ሰዎች በክርስቶስ አመኑ ተቃውሞ ቢገጥማቸውም ጳውሎስና በርናባስ በዚያ ለተወሰነ ጊዜ ተቀመጡ። ሉቃስ በዚህ ስፍራ ተአምራት ከተፈጸሙበት ምክንያቶች ውስጥ አንዱን

የጳውሎስ አገልግሎት በኢቆንዮን፥ በልስጥራንና በደርቤን እና የጳውሎስና በርናባስ ወደ አንጾኪያ መመለስ (ሐዋ. 14፡1-28) Read More »

የጳውሎስና በርናባስ አገልግሎት በቆጵሮስ፣ ጲስዲያ እና አንጾኪያ (ሐዋ. 13፡1-52)

ተመስገን ወጣት ክርስቲያን ነው። አባቱ የቤተ ክርስቲያን መሪ ነበሩ። ተመስገን በትምህርቱ ጎበዝ ስላልነበረ የማትሪክ ውጤቱ ሳይሰምርለት ቀረ። ይህም ቀጣይ የትምህርት ዕድሉን አበላሸበት። ሥራ የማግኘት ዕድሉም የመነመነ ሆነ። «የማደርገውን አውቃለሁ። ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ ገብቼ ወንጌላዊ እሆናለሁ። በዚህ ዓይነት እግዚአብሔርን እያገለገልሁ፥ ክፍያም አገኛለሁ። ከዚህም በላይ በቤተ ክርስቲያኔ ውስጥ በሌሎች የተከበርሁ እሆናለሁ» ሲል አሰበ። ይህንንም አሳብ ለአባቱ

የጳውሎስና በርናባስ አገልግሎት በቆጵሮስ፣ ጲስዲያ እና አንጾኪያ (ሐዋ. 13፡1-52) Read More »

አይሁዶች ለሁለተኛ ጊዜ ክርስቲያኖችን አሳደዱ (የሐዋ. 12፡1-25)

ክርስቶስ ከተሰቀለ፥ ከሞት ከተነሣ፥ ወደ ሰማይ ካረገና ቤተ ክርስቲያንም ከተመሠረተች አሥራ አራት ዓመት ሆኖታል። ቤተ ክርስቲያን በአንድ ወቅት የተነሣባትን ስደት ተቋቁማለች። አሁን ደግሞ ስደት ለሁለተኛ ጊዜ ተነሳባት፡፡ ስደት በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን ላይ በተደጋጋሚ የሚደርስና በየጊዜው እየጨመረ የሚሄድ ነገር በመሆኑ፥ ሉቃስ ስለ ስደት እንዲያውቁ ፈለገ፡፡ የሁለተኛው ስደት ዋናው ቀስቃሽ ሄሮድስ አግሪጳ ነበር። ሄሮድስ አግሪጳ ይሁዳን፥ ሰማርያንና

አይሁዶች ለሁለተኛ ጊዜ ክርስቲያኖችን አሳደዱ (የሐዋ. 12፡1-25) Read More »

ጴጥሮስ የገጠመው ተቃውሞ እና የአንጾኪያ ቤተ ክርስቲያን (የሐዋ. 11፡1-30)

የኢየሩሳሌም አይሁዶች ጴጥሮስ ከአሕዛብ ጋር ሲተባበር አይተው ተቃወሙት (የሐዋ. 11፡1-18) ጴጥሮስ፥ እግዚአብሔር አድልዎን እንደማይፈቅድ ያቀረበለትን ፈተና አልፎአል። ሌሎች የአይሁድ ክርስቲያኖችስ? በሐዋርያት ሥራ 6 ላይ እንደተገለጸው የአይሁድ ክርስቲያኖች፥ በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ በአሕዛብ ላይ የነበራቸውን ጥላቻ ማስወገድ ነበረባቸው። ይህ ግን ለረጅም ጊዜ በመጥፎ ገጽታው ቀጥሎ ነበር። የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ለእግዚአብሔር አልታዘዝም፥ ባሕሉንም አልተውም ብትል ኖሮ፥ አሕዛብ ወደ

ጴጥሮስ የገጠመው ተቃውሞ እና የአንጾኪያ ቤተ ክርስቲያን (የሐዋ. 11፡1-30) Read More »

ጴጥሮስ በይሁዳና ቂሣርያ ያካሄደው አገልግሎት (የሐዋ. 9፡32-10፡48)

እስካሁን ወንጌል በሦስት ዐበይት የዓለም ክፍሎች ሊዳረስ ችሎአል። እነርሱም በኢየሩሳሌም የነበሩ አይሁዶች፥ በይሁዳ የነበሩ አይሁዶችና በሰማርያ የነበሩ ከፊል አይሁዶች ናቸው። አንድ የዓለም ክፍል ግን አሁንም ይቀራል፤ ይህም «እስከ ምድር ዳርቻ» ያለው የአሕዛቡ ዓለም ነው። ስለዚህ ሉቃስ በዚህ ክፍለ ዓለም ወንጌል እንዴት እንደ ተዳረሰ ይነግረናል። ምንም እንኳ አይሁዶች የሰማርያ ሰዎችን ቢጠሏቸውም፥ ቢያንስ ግማሽ አይሁዶች ነበሩ። የብሉይ

ጴጥሮስ በይሁዳና ቂሣርያ ያካሄደው አገልግሎት (የሐዋ. 9፡32-10፡48) Read More »

የጳውሎስ መለወጥ (የሐዋ. 9፡1-31)

በአንድ ወቅት አንድ ጫማ የሚሸጥ ሰው ነበረ። አንድ ቀን አንድ ሰው ስለ ክርስቶስ መሰከረለት። መንፈስ ቅዱስ ልቡን ለውጦ በክርስቶስ እንዲያምን ረዳው። ወዲያውኑ ሥራውን ትቶ ተነሣና መጀመሪያ ለአነስተኛ ቡድኖች፥ ከዚያም በሺህ ለሚቆጠሩ ሰዎች ስለ ክርስቶስ መመስከር ጀመረ። በምዕራቡ ዓለም ይህ ሰው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ለውጧል። ለክርስቲያን ሠራተኞች ያቋቋመው ትምህርት ቤት ዛሬም ዓለምን በመለወጥ ላይ ይገኛል።

የጳውሎስ መለወጥ (የሐዋ. 9፡1-31) Read More »

የመጀመሪያው የክርስቲያኖች ስደት እና የፊሊጶስ ምስክርነት (የሐዋ. 8፡1-40)

የመጀመሪያው የክርስቲያኖች ስደት (የሐዋ. 8፡1-3) ክርስቶስ ስደት በደቀ መዛሙርቱ ላይ እንደሚመጣ በተደጋጋሚ አሳስቦአቸው ነበር። ለብዙ ዓመት፥ ክርስቲያኖች በአይሁዶች ዘንድ ተቀባይነት አግኝተው በሰላም ይኖሩ ነበር። ምንም እንኳ አልፎ አልፎ ሐዋርያት ቢታሰሩና ቢሰደቡም፥ ጠቅለል ባለ መልኩ ሲታይ፥ ክርስቲያኖች በሰላም ይኖሩ ነበር። ከእስጢፋኖስ መገደል በኋላ ግን የአይሁድ መሪዎች ስደትን አስነሡ። በሳውል አስተባባሪነት ክርስቲያኖች እየተያዙ እስር ቤት ይጣሉ ጀመር።

የመጀመሪያው የክርስቲያኖች ስደት እና የፊሊጶስ ምስክርነት (የሐዋ. 8፡1-40) Read More »

እስጢፋኖስ የመጀመሪያው የቤተ ክርስቲያን ሰማዕት (የሐዋ.6፡8-7፡60)

ሉቃስ ስለ ጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ በሚናገርበት ጊዜ፥ ትኩረቱን ከጴጥሮስ ወደ ጳውሎስ ላይ ያደርጋል። ነገር ግን ሉቃስ መንፈስ ቅዱስ ወንጌልን እስከ ምድር ዳርቻ ለማድረስ ጳውሎስን እንዴት እንደ ተጠቀመበት ከመግለጹ በፊት፥ ቤተ ክርስቲያን በኢየሩሳሌም ተወስና ከተቀመጠችበት ሁኔታ በመነሣት በሮም ማዕከል ስለሆነችበት ሁኔታ ያብራራል። እግዚአብሔር ወንጌልን መጀመሪያ ወደ ሰማርያ፥ ቀጥሎም ብዙ አሕዛብ በክርስቶስ ወዳመኑባት እንጾኪያ ለማድረስ የተጠቀመባቸው

እስጢፋኖስ የመጀመሪያው የቤተ ክርስቲያን ሰማዕት (የሐዋ.6፡8-7፡60) Read More »

መከፋፈል በአይሁዶች መካከል (የሐዋ 6፡1-7)

በኢትዮጵያ በአንዲት ትልቅ ከተማ ውስጥ ከአንድ ትልቅ ነገድ የተገኙ ሰዎች ይኖሩ ነበር። ለሥራ ወደ አካባቢው የሄዱ የደቡብ ኢትዮጵያ ተወላጆች በአባልነት የሚሳተፉበት ቤተ ክርስቲያን በአካባቢው ነበረች። ሁሉም እንዲሰማው ሲባል አምልኮው በአማርኛ ቋንቋ ተደረገ ምንም እንኳ ትልቅ ጎሣ ከሚባለው ወገን ጥቂት ሰዎች በቤተ ክርስቲያኒቱ አምልኮ ፕሮግራም ላይ ቢገኙም፥ አገልግሎቱ በራሳቸው ቋንቋ ስለማይሰጥ ብዙዎች ቤተ ክርስቲያኒቱን እንደ ውጭ

መከፋፈል በአይሁዶች መካከል (የሐዋ 6፡1-7) Read More »