የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት በወንጌላት

ጥያቄ፡- ዘኁል. 23፡19-20 አንብብ። ሀ) እነዚህ ቁጥሮች እግዚአብሔር ስለሚሰጠን ተስፋዎችና ስለ አፈጻጸማቸው ምን ያስተምሩናል? ለ) ሰዎች ቃል ከገቡላችሁ በኋላ እስከተወሰነ ጊዜ ያልፈጻሙላችሁን ተስፋዎች ዘርዝሩ። እዚህ የተገባላችሁ ተስፋዎች በዘግዩ ጊዜ ምን ተሰማችሁ? ) እግዚአብሔር ተስሩ ከሰጣችሁ በኋላ በፍጥነት የፈጸመላችሁን ዘርዝሩ። መ) ገና ወደፊት የሚፈጽምላችሁ ተስፋዎችስ የትኞቹ ናቸው? እግዚአብሔር እነዚህን ተስፋዎች ሳይፈጽምላችሁ ለረጅም ጊዜ የቆየበት ምክንያት ምን ይመስላችኋል? 

አንድ ሰው ተሉ ሊፈጽምልን የገባውን ቃል ሳይፈጽም ቢዘገይ የሚያስከትለውን ተስፋ መቁረጥ ሁላችንም ተለማምደነዋል። አንዳንድ የሚቀርቡን ሰዎች የገቡልንን አንዳንድ ተስፋዎች ፍጹም ሳያሟሉ ሲቀሩ ይህ በልባችን ከፈጠረው ቅሬታ ጋር ዝም ብለን እንኖራለን። በመጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ ሁልጊዜ እንደሚፈጽም ተነግሮናል። እኛ በምንፈልገው ፍጥነት ወይም ባሰብነው መንገድ ባይሆንም እንደሚፈጸሙ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን አለን። 

ባለፈው ሳምንት እግዚአብሔር ለሕዝቡ ለእስራኤል ሁላት ቀና የተስፋ ቃሎችን በነቢያቱ አማካይነት እንደሰጠ ተመልክተናል። የመጀመሪያው አንድ ቀን እንደ ጻዊት ያላ በመንፈስ የተሞላ መሪ በእስራኤል ብቻ ሳይሆን በዓለም ሁሉ ላይ ለመንገሥ ይመጣል የሚል ነበር። ሁለተኛው ደግሞ መንፈሱ በሰዎች ሁሉ ውስጥ የሚኖርበት፥ የእግዚአብሔር ሕግጋት በልባቸው የሚጻፍበት፥ ሰዎች ከእግዚአብሔር ዘንድ እንዳይባዝኑ ከእርሱ የሚማሩበትና እርሱን በመታዘዝ የሚመላለሱበት አዲስ ዘመን በመላው ዓላም እንደሚመጣ እግዚአብሔር ቃል መግባቱ ነው። 

እግዚአብሔር እነዚህን የተስፋ ቃሎች ከሰጠ በኋላ አይሁዶች አስቸጋሪ ጊዜ ገጠማቸው። በመጀመሪያ ወደ ባቢሎን ተማርከው ተወሰዱ። አይሁዶች እንደ አንድ ሕዝብ በዓለም ሁሉ ከተበተኑ በኋላ አንዳንዶቹ ተመልሰው በከነዓን መኖር ጀመሩ። ቢሆንም እንደ አንድ ሕዝብ ሁልጊዜ በማያቋርጥ የአሕዛብ መንግሥታት ተጽእኖ ሥር ወደቁ። በመጀመሪያ ባቢሎን፥ ቀጥሎ ፋርስ፥ ቀጥሎም ግሪክ፥ በመጨረሻም ሮም ተፈራርቀው ገዟቸው። የመጨረሻው የብሉይ ኪዳን ነቢይ ሚልክያስ በ400 ዓ.ዓ. ስለ መሢሑ መምጣት የማጠቃለያ አመልካች ትንቢት እስካመጣበት ጊዜ ድረስ የእግዚአብሔር አፍ ሆነው ለሕዝቡ የሚናገሩ ነቢያት ተመናምነው ነበር። ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያስተላልፍ የነበረው ትንቢታዊ መልእክት ቆመ። ከዚያ ጊዜ ወዲህ ለ400 ዓመታት እግዚአብሔር ቃሉን ለሕዝቡ እንዲናገር የላከው ነቢይ አልነበረም። ይህ ዘመን «400 የፀጥታ ዓመታት» በመባል ይታወቃል። 

ጊዜው እየረዘመ ሲሄድ የእግዚአብሔር ሕዝብ ስለ መሢሑ መምጣት ሁለት የተለያዩ አቋሞችን ያዙ። ብዙዎቹ እግዚአብሔር የሰጠውን የተስፋ ቃል ለመፈጸም አይችልም ብለው ተስፋ ቆረጡ። እግዚአብሔርን የሚያመልኩት ጥልቅ ትርጉም አግኝተውበት ሳይሆን በዘልማድ ብቻ ሆነ። በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር የት ነበር? ስለ መሢሑና ስለ አዲሱ ዘመን የተገቡት ተስፋዎች የሚፈጸሙት መቼ ነበር? ከዚህ በመነሣት እግዚአብሔር ሕዝቡን ትቶታል፥ ከእንግዲህ ወዲህ ለሕዝቡ የሚገደውም አይደለም አሉ። 

ጥያቄ፡- ሀ) እግዚአብሔር ለሕይወትህ የገባው ቃል ተሎ በማይፈጸምበት ጊዜ እንደዚህ ዓይነት ስሜት ተሰምቶህ ያውቃልን? ስለ ሁኔታውና እግዚአብሔር በሁኔታው ውስጥ ስላስተማረህ ነገር አብራራ። ለ የገባልህ ቃል በመጨረሻ እንዴት ተፈጸመ? 

ሌሎች ግን ስለ አዲሱ ዘመንና ስለ መሢሑ መምጣት የነበራቸው ጉጉት በጣም ጽኑ ነበር። ከፖለቲካ ባርነት ነክ የሚወጡባትን ቀን ናፈቁ። ነገር ግን ከመንፈሳዊ ባርነት ነፃ ወጥተው ሙሉ ለሙሉ እግዚአብሔርን መታዘዝ የሚያስችላቸውን የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ላመታጠቅ የጓጉ ጥቂቶች ብቻ ነበሩ። 

ከ400 ዓመታት የፀጥታ ዘመን በኋላ በድንገት የእግዚአብሔር መንፈስ መንቀሳቀስ ጀመረ። መሢሑ የሚነግሥስት የተለሩው ፍጻሜና መንፈስ ቅዱስ ከሰው ልጅ ጋር በሚያደርገው ግንኙነት አዲስ ዘመን የሚያመጣበት ጊዜ ደረሰ። ነገር ግን ይህ የተከናወነው ሰዎች ከጠበቁት በተለየ መንገድ ስለነበረ የመንፈስ ቅዱስን ሥራ ልብ ለማለት አልቻሉም። እንዲያውም የብሉይ ኪዳን ነቢያት የተናገሩለትን መሢሑን ሰቅለው ገደሉት። የእግዚአብሔር መንገዶች ከሰው መንገዶች በጣም የተለዩ ናቸው። ደግሞም የመንፈስ ቅዱስ ሥራ አስቀድመን የምንገምተው አይደለም። 

የመሢሑን ታሪክ በምንመለከትባቸው አራት ወንጌላት የመንፈስ ቅዱስን ሥራ በሁለት ዋና ገጽታዎች እንመለከታለን። በመጀመሪያ መንፈስ ቅዱስ ክመሢሑ ከኢየሱስ ጋር የተቆራኘና በአገልግሎቶቹ ሁሉ ውስጥ ዋና ተሳታፊ ነበር። ሁለተኛው መንፈስ ቅዱስ በኋላ ከሚከናወነው የደቀ 

መዛሙርት ሥራ ጋርም ጥብቅ ቁርኝት ነበረው። መንፈስ ቅዱስ በእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ ውስጥ የሚኖርበትን ዘመን ኢየሱስ ባያስጀምርም እንኳ ይህ ዘመን እርሱ ደቀ መዛሙርትን በምድር ትቶ ወደ ሰማይ ስሚሄድበት ጊዜ እንደሚሆን በአጽንኦት ተናግሮ ነበር። 

ጥያቄ፡- የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብብ። ማቴ. 3፡11፤ 3፡16፤12፡18፤ ማር. 1፡12፤ ሉቃስ 1፡35፤ 4፡14፤ ዮሐ 3፡34፤ 15፡26፤ 20፡22፤ የሐዋ. 1፡2፤ 10፡38፤ ሮሜ 8፡11፤ ዕብ. 9፡14፤ 1ኛ ጴጥ. 3፡18። እነዚህ ጥቅሶች በመንፈስ ቅዱስና በኢየሱስ ክርስቶስ መካከል ስላለው ግንኙነት ምን ያስተምሩናል?

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.