የሕይወት እንጀራ

የማቴዎስ ወንጌል

ማቴዎስ 21፡1-27

ኢየሱስ እንደ ሰላም ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ (ማቴ. 21፡1-11) በዚህን ጊዜ ከዳዊት የዘር ሐረግ የወጣ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን ከገዛ ከ600 ዓመታት በላይ አልፎ ነበር። እነዚህ ዓመታት አይሁዶች መሢሑን ሲናፍቁና ሲጠብቁ የቆዩባቸው ጊዜያት ነበሩ። ኢየሱስ ይፋዊ አገልግሎቱን በጀመረ ጊዜ፥ ሰዎች ደጋግመው የሚያነሡት ጥያቄ፥ «ይህ የዳዊት ንጉሥ ነውን?» የሚል ነበር። አንድ ቀን ንጉሣቸው በአህያ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ። ለምን በሰጋር በቅሎ ላይ ሳይሆን በአህያ ላይ ተቀመጠ? ክርስቶስ ሌላ የመጓጓዣ እንስሳ ለማግኘት የሚያስችል ገንዘብ አልነበረውም? በጥንት ዘመን አንድ ንጉሥ የሚቀመጥበት የመጓጓዣ እንስሳ ማንነቱን ያሳይ ነበር። በፈረስ ላይ ከተቀመጠ ይህ ኃይልና ሥልጣን ያለው ድል ነሺ ንጉሥ እንደሆነ ያሳይ ነበር። ነገር ግን በአህያ ላይ ተቀምጦ ከመጣ በትሕትና ሕዝቡን የሚያገለግል ሰላማዊ ንጉሥ መሆኑን ያሳይ ነበር። (ከመሳ. 10፡4፤ 2ኛ ሳሙ. 16፡1-2 ሉሎች የአይሁድ መሪዎች በአህያ ላይ ተቀምጠው መጓዛቸውን የሚያመለክቱ ምሳሌዎችን ተመልከት። ይህ ትንቢት ስለመፈጸሙ ዘካ 9፡9ን አንብብ።) ኢየሱስ በአህያ ላይ ተቀምጦ ሲመጣ አይሁዶች ከዳዊት የዘር ሐረግ የወጣ መሢሕ መሆኑን እየገለጸ እንደሆነ ተረድተዋል። በዚህ ጊዜ እጅግ ደስ ተሰኝተው እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ጀመር። ኢየሱስ ሰዎች መሢሕነቱን እንዳይናገሩ ሲያስጠነቅቅ የቆየ ሲሆን (ማቴ. 1፡9)፥ በዚህ ጊዜ ግን የተሰጠውን ክብር ተቀብሏል። የክርስቶስ የሕይወት ፍጻሜ እየተቃረበ ሲመጣ፥ ማቴዎስ አሁንም ክርስቶስ ባደረጋቸውና ጥንታዊ ትንቢቶችን በመፈጸሙ ላይ ትኩረት አድርጓል። ስለ መሢሑ መምጣት የሚናገር የብሉይ ኪዳን የተስፋ ቃል ሁሉ፥ በክርስቶስ እንደ ተፈጸመ፥ ለአይሁዶች በድጋሚ አሳይቷል። ክርስቶስን ካልተቀበሉ ሌላ መሢሕ ሊኖራቸው አይችልም ነበር። ኢየሱስ ቤተ መቅደሱን አፅዳው (ማቴ. 21፡12-17) ኢየሱስ ይናደዳል ብለን አንገምትም። ስለዚህ እርሱ የዋህ፥ ታጋሽና ደግ እንደሆነ እናስባለን። በእርግጥም ኢየሱስ በተለይ ለኃጢአተኞች እንዲህ ዓይነት ባሕርይ ያሳይ ነበር። ነገር ግን ክርስቶስ ሰዎች የእግዚአብሔርን አምልኮ ሲያበላሹ በመመልከቱ በጣም ተቆጣ። ፈሪሳውያን ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር እንዳይቀራረቡ የተሳሳተ መንገድ በማሳየታችው ተቆጣቸው። በቤተ መቅደሱ ሕዝቡ እግዚአብሔርን እንዳያማልክ ባደረጉትም ወገኖች ላይ ተቆጣ። [ማስታወሻ:- ክርስቲያኖች ሊቆጡ ይችላሉ? መልሱ፥ አዎን የሚል ነው፡፡ (ኤፌ 4፡26 አንብብ፡፡) መቆጣት ያለብን ግን ኃጢአተኛችን ሳይሆን፥ በሰዎችና በማኀበረሰቡ ኃጢአት ላይ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ክብር በሚያጎድፉ ነገሮች ላይ ሊሆን ይገባል። ብዙውን ጊዜ ግን ኃጢአትን እታገሥ በሆነ መንገድ የሚጎዱንን ሰዎች እንቆጣለን፡ ይህ ኃጢአት ስለሆነ መናዘዙ ተገቢ ነው።] የውይይት ጥያቄ:- ሀ) ብዙ ሰዎች በተሳሳተ መንገድ የሚቆጡባቸውን ጉዳዮች ዘርዝር። ለ) እግዚአብሔር ክርስቲያኖች እንዲቆጡ የሚፈልባቸውን ነገሮች ዘርዝር፡፡ ሐ) የተቆጣህነትን የመጨረሻ ጊዜ አስታውስና ይህ የጽድቅ ቁጣ ነበር ወይስ የኃጢአት? በእነዙህ በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? ሄሮድስ የሠራው ቤተ መቅደስ አራት የተለያዩ ክፍሎች ነበሩት፡፡ በውስጠኛው ክፍል የካህናት አደባባይ ይገኛል። በዚህ አደባባይ ውስጥ ቆመው ሊያመልኩ የሚችሉት ካህናት ብቻ ነበሩ፡፡ ከዚያ ቀጥሉ አይሁዳውያን ወንዶች የሚያመልኩበት የወንዶች አደባባይ ይገኛል። ሦስተኛው አይሁዳውያን ሌቶች የሚያመልኩበት የሴቶች አደባባይ ነበር፡፡ በመጨረሻም፥ ለአሕዛብ አምልኮ የተፈቀደ የአሕዛብ አደባባይ ተዘጋጅቷል። ለኣሕዛብ ከዚህ ውጫዊ አደባባይ በቀር ወደሌሎቹ አደባባዮች ለመቅረብ መሞከር ራስን ለሞት መጋበዝ ነበር፡ በዚሁ የአሕዛብ አደባባይ ነበር ነጋዴዎች ንግዳቸውን የሚያጧጡፉት። ሰዎች የአሕዛብ ገንዘቦቻቸውን ወደ ተቢው የቤተ መቅደስ ገንዘብ እንዲለውጡ የሚያስችል ገንዘብ ለዋጮች ነበሩ። እንዲሁም፥ ለመሥዋዕት እንስሳትን የሚሸጡ ሰዎች ነበሩ፡፡ የሚያሳዝነው እነዚህ ነጋዴዎች ብዙውን ጊዜ ከካህናት ጋር በመተባበርና ሕዝቡ የተፈለጉትን እንስሳት በውድ ዋጋ እንዲገዙ በማስገደድ ከፍተኛ ገንዘብ ለማትረፍ ይሞክሩ ነበር፡፡ (ይህ በፋሲካ ሰሞን ዶሮ እንደሚወደድ ማለት ነው፡፡) ኢየሱስ ነጋዴዎችን ያስወጣው ከዚህ የአሕዛብ አደባባይ ነበር፡፡ ማርቆስ ነጋዴዎቹ የአሕዛብን አምልኮ በማደናቀፋቸው ኢየሱስ በመቆጣቱ ላይ ሲያተኩር፥ ማቴዎስ የአምልኮው አካል በነበረው ሙስናና ስግብግብነት ላይ አጽንኦት ሰጥቷል፡፡ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ቢቆጣም፥ ኢየሱስ ሕዝቡን በመፈወስ ርኅራኄውን አሳይቷል። ልጆች ቀደም ሲል ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም በአህያ ላይ ተቀምጦ ሲገባ ከተደረለት አቀባበል የሰሟቸውን ቃላት በመደጋገም፣ “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ” ይሉ ጀመር፡፡ ኢየሱስ ይህ የትንቢት ፍጻሜ መሆኑ ገብቶታል። ምንም እኳ የሃይማኖት መሪዎች ባያመሰኙትም፣ ልጆች ሳያውቁ ለይተው ሊያመሰኙት ቻሉ፡፡ ኢየሱስ የበለስ ዛፍን ረገመ (ማቴ. 21:18-22)። አንድ ቀን ኢየሱስ፣ የፍሪ ምልክት በምታሳይ ዛፍ አጠገብ አለ፡፡ ነገር ግን ፍሪ ስላልነበራት ረግሞ እንድትደርቅ አደረጋት፡፡ ኢየሱስ ለምን ይህን አደረገ? ኢየሱስ በለሲቱ የእስራኤል ሕዝብ ተምሳሌት እንደሆነች ገልጾአል፡፡ እግዚአብሔር እስራኤል ለስሙ ክብርን እንድታመጣ በማሰብ ነበር የመረጣትና የፈጠራት። እንደ በለሲቱ ሁሉ፥ እስራኤልም ከርቀት ስትታይ ፍሪያማ ትመስል ነበር። በቅርብ ሲታዩ ግን አይሁዶች ፍሬ (ጽድቅ፥ ፍቅር፥ ፍትሕ) እንደሌላቸው ይታወቅ ነበር። በለሲቱ እንደ ተረገመች ሁሉ፥ አይሁዶችም ለእግዚአብሔር ፍርድ ራሳቸውን አመቻችተው ነበር። ከዚያን ጊዜ በኋላ ኢየሩሳሌም ለአርባ ዓመታት ቆይታ በሮማውያን እጅ ትደምስሳለች። ለቀጣይ 1900 ዓመታት አይሁዶች አገር አልነበራቸውም። የሃይማኖት መሪዎች የኢየሱስን ሥልጣን ተጠራጠሩ (ማቴ. 21፡23-27) ፈሪሳውያንና የሃይማኖት መሪዎች በኢየሱስ ላይ የሚሰነዝሩት የቃላት ጦርነት ቀጥሏል። መሪዎቹ ኢየሱስን በሕዝብ ፊት ለማሳጣት የሚችሉትን ጥረት ሁሉ ያደርጉ ነበር፡፡ ኢየሱስን ለማሳጣት የታሰበው የመጀመሪያው ጥያቄ የተነሣው ከሰዱቃውያን ነበር፡፡ ዋንኞቹ ካህናትና ሽማግሌዎች ለአብዛኞቹ የአገሪቱ ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ኃላፊነቶች ነበረባቸው። ዋንኛው አጀንዳቸው ሥልጣን ነበር። የእነርሱ ሥልጣን የመነጨው በአይሁዶች ላይ እንዲገዙ ከሾሟቸው ሮማውያን ነበር፡፡ ኢየሱስን ሰዎችን ከቤተ መቅደሱ ለማስወጣትና ለመፈወስ የሚያስችል ሥልጣን ከየት አገኘ? እነዚህ ነገሮች ስለ ኢየሱስ ምን እንደሚያሳዩ የመገንዘብ ፍላጎት አልነበራቸውም። የሚያሳስባቸው ጉዳይ ቢኖር፥ የእርሱ ሥልጣን የእነርሱን ሥልጣን እያደበዘዘ መሄዱ ወይም ሰዎች በሮም ላይ ቢያምፁ የሚደርስባቸው ችግር ብቻ ነበር። የክርስቶስ ሥልጣን ከሰማይ መምጣቱን ለማረጋገጥ የፈጸማቸው ተአምራትና ያስተማራቸው እውነቶች ይበቁ ነበር፡፡ እነርሱ ግን የዚህ ዓይነቱን ሥልጣን ለመቀበል አልፈለጉም። ኢየሱስ ግን የጥያቄያቸውን አፈሙዝ ወደ ራሳቸው አዞረ። በዚህ ጊዜ መጥምቁ ዮሐንስ እንደ ነቢይና ለእምነቱ እንደ ተሠዋ ጻድቅ ይታሰብ ነበር። ነገር ገን እነዚህ የሃይማኖት መሪዎች ዮሐንስ በሚያገለግልበት ጊዜ ሊቀበሉት አልፈለጉም ነበር። የሃይማኖት መሪዎቹ የዮሐንስ ሥልጣን ከሰማይ ወይ ከምድር መሆኑን ለመናገር አልፈለጉም ነበር። ሕዝቡ ዮሐንስ የእግዚአብሔር ነቢይ እንደሆነ ያምኑ ስለነበር፥ ችግር እንዳይፈጠርባቸው በመስጋት አገልግሎቱ ሰብአዊ ሥልጣን ብቻ ነበር ለማለት አልደፈሩም። ከእግዚአብሔር ነበር ካሉ ደግሞ ለምን አልሰማችሁትም? የሚል ጥያቄ ስለሚከተል፥ እንደዚያ ለማለት አልፈለጉም። ኢየሱስም ጥያቄያቸውን ለመመለስ ባለመፈለጉ ትተውት ሄዱ። (ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ.አይ.ኤም ከታተመውና የአዲስ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ ስለዚህ አስደናቂ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡)

ማቴዎስ 21፡1-27 Read More »

ማቴዎስ 20፡1-34

የወይን ሠራተኞች ምሳሌ (ማቴ. 20፡1-16) ሁላችንም ፍትሐዊ ስለሆነውና ስላልሆነው ጉዳይ ጠንካራ ግንዛቤ አለን። አንድ ሰው እኛ የምንሠራውን ሥራ እየሠራ የበለጠ ደመዎዝ ቢያገኝ እናማርራለን። በዚህም ሁሉም ሰው እኩል ሊስተናገድ እንደሚገባ እናስባለን። ይሁንና፥ እግዚአብሔር ፍትሐዊ ነው? ሁሉንም ሰው በእኩል ደረጃ ያስተናግዳል? ወይስ እግዚአብሔር የሚሠራው በፍትሐዊነት ሳይሆን በጸጋ ይሆን? ኢየሱስ ራሳችንን ከሌሎች ጋር ላለማነጻጸር ወይም እግዚአብሔር በእኩል ደረጃ እያስተናገደን መሆኑን ለመፍረድ የሚያስችል ምሳሌ ተናግሯል። ርስት የነበረው አንድ ሀብታም ሰውዩ ነበር፡፡ ይህ ሰው ሠራተኞችን ለመቅጠር ፈለገና ጠዋት በሁለት ሰዓት ላይ ወደ ከተማ ሄዶ፥ የተወሰኑ ሰዎችን አንድ ዲናር ለመክፈል ተስማምቶ ቀጠረ። አንድ ዲናር በዘመኑ የአንድ ቀን ደመወዝ ነበር፡፡ አሁንም በሦስት ሰዓት፣ በቀትርና በዘጠኝ ሰዓት ወደ ከተማ ተመልሶ ሄዶ ሌሎች ሠራተኞችን ቀጠረ። ለእነዚህ ሰዎች አከፋፈሉ ፍትሐዊ እንደሚሆን እንጂ ስንት እንደሚከፍላቸው አልነገራቸውም ነበር። ደመወዛቸውን የሚከፍልበት ጊዜ ሲደርስ አርፍዶ ለቀጠራቸው ሰዎች ቅድሚያ ሰጠ። ለእነዚህ ሰዎች የሙሉ ቀን ደመወዝ ነበር የከፈላቸው። ቀኑን ሙሉ ሠርተው የዋሉት ሰዎች ይህንን ሲመለኮቱ ደስ አላቸው። ለእነርሱ የበለጠ የሚከፍላቸው መስሏቸው ነበር። ባለ ሀብቱ ግን ለሁሉም እኩል አንድ ዲናር ሰጣቸው። “ይሄ ፍትሐዊ አይደለም” ብለው ቅር አላቸው። ቀኑን ሙሉ ሲሠራ የዋለው ሰውዬ ያማርር ጀመር። ነገር ግን እግዚአብሔር የሚሠራው በፍትሐዊነት ሳይሆን በጸጋ ነው። ሞግሱን የምናገኘው በጥረታችን ሳይሆን በነጻ ነው። ስለሆነም፥ ባለ ሀብቱ ለሁሉም ቃል የገባውን ስለ ሰጠ ፍትሐዊ ነበር። እነዚሁ መርሆዎች ለእግዚአብሔርም መንግሥት ይጠቅማሉ። እኛ ፍትሐዊነትን በምንረዳበት መልኩ እግዚአብሔር ቢሠራ ማናችንም ከዘላለም ፍርድ በስተቀር፥ ከእግዚአብሔር ምንም ነገር ልንቀበል አንችልም ነበር። ስለሆነም ከእግዚአብሔር የምንቀበለው ነገር ሁሉ ነፃ የጸጋ ስጦታ ነው። በመሆኑም እግዚአብሔር አንድ ከእኛ በላይ የስብከት ችሎታ ያለው ሰው መርጦ ከእኛ በላይ ቢከፍለው፥ ራሳችንን ከዚያ ሰው ጋር የማወዳደርም ሆነ የማማረር መብት የለንም። ምክንያቱም የተቀበልነው የሥራችንን ውጤት ሳይሆን ነጻ ስጦታ ስለሆነ ነው። የውይይት ጥያቄ፡- ሀ) ራሳችንን ከሌሎች ሰዎች ጋር ስናነጻጽርና ከእግዚአብሔር ዘንድ እኩል ወይም ፍትሐዊ መስተንግዶ እየተደረገልን እንዳልሆነ ስናስብ፥ እንዴት እንደምናዝን ወይም እንደምንቀና የሚያሳይ ምሳሌ ስጥ። ለ) በዚህ ምሳሌ መሠረት፥ ሌሎች ከእኛ የበለጡ በሚመስልበት ጊዜ ኢየሱስ ምን ዓይነት ምላሽ እንድንሰጥ የሚፈልግ ይመስልሃል? ኢየሱስ አሁንም በመንግሥቱ ስለሚኖረው አመራር አስተማረ (ማቴ 20፡17-28) ኢየሱስ በገሊላና ከሊላ ውጭ ያካሄደውን አገልግሎት ፈጽሞ ወደ ኢየሩሳለም በመጓዝ ላይ ነበር፡ ሊሰቀል ጥቂት ወራት ብቻ ቀርተውታል። በመንገድ ላይ ለደቀ መዛሙርቱ፥ ስለ መጭው ሞቱና ትንሣኤው ቢናገራቸውም፥ አእምሯቸው በግል ጉዳዮች ተይዞ ነበር። በጉዞ ላይ ሳሉ የያዕቆብና የዮሐንስ እናት ወደ ኢየሱስ መጥታ፥ ሁለቱ ልጆቿ ከእርሱ ቀጥሎ ከፍተኛ ሥልጣን እንዲኖራቸው ጠየቀች፡፡ ይህ ከፍተኛ ሥልጣን የመፈለጉ አዝማሚያ በደቀ መዛሙርቱ መካከል ክፍፍልን እንዳያስከትል ያሰጋ ነበር፡፡ ስለሆነም ኢየሱስ እንደገና ለዚህ ችግር በመመለስ ለደቀ መዛሙርቱ ሦስት ጠቃሚ ትምህርቶችን ሰጥቷል። ሀ. በእግዚአብሔር መንግሥት፤ መሪነት የሚገኘው የስደትን «ጽዋ» በመጠጣት ነው፡፡ ይህም የኢየሱስ መንገድ ወደ መስቀልና ሞት እንደመራው መሆኑ ነው። ለ. ለእያንዳንዱ ግለሰብ የሚሰጠውን የመሪነት ደረጃ የሚወስነው እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ በምድራዊ መንግሥት፥ በቤተ ክርስቲያንም ሆነ በሰማያዊ መንግሥት ነገሮች የሚወሰኑት በሰው ሳይሆን በእግዚአብሔር ነው። ስለሆነም ማንም ሰው ለመሪነት ሊታገልም ይህን ዕድል በሚያገኙት ላይ ሊቀና አይገባውም፡፡ ሐ. የእግዚአብሔር መንግሥት አመራር፥ ከሰው መንግሥት አመራር የተለየ ነው። አመራር ዝናን፥ ሀብትንና ሥልጣንን በማምጣትና በኃይል የሚፈጸም ላይሆን፥ መሥዋዕትነትንና ራስን ለሌሎች አሳልፎ መስጠትን የሚጠይቅ ነው። በእግዚአብሔር ዓይኖች ፊት ከሁሉም የሚበልጠው መሪ፣ በከፍተኛ ትሕትናና መሥዋዕትነት ሌሎችን የሚያግለል ነው። ነገር ግን አምላክ የሆነው ክርስቶስ የተናገረው ስለዚህ ጉዳይ ብቻ አልነበረም። እርሱ አምላክ በመሆኑ ሰዎች እንዲያከብሩት፥ ገንዘብ እንዲሰጡት፥ እንዲያመልኩት፣ ጥሩ ቤት እንዲያዘጋጁለት ሊጠይቅ ሲችል፥ እርሱ ይህን ሁሉ አልፈለገም፡፡ ድሀ ሆኖ እየተመላለሰ ሕይወቱን ለብዙዎች ቤዛ አድርጎ ሰጠ። “ቤዛ” አንድን ባሪያ፣ ነጻ ለማውጣት የሚከፈለውን ዋጋ ያመለክታል። ክርስቶስ በሞቱ እንድንወጣ የሚያስፈልገውን የኃጢአት ዋጋ ከፍሎልናል። መንፈሳዊ መሪዎችም ሕይወታቸውን ለሌሎች አሳልፈው መስጠት ስላለባቸው ሰማያዊ ዋጋ መክፈል ይኖርባቸዋል። የውይይት የያቄ:- በቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ መሪ መሆን የሚያስከፍላቸውን የተለያዩ መንፈሳዊ ዋጋዎች ዝርዝር ኢየሱስ ሁለት ዓይነ ስውራንን ፈወሰ (ማቴ 20፡29-34) ኢየሱስ ለሁለት ዓይነ ስውራን በሰጠው ምላሽ፣ የመሢሕነት ኃይሉን ከማሳየቱም በላይ አመራር እንዴት ሊካሄድ እንደሚገባ ምሳሌ ሰጥቷል። አይነ ስውራኑ ኢየሱስ የዳዊት ልጅ እንደሆነ በመግለጽ እንዲፈውሳቸው ተማጥነውታል። ምንም እንኳ ሥራ ቢበዛበትና ወደሚሞትባት ኢየሩሳሌም በመሄድ ላይ የነበረ ቢሆንም፥ ኢየሱስ የዓይነ ስውራኑን ልመና በማድመጥ ዓይኖቻቸውን ፈውሷል። ይህ ራሱን ለሰዎች አሳልፎ እንደ ሰጠ ያመለክታል። (ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ.አይ.ኤም ከታተመውና የአዲስ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ ስለዚህ አስደናቂ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡)

ማቴዎስ 20፡1-34 Read More »

ማቴዎስ 19፡1-30

ኢየሱስ ስለ ጋብቻና ፍቺ አብራራ (ማቴ. 19፡1-12) አብዛኞቹ ሰዎች ግልጽ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትእዛዝ በማይኖርበት ጊዜ፥ በደንቦችና ሕግጋት ለመተዳደር ይፈልጋሉ፡፡ ግልጽ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትእዛዝ በማይኖርበት ጊዜ፥ «ይህን ላደርግ እችላለሁ?” ለሚለው ጥያቄ መልስ ይፈልጋሉ፡፡ ሌሎች ከሕይወታቸው ጋር ስለማያዛምዷቸው ሥነ መለኮታዊ እውነቶች ይከራከራሉ፡፡ በኢየሱስ ጊዜ፥ የሃይማኖት መሪዎች ከተከራከሩባቸው ጉዳዮች አንዱ የፍች ጥያቄ ነበር፡፡ በወቅቱ ሁለት ቡድኖች የነበሩ ሲሆን፥ አንደኛው ወገን ፍች በዝሙት ምክንያት ብቻ ሊካሄድ እንደሚችል ያስተምር ነበር። ሁለተኛው ወገን አንድ ሰው ባሻው ምክንያት ሚስቱን ሊፈታ እንደሚችል ይገልጽ ነበር። ሚስቱ ወጥ ካሳረረች ወይም ከእርስዋ የተሻለች ቆንጆ ልጃገረድ ካገኘ ሊፈታት ይችል ነበር። ኢየሱስ ሕይወትን የሚመለከተው በተለየ ዓይን ነው። ፍሬ በሌላቸው ሥነ መለኮታዊ ክርክሮች ላይ ጊዜውን ለማሳለፍም ሆነ ሰዎች የሚያደርጓቸውን ተግባራት ዝርዝር ለመስጠት ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ ከተግባራት በስተ ጀርባ ባሉት መርሆዎች ላይ ያተኩር ነበር። ስለሆነም የትኛውም ፈሪሳዊ ከፈልገው በላይ አጥልቆ በመመልከት የጋብቻን ዓላማ መርምሯል። ኢየሱስ ያለዝሙት ምክንያት መፋታት እንደማይቻል የሚያስተምረውን ቡድን አሳብ ቢቀበልም፥ በእግዚአብሔር ፍጹማዊ አሳብ ላይ ትኩረት አድርጓል። እግዚኣብሔር ጋብቻን የፈጠረው ሁለት ሰዎች በሥጋ፣ በአሳብ፥ በልብና በዓላማ አንድ ይሆኑ ዘንድ ነው። ጋብቻን ከዚህ አሳንሶ የሚመለከት ማንም ሰው ከእግዚአብሔር ፍላጎቶችና ፈቃድ ውጭ ይኖራል። የውይይት ጥያቄ- ሀ) ሦስት አማኞች መልካም ጋብቻ ምን ዓይነት እንደሆነ እንዲገልጹ ጠይቃቸው። በባልና በሚስት መካከል ሊኖር የሚገባው ምን ዓይነት እንኙነት ነው? ለ) በባልና በሚስት መካከል ሊኖር የሚገባው ምርጥ የዕለት ተዕለት እንኙነት ምን ዓይነት ይመስልሃል? ኢየሱስ ልጆችን ያከብራል (ማቴ. 19፡13-15) ልጆች ለኢየሱስ አስፈላጊዎች ናቸው? ይህ ታሪክ ኢየሱስ ልጆች በጣም አስፈላጊዎች ናቸው ብሎ እንደሚያስብ በግልጽ ያሳያል። እርሱ ፍቅሩን ለልጆች ለማሳየት ጊዜ አጥቶ አያውቅም። እኛስ? ለዚህ ክፍል ተጨማሪ ማብራሪያ በማቴ. 18፡1-9 ላይ የተሰጠውን አስተያየት አንብብ።) ኢየሱስን ለመከተል የፈለገ ሀብታም ወጣት ሹም (ማቴ. 19፡16-30) በክርስትና ሕይወት ከሚያጋጥሙን ዐበይት አደጋዎች አንዱ ከክርስቶስ በላይ ሌላ ነገርን መውደድ ነው። ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ፥ በመዝሙር በማገልገል፥ በመጸለይና በመስበክ ጥሩ ግብረገባዊ ሕይወት ብንመራም፥ የገንዘብ፥ የሰው ወይም የትምህርት የመሳሰለ ሌላ ፍቅር ከልባችን ውስጥ ተሰውር ሊቀመጥ ይችላል። ነገር ግን የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ለመሆን ከፈለግን፥ ከሁሉም በላይ እርሱን ልንወድ ይገባል። ከእርሱ ጋር ያለን ግንኙነት ከየትኛውም ነገር በላይ አስፈላጊ ነው። ማቴዎስ ይህን እውነት ለማብራራት ምሳሌ ሰጥቷል። ኣንድ ቀን አንድ ሀብታም ወጣት ወደ ኢየሱስ መጣ፡፡ ይህ ወጣት የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት ይችል ዘንድ ኢየሱስ እንድ ትእዛዝ ወይም ቀለል ያለ ነገር እንዲሰጠው ጠየቀ፡፡ ኢየሱስ ሰውዬው ግብረገባዊ ሕይወት እንደሚመራ ያውቅ ነበር። ዐሥርቱን ትእዛዛት በሙሉ እንደ ጠበቀ ሲናገር፥ ኢየሱስ አልጠረጠረውም። ይህ ሰው ወደ ቤተ ክርስቲያናችን ቢመጣ ኖሮ፥ በደስታ ተቀብለን የኳየር ዘማሪ ወይም የሽማግሌዎች ቦርድ አባል እናደርገው ነበር። ግለሰቡ ጥሩ ሰው፣ ቀናተኛና ሀብታም ነበር። ኢየሱስ ግን ከጥሩ ውጫዊ ማንነቱ አጥልቆ ወደ ልቡ ተመለከተ። ለሰውዬው የግል ጣዖት የሆነበት ሌላ ፍቅር ነበረው። ያም የገንዘብ ፍቅር ነበር። ስለሆነም፥ ኢየሱስ ከጣዖቱ እንዲላቀቅ ጠየቀው። “ገንዘብህን ተወውና ደቀ መዝሙሬ ልትሆን ትችላለህ” አለው። ሰውዬው ግን ገንዘቡን በጣም ይወድ ስለነበር፡ አዝኖ ኢየሱስን ትቶ ተመልሶ ሄደ። ኢየሱስ በሰው ልብ ውስጥ አንድ ተቀዳሚ ፍቅር ብቻ ሊኖር እንደሚገባ አስተምሯል፡፡ ይህም ለእግዚአብሔር የሚኖረን ፍቅር ነው። አንድ ነገር በጣም አስፈላጊ ቢሆንብንና ኢየሱስ ያንን «ተው» በሚለን ሰዓት ፈቃደኞች ባንሆን፥ ነገሩ ጣዖት ይሆንብናል ማለት ነው። ለብዙ ሰዎች እግዚአብሔርን ከሁሉም በላይ እንዳይወዱት የሚቀናቀናቸው ገንዘብ ነው። ለሌሎች ትምህርት ነው። ለምሳሌ፥ ለአብርሃም ልጁ ይስሐቅ ጣዖት ሊሆንበት ይችል ነበር። ለዚህም ነው እግዚአብሔር ይስሐቅን እንዲሠዋለት የጠየቀው። አብርሃም እግዚአብሔርን ከሁሉም በላይ እንደሚወድ በማሳየቱ የጣዖት አደጋ ይሆንበት የነበረ የልጁ ይስሐቅ ፈተና ተወገደለት፡፡) ወጣቱ ባለጸጋ ከዘላለማዊው ሕይወት ይልቅ ጊዜያዊው ሀብት ስለ በለጠበት ኢየሱስን ላለመከተል መረጠ። በአንጻሩ ጴጥሮስና ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን ለመከተል ሲሉ ዋስትናቸውንና ምድራዊ ሀብታቸውን ሁሉ ወደ ጎን ትተዋል። እንግዲህ ምን ያገኙ ይሆን? ጊዜያዊና ዘላለማዊ ሽልማቶችን ያገኛሉ? ኢየሱስ በዘላለማዊ መንግሥቱ ውስጥ ሥልጣን እንደሚኖራቸው ገልጾላቸዋል። አንዳንድ ምሑራን የደቀ መዛሙርቱ በአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ላይ መንገሥ፣ በሺህ ዓመቱ ዘመን፥ ደቀ መዛሙርቱ ከክርስቶስ ጋር እንደሚነግሡ ያሳያል ይላሉ። ምናልባትም ይህ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ሥልጣን እንደሚኖራቸው የሚያመለክት ይሆናል፡፡ የዘላለም ሕይወትም ይኖራቸዋል። ሁለተኛ፥ በምድር ላይ ሥጋዊ ቤተሰቦቻቸውን ሊያጡ ቢችሉም፥ ይበልጥ አስፈላጊ የሆኑ መንፈሳዊ ቤተሰቦች ይኖሯቸዋል። የውይይት ጥያቄ፡- ሀ) ፍቅራችንን በመካፈል ክርስቲያኖች በሙሉ ልባችን ኢየሱስን እንዳንወድና እንዳንከተል ሊያደርጉ የሚችሉ አንዳንድ ነገሮች ምንድን ናቸው? ለ) አንዳንድ ጊዜ በልብህ ኢየሱስ እንዳይነግሥ ጣዖት አድርገህ የምታስቀምጣቸው ነገሮች ምንድን ናቸው? ሐ) ልብህን መርምርና ለኢየሱስ ብለህ የምታስወግደው ነገር ካለ ተመልከት፡፡ አሁኑኑ ይህንኑ አድርግ፡፡ (ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ.አይ.ኤም ከታተመውና የአዲስ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ ስለዚህ አስደናቂ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡)

ማቴዎስ 19፡1-30 Read More »

ማቴዎስ 18፡15-35

የእግዚአብሔር ደቀ መዝሙር መሆን ማለት ስለ ኃጢአትና ስለ ተበላሸ ግንኙነት መጨነቅን ይጠይቃል (ማቴ 18፡15-20) በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ኃጢአትና የተበላሸ ግንኙነት በሚከሰትበት ጊዜ፥ ሰዎችን በሦስት መንገዶች እናስተናግዳለን። በመጀመሪያ፣ ጉዳዩን ችላ ብለን እንተወዋለን። ይህም፥ ሁሉም ኃጢአት ይፈጽማል፣ ሰዎች ሁልጊዜም በትግል ላይ ናቸው፡፡ እኔ ምን ላደርግ እችላለሁ? ይህ የእኔ ሥራ አይደለም” የሚል ምክንያት እናቀርባለን፡፡ ይህም መከፋፈል እንዲበዛ፥ ኀጢአት እየጨመረ እንዲሄድ እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን ኅብረትና ምስክርነት፣ ደግሞም የክርስቶስ ስም እንዲሰደብ ያደርጋል። ሁለተኛ፥ ስለ ጉዳዩ ማውራት እንጀምራለን፡፡ «ለእገሌ ትጸልይለታለህ? እባክህ በዝሙት ወድቋል፡፡ እገሌና እገሌ እየተጣሉ መሆናቸውን ታውቃለህ? ለእነዚህ ሰዎች መጸለይ አለብን፡፡ ስለ እኔ ምን እንዳለች ታውቃለህ?» እያልን ለሌሎች እናወራለን፡፡ ብዙውን ጊዜ በኀጢአት ስለወደቁት ወይም በጠብ ውስጥ ስላሉት ሰዎች መንፈሳዊ ሽሙጥን የተላበሰ ቃል እንናገራለን። ጉዳዩን በጸሎት ርእስነት ብናቀርበውም፥ የሚያስደስተን ስለተከሰተው ችግር ለሰዎች ማውራቱ ነው። ይህም ቤንዚን እንደ ተጨመረበት እሳት መከፋፈሉንና ኃጢአቱን ያባብሰዋል። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ኃጢአትና መከፋፈል ሲደርስ እንድንጠቀምበት የተፈቀደልንን ብቸኛና ሦስተኛ አማራጭ ኢየሱስ ሰጥቶናል። እዚህ ላይ ችግሩን ቸል እንድንል ወይም ለሌሎች እንድናወራ አልተፈቀደልንም። እንዲህ ዓይነት ችግሮችን ለመፍታት ኢየሱስ ያቀረባቸው ዘዴዎች ምንድን ናቸው? ሀ. የኃጢአትንና የተበላሸ ግንኙነት ምክንያት መመርመር የእያንዳንዱ ክርስቲያን ኃላፊነት ነው፡፡ ክርስቶስ አንድ ሰው ከበደለን፥ ስለ ጉዳዩ ለመነጋገርና አለመግባባትን ለማስወገድ የመጀመሪያውን እርምጃ መውሰድ እንዳለብን ተናግሯል። ነገር ግን የማቴዎስ 7፡1-5ን መርሆዎች ማወቁ ጠቃሚ ነው፡፡ ልባችንን በመመርመር የትኛውንም የኃጢአት “ምሰሶ”፥ ማለትም ጥላቻ ወይም ቁጣ ከሕይወታችን ማስወገድ አለብን፡፡ ከዚያ በኋላ በክርስተቶስ (ወንድማችን ወይም እኅታችን) ከሆነው ሰው ጋር ልንወያይ እንችላለን። ለ. ችግሩ በወሬ መዛመት የለበትም፡፡ ስለ ጉዳዩ ደብዳቤ መጻፍም ሆነ ለጓደኛ ማውራት አያስፈልግም፡፡ በቀጥታ ወደ በደለን ግለሰብ ሄደን በደሉን በመግለጽ፣ ለኑዛዜ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ይኖርብናል። ዓላማችን ፍርድ ሳይሆን፥ ይቅርታና ዕርቅ መሆን አለበት፡፡ ሐ. የኃጢአቱ ምንነት ከታወቀ በኋላ፣ “ግለሰቡ ንስሐ ገብቶ ወደ እውነት ለመመለስ ካልፈለገ፣ ሁለት መንፈሳውያን ሰዎች ምስክር እንዲሆኑ አድርግ። እነዚህ አንተን የሚደግፉ ጓደኞችህ ላይሆኑ፥ ትክክለኛ ጥያቄዎችን የሚጠይቁ ትክክል የሆነውን እና ስሕተት የሆነውን የሚለዩ እንዲሁም ግልጽ ብያኔ ሊሰጡ የሚችሉ መንፈሳውያን ሰዎች ሊሆኑ ይገባል። (ዋናው ነገር አንደኛው ጥፋተኛ መሆኑና ሌላኛው ትክክል መሆኑ ሳይሆን፥ ኃጢአትን ለማስወገድና የተበላሸውን ግንኙነት ለማደስ የማይፈልግ ሰው በሚያጋጥምበት ጊዜ እንዴት ምላሽ መሰጠት እንዳለብን ማወቁ ነው፡፡) አሁንም በሐቆቹ ላይ ውይይት ተካሂዶ አድልዎ የሌለበት ፍርድ መሰጠት አለበት። ሦስት ሰዎች ብቻ ጉዳዩን ማወቃቸው የግለሰቡን አእምሮ ለመለወጥና ወደ ንስሐ ለመምራት ሊቀልል ይችላል። መ. ግለሰቡ ንስሐ ለመግባት ባይፈልግና ግንኙነቱ ባይጠገንስ? ለለ ጉዳዩ ልንዘናጋና እግዚአብሔር እንዲያስተካክለው ልንተወው ይገባልን? ኢየሱስ «አይሆንም!» ብሏል። ኃጢአትና መከፋፈል የኋላ ኋላ ጠቅላላይቱን ቤተ ክርስቲያን ስለሚያጠፉአት፣ እንደ እባጭ የሚወገድበትን መንገድ መፈለግ ያሻል። ስለሆነም፥ ሽማግሌዎቹ ጉዳዩን በግልጽ ወደ ቤተ ክርስቲያን ማምጣት አለባቸው። ችግሩን ገልጸው ለመፍታት የሞከሩባቸውን መንገዶች ማብራራት አለባቸው። ከዚያም ግለሰቡን (ካልታዘዝ) ከቤተ ክርስቲያን አባልነት መሰረዝ ይኖርባቸዋል። ግለሰቡን እንደ አረማዊ ወይም ቀራጭ መቁጠር ማለት መጥላትን ኣያመለክትም፡፡ ነገር ግን የቤተሰቡ አባል እንዳልሆነ መቍጠር ማለት ነው። የዚህ እርምጃ ዓላማ ኃጢአትን ማስወገድ ብቻ ሳይሆን፥ ዕርቅም ጭምር ነው። ጳውሎስ ይህንን ሂደት «ለሰይጣን አሳልፎ መስጠት» ሲል ይጠራዋል (1ኛ ቆሮ. 5፡5)። ግለሰቡን ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እንክብካቤ በማስወጣታችን፥ እግዚአብሔር ንስሐ ይገባ ዘንድ እንዲፈርድበት መጠየቃችን ነው፡፡ የውይይት ጥያቄ፡- ሀ) በቤተ ክርስቲያንህ ውስጥ መከፋፈልን ስላስከተለ ወይም በማስከተል ላይ ስላለ ኃጢአት ግለጽ። የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ችግሩን ለማስተካከል ምን እርምጃ ወሰዱ? ለ) በማቴ. 18፡15-20 ላይ በመመሥረት እንዴት ሊያስተካክሉት ይገባ ነበር? ኢየሱስ ክርስቲያኖችና ሽማግሌዎች ይህን ሂደት በሚከተሉበት ጊዜ፥ በሥልጣኑ ሊጠቀሙ እንደሚችሉ ገልጾላቸዋል። ኢየሱስ የዘረዘራቸውን ደረጃዎች ከተከተሉ በኋላ ግለሰቡን ለፍርድ አሳልፈው ሊሰጡ ይችላሉ። ይቅርታ ከተደረገም ግለሰቡ ሙሉ በሙሉ ይቅር መባሉን ሊያሳውቅ ይችላል። የክርስቶስ ደም ኃጢአትን ሁሉ ይሸፍናልና። ኢየሱስ አንድነት፥ ለመንፈሳዊ ጤንነትና ለቤተ ክርስቲያን ኃይል በጣም አስፈላጊ መሆኑን ገልጾአል፡፡ ክፍፍል ካለ፣ እግዚአብሔር ተግባሩን በሚገባ አያከናውንም፡፡ አንድነት ካለ ግን የሰዎቹ ቁጥር ሁለት ወይም ሦስት ቢሆንም፣ አማኑኤል የሆነው ኢየሱስ ጸሎታቸውን ለመስማት በመካከላቸው ይኖራል። ክርስቶስ ስለ ይቅርታና ምሕረት ኣስተማረ (ማቴ. 18፡21-35) አንድ ሰው ሌላውን በመበደሉ ምክንያት ክፍፍል በሚከሰትበት ወቅት፥ ሁለት ችግሮች ሊከሰቱ ይችላሉ። በመጀመሪያ፣ ይቅርታንና ዕርቅን ያለመፈለግ ችግር ሊኖር ይችላል። ኢየሱስ የተበደለው ግለሰብ እንኳ ለዕርቅ የመጀመሪያውን እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባ በመግለጽ፥ በመጨረሻው ክፍል ለዚህ ጉዳይ እልባት ሰጥቷል። አይሁዶች አንድ ሰው ሦስት ጊዜ ይቅር ማለት እንዳለበት ያምኑ ስለነበር፥ ጴጥርስ ሰባት ጊዜ ሲል ጉዳዩን ያጋነነው መስሉት ነበር፡፡ ክርስቶስ ቀን 490 ጊዚያት ማለትም ሁልጊዜ ይቅር ማለት እንዳለብን ተናግሯል በደልን መቁጠር የለብንም (1ኛ ቆሮ. 13፡5)። ሌሎችን ይቅር ለማለት አለመፈለጉ ምን ያህል የሞኝነት ተግባር እንደሆነ ለማሳየት፣ ኢየሱስ የሁለት ባሪያዎችን ምሳሌ ተናገረ። አንደኛው ባሪያ ከጌታው እንድ ሚሊዮን ብር ተበድሮ ነበር። እንዲከፍል በተናገረው ጊዜ ምሕረት በመጠየቁ፣ ይቅር ተባለ። ሌላ ባሪያ አንድ ሚሊዮን ብር ከተበደረው ባሪያ ጥቂት ገንዘብ ተበድሮ ነበር፡፡ እንዲከፍለው በጠየቀው ጊዜ ምሕረትን እንዲያደርግለት ለመነው፡፡ ሰውዬው ግን ምሕረትን ለማድረግ ስላልፈለገ፥ አሳሰረው። የባሮቹ ጌታ ስለ ጉዳዩ በሰማ ጊዜ፣ የመጀመሪያውን ባሪያ በጭካኔው በከፋ ሁኔታ ቀጣው፡፡ በዚህ ምሳሌ ውስጥ በባሮቹ ጌታ የተመሰለው እግዚአብሔር ሲሆን የመጀመሪያው ባሪያ ሁላችንንም ይወክላል፡፡ ሁላችንም በእግዚአብሔር ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኃጢአቶች የፈጸምን ቢሆንም፥ ምሕረትን በጠየቅን ጊዜ ግን ይቅር ይለናል። ከዚህ እንጻር አንድ ሰው በእኛ ላይ የሚፈጽመው ኃጢአት የጥቂት ገንዘብ ዕዳ ያህል ነው። እንዲህ ዓይነቱን አነስተኛ ኃጢአት ይቅር ለማለት ባንፈልግ፣ የእግዚአብሔርን ጸጋና ምሕረት በትክክል አልተረዳንም ማለት ነው። ይህም ከእግዚአብሐር አሰቃቂ ቅጣት እንድንቀበል ያደርጋል። የውይይት ጥያቄ፡- ሀ) ብዙውን ጊዜ ሰዎች በቃል ብቻ ሳይሆን ከልባቸው ይቅር ለማለት ባለመፈለጋቸው አለመስማቶችና ክፍፍሎች እየጨመሩ ይሄዳሉ። ለዚህ አንድ ምሳሌ ስጥ፡፡  ለ) የሌሎችን ኃጢአት ይቅር ለማለት በማንፈልግበት ጊዜ፥ ኢየሱስ አግዚአብሔር ኃጢአታችንን ይቅር ስለ ማለቱ ምን አስተማረ? ሐ) በቤተ ክርስቲያንህ ክፍፍል ካለ፣ ይህንን ምንባብ እንዴት አድርገህ ታስተምራለህ? (ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ.አይ.ኤም ከታተመውና የአዲስ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ ስለዚህ አስደናቂ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡)

ማቴዎስ 18፡15-35 Read More »

ማቴዎስ 18፡1-14

እጅጉ በጣም የተከበረ የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አባል ነበረ። ሁልጊዜም ችግር የሚገጥማቸውን ሰዎች ከመርዳት አይቆጠብም ነበር። በጽጻት፥ ወንበሮችን በማስተካከል፥ በሌላም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተግቶ ያገለግል ነበር። በዚህ አገልግሎቱ ምክንያት ለሽምግልና አገልግሎት ተመረጠ። ከዚያ በኋላ ግን ባሕርዩ ተቀየረ፡፡ እንደ በፊቱ ሰዎችን በመርዳት ፈንታ ማዘዝ ጀመረ። አሳቡን የሚቀናቀን ሰው ሁሉ ያበሳጨው ጀመር፡፡ የሽምግልና ሥልጣኑን የሚያጠናክርባቸውን መንገዶችና፥ በሥልጣኑ ራሱንና ቤተሰቡን የሚረዳባቸውን ስልቶች መወጠን ጀመረ። የውይይት ጥያቄ፡- ሀ) ብዙ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ሥልጣን ካገኙ በኋላ፥ ባሕሪያቸው የሚቀየረው በምን መንገዶች ነው? ለ) ይህ የሚሆነው ለምን ይመስልሃል? ቀደም ብለን ማቴዎስ በአምስት የማስተማሪያ ክፍሎች ላይ እንደሚያተኩር ገልጾልናል። የመጀመሪያው ማቴዎስ 5-7 ነው። ቀጣዩ በምዕራፍ 3 የቀረቡትን ብዙ ምሳሌዎች ይይዛል። ሦስተኛው ማቴዎስ 18 ሲሆን፥ በደቀ መዝሙርነት ላይ ያተኩራል። ኢየሱስ ስለ መሪነትና በእግዚአብሔር መንግሥት ታላቅ ስለ መሆን አስተማረ (ማቴ. 18፡1-9)። ደቀ መዛሙርቱ ባለማቋረጥ ከሚነጋገሩባቸው ጉዳዮች ኣንዱ፥ በክርስቶስ መንግሥት ታላቅ መሪ ስለ መሆን ነበር። ክርስቶስ አልፎ በተሰጠባት ምሽት እንኳ፥ ስለዚህ ጉዳይ ይነጋገሩ ነበር። (ሉቃስ 22፡24-30 ኣንብብ።) ማቴዎስ የተሳሳተ የመሪነት ግንዛቤ ለቤተ ክርስቲያን እጅግ አደገኛ ከሆኑት ነገርች አንዱ መሆኑን በመገንዘብ፥ ክርስቶስ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት አመራር የገለጻቸው የተለያዩ ታሪኮችን በወንጌሉ ውስጥ አካትቷል። በኣይሁድ ባሕል የአንድን ሰው የሥልጣን ደረጃ ማወቁ አስፈላጊ ነበር፡፡ አይሁዶች ብዙውን ጊዜ አንድ ሰው ከእነርሱ በላይ የተከበረ መሆን አለመሆኑን ለማወቅ ይፈልጉ ነበር፡፡ ስለሆነም ደቀ መዛሙርት፥ ክርስቶስ በመንግሥቱ ውስጥ ያላቸውን ደረጃ ከታላቁ እስከ ታናሹ በመግለጽ፥ ማንን እንደሚያከብሩና ማን እንዲያከብራቸው ለማወቅ ጠየቁት። ኢየሱስ የእርሱ የአመራር መንገድ ሙሉ በሙሉ ከዓለም የተለየ እንደሆነ ገለጸላቸው። የእርሱ አመራር ኃይልና ሥልጣን የሚንጸባረቅበት ሳይሆን፥ ትሕትና ራስ ወዳድ አለመሆንና ፍጹም መተማመን የሚሰፍንበት እንደሆነ አብራራላቸው። ኢየሱስ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንዴት መግባት እንዳለብን ለማሳየት፣ ልጆችን እንደ ምሳሌ አድርጎ አቅርቦላቸዋል። የክርስቶስ መንሥት አባል ለመሆን የሚፈለግ ሰው፣ መሠረታዊ እሴቶቹን መቀየር አለበት። ዛሪ በብዙ አገሮች እንደሚታየው በአይሁድ ኅበረሰብ፥ ልጆች ብዙም ትኩረት አይሰጣቸውም ሰዎች ልጆችን ቢወዱም፥ ከእነርሱ ጋር በመነጋገር፣ በማስተማር ወይም አሳባቸውን በመስማት ብዙ ጊዜ አያጠፉም «ልጅ ምን ሊያስተምረኝ ይችላል?» ብለው ያስባሉ። ነገር ግን ልጆች በእግዚአብሔር መንግሥት መሠረታዊ የሆኑ ሁለት ብቃቶች አሏቸው። በመጀመሪያ፣ ሙሉ በሙሉ በሰዎች ይተማመናሉ። አንድ ልጅ አንድን ሰው ካወቀና ካመነ፥ ሁልጊዜም ከልቡ ያምነዋል። ትንሽ ልጅ የሚያምነው ሰው እንደሚይዘው ካወቀ ከዛፍ ላይ እንኳ ያለፍርሃት ሊዘልል ይችላል። የእግዚአብሔር ልጆችም በክርስቶስና በሰማያዊ አባታችን ላይ ፍጹማዊ እምነት ሊኖራቸው ይገባል። ሁለተኛ፥ ትንሽ ልጅ ለማኅበራዊ ሥልጣን ግድ የለውም ትንሽ ልጅ ታላቅ ወይም ታናሽ መሆኑ፥ ማን ትልቅ ወይም ትንሽ መሆኑ፣ የየትኛው ጎሳ አባል መሆኑ እያስጨንቀውም። በትንሽ ልጅ አመለካከት አስፈላጊው ነገር የፍቅር ግንኙነት መኖሩ ብቻ ነው። በእግዚአብሔር መንግሥትም፣ አስፈላጊው ጉዳይ ብዙ ሥልጣን ወይም የሌሎችን እክብሮት መሻት ሳይሆን፣ እግዚአብሔርን መውደድና እርስ በርስ መዋደድ ነው። ማኅበራዊ የሥልጣን ደረጃ በዓለም አስፈላጊ ቢሆንም፥ በቤተ ክርስቲያን ስፍራ የለውም፡፡ እግዚአብሔር መማር አለመማራችንን ነጋዴ ወይ ገበሬ መሆናችንን፥ የተራ ወይም የንጉሥ ቤተሰብ መሆናችንን፥ አይጠይቅም። እነዚህ ሁሉ አስፈላጊዎች አይደሉም። አስፈላጊው የእዚአብሔር ቤተሰብ አካል መሆናችን ነው፡፡ ኢየሱስ ልጆችን በምሳሌነት በመጠቀም በሁለት ደረጃዎች አማካይነት ተናሯል። በመጀመሪያ፣ ስለ ሥጋዊ ልጆች ተናገሯል። በቤተ ክርስቲያን ወላጆችና አዋቂ ሰዎች ልጆችን ችላ ማለት የለባቸውም። ልጆች በእግዚአብሔር ዓይኖች ፊት ከፍተኛ ግምት የሚሰጣቸው ናቸው። ስለሆነም በአንድ ሰው መጥፎ ቃላት፥ ተግባራት ወይም የማስተማር ጉድለት ትንሽ ልጅ ከእግዚአብሔር ከራቀ፥ እግዚአብሔር አሰናካዩን ሰው በኃላፊነት በመጠየቅ ይፈርድበታል። ኢየሱስ ስለዚህ ጠንካራ አገላለጽ ተጠቅሟል። ይህ ኃጢአት በእግዚአብሔር ዓይኖች ፊት በጣም ከባድ ነው፥ ይህን ኃጢአት በልጆች ላይ የሚፈጽሙ ወፍጮ በአንገቱ ላይ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ወይም ሰውነትን ከመቆረጥ የከፋ ቅጣት እንደሚያስከትል ገልጾአል። በዓለም ሁሉ ከሚገኙ ክርስቲያኖች ከ80 እጅ በላይ የሚበዙት በክርስቶስ ያመኑት፣ ከ15 ዓመት ዕድሜያቸው በፊት ነው። ይህም ሆኖ በአብዛኞቹ አብያተ ክርስቲያናት ለዚህ የዕድሜ ክልል ትኩረት ሲሰጥ አይታይም፡፡ ትናንሽ ልጆች ገና በስሜት የሰከኑ አይደሉም። ስለሆኑም፣ የእግዚአብሔርን ፍቅር ካላሳየናቸውና የማመን ዕድል ከነፈግናቸው ወይም አዋቂዎች ለእግዚአብሔር እንዴት እንደሚኖሩ ካላሳዩዋቸው፥ በቀላሉ ከእግዚአብሔር ፊታቸውን ሊያዞሩ ይችላሉ። ነገር ግን በአዋቂዎች ላይ ጥሩ ምሳሌዎችን ከተመለከቱ፥ በፍጥነት ሊያምኑና እንደ ሳሙኤል ከልጅነታቸው ጀምር እግዚአብሔርን ሊያገለግሉ ይችላሉ (1ኛ ሳሙ. 2-3)። ሁለተኛ፥ ይህ በቤተ ክርስቲያን መሪዎችና ምእመናን (እነርሱም ለእግዚአብሔር እንደ ትናንሽ ልጆች በመሆናቸው) መካከል ሊኖር ስለሚገባው ግንኙነት ጠቃሚ ትምህርት ይሰጣል። መሪዎች ምእመናንን የሚያስተናግዱበት ሁኔታ በጣም አስፈላጊ ነው። መሪዎች በቃላቸው፥ በተግባራቸው ወይም በአመለካከታቸው፥ እነዚህ መንፈሳዊ ልጆች ከእምነት እንዲመለሱና በኃጢአት እንዲወድቁ ካደረጓቸው፥ የእግዚአብሔር ቅጣት ያይልባቸዋል። የውይይት ጥያቄ፡- ሀ) በብዙ የኢትዮጵያ ክፍሎች (በቤተ ክርስቲያን ሳይቀር) ብዙ ኣዋቂዎች ለልጆች ካላቸው አመለካከት፣ የኢየሱስ የሚለየው እንዴት ነው? ለ) እግዚአብሔር ለልጆች ያለው ፍቅር ተግባራዊ ይሆን ዘንድ፤ በቤተ ክርስቲያንህ ውስጥ ሊካሄዱ የሚገባቸው ለውጦች ምንድን ናቸው? ሐ) የኢየሱስ አመለካከት ብዙ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች መንፈሳዊ ልጆችን (ምእመናን) ከሚያስተናግዱበት ሁኔታ የሚለየው እንዴት ነው? መ) ኢየሱስ ከቤተ ክርስቲያን መሪዎችና ከአመለካከቶቻቸው ምን ዓይነት ለውጥ የሚፈልግ ይመስልሃል? እግዚአብሔር ለአንድ የጠፋ በግ ላይቀር ይገደዋል (ማቴ.18፡10-14) የአንድ ልጅ ወይም የኣንድ አዲስ ክርስቲያን ከእምነቱ ወደ ኋላ መመለስ፥ ክርስቶስን ምን ያህል ያሳስበው ይሆን? በቤተ ክርስቲያናችን ሌሎች ብዙ ሰዎች ካሉ መጨነቅ አለብን? ብዙውን ጊዜ ዓለማዊ የቤተ ክርስቲያን መሪና፥ መንፈሳዊ የቤተ ክርስቲያን መሪ፥ በዚህ ጉዳይ ላይ ይለያያሉ። «ወደ ዓለም ለመመለስ ከፈለገ የራሱ ጉዳይ። ሁሉንም ሰው ለመከተል የሚበቃ ጊዜ የለንም፤ ቤተ ክርስቲያን ሰው አላነሣትም፤ የራሱ ችግር ነው፤ በቂ እምነት የለውም።» ይሉ ይሆናል። በቃላት ባይገለጽም እንኳ፥ እነዚህ ሁሉ ማመኻኛዎች በልባችን ውስጥ የሚጉላሉ ወይም በተግባራችን የሚገለጹ ከሆነ፥ የክርስቶስ ልብ ያለን መሪዎች አይደለንም ማለት ነው። ምክንያቱም ክርስቶስ ዘጠና ዘጠኝ በጎችን ትቶ አንድ ትንሽ ጠቦት ፍለጋ የሚሄድ አምላክ ነው። እንደ ክርስቶስ መልካም እረኞች የመሆናችን ምልክቱ ለእያንዳንዱ ትንሽ ልጅና በኃላፊነታችን ሥር ላለው የእግዚአብሔር መንጋ መንፈሳዊ ሁኔታ ሁሉ የምናስብ መሆናችን ነው፡፡ ስለሆነም የመሪነት ጥያቄ፥ «መንጋውን እንዴት ልቆጣጠረው እችላለሁ? ወይም «ከአገልግሎቱ እንዴት ልጠቀም እችላለሁ?» የሚል ሳይሆን፥ «እያንዳንዱ የእግዚአብሔር በግ ጤናማ ሆኖ በመንጋው ውስጥ እንዲኖር ራሴን እንዴት ልሰጥ እችላለሁ?» የሚል መሆን አለበት። (ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ.አይ.ኤም ከታተመውና የአዲስ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ ስለዚህ አስደናቂ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡)

ማቴዎስ 18፡1-14 Read More »

ማቴዎስ 17፡1-27

ኢየሱስ ክብሩን ለጥቂት ደቀ መዛሙርት ገለጠ (ማቴ. 17፡1-13) ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ አንዳንዶቹ ከመሞታቸው በፊት የሰው ልጅ በክብሩ ሲመጣ እንደሚያዩት ተናግሮ ነበር፡፡ ይህ የሆነው መቼ ነው? ሁሉም ደቀ መዛሙርቱ ከክርስቶስ ምጽአት በፊት ስለ ሞቱ፥ ይህ ሌላ ነገር የሚያመለክት መሆን አለበት። ምንም እንኳ አንዳንድ ምሑራን ይህ የክርስቶስን ትንሣኤ ወይም የቤተ ክርስቲያንን ጅማሬ እንደሚያመለክት ቢያምኑም፣ ክርስቶስ ለማለት የፈለገው ከደቀ መዛሙርቱ አንዳንዶቹ የመንግሥቱን ክብር በተራራ ላይ እንደሚመለክቱ ይምስላል ይላሉ። በተራራው ላይ መለኮታዊ ክብሩን አንጸባርቋል። ተመሳሳይ ወንጌላት ሁሉ ክርስቶስ ይህን ከተናገረ በኋላ፥ በተራራው ላይ እንደ ተለወጠ የሚያመለክተውን ታሪክ ጽፈዋል። ይህም ጸሐፊዎቹ ሁሉ ይህን የተስፋ ቃል ፍጻማ እንደ ተመለከቱ የሚያሳይ ይመስላል። ኢየሱስ ከሙሴና ኤልያስ ጋር ለምን ተገናኘ? ለዚህ ምክንያቱ ሙሴና ኤልያስ የብሉይ ኪዳን ልዑካን መሆናቸው ነው። ሙሴ ሕግንና ከዘፍጥረት እስከ ዘዳግም ያሉትን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ይወክላል። በሲና ተራራ የብሉዩን ቃል ኪዳን እግዚአብሔር የሰጠው ለእርሱ ነበር። ኤልያስ ነቢያትን፥ የተቀሩትን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትና የሁሉንም ነገሮች በሚያድስ አካል ይመሰላል (ሚል. 4፡5-6)። ስለሆነም፥ ክርስቶስ ብሉይ ኪዳን በሙሉ ማለትም ሕግና ነቢያት እንዴት በእርሱ እንደ ተፈጸመ አሳይቷል። ሁሉም ወደ ክርስቶስ ቢያመለክቱም ለእርሱ የሚገዙ ናቸው። የክርስቶስ ሞት በብሉይ ኪዳን እንደ ተተነበየ ሁሉ፥ እነ ሙሴ የተሰባሰቡት መፈጸም በሚኖርበት ሞቱ ላይ ለመነጋገር ነበር፡፡ በዚህ አጋጣሚ ክርስቶስ እጅግ ለሚቀርቡት ሦስት ደቀ መዛሙርቱ ስለ መለኮታዊ ባሕርዩና ስለ መጭው ሞቱ ኣስተምሮአል። ይህ ሁሉ በብሉይ ኪዳን ትንቢቶች የተነገረ ነበር። በዚህ ክፍል ውስጥ የክርስቶስ ሞት ሦስት ጊዜ ተጠቅሷል። ይህ እግዚአብሔር አብ ለሁሉም በሚሰማ ድምፅ ክርስቶስ እርሱ የሚወደው ልጁ እንደሆነ ለሁለተኛ ጊዜ የተናገረበት ወቅት ነበር፡፡ ኢየሱስ አጋንንት የነበሩበትን ልጅ ፈወሰ (ማቴ. 17፡14-23) የክርስትና ሕይወት የተራራና ሸለቆ ገጠመኞችን እንደሚያካትት መግለጽ ይቻላል። አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ሕይወታችንን ሁሉ በተራራ ላይ እንድናሳልፍ የሚፈልግ ይመስለናል። ሁልጊዜ እየዘመርን፥ እየጸለይንና እያመለክን እንቆያለን። ከዚህ የበለጠ ምን አለ? ነገር ግን ምንም እንኳ እግዚአብሔር ለልጆቹ አንዳንድ ጊዜ የተራራ ላይ ሕይወት እንዲመሩ ቢያደርጋቸውም፥ እምነታቸው የሚጠናከረውና የሚታየው በሸልቆ ውስጥ ነው። እግዚአብሔርን የምናገለግለው በሸለቆ ስለሆነ፥ እግዚአብሔር ወደ ሸለቆ እንድንመለስ ይፈልጋል። ኢየሱስ፥ ጴጥሮስ፥ ያዕቆብና ዮሐንስ ከተራራው በወረዱ ጊዜ፥ ወዲያው የሕይወት እውነተኛ ገጽታ ታያቸው። የሕይወት ክብደት፥ መንፈሳዊ ውጊያና የእምነት አስፈላጊነት ጠበቃቸው። የተቀሩት ዘጠኝ ደቀ መዛሙርት ከልጁ አጋንንትን ለማስወጣት ሞክረው ነበር፡፡ ቀደም ሲል አጋንንትን ለማስወጣት የቻሉ ሲሆን፥ አሁን ን አልተሳካላቸውም ነበር። ክርስቶስ አጋንንቱን ካወጣ በኋላ፥ አጋጣሚውን ተጠቅሞ ስለ መንፈሳዊ ውጊያ አስተማረ። በዚህ ክፍል ሦስት ዐበይት ትምህርቶች ቀርበዋል። በመጀመሪያ፥ ደቀ መዛሙርት አሁን ከሰይጣን ጋር ለነበራቸው ውጊያ በቀደሙት ድሎች መተማመን አላስፈለጋቸውም። በፊት ማሸነፋችን ለአሁኑ ድል ዋስትና አይሰጠንም። ሁለተኛ፣ ኃይሉ የሚወጣው ከእኛ ሳይሆን ከእግዚአብሔር እንደሆነ ማስታወስ አለብን። ለዚህ ነው ሁሉም መንፈሳዊ ጦርነቶች እግዚአብሔር ላይ ሙሉ በሙሉ ጥገኞች መሆናችንን የሚያሳይ ጸሎት ማካተት ያለባቸው። ሦስተኛ፣ ሁሉ መንፈሳዊ ጦርነቶች ተመሳሳይ አይደሉም። አንዳንዶችን በቀላሉ ማሸነፍ ሲቻል ሌሎች ደሞ ረዥምና አስቸጋሪ ውጊያን ይጠይቃሉ። ጦርነቱ የሚካሄደው በአጋንንት ላይ ብቻ ሳይሆን፥ ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ላይ ለመደገፍ ጭምር ነው፡፡ መጾምና በጋራ መጸለይ ልባችንን ከእግዚአብሔር ጋር እንድናስተባብር ይረዳናል። ሙሉ በሙሉ በእርሱ ላይ በምንደፍበት ጊዜ፥ እግዚአብሔር ልናስብ ከምንችለው በበለጠ መንገድ ይሠራል። አሁንም ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ስለ መጭው ሞቱ ነገራቸው። የኢየሱስ አሳብ ሙሉ በሙሉ ባይገባቸውም ኀዘን አጠላባቸው። ኢየሱስ የቤተ መቅደስን ቀረጥ ከፈለ (ማቴ. 17፡24-27) ኢየሱስ ለቤተ መቅደስ ቀረጥ እንደከፈለ የሚያስረዳውን ይህንኑ ታሪክ የጠቀሰው፥ ቀራጩ ማቴዎስ ብቻ ነው። ይህ ከ20 ዓመት በላይ የሆናቸው የአይሁድ ዜጎች ሁሉ የሚጠየቁት ቀረጥ ነበር፡፡ ኢየሱስ፥ ጴጥሮስ አሁን የእግዚአብሔር መንግሥት አካል በመሆኑ ከሌሎች፥ የማያምኑ አይሁዶች እንደሚለይ ገለጸለት። ንጉሥ ወይም የንጉሥ ልጅ ከሌሎች ቀረጥ የመሰብሰብ እንጂ፣ የመክፈል ተግባር እንደማይፈጽሙ ሁሉ፥ የሰማዩ መንግሥት ገዥ የሆነው ክርስቶስ፥ የሰማዩ ንጉሥ ልጆች የሆኑት ጴጥሮስና ሌሎች ደቀ መዛሙርት የቤተ መቅደስ ቀረጥ መክፈል አልነበረባቸውም ነበር። ይህ የማያምኑ አይሁዶች ተግባር መሆን ነበረበት፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ ሌላም ነጥብ አስተምሯል። ክርስቲያኖች ስለሚገደዱ ላይሆን ለወንጌሉ አላስፈላጊ ጥላቻ ላለማጣት የሚያደርጓቸው ነገሮች አሉ። ስለሆነም፣ በእግዚአብሔር ተአምር የተገኘውን ገንዘብ ኢየሱስና ጴጥሮስ ለሮማ መንግሥት ቀረጥ ከፍለውታል፡፡ የውይይት ጥያቄ፡- ሀ) ክርስቲያኖችን ስለሚያጋጥማቸው መንፈሳዊ ውጊያ፥ አንዳንድ ምሳሌዎችን ልጥ። በቀደምት ድሎች ወይም በራሳችን ብርታት ላይ በምንደገፍበት ጊዜ፥ በአብዛኛው ልንሸነፍ የምችንለው እንዴት ነው? ከክርስቶስ ጋር ያለንን ተገቢ የጥገኝነት ንኙነት በጸሎትና በጾም አማካኝነት የምናሳየው እንዴት ነው? ለ) ክርስቲያን ማድረግ ሳይኖርበት ሌሎችን ላለማስቀየም የሚፈጽማቸውን ተግባራት ምሳሌዎች ዘርዝር። (ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ.አይ.ኤም ከታተመውና የአዲስ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ ስለዚህ አስደናቂ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡)

ማቴዎስ 17፡1-27 Read More »

ማቴዎስ 16፡1-28

ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ኢየሱስን ፈተኑት (ማቴ. 16፡1-12) ኢየሱስ በሽተኞችን በመፈወስ፥ አጋንንትን በማውጣት፣ እንዲሁም ሙታንን በማስነሣት ተኣምራዊ ኣገልግሎት አካሂዷል። ይህም ሆኖ፥ የሃይማኖት መሪዎቹ ክርስቶስ መሢሕ አይደለም ብለው ደምድመው ነበር። ሰዎች አስቀድመው ስለ አንድ ነገር በልባቸው ከወሰኑና አዲስ እውነት ለመቀበል አእምሯቸውን ከዘጉ፥ ታላላቅ ተአምራት ቢሠሩ እንኳ ምንም ነገር ወደ እምነት አያመጣቸውም። ምንም እንኳ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ለዓመታት ጠላቶች የነበሩ ቢሆኑም፥ የጋራ ጠላታቸው የነበረውን ኢየሱስን ለማሸነፍ አብረው ይሠሩ ነበር። ለሁለተኛ ጊዜ ወደ እርሱ መጥተው መሢሕነቱን ለማረጋገጥ “ከሰማይ ምልክትን” እንዲያሳያቸው ጠየቁት። የሃይማኖት መሪዎቹ ከኢየሱስ ተአምራት በቂ ማረጋገጫ ስላገኙ፥ የማመን ፍላጎት ቢኖራቸው ኖሮ፥ ይህንኑ ያደረጉ ነበር። እነርሱ ግን የማመን ፍላጎት አልነበራቸውም። ኢየሱስም ለመታየት ብሎ ተአምራት አልሠራም። ስለሆነም፥ ኢየሱስ «ከዮናስ ምልክት» ማለትም ከሞቱ፥ ከመቀበሩና ከመነሣቱ ተአምር በቀር ሌላ ነገር ሊያሳያቸው እንደማይፈልግ በድጋሚ ኣስገነዘባቸው። ከዚያ በኋላ ኢየሱስ የሃይማኖት መሪዎችን ገሠጻቸው። ተራ ሰዎች የኣየሩንና የጸሐዩን ሁኔታ ተመልክተው የዝናብን መምጣት ወይም አለመምጣት ሊተነብዩ ይችላሉ። የሃይማኖት መሪዎቹ ግን የኢየሱስን መሢሕነት የሚያመለክቱ እነዚያ ሁሉ ማረጋገጫዎች እያሉ፥ የብሉይ ኪዳንን ትንቢቶች ሊረዱ ኣልቻሉም ነበር። ብዙዎቻችን እንደ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን የመሆን ዝንባሌ ማሳየታችን ኢየሱስን አሳስቦታል፡ በውጫዊ ሕግጋት ላይ እያተኮሩ የእግዚአብሔር እጅ ታላላቅ ነገሮችን ሲሠራ ለማየት ባለመፈለጋቸው፥ ኢየሱስ ግብዝታቸውንና መንፈሳዊ ትዕቢታቸውን «የፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን እርሾ» ሲል ጠርቷል። ስለሆነም ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱ ከእነዚህ አመለካከቶች ሙሉ በሙሉ እንዲጠበቁ አስጠንቅቋል። እንዲህ ዓይነቱ እርሾ በሰው ሕይወት ውስጥ ካደገ በኋላ ያጠፋዋልና፡፡ የውይይት ጥያቄ:- ሀ) ከላይ የተገለጹት ዝንባሌዎች ብዙውን ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚታዩት እንዴት ነው? ለ) የዚህ አይነት እርሾ በልብህ ውስጥ እንዳይኖር ምን እያደረግህ ነው? ኢየሱስ ስለ እርሾ ሊናገር፥ ደቀ መዛሙርቱ ምግብ ላይዙ በመምጣታቸው ጌታ የሚገስጻቸው መሰላቸው መንፈሳዊ እውነትን ለመረዳት አለመቻላቸው ኢየሱስን አሳዘነው እርሱ ከእነርሱ ጋር እያለ እንዴት ለሥጋዊ ምግብ ይጨነቃሉ? በትንሽ ምግብ አምስት ሺህ፥ በኋላም አራት ሺህ ሰዎችን ሲመግብ እይተዋል። ኢየሱስ ፍላጎቶቻቸውን ስለሚያሟላ፣ ደቀ መዛሙርቱ ለመሠረታዊ ነገሮች መጨነቅ አልነበረውም። ጴጥሮስ የክርስቶስን መሢሕነት መሰከረ (ማቴ 16፡13-20) የማቴዎስ መጽሐፍ ማዕከል ጴጥሮስ ስለ ኢየሱስ የለጠው ምስክርነት ነው። ማቴዎስ የኢየሱስን ተአምራትና ትምህርቶች በማቅረብ እርሱ አይሁዶች ሊያምኑበት የሚገባ መሢሕ መሆኑን መስክሯል አሁን ምርጫው የራሳቸው ነበር፡፡ ያ ሁሉ ማረጋገጫ እያለ በኢየሱስ ላለማመን እንደ ወሰኑት ፈሪሳውያን ሊሆኑ ይሻሉ? ወይስ የሃይማኖት ምሁር ባይሆንም እንኳ ኢየሱስ መለኮታዊ መሢሕና “የሕያው እግዚአብሔር ልጅ” እንደሆነ በግል ሊመለከት እንደቻለው እንዲ ጴጥሮስ ሊሆኑ ይሻሉ? ይህ የጴጥሮስ ምስክርነት የመጽሐፉ ማእከላዊ ነጥብ ነው። ከዚያ በኋላ፥ ማቴዎስ በመጪው የኢየሱስ ሞት ላይ ያተኩራል። ኢየሱስ ራሱ ለደቀ መዛሙርቱ ስለ ሞቱና ትንሣኤው አስተምሯል። ኢየሱስ “ቤተ ክርስቲያን” የሚለውን ቃል ሁለት ጊዜ ብቻ ጠቅሷል። ይህ ቤተ ክርስቲያን የተባለ የአማኞች የአንድነት አካል መጀመሩን የሚያሳይ ቀዳሚ ቃል ነው (ማቴ 18፡17 አንብብ።) በግሪክ ቋንቋ፥ ቤተ ክርስቲያን የሚለው ቃል “ተጠርተው የወጡ የክርስቶስ ተከታዮች ስብስብ” የሚል ፍች ይሰጣል፡ በኣዲስ ኪዳን ይህ ቃል የሚያመለክተው፥ የቤተ ክርስቲያንን ሕንጻ ሳይሆን፥ የክርስቲያኖችን ቡድኖች ነው። እነዚህም በአንድ ቤት ውስጥ የሚሰባሰቡትን ወይም ከኣንድ የቤት ቤተ ክርስቲያን የሚበልጡ ወገኖች የሚካተቱበትን የአንዲት ከተማ ወይም በየትኛውም ስፍራ የሚገኙትን ክርስቲያኖች ሁሉ የሚያመለክት ሊሆን ይችላል። ይህ በኢትዮጵያ ቃሉ በቀዳሚነት ክርስቲያኖች የሚሰባሰቡበትን ሕንጻ ከሚያመለክትበት ሁኔታ የተለየ ነው፡፡ በዚህ ክፍል ምሑራን የሚከራከሩባቸው ሁለት ዐበይት ጥያቄዎች አሉ። በመጀመሪያ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያኑን የሚሠራበት ዓለት ምንድን ነው? ሁለተኛ ለጴጥሮስ የተሰጠው ሥልጣን ምንን ያመለክታል? 1 የቤተ ክርስቲያን መሠረት የሆነው ዓለት ምንድን ነው? ለዚህ ጥያቄ የሚቀርቡ አራት ዐበይት ትርጉሞች አሉ። ሀ. አንዳንዶች ዓለቱ ጴጥሮስ እንደሆነ ያምናሉ። ክርስቶስ ስሙን “ዓለት” የሚል ፍቺ ወደሚሰጠው ጴጥሮስ የለወጠው ለዚሁ ነው ይላል። የሮም ካቶሊኮች ይህ ቃል ጴጥሮስና ከእርሱ በኋላ የሚሾሙት ሊቀ ጳጳሳት መንፈሳዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ለእግዚአብሔር፥ የክርስቶስን ያህል ሥልጣን እንዳላቸው የሚያሳይ መሆኑን ያምናሉ። ሊቀ ጳጳሱና ካህናቱ የአማኙን መዳን ወይም አለመዳን የመወሰን መብት እንዳላቸው ያምናሉ። ይህ አተረጓጎምና ለሊቀ ጳጳሱ የተሰጠው ሥልጣን ሊሆን የማይችል ነው፡፡ ክርስቶስ ለጴጥሮስ ይህን ሥልጣን ቢሰጠው እንኳ፥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የጴጥሮስ ሥልጣን ወደ ሌሎች የቤተ ክርስቲያን መሪዎች እንደሚተላለፍ የሚያመለክት አሳብ የለም። እግዚአብሔር ጴጥሮስ የመጀመሪያውን ስብከት በበዓለ ኀምላ እንዲያቀርብ በማድረጉ፥ በአይሁዶች መካክል ቤተ ክርስቲያን ተወልዳለች (የሐዋ. 2:38-41)። እግዚአብሔር ሰማርያውያን እውነተኛ አማኞች መሆናቸውን እንዲመሰክርና መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ ተጠቅሞበታል (የሐዋ. 8፡14-17)። እንዲሁም፥ ጴጥሮስ ለቆርኔሌዎስ በመመስከር አሕዛብን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንዲያመጣ ተጠቅሞበታል (የሐዋ. 10፡27-48)። ለ. ሌሎች ደግሞ ጴጥሮስ የሌሎች ሐዋርያት እንደራሴ እንደሆነ ያስባሉ። በኤፌ. 2፡20 ጳውሎስ ሁሉም ሐዋርያት የቤተ ክርስቲያን መሠረት እንደሆኑ ገልጾአል። እነዚህ ሐዋርያት ወንጌልን የመስበክ ብቻ ሳይሆን፥ በዓለም ሁሉ የማሰራጨት ኃላፊነት ተሰጥቷቸው ነበር። በተጨማሪም፥ ለቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደ ሆነ፥ እውነተኛው ዶክትሪን የትኛው እንደሆነ፥ ክርስቶስ ማን እንደ ነበረ የመመስከር ሥልጣን ነበራቸው። በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ፥ ሐዋርያት የቀድሞይቱን ቤተ ክርስቲያን ሊመሩና አስተምህሮቷን መልክ ሲያስይዙ እንመለከታለን። ሐ. ዓለቱ ኢየሱስ ነው። ኢየሱስ በዚህ ስፍራ ለዓለት ሁለት ቃላት ተጠቅሟል። ስምዖን የሚለውን ስም ወደ ጴጥሮስ በለወጠበት ጊዜ የተጠቀመው ቃል «ትንሽ ዓለት» የሚል ፍች ይሰጣል። ስለሆነም፥ ክርስቶስ ስምዖን ጴጥርስ (ትንሽ ዓለት) ሲሆን፥ በዚህ “ትልቅ ዓለት” ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ ብሏል። ትልቁ ዓለት ማን ነው? ሰዎች የሚሰናከሉበትና የእግዚአብሔር አዲስ ዕቅድ የማዕዘን ራስ የሆነው የተተወው ዓለት ማን ነው? እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ ግልጽ ነው (ማቴ. 21፡42-44 አንብብ።) የቤተ ክርስቲያን መሠረት የሆነው ክርስቶስ ነው። (1ኛ ቆሮ. 3፡11 አንብብ።) ከሞተ፥ ከተቀበረና ሞትን አሸንፎ ከተነሣ በኋላ፥ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን ለመመሥረት መንፈስ ቅዱስን ላከ። የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ መሆኑ መጠን፥ ክርስቶስ ገዥ ነው። መ. ዓለቱ ጴጥሮስ የሰጠው ምስክርነት ነው። አንድ ሰው ለመዳንና የቤተ ክርስቲያን አካል ለመሆን ማንን ማመን አለበት? ማመን ያለበት ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ የሆነ መሢሕ መሆኑን ነው። ይህ መሠረታዊ የአስተምህሮ ሐቅ አንድ ሰው ደኅንነትን ለማግኘትና የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባል ለመሆን ሊያሟላው የሚገባው መሠረታዊ እውነት ነው። 2 ክርስቶስ ለጴጥሮስ የመንግሥተ ሰማይን ቁልፎች እንደ ሰጠ ሲናገር ምን ማለቱ ነው? በማቴዎስ 18፡18፣ ለሁሉም ደቀ መዛሙርት ተመሳሳይ ሥልጣን ተሰጥቷል። አሁንም ምሑራን በዚህ ጉዳይ ላይ በመስራከር የተለያዩ ኣተረጓጎሞችን ይሰጣሉ። ሀ. የሮም ካቶሊክ ክርስቲያኖች ይህን ጥቅስ የሚጠቀሙት የሊቀ ጳጳሱን ሥልጣን ለማረጋገጥ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ክርስቶስ ለጴጥሮስ ታላቅ ሥልጣን እንደ ሰጠው ያምናሉ፡ ካቶሊኮች ጴጥሮስ በምእመናን ላይ መንፈሳዊ ሥልጣን (ቁልፍ) እንዳለውና በእርሱ ውሳኔ የዘላለምን ሕይወት ሊያገኙ ወይም ወደ ሲኦል ሊወርዱ እንደሚችሉ ያስባሉ፡፡ ከዚህ በመነሣት፥ በአሁኑ ዘመን የሚያገለግለው ሊቀ ጳጳስ የጴጥሮስ ቀጥተኛ ተተኪ እንደሆነና ይህንኑ ተመላላይ ሥልጣን እንደ ተቀበለ ያስተምራሉ። ነገር ግን እነዚህ ምንባቦች ለጴጥሮስ ይህን ያህል ያልተገደበ ሥልጣን መስጠታቸው አጠራጣሪ ከመሆኑም በላይ፣ አዲስ ኪዳን ውስጥ ይህ ሥልጣን ወደ ሌሎች የቤተ ክርስቲያን መሪዎች እንደሚተላለፍ የሚያመለክት አሳብ አለመጠቀሱ ሊጤን ይገባል። ስለሆነም ይህ ትክክለኛ አተረጓጎም እንዳልሆነ እንረዳለን። ለ. ሌሎች ክርስቲያኖች እነዚህ ምንባቦች ለጴጥሮስ ከፍተኛ ሥልጣን እንደተሰጠው የሚያመለክቱ መሆናቸውን ይሰማሉ። ይህ ግን ጴጥሮስ «አንተን ወደ መንግሥተ ሰማይ አስገባሃለሁ እላስገባህም?» የሚልበት ኃጢአትን ይቅር የማለትና ያለማላት ሥልጣን እንልሆነ ያስረዳሉ። ይህ ግን በእግዚአብሔር የተስፋ ቃሉችና በግለሰቡ እምነት ላይ ተመሥርቶ ጴጥሮስ የእግዚአብሔር መንግሥት አካል መሆኑን የሚያውጅበት ሥልጣን ነው። በግሪኩ መጽሐፍ ቅዱስ ለጴጥሮስ የተሰጠው ሥልጣን «የመንግሥተ ሰማይን ቁልፎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር ላይ ያሰርከው ሁሉ ቀደም ሲል በሰማይ የታሰረ ነው በምድር የፈታከው ሁሉ ቀደም ሲል በሰማይ የተፈታ ነው።” ተብሎ ሊነበብ ይችላል፡፡ እነዚህ ምሑራን ጴጥሮስ በክርስቶስ ያመኑት እንደዳኑና ያላመኑት ግን ጥሩ አይሁዶች ቢሆኑም

ማቴዎስ 16፡1-28 Read More »

ማቴዎስ 15፡1-39

ማቴዎስ በክርስቶስና የሃይማኖት መሪዎች መካከል ወደነበረው ግጭት እየተመላለሰ ይናገራል። ቀደም ሲል ሰንበትን በመጠበቁ ጉዳዩ ላይ የተጋጩ ሲሆን፥ አሁን ደግሞ ስለ ሥርዓታዊ ንጽሕና ተከራከሩ። የብሉይ ኪዳን ካህናት ለእግዚአብሔር መሥዋዕቶችን ከማቅረባቸው በፊት እጆቻቸውን የመታጠብ ግዴታ ስለነበረባቸው (ዘጸ 30፡17-20)፥ ፈሪሳውያን አይሁዶች ሁሉ ከየትኛውም ሃይማኖታዊ ተግባር በፊት መታጠብ እንዳለባቸው አስተማሩ። ይህም ለምግብ ከመጸለይና ከመመገብ በፊት እጅ መታጠብን ይጨምር ነበር። ፈሪሳውያን፥ አይሁዶች እግዚአብሔርን ለምግቡ አመስግነው መብላት ከመጀመራቸው በፊት በተወሰነ መንገድ መታጠብ እንዳለባቸው ያስተምሩ ነበር። የውይይት ጥያቄ፡- ሀ) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጠቀሱትንና ክርስቲያኖች ለእውነተኛ መንፈሳዊነት ጠቃሚዎች ናቸው የሚሏቸውን አንዳንድ ልምምዶች ዘርዝር። ለምላሉ፥ በጸሎት ጊዜ ዓይንን መጨፈን፥ ፊልም አለማየት የመሳሰሉትን። ለ) ምንም እንኳ እነዚህ ባሕላዊ ልምምዶች ቢሆኑም፥ ክርስቲያኖች ከእግዚአብሔር ቃል እኩል ሊያዩዋቸው የሚችሉባቸውን መንገዶች ዓለጽ፡፡ ፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርት እነዚህን የመታጠብ ባሕሎች እያከበሩ ኣለመሆናቸውን ሲገልጹ፥ ክርስቶስ ደግሞ ለሕዝቡ ስለ እውነተኛ መንፈሳዊ ንጽሕና አስተማረ፥ እንዲሁም ክርስቶስ ለፈሪሳውያን በሚከተለው መንገድ ምላሽ ሰጥቷል። ሀ. በሰው ሠራሽ ደንቦች ላይ በማተኮር፥ ፈሪሳውያን ብዙውን ጊዜ እውነተኞቹን የእግዚአብሔር ሕግጋት ይተላለፉ ነበር። የራሳቸውን የራስ ወዳድነት ዓላማዎች ለማሳካት፥ ሕጉን በመሣሪያነት ይጠቀሙ ነበር። ለምሳሌ፥ ለቤተሰቦቻቸው ገንዘብ ላለመስጠት ገንዘባቸው «ቁርባን» እንደሆነ ይናገሩ ነበር። ይህም “ለእዚአብሔር ሊሰጥ የተለየ” የሚል ፍች ያለው የኣይሁዶች ቃል ነበር። ይህን ማለታቸው ግን ገንዘብን ለራሳቸው ፍላጎት ከመጠቀም አላገዳቸውም ነበር። ነገር ገን ለሌሎች፥ በተለይም ለወላጆቻቸው ገንዘብ ላለመስጠት ማመኻኛ ሆኗቸዋል። ሊ ሰዎችን መንፈሳዊ በሚያስመስሉ ደንቦች ላይ ማተኮሩ፥ እጅግ መንፈሳዊ የሆነውን ነገር ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖራቸውን ቀንኙነትና ሌሎችን መውደድ እንዳይመለከቱ ዓይኖቻቸውን አሳውሮታል። ሰዎች መንፈሳዊነትንና ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት ማድረግን እንደ ማበረታታት፥ በውጫዊ ተግባራት ላይ ትኩረት አድርገዋል። ሒ በእግዚአብሔር ዓይኖች ፊት አንድን ሰው የሚያረክሰው ከአፉ የሚወጣው ነው። የምንበላው ምግብ እያረከሰንም፡፡ በልባችን ውስጥ ያለውና በአፋችን በኩል የሚወጣው ግን ሰውን በእግዚአብሔር ፊት ያረክሰዋል። የኃጢአት ምንጩ ሰዎች የሚለብሱት፥ የሚበሉት ወይም የሚጠጡት ነገር አይደለም። የኃጢአት ምንጭ ክፉ ልብ ነው። የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚቃረኑ ውጫዊ ነገሮች ሁሉ የሚመነጩት፥ ከክፉ ልብ ነው። ይህም የምንበላው ምግብ (ለምሳሌ፥ የሙስሊሞች ምግብ) እንደማያረክሰን ያሳያል።ይህ ባሕላችን ይህ ጥሩ ነው ያ መጥፎ ነው ብሎ በሚያስተምረን ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ነው። መ. ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱ ሕዝቡን ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ የሚመሩትን ወገኖች ለመቃወም እንዳይፈሩ አስጠንቅቋቸዋል። ክርስቶስ ለኃጢአተኞች ስሜት ይጠነቀቅ ነበር። ነገር ግን ፈሪሳውያን ብዙ ሰዎችን ወደ ኃጢአትና የሐሰት ሃይማኖት እየመሩ በመሆናቸው፥ ክርስቶስ በግልጽ ለመናገር ፈለገ። ደቀ መዛሙርቱ ፈሪሳውያን በቃሉ እንደ ተቀየሙ ሲነግሩት፥ ሰዎች ሰምተው ይማሩ ዘንድ አንዳንድ ጊዜ በግልጽ መናገሩ አስፈላጊ እንደሆነ ገለፁላቸዋል። ፈሪሳውያን እግዚኣብሔር ፈጥኖ ሊነቅላቸው የሚገባ አረሞች ነበሩ። የደኅንነትን መንገድ የሚያውቁ ቢመስሉም፥ ለራሳቸው ዕውሮች ሆነው ሳለ፥ ሌሎች መንፈሳዊ ዕውራንን ለመምራት ይፈልጉ ነበር። ውጤቱ ግን እነርሱም ሆኑ የሚመሯቸው ሰዎች ወደ ሐሰት ትምህርትና የእግዚአብሔር ፍርድ ጉድጓድ መውደቃቸው ነበር። (ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ.አይ.ኤም ከታተመውና የአዲስ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ ስለዚህ አስደናቂ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡)

ማቴዎስ 15፡1-39 Read More »

ማቴዎስ 14፡1-36

ማቴዎስ  14፥ የክርስቶስ አገልግሎት ረዥሙ ዕለት በመባል ይታወቃል። በአንድ ቀን ክርስቶስ ታላላቅ ተቃውሞዎችና ፈተናዎች እጋጥመውታል። የአክስቱ ልጅና የመንሥቱ ኣገልጋይ የነበረው መጥምቁ ዮሐንስ ተገደለ። ክርስቶስ ምንም እንኳ ድካም ቢሰማውና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ብቻ ለመሆን ቢፈልግም፥ ብዙ ሰዎች ስለሚከተሉት ለራሱ ጊዜ አላገኘም፤ አምስት ሺህ ሰው መገበ። ከዚያ በኋላ ግን ደቀ መዛሙርቱ ማዕበል በበረታባቸው ጊዜ በእርሱ አለማመናቸውን ታዘበ። ከዚያም አሳዛኝ ነገሮች ደረሱበት። ነገር ግን ክርስቶስ የአባቱን ድምፅ ይሰማ ስለነበር፥ እነዚህን ነገሮች የእግዚአብሔርን ፍላጎት ለማሟላቱ ተግባር እውሏቸዋል። ይህ ብዙውን ጊዜ በቤተ ክርስቲያን መሪዎች ላይ ይደርሳል። ሰዎች ሲሞቱ፥ በኃጢአት ሲወድቁ ወይም እምነታቸውን ሊተዉ በከፍተኛ ደረጃ እንከፋለን። የራሳችን ዕቅዶች ቢኖሩንም፥ በጊዜ ሰሌዳቸው መሠረት አይከናወኑም። የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በዚህ ምክንያት ሊቆጡ ወይም ተስፋ ሊቆርጡ ይችላሉ። ነገር ግን በእያንዳንዱ ተስፋ መቁረጥና ችግር ውስጥ የእግዚአብሔርን እጅ ማየቱ ከሁሉም የበለጠ ነው። የመጥምቁ ዮሐንስ አንገት በሰይፍ ተቀላ (ማቴ. 14፡1-12) የብሉይ ኪዳን የመጨረሻው ታላቅ ነቢይ የነበረው መጥምቁ ዮሐንስ፥ ለረዥም ጊዜ ታስሮ ቆየ። ከዚያም በንጉሥ ሄሮድስ ቤተሰብ ተንኮል ምክንያት ሞት ተፈረደበት። ዮሐንስ የታሰረው የእግዚአብሔርን ቃል እየተናገረ የባለሥልጣናትን ሰላም እንዳይነሣ በማሰብ ነበር። ለእምነቱ መከራ ተቀብሎ ሞተ። ይህ ሁኔታ ክርስቶስን በከፍተኛ ደረጃ ሳያሳዝነው አልቀረም። ይህ ድርጊት የእግዚአብሔርን ሕዝብ ኃጢኣት ተቃውመው የተናገሩትን ነቢያት ከገደሉት የብሉይ ኪዳን አይሁዶች የተለየ አልነበረም። ይህንኑ የመሰለ የጭካኔ ተግባር ከኣንድ ዓመት በኋላ በክርስቶስ ላይ ሊደርስ ነው። ይህ ሁኔታ ክርስቶስን ለመከተል በሚመርጡ ሰዎች ላይም ስለሚደርሰው አደጋ የሚያስተላልፈው መልእክት አለው። እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ ሕዝቡን ከሞት ቢያድንም (የሐዋ. 12፡6-11)፥ ስለዚህ በሌሎች ጊዜያት መከራ ተቀብለው እንዲሞቱ የሚፈቅድበት ጊዜ አለ (የሐዋ. 7፡54-60)። ክርስቶስ አምስት ሺህ ሰዎችን መገበ (ማቴ. 14፡13-21) ክርስቶስ የአክስቱ ልጅ በሆነው መጥምቁ ዮሐንስ ላይ ስለደረሰው የሞት አደጋ ከሰማ በኋላ፥ ለመጸለይና ለማሰላሰል የተወሰነ ጊዜ ፈለገ። ነገር ግን በጀልባ ለጥ ወዳለ ስፍራ ለመሄድ በፈለገ ጊዜ፥ ከአምስት ሺህ በላይ የሆኑ ሰዎች (ማለትም ተጨማሪ አምስት ሺህ ሴቶችና ልጆች) ይከተሉት ጀመር። ክርስቶስ ለግል ጊዜው አክብሮት ባለመስጠታቸው ወይም ራስ ወዳድ በመሆናቸው ሊቆጣቸው ይችል ነበር። ማቴዎስ እንደሚነግረን ግን፥ ክርስቶስ የግል ሥቃይ ቢኖርበትም ለሕዝቡ ከመራራት አልታቀበም። ስለሆነም፥ ቃሉን በማስተማር፥ የታመሙትን በመፈወሰ፥ እንዲሁም ረሃብተኞችን በመመገብ ረዳቸው። (ክርስቶስ አምስት ሺህ ሕዝብ የመገበበት ተአምር በአራቱም ወንጌላት ውስጥ ከተመዘገቡት ጥቂት ተአምራቶች አንዱ ነው።) ነገር ግን ክርስቶስ እንክብካቤውን ያሳየው ለሕዝቡ ብቻ አልነበረም። ለደቀ መዛሙርቱም እነርሱንና ያላቸውን ጥቂት ሀብት በመጠቀም፥ የሰዎችን ፍላጎት ሊያሟላ እንደሚችል አስተምሯቸዋል። ክርስቶስ ይህ በራሳቸው ሊወጡ የማይችሉት ተግባር መሆኑን እያወቀ ደቀ መዛሙርቱ ሕዝቡን እንዲመግቡ ነገራቸው። ይህን የተናገረው የማይቻል ነገር ሊያደርጉ እንደሚችሉ ለማስተማር ነበር። ወደ እርሱ ከተመለሱ እነርሱንና ሀብታቸውን በመጠቀም ከችሎታቸው የላቀ ተግባር ሊያከናውን ይችል ነበር። ከዚህ ክፍል የሚከተሉትን እውነቶች ልንመለከት እንችላለን። ሀ. ደቀ መዛሙርቱ ሕዝቡን እንዲመግቡ የተናገረው ክርስቶስ ነበር። በዚህም ክርስቶስ ፍላጎታቸውን እንዲያሟላ እያስገደዱት አልነበሩም። ሰዎች የማይቻል ተግባር ለመፈጸም የሚሞክሩባቸው ሁለት አማራጮች አሉ። በመጀመሪያ፥ የእግዚአብሔር ልጆች አንድ ታላቅ ነገር (ለምሳሌ፥ አዲስ የቤተ ክርስቲያን ሕንጻ) የሚፈልጉባቸው ጊዜያት አሉ። ነገር ግን ብዙውን ጊዜ እነሣሽ ምክንያታቸው በራስ ወዳድነት ስሜት የጎደፈ ነው። ለምሳሌ ያህል ትልቅ ቤተ ክርስቲያን በመገንባት ለራሳችንና ለቤተ ክርስቲያናችን የበለጠ ክብር እንደምናመጣ ልናስብ እንችላለን። እግዚኣብሔርን ሳይጠይቁ ወይም እምነታቸውን የሚፈትነው እግዚአብሔር መሆኑን ሳያረጋግጡ ክርስቲያኖች የሕንጻውን ሥራ ይጀምሩና እግዚአብሔር ፍላጎታቸውን እንዲያሟላላቸው ይጠይቃሉ። ብዙውን ጊዜ የዚህ ዓይነቱ እምነት ለሰዎቹም ሆነ ለእግዚአብሔር ስም ኃፍረትን ያስከትላል። ሁለተኛ፥ እግዚአብሔር ሰዎች አንድን የማይቻል ተግባር እንዲፈጽሙ በግልጽ የሚናገርባቸው ጊዜያት አሉ። ይህ በእግዚአብሔር ተማምነን እርሱ ሊሠራ የሚችለውን የምንመለከትበት መልካም አጋጣሚ ነው። ለ. በማይቻሉ ሁኔታዎች ውስጥ እግዚአብሔር የራሱን ታላቅነት እንድንረዳ ለማገዝ ይፈልጋል። በራሳችን ሀብት የምንችለውን ብቻ የምናደርግ ከሆንን፥ የእግዚአብሔርን እገዛ እንፈልግም። እምነታችንም አይፈተንም። የእግዚአብሔርን እጅ በሥራ ላይ ልንመለከት የምንችለው እግዚአብሔር የማይቻለውን እንድናደርግ በሚጠይቀን ጊዜ ብቻ ነው። አንድ ሰው እንደተናገረው፥ እግዚኣብሔር የማይቻል ነገር የሌለበትን ተግባር ለእርሱ እንድንፈጽም አይጠይቀንም። በዚህ ጊዜ ብቻ ነው ውጤቱ የእግዚአብሔር እንጂ የእኛ የማይሆነው። ሐ. እግዚአብሔር አንድን ታላቅ ነገር እንድንሠራ በሚጠይቀን ጊዜ፥ ካለን ነገር ይጀምራል። እግዚአብሔር ብዙውን ጊዜ ከባዶ አይጀምርም። ክርስቶስ የማይቻለውን አምስት ሺህ ሰዎችን የመገበው በደቀ መዛሙርቱ እጅ በነበረው ጥቂት እንጀራና ዓሣ አማካኝነት ነበር፡፡ በመጀመሪያ ደቀ መዛሙርቱ ያላቸውን ለእርሱ መስጠት ነበረባቸው። እግዚአብሔር በራስ ወዳድነት ሀብታችንን የሙጥኝ ብለን፥ «እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተው አድርገው» በምንልበት ጊዜ ለመሥራት አይፈልግም። እግዚአብሔር ሕዝቡ ያለውን እንዲሠዋ ይሻል። ከዚያም የመፍትሔው አካል እንድንሆን ይፈቅድልናል። ነገር ግን፥ «ይህ የማይቻል ነገር መሆኑ ግልጽ ነው። ስለሆነም፥ የምችለውን አደርጋለሁ፥ ላደርገው የምችለውም ይህንኑ ብቻ ነው» ከሚል አመለካከት መቆጠብ አለብን። ያለንን ከሰጠን በኋላ እግዚአብሔር እንዴት እንደሚሠራ መጠባበቅ አለብን። መ. እግዚአብሔር የልጆቹን ፍላጎት የሚያሟላው በሚያገለግሉበት ወቅት ነው። ብዙውን ጊዜ ግን ሥራውን ከመጀመራቸው በፊት ፍላጎታቸውን አያሟላላቸውም። ደቀ መዛሙርቱም ተርበው ነበር። ምግብ ስጠንና ከበላን በኋላ የተረፈውን ለሰዎች እንሰጣለን ሊሉ ይችሉ ነበር። ክርስቶስ ግን ለደቀ መዛሙርቱ የሰጣቸው ለሰዎች ከሰጡ በኋላ ነበር። ደቀ መዛሙርቱ እያንዳንዳቸው አንድ ቅርጫት ምግብ ያገኙት (12 ቅርጫት ምግብ ስለ ተረፈ) የሕዝቡን ፍላጎት ለማሟላት ከሰጡ በኋላ ነበር። የውይይት ጥያቄ፣ ሀ) ክርስቲያኖች የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሳይጠይቁ ወይም በራስ ወዳድነት ምክንያቶች አንድን ነገር ሊጀምሩ የሚችሉባቸውን መንገዶች ግለጽ። ለ) እግዚአብሔር አንድ የማይቻል ተግባር እንድትፈጽም ከጠየቀህ በኋላ በታዘዝኸው ጊዜ እንዴት ፍላጎትህን እንዳሟላ የሚያስረዱትን ምሳሌዎች ዘርዝር። ሐ) ከዚህ ስለ መታዘዝና የእግዚአብሔር ቸርነት የምንማራቸው ሌሎች ትምህርቶች ምንድን ናቸው? ማቴዎስ ክርስቶስ እንደ መሢሕና ፈጣሪ የሕዝቡን ሥጋዊ ፍላጎቶች እንዳሟላ ገልጾአል። እግዚአብሔር በምድረ በዳ ውስጥ በሙሴ አማካኝነት ለሕዝቡ ምግብን እንደ ሰጣቸው ሁሉ፥ ክርስቶስም በተአምር የሕዝቡን ፍላጎቶች ለማሟላት ችሏል። በተጨማሪም ማቴዎስ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ስለሚበሉት ምግብ መጨነቅ እንደሌለባቸው ተናግሯል። ክርስቶስ የደቀ መዛሙርቱን ፍላጎት ያሟላል። ክርስቶስና ጴጥሮስ በውኃ ላይ ተራመዱ (ማቴ. 14፡22-36) ክርስቶስ ኅዘን በደረሰበት ጊዜ ሳይቀር ተግባሩን ለመቀጠል ኃይልን ከየት አገኘ? ይህን ኃይል ያገኘው ከእግዚአብሔር ጋር ካሳለፈው የግል የጸሎት ጊዜ ነበር። ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ይወዳቸው የነበረ ቢሆንም፥ በተለይም ብዙ ሠርቶ በደከመና ችግር በደረሰበት ወቅት ከእግዚአብሔር ጋር የግል ጊዜ የማሳለፉን ጠቀሜታ ተገንዝቦ ነበር። ስለሆነም፤ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን በጀልባ ከሰደዳቸው በኋላ፥ ለብቻው ወደሚጸልይበት ስፍራ ሄደ። ከሌሎች ሰዎች ጋር መጸለይ መልካም ነው። ነገር ግን የግል ጊዜ ወስደን እግዚአብሔር በቃሉ ሲናገር ካላዳመጥንና ወደ እርሱ ካልጸለይን፥ ፍሬያማ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ልንሆን እንደማንችል ከክርስቶስ ምሳሌነት እንማራለን፡፡ ነገር ግን ደቀ መዛሙርቱን በጀልባ የላከበት ሌላም ምክንያት ነበር። ክርስቶስ በእርሱ ላይ የነበራቸውን እምነት ለመፈተን ፈልጎ ነው። ክርስቶስ ማዕበሉ እንደሚነሳ ቢያውቅም፣ ደቀ መዛሙርቱን ወደዚያው ላካቸው። ሕይወት ዘመናቸውን በሙሉ በውኃ ላይ ቢያሳልፉም፥ ክርስቶስ ዓሣ አጥማጆቹ ከማዕበሉ የማያመልጡበትን ሁኔታ አደረገ። ቀደም ሲል እርሱ በማዕበል ውስጥ አብሯቸው ነበር። በዚህ ጊዜ በማዕበል ውልጥ ብቻችንን ነን ብለው ያስቡ ነበር። በማዕበሉ መካከል ክርስቶስ እየተራመደ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጣ። ጴጥሮስ ክርስቶስ በውኃ ላይ ሲራመድ ባየ ጊዜ፥ እንደ እርሱ ለማድረግ ፈለገ። ክርስቶስም ጴጥሮስ በውኃ ላይ እየተራመደ ወደ እርሱ እንዲመጣ ጠራው። ጴጥሮስ ክርስቶስን እየተመለከተ በውኃው ላይ ከተራመደ በኋላ፥ ማዕበሉንና ነፋሱን ሲያይ መስመጥ ጀመረ። ክርስቶስ ግን በፍጥነት ኣዳነው። ክርስቶስ ወደ ጀልባይቱም ሲገባ ማዕበሉ ጸጥ አለ። ማቴዎስ ይህን ታሪክ የጨመረው ለምንድን ነው? በመጀመሪያ፥ ታሪኩ የክርስቶስን ኃይል ያሳያል። ክርስቶስ በውኃ ላይ በመጓዙና ማዕበሉን ጸጥ በማሰኘቱ፥ በተፈጥሮ ላይ ሙሉ ሥልጣን እንዳለው አሳይቷል። እንዲህ ዓይነት ኃይል ያለው እግዚአብሔር ብቻ በመሆኑ፥ ኣይሁዶች ስለ ክርስቶስ ኃይል ማወቅ ያስፈልጋቸው

ማቴዎስ 14፡1-36 Read More »

ክርስቶስ በምሳሌዎች አማካኝነት ስለ እግዚአብሔር መንግሥት አስተማረ (ማቴዎስ 13:1-58)

ክርስቶስ ካስተማረባቸው ዘዴዎች አንዱ በምሳሌዎች መጠቀም ነበር። (አንዳንድ ምሑራን ከ60 በላይ ምሳሌዎች ወይም ምሳሌ መሰል አባባሎች እንዳሉ ይናገራሉ። ይህም ከክርስቶስ ጠቅላላ ትምህርት ሲሶው ያህል ነው።) ምሳሌዎችን በትክክል ለመተርጎም ይቻለን ዘንድ፥ የምሳሌዎችን ምንነትና እንዴት ልንረዳቸው እንደሚገባን ማወቅ አለብን። ምሳሌዎች ስውር መልእክት የሚያስተላልፉ እንቆቅልሾች (allegories) አይደሉም። እያንዳንዱ የታሪኩ ዝርዝር መንፈሳዊ ትርጉም እንዲሰጥ ሆኖ የተዘጋጀ ልብወለዳዊ ታሪክም አይደለም። ነገር ግን ምሳሌዎች አንድ ዐቢይ መንፈሳዊ እውነት ለማብራራት የሚቀርቡ ቀላል ታሪኮች ናቸው። ክርስቶስ አንዳንድ ምሳሌዎችን የተረጎመ ቢሆንም፡ አብዛኞቹ ምሳሌዎቹ አልተተረጎሙም። ስለሆነም፥ ምሳሌዎችን በምንተረጉምበት ጊዜ፥ የሚከተሉትን የትርጉም ሂደቶች መከተል አለብን፡፡ ሀ. ጠቅላላውን ታሪክ ክርስቶስ ምሳሌውን ከተናገረው የአይሁድ ባሕል አንጻር መረዳት አለብን። ለ. ከዚያም፥ «በዚህ ታሪክ እየተብራራ ያለው ዐቢይ መንፈሳዊ እውነት ምንድን ነው?» ብለን መጠየቅ ኣለብን። ሐ. በመጨረሻም፥ «ይህ መንፈሳዊ እውነት ዛሬ ከእኛ ሕይወት ጋር እንዴት ይዛመዳል?» ብለን እንጠይቃለን። ክርስቶስ በተአምራት አማካኝነት በማስተማር ሁለት ነገሮችን አከናውኗል። በመጀመሪያ፥ ለምትህርቱ ልባቸውን ለከፈቱት ሰዎች፥ እነዚህ ምሳሌዎች ጥልቅ መንፈሳዊ እውነቶችን ለማብራራት እንደ መልካም የማስተማሪያ መሣሪያዎች አገልግለዋል። ክርስቶስ ብዙ ሰዎች ንድፈ አሳባዊ እውነቶችን ለመረዳትና ከሕይወታቸው ጋር ለማዛመድ እንደሚቸገሩ ስለሚያውቅ፥ መንፈሳዊ እውነቶችን ለማብራራት በእነዚህ ምሳሌዎች ተጠቅሟል። ሁለተኛ፡ ለመንፈሳዊ እውነቶች ልባቸውን ላልከፈቱ ሰዎች፥ እነዚህ ምሳሌዎች የወንጌሉን እውነት ስለሚደብቁ የእግዚአብሔርን ፍርድ ያመለክታሉ። ማቴዎስ ከክርስቶስ ምሳሌዎች ብዙዎችን ሰብስቦ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ያሰፈረ ይመስላል። ክርስቶስ የጀመረውን የመንግሥተ ሰማይ ምሥጢራት የሚያብራሩ ሰባት ምሳሌዎች ቀርበዋል። ሀ. የአራት ዓይነት መሬቶች ምሳሌ (ማቴ. 3፡1-23)። ክርስቶስ የመጣው ወንጌልን እየሰበከ ነበር። ከዚያም ደቀ መዛሙርቱና እኛም መልካሙን የምሥራች ወደ ሰዎች ሁሉ እንድናደርስ አዝዞናል። ነገር ግን ሰዎች ለምስክርነታችን የምንፈልገውን ዓይነት ምላሽ በማይሰጡበት ጊዜ፥ እንዳንደነቅ ወይም ተስፋ እንዳንቆርጥ፥ ክርስቶስ አራት የተለያዩ ነገሮች ስላጋጠሙት ስለ ግብርና የሚያስረዳ ምሳሌ ተናግሯል። አንዳንድ ዘሮች በፍጹም አይጎነቁሉም። ይህ ወንጌሉን ከሰሙ በኋላ ለማመን ከመወሰናቸው በፊት፥ ሰይጣን ዘሩን በመውሰዱ ምክንያት ምላሽ ከመስጠት የሚታቀቡትን ሰዎች የሚያመላክት ነው። ሌሎች ዘሮች በድንጋያማ መሬት ላይ ይወድቃሉ። እነዚህ ሰዎች ወንጌሉን ሰምተው ማመናችውን ይናገራሉ። ነገር ግን ያልተጠበቁ ነገሮች፣ ችግሮች ወይም ስደት ስለሚደርስባቸው፥ ለወንጌሉ ጀርባቸውን ሰጥተው ወደ ዓለም ይመለሳሉ። በአረሞች መካከል የሚወድቁ ዘሮች ይታነቃሉ። እነዚህ ወንጌሉን ሰምተው በክርስቶስ የሚያምኑ ሰዎች ናቸው። ነገር ገን የዓለም ነገሮች (ገንዘብ፥ ሥራ፥ ትምህርት፥ ቤተሰብ፥ ወዘተ…) እምነታቸውን አንቆ ስለሚገድልና ወደ ዓለም እንዲመለሱ ስለሚያደርግ፥ ልባቸው የተከፋፈለ ይሆናል። አንዳንድ ዘሮች በመልካም መሬት ላይ ይወድቃሉ። እነዚህ ወንጌሉን ሰምተው በሚያምኑትና እምነታቸውም በመንፈሳዊ ፍሬዎች የሚታዩ ናቸው። የውይይት ጥያቄ፡- እነዚህ አራት ምላሾች ለወንጌሉ ሲሰጡ የተመለከትክበትን ሁኔታ ግለጽ። ደቀ መዛሙርቱ ክርስቶስ በማቴ. 5-7 ካቀረባቸው ዓይነት ግልጽ ስብከቶች፥ ስውር ትርጉም ወዳላቸው ምሳሌዎች በመዛወር፥ የማስተማር ዘዴ መቀየሩን ተመልክተዋል። ምክንያቱን በጠየቁት ጊዜ፥ እንደ ደቀ መዛሙርቱ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት የመማር ዕድል እንደነበራቸው ገልጾአል። በክርቶስ ማመናቸውን ስላሳዩ፥ የበለጠ እውነት ጨምሮላቸዋል። ነገር ግን ሌሎች፥ በተለይም የሃይማኖት መሪዎች ክርስቶስን የመቃወም አቋም ስለወሰዱ፥ የመገንዘብ ዕድል አልነበራቸውም። ተቃውሟቸው ድንገተኛ ክስተት አልነበረም። በኢሳይያስ ዘመን ብቻ ሳይሆን፥ በክርስቶስም ዘመን የሚኖሩትን ሰዎች የገለጸውን የኢሳይያስ 6፡9-10 ትንቢት ፈጽሟል። ደቀ መዛሙርቱ ዕድለኞች ነበሩ። ምንም እንኳ የብሉይ ኪዳን ነቢያት የክርስቶስን መምጣት ሲናፍቁም፥ እርሱንም ሆነ የትንቢታቸውን ፍጻሜ ለመመልከት አልታደሉም ነበር። ለ. የአረሞች ምሳሌ ማቴ. 13፡24-30)። አይሁዶች የመሢሑ መንግሥት፥ ጠላቶቻቸውን እንደሚያወድምና በክፉዎች ላይ እንደሚፈርድ አስበው ነበር፡፡ ክርስቶስ ግን መንግሥቱ የዚያን ዓይነት መንገድ እንደማይከተል ገልጾላቸዋል። የመንግሥቱን ዘገምተኛ ዕድገት ከሁለት ሰዎች ጋር አነጻጸረ። ገበሬው ስንዴ ሲዘራ ጠላቱ ከስንዴው ጋር የሚመሳሰል እንክርዳድ ጨመረበት። ሠራተኞቹ እንክርዳዱን ለመንቀል ሲፈልጉ፥ ገበሬው ስንዴውና እንክርዳዱ አድገው በቀላሉ እስከሚለዩበት ጊዜ ድረስ እንዲታገሡ ነገራቸው። ክርስቶስ የምሳሌዎቹን ትርጉም በማቴ. 3፡36-43 ኣብራርቷል። ገበሬው ክርስቶስ፣ እርሻው ዓለም፥ ስንዴው እማኛችን ይወክላሉ። ጠላት የተባለው ሰይጣን ሲሆን፥ አረሞቹ የክርስቶስ ተከታዮች ነን የሚሉ የሰይጣን «ልጆች። ናቸው። ክርስቶስ መንግሥቱ ቀስ እያለች ስታድግ በክርስቶስና በሰይጣን መንግሥታት መካከል የማያቋርጥ ትግል እንደሚካሄድ አስረድቷል። ከዚህ ትግል ውስጥ የተወሰነው በእያንዳንዱ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስለሚካሄድ የተሰወረ ይሆናል። ለዚህም ምክንያቱ የሰይጣንና የክርስቶስ መንግሥት ተከታዮች መኖራቸው ነው። ማን እውነተኛ፡ ማን ደግሞ ሐሰተኛ አማኝ እንደሆነ ለመረዳት ያስቸግራል። አንዳንድ ጊዜ ክርስቲያኖች፥ ክርስቲያኖች እንዳልሆኑት፥ ክርስቲያኖች ያልሆኑት ደግሞ እንደ ክርስቲያኖች ሊመላለሱ ይችላሉ። የክርስቶስ እውነተኛ ተከታዮች ያልሆኑ ሰዎች፥ ክርስቶስን «ጌታ ሆይ» ብለው ሊጠሩትና ተአምራትን ሳይቀር ሊፈጽሙ እንደሚችሉ ቀደም ብለን ተመልክተናል። እውነተኛ ክርስቲያኖችን ከሐሰተኞቹ መለየት የቤተ ክርስቲያን መሪዎችና አገልጋዮች ኃላፊነት አይደለም። የመጨረሻው ዘመን በመጣበት ጊዜ ክርስቲያኖች ባልሆኑት ላይ ፍርድ ይሰጣል። በዚያን ጊዜ በስንዴ ተምሳሌትነት የተገለጹት የእግዚአብሔር ልጆች በከፍተኛ ደረጃ ይባረካሉ። ንጹሕ ቤተ ክርስቲያን ብንሻም፣ ይህ በዘመናችን የሚሳካ አይሆንም። ሁልጊዜም ክርስቲያኖች ነን ብለው የሚገበዙና የሐሰት አስተማሪዎች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይኖራሉ። ስለዚህ ከስንዴው ወገን ነን ወይስ ከእንክርዳዱ ብለን ራሳችንን ልንጠይቅ ይገባል። የውይይት ጥያቄ፡- ይህን እሳት በቤተ ክርስቲያንህ ውስጥ ያየኽው እንዴት ነው? ሐ. የሰናፍጭ ንጣትና ያእርሾ ምሳሌዎች (ማቴ 13፡31-35)። ክርስቶስ መንግሥቱ ከትንሽ ብትጀምርም እንኳ እያደገች በመሄድ ታላቅ እንደምትሆን ተናግሯል። ክርስቶስ ተመሳሳይ ፍች ያላቸውን ሁለት ምሳሌዎች ተናገረ፡፡ የሰናፍጭ ቅንጣት በአይሁዶች ዘንድ ከታወቁ ትናንሽ የተክል ዘርች አንዱ ነው፡ ነገር ግን ይህ አነስተኛ ዘር በከፍተኛ ደረጃ በማደግ የወፎች መኖሪያ እስከ መሆን ድረስ ይደርሳል፡፡ ብዙ ሑራን ይህ የወፎች ማረፊያነት ምሳሌ፥ ከዳን. 4፡20-21 እንደ መጣ ያስባሉ። ይህ ምሳሌ የክርስቶስ መንግሥት በ12 ደቀ መዛሙርት አማካኝነት በአነስተኛ ደረጃ እንደሚጀምር ያሳያል፡ ነገር ግን በምድር ላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አማኞች እስኪኖሩት ድረስ ማደጉን ይቀጥላል። መንግሥቱ ከፍጻሜ በሚደርስበት ጊዜ፥ ክርስቶስ በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ሰዎች ልብ ውስጥ ይገዛል። ይኽው መንግሥት ክርስቶስ በምድር ነገሥታት ሁሉ ላይ እስከሚቆጣጠርበት ጊዜ ድረስ ማደጉን ይቀጥላል። እርሾም በጣም አነስተኛ ነገር ነው። ነገር ቀን ትንሽ እርሾ ብዙ ሊጥ ሊያቦካ ይችላል፡፡ ብዙውን ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ እርሾን የጥፋት ተምሳሌት አድርጎ ይጠቀማል ማቴ 16፡6፤ 1ኛ ቆሮ. 5፡6-8)። እዚህ ላይ ግን እንደ ስናፍጭ ቅንጣት ሁሉ እርሾ የክርስቶስን መንግሥት መስፋፋት ያመለክታል፡፡ ከአይሁድ ሕዝብ ወይም ከርመ ሠራዊት ሲነጻጸሩ፥ ክርስቶስና ደቀ መዛሙርቱ ከቁም ነገር የማይቆጠሩ ሊመስሉ ቢችሉም፣ ከጊዜ በኋላ በአለም ሁሉ ይስፋፋሉ። የውይይት ጥያቄ፡- የእግዚአብሔር መንግሥት (ቤተ ክርስቲያንን ከአነስተኛ ጀምሮ ወደ ታነት ሊያድ የተመለከትንው እንዴት ነው? መ. የተሰወረች መዝገብና የዕንቁ ምሳሌዎች (ማቴ 13፡44-46)። የእግዚአብሔር መንግሥት ምን ያህል ገንዘብ ያመጣል? አንድ ሰው ይህን መንግሥት ለማግኘት ምን ማድረግ ይኖርበታል? የእግዚአብሔር መንግሥት ለሰው ሕይወት እጅ አስፈላጊ መሆኑንና ይህን መንግሥት ለማግኘት ሌሎች ሀብቶቻችንን መተው እንዳለብን ለማሳየት፥ ክርስቶስ እነዚህን ሁለት ምሳሌዎች ተናግሯል። አንድ ሰው ብዙ ሀብት ያለውን መሬት ለመግዛት ንብረቱን ሁሉ መሸጥ ነበረበት። እንዲሁም አንድ ነጋዴ ከፍተኛ ዋጋ ያለውን ዕንቁ ለመግዛት ትናንሽ ጌጣጌጦቹን ሁሉ ሸጠ። በዚህ መሠረት የእግዚአብሔር ዘላለማዊ መንግሥት አባል ለመሆንና እጅግ የላቀ በረከት ለመቋደስ የሚፈልጉ ሰዎች ሁሉ፥ የሚወዷቸውን ሌሎች ነገሮች ትተው መንግሥቱን መሻት ይኖርባቸዋል። የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማግኘት፥ እያንዳንዳችን ራሳችንን የሰጠን የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት መሆን አለብን። የውይይት ጥያቄ፡- ሀ) ብዙ ሰዎች የሚወዷቸውን ነገሮች መተው እንዳለባቸው ሳያስቡ ክርስቲያኖች ይሆናሉ። እነዚህ ምሳሌዎች ስለ እነዚህ ሰዎች ምን ያስተምራሉ? ለ) ዛሬ ክርስቲያኖች የክርስቶስን ዘላለማዊ መንግሥት ለማግኘት ከልባቸው ከፈለጉ ሊተዉአቸው የሚገቧቸው ነገሮች ምንድን ናቸው? ሠ. የመረብና ዓሣ ምሳሌ (ማቴ. 13፡47-50)። የስንዴና እንክርዳድ ምሳሌ፥ የክርስቶስን መንግሥት ዕድገት ረዥም ሂደትና እስከ መጨረሻው ዘመን ድረስ ክርስቲያኖችና ዓለማውያን ጎን ለጎን እንደሚጓዙ ሲያመለክት፥ ይህ ምሳሌ መጭውን ፍርድ ያሳያል። ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎቹ ዓሣ አጥማጆች ስለነበሩ፥ ክርስቶስ ይህንን ሙያ በምሳሌነት ተጠቅሟል። ዓሣ አጥማጆቹ ከሚጠቀሙባቸው መረቦች አንዱ

ክርስቶስ በምሳሌዎች አማካኝነት ስለ እግዚአብሔር መንግሥት አስተማረ (ማቴዎስ 13:1-58) Read More »