የሕይወት እንጀራ

ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር

This entry is part 52 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ሀ. አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር  ከታላቁ የነጭ ዙፋን ፍርድ እንዲሁም ከመጀመሪያው ሰማይና ምድር ውድመት በኋላ የሚሆነውን ነገር አስመልክቶ ዮሐንስ የሚከተለውን ጽፏል፡- “አዲስ ሰማይና አዲስ ምድርን አየሁ፥ ፊተኛው ሰማይና ፊተኛዪቱ ምድር አልፈዋልና” (ራእይ 21፡1)። ስለ አዲሱ ሰማይ የተገለጠ ነገር የለም። ስለ አዲሲቱ ምድር የተገለጠ ነገር ቢኖር “ባሕርም ወደ ፊት የለም” የሚለው ነው (ራእይ 21፡1)። ስለ አዲሲቱ ሰማይና ምድር መጽሐፍ ቅዱስ ዝም የማለቱ ምክንያት በየትኛውም ስፍራ ማብራሪያ አልተሰጠውም። ይልቁንም ትኩረታችንን ወደ አዲሲቱ የኢየሩሳሌም ቅድስት ከተማ ይወስደዋል።  ለ. የአዲሲቱ ኢየሩሳሌም አጠቃላይ ገለጣ  ዮሐንስ የተመለከተውን ነገር እንዲህ ሲል ያወጋናል፡- “ቅድስቲቱም ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም፥ ለባልዋ እንደተሸለመች ሙሽራ ተዘጋጅታ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ” (ራእይ 21፡2)። የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎችን ሁሉ የሚገጥማቸው ቅፅበታዊ ችግር ዮሐንስ የተመለከተው ነገር ፍች ነው። ቀጥተኛ እሳቡን ከወሰድን፥ ዮሐንስ የተመለከተው፥ ከምድር ጋር አብራ ከጠፋችው አሮጌዪቱ ኢየሩሳሌም በተቃራኒ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ተብላ የተጠቀሰች ቅድስት ከተማን መሆኑን እንረዳለን። ከተማዪቱ “ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደወረደች” ተገልጧል። እንደተፈጠረች ግን እልተገለጠም። ከሺህ ዓመት መንግሥት በፊት ከአሁኗ ምድር በላይ የነበረች ከተማም ትመስላላች። ከሞት ለተነሡትና ወደ ቅድስናቸው ለገቡት አማኞች በሺህ ዓመቱ መንግሥት ጊዜ በዚህ ሁኔታዋ በመኖሪያነት ሳታገለግል አትቀርም። ስለ ሺህ ዓመቱ ዘመን ምድር ከቀረበው ገለጣ ለመረዳት እንደሚቻለው፥ በምድር ላይ እንደ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ያለ ከተማ አልነበረም። እንዳንዶች ጌታችን ዮሐንስ 14፡3 ውስጥ ሜጄ ስፍራ አዘጋጅላችኋለሁ”፥ ሲል ስለ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም መናገሩ ነበር ብለው ያምናሉ። በራእይ መጽሐፍ መሠረት አዲሲቱ ከተማ ካሰማይ በመምጣት በአዲሲቱ ምድር ላይ እንድትቀመጥ የተወሰነ ይመስላል።  ዮሐንስ በተጨማሪም ከተማይቱን “ለባሏ እንደተሸለመች ሙሽራ” ብሉ ይገልጣታል። አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ለባሏ እንደተሸለመች ሙሽራ ውብ ናት። ስለሆነም፥ ከተማዪቱ አካላዊ ሕልውናና የሙሽራ ውበት ያላት መሆኑ ግልጥ ነው።  ምንም እንኳ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ አዲሱ ሰማይና አዲሲቱ ምድር የሚናገሩ ክፍሎች ብዙዎች ባይሆኑ፥ አሳቡ ራእይ መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሰው ለመጀመሪያ ጊዜ አለመሆኑ ግልጥ ነው። ኢሳይያስ 65፡17 ውስጥ እግዚአብሔር እንዲህ ብሏል፡- “እሆ፥ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እፈጥራለሁና፤ የቀደሙትም አይታሰቡም፥ ወደ ልብም አይገቡም።” ይህ ጥቅስ የሚገኘው ካሺህ ዓመቱ መንግሥት ጋር በተዛመደ ሁኔታ በመሆኑ፥ አንዳንዶች በሺህ ዓመቱ ዘመን ስለምትታደሰው ኢየሩሳሌም የሚናገር ነው ይላሉ። ይሁንና፥ ይህ ክፍል አዲሲቱ ምድር ላይ የምትሆነውን አዲሲቱን ኢየሩሳሌም የሚያመለክት መሆኑን መረዳቱ የተሻለ አማራጭ ይሆናል።  ሌላው ጥቅስ ኢሳይያስ 66፡22 ውስጥ ያለው ሲሆን፥ የሚከተለውን እሳብ ያስተላልፋል፡- “እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ከፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፥ እንዲሁ ዘራችሁና ስማችሁ ጸንተው ይኖራሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።” ምድራዊቷ ኢየሩሳሌም በሺህ ዓመቱ ፍጻሜ ላይ የምትደመሰስ ስትሆን፥ አዲሲቷ ኢየሩሳሌም ግን እንደ እስራኤል ዘር ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።  2ኛ ጴጥሮስ 3፡13 ውስጥ ስለ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር የተነገረው ሌላ ትንቢት፥ “ጽድቅ የሚኖርባት” እንደምትሆን ያስረዳል። ስለሆነም፥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱት ቃላት ሁሉ የሚያስረዱት፥ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር የታሪክ የመጨረሻ ግብና የቅዱሳን የማረፊያ ስፍራ መሆናቸውን ነው ብሎ ለመደምደም ይቻላል።  ዮሐንስ አዲስ ሰማይን፥ አዲስ ምድርንና አዲሲቱን ኢየሩሳሌም ካስተዋወቀ በኋሳ፥ ራእይ 21:3-8 ውስጥ ዋነኛ ባሕርያቸውን ይገልጣል። በዚያ ስፍራ እግዚአብሔር ከሰዎች ጋር ይኖራል፤ “አምላካቸውም ይሆናል”። ኀዘን፥ ሞትና ሥቃይ ከእንግዲህ አይኖርም፤ “የቀደመው ሥርዓት እልፎአልና” (ቁ.4)። ይሄው እሳብ ቁጥር 5 ውስጥ ““እነሆ፥ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ” በሚለው ዓረፍተ ነገር ተረጋግጧል።  ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ አልፋና ኦሜጋነቱ በአዲሲቱ፥ ኢየሩሳሌም “ለተጠማ የሕይወትን ውኃ ምንጭ እንዲያው እኔ እሰጣለሁ። ድል የሚነሣ ይህን ይወርሳል፤ አምላክም እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል” (ቁ. 6-7) በማለት ተስፋ ይሰጣል። በአንጻሩ፥ በክፉ ሥራዎቻቸውና በእምነት እልባነታቸው የተገለጡት ያልዳኑ ሰዎች፥ “ዕድላቸው በዲንና በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይሄውም ሁለተኛ ሞት ነው” (ቁ. 8)። አካላዊና መንፈሳዊ ከሆነው የመጀመሪያው ሞት ጋር ሲነጻጸር፥ ሁለተኛው ሞት ለዘላለም ከእግዚአብሔር መለየት ነው።  ሐ. የአዲሲቱ ኢየሩሳሌም ራእይ  ዮሐንስ “የበጉ ሚስት የሆነችውን ሙሽራ፥ እንዲመለከት ተጋብዞ ነበርና፥ “በመንፈስ ወደ ታላቅና ረጅም ተራራ” ተወሰደ (ራእይ 21፡9-10)። እዚያ ሆኖ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ ይመለከታል።  እንደ ቀጣዩ ራእይ 21 ገላጣ፥ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም “የእግዚአብሔር ክብር” አለባት፤ “ብርሃንዋም እጅግ እንደከበረ ድንጋይ እንደ ኢያሰጲድ ድንጋይ ሆኖ እንደ ብርሌ የጠራ ነበር” (ቁ. 11)። ምንም እንኳ ኢያሰጲድ የተለያየ ቀለም ያላቸውን ድንጋዮች የሚያመለክት ቢሆንና እብዛኞቹ የዘመናችን የኢያሰጲድ ድንጋዮች የጠሩ ባይሆኑ፥ እዚያ የተጠቀሰው ድንጋይ ግን እንደ ብርሌ የሚያንጸባርቅ መሆኑ ተመልክቷል። ዮሐንስ ሊጎልጥ የፈለገው እጅግ የላቀውን ውበት ነው።  ቀጣዮቹ ቁጥሮች እንደሚያስረዱት የከተማይቱ ቅጥር አንድ መቶ አርባ አራት ክንድ ሲሆን፥ በአሥራ ሁለት መላእክት የሚጠበቁ አሥራ ሁለት ደጆች አሏት (ራእይ 21 ፡12)። ደጆቿ ላይ የአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ስሞች ተጽፈውባቸዋል። ከተማዪቱ በቅርፅ አራት ማዕዘን ስትሆን፥ ወደ ሰሜን፥ ደቡብ፥ ምሥራቅና ምዕራብ ትመለከታለች። ይህ ምናልባትም እንደአሁኗ ምድር በአዲሲቱም ምድር የተለያዩ አቅጣጫዎች የሚኖሩ መሆኑን ያመለክታል። ቅጥርዋ ያረፈው እሥራ ሁለት መሠረቶች ላይ ሲሆን፥ እንደ ቁጥር 14 አገላለጥ መሠረቶቹ ላይ የአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ስሞች ተጽፈውባቸዋል።  ከተማዪቱ ተለክታ የተገኘው ውጤት አሥራ ሁለት ሺህ ምዕራፍ ወይም ወደ ሦስት ሺህ ሦስት መቶ ኪሎ ሜትር ያህል ርዝመት ነው። ቁመቷም ከወርዷ ጋር እኩል ነበር። ይህ ከተማዪቱ ሰቅርፅ ኩብ ናት ወይስ ፒራሚዳዊ? የሚል ጥያቄ አስነሥቷል።  ምናልባትም ፒራሚዳዊ ቅርፅ እንዳላት መገመቱ ሳይሻል አይቀርም። ራእይ 22: 1-2 ውስጥ እንደተመለከተው፥ በከተማዪቱ መካከል ውኃ እንዴት እንደሚፈስ ለማብራራት ይህ ይረዳል።  በከተማዪቱ ውስጥ የሚገኙት ነገሮች በአጠቃላይ ብርሃን አስተላላፊዎች ናቸው። ወርቁ እንኳን እንደ ብርጭቆ የጠራ ነው (21፡18)። የከተማዪቱ ግድግዳ መሠረቶች ቤተ ክርስቲያንን የሚወክሉ አሥራ ሁለት ደቀ መዛሙርት ስሞች የተጻፉባቸውና በአሥራ ሁለት ውብ ድንጋዮች የተጌጡ ሲሆኑ፥ በቀስተ ደመናና በከተማዪቱ ድንቅ ብርሃን ውስጥ የሚገኙ ቀለማትን ያንጸባርቃሉ። ይህ ሁሉ ተዋሕዶ ሲታይ ልብን ይመስጣል (ቁ. 19-20)።  የካተማዪቱ ደጆች ሰፋፈ፥ እያንዳንዳቸው ከዕንቁ የተሠሩና አደባባይዋ ጥሩ ብርጭቆ የሚመስል ወርቅ እንደሆነ ተገልጧል (ቁ. 21)። እግዚአብሔር በውስጧ ስለሚኖር፥ ለከተማይቱ መቅደስ አያስፈልጋትም (ቁ. 22)፤ የእግዚአብሔርና የበጉ ክብር ስለሚያበራላትም የፀሐይ፥ የጨረቃ ወይም የከዋክብት ብርሃን አያስፈልጋትም (ቁ. 23)። ከአሕዛብም የዳኑት በከተማይቱ ብርሃን እየተመላለሱ በነጻነት ወደ ሰሮቿ ይገባሉ። በዚያም ሌሊት ስለሌለ” ደጆቿ ከቶ አይዘጉም (ቁ. 25)።  በዚህ ገለጣ መሠረት፥ የከተማይቱ ነዋሪዎች የሁሉም ዘመናት ቅዱሳን ናቸው። የተጠቀሱት እስራኤልና አሕዛብ ብቻ ሳይሆኑ፥ ቤተ ክርስቲያንን የሚወክሉ አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ጭምር ናቸው። ይህ በዕብራውያን መልእክት ምዕራፍ 12፡22-24 ውስጥ ከተገለጠው አሳብ ጋር ይስማማል። ምንባቡ እንደሚያስረዳው፥ በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም የሚገኙ ቅዱሳን፥ “አእላፋት መላእክትን፥ በሰማይ የተጻፉትን የበኩራት ማኅበር፥ የሁሉም ዳኛ የሚሆነውን እግዚአብሔርን፥ ፍጹማን የሆኑትን ጻድቃን መንፈሶችና የአዲስ ኪዳን መካከለኛ የሆነው ኢየሱስን” ያጠቃልላሉ። ከዚህ በመነሣት፥ ቤተ ክርስቲያን፥ “ፍጹማን የሆኑት የጻድቃን መንፈሶች፥ መግለትም በቤተ ክርስቲያን ያልተካተቱት አይሁዶችና እሕዛብ፥ መላእክትና የአዲሱ ኪዳን መካከለኛ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም ይገኛሉ በማለት ለመደምደም ይቻላል።  ዮሐንስ ስለ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ባቀረበው ተጨማሪ ማብራሪያ፥ በአደባባይዋ መካከል ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን የሚወጣውን እንደ ብርሌ የሚያንጸባርቀውን የሕይወትን ውኃ ወንዝ”” እንደተመለከተ ይገልጣል (ራእይ 22:1)። በከተማይቱ አደባባዮች መካከልና ከወንዙ ወዲያና ወዲህ አሥራ ሁለት ዓይነት ፍሬዎችን የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ እንደሚገኝና ለሕዝብ ፈውስን ወይም ጤናን እንደሚሰጥ ገልጧል (ራእይ 22፡2)።  “ይህ የዘላለም መንግሥት ገለጣ ከሆነ፥ ፈውስ ያስፈለገው ለምንድነው?” የሚል ጥያቄ ሲነሣ ቆይቷል። “ለሕዝብ ጤና” የሚለው አተረጓጎም ከተወሰደ ችግሩ በቀላሉ ይወገዳል። ከሕይወት ውኃ በተጨማሪ የዛፍ ፍሬ መኖሩ ቅዱሳን ለዘላለም የሚኖራቸውን አካላዊ ሕልውና የሚገልጥ ሊሆን ይችላል።  ዮሐንስ በተጨማሪም፡- “ከእንግዲህ ወዲህ መርገም ከቶ አይሆንም። የእግዚአብሔር የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ ይሆናል፥ ባሪያዎቹም ያመልኩታል” ይላል (ቁ. 3)። በዚህ የበረከት ወቅት ቅዱሳን እግዚአብሔርን ፊት ለፊት የሚመለከቱት

አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር Read More »

ታላቁ የነጭ ዙፋን ፍርድ

This entry is part 51 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ሀ. የታላቁ ነጭ ዙፋን የመጨረሻ ፍርድ  እንደ ሰብአዊ ታሪከ ድምዳሜነቱ በሺህ ዓመቱ መንግሥት መጨረሻ ላይ የታላቁ ነጭ ዙፋን ፍርድ የሚኖር መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል (ራእይ 20፡11-15)። ቀደም ሲል ለጻድቃን ከተደረጉትና በዓለም በሚኖሩ እስራኤላውያን እንዲሁም እሕዛብ ላይ ከተበየኑት የተለያዩ ፍርዶች ጋር ሲነጻጸር ይህ የመጨረሻው ፍርድ ነው። ከዐውደ-ንባቡ አኳያ ስንመለከተው ይህ ፍርድ ኃጢአተኞችን ብቻ ይመለከታል።  ለ. የሰማይና የምድር ውድመት  ታላቁ የነጭ ዙፋን ፍርድ ከመካሄዱ በፊት የሚከተለው ነገር እንደሚሆን ራእይ 20፡11 ውስጥ ተጽፏል፤ “ምድርና ሰማይም ከፊቱ ሸሹ፤ ስፍራም እልተገኘላቸውም።” ሰብአዊ ታሪከ ዘመኑን ስሰፈጀ፥ ራእይ 21፡1 ውስጥ እንደተገለጠው አሮጌው ፍጥረት ይደመሰሳል። “ፊተኛው ሰማይና ፈተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፥ ባሕርም ወደፊት የለም።” 2ኛ ጴጥሮስ 3፡10-12 ይህንኑ ክሥተት በማመልከት ታላቁን አወዳደቅ በሚከተሉት ቃላት ይገልጣል፡- “በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፥ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኩሳት ይቀልጣል፥ ምድርም በእርሷ ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል” (ቁ. 10)። ቀጣዩ ቁጥርም ይህንኑ ያረጋግጣል፤ “ስለዚያ ቀን ሰማያት ተቃጥለው ይቀልጣሉ፤ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኩሳት ይፈታል”፤ ቁጥር 11 እና 12 ውስጥ ደግሞ አሳቦቹ ተዋሕደው፥ “ሰማያት ተቃጥለው ይቀልጣሉ፥ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኩሳት ይፈታል” ተብሏል።  ሐ. ድነት ያላገኙ ሙታን ትንሣኤ  ራእይ 20፡12 ውስጥ እንደተጠቀሰው፥ “ሙታንንም ታናናሾችንና ታላላቆችን በዙፋኑ ፊት ቆመው ዮሐንስ ተመልክቷል። ራእይ 20፡13 ውስጥ ደግሞ፥ “ሳሕር በእርሱ ውስጥ ያሉትን ሙታን ሰጠ፤ ሞትና ሲኦልም በነርሱ ውስጥ ያሉትን ሙታን ሰጡ” በማለት ያክላል። ድነት ያላገኙ ሙታን ሁሉ ከሞት ተነሥተው ፍርዳቸውን ለመቀበል በእግዚአብሔር ፊት ቆመዋል። ከዮሐንስ 5፡27 እንደምንረዳው፥ ፈራጁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በዚያ ክፍል እግዚአብሔር አብ ለወልድ “የሰው ልጅም ስለሆነ ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን ሰጠው”ይላል።  መ. የሰዎችን ሥራዎች የሚገልጡ መጻሕፍት ተከፈቱ  ራእይ 20፡12 ውስጥ “መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ፤ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈሉ” ይላል። ቀጣዩ ቁጥር ይህንኑ የፍርድ እውነታ እንዲህ ይደግመዋል፡-  “እያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን ተከፈለ።” ጳጋን ያለመቀበል ውጤት እዚህ ላይ በግልጥ ይታያል። ከክርስቶስ ውጭ ይቅርታ ስለሌለ (ሐዋ. 4፡12)፥ ጸጋውን ያልተቀበሉ ሁሉ ስለ ኃጢአታቸው ተገቢውን ቅጣት ይቀበላሉ።  የሰዎች ሥራ ብቻ ሳይሆን ስማቸውም በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ መኖሩ ይጣራል። ስማቸው ከመጽሐፉ ውስጥ ከሌለ፥ የዘላለም ሕይወት የላቸውም ማለት ነው።  ይህ ጥፋታቸውን ገሃድ ያደርገውና፥ ራእይ 20፡14-15 ውስጥ እንደተጠቀሰው፥ “ሞትና ሲኦልም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣሉ። ይህም የእሳት ባሕር ሁለተኛው ሞት ነው። በሕይወትም መጽሐፍ ውስጥ ተጽፎ ያልተገኘው ማንኛውም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣለ” የተባለው ይፈጸማል።  ምንም እንኳ ፍርድ ከተሰጣቸው መካከል በአንጻራዊነት አንዳንዶቹ ከሌሎቹ የተሻለ መልካምነት ሊኖራቸው ቢችል፥ የዘላለም ሕይወት ማጣት እጅግ የከፋ ነው። የዘላለም ሕይወት የሌላቸው ሰዎች ሁሉ ከሥራዎቻቸውና በክርስቶስ ካለማመናቸው አኳያ ተፈርዶባቸው፥ ወደ እሳት ባሕር ይጣሳሉ። የሚያሳዝነው፥ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው ክርስቶስ ለዳኑት እንደሞተ ሁሉ ለእነርሱም የሞተ መሆኑ ነው።  2ኛ ቆሮንቶስ 5፡19 ውስጥ፥ “እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውንም አይቆጥርባቸውም ነበር” ይላል። 1ኛ ዮሐንስ 2፡2 ውስጥ ደግሞ ክርስቶስ፥ “የኃጢአታችን ማስተሥረያ ነው፥ ለኃጢአታችንም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ኃጢአት እንጂ” የሚል ቃል እናነሳለን። እነዚህ ወደ ዘላለማዊ ቅጣት የሚጣሉ ሰዎች በክርስቶስ ቢያምኑ ኖሮ ይድኑ ነበር። የሚጠፉት እግዚአብሔር ስላልወደዳቸው ወይም ጻጋው ስላልበቃቸው ሳይሆን፥ ለማመን ባለመፈለጋቸው ነው። ወንጌሉን የመስማት ዕድል ያልነበራቸው ሰዎች ደግሞ እግዚአብሔር በተፈጥሯዊ ዓለም የሰጣቸውን ምስክርነት ባለመቀበላቸው ይጠፋሉ (ሮሜ 1፡18-20)። እነዚህ የበራሳቸውን ብርሃን ያልተቀበሉና ተገቢ ቅጣታቸውን ያገኙ ናቸው። የነጩ ዙፋን ፍርድ ክርስቶስን እንደ አዳኛቸውና ጌታቸው አድርገው ባልተቀበሉ ሰዎች ሁሉ ላይ የሚደርስ እጅግ አሳዛኝ ፍጻሜ ነው። ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

ታላቁ የነጭ ዙፋን ፍርድ Read More »

በሰይጣንና በወደቁ መላእክት ላይ የሚሰጠው ፍርድ

This entry is part 50 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ሀ. በክርስቶስ መስቀል አማካይነት በሰይጣን ላይ የተሰጠ ፍርድ  በሰይጣንና በእግዚአብሔር መካከል ግጭት የተፈጠረው፥ አዳምና ሔዋን ከመፈጠራቸው ረዥም ጊዜ በፊት ሰይጣን መጀመሪያ ከነበረበት ቅዱስ ስፍራ በወደቀ ጊዜ ነበር (የዚህን መጽሐፍ ምዕራፍ 22 ይመልከቱ)። በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ፥ በሰይጣን ላይ የተለያዩ ፍርዶች ተሰጥተዋል። ከነዚህም አንዱ በኤደን ገነት ውስጥ በእባቢቱ ላይ የተሰጠው ፍርድ ሲሆን፥ የሚያመላክተው በሰይጣን ላይ የሚደርሰውን (የሚመጣውን) የመጨረሻ ውድቀት ነው (ዘፍጥ. 3፡15)። በዚያ ስፍራ የሴቲቱ ዘር የሰይጣንን ራስ እንደሚቀጠቅጥና ሰይጣንም የርሱን ተረከዝ እንደሚቀጠቅጥ ተገልጧል። ይህም የክርስቶስን መስቀል ያስከተለውንና በእግዚአብሔርና በሰይጣን መካከል የነበረውን ግጭት ያመለክታል። ክርስቶስ በመስቀል ላይ ቢሞትም ከሞት ተነሥቷል። ይህም “ዕኮናውን ትቀጠቅጣለህ” የሚለውን ቃል ያመለክታል። በአንጻሩ ግን ሰይጣን ፍጹም መሸነፉን የሚያመለክት ከፍተኛ ቁስል ደርሶበታል። ያም “ራስህን ይቀጠቅጣል” የተባለው ነው። ክርስቶስ በሞቱ በሰይጣን ላይ ዘላቂ ድል ተቀዳጅቷል።  ይህ እውነት ክርስቶስ መንፈስ ቅዱስ በመጣ ጊዜ፡- “ስለ ፍርድም የዚህ ዓለም ገዢ ስለተፈረደበት ነው” ባለበት ዮሐንስ 16፡11 ውስጥ ተመልክቷል። ሰይጣን በእግዚአብሔር ላይ በማመፁ በመስቀል ላይ ተፈርዶበታል። በሞት ፍርድ ሥር የነበረውን የሰው ዘር ለማዳን ሲባልም የክርስቶስ ሞት አስፈላጊ ሆነ።  ቀደም ሲል በክርስቶስ ሕይወት የታየ ሌላ ክሥተትም ክርስቶስ ሰይጣንን ያሸነፈው መሆኑን አመልክቷል። ወንጌሉን ለመስበክና ተአምራት ላማድረግ የተላኩት ሰባ ሰዎች ተመልሰው፥ “ጌታ ሆይ፥ አጋንንት እንኳ በስምህ ተገዝተውልናል” አሉ (ሉቃስ 10፡17)። ክርስቶስም ሲመልስሳቸው “ሰይጣንን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ። ብሏል (ቁ. 18)። ይህ የሰይጣንን የመጨረሻ ውድቀት የሚያመላክት ትንቢታዊ ገላጣ ነበር።  ለ. የሰይጣን ከሰማይ መጣል  ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት አርባ ሁለት ወራት ቀደም ብሎ በሺህ ዓመቱ መንግሥት መጀመሪያ አካባቢ፥ የቅዱሳን መላእክት አለቃ በሆነው ሚካኤልና ሰይጣን (“ዘንዶው” ተብሎ የተገለጠው) መካከል በሰማይ ጦርነት ይካሄዳል (ራእይ 12፡7-9)። ሰይጣን በሚዋጋበት ጊዚ “መላእክቱ” ማለትም የወደቁት መላእክት ከጎኑ ይቆማሉ። ሰይጣንና የወደቁት መላእክት በውጊያው ይሸነፋሉ፤ “ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ” (ራእይ 12፡9)።  ራእይ 12፡10 ውስጥ እንደተገለጠው፥ ዕይጣን ባለማቋረጥ ወንድሞችን በመክሰስ በአምላካችን ፊት ቀንና ሌሊት ያሳጣቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰኢዮብ የተጠቀሰው የሰይጣን የክስ ተግባር፥ በመጨረሻ በራሱ በሰይጣን ላይ የሚደርሰውን የኋላ ኋላ ፍርድ በማመልከት ይጠቃለላል። ከዚህ ነጥብ ጀምሮ፥ ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት ሰግምት እርባ ሁለት ወራት በፊት (ራእይ 12፡6 ይመልከቱ) ትንቢታዊ ፕሮግራም መሠረት ሰይጣንና ክፉ መላእክት ላረዥም ጊዜ ከሰማይ ይወገዳሉ። ክርስቶስን ለመፈተን ባልቻለ ወቅት መታየት የጀመረው የሰይጣን ሽንፈት ክርስቶስና ተከታዮቹ አጋንንትን ባስወጡበት ክንውን ገሃድ ለመሆን ችሏል። ክርስቶስ የመስቀል ላይ ሞት የተረጋገጠው የሰይጣን ድል መሆን በፍጥነት ወደ ፍጻሜው በመገስገስ ላይ ነው። ቀደም ሲል ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘውና ፍርድ የተሰጠው ሰይጣን አሁን ፍርዱ ተፈጻሚ ይሆንበታል።  ሐ. የሰይጣን ታሥሮ ወደ ጥልቁ መጣል  በክርስቶስ ዳግም ምጽአት ወቅት ፍርድ የሚሰጠው በተሳዳቢዋ ዓለምና በአለቆቿ ሳይ ብቻ ሳይሆን፥ በሰይጣንና በወደቁት መላእክት ላያም ነው። በራእይ 20፡1-3 ውስጥ ዮሐንስ የሚከተለውን ጽፏል፡- “የጥልቁንም መክፈቻና ታላቁን ሰንሰለት በእጁ የያዘ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ። የቀደመውንም እባብ ዘንዶውን እርሱም ዲያብሎስና ሰይጣን የተባለውን ያዘው፥ ሺህ ዓመትም አሠረው፥ ወደ ጥልቅም ጣለው፥ አሕዛብንም ወደፊት እንዳያስት ሺህ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ በእርሱ ላይ ዘግቶ ማኅተም አደረገሰት፤ ከዚያም በኋላ ለጥቂት ጊዜ ይፈታ ዘንድ ይገባዋል።”  በዚህ ራእይ፥ ስለ ሰይጣን ፍርድ ተጨማሪ ነገር ተገልጧል። የሰይጣን መታሠር ወደ ጥልቁ መጣልና የተዘጋበት መሆኑ ብቻ ሳይሆን፥ ይህ ፍርድ የተሰጠበት ምክንያትም ለዮሐንስ ተነግሮታል። የዚህ ፍርድ ዓላማ የሺህ ዓመቱ መንግሥት አገዛዝ እስኪፈጸም ሰይጣን ሕዝቦችን እንዳያስት ነው። እውነቱ ለዮሐንስ በራእይ የተገለጠ ስለሆነ የዚህ ራእይ ፍች ግልጥ ነው። ሰይጣን አዳምና ሔዋን ከተፈጠሩበት ጊዜ አንሥቶ ያደርግ እንደነበረው ዓለምን ሊያታልል አይችልም።  በክርስቶስ ምድራዊ የሺህ ዓመት አገዛዝ ወቅት የሰይጣን መታሠር ግልጥ እውነትነት፥ የሺህ ዓመቱ መንግሥት ገና የሚሆን እንጂ አሁን ያለ የእግዚአብሔር አገዛዝ ላለመሆኑ ሌላው ጠቃሚ ማረጋገጫ ነው። ቀደም ሲል እንደተመለከትነው (ምዕራፍ 23)። ሰይጣን አሁን ያልታሠረ መሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ግልጥ ሆኗል። ራእይ 19-20 ውስጥ ያለው ቃል በቀጥታ መፈጻም ካለበት፥ መጀመሪያ የክርስቶስ ምጽአት፥ ከዚያ ቀጥሉ ወዲያው የሰይጣን መታሠር ተግባራዊ ሊሆን የግድ ነው። ራእይ ምዕራፍ ሀያ ውስጥ ከርሱ ቀደም ብለውና በኋላ ከሚፈጸሙት ክሥተቶች ጋር የሺህ ዓመቱ መንግሥት ስድስት ጊዜ ተጠቅሷል። በግልጥ እንደሚታየው፥ ሰይጣን የሚታሠረው የሺህ ዓመቱ መንግሥት ጊዜ ከመጀመሩ በፊት ነው።  ስለወደቁት መላእክት እዚህ ምንም ሳይጠቀስ፥ ከሰይጣን ጋር ከአርባ ሁለት ወራት በፊት ከሰማይ እንደተጣሉ ሁሉ አብረውት እንደሚታሠሩ ለመገመት ይቻላል። መጨረሻው ላይ ለአጭር ጊዜ ሲፈታ ከሚሆነው በቀር፥ በሺህ ዓመቱ መንግሥት ውስጥ ሰይጣን ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ሲያደርግ የሚያሳይ መረጃ የለም።  መ. የሰይጣን የመጨረሻ ፍርድ  በራእይ 20፡7 ውስጥ “ሺሁም ዓመት ሲፈጸም ሰይጣን ከእሥራቱ ይፈታል” ይሳል። ቀጠል አድርገን ስናነብ ደግሞ የሚከተለውን አሳብ እናገኛለን፡- “በአራቱም በምድር ማዕዘን ያሉትን አሕዛብ፥ ሰግንና ማጎግን እንዲያስታቸው ለሰልፍም እንዲያሰከትታቸው ይወጣል፤ ቁጥራቸውም እንደ ባሕር አሸዋ የሚያህል ነው። በውጫዊ ጎጽታቸው ብቻ ክርስቶስን እንከተላለን ይሉ የነበሩ ሰዎች በሰይጣን እየተመሩ አሁን እውነተኛውን ማንነታቸውን ያሳያሉ። እነዚህ በሺህ ዓመቱ መንግሥት ዘመን የተወለዱ ልጆች ናቸው፤ ምንም እንኳ በሁኔታዎች አስገዳጅነት በክርስቶስ አምነናል ቢሉ፥ አሁን ግን በግልጥ ዓመፅ የቅዱሳንን ሰፈር እና የተወደደችውን ከተማ ማለትም ኢየሩሳሌምን ይወራሉ። ዕድል-ፈንታቸው ቅፅበታዊ ፍርድ ሲሆን፥ ራእይ 20፡9 ውስጥ እንደሚለው፥ “እሳት ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወርዳ በሳቻቸው።”  ከዚያም ወዲያውኑ «ያሳታቸውም ዲያብሎስ፥ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት ወደ እሳቱና ወደ ዲኑ ባሕር ተጣል፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ቀንና ሌሊት ይሣቀያሉ” (ቁ. 10)። እግዚአብሔር ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ያዘጋጃቸው የመጨረሻ  መቅጫ የእሳት ባሕር እንደመሆኑ፥ የሰይጣን መጨረሻ በዚሁ ይደመደማል (ማቴ. 25፡4 )።  የወደቁ መላእክትም ሰይጣን መጀመሪያ በእግዚአብሔር ላይ የወጠነው ዓመፅ ተካፋዮች ስለነበሩ ፍርድ ተሰጥቷቸዋል (ኢሳ. 14፡12-17፤ ሕዝ. 28፡12-19)። 2ኛ ጴጥሮስ 2፡4፥ “እግዚአብሔር ኃጢአትን ላደረጉ መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ጥሎ በጨለማ ጉድጓድ ለፍርድ ሊጠበቁ አሳልፎ” እንደሰጣቸው ይናገራል። “ገሃነም” የሚለው ቃል የሚያመለክተው፥ ኃጢአተኛ ወደ ዘላለማዊ የቅጣት ስፍራ ከመሄዱ በፊት ለጊዜው የሚቆይበትን ስፍራ ማለትም “ሲኦልን” ሳይሆን፥ ዘላለማዊውን የቅጣት ስፍራ ነው (ራእይ 20፡13-14)።  – የመላእክትም ፍርድ ይሁዳ መጽሐፍ ቁጥር 6 ውስጥ እንዲህ ተመልክቷል። “መኖሪያቸውን የተዉትን እንጂ የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን መላእክት በዘሳሰም እሥራት ከጨለማ በታች እስከ ታላቁ ፍርድ ቀን ድረስ ጠብቋቸዋል።” ይህ አሳብ ስለ ሰይጣንና መላእክቱ ውድቀትና ፍርድ ከሚናገሩት ሴሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባቦች ጋር ሲያያዝ፥ የሚያስተላልፈው ግልጥ መልእክት አለ። ይሄውም ምንም እንኳ ሰይጣንና አንዳንድ ክፉ መላእክት የተወሰነ ነጻነት ቢሰጣቸው፥ በቅዱሳን መላእክትና በእግዚአብሔር ሰዎች ላይ የማያቋርጥ ጦርነት ቢከፍቱም፥ የታሠሩና ነጻነት የተነፈጋቸው ሌሎች መላእክት የሚኖሩ መሆናቸውን ነው። ይሁን እንጂ፥ ክፉዎቹ መላእክት ሁሉ “ለታላቁ ፍርድ ቀን” የተወሰኑ ናቸው። ይህ “የታላቁ ፍርድ ቀን” በሺህ ዓመቱ መንግሥት ፍጻሜ ሰንሰይጣንና በወደቁት መላእክት ሁሉ ላይ የሚሰጥ ነው።  ምንም እንኳ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሰይጣንና የወደቁ መላእክት በዓለም ላይ ከፍተኛ ኃይልና ተጽዕኖ ሲያሳድሩና ባለማቋረጥ እግዚአብሔርን ሲቃወሙ፥ የኋላ ኋላ ሽንፈታቸውና ዘላለማዊ ፍርዳቸው አይቀሬ ነው። እንደ ኢዮብ የሰይጣን ጥቃት የደረሰባቸው ክርስቲያኖች የኋላ ኋላ ድላቸው የተረጋገጠ እንደሚሆንና፥ እግዚአብሔር በራሱ ጊዜ በጠላቶቹ ላይ የሚፈርድባቸው መሆኑን በመረዳት ሊያርፉ ይችላሉ። በሰይጣንና በመላእክቱ ላይ የሚሰጠው ፍርድ ዘላለማዊ የመሆኑ ግንዛቤ የመጣው፥ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ሰሺህ ዓመቱ መንግሥት መጀመሪያ እሳት ባሕር ውስጥ ተጥለው እስከ መንግሥቱ ፍጻሜ እዚያው ከመሆናቸው የተነሣ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ እንደሚናገረው፥ ሁለት ዓበይት ፍርዶች ብቻ አሉ። እነዚህም ማለቂያ የሌለው ሰማያዊ በረከት መቀበልና ዘላለማዊ የሆነው የእሳት ባሕር ሥቃይ ናቸው። ምንጭ፡- “ዋና

በሰይጣንና በወደቁ መላእክት ላይ የሚሰጠው ፍርድ Read More »

የሺህ ዓመቱ መንግሥት

This entry is part 49 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ህ. የእግዚአብሔር መንግሥት ፅንሰ-ሃሳብ  መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የእግዚአብሔር መንግሥት ሲባል በአጠቃላይ እግዚአብሔር ዓለማትን የሚገዛ መሆኑን ያመለክታል። እግዚአብሔር ሁልጊዚ ሉዓሳዊና ሁሉን ቻይ ሆኖ ስለሚኖር መንግሥቱም ዘላለማዊ መሆኑ ይታመናል። ሰእግዚአብሔር ብርታት ዝቅ የተደረገው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ለዚህ አባባል እንዲህ በማለት ምስክርነቱን ይሰጣል፡- «ዘመኑም ከተፈጸመ በኋላ እኔ ናቡከደናዖር ዓይኔን ወደ ሰማይ አሣሁ፥ አእምሮዬም ተመለሰልኝ፤ ልዑሉንም ባረክሁ፥ ስቶሳሰም የሚኖረውን አመሰገንሁ አከበርሁትም፤ ግዛቱ የዘላለም ግዛት ነውና። ምድርም የምኖሩ ሁሉ እንደ ምናምን ይቆጠራሉ፤ በሰማይም ሠራዊት በምድርም ላይ ሰሚኖሩ መካከል እንደ ፈቃዱ ያደርጋል፤ እጁንም የሚከለክላት ወይም ምን ታደርጋለህ የሚለው የለም” (ዳን. 4፡34-35)።  ከዘመናት በፊት ሰይጣንና እርሱን የደገፉ የመላእክት ጭፍሮች የእግዚአብሔርን የዓለማት ገዢነት ተቃውመው ነበር። እግዚአብሔር ዓመፀኞቹን በመቅጣት ሉዓላዊነቱን አሳይቷል። የኃጢአት ወደ ዓለም መቀባትም በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የእግዚአብሔርን ሉዓላዊነት እስገንዝቧል። ይህ የሚያመለክተው፥ የመለኮታዊ መንግሥትን ፅንሰ-አሳብን ነው። በሌላ አባባል እግዚአብሔር ምንም እንኳን ዛሬ በፍጥረታቱ አማካይነት ቢሠራ፥ ብቸኛና ታላቅ ገዢ ግን እርሱ ነው።  አዳም ሲፈጠር ምድርን እንዲገዛ ተፈቅዶለት ነበር (ዘፍጥ. 1፡26፥ 28)። ይሁንና፥ አዳምና ሔዋን ለእግዚአብሔር ባለመታዘዝ የተከለከለውን የዛፍ ፍሬ በሉ። አዳም በኃጢአት በመው፪ቁ የመግዛት መብቱን አጣ። ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር በሉዓላዊነቱ የተወሰኑ ሰዎችን ብቻ መርጦ የአገዛዝ ኃላፊነት ሰጣቸው። በዚሁ መሠረት አንዳንድ ሰዎች ገዥነት የተፈቀደላቸው መሆኑን ከታሪክ እንረዳለን። ለምሳሌ፥ ዳንኤል እግዚአብሔር ናቡከደነፆርን የቀጣው መሆኑን ሲገልጥ፥ “ልዑል አምላክም በሰዎች መንግሥት ላይ እንዲሠለጥን፥ የሚወደውንም እንደሚሾምበት እስኪያውቅ ድረስ” ብሏል (ዳን. 5፡21)።  በብሉይ ኪዳን፥ መለኮታዊ አገዛዝ ያለበት መንግሥት በዓቢይነት የታየው በሳኦል፥ በዳዊትና በሰሎሞን በተጀመረው የእስራኤል መንግሥት ጊዜ ነበር። የአሕዛብ መሪዎችም በሉዓላዊው የእግዚአብሔር ዓላማ ውስጥ የፖለቲካ አገዛዝ ክልል እንዲይዙ ተፈቅዶላቸው ነበር። የዚህ በእግዚአብሔር ፈቃድ የሚካሄድና የሚመራ አጠቃላይ የመንግሥት ፅንሰ-አሳብ ሮሜ 13፡1 ውስጥ በሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ተገልጧል፡- ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለሥልጣኖች ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው።››  መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ሉዓላዊነት በፖለቲካዊ መንግሥታትና በአዛዛቸው ላይ የሚገለጥ መሆኑን ከማስገንዘቡም ሌላ፥ እግዚአብሔር በሰዎች ልብ አማካይነት ስለሚዛው መንፈሳዊ መንግሥትም ምስክርነቱን ይሰጣል። ይህ ከሰው ዘር ጅማሬ አንሥቶ ሲከናወን የቆየ ነው። መንፈሳዊው መንግሥት በገዛ ፈቃዳቸው ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ያስገዙ ሰዎችንም ሆነ መላእክትን ያካትታል። ጳውሎስ ሮሜ 14፡17 ውስጥ ሰለዚሁ መንፈሳዊ መንግሥት የሚከተሰውን በመግለጥ ጽፏል፡- “የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሠላም ሰመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ፥ መብልና መጠጥ እይደለችምና።”  ማቴዎስ ወንጌል ውስጥ፥ የሰማይ መንግሥት» እና «“የእግዚአብሔር መንግሥት”፥ የሚሉ ሐረጎችን በመጠቀም ረገድ ተጨማሪ ልዩነት ተ፪ርጓል። ሌሎቹ ወንጌላት “የእግዚአብሔር መንግሥት” የሚሏቸውን ማቴዎስ በተደጋጋሚ የሰማይ መንግሥት” ስለሚል፥ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች ሁለቱም የሚያስተላልፉት ተመሳሳይ መልእክት ነው ብለው ያስባሉ። ሐረጎቹ በጣም የሚመሳሰሉ ቢሆኑም፥ ያጠቃቀማቸው ሁኔታ ሲታይ የሰማይ መንግሥት ከእግዚአብሔር መንግሥት የሚሰፋ ይመስላል። ይሄውም በስንዴና በእንክርዳዱ ምሳሌ ውስጥ መንግሥተ ሰማይ እንክርዳድን፥ የመረቡ ምሳሌ ደግሞ መንግሥተ ሰማይ መልካምና ክፉ ዓሣዎችን ያካተተ ይመስላል (ማቴ. 13፡24-30፥ 36-43፥ 47-50)።  በሌላ በኩል፥ የእግዚአብሔር መንግሥት ዳግም በመወለድ የሚገቡባት እንጂ በተለምዶ የጌታ ነኝ የሚሉ ሰዎች ስብስብ አይደለችም። ይህም ክርስቶስ ለኒቆዲሞስ በተናገረው እሳብ እንዲህ ተብራርቷል፡- “እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም” ዮሐ. 3፡5)። ይሁን እንጂ፥ አብዛኛዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኞች በሁለቱ መንግሥታት መካከል ምንም መሠረታዊ ልዩነት የለም የሚለውን አመለካከት ይመርጣሉ።  ሆኖም በአሁኑና በሺህ ዓመቱ መንግሥት መካከል ንጽጽር ሲደረግ የጎሳ ልዩነት አለ። የአሁኑ መንግሥት “ምሥጢራት” የተሰኙ ዓበይት ገጽታዎች አሉት፤ “ምስጢራቱ” ሰብሉይ ኪዳን ዘመን ያልተሰጡ መንስጦች ናቸው (ማቴ. 13)። ዳሩ ግን ምሥጢራዊ ያልሆነ መንግሥት ከከርስቶስ ዳግም ምጽአት በኋላ ይመሠረታል።  በማይታይና በሚታየው መንግሥት መካከል ልዩነትም አለ። የማይታየው መንግሥት በአሁኑ ዘመን እግዚአብሔር በአማኞች ልብ ውስጥ የሚያካሂደው አገዛዝ ሲሆን፥ የሚታየው መንግሥት ከዳግም ምጽአት በኋላ ሰዎች ሁሉ በምድር ላይ የሚመለከቱት የከበረ መንግሥት ነው። የአሁኑን ዘመን መለኮታዊ አገዛዝ ክልል በሺህ ዓመቱ መንግሥት ጊዜ ከሚሆነው ጋር ለማነጻጸር፥ ይህ ልዩነት በጣም አስፈላጊና ወሳኝ ነው።  የመንግሥትን ፅንሰ-ሃሳብ ከሺህ ዓመቱ መንግሥት ጋር ለማዛመድ በተደረገው ጥረት ሦስት ዓይነት አመለካከቶች ቀርበዋል። የቅድመ ሺህ ዓመታውያን (premillenialism/ ፕሪሚሊኒያሊዝም) አመለካከት፥ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው፥ መጀመሪያ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት እንደሚፈጸምና በኋሳ የሺህ ዓመቱ መንግሥት በምድር ላይ የሚመሠረት መሆኑን ነው፤ ከሺህ ዓመቱ መንግሥት በኋላ ዘላለማዊው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ይለጥቃል ይላል። ይህ አመለካከት ቅድመ ሺህ ዓመታዊ የተባለው የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ከሺህ ዓመቱ መንግሥት የሚቀድም መሆኑን ስለሚያስተምር ነው።  ሁለተኛው አመለካከት፥ በምድር ላይ የሺህ ዓመት መንግሥት አይመሠረትም የሚለውና እልሶሺህ ዓመታዊ (amillenialism/ኢሚሊኒያሊዝምን የተሰኘው ነው። ይህ አመለካከት ክርስቶስ ዳግም ሲመለስ ያለ ምንም የሺህ ዓመት መንግሥት ጣልቃ ገብነት አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር የሚመሠረት መሆኑን ያስተምራል። አመለካከቱ ብሉይም ሆነ አዲስ ኪዳን ስለ ሺህ ዓመቱ መንግሥት የሚናገሩትን ምንባቦች ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ በመተርጎም የዚህ መንግሥት ዘመን በቤተ ክርስቲያን አማካይነት በአሁኑ ጊዜ በምድር ወይም በሰማይ በመከናወን ላይ ነው ይላል።  ሦስተኛው የድህረ-ሺህ ዓመታዊነት (postmillenialism/ፖስትሚሊኒያሊዝም) አመለካከት ነው። ይህ አመለካከት በአሁኑ ጊዜ ወንጌል ዓለምን ሁሉ አሽንፎ ወርቃማ ዘመን የሚያመጣ መሆኑንና ለሺህ ዓመቱ መንግሥት የተተነበየው ሠላምና ጽድቅ በተወሰነ ደረጃ ተፈጻሚ እንደሚሆን ያምናል። አመለካከቱ ይህ ስያሜ የተሰጠው፥ የክርስቶስን ዳግም ምጽአት የወርቃማው ዘመን ጫፍ ወይም የሺህ ዓመቱ መንግሥት ፍጻሜ አድርጎ ስለሚመለከት ነው። አክራሪ የሆኑ የድህረ-ሺህ ዓመታዊ መንግሥት አመለካከት ተከታዮች ክርስቶስ ለሺህ ዓመታት በሰዎች ልብ ውስጥ የሚገዛ መሆኑን ያስተምራሉ። ወደ ለዘብተኛነት የሚያዘመው ድህረ-ሺህ ዓመታዊ አመለካከት ደግሞ፥ ከዘገምተኛ ለውጥ ሂደት አመለካከት ጋር የሚመሳሰል ሲሆን፥ ዓለም ቀስ በቀስ እየተሻሻለች እንደምትሄድና በመጨረሻ ወደ ወርቃማው ዘመን ለመድረስ እንደሚቻል ያምናል። የህያኛው ክፍለ-ዘመን ታሪክ አካሄድ የእግዚአብሔር ዓላማ በሰዎች አማካይነት ውብ እየሆነ በዓለም ያከናወናል የሚለው እምነት ከሚሰጠው መረጃ ደካማነት የተነሣ ተቀባይነት የሌለው ሆኗል። በመሆኑም በአሁኑ ዘመን እብዛኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኞች አንድም የሺህ ዓመታት ዘመን እንደሌለ ወይም ክርስቶስ ከሺህ ዓመት በፊት እንደሚመጣ የሚያምኑ ብቻ ናቸው።  የሺህ ዓመቱ መንግሥት በትክክል በምድር ላይ የሚመሠረት መሆኑን በመደገፍና በመቃወም የሚነሡ በርካታ ሙግቶች ቢኖሩም፥ መፍትሔው የሚገኘው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትንቢቶች በቀጥታ በሚፈቱበት መንገድ ነው። በዚህ ውይይታችን፥ ትንቢት እንደማንኛውም መለኮታዊ መገለጥ በቀጥታ መተርጎም የሚኖርበት መሆኑን እንመለከታለን። በመሆኑም፥ ብዙ የብሉይ ኪዳን ትንቢቶችና አዲስ ኪዳን ውስጥ የራእይ ምዕራፍ ሀያ ዋነኛ እሳብ በቀጥታ የሚናገሩትን መልእክት እንዲያስተላልፉ ሆነው ተተርጉመዋል። በዚሁ መሠረት ከክርስቶስ ጳግም ምጽአት በኋላና፥ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ከመፈጠራቸው በፊት የክርስቶስ የሺህ ዓመት መንግሥት ምድር ላይ የሚመሠረት መሆኑን ትንቢቶቹ ያስረዳሉ።  ለ. የሺህ ዓመቱ መንግሥት፥ የእግዚአብሔር አገዛዝ ሰምድር ላይ  የእግዚአብሔር መንግሥት በቀዳሚነት በሰዎች ልብ ውስጥ የሚፈጸም መንፈሳዊ አገዛዝ መሆኑን ከሚናገረው እልቦ.ሺህ ዓመታውያን አመለካከት ባሻገር፥ በምድር ላይ ክርስቶስ የሚገዛበት መንግሥት እንደሚመሠረት የሚያመለክተውን ድምዳሜ የሚደግፉ አያሌ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባቦች አሉ። ክርስቶስ በዚሁ ምድራዊ መንግሥት ላይ ዋነኛው ፖለቲካዊና መንፈሳዊ መሪ ከመሆኑም በላይ፥ አምልኮ የሚቀርብለት ንጉሥም ነው። ይህ ፅንሰ-አሳብ በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን ውስጥ በሚገባ ዳብሮ ቀርቧል።  ሕዝቦች በእግዚአብሔር ላይ ማመፃቸው በተመዘገበበት መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ሁለት ውስጥ፥ ለእግዚአብሔር ልጅ፥ “ለምነኝ አሕዛብን ላርስትህ የምድርንም ዳርቻ ለግዛትህ እሰጥሃለሁ” የሚል ቃል ተገብቶለታል (ቁ. 8)። ይህ መንፈሳዊ አገዛዝ ሳይሆን፥ ፖለቲካዊ መሆኑ በቀጣዩ ቁጥር ውስጥ እንዲህ ተመልክቷል፡- “በብረት በትር ትጠብቃቸዋለህ፥ እንደ ሸከላ ሠሪ ዕቃም ትቀጠቅጣቸዋለህ” (ቁ. 9)። ይህ የሚያመለክተው፥ ቤተ ከርስቲያንን ወይም በሰማይ የሚሆነውን መንፈሳዊ አገዛዝ ሳይሆን ኃጢአተኞችን ወደ ታች ዝቅ አድርጎ የሚገዛ ፍጹማዊ ንጉሥን ነው።  የመንግሥቱን ምድራዊ ባሕርይ የሚያጎላው ሌላ ምንባብ ኢሳይያስ ምዕራፍ 11 ውስጥ ያለው ነው።

የሺህ ዓመቱ መንግሥት Read More »

የእስራኤልና የአሕዛብ ፍርድ

This entry is part 48 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ሲመጣ፥ በምድር ላይ መንግሥቱን በሚመሠርቱት ታላላቅ ክንውኖች ውስጥ በእስራኤልና በአሕዛብ ላይ የሚተላለፉ ፍርዶች ይካተታሉ። ፍርዶቹ የሚጀምሩት ትንሣኤ ባገኙ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን (እስራኤልና አሕዛብ እና በታላቁ መከራ ዘመን እንዲሁ ትንሣኤ ባገኙ ቅዱሳን (እስራኤልና አሕዛብ) ይመስላል። በምድር ላይ ሰሕይወት በሚኖሩ አይሁዶችና አሕዛብም ላይ ፍርድ ይሰጣል። የኋለኞቹ ፍርዶች ለእግዚአብሔር መንግሥት በተገቡትና ከመንግሥቱ የሚገለሉትን ሰዎች የመለየት ተግባራት ናቸው።  ሀ. ከምት የተነሡ እስራኤላውያንና አሕዛብ ፍርድ  ባለፈው ምዕራፍ እንደተመለከተው፥ የትንሣኤ ትምህርት ብሉይ ኪዳን ውስጥ የታወቀ እውነት ነው። በቤተ ክርስቲያን መነጠቅ ወቅት ከሚካሄደው ትንሣኤ በተጨማሪ፥ ክርስቶስ መንግሥቱን ለመመሥረት ወደ ምድር ከሚመጣበት ሁኔታ ጋር በተያያዘ መንገድ የሞቱ ቅዱሳን ከሞት ይነሣሉ። እስቀድሞ እንደተገለጠው፥ ይህን እውነት ዳንኤል 12፡2፥ ኢሳይያስ 26፡19 እና ኢዮብ 19፡25-26 ውስጥ እንመለከታለን። የእስራኤል ትንሣኤ በዳግም ምጽአቱ ወቅት ከሚፈጸመው የሕዝቦቹ መታደስ ጋር በተያያዘ ሁኔታም ተመልክቷል። ሕዝቅኤል 37 ውስጥ በቀረበው ራእይ የደረቁ እጥንቶች ወደ ሕያው አካልነት መቀየር የእስራኤል ሕዝብ መታደስ ተምሳሌት ሲሆን፥ እስራኤላውያን ከመቃብራቸው የሚወጡበት ጊዜ መሆኑንም እንረዳለን (37፡12-14)። እዚህ ላይ ተምሳሌታዊውና ቀጥተኛው ትንቢት የተዋሐደ ይመስላል። ዳዊት ከሞት ተነሥቶ በክርስቶስ ሥር በመሆን እንደሚገዛ በዚሁ ምዕራፍ ተገልጧል። በአጠቃላይ ስለ ሙታኝ ትንሣኤ ለሚያምኑ ሁሉ ብሉይ ኪዳን የጸና እምነት ያስጨብጣል።  በታላቁ መከራ ወቅት በሰማዕታትነት የሚሞቱ ሰዎች ትንሣኤ በክርስቶስ ዳግም ምጽአት የሚፈጸም መሆኑ ራእይ 20 ውስጥ ተገልጧል። ይህ ምናልባትም ከብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ትንሣኤ ጋር በአንድነት የሚፈጸም ይሆናል። የተነሡትም ሺህ ዓመት ከክርስቶስ ጋር እንደሚኖሩና እንደሚነግሡ ተገልጧል (ራእይ 20፡4)። ሽልማታቸውንም ቤት ክርስቲያን በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት በምትሸለምበት አኳኋን የሚቀበሉ ይመስላል። እገልግሎታቸውና እስከ ሞት ድረስ ለእግዚአብሔር በታማኝነት መጽናታቸው፥ በምድር ላይ ከክርስቶስ ጋር ሰመንገሣቸው እውቅናን ያገኛል።  ቤተ ክርስቲያን ክክርሰቶስ ጋር መግዛቷ የተጠቀሰ ክመህኑ እውነት እንጻር እንዳንድ ግራ መጋባቶች ተፈጥረዋል። ከሺህ ዓመቱ መንግሥት ሰፊት ከሞት የሚነሡ ቅዱሳን ሁሉ በተመሳሳይ መንገድ የሺህ ዓመቱ ንግሥና ተካፋይ እንደሚሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ይጠቁማል። እያንዳንዱ በራሱ ተራና በእግዚአብሔር ሉዓላዊ ዓላማ መሠረት ተግባራዊ ይሆናል። ቤተ ክርስቲያን እንደ ክርስቶስ ሙሽራ ትነግሣለች። ከሞት የሚነሡ ቅዱሳንም በተወሰነላቸው ብቃት መሠረት ድነትን እንዳገኙ እስራኤላውያን ወይም አሕዛብ ያነግሣሉ። ይህን ሁኔታ አስቴር እንደ ንግሥት፥ መርዶክዮስ ደግሞ እንደ የንጉሡ ጠቅላይ ሚኒስቴር ከሆኑበት የመጽሐፈ አስቴር ምሳሌ ለመረዳት ይቻላል። አስቴርና መርዶክዮስ የንግሥናው ተካፋዮች ናቸው፤ የንግሥናቸው መንገድና ብቃት ግን የተለያየ ነበር። በሺህ ዓመቱ መንግሥትም የሚሆነው ይኸው ነው።  ስለሆነም፥ በክርስቶስ ዳግም ምጽእት ወቅት ከእስራኤልም ሆነ ከአሕዛብ የሞቱት ቅዱሳን እንደሚነሡ በመግለጥ መደምደም ይቻላል። ይህ ትንሣኤ የቤተ ክርስቲያን ንጥቀትና መለወጥ ተካፋዮች ያልሆኑትን ሁሉ ያጠቃልላል።  ለ. በሕይወት የሚቆዩ እስራኤላውያን ፍርድ  ክርስቶስ ዳግም ሲመጣ፥ ሕዝቡ የሆኑትን እስራኤላውያን ከአሳዳጆቻቸው ይታደጋል። እስከ ዳግም ምጽአቱ ድረስ ብዙዎች ይገደላሉ (ዘካ. 13፡8)፣ እስከ ምጽአቱ የሚቆዩት ግን በክርስቶስ ነጻ አውጪነት ይድናሉ (ሮሜ 11፡26)። ያም ሆኖ፥ ከጠላቶቻቸው ጥቃት የሚተርፉት እስራኤላውያን ሰሙሉ ወደ መንግሥቱ የመግባት ብቃት እይኖራቸውም። የዚህ ምክንያቱ አንዳንዶቹ በጌታ ያልዳኑ መሆናቸው ነው። በእርሱ ፊት ቀርሰው ይፈረድባቸዋል (ሕዝ. 20፡33-38)። መጀመሪያ እስራኤላውያን ሁሉ ከምድር ዳርቻ ይሰበሰባሉ (ሕዝ. 39:28)። ሕዝቅኤል 20፡35-38 ውስጥ ጌታ የሚከተለውን ተናግሯል፡- “ወደ አሕዛብም ምድረ በዳ አመጣችኋለሁ፤ ከዚያም ፊት ለፊት ከእናንተ ጋር እፋረዳለሁ። የግብፅ ምድረ በዳ ክአሳቶቻችሁ ጋር እንደተፋረድሁ እንዲሁ ከእናንተ ጋር እፋረዳለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። ከበትርም በታች እሳልፋችኋለሁ፥ ወደ ቃል ኪዳንም እሥራት አገባችኋለሁ፤ ከእናንተም ዘንድ ዓመፀኞችንና የበደሉኝን እለያለሁ፤ ካኖሩባትም ምድር አወጣቸዋለሁ፥ ወደ እስራኤል ምድር ግን አይገቡም፤ እኔም እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።”  በዚህ ምንባብ መሠረት፥ ዳግም የሚሰበሰቡት እስራኤላውያን ሁለት ላይ ይከፈላሉ፤ እነዚህም ኢየሱስ ክርስቶስን እንደመሢሐቸውና እዳኛቸው በመቀበል ወደ መንግሥቱ የሚገሱና በዓመፀኛነታቸውና በአለማመናቸው በመቀጠል ከእግዚአብሔር መንግሥት የሚገለሉ ናቸው። ምንም እንኳ እስራኤል በአገር ደረጃ ሞጎስ ቢደረግላትና እግዚአብሔርም ልዩ በረከቶችን ሲያሳያት፥ ግላዊ ድነት የሚመሠረተው ግለሰቡ ከእግዚአብሔር ጋር በሚኖረው ግንኙነትና እምነት ላይ ነው።  ከዚህ ቀደም ለሽመናት እንደሆነው፥ በአሁኑ ጊዜም እንደ “እውነተኛ እስራኤል” የተቆጠሩ (የዳኑ) እና ባለመዳናቸው ምክንያት በስም ብቻ እስራኤሳውያን የሆኑ ቡድኖች አሱ። ጳውሎስ ሮሜ 9፡6 ውስጥ እንደገለጠው፥ “ከእስራኤል የሚወለዱ ሁሉ እስራኤል አይደሉም።” ያልዳኑት የሥጋ ልጆች” እንጂ የእግዚአብሔር ልጆች እንዳልሆኑ ገልጧል (ሮሜ. 9፡8)። ዓመፀኞቹ ሲወገዱ፥ እውነተኛ ድነት ያገኙት እስራኤላውያን ብቻ ወደ ምድሪቱ ገብተው ይወርሷታል። ያልዳኑት ግን ወደ ምድሪቱ አይገቡም (ሕዝ. 20፡38)።  ሐ. በሕይወት የሚኖሩ አሕዛብ ፍርድ  በአሕዛብ ላይ የሚደርሰው ፍርድ በእስራኤል ላይ ከሚፈጸመው በተለየ መንገድ ይስተናገዳል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማቴዎስ 25፡31-46 ውስጥ ይህ ፍርድ ዳግም ምጽአቱን ተከትሎ ወዲያውኑ እንደሚፈጸም ገልጧል። የሚከናወንበትን ሁኔታ ቁጥር 31 ውስጥ ሲገልጥ፥ ምጽአቱ “የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል” ብሏል።  በቀጣዩ ጎብጣ፥ አሕዛብ እንደ በጎችና ፍየሎች በእረኛ ፊት የሚቀርቡ መሆኑ ተመልክቷል። በዓይነታቸው እንደመለያየታቸው፥ ለሁለት ይክፈሉና በጎቹ ንጉሡ በስተቀኝ፥ ፍየሎቹ ደግሞ በስተግራ ይቆማሉ። ከዚያም በጎች ወደ መንግሥቱ እንዲገቡ ንጉሡ ይጋብዛቸዋል። እንዲህም ይላቸዋል፡- “እናንተ የአባቴ ብሩካን፥ ኑ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታሥሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና። ጻድቃንም መልሰው ይሉታል፡- ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ?” (ቁ. 34-37)።  በጎቹ እነዚህን የጽድቅ ተግባራት መቼ እንዳከናወኑ ሲጠይቁት፥ ማቴዎስ 25፡40 ውስጥ ንጉሡ እንዲህ ይመልስላቸዋል፥ “እውነት እላችኋለሁ ከሁሉ ከሚያንሡ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።”  ከዚያም፥ ንጉሡ በስተግራው ወዳሉት ዞር በማለት እንዲህ ይላቸዋል፡- “እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ” (ቁ. 4 )። በጎቹ የሠሯቸውን ዓይነት በጎ ተግባራት እንዳላከናወኑም ይነግራቸዋል። ፍየሎቹም፥ “ጌታ ሆይ፥ ተርበህ ወይስ ታርዘህ ወይስ ታመህ ወይስ ታሥረህ መቼ አይተን አላገለገልንህም? ይሉታል” (ቁ. 44)። ንጉሡም፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሡ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም ብሎ ይመልስላቸዋል” (ቁ. 45)። ከዚያ በኋላ፥ ፍየሉቹ ወደ ዘላለም ቅጣት ሲጣሉ፥ በጎቹ ደግሞ ወደ ዘላለም የሕይወት በረከት ይወሰዳሉ።  ይህ ምንባብ ለበጎ ሥራ አጽንኦት በመስጠቱ አንዳንድ አለመግባባቶች ፈጥሯል። ላይ ላዩን ብቻ ከተመለከትነው በጎቹ፥ በሰናይ ምግባራቸው የዳኑና ፍየሎቹ ግን ሰናይ ምግባር ባለማሳየታቸው ለጥፋት የተዳረጉ ሊመስለን ይችላል። ይሁንና፥ በየትኛውም ሥፍረ-ዘመን ቢሆን ድነት በሰናይ ምግባር እንደማይገኝ መጽሐፍ ቅዱስ ግልጥ አድርጓል። በሰናይ ምግባራት ላይ ከፍተኛ እጽንኦት የሚስጠው የሙሴ ሕግ እንኳ ድነት በሰዎች ሥራ የሚገኝ መሆኑን አይናገርም። ይልቁንም፥ ድነት በሁሉም ሥፍረ-ዘመናት አንድ መሆኑ በሚከተለው አኳኋን ተገልጧል፡- “ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም” (ኤፌ. 2፡8-9)።  ሰው ከኃጢአት ተፈጥሮ ጋር በመወለዱና በእግዚአብሔር ላይ ባመፀው የመጀመሪያ አባቱ ሳቢያ ከያዘው ስፍራ የተነሣ፥ የውርስ ኃጢአት ከድነት እርቆታል። ከዚህም የተነሣ ሰዎች ሁሉ ከሞት ዕዳ ጋር ስለተወለዱ፥ በራሳቸው ምንም ተስፋ የላቸውም። ስለሆነም፥ በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን ሰዎች ሊድኑ የሚችሉት በክርስቶስ መሥዋዕት ብቻ ነው (ሮሜ 3፡25-26)። የሥራ ሕግ የሚያደርሰው ወደ ኩነኔ ሲሆን፥ የእምነት ሕግ ደግሞ ወደ ድነት ያደርሳል (ሮሜ 3፡27-28)። ይህ ሰሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም በሚገባ የተመሠረተ ከሆነ፥ የበጎችና የፍየሎች ፍርድ የሚብራራው እንዴት ነው?  በዚህ ፍርድ ውስጥ የምንመለከተው መርህ ሥራ የድነት መሠረት ሳይሆን፥ ሥራ የመዳናችን ማረጋገጫ መሆኑን ነው። ድነት የሚገኘው በእምነት ብቻ ቢሆንም፥ እምነት ያለ ሥራ የሞተና እውነትነት የሌለው ነው (ያዕ. 2፡26)።  በታላቁ መከራ ዘመን በበጎች የሚከናወኑ መልካም ሥራዎች በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ከሚያልፉ ሰዎች አንጻር እጅግ አስፈላጊና ጠቃሚ ነው። በዚህ ወቅት ዓለም አቀፋዊ ፀረ-ሴማዊነት ሰለሚሰፋፋ፥ ብዙ አይሁዶች ይገደላሉ። በነዚያ ሁኔታዎች፥ ከአይሁዶች ጋር

የእስራኤልና የአሕዛብ ፍርድ Read More »

ትንሣኤዎቹ

This entry is part 47 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ሰዎች ሁሉ በአንድ ጊዚ ይነግሉ ከሚሰው ድጋፍ-አልባ ንድፈ-አሳብ ሳቢያ በትንቢት አተረጓጎም ዙሪያ እያሌ ውዝግብ ሲፈጠር ቆይቷል። ይህ ንድፈ-አሳብ መጽሐፍ ቅዱዕ ሰለተለያዩ ትንሣኤዎች ያስቀመጣቸውን ዝርዝር ጉዳዮች ጎለል ያደርጋል። መጽሐፍ ቅዱስ የሚያቀርብልን ወደ ሰባት የሚደርሱ ትንሣኤዎችን ነው። ከእነዚህም አንዳንዶቹ ከዚህ በፊት የተከናወኑ ሲሆኑ፥ ሌሎቹ ደግሞ በረዥም ክፍለ-ጊዚያት የተራራቁ ናቸው። እነዚህም ከክርስቶስ የሺህ ዓመታት አገዛዝ ቀድመው ወይም ተከትለው የሚፈጸሙ ትንሣኤዎች ናቸው። ሁሉም በየራሳቸው ጊዜና ቦታ እንደሚሠ እና የሰው ዘር ሕልውና ግን ለዘላለም እንደሚቀጥል መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል። የትንሣኤው ትምህርት ጥናት እንደሚያመለክተው፥ ይህን የክርስትና እምነትና ተስፋ ማዕከላዊ እውነት በተመለከተ ትንቢታዊው ፕሮግራም ውስጥ ጠቃሚ መግለጫ አለ።  ሀ. የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ  በትንሣኤዎች ቅደም ተከተል መሠረት፥ ቀዳሚውን ስፍራ የያዘው የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ነው። ያም በብሉይ ኪዳን ትንቢት (እንደ መዝሙር 16፡9-10)፥ ሰአራቱ ወንጌላትና በሥነ-መለኮታዊ ረገድ ደግሞ ከሐዋርያት ሥራ ጀምሮ አዲስ ኪዳን ውስጥ የተብራራ ጉዳይ ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ 1ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ 15 ውስጥ በስፋት እንደሚሟገተው፥ የክርስቶስ ትንሣኤ የክርስቲያን እምነትና ተስፋ ሁሉ የሚያርፍበት ማዕከላዊ ትምህርት ነው። ከአንድ የሚበልጡ ትንሣኤዎች እንዳሉ የሚያረጋግጡትን ሐቆች በምንመለከትበት ጊዜ፥ የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ቀደም ሲል የተፈጻመ ልዩ ክሥተት መሆኑን ሁሉም ሊቀበሉት ይገባል።  ለ. የኢየሩሳሌሙ የቅዱሳን ትንሣኤ  ማቴዎስ 27፡52-53 ውስጥ ያለው ቃል እንደሚያስረዳን፥ ክርስቶስ ከሞት በተነሣ ጊዜ የቅዱሳንም ምሳሌነት ትንሣኤ ተካሂዷል። በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ወቅት የሚከተለው ክሥተት እንደተፈጸሙ ምንባቡ እንዲህ ይጎልጣል፡- “መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ። ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ።”  ይህን እንግዳ ክሥተት በተመለከተ የቀረበ ማብራሪያ የትም አይገኝ። መቃብሮች በክርስቶስ ሞት ጊዜ ቢከፈቱም፥ ክርስቶስ እስከተነሣበት ጊዜ ድረስ ቅዱሳኑ ከሞት ያልተነሡ ይመስላል። ለዚህም ምክንያቱ፥ በኩራት የሆነው ክርስቶስ ለዘላለም በማይጠፋ የትንሣኤ አካል ከሞት በመነሣት የቀዳሚነቱን ስፍራ እንደያዘ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ መናገሩ ነው። በአንጻሩም እንደ አልዓዛር ከሞት የተነሡ ሰዎች እንደገና ሞተው ተቀብረዋል። ክርስቶስ ግን ዳግም ወደ መቃብር ላይመለስ ነው የተነሣ።  በክርስቶስ ትንሣኤ ተነሡትና በአንጻራዊነት አነስተኛ ቁጥር ለነበራቸው ቅዱሳን ትንሣኤ ተስማሚ ፍች ሊሆን የሚችል እሳብ ባለፈው በተፈጸመው የሌዋውያን መሥዋዕት ክንውን ውስጥ የሚገኝ ይመስላል። ሦስተኛው የመከር በኩራት በዓል (ዘሌ. 23፡9-14) ከሚያካትታቸው ነገሮች አንዱ፥ በመከሩ መጀመሪያ እስራኤላውያን የበኩራቱን ነዶ በእግዚአብሔር ፊት የሚወዘውዙበትና፥ ቀጣዩን መከር በመጠበቅ ተስማሚ መሥዋዕት የሚያቀርቡበት ሥርዓት ይገኝበታል። በክርስቶስ ትንሣኤ ወቅት የሆነው የነዚያ ቅዱሳን ትንሣኤ በኩርነት በመወከል፥ ክርስቶስ በትንሣኤው ብቻውን እንዳልሆነና ለሚመጣው ታላቅ መከር የፈር ቀዳጅነቱን ተግባር እንደሚወጣ ያሳያል። እነዚህ ቅዱሳንም የትንሣኤ ምሳሌዎች ነበሩ።  ምንም እንኳን አንዳንድ ሰዎች ማቴዎስ ወንጌል ውስጥ የሚገኙትን ማጣቀሻዎች እንደ አልዓዛር ትንሣኤ ወደ ሕይወት መመለስ ብቻ እድርገው ቢተረጉሟቸው፥ በክርስቶስ ትንሣኤ ወቅት መፈጸሙ ዘላቂ ትንሣኤን የሚያመለክት ነው። ስለሆነም፥ እነዚህ ቅዱሳን ተልእኳቸውን ከፈጸሙ በኋላ ወደ ሰማይ ያረጉ መሆናቸው አያጠራጥርም። ያም ሆነ ይህ+ የእነዚህ ቅዱሳን ትንሣኤ፥ ትንሣኤዎች ሁሉ በአንድ ታላቅ የወደፊት ትንሣኤ እንደማይጠቃለሱ የሚያረጋግጥ ታሪካዊ ክሥተት ነው።  ሐ. የቤተ ክርስቲያን ትንሣኤ  ቀደም ሲል ክርስቶስ ለቅዱሳኑ ሰሰሚመጣበት ሁኔታና ስለመነጠቅ በተነሣው ትምህርት ውስጥ እንደተገለጠው፥ ክርስቶስ የራሱ ለሆኑት ሲመጣ በርሱ የሞቱት ይነሣሉ። ከዚያም በሕይወት ከነበሩትና ከሚለወጡት ክርስቲያኖች ጋር፥ ጌታን በአየር ይቀበሉና ወደ ሰማይ ያርጋሉ። 1ኛ ተሰሎንቄ 4:13-18 እና 1ኛ ቆሮንቶስ 15፡51-58 እንደሚያዕተምሩት፥ ከሞት የተነሡትና በሕይወት የነበሩት ክርስቲያኖች የክርስቶስን የሚመስል ትንሣኤ አካል ይቀበሳሉ (1ኛ ዮሐ. 3፡2)። የቤተ ክርስቲያን ትንሣኤ የመጀመሪያው ብዝሃ ትንሣኤ ሲሆን፥ ለተከታታይ ትንሣኤዎች ግንባር ቀደሙ ነው።  መ. የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ትንሣኤ  ኢዮብ 19፡25-26 ውስጥ እንደተገለጠው፥ ምንም እንኳኝ ብሉይ ኪዳን በተደጋጋሚ ስለ ትንሣኤ ትምህርት ቢያመለክትም፥ ትንቢት ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ አልተሰጠውም። ይሁንና፥ ተጠቅሰው የምናገኛቸው አሳቦች የሚያመለክቱት የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ትንሣኤ የሚፈጸመው፥ በንጥቀት ወቅት ሳይሆን፥ ወደ ምድር በሚመለስበት ዳግም ምጽአቱ ጊዜ መሆኑን ነው።  ዳንኤል፥ ምዕራፍ 12 ቁጥር 1 ውስጥ ታላቁን መከራ ከገለጠ በኋላ፥ ቁጥር 2 ውስጥ ደግሞ ትንሣኤን ያብራራል። ከዚህ ክፍል እንደምንመለከተው፥ ትንሣኤ ከታላቁ መከራ የሚቀጥልና የመጨረሻ ክፍል ሆኖ ቀርቧል። ስለሆነም፥ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን የሚነሡት፥ በመነጠቅ ጊዜ ሳይሆን፥ በመንግሥት ምሥረታ ወቅት ነው። ከመጽሐፈ ኢዮብ ተመሳሳይ አሳብ ለመረዳት እንደሚቻለው፥ ትንሣኤ ክርስቶስ እግሮቹን በምድር ላይ ከሚያሳርፍበት መን ጋር ተያይዟል።  በተመሳሳይ ሁኔታ፥ ሙታን ከመቃብር የሚነቁበት የትንሣኤ ትምህርት ክርስቶስ በዓለም ላይ ሊፈርድ ከሚመጣበት ዘመን ጋር ተዛምዷል (ኢሳ. 26፡19-21)። በተጨማሪም፥ “በክርስቶስ የሞቱት” የሚለው ሐረግ ሰመነጠቅ ጊዚ የሚነሡትን ለመግለጥ እንዳገለገለ መረዳቱ ተገቢ ነው (1ኛ ተሰ. 4፡16)። “በክርስቶስ” የሚለው እገላለጥ ከመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት የተነሣ አማኙ አሁን ያለውን ስፍራ ያመለክታል።  ይህ ገለጣ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው፥ ሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 2 ውስጥ ሲሆን፥ ስለ ብሉይ ኪዳን ቅዱሳን አልጎለጠም። ምንም እንኳ የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች አሳብ ሲለያዩና አንዳንዶቹ መነጠቅ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳንን ይጨምራል ቢሉ፥ አብዛኛው መረጃ የሚያመለክተው ግን፥ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን የሚነሡት በክርስቶስ ዳግም ምጽአት ወቅት መሆኑን ነው። ያም ሆነ ይህ፥ የብሉይም ሆነ የእዲስ ኪዳን ቅዱሳን ከሺህ ዓመቱ መንግሥት በፊት ይነሣሉ።  ሠ. የታላቁ መከራ ወቅት ቅዱሳኝ ትንሣኤ  በታላቁ መከራ ወቅት በሰማዕትነት ስለሞቱ ሰዎች ክርስቶስ መንግሥቱን በምድር ላይ ለመመሥረት ከሚመጣበት ሁኔታ ጋር በተያያዘ መንገድ ልዩ ስሳ ተሰጥቷል። ራእይ 20፡4 ውስጥ ዮሐንስ ስለእነዚህ ወገኖች የሚከተላውን ገልጧል፡- “ስለ ኢየሱስም ምስክርና ስለ እግዚአብሔር ቃል ራሶቻቸው የተቆረጡባቸውን ሰዎች ለአውሬውና ለምስሉም ያልሰገዱትን፥ ምልክቱንም በግንባሮቻቸው በእጆቻቸውም ላይ ያልተቀበሉትን አየሁ፤ ከክርስቶስም ጋር ሺህ ዓመቱኝ ኖሩና ነገሡ”።  በታላቁ መከራ ዘመን በሰማዕትነት የሚሞቱ ቅዱሳን ክርስቶስ መንግሥቱን ለመመሥረት ሰሚመለስበት ጊዜ የሚነሡ ስለመሆናቸው ከላይ የቀረበው ዓረፍተ ነገር ግልጥ መረጃ ነው። ራእይ 20፡5 ውስጥ የተጠቀሰው ቃል፥ “የቀሩቱ ሙታን ግን ሺህ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ በሕይወት አልኖሩም። ይህ የፊተኛው ትንሣኤ ነው” ሲል ያውጃል። ከእርሱ በፊት የክርስቶስ፥ የቤተ ክርስቲያንና የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ትንሣኤዎች ተካሂደው ሳለ፥ ይህ እንዴት የፊተኛው ትንሣኤ ይሆናል? የሚል ተገቢ ጥያቄ ይነሣል።  ለዚህ መልሱ “የፊተኛው ትንሣኤ” የሚለው ሐረግ ምንም እንኳ በጊዜ ርዝመት ቢለያዩ፥ የጻድቃንን ትንሣኤዎች ሁሉ ያመለክታል የሚል ነው። ሁሉም ከኃጢአተኞች የመጨረሻ ትንሣኤ በፊት የሚከናወኑና “ፊተኛ” ናቸው። ስለሆነም፥ «{የፊተኛው ትንሣኤ” የሚለው ሐረግ የክርስቶስን ትንሣኤ ጨምሮ፥ የሁሉንም የቅዱሳን ትንሣኤዎች የሚመለከት ነው።  ረ. የሺህ ዓመቱ ቅዱሳን ትንሣኤ  መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በየትኛውም ስፍራ ስለ ሺህ ዓመቱ ቅዱሳን ትንሣኤ በግልጥ የተቀመጠ እሳብ ባለመኖሩ፥ አንዳንዶች ወደ ሺህ ዓመቱ መንግሥት የሚገቡ ቅዱሳን ከቶውንም እንደማይሞቱ ይናገራሉ። በሺህ ዓመቱ መንግሥት መጨረሻ ላይ ሕይወት የሚኖሩ ሰዎች ስለመነጠቃቸውም መጽሐፍ ቅዱስ የሚገልጠው ነገር የለም። እነዚህ ሁለቱም ትንቢታዊ ነገሮች ዛሬ በሕይወት ለሚኖሩ ቅዱሳን አንገብጋቢ ጉዳዮች አይደሉም። ከዚህ ጋር የሚዛመደው እውነት ክርስቶስ መንግሥቱን ለመመሥረት ከተመለሰ በኋላ ሊገለጥ ይችላል።  ይሁን እንጂ፥ የመከራውን ዘመን የሚያልፉ ቅዱሳኝ ዕድሜያቸው የሚገፋ ከመሆኑም ሌላ፥ በሺህ ዓመቱ አገዛዝ ዘመን ሁሉ በሕይወት የመኖራቸው ነገር አጠራጣሪ ነው። አዳምና ቀደምት ክርስቲያኖች እንኳ ለሺ ዓመት በሕይወት አልኖሩም። ስለሆነም ምንም እንኳ ዕድሜያቸው ሊረዝም ቢችል፥ ሺሁን ዓመት በሙሉ እንደማይኖሩና መሞታቸው እንደማይቀር ይታመናል።  ኢሳይያስ 65፡20 ውስጥ፥ ከዚያ ወዲህ ጥቂት ዘመን ብቻ የሚኖር ሕፃን፥ ወይም ዕድሜውን ያልፈጸመ ሽማግሌ አይገኝም፥ ጎልማሳው መቶ ዓመት ሆኖት ይሞታልና፥ ኃጢአተኛውም የመቶ ዓመት ሆኖት የተረገመ ይሆናልና” የሚል ቃል አለ። በሌላ በኩል፥ ይህ ዓረፍተ ነገር ዕድሜ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚጨምርና እንድ ሰው መቶ ዓመት ሆኖት ገና ሕፃን እንደሚሆን ያመለክታል። ሰሺህ ዓመቱ መንግሥት ዘመን፥ ሰዎች ዕድሜ እስኪጠግቡ ይኖራሉ። ይህ ግን ላለመሞታቸው ዋስትና አይሰጥም። በተቃራኒው በመቶ ዓመት ዕድሜው የሚሞት ሰው የሚሞተው በኃጢአቱ ምክንያት ስለሚሆን ሞት የሚመጣው እንደ ፍርድ ነው። 

ትንሣኤዎቹ Read More »

የክርቶስ ዳግም ምጽአት

This entry is part 46 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ሀ. የዳግም ምጽአቱ ጠቀሜታ  ቀደም ሲል ባሉት የዳግም ምጽእት አስተምህሮ ጥናቶች ንጥቀትን አስመልክቶ ዋና ዋና ነጥቦችን፥ እንዲሁም የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ለቅዱሳኑ፥ በምዕራፍ 12 እና ከቅዱሳኑ ጋር፥ መምጣቱን በምዕራፍ 13 ውስጥ በግልጥ ተመልክተናል። አሁን ደግሞ ክርስቶስ መንግሥቱን ለመመሥረት ከቅዱሳኑ ጋር ዳግም ስለመምጣቱና ይህም ሁኔታ ጎና የሚፈጸም ዋና ትንቢት መሆኑን እንመለከታለን። በመቀጠልም ከዚህ ምዕራፍ ጋር የተያያዙት ምዕራፎች፥ ስለ ትንሣኤ፥ ስለ እግዚአብሔር ፍርድ እና ሰለ ሺህ ዓመቱ አገዛዝ ያስተምራሉ። እነዚህ ታላላቅ ጉዳዮች በአንድ ላይ በመጣመር መጽሐፍ ቅዱስ ስለታሪክ ዓሳማና መጨረሻ የሚያስተምረውን ይገልጣሉ። ይህም ደግሞ ከታሪክ አንጻር መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት መፍታት (መረዳት) እንዳለብን ያስተምረናል።  ኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥቱን በምድር ላይ ለመመሥረት የሚመጣ የመሆኑ ጠቀሜታ ብሉይና አዲስ ኪዳን ውስጥ ብዙ ስፍራ ተገልጿል። በተገለጠው መሠረት ትምህርቱ የሰው ዘር ታሪክ ማብቂያ ብቻ ሳይሆን፥ ይልቁንም የእግዚአብሔር ፕሮግራም ከፍተኛ ክንውን ነው። ይሁን እንጂ፥ የክርስቶስን ዳግም ምጽአት ትምህርት፥ እንዲሁም ክርስቶስ በምድር ላይ ስለሚመሠርተው መንግሥት የሚገልጠውን ሰፊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የማይቀበሉ ወይም የሚያቃልሉ አስተምህሮዎች አሉ። እንዲህ ያሉ አስተምህሮዎች የትንቢቶችን ትርጉምና መጽሐፍ ቅዱሳዊውን መገለጥ ይክዳሉ።  የክርስቶስ መንግሥቱን ለመመሥረት ዳግም መምጣት፥ የእግዚአብሔር ቃል ፍጻሜና የብሉይ ኪዳን ትንቢት ዋና ጉዳይ ነው። እግዚአብሔር ከአብርሃም፥ ከእስራኤል፥ ከዳዊት ጋርና እንዲሁም ለአዲስ ኪዳን የገባቸው ቃል ኪዳናት ከርሱ ፕሮግራም ጋር የተያያዙና ከሁሉ የላቁ ናቸው። መዝሙረ ዳዊት ውስጥ ካሉት መገለሶች ብዙዎቹ፥ እንዲሁም የታላላቆቹና የአናሳዎቹ ነቢያት ትንቢቶች፥ በዚህ ታላቅ ጉዳይ ዙሪያ የተካተቱ ናቸው። እንደ ዳንኤል፥ ዘካርያስ እና ራእይ ያሉ ታላላቅ የትንቢት መጻሕፍት የሚያተኩሩት በክርስቶስ ዳግም ምጽአት፥ እንዲሁም ታሪክና የመንግሥቱን ፍጻሜ በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ነው። በመሆኑም የክርስቶስ ዳግም ምጽእት አስተምህሮ የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚ የሆነን ሰው አጠቃላይ ሥነ-መለኮታዊ አቋም በብዙ መልኩ ይወስነዋል። ገና የሚፈጸሙ ትንቢታዊ ሁኔታዎችን ቅደም ተከተል እንደ እግዚአብሔር ቃል መገለጥ በዝርዝርና በታማኝነት ለማቅረብ የሚደረገውን ሙከራም የሚያረጋግጥ ይሆናል።  ለ. ስለ ዳግም ምጽአት የተነገሩ የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች  የቤተ ክርስቲያን መነጠቅ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ፈጽሞ ያልተጠቀሰና የአዲስ ኪዳን አስተምህሮ ቢሆንም (ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን በዚህ ሁኔታዋ በብሉይ ኪዳን ያልተገለጠች ምሥጢር ነበረች)፥ የዳግም ምጽአት ጉዳይ ግን ብዙዎቹ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ የዳበረ ነበር።  የክርስቶስን ዳግም ምጽአት አስመልክቶ ከተነገሩት ግልጥ ትንቢቶች የመጀመሪያው ዘዳግም 30፡1-3 ውስጥ የተጠቀሰው ሳይሆን አይቀርም። የእስራኤልን ወደ ምድሯ መሰባሰብ አስመልክቶ በተነገረው በዚህ ትንቢት፥ ሕዝቦቿ በመንፈሳዊ ሁኔታቸው ወደ እግዚአብሔር እንደሚመለሱ ተገልጦ፥ “አምላክህ እግዚአብሔርም ምርኮህን ይመልሳል፥ ይራራልህማል፤ አምላክህም እግዚአብሔር አንተን ከበተነበት ከአሕዛብ ሁሉ መካከል መልሶ ይሰበስብሃል” (ቁ.3) ተብሏል። “መልሶ ይሰበስብሃል” የሚለው ገለጣ የሚያመለክተው፥ እግዚአብሔር በሁኔታዎች ጣልቃ የሚገባ መሆኑንና በኋሳ ከተመለከተው ጥቅስ አንጻር ደግሞ ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት ጋር በግልጥ ተገናኝቷል።  ምንም እንኳን መዝሙራት የብሉይ ኪዳንን የአምልኮ መጻሕፍት የሚያካትቱ ቢሆኑ፥ በተደጋጋሚ የሚገልጡት ግን ስለ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ነው። መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 2 ውስጥ እግዚእብሔር ከሕዝቦች ጋር ያደረገውን ክርክር ይገልጣል። የዓለም ገዢዎች እግዚአብሔርንና ሥልጣኑን ያለመቀበል ፍላጎት ቢኖራቸውም፥ የዳዊት ዓላማ ግን ““እኔ ግን ንጉሤን ሾምሁ፥ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ” (መዝ. 2፡6) የሚል ነው። ይህ እግዚአብሔር የሚሾመው ንጉሥ ኃጢአተኞችን የሚያጠፋ መሆኑን ይሄው መጽሐፍ እንዲህ በማለት ይተነብያል፡- “ዕብረት በትር ትጠብቃቸዋለህ፥ እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃም ትቀጠቅጣቸዋለህ” (ቁ.9)።  መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 22፥ 23 እና 24 ውስጥ ክርስቶስ ነፍሱን ስለ በጎቹ እንደሚሰጥ መልካም እረኛ ዮሐ. 10፡11)፥ የራሱ ለሆኑት ሁሌ ለመማለድ እንደሚኖር ታላቅ እረኛ (ዕብ, 13፡20)፥ እና ለታማኞቹ እረኞች ዋጋቸውን ለመስጠት እንደ ክብር ንጉሥ እንደሚመጣ የእረኞች አለቃ (1ኛ ጴጥ. 5፡4) ተጎልጧል። ምዕራፍ 24 የሺህ ዓመቱን መንግሥት ሁኔታ ሲገልጥ፥ “ምድርና ሞላዋ የእግዚአብሔር ናት” (ቁ.1) ይላል። የኢየሩሳሌም በሮች የክብር ንጉሥን ይቀበሉ ዘንድ ይከፈቱ ተብሏል (24፡7-10)።  መዝሙር 50፡2 ውስጥ ክርስቶስ ጽዮን ላይ ሆኖ ዓለምን የሚገዛ መሆኑ ተገልጧል። ስለ ሺህ ዓመቱ መንግሥት በምናጠናበት ጊዜ በኋላ እንደምንመለከተው፥ መንግሥታትን ሁሉ ለመግዛት ወደ ምድር የሚመጣ መሆኑ መዝሙር 72 ውስጥ ተጎልጧል። መዝሙር 89፡36 ደግሞ በዳዊታዊው ቃል ኪዳን መሠረት ከዳግም ምጽአቱ በኋላ የክርስቶስ ዙፋን የሚመሠረት መሆኑን ይገልጣል። መዝሙር 96 የእግዚአብሔርን ሞገስና ክብር ካመለከተ በኋላ፥ ምድርና ሰማይ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይላቸዋል፤ ይመጣልና፤ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣልና፤ እርሱም ዓለምን በጽድቅ እሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል” (ቁ. 13) ይላል።  ክርስቶስ በአሁኑ ጊዜ በአብ ቀኝ መሆኑ መዝሙር 110 ውስጥ ተገልጧል፤ ጠላቶቹን እንደሚገዛና ኃይልና ሥልጣኑም ከጽዮን እንደሚወጣ ተመልክቷል (ቁ. 2 እና 6)። ዳግም የመምጣቱና ምድርን የመግዛቱ እውነት በነዚህ ትንቢቶች ግልጥ ነው። ይህ እውነት የብሉይ ኪዳን ዋና መገለጥ ወይም ራእይ ነው።  ጉዳዩ የዋና ዋናዎቹና አነስተኞቹ ነቢያት መልእክት ዋና ፍሬ እሳብ መሆኑ ተረጋግጧል። በኢሳይያስ 9፡6-7 ታላቅ ትንቢታዊ ገለሳ፥ ክርስቶስ እንደተወለደ ሕፃንና ““ኃያል አምላክ” ተገልጧል። ዳዊት ዙፋን ላይ የሚመሠረተው መንግሥቱ ፍጻሜ የለውም። ኢሳይያስ ምዕራፍ 11-12 ውስጥ ባለው ክፍል ደግሞ ክርስቶስ መንግሥቱን ለመመሥረት ዳግም የመምጣቱ ውጤት ጉልህ ምስል ተስሏል። ይህ ጉዳይ ስለ ሺህ ዓመቱ መንግሥት በምናጠናበት ክፍል ይብራራል። የመንግሥቱ አገዛዝ መቅደም ግን ስለ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት በትክክል በተገለጠውና በኃጢአተኞች ላይ በሚገለጠው መለኮታዊ ኃይል ትምህርት ላይ የሚመሠረት ይሆናል። ክርስቶስ ዳግም ምጽአቱ በምድር ላይ የሚፈርድበት ትክክለኛ ትዕይንትም ኢሳይያስ 3፡1-6 ውስጥ ተገልጧል።  የአሕዛብ ዘመንና እግዚአብሔር ለእስራኤል ያለው ፕሮግራም በተገለጠበት የዳንኤል ትንቢት፥ የሁለቱም ክንውኖች ፍጻሜ ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት ጋር ተዛምዷል (ዳን. 1፡13-14)። ይህ ከፍል የክርስቶስን ዳግም ምጽአት እንዲህ በማለት ይገልጠዋል፡- በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እሆም የሰው ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ፥ በዘመናት ወደሸመገለውም ደረሰ፤ ወደፊቱም አቀረቡት። ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ ይገዙለት ዘንድ ግዛትና ከብር መንግሥትም ተሰጠው፤ ግዛቱም የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው፥ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው”። ዳንኤል የናቡከደናፆርን ሕልም በፈታበት ዳንኤል 2:44 ውስጥም “ዘላለም የማይፈርስ መንግሥት” በማለት ይህንኑ እውነት ተንብዮ ነበር።  ብዙዎቹ አነስተኛ ነቢያትም በተለይ ዘካርያስ፥ ይህን ፍሬ አሳብ በተመሳሳይ ሁኔታ ይጠቅሱታል። ዘካርያስ 2: 10-11 ውስጥ ባለው ክፍል እንዲህ ተብሏል፡- የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እነሆ መጥቼ በመካከልሽ እኖራለሁና ዘምሪ፥ ደስም ይበልሽ ይላል እግዚአብሔር። በዚያን ቀን ብዙ አሕዛብ ወደ እግዚአብሔር ይጠጋሉ፥ ሕዝብም ይሆኑኛል፤ በመካከልም እኖራለሁ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወደ አንቺ እንደ ላከኝ ታውቂያለሽ”። ይህ በትክክል የሚያመለክተው ክርስቶስ በዳግም ምጽአቱ ምድርን ለሺህ ዓመት የሚገዛት መሆኑን ነው። ይህ ጉዳይ ዘካርያስ 8፡3-8 ውስጥ በበለጠ ግልጥነት እንዲህ ተመልክቷል፡- “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ወደ ጽዮን ተመልሻለሁ፤ በኢየሩሳሌምም መካከል እኖራለሁ፤ ኢየሩሳሌምም የእውነት ከተማ ትባላሳች፤ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ተራራ፥ የተቀደሰ ተራራ ይባላል” (ቁ.3)። ከቁጥር 4-8 ባለው ክፍል ዳግም የእስራኤል ልጆች ከዓለም ሁሉ ተመልሰው ኢየሩሳሌም ውስጥ እንደሚኖሩና፥ ልጆቻቸውም በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ እንደሚቦርቁ ይገልጣል።  ዘካርያስ 14:1.4 ውስጥ የተጠቀሰው ቃል የክርስቶስን ዳግም መካከለኛው ምሥራቅንና ኢየሩሳሌምን የሚያጥለቀልቃት የዓለም ጦርነት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርስ እንደሚሆን ያስገነዝባል። ይህንን ዘካርያስ፥ በዚያን ቀን እግሮቹ በኢየሩሳሌም ትይዩ፥ በምሥራቅ በኩል ባለው ሰደብረዘይት ላይ ይቆማሉ፤ ደብረዘይትም በመካከል ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ ይሰነጠቃል፥ እጅግም ታላቅ ሽለቆ ይሆናል፤ የተራራውም እኩሌታ ወደ ሰሜን፥ እኩሌታውም ወደ ደቡብ ይርቃል” (ቁ.4) በማለት ይገልጠዋል።  በክርስቶስ ዳግም ምጽአት ጊዜ የደብረዘይት ተራራ ሁለት ላይ የመሰንጠቁ ጉልህ ገለጣ የሚያመለክተው ከዚያ ቀደም ከተከናወኑ ነገሮች ሁሉ የከርስቶስን ዳግም ምጽአት የሚተካከል አለመኖሩን ነው። የክርስቶስ ዳግም ምጽአት በጰንጠቆስጤ ዕለት፥ ወይም ኢየሩሳሌም ሰፈረሰችበት 70 ዓ.ም. ተከናውኗል የሚለው ትምህርት ከሌሎች መሰል ትንቢቶች ጋር የሚቃረን ነው። የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ወደፊት የሚከናወን መሆኑን የሚያመለክቱ ትንቢቶች (ለምሳሌ ራእይ) ይህን አተረጓጎም ይቃረኑታል፤ በዚህ ምንባብ እንደተመለከተው፥ የደብረዘይት ተራራ ሳይለወጥ መኖሩም አሳቡን

የክርቶስ ዳግም ምጽአት Read More »

ታላቁ መከራ

This entry is part 45 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ሀ. ታላቁ መከራ ከአጠቃላይ መከራ ጋር ሲነጻጸር  የታላቁን መከራ አስተምህሮ በተመለከተ የተለያዩ ግራ መጋባቶች ታይተዋል። የዚህ ምክንያቱ የእግዚአብሔር ሕዝብ የሚያልፍበትን የተለያዩ መከራዎችና ፈተናዎች በታወቀ ጊዜ እንደሚመጡ ብሉይና አዲስ ኪዳናት ውስጥ ከተገለጠው ታላቅ መከራ ለመለየት አለመቻል ነው። መከራ የሚለው አሳብ የሚያመለክተው ጫናን፥ ጉስቁልናን፥ የልብ ስብራትንና ችግር የምንላቸውን ነገሮች ሁሉ ነው። መከራ ስንል በአጠቃላይ ለሰው ዘር እውን ስለሆኑ ችግሮች መናገራችን ነው። ይህ ዓይነት መከራ ከሰው ልጅ ኃጢአትና በእግዚአብሔር ላይ ማመፅ ሳቢያ ይመጣል። በእግዚአብሔርና በሰይጣን መካከል በምድር ከሚከናወን የዓላማ ልዩነት የተነሣ የሚፈጠር ችግርም ነው።  ኢዮብ 5፡7 ውስጥ “የአሞራ ግልገሎች ግን ወደ ላይ እየበረሩ ክፍ እንዲሉ ሰው እንዲሁ ለመከራ ተወልዶአል” ይላል። ክርስቶስም ይህንኑ ዮሐንስ 16፡33 ውስጥ ሰደቀ መዛሙርቱ ሲያረጋግጥ፥ “በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ” ብሏል። ብሉይ ኪዳን ውስጥ ኢዮብ የደረሰበት መከራና አዲስ ኪዳን ውስጥ የተጠቀሰው የጳውሎስ ሥጋ መውጊያ ችግር በሰው ልጆች ላይ ያለማቋረጥ ለሚደርሰው መከራና ጉስቁልና እንደ ምሳሌ የሚወሰዱ ናቸው። ከአዳም ጀምሮ ይህ የሰው ልጆች መታወቂያ ሆኗል። በሺህ ዓመቱ መንግሥት ጊዜ በአያሌው የሚቃለል ቢሆንም፥ የሰው ልጅ ታሪክ እስኪያበቃ ድረስ ይቀጥላል።  መከራና ሥቃይ በጣምራነት ባጠቃላይ የሰው ዘር ላይ ከሚያደርሱት ጉዳት አንጻር፥ በዘመኑ መጨረሻም ችግር የሚኖርበት የተለየ ጊዜ መኖሩን መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል። ይህ የሚሆነው፥ በተለይ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት መዳረሻ በሆነው የአርባ ሁለት ወራት ጊዜ ሰሚኖረው ታላቅ መከራ ነው።  ለ. ስለ ታላቁ መከራ የብሉይ ኪዳን አስተምህሮ  እስራኤል በኋለኛው ዘመኗ መከራ በሚደርስባት ጊዜ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ያለባት ስለመሆኑ ማስጠንቀቂያ የተነገራት ገና መጀመሪያ ዘዳግም 4፡29-30 ውስጥ ነበር። ይህ የተለየ ጊዜ የተነገረው ሰነቢዩ በኤርምያስ ነው። የመከራው ጊዜ የሚጀምረው እስራኤላውያን በከፊል ወደ ምድራቸው ከተመለሱ በኋላ እንደሚሆን ነቢዩ ምዕራፍ 30፡1-10 ውስጥ እንዲህ በማለት ተንብዮአል፡- “እነሆ የሕዝቤኝ የእስራኤልንና የይሁዳን ምርኮ የምመልስበት ዘመን ይመጣልና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ለአባቶቻቸውም ወደሰጠኋት ምድር እመልሳቸዋለሁ፥ እነሱም ይገዟታል” (ቁ.3)።  ወዲያውኑ በመቀጠል ከቁጥር 4-7 ባለው ክፍል እስራኤላውያን ወደ ምድራቸው ከተመለሱ በኋላ በሚኖረው ጊዜ ስለሚደርስባቸው መከራ ተጎልጧል። ያኔ እስራኤል ልጅ እንደምትወልድ ሴት ምጥ ይይዛታል። የመከራው ጊዜ በተለይ ኤርምያስ 30፡7 ውስጥ እንዲህ ተገልጧል፡“ወዮ! ያ ቀን ታላቅ ነውና፥ እርሱንም የሚመስል የለምና፤ ያ የያዕቆብ መከራ ዘመን ነው፥ ነገር ግን ከእርሱ ይድናል”  እስራኤል ምንም እንኳን በዚህ ታላቅ መከራ ውስጥ ብታልፍ፥ እግዚአብሔር በመጨረሻ የባርነት ቀንበሯን እንደሚሰብርና አሕዛብን ከማገልገል ነጻ እንደሚያወጣት ተስፋ ሰጥቷታል። ቁጥር 9 ውስጥ እንደተገለጠው፥ “ለአምላካቸው ለእግዚአብሔርም፥ ለማስነሣላቸው ለንጉሣቸው ለዳዊትም ይገዛሉ እንጂ ሌሉች አሕዛብ እንደገና አይገዟቸውም”። ይህ ትንቢት ዳዊት ከሞት ተነሥቶ በሺህ ዓመቱ መንግሥት ጊዜ ከክርስቶስ ጋር በእስራኤል ላይ የሚነግሥ መሆኑን ያመለክታል። ለዚህ ነው እስራኤል ተስፋ እንዳትቆርጥ “ያዕቆብም ይመለሳል፥ ያርፍማል፥ ተዘልሎም ይቀመጣል፥ ማንም አያስፈራውም” (ቁ.10) የሚል ዋስትና የተሰጣት።  የያዕቆብ መከራ ጊዜ ወይም ታላቁ ፍዳ፥ ዳንኤል 9፡27 ውስጥ የተጠቀሰው ቃል ኪዳን ከፈረሰ በኋላ እንደሚሆን በዚሁ ክፍል ተመልክቷል። ጊዜው የሰባቱ ዓመት አጋማሽ ወይም ሦስት ዓመት ተኩል እንደሚሆን በማያሻማ ሁኔታ ተገልጧል፥ “የሚመጣውም አለቃ” (ዳን. 9፡26)፥ “ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ** (9፡27)፥ ማለት ለሰባት ዓመት ያደርጋል። ይሁን እንጂ ቃል ኪዳኑን በሱባዔው እጋማሽ፥ ማለት ከሦስት ዓመት ተኩል በኋላ ያፈርስና “መሥዋዕቱንና ቁርባኑን ያስቀራል”፥ ቤተ መቅደሱንም ያረክሳል።  ዳንኤል 12:11 ውስጥ እንዲህ ተብሎ ሁኔታው ተብራርቷል፡- “የዘወትሩም መሥዋዕት ከቀረ ጀምሮ፥ የጥፋትም ርኩሰት ከቆመ ጀምሮ ሺህ ሁለት መቶ ዘጠነኛ ቀን ይሆናል”። ይህ ጥቂት ቀናት ተጨምሮበት ሦስት ዓመት ተኩል ይሆናል። ጊዜው የክርስቶስን ዳግም ምጽአትና ከዚያ የሚከተሉትን የመጀመሪያ ፍርዶች የሚያጠቃልል ሳይሆን አይቀርም። ዳንኤል 12፡12 ውስጥ የተገለጠውና ከ1335 ቀናት በኋላ የሚመጣው በረከት ታላቁን የመከራ ጊዜ፥ የክርስቶስን ዳግም ምጽአትና ፍርዶቹን ብቻ ሳይሆን፥ የተባረከውን የክርስቶስ ሺህ ዓመት መንግሥት በምድር መመሥረትን ይጨምራል። በዚሁ መሠረት የታላቁ መከራ ጊዜ አርባ ሁለት ወራት ወይም ሦስት ዓመት ተኩል መሆኑ ታውቋል።  ታላቁ የፍዳ ጊዜ በኢየሱስ ክርስቶስ ምጽአት ወቅት የሚያበቃ መሆኑ በግልጥ ይታወቃል። ዳንኤል 7፡13-14 ውስጥ በተጠቀሰው ትንቢት መሠረት ጊዜው የሰው ልጅ (ክርስቶስ) ከሰማይ የመምጣቱንና መንግሥታትን በሥልጣኑ ሥር የማድረጉን ክንዋኔ ያጠቃልላል። በክርስቶስ ዳግም ምጽአት ዋዜማ ላይ የሚኖረው ክፉ መንግሥትና ንጉሥ ይደመሰሳሉ (ዳን. 7፡26)። ከዚያም መጀመሪያ የሺህ ዓመቱ የክርስቶስ አገዛዝ፥ ለጥቆም በአዲስ ሰማይና አዲስ ምድር የሚመሠረተው ዘላለማዊ የእግዚአብሔር መንግሥት ይመጣሉ። የብሉይ ኪዳን አስተምህሮ በአንጻራዊ መልኩ ያብቃ ቢሆንም፥ ይህን ክንዋኔ በተመለከተ ግን አዲስ ኪዳናዊው ራእይ ሊታከልበት ይችላል።  ዳንኤል 11፡36-39 ውስጥ በተመለከተው ትንቢት መሠረት፥ በመጨረሻው ዘመን የሚኖረው ሃይማኖት የዓለም መሪ ወይም ገዢ ሰሚሆነው ሰውዬ የሚመራና በእግዚአብሔር ሳይሆን፥ በሌሎች አማልክት ላይ የሚመሠረት ይሆናል። እነዚህ ጥቅሶች ውስጥ እንደተመለከተው፥ ይህ መሪ ቀድሞ የነበሩትን አማልክት ሁሉ የማያከብርና እራሱን ከእግዚአብሔር በላይ ከፍ ከፍ የሚያደርግ ነው። የሚያከብረው የአምባዎችን አምላክ ማለት የጦርነት አምላክን ብቻ ይሆናል። ቁሳዊነት እንጂ፥ fእምልኮ መንፈስ ያለበት ሰው አይሆንም። የዚህ ሰው መንግሥት የሚያከትመው፥ ከቁጥር 40-45 ባለው ክፍል እንደተመለከተው፥ እጅግ ታላቅ በሆነ ጦርነት ነው። ከደሱብ፥ ከሰሜንና ከምሥራቅ ሠራዊቶች ይመጡበታል። የሚመጣበትን ሠራዊት ለተወሰነ ጊዜ የሚመክት ቢመስልም፥ ታላቁ ፍዳ እንዲያከትም የሚያደርገው የክርስቶስ ዳግም ምጽአት እስኪሆን ድረስ ጦርነቱ የከፋ ይሆናል።  ሐ. የፍዳው ዘመን በአዲስ ኪዳን አስተምህሮ  ዳግም ምጽአቱና የዓለም ፍጻሜ መቼ እንደሚሆን ክርስቶስ በደቀ መዛሙርቱ በተጠየቀ ጊዜ፥ ለእኛ የሚሆኑ የዘመኑን ምልክቶች ነው አስቀድሞ የነገራቸው። ከነዚህ ብዙዎቹ በክርስቶስ ቀዳሚና ዳግም ምጽአቶች መካከል ባለው ጊዜ መከናወን ያለባቸው እንደመሆናቸው ተፈጽመዋል (ማቴ. 24፡3-14)።  ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱ ስለሚመጡት ምልክቶች በጠየቁት ጊዜ ማቴዎስ 24፡15-29 ውስጥ ሲመልስ የገለጠላቸው ታላቁን መከራ ነው። መከራው የሚጀምረው “በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ” (ቁ.15) ሰዎች ሲመለከቱ፥ እንዲሁም የቤተ መቅደሱን መርከስና ሰሜድትራንያን አካባቢ የሚነሣው መሪ ራሱን በእግዚአብሔር ስፍራ ቤተ መቅደሱ ውስጥ ሲያኖር መሆኑን ከማስጠንቀቅ ጋር ገለጠሳቸው። አንድ ቀን ራሱን የቻለ ክንውን ሆኖ የሚገለጠው ይህ ዕለት በሚከሠትበት ጊዜ፥ ሕይወታቸውን ለማዳን ወደ ተራራዎች እንዲሸሹም የእስራኤልን ልጆች አስጠነቀቃቸው።  ክርስቶስ ይህንኑ ዕለት ማቴዎስ 24፡21-22 ውስጥ ሲገልጠው እንዲህ ብሏል፡- “በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ያልሆነ፥ እንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናል። እነዚያ ቀኖችስ ባያጥሩ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም ነበር፤ ነገር ግን እነዚያ ቀኖች ስለተመረጡት ሰዎች ያጥራሉ። ክርስቶስ ታላቁን የመከራ ጊዜ ከሌሎቹ የመከራ ጊዜያት ሁሉ ጋር በማነጻጸር ነው የሚገልጠው። መከራው፥ ዓለም ከዚያ በፊት የተለማመደቻቸውን ነገሮች ሁሉ እስኪሸፍን ድረስ የገዘፈ ነው።  ይህ መከራ ሳያጥር (ቶሉ ባያበቃ) ኖሮ የሰው ዘር ምድር ላይ ባልተረፈ ነበር። አንዳንድ ሰዎች “ባያጥር” የሚለውን ቃል እንደተገነዘቡት፥ ወቅቱ ከአርባ ሁለት ወራት ያነሰ ጊዜ መሆኑን ይህ አያመለክትም። ቃሉ የሚያስረዳው፥ የመከራው ጊዜ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ምክንያት ሳያጥር ኑሮ፥ ታላቁ መከራ የሰውን ዘር ሁሉ ያጠፋ የነበረ መሆኑን ነው። “ስለተመረጡት” የሚለው ቃል የሚያመለክተው፥ የዳኑ እስራኤላውያንን ወይም የዳኑ አሕዛብን ወይም ሁለቱንም ነው። የክርስቶስ መመለስ ዓላማ በዓለም ለመፍረድ ሲሆን፥ በስሙ ያመኑትን ግን ከክፉ ሁሉ ይሰውራቸዋል።  ጌታችን ስለ መከራው ጊዜ አንዳንድ ባሕርያት ቀጥሎ ባሉት ቁጥሮች ገልጧል። ያኔ ሐሰተኛ ነቢያትና ሐሰተኛ ክርስቶሶች ይነሣሉ (ማቴ. 24፡23-24)። ክርስቶስ በምሥጢር መጥቷል የሚል ሐሰተኛ ወሬም ይኖራል (ቁ. 26)። ለዚህ ነው ያን ጊዜ ማንም እንዳይታለል ደቀ መዛሙርቱን ያስጠነቀቃቸው። ምክንያቱም የክርስቶስ ዳግም ምጽአት፥ መብረቅ ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚታይ ግልጥ ክንውን ይሆናል (ቁ. 27)። የፍዳው ጊዜ ሁኔታም “ፀሐይ ይጨልማል፥ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥ የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ” ተብሎ ቁጥር 29 ውስጥ ተገልጧል። ከዚህ በመቀጠል ነው የክርስቶስ ምጽአት የሚሆነው።  ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱ ስለ

ታላቁ መከራ Read More »

ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት ቀደም ብለው የሚከናወኑ ሁኔታዎች

This entry is part 44 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ሀ. የአሁኑ ዘመን ዓበይት ሁኔታዎች  ባለንበት የጸጋ ዘመን ብዙ ትንቢቶች በመፈጸም ላይ ናቸው። የዘመኑ አጠቃላይ ሁኔታም ማቴዎስ ምዕራፍ 13 ውስጥ በሚገኙ ሰባት ምሳሌዎች ተብራርቷል። እንደ መግቢያ በተቆጠረው የዘሪው ሰው ምሳሌ፥ ሰዎች የእግዚአብሔርን እውነት የሚቀበሉባቸው የተለያዩ ሁኔታዎች ተገልጠዋል። እውነት አንዳንድ ጊዜ ጠጣር መንገድ ዳር ይወድቅና የወፎች ቀለብ ይሆናል። ሌላው እውነት ደግሞ ብዙ አፈር በሌለው ጭንጫ መሬት ላይ ይወድቅና ገና በመብቀል ላይ ሳለ ሥሩን ለመስደድ ባለመቻሉ ይደርቃል። የቀረው በጥሩ መሬት ላይ ሲዘራም፥ በእሾህ ይታነቅና ፍሬ አልባ ይሆናል። ከዘሩ የተወሰነው ክፍል ብቻ መልካም መሬት ላይ ወድቆ መቶ፥ ስድሳ ወይም ሠላሳ ፍሬ ይሰጣል (ማቴ. 13፡1-9፥ 18-23)።  በስንዴ መካከል የተዘራው እንክርዳድ ምሳሌ፥ እስከ መከር ጊዜ ድረስ ሳይፈረድበት የሚቆየውን አደገኛ የውሸት እምነት ያመለክታል (ቁ. 24-30፥ 36-43)። የሰናፍጭ ቅንጣት ምሳሌ በበኩሉ የክርስቲያኑ ማኅበረሰብ በፍጥነት ከትንሽ ወደ ላቀ እንቅስቃሴ የሚደርስ መሆኑን ነው የሚገልጠው (ቁ. 31-32)። የእርሾው ምሳሌ ከመልካሙ ምግብ ጋር ተቀይጦ ሁሉንም ስለሚያበላሸው ክፋት ይናገራል (ቁ. 33-35)። ማቴዎስ 13፡44 ውስጥ የተጠቀሰው የተሰወረው መዝገብ፥ ምናልባት ሰአሁኑ ዘመን በዓለም ዙሪያ የተበተኑትን እስራኤላውያን የሚያመለክትና ሕዝቡ በከርስቶስ ሞት ዳግም የተገኘ መሆኑን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል። እጅግ የተወደደው ዕንቁ (ቁ. 45፥ 46) ምሳሌ ደግሞ፥ ክርስቶስ ስለሞተላት ቤተ ክርስቲያን ያመለክታል። እርሷም በግልጥ የምትታይ ስትሆን፥ እስራኤል ግን እንደ ብሔርነቷ ከዚህ ሁኔታ ስውር ሆና ያለች ትመስላለች። ከሁሉም ዓይነት የሰበሰበችውን መረብ የሚያመለክተው ምሳሌ (ቁ. 47-51)፥ በዘመኑ መጨረሻ የዳኑት ካልዳኑት እንደሚለዩ ያስረዳል።  ሰአጠቃላይ ማቴዎስ ምዕራፍ 13 የሚናገረው፥ በክርስቶስ የመጀመሪያና ሁለተኛ ምጽአቶች መካከል ስለሚገኘው ጊዜ ሲሆን፥ ስለ ንጥቀት ወይም ስለ ቤተ ክርስቲያን ሁኔታዎች አይጠቅስም። ይህ ክፍል የእምነት መግለጫ መጠንንና ተደባልቆ የሚገኘውን መልካምና ክፉ ምስል ይገልጣል።  በፍርድና መለየት እልባት የሚያገኘው የመልካምና ክፉ አብሮ አደግነት፥ የአሁኑ ክፍለ-ጊዜ መለያ ነው። የእግዚአብሔር መንግሥት በወንጌል ስብከትና በሰዎች ጥረት የኋላ ኋላ እንደሚያሸንፍ የሚያስረዳው የድህረ ሺህ ዓመት አመለካከት ከዚህ አሳብ ጋር አይሄድም። በሌላም በኩል እግዚአብሔር እራሱ ዓላማውን ስለሚያከናውን ለተስፋ መቁረጥ ምክንያት የሚሆን መሠረት አይኖርም። አንዳንድ ዘር ከመልካም መሬት ላይ ወድቆ ፍሬ ይሰጣል። እንክርዳዱ ውስጥ ስንዴ፥ በተበላሸ ዓሣ መካከል ደህና ዓሣ ይኖራል። ከበዓለ ኀምሳ ዕለት ጀምሮ የነበሩት ዓመታት ያህንኑ ማቴዎስ 13 ውስጥ የተጠቀሰ ታላቅ ትንቢት ትክክለኛነት አረጋግጠዋል።  ማቴዎስ ምዕራፍ 24 ውስጥም በመጨረሻው ዘመን ላይ በማተኮር ስለ አሁኑ ዘመን የቀረበ ተመሳሳይ ምስል አለ። ከ4-14 በሚገኙት ቁጥሮች ውስጥ የመጨረሻው ዘመን ዘጠኝ ምልክቶች ተሰጥተዋል፡- (1) ሐሰተኛ ክርስቶሶች (ቁ.5)፥ (2) ጦርነቶችና የጦርነት ወሬዎች (ቁ.6)፡(3) ረሃብ (ቁ.7)፥ (4) ቸነፈር(ቁ.7)፥ (5) የምድር መናወጥ (ቁ.7)፥ (6) ሰማዕትነት (ቁ.9-10)፥ (7) ሐሰተኛ ነቢያት (ቁ.11)፥ (8) የዓመፃ ብዛትና ለክርስቶስ ያለ ፍቅር መቀዝቀዝ (ቁ. 12)፥ (9) የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ መሰበክ (ቁ. 14)።  የዚህ ዘመን ሌላ ገጽታ ያልዳኑ ሰዎች ቤተ ክርስቲያን ውዕጥ ሆነው ከእውነተኛ እምነት ውጭ መመላለሳቸው ነው። 2ኛ ጴጥሮስ ምዕራፍ 2 እና 3 የነዚህን ሰዎች ሁኔታ በአራት ይመድባል፡- (1) የክርስቶስን አካልነትና መለኮትነት መካድ (2፡1)፥ (2) ክርስቶስ በመስቀል ላይ በመሞት ያስገኘልንን ሥራ መካድ (2፡1)፥ (3) ከሥነ-ምግባራዊነት የወረደና የዘቀጠ ምግባረ ብልሹነት (2፡2-22)፥ (4) ስለ ክርስቶስ ዳግም ምጽአትና ከርሱ ጋር ከተያያዙ ትምህርቶች መራቅ ናቸው (3፡1-13)። የአዲስ ኪዳን ሌሎች ምንባቦችም ስለ ክህደት የሚሉት አላቸው (1ኛ ጢሞ. 4፡1-3፤ 2ኛ ጢሞ. 3፡1-9፤ ይሁዳ 3-19)። ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቀስ በቀስ ስለሚፈጸመው ክህደት የሚናገሩት እነዚህ ሁሉ ትንቢቶች ከመጀመሪያው ምዕተ ዓመት ጀምሮ እስከአሁን በመፈጸም ላይ ናቸው። ዋነኛው ክህደት የሚካሄደው፥ ቤተ ክርስቲያን ስትነጠቅና ያልዳኑ አማኞች ነን ባዮች ብቻ ሲቀሩ ነው።  እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያኑን ከጠራበት ዓላማ አንጻር፥ የአሁኑ ዘመን የሚያበቃው፥ ድንገት በሚከናወነው መነጠቅ ነው። በየትኛውም የብሉይ ኪዳን ትንቢት ያልተጠቀሰው ይህ ክስተት፥ ቤተ ክርስቲያን በሚያስደንቅ ሁኔታ ከምድር እንደምትነጠቅ ያመለክታል። በክርስቶስ የሞቱት በዚህ ጊዜ የሚው ሲሆን፥ በሕይወት የሚኖሩ ክርስቲያኖች ደግሞ ሞትን ሳይቀምሱ ወደ ሰማይ ይነጠቃሉ (1ኛ ቆሮ. 15፡51-58፤ 1ኛ ተሰ. 4፡13-18)። እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን እንደ ልዩ የቅዱሳን ስብስብ በማድረግ የወጠነውን ዕቅድ ይህ ክንውን ከፍጳሜ ያደርሰዋል። የቤተ ክርስቲያን ከዓለም መወሰድ፥ ክርስቶስ ወደ ምድር ተመልሶ የሺህ ዓመት መንግሥቱን ወደሚመሠርትበት ዘመን የሚያመሩትን ዓበይት ክንውኖች ያስከትላል። በመነጠቅና በዳግም ምጽአቱ መካከል የሚኖሩ ሦስት ዓበይት ክፍለ ጊዜያትን ለማጤን ይቻላል። እነርሱም (1) የዝግጅት፥ (2) የሠላምና (3) የስደት ጊዜያት ናቸው።  ለ. ከመነጠቅ በኋላ የሚኖረው የዝግጅት ጊዜ  የዳኑትን ሁሉ ከምድር የሚያስወጣው የመነጠቅ ክንውን፥ በሰብአዊ ታሪክ ውስጥ እስደናቂ የእግዚአብሔር ጣልቃ ገብነት ይሆናል። ይህ ወደ ዳግም ምጽአቱ ታላቅ ፍጻሜ በፍጥነት የሚገሰግሱትን ተከታታይ ሁኔታዎች የሚጀምር ምልክት ነው። የክርስቲያኖች ሁሉ ከምድር መነጠቅ በዓለም ታሪክ ላይ አጠቃላይ ተጽዕኖ የሚያስከትል መሆኑ ግልጥ ነው። በዚህ ጊዜ በዓለም ላይ ክፋት በከፍተኛ ደረጃ የሚነግሥ ከመሆኑም ባሻገር፥ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የሰይጣን ዓላማ ይከናወናል።  ከመነጠቅ በኋላ የሚመጣው ጊዜ ለሚቀጥሉት ዓበይት ክንውኖች ዝግጅት የሚደረግበት ይሆናል። እነሱም ከሦስት ዓበይት የትንቢት ጉዳዮች፥ ማለትም ከቤተ ክርስቲያን፥ ከእስራኤልና ከአሕዛብ ጋር የሚዛመዱ ናቸው።  1. እምነቷ የይስሙላ የሃና እውነተኛ ያልሆንችው ቤተ ክርስቲያን፥ በመነጠቅ ጊዜ በምድር ላይ ትቀራለች። እውነተኛይቱ ቤተ ክርስቲያን በታላቁ መከራ ውስጥ የማለፍ አለማለፍዋ ጉዳይ በማከራከር ላይ ያለ ነገር ቢሆንም፥ እንደ ክርስቶስ አካልነቷ በመነጠቅ ጊዜ የምትወሰድ ለመሆኑ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኞች ይስማማሉ። በምድር የምትቀረው ያልዳኑ ሰዎች የተከማቹባትና እውነተኛ ያልሆነችው ቤተ ክርስቲያን ስትሆን፥ ክንውኑም ከክርስቲያኑ ኅብረተሰብ ጋር የሚዛመደውን ትንቢት የሚፈጽም ይሆናል።  እውነተኛ ያልሆነችው ቤተ ክርስቲያን ከመነጠቅ በኋላ ራእይ 7 ውስጥ እንደተጠቀሰው በጋለሞታ ተመስላለች። ይህች ጋለሞታ የጊዜው ፖለቲካ መገለጫ በሆነው ቀይ አውሬ ላይ ተቀምጣ ትታያለች። ይህም በብዙ ውኃዎች በተመሰለው የዓለም ሕዝብ ሁሉ ላይ የሚኖራትን የፖለቲካ ሥልጣን ያመለክታል (ራእይ 17፡1፥ 15)። ክዚህ ገልጣ የምንረዳው፥ እውነተኛ ያልሆነችው ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ አማኞች ከተወሰዱ በኋላ ሙሉ በሙሉ በክህደቷ የምትጋለጥ መሆኑን ነው። ከመነጠቅ በኋላ የሚኖረው ክፍለ-ጊዜ በሃይማኖት ረገድ ወደ ዓለም ቤተ ክርስቲያንና እውነተኛ አስተምህሮ ወደራቀው የዓለም ሃይማኖት ግስጋሴ የሚደረግበት ይሆናል።  2. የዝግጅቱ ጊዜ ለእስራኤል የተሐድሶ ወቅት ነው። ሮሜ 11፡25 ውስጥ እንደተገለጠው፥ የኦሁኑ የእስራኤል ድንዛዜ ይወገድና ኢየሱስ ክርስቶስ እውነትም መሢሐቸውና አዳኛቸው መሆኑን ብዙዎች ይረዳሉ። ከመነጠቅ በኋላ በሚኖሩት ቀናት፥ በሺህ የሚቆጠሩ አይሁዶች ክርስቲያኖች ሲነጠቁ የተዉአቸውን መጽሐፍ ቅዱሶችና የክርስቲያናዊ አስተምህሮ መጻሕፍት በማንበብ ወደ ክርስቶስ ሊመለሱ ይችላሉ። መጽሐፍ ቅዱስን ከመሢሑ የመምጣት ተስፋ ጋር የሚያዛምዱትን የራሳቸውን መጻሕፍት ሰመጠቀምም በክርስቶስ ያምናሉ። ድንገት የሚሰወሩት ክርስቲያኖች የት እንደደረሱ ለማወቅ ከፍተኛ ጉጉት እንደሚኖራቸውም አይጠረጠርም። በዚህ ምርምራቸው ሳቢያ ብዙዎች በክርስቶስ ያምናሉ። በመጀመሪያው መቶ ክፍለ-ዘመን እንደነበረችው ቤተ ክርስቲያን፥ አይሁዶች የራሳቸውን ሕዝቦችና አሕዛብን ለክርስቶስ በመማረክ የወንጌሱ አምባሳደሮች ይሆናሉ። የታደሰው የወንጌል ስርጭት በዚህ አኳኋን በዓለም ሁሉ ይሰራጫል። አይሁዶች ቀደም ሲል በዓለም ሁሉ ተበትነው ብዙ ቋንቋዎች ማወቃቸው፥ የተሳካ የወንጌል ስርጭት በማካሄድ ብዙዎችን ወደ ክርስቶስ ለመመለስ እንደሚረዳ አይጠረጠርም። ይሁን እንጂ፥ በመጀመሪያው ምዕተ ዓመት እንደታየው ሁሉም አይሁዶች ወደ ክርስቶስ ስለማይመለሱ ድነትን የሚያገኙት የሚያምኑ ብቻ ናቸው።  3. የአሕዛብን ፖለቲካ በተመለከተ፥ የዝግጅት ጊዜ ጥንታዊው የሮም አገዛዝ ሥርዓት እንዲያንሰራራ ያደርጋል። ቀደም ሲል እንደተገለጠው፥ ዳንኤል ምዕራፍ ሁለት የተገለጡት እግሮችና፥ ዳንኤል 7:7 ውስጥ የተገለጡት የአራተኛው እውሬ የአሥር ቀንዶች ደረጃዎች ገና ከፍጻሜ አልደረሱም። ይህ ትንቢት ራእይ ምዕራፍ 13 ውስጥ ከተጠቀሰው ተጨማሪ አሳብ ጋር እንደሚያሳየው፥ የሮም መንግሥት አሥር አገሮችን የሚያሰባስብ ኮንፌዴሬሽን ፈጥሮ እንደገና የሚያንሰራራ ይመስላል። የእውሮፓ የጋራ ገበያ ምናልባትም ለዚህ እርምጃ ግንባር ቀደም ይሆናል። የፖለቲካዊ ኃይሉ ማዕከል የሚያርፈው ግኝ ከአውሮፓ ይልቅ ሜድትራኒያን አካባሲ ሆኖ፥

ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት ቀደም ብለው የሚከናወኑ ሁኔታዎች Read More »

እስራኤል በታሪክና በትንቢት

This entry is part 43 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ሀ. እስራኤል ከሥፍሩ-ዘመናት ጋር ያላት ግንኙነት  የእስራኤል ታሪክ በዘፍጥረት ምዕራፍ 12 ለአብርሃም በቀረበለት ጥሪ የሚጀምር ሲሆን፥ የብሉይ ኪዳን ዓቢይ አሳብ ነው። አዲስ ኪዳን ወንጌሳትና የሐዋርያት ሥራ ውስጥ፥ ከመጀመሪያው ክፍለ-ዘመን ስለ እስራኤል ተጨማሪ ግንዛቤ ተሰጥቷል። በሌሎች የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥም ስለ እስራኤል የተጠቀሱ ታሪካዊና ትንቢታዊ ነገሮች አሉ።  ከተስፋ ቃሉ ሥፍረ-ዘመን (ምዕራፍ 20ን ይመልከቱ) ጀምሮ፥ እስራኤል የሁሉም ሥፍረ-ዘመናት ተካፋይ ናት። በተስፋ ሥፍረ-ዘመን ከአብርሃም ጋር የተደረገው ቃል ኪዳን እግዚአብሔር በቀጣይ ትውልዶች ከእስራኤል ጋር ላከናወናቸው ተግባራት ሰፊ መሠረት ጥሏል። የሕግ ሥፍረ-ዘመን በዘፍጥረት ምዕራፍ 19 የሚጀምር ዋነኛ የእስራኤል ሕይወት ነው። ይህ ዘመን የብሉይ ኪዳን ዋና ሥፍረ-ዘመን እንደመሆኑ፥ የእስራኤልን ታሪክ እስከ ጌታ ስቅለት ድረስ የሚወስን በመሆን ኖሯል። ከተመዘገበው የእስራኤል ታሪከ አብዛኛው ከሕግ ሥፍረ-ዘመን ጋር ይዛመዳል።  በጸጋ ሥፍረዘመን፥ እስራኤል የጸጋን ዕድሎች ማለት ድነትንና የሕይወትን መመሪያ ከአሕዛብ ጋር ትጋራለች። እስራኤል በወደፊቱ ሥፍረ-ዘመን ተስፋ የተገባላትን ምድር በመያዝና ለኢየሱስ ክርስቶስ ንጉሥነት በመገዛት ዓቢይ ሚና ትጫወታለች። ምንም እንኳ ከአሕዛብ ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ቢሆን፥ እስራኤል ከእብርሃም ጀምሮ እስከ መጨረሻው ባለው የዓለም ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ሚና ትጫወታለች (ለተጨማሪ ማብራሪያ ስፍረ-ዘመናት የሚልውን ርዕስ ይመልከቱ)።  ለ. እስራኤል ከቃል ኪዳኖች አንጻር  መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ኪዳኖች ከተለያዩ ሥፍረ-ዘመናት ጋር በቅርብ የተያያዙ ናቸው። ዘፍጥረት ምዕራፍ 12 ውስጥ ከሚገኘው የአብርሃም ቃል ኪዳን ጀምሮ በእያንዳንዱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ኪዳኖች ውስጥ እስራኤል ዋነኛ ሚና አላት። (ምዕራፍ 21 ውስጥ ፡፡ቃል ኪዳኖቹ” የሚለውን ይመልከቱ።)  በእስራኤል ታሪክና በትንቢት ውስጥ አምስቱ ቃል ኪዳኖች ወሳኝ ናቸው። አስቀድሞ እንደተገለጠው፥ አብርሃማዊው ቃል ኪዳን ለእስራኤል ፕሮግራም መሠረት ነው። በሕግ ሥፍረ-ዘመን የሙሴ ሕግ የእስራኤልን ሕይወት እቅድመ ሁኔታነት የሚወሰን ሲሆን፥ ከዘጸአት 19 ጀምሮ ከጠቅላላው ብሉይ ኪዳን ጋር ይዛመዳል። ከነዓንን ይወርሱ ዘንድ የተሰጠው ቃል ኪዳን ከእስራኤል የመሬት ይዞታ ጋር ይገናኛል። የመሬት ይዞታው ተለዋዋጭ ገጽታ ሲኖረውም፥ የኋላ ኋላ በሺህ ዓመቱ መንግሥት ጊዜ የከነዓን ምድር ለዘለቄታው በእስራኤል ቁጥጥር ሥር ይውሳል። ለዳዊት የተገባለት ቃል ኪዳን እስራኤል ከዳዊት ዙፋን ጋር ያላትን ግንኙነት የሚወሰን ሲሆን፥ ወደፊት በሺህ ዓመቱ ዘመን ክርስቶስ በምድር ላይ እንደሚነግሥና፥ ዳዊትም ከሞት ተነሥቶ በልዑልነት የሚገዛ መሆኑን ያመለክታል። ብሉይ ኪዳን ውስጥ የተተነበየው አዲስ ኪዳን እስራኤል በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ከምታገኘው በረከት ጋር የሚገናኝ ሲሆን፥ በሙሴ በኩል ከተሰጠው ቃል ኪዳን ጋር የሚነጻጸርና የሚተካውም ነው። ቃል ኪዳኖች ከእስራኤል ጋር ያላቸው ዝርዝር ግንኙነት ምዕራፍ 21 ውስጥ ተዘርዝሯል።  ሐ. የእስራኤል ታሪክ በብሉይ ኪዳን  ምንም እንኳ ትክክለኛው የእስራኤል ታሪክ የሚጀምረው እስራኤል ከተባለው ያዕቆብ ሲሆን፥ በአብዛኛው የአብርሃምንና የይስሐቅን ሕይወት ያካትታል። አብርሃምና ይስሐቅ የያዕቆብ አባትና አያት ናቸው። መጀመሪያ በከለዳውያን ዑር ይኖር የነበረው አብርሃም በሰሜን ምዕራብ ወደምትገኘው ካራኝ ሁለት ሺህ ኪሎ ሜትር ያህል ከእሳቱ ጋር ተጉዞ በመሄድ ሀብታም ከብት አርቢ ሊሆን በቅቷል። አባቱ ከሞተ በኋላ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ፥ ከሚስቱ ሣራና ከወንድሙ ልጅ ሎጥ ጋር ወደ ተስፋይቱ ምድር ተጓዘ። ያም ከካራን ወደ ሰሜን ምዕራብ ተጨማሪ የሁለት ሺህ ኪሎ ሜትር መንገድ ነበር። ከዚያም እግዚአብሔር ሰተስፋይቱ ምድር ከአብርሃም ጋር ይሠራ ጀመር።  ታላቅ በሆነው አብርሃማዊ ቃል ኪዳን አማካይነት ታላቅ ሰውና የታላቅ ሕዝብ አባት እንደሚያደርገው፥ እንዲሁም በዘሩ በኩል ዓለሙን ሁሉ እንደሚባርክ እግዚአብሔር ለአብርሃም ቃል ገብቶለታል። ቀደም ሲል አብርሃማዊው ቃል ኪዳን ውስጥ እንደተመለከተው (ምዕራፍ 21)፥ እነዚህ የተስፋ ቃሎች በትክክል ተፈጽመዋል። አብርሃምና ሣራ እጅግ ካረጁና የመውለጃ ዕድሜያቸው ካለፈ በኋላ፥ በተአምራዊ መንገድ ይሰሐቅ ተወለደ። ከዚያም በተወሰነው ጊዜ፥ ይስሐቅና ርብቃ ያዕቆብንና ዔሳውን ወለዱ። ከመንትያ ወንድማማቾች መካከል ታናሹ ያዕቆብ የእስራኤል ሕዝብ መሪ ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር መረጠው።  የአብርሃም፥ የይስሐቅና የያዕቆብ ታሪክ ከዘፍጥረት 12-50 የተዘረዘረ ሲሆን፥ ከዚህ የምንረዳው እግዚአብሔር በዚህ ታሪክ ላይ የሰጠውን ትኩረት ታላቅነት ነው። በተለይም ጠቅላሳው የፍጥረት ታሪክ በሁለት ምዕራፎች (ዘፍጥ. 1-2)፥ ፀኃጢአት የመውደቅ ሁኔታም በአንድ ምዕራፍ (ዘፍጥ. 3) ብቻ ተጠቃሎ እንደቀረበ ስንመለከት፥ የነአብርሃም ታሪክ ዋነኛነት በግልጥ ይታያል። ከመለኮታዊ ዕይታ አንጻር፥ የእስራኤል ታሪክ ለጠቅላላው ታሪክ ቁልፍ ነው።  ዘፍጥረት 15፡13-14 ውስጥ ለአብርሃም ከተሰጠው ትንቢት ጋር በሚስማማ መልኩ፥ በረሃብ ወቅት እስራኤላውያን ወደ ግብፅ ወረዱ። ወደዚያ የሚሄዱበት መንገድ የተጠረገላቸው የአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣን በነበረው ዮሴፍ አማካይነት ነበር። ግብፅ አብርሃምንና ቤተሰቡን በመልካም ሁኔታ ተቀብላ ዮሴፍ በሕይወት በኖረባቸው ጊዜያት ሁሉ ስትንከባከባቸው ቆየች። ይሁን እንጂ፥ የተደረገው የአገዛዝ ለውጥ የድሉት ማዕረጋቸውን ነጥቆ፥ ባሪያዎች ስላደረጋቸው፥ እስራኤሳውያን ላአያሌ መቶ ዓመታት የሥቃይ ሕይወት ኖሩ። በባርነታቸው ወደ ጌታ በጮኹ ጊዜ፥ ጌታ ሕዝቡን ወደ ተስፋይቱ ምድር ይመራቸው ዘንድ ሙሴንና ኢያሱን አስነሣቸው። ምንም እንኳ እስራኤላውያን በቃዴስ በርኔ እግዚአብሔርን ባይታዘዙት (ዘኁ. 14)፥ እና ከዚህም የተነሣ ለአርባ ዓመታት በምድረ በዳ ሲቅበዘበዙ፥ በመጨረሻ ግን እግዚአብሔር ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ምድሪቱን እንዲይዙና ከሙሴ ሞት በኋሳ ዮርዳኖስን ተሻግረው አብዛኛውን ክፍል እንዲቆጣጠሩ አስችሏቸዋል።  እስራኤላውያን ሰኢያሱ ዘመን ወደ ተስፋይቱ ምድር ተመልሰው እንደ አንድ አገር ቢበለጥጉም፥ መጽሐፈ መሳፍንት ውስጥ እንደተመለከተው በሥነ-ምግባራዊ ሕይወታቸው ከእግዚአብሔር ተለይተው ተዋረዱ።  በዚህም ጊዜ እግዚአብሔር ነቢዩ ሳሙኤልን አስነሣ። እርሱም በአብዛኛው የእስራኤልን መንፈሳዊ ሕይወት ዳግም በመገንባት፥ ሰሳኦል፥ በጻዊትና በሰሎሞን ዘመነ መንግሥት ለነበረው ክብር መሠረት ጥሏል። የመጀመሪያው የእስራኤል ንጉሥ የነበረው ሳኦል ባይሳካለትም፥ እርሱን የተካው ዳዊት ታላቅ የጦር ሰው በመሆኑ የተስፋይቱ ምድር አካል የሆኑትን ሰፊ ግዛቶች ላመያዝ ችሏል።  የዳዊት ልጅ ሰሎሞን ለአብርሃም የተነገሩትን አብዛኛዎቹን አካባቢዎች ማለት፥ ከግብፅ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ እስኪቆጣጠር ድረስ ድንበሩን አሰፋ። ሚስቶችን እንዳያበዛና ሰፈረሶች ብርታት እንዳይደገፍ እግዚአብሔር የሰጠውን ትእዛዝ አለመስማቱ (ዘዳግ. 17፡16-17)፥ መንግሥቱ እንዲከፋፈልና ከርሱ በኋላ የእስራኤል ኃይል በፍጥነት እንዲንኮታኮት ምክንያት ሆኗል። የሰሎሞን ልጆች ያደጉት ለእግዚአብሔር ሕግ ግድ ባልነበራቸው አረማውያን ሚስቶቹ ነበር። ከርሱ ሞት በኋላ ብዙም ሳይቆይ፥ እሥሩ የስሜን ነገዶች (እስራኤል) ለብቻቸው ተገንጥሰው በክፉ ነገሥታት ሲመሩ ኖረዋል። እነዚህ ወገኖች በ721 ዓ.ዓ. በአሦራውያን እንዲማረኩ እግዚአብሔር ፈርዶባቸዋል። ሁለቱ የደቡብ መንግሥት ነገዶች (ይሁዳ)፡ምንም እንኳን አንዳንድ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረባቸው ነገሥታት የተነሡላቸው ቢሆንም፥ እንደ እስራኤል ሁሉ በኃጢአት ወጥመድ መያዛቸው አልቀረም። ከዚህም የተነሣ፥ በ605 ዓ.ዓ. በባቢሎናውያን ምርኮ ተወሰዱ።  ኤርምያስ 29፡10 ውስጥ በተሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት፥ ከሰባ ዓመቱ የባቢሎናውያን ምርኮ ፍጻሜ በኋሳ እስራኤል ወደ ምድሯ ተመለሰች። መጽሐፈ ዕዝራ የሕዝቡን መመለስና ቤተ መቅደሱን ለመገንባት ለሀያ ዓመታት ያደረጉትን ጥረት ይገልጣል። ነህምያ ደግሞ ከአንድ መቶ ዓመታት ያህል ጊዜ በኋላ የኢየሩሳሌምን ቅጥሮችና የከተማይቱን ዳግም መታነጽ በመግለጥ ታሪኳን ይቋጫል። ይሁንና፥ እስራኤላውያን ወደ ምድራቸው ቢመለሱም፥ እግዚአብሔርን ባለመከተላቸው ሳቢያ ለ200 ዓመታት ሰሜዶንና በፋርስ አገዛዝ ሥር ቆይተዋል። ታላቁ እስክንድር በ323 ዓ.ዓ. ከሞተ በኋላ ደግሞ ከሦሪያና ከግብፅ ጋር ይዋጉ ጀመር።  በ242 ዓ.ዓ. ኃያሉ የሮማውያን አገዛዝ ሲሲሊን በመውረር የመስፋፋት ዘመቻውን ተያያዘው። ኢየሩሳሌም ራሷ በ63 ዓ.ዓ. ታምፒዬስ በተባለው የሮም ጄኔራል በቅኝ ተያዘችና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አይሁዶችን በባርነት ያጋዙ ሮማውያን ጭካኔ  ማነጣጠሪያ ሆነች። በኋላ በሮማውያን ባለሥልጣናት ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቀለ። በመጨረሻም (በ70 ዓ.ም.) የኢየሩሳሌም ከተማ ተደመሰሰች፥ እስራኤላውያንም አገራቸውን ጥለው በዓለም ሁሉ እንዲበተኑ ተደረገ። እስከ ሀያኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ እሰራኤላውያን ወደ አገራቸው ለደመሰሰና ምድራቸውን እንደ አገር ለማደራጀት አልቻሉም ነበር። በ1948 ዓ.ም. ነው እንደ አንድ ፖለቲካዊ መንግሥት እውቅና ያገኙት።  መ. የእስራኤል ታሪክና የተፈጸመ ትንቢት  የብሉይ ኪዳን ታሪክ በአብዛኛው የታላላቅ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትንቢቶች ፍጻሜ ነው። በመቶዎች የሚቆጠሩ ትንቢቶች ቃል በቃል ተፈጽመዋል። ለአብርሃም በተሰጡት ትንቢቶች መሠረት፥ እስራኤል ታላቅ እገር ሆነች። ብሉይ ኪዳን እስራኤላውያን ከምድራቸው እንደሚወጡ የሚናገሩ ሦስት ትንቢቶችን ያስተላለፈ ሲሆን፥ እነዚህም በሚከተለው መንገድ ተፈጻሚነትን አግኝተዋል፡- (1) ወደ ግብፅ መሄዳቸው፥ ለባርነት መዳረጋቸውና ተለቀው መመለሳቸው፥ (2) በባቢሎናውያኝና አሦራውያን ምርኮ ተወስደው

እስራኤል በታሪክና በትንቢት Read More »