ምዕራፍ 1 – ስለ መዳንህ ምን ያህል እርግጠኛ ነህ

ጸሎት

‹‹አባት ሆይ ቀረቤታህ እንዲሰማኝ እርዳኝ፣ መንፈስህ ለመንፈሴ የሚያደርገውን ምስክርነት እንድለማመድ እርዳኝ፡፡ የአንተ መሆኔን በልቤ ውስጥ አረጋግጥልኝ፡፡ አሜን፡፡››

ለምን ስለ መዳኔ እርግጠኛ መሆን ያስፈልገኛል?

ስለመዳን ወይም አለመዳንህ ጥርጣሬ ካለህ ወይም ትክክለኛ ባልሆኑ ነገሮች መሠረት ላይ መዳንህን ለማረጋገጥ የምትሞክር ከሆነ፣ በክርስትና ሕይወትህ ወጀብ በመጣ ጊዜ፣ በታማኝነትና በእርግጠኝነት ጸንተህ ለመኖር ትቸገራለህ፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን፣ ክርስቶስን ለመቀበል የወሰንከው ውሳኔ ፈጠራ፣ የማይረባና ሃሳባዊ እንደሆነ ለማሳመን የሚጥር ሰይጣን የተባለ ጠላት እንዳለህ መዘንጋት የለብህም፡፡ አንዳንድ ክርስቲያኖች አንዳች ኃጢአት ቢያደርጉ፣ ድነታቸውን (የዘላለም ሕይወታቸውን) እንደሚያጡ በማሰብ የሕይወታቸውን ዘመን በሞላ በፍርሃት ያሳልፋሉ፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ በሕይወታቸው እግዚአብሔር ይቅር ሊለው የማችለው በደል እንዳለ ያስቡና መዳናቸውን በመጠራጠር ኑሯቸውን በፍርሃት ይገፋሉ፡፡ ይህንን ጥናት በምታደርግበት ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ፣ እኛ ክርስቲያኖች ስሜቶቻችን፣ ሁኔታዎቻችን ወይም ዲያብሎስ ከሚነግሩን በተቃራኒው፣ ያለምንም ጥርጥር ለዘላለም እንደዳንን እና ወደ መንግስተ ሰማይ ጉዞ መጀመራችንን እንደሚነግረን ትረዳለህ፡፡

ምን ትጠብቅ ነበር?

ከሰብአዊ ባህሪ ዉጪ መለኮታዊ ስለሆነ ነገር ሲታሰብ፣ በርካታ ሰዎች ማስረጃዎችን ከ ሆሊሁድ መንደር መቃረም ይቀናቸዋል፡፡ በዚህኛው የትወና አለም ያሉ ሰዎች በገሃዱ አለም ካሉቱ በተለየ መንገድ በመድረክ ልዩ ብርሃን እና አስገምጋሚ ድምፅ በመታጀብ ከግርግዳ ጋር ያለጉዳት ተላትመው የሚነሱ መላእክቶች፣ በአንዴ በሁሉ አቅጣጫ ያለችግር የሚመለከቱ እና ተአምራዊ ጉልበት የታጠቁ ሆነው ይቀርባሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች በምናቡ አለም ካሉባቸው ችግሮች ለመላቀቅ በተረከዞቻቸው ወለሉን ሶስት ጊዜ ደቃ፣ ደቃ ማድረግ ብቻ ይበቃቸዋል፤ በዛ ቅፅበት ሁሉም ችግሮቻቸው ይፈታሉ፡፡

ነገር ግን በምንኖርበት ገሃድ አለም፣ ከአፅናፈ አለሙ እውነተኛ አምላክ ጋር ወዳለ እውነተኛ ሕብረት ስንገባ ሕይወት ተውኔታዊ መሆኗ ያከትማል፡፡ ይህ ጉዳይ ለአንዳንዶች አደናጋሪ ነው፡፡ እርግጡን ለመናገር፣ በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው እንደግርግዳ ተላታሚዎቹ መላዕክት አይነት ገጠመኝ የሚለማመዱት፡፡

ስለ እግዚአብሔር ለማወቅና እግዚአብሔር ከሰው ጋር ስለሚያደርገው ግንኙነት ለመረዳት በሆሊውድ ፊልሞች፣ ወይም በባህላችን፣ ወይም በአይነ ህሊናችን ስዕል ላይ መደገፍ ትልቅ ስህተት ነው። ስለ እነዚህ ጉዳዮች ለማወቅ ብቸኛ ምንጫችን ሊሆን ያሚገባው መጽሐፍ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚብሔር፣ ስለ ልጁ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ስለ ድነት፣ ስለ መንግስተ ሰማይና ገሃነመ እሳት፣ እና ስለሌሎች በርካታ ጉዳዬች የመረጃ ምንጫችን ነው፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስን በልብህ የተቀበልክባትን ጊዜ መለስ ብለህ አስብ፡፡ ኢየሱስን ስትቀበል አገኛቸዋለሁ ብለህ በጉጉት ትጠባበቃቸው የነበሩት ነገሮች ይታወሱሃል? ፃፋቸው፡፡ እነዚህ ነገሮች ተሟልተውልሃል?

‹‹ስለ ምንም ነገሮች እርግጠኛ መሆን እችላለሁ?››

ኢየሱስ ክርስቶስን አዳኝህ እንዲሆን በጋበዝከው ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ስለምን ነገሮች እርግጠኛ መሆን እንደምትችል ነገሮሃል? አምስት ቁልፍ ነጥቦችን እንመልከት፡፡

1. ክርስቶስ ወደ ሕይወትህ እንደመጣ እርግጠኛ መሆን ትችላለህ፡፡

‹‹እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፣ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።›› -ራዕይ 3፡20

በጥቅሱ ውስጥ የሰፈረው ‹‹ደጅ›› የሚለው ቃል ምንን የሚወክል ይመስልሃል?

ሰውየው ደጁን ሲከፍትለት ኢየሱስ ምን እንደሚያደረግ ተናገረ?

እንዴት ነው አንድ ሰው ለኢየሱስ ‹‹ደጁን የሚከፍትለት››?

ይህንን ተግባር ፈጽመሃል? ከሆነ፣ መቼ?

‹‹ለተቀበሉት ሁሉ ግን፣ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤›› -ዮሐንስ 1፡12

በዚህ ጥቅስ መሠረት፣ አንድ ሰው የእግዚአብሔር ልጅ ተብሎ ለመጠራት መፈፀም ያለበት ሁለት ነገሮች ምንድን ናቸው?

_____________________________________

_____________________________________

እነዚህን ሁለት ነገሮች አድርገሃል? ካደረግህ፣ መቼ?

2. ‹‹አዲስ ፍጥረት›› ለመሆን ‹‹ዳግም እንደተወለድክ›› እርግጠኛ መሆን ትችላለህ፡፡

‹‹ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፣ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።›› -2ቆሮንቶስ 5፡17

ክርስቲያን መሆን አንድን ክለብ እንደ መቀላቀል ወይም የመድኀን ዋስትናን እንደመግዛት አይደለም፡፡ አዲስ ፍልስፍናን መቀበልም አይደለም፡፡ ክርስቶስን በሕይወትህ ስትቀበል ወደ አዲስ ማንነት ተለውጠሃል፡፡

2 ቆሮንቶስ 5፡17 አንብብ፡፡ ክርስቶስን ወደ ሕይወትህ በመጋበዝህ ምክኒያት፣ ‹‹በክርስቶስ ሆነሀል›› ተብለሃል፡፡ እርሱ በአንተ ውስጥ አለ፣ አንተ ደግሞ በእርሱ ውስጥ! ‹‹በክርስቶስ ያሉ›› ምን እንደሆነላቸው ነው ይህ ጥቅስ የሚናገረው?

የሚከተለውን ጥቅስ አሰላስል፡-

በዮሐንስ 3፡5-6 ላይ ኢየሱስ ‹‹ከውሃና ከመንፈስ ስለመወለድ›› ያወራል፡፡ ‹‹ከውሃ መወለድ›› አካላዊ ልደትን ያመለክታል – በዚህ ምድር ላይ የኖረ ሁሉ ‹‹ከውሃ ተወልዷል››፡፡ ነገር ግን ይህ፣ የእግዚአብሔርን መንግስት ለመውረስ እንደማያበቃ ኢየሱስ ተናግሯል፡፡ የእግዚአብሔር መንግስት በመንፈሳዊው ገፅ/አለም ላይ የምትኖር ስለሆነ እኛም የዚህች ስፍራ ባለአገሮች ለመሆን ከመንፈስ መወለድ አለብን፣ ይህም ልደት ‹‹ዳግም ልደት›› ይባላል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ሕይወትህ በምትጋብዝበት ወቅት በመንፈሳዊው ግዛት ውስጥ ተወልደሃል፡፡ ከዛ በፊት ግን በመንፈስ የሞትክ ገፀ-ሁለት ፍጥረት ነበርክ – አካላዊና አእምሮአዊ፡፡ ነገር ግን የክርስቶስ መንፈስ ወደ ሕይወትህ ሲገባ ሦስተኛውን ሕያው ገጽ ተጎናጸፍክ – ይህም መንፈሳዊ ይባላል! ከረጅም ዘመን መለያየት በኋላ አንተ እና እግዚአብሔር በተመሳሳይ ሞገድ ተገናኛችሁ !

መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹አሮጌው ነገር አልፎአል፣›› ሲል ስለምን እያወራ እንደሆነ ታስባለህ?

ወደ ሕይወት ስለመጡት ስለ ‹‹አዲስ›› ነገሮችህ ምን ትላለህ?

ከመጽሐፍ ቅዱስህ ውስጥ ዮሐንስ 3፡1-10 አውጥተህ አንብብ፡፡ ኒቆዲሞስ ኢየሱስን ከመገናኘቱ በፊት በጣም ሃይማኖተኛ ሰው ነበርን? (በተለይ ቁጥር 1 እና 10 ተመልከት)

ኢየሱስ፣ ኒቆዲሞስ ገና ስለሚያስፈልገው ነገር ነገረው፡፡ ምን ነበር የነገረው? (ቁጥር 3 እና 5 ተመልከት)

ለሎች ተጨማሪ ጥቅሶች፦

‹‹ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፣ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ።›› -1ጴጥሮስ 1፡23

‹‹ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው።›› -1ዮሐንስ 5፡4

3. ያለፈ፣ የአሁንና የሚመጣው ዘመን ኃጢአትህ ሁሉ ይቅር እንደተባለልህ እርግጠኛ መሆን ትችላለህ፡፡

‹‹ነገር ግን በደላችሁ በእናንተና በአምላካችሁ መካከል ለይታለች፣ እንዳይሰማም ኃጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል።›› -ኢሳይያስ 59፡2

‹‹ኃጢአትን የምትሠራ ነፍስ እርስዋ ትሞታለች፤›› ሕዝቅኤል 18፡20

‹‹የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤›› ሮሜ 6፡23

ከላይ በተዘረዘሩት ሦስት ጥቅሶች መሠረት፣ እኛን ከእግዚአብሔር የለየውና በመጨረሻም ወደ ሞት እንድናመራ የሚያደርገን ነገር ምንድን ነው?

ማስታወሻ፡- በደል፣ መተላለፍ እና ኃጢአት አንድ ተመሳሳይ ጉዳይን ያመለክታሉ – ይህም የእግዚአብሔርን ሕግ መጣስ፡፡ የዚህ ደመዎዝ ደግሞ ከእርሱ በመለየት መኖር ነው፡፡

ከዚህ በታች ባሉት ሦስት ጥቅሶች መሠረት፣ ኃጢአቶችህን ለእግዚአብሔር ስትናዘዝና ክርስቶስን የሕይወትህ አዳኝ እንዲሆን ስትጠይቀው፣ ኃጢአቶችህ ምን ሆኑ?

  1. መዝሙር 32፡5 ­­­­­­­­­­­­­­­­­­­­­­­­­______________________
  2. መዝሙር 103፡12 ­­­­­­­­­­­­­­­­­­­­­­­­­___________________
  3. ኢሳይያስ 43፡25 ­­­­­­­­­­­­­­­­­­­­­­­­­______________________

‹‹በኃጢአት በምወድቅበት ጊዜ ምን ላድርግ?››

ኃጢአት ሁል ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር ያለህን ግንኙነት ያሳምማል፣ እንቅፋትም ይሆናል፡፡ ለዚህም ነው እግዚአብሔር ኃጢአትን የሚጠየፈው፡፡ ነገር ግን በኃጢአት ‹‹የአጥፊነት›› ሃሳብ ላይ ከእግዚአብሔር ጋር ስንስማማ (ስንናዘዝ ማለት ነው) እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ይቅር ይላል፣ ያጠራዋል፣ ካስወገደውም በኋላ ፈፅሞ አያስበውም፡፡ ይህም፣ ከእግዚአብሔር ጋር ለሚኖረን ለታደሰና ላልተከለከለ ቀጣይ ሕብረት መንገድ ይጠርጋል፡፡ ‹‹በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።›› -1ዮሐንስ 1፡9

4. በአንተና በእግዚአብሔር መካከል አዲስ ሕብረት መመስረቱን እርግጠኛ መሆን ትችላለህ፡፡

ክርስቶስን ወደ ሕይወትህ ከመጋበዝህ በፊት ከእግዚአብሔር ተለይተህ በመንፈስ የሞትክ፣ የኃጢአት እዳ ያለብህና ‹‹የእግዚአብሔር ጠላት›› ነበርክ (ሮሜ 5፡10)፡፡

ከዚህ በታች ያሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ከተመለከትክ በኃላ አሁን ከእግዚአብሔር ጋር ያለህን ግንኙነት እንዴት እንደሚገልጡት ፃፍ፡፡ በአንድ ክፍል ውስጥ በርካታ ሃሳቦችን ልትይዝ ትችላለህ፡፡

  1. ዮሐንስ 15፡15__________________
  2. ሮሜ 8፡14-17__________________
  3. 1ቆሮንቶስ 6፡17_________________
  4. ኤፌሶን 2፡19___________________

5. ከእንግዲህ ወዲህ ከእግዚአብሔር ዳግሞ ተለይተህ እንደማትጠፋ እርግጠኛ መሆን ትችላለህ፡፡

‹‹ሞት ቢሆን፣ ሕይወትም ቢሆን፣ መላእክትም ቢሆኑ፣ ግዛትም ቢሆን፣ ያለውም ቢሆን፣ የሚመጣውም ቢሆን፣ ኃይላትም ቢሆኑ፣ ከፍታም ቢሆን፣ ዝቅታም ቢሆን፣ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።›› -ሮሜ 8፡38-39

“የዘላለም ሕይወቴ ምን ያህል ከእኔ ጋር ይሰነብት ይሆን?” የሚል ጥያቄ ያሳስብሃል?

‹‹ከእኔ ጋር እንደሚሰነብት አንዳች አልጠራጠርም፣›› ልትል ትችል ይሆናል፡፡ ምክኒያትህ ደግሞ በአሁኑ ሰአት “ነገሮች በጣም በጥሩ ሁኔታ ላይ ስላሉ” የሚል ይሆናል፡፡ ዛሬ ላይ ከእግዚአብሔር ጋር በእርጠኝነት እንደተጣበቅህ ይሰማህ ይሆናል። እርሱንም ደስ ለማሰኘት ፍላጎት አለህ፡፡ የሚከተሉት ጥያቄዎች አሳስበውህ ያውቃሉ፡- ‹‹ከአመት በኃላ ነገሮች እንዳልሆኑ ቢሆኑስ? ሁኔታዎች ወዳልጠበኩት መንገድ ቢነጉዱስ? እግዚአብሔር ደኅንነቴን ዳግመኛ ጥያቄ ውስጥ ያስገባው ይሆን? የሰጠኝን ሕይወት መልሶ ይወስደው ይሆን? በእኔ ተስፋ ይቆርጥ ይሆን? ጌታን ወደ ሕይወቴ ከመጋበዜ በፊት ከእግዚአብሔር ተለይቼ ነበር፣ ይህ ዳግመኛ በሕይወቴ ይፈጸም ይሆን?›› ለነዚህ ጥያቄዎች ጳውሎስ በሮሜ 8፡38-39 ላይ የሰጠውን ምላሽ እንመልከት፡፡

‹‹ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።››

‹‹ከዚህ ነገር በስተቀር›› የሚል ሃረግ በዚህ ጥቅስ ውስጥ ምን ያህል ጊዜ ሰፍሯል? (በመፈለግ ጊዜ አታጥፋ – ፈፅም የለም!) ይህ ምን ያስረዳሃል?

የሚከተሉትን ጥቅሶች በመጽሐፍ ቅዱስህ ውስጥ ካነበብክ በኃላ በግራ የቀረቡትን ጥቅሶች ስለዘላለም ደኅንነትህ እውነታ ከሚያወሩት በስተቀኝ ከቀረቡት ዐረፍተ ነገሮች ጋር መስመር በማስመር አዛምድ፡፡

ዮሐንስ 6፡37                   . ማንም እና ምንም ከእጄ አያወጣህም

ዮሐንስ 10፡27-29         . እግዚአብሔር አይለቅህም ከቶም አይተውህም

ዕብራዊያን 13፡5             . ኢየሱስ ከቶ ወደ ዉጭ አያወጣህም

በሌላ አነጋገር፣ አንድ ጊዜ የእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ ከገባህ በኋላ ለዘላለም እዛው ትኖራለህ!

‹‹ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፣ እድፈትም ለሌለበት፣ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል።›› 1ጴጥሮስ 1፡4-5

  1. ከላይ በሰፈረው በ (1ጴጥሮስ 1፡3-5) ጥቅስ መሠረት፣ የዘላለም ሕይወት ስጦታን ለአንተ ያዘጋጀው ማነው?
  2. ይህ ሃሳብ በድነትህ እርግጠኛ እንድትሆን ያደርግሃል?
  3. በምን አይነት ቅድመ ሁኔታ ነው ይህ ሕይወት የተዘጋጀለህ?
  4. ይህን ሕይወት ለመቀበል በደህና እዚያ እንደምትደርስ ምን እርግጠኛ እንድትሆን ያደርግሃል?
  5. ‹‹ምናልባት››፣ ‹‹ቢሆን››፣ ወይም ‹‹ሁሉ ነገር በመልካም ከሄደ›› የሚሉ ቃላት ወይም ሃረጋት ምን ያህል ጊዜ በጥቅሱ ውስጥ ተገኝተዋል?
  6. ይህ ምን ያስረዳሃል?

‹‹እንደዳንኩ ‹ባይሰማኝስ›››?

እያንዳንዱ ሰው በተለየ መንገድ ‹‹ተበጅቷል››፡፡ አንዳንድ ሰዎች በጣም ስሜታዊ ናቸው፣ ሌሎች ደግሞ ጭምትና ምክኒያታዊያን ናቸው፡፡ አንዳንዶች በአካባቢያቸው ስለምትደረገው ስለ እያንዳንዷ ጥቃቅን ነገር ሳይቀር ንቁዎች ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ ለታላላቅ ፍንዳታዎች ካልሆነ በቀር በዙሪያቸው ላሉ ጥቃቅን ጉዳዮች እምብዛም ናቸው፡፡ እግዚአብሔር አንተን የሰራበት መንገድ ክርስቶስን ወደ ሕይወትህ ለመጋበዝ በምታሳየው ምላሽ ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡

‹‹ክርስቶስ የገዛውን ይህን የዘላለም ሕይወት እግዚአብሔር መልሶ ይወስደው ይሆን? ፈፅሞ! እዳው ተከፍሎ ያበቃ ስለሆነ እግዚአብሔር መልሶ እዳውን ከእኛ ቢጠይቅ እግዚአብሔርን ፍትሃዊ አያደርገውም፡፡ አስቀድሞ እኛን ይኮንን የነበረው የእግዚአብሔር ጽድቅ ዛሬ ደግሞ እኛን ስለማጽደቅ ከጎናችን ነው፡፡ ይህ ምንኛ የደኅንነታችን ዋስትና ነው! ምድራዊ ዳኛ እንኳን ለአንድ ቅጣት ሁለት ጊዜ ዋጋ እንዲከፈልበት አይጠብቅም፡፡›› -ዋችማን ኒ

2ቆሮንቶስ 5፡7 አንብብ፡፡ ይህ ጥቅስ በምን ‹‹እንመላለሳለን›› (ወይንም በአንዳንድ ትርጉሞች ላይ እንዳለው በምን ‹‹እንኖራለን››) ነው የሚለው? በሌላ አነጋገር ሕይወታችንን ለመምራት፣ ትክክል የሆነውን ካልሆነው ለመለየት፣ ልንወስድ ያለው እርምጃ ወይም ውሳኔ ትክክል እንደሆነ ለመለካት በምን ላይ እንደገፍ?

ለምላሹ፣ ከዚህ በታች ከቀረቡት መካከል ምረጥ፡-

  1. በስሜታችን ላይ
  2. በሌሎች ሰዎች ሃሳብ ላይ
  3. ትክክል መስሎ በሚታየን ላይ
  4. በእምነት ላይ
  5. በሙከራ ላይ
  6. በአምክንዮአችን ላይ

ክርስቶስ የሕይወትህ አዳኝ እንዲሆን በፈቀድህ ጊዜ በሕይወትህ እንደተከናወኑ እርግጠኛ ልትሆንባቸው የሚገቡህ የአምስቱ ነጥቦች ማጠቃለያ ከዚህ በታች ቀርቦልሃል፡-

  1. ክርስቶስ ወደ ሕይወትህ እንደመጣ እርግጠኛ መሆን ትችላለህ፡፡
  2. ‹‹አዲስ ፍጥረት›› ለመሆን ‹‹ዳግም እንደተወለድክ›› እርግጠኛ መሆን ትችላለህ፡፡
  3. ያለፈው፣ የአሁኑና የወደፊት ኃጢአትህ ሁሉ ይቅር እንደተባለልህ እርግጠኛ መሆን ትችላለህ፡፡
  4. በአንተና በእግዚአብሔር መካከል አዲስ ሕብረት መመስረቱን እርግጠኛ መሆን ትችላለህ፡፡
  5. ከእንግዲህ ወዲህ ከእግዚአብሔር ዳግም ተለይተህ እንደማትጠፋ እርግኛ መሆን ትችላለህ፡፡

ከሕይወትህ ጋር ማዛመድ፡-

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተማርከውን ቁም ነገር ወደ ሕይወትህ ለማዛመድ ሳታቅድ መጽሐፍ ቅዱስን አታጥና፡፡ ከጥናትህ በኃላ አንድ የሚያዝህን ነገር ማድረግ ይኖርብሃል፡፡

አሁን ምን ያህል እርግጠኛ ነህ?

ዛሬ ምሽት ብትሞት፣ ወደ መንግስተ ሰማይ ሄደህ የዘላለም ሕይወትህን ከእግዚአብሔር ጋር እንደምታሳልፍ ምን ያህል እርግጠኛ ነህ? መልስህን ከዚህ በታች በቀረበው የቁጥር መለኪያ አመልክት፡፡

ፈፅሞ እርግጠኛ አይደለሁም 1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 ፍፁም እርግጠኛ ነኝ

መልስህ ከ ‹10› ያነሰ ከሆነ፣ በዚህ ጉዳይ ላይ ምንድን ነው እንድትጠራጠር ያደረገህ? ምንድን ነው ‹‹ፍፁም እርግጠኛ›› እንዳትሆን ያደረገህ?

የቃል ጥናት ጥቅስ፡-

‹‹እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው። ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።›› -1ዮሐንስ 5፡11-12

ስለ 1ዮሐንስ 5፡11-12:- በጋብቻ ስነስርአቴ ላይ አንድ ወዳጄ ‹‹ይህ ላንተና ለባለቤትህ ነው፣›› በማለት ፖስታ ሰጠኝ፡፡ እርግጥ ነው በድርጊቱ ተናድጃለሁ፡፡ ‹‹ለምንድን ነው ወዳጄ በሰርጌ እለት ርካሽ የሆነ ነገር ለስጦታ የሚያበረክትልኝ?›› ነበር ጥያቄዬ፡፡ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ፖስታዎች በቤቴ ባለ መሳቢያ ውስጥ አሉና በድርጊቱ ተበሳጨሁ፡፡ ኋላ ላይ ፖስታውን ስከፍት የመቶ ዶላር ኖት ሆኖ አገኘሁበት፡፡ በዚሁ ቅፅበት የመቶ ዶላር እዳ የያዘ ቢል እጄ ላይ መድረሱ ደግሞ ጉዳዩን አስገራሚ ያደርገዋል፡፡ ፖስታውን የተቀበለ ገንዘቡን አግኝቷል፡፡ በተመሳሳይ ኢየሱስን በሕይወትህ ስትቀበለው፣ የዘላለምን ሕይወት አብረህ ተቀብለሃል፣ ምክንያቱም የዘላለም ሕይወት በእርሱ ውስጥ ነውና!

ምዕራፍ ሁለትን ያጥኑ

Leave a Reply

%d bloggers like this: