የሕይወት እንጀራ

ትንቢተ ሕዝቅኤል

ሕዝቅኤል 40-48

የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) ከዚህ በፊት የቀመስከውን ወይም ያለፍህበትን አስቸጋሪና ከባድ ሁኔታን ጥቀስ። ለ) በእነዚህ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ስታልፍ በጽናት እንድትቆይ ያደረገህ «ተስፋ» ምን ነበር? ሐ) በከባድ መከራና ችግር ውስጥ እንኳ ክርስቲያን ደስተኛ ሆኖ እንዲጸና ሊያደርገው የሚገባ «ተስፋ» ምንድን ነው? መ) 1ኛ ተሰሎንቄ 14፡13-18፤ ቲቶ 2፡14፤ ዕብራውያን 6፡17-20፤ 1ኛ ዮሐንስ 3፡1-3 አንብብ። የሚያበረታቱንን የተለያዩ «ተስፋዎች» ዘርዝር። ክርስቲያኖች በምንም ዓይነት አስቸጋሪና ከባድ ሁኔታ ውስጥ ብንሆን፥ ምንም ያህል የጨለመና የከፋ ሁኔታ ቢያጋጥመን፥ ምንም ያህል ከፍተኛ ስደት ቢደርስብን፥ ልንበረታታና ልንጽናና የምንችልበት ብርሃን ወይም ተስፋ አለን። ይህ ተስፋ አሁን በመደረግ ላይ ካለው ባሻገር ወደፊት የሚሆነውን ያመለክታል። ይህ ተስፋ የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ተስፋ፥ የዘላለም ሕይወት ተስፋ፥ አንድ ቀን ኢየሱስ ክርስቶስን የምንመስልበት ተስፋ፥ ከሞት እንደምንነሣና ከጌታ ጋር ለዘላለም በመንግሥተ ሰማያት መሆናችንን የሚመለከት ተስፋ ነው። ሌሎች በርካታ የተስፋ ቃሎችም አሉን። እነዚህ የተስፋ ቃሉች «የነፍስ መልሕቆች» ስለሆኑና በታላቅ የመከራ ማዕበል ውስጥ ብንሆንም እንኳ ለእግዚአብሔር በታማኝነት እንድንቆም ስለሚያደርጉን ክርስቲያኖች እነዚህን የተስፋ ቃሎች ሊረዷቸውና ሊያምኑባቸው ይገባል። እግዚአብሔር ለአይሁድ «ተስፋ» ሰጥቷል። የኢየሩሳሌም መደምሰስ፥ በአሕዛብ መካከል መበተን፥ ለአሕዛብ ተገዥ መሆን፥ ሂትለር ፈጽም ሊያጠፋቸው የመቃረቡ ጉዳይና በዘመናት ሁሉ የገጠማቸው ስደት መዘተ. ለአይሁድ ከባድና አስቸጋሪ ቢሆንባቸውም፥ የብርሃን ተስፋ ግን ነበራቸው። ይህም ተስፋ እጅግ አስቸጋሪ በሆኑ ጊዜያት አይሁድን አጽንተ የሚያቆማቸው መልሕቅ ነበር። እነዚህ የተስፋ ቃሎች ምን ነበሩ? ባጭሩ አይሁድ አንድ ቀን ከተበተኑበት ስፍራ ወደገዛ ምድራቸው እንደሚሰበሰቡ ተስፋ ተሰጥቶአቸው ነበር። ሰላምና ብልጥግና ወደሞላባት ወደ ተስፋይቱ ምድር ወደ ከነዓን ይመለሳሉ። ጠላቶቻቸውን ሁሉ ያሸንፋሉ። የዳዊት መንግሥት ክብርም ይመለስላቸዋል። የተከፋፈለው መንግሥት ፈውስ ያገኝና በአንድ ንጉሥ ጥላ ሥር አንድ መንግሥት ይሆናል። ይህ ንጉሥ መሢሑ ነው። መሢሑ በኢየሩሳሌም የሚነግሥ ሲሆን፥ የዓለም መንግሥታትና አሕዛብ ሁሉ ይታዘዙለታል። አይሁድ፥ ራሱ በደነገገላቸው መንገድ እግዚአብሔርን የማምለክ ነፃነት ይኖራቸዋል። አይሁድ እነዚህን የተስፋ ቃሎች በአእምሮአቸው በመያዝ፥ ለብዙ ዘመናት በፍትሕ አልበኝነት እነርሱን ለማጥፋት የተደረጉትን ሙከራዎች ሁሉ ተቋቊመዋል። የእስራኤል ሕዝብ ሕልውና እስከ ዛሬ ድረስ ሊቆይ የቻለው አይሁድ በእነዚህ የተስፋ ቃሎች ባለማቋረጥ በማመናቸው ነበር። ሕዝቅኤል 40-48 እግዚአብሔር ለአይሁድ ያለውን ዕቅድ የሚያጠቃልልበት የመጨረሻው ዘመን መግለጫ ነው። ሕዝቅኤል በነበረበትና በሌሎችም ዘመናት ሁሉ በምርኮ ላይ ለነበሩ አይሁድ ተስፋ በመስጠት፥ እግዚአብሔር እንዳልረሳቸው ነገር ግን አንድ ቀን ከእነርሱ ጋር እንደሚሠራ የሚያረጋግጥ ነበር። እነዚህን ምዕራፎች በሚመለከት በክርስቲያኖች በርካታ የአመለካከት ልዩነት አለ። አንዳንዶች አዲስ ኪዳን ኢየሱስ በአይሁድና በአሕዛብ መካከል የነበረውን የልዩነት ግድግዳ እንዳፈረሰ ስለሚያስተምር እነዚህ ምዕራፎች ልክ እዚህ ስፍራ በተገለጸበት መልኩ የሚፈጽሙበት መንገድ የለም ብለው ያምናሉ (ኤፌሶን 2፡14)። ኢየሱስ በመስቀል ላይ የከፈለው መሥዋዕትነት የጥንቱን የመሥዋዕት ሥርዓት አስወግዶአል (ዕብራውያን 10፡11-18)። አሁን እግዚአብሔር በሰዎች ልብ ውስጥ ያደረ ስለሆነ ቊሳዊ የሆነ የሚታይ ቤተ መቅደስ አያስፈልግም (1ኛ ቆሮንቶስ 3፡16)። ሌሎች ክርስቲያኖች ደግሞ እነዚህ የተስፋ ቃሎች በከፍተኛ ደረጃ በቀጥታ መፈጸም አለባቸው በማለት አጥብቀው ይከራከራሉ። አይሁድ የሚመለሱበት አገር ሊኖራቸው ይገባል። መሢሑ ኢየሱስ ክርስቶስ በመካከላቸው ሊኖርና ሊገዛቸው ይገባል። የብሉይ ኪዳንን የአምልኮ ሥርዓት የሚከተል አንድ ዓይነት የአምልኮ አፈጻጸም ሊኖር ያስፈልጋል። እነዚህ መሥዋዕት ስለ ኃጢአት የሚቀርቡ ከመሆን ይልቅ የኢየሱስን ሞት የሚያስታውሱ ተምሳሌታዊ ተግባራት ይሆናሉ። እነዚህን ምዕራፎች በቀጥታ ካልተረዳናቸውና ካልተቀበልናቸው ትርጒማቸውን በምን እናውቃለን? የሚሉ ናቸው። እነዚህ ለአይሁድ የተሰጡ የተስፋ ቃሎች ወዲያውኑ ለእነርሱ ትርጒም የማይሰጡ ሆነው በመንፈሳዊ አንጻር በቤተ ክርስቲያን ብቻ የሚውሉ ከሆነ አይሁድ እግዚአብሔርን ተስፋ በማድረግ የሚያምኑት እንዴት ነው? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ መጨረሻው ዘመን ከተሰጡት ሌሎች የተስፋ ቃሎች ጋር ይህ ክፍል ያለው ግንኙነት ምንድን ነው? ሁሉም ተምሳሌታዊ ናቸውን? እነዚህን ምዕራፎች የሚመለከት ትርጕም ለማዘጋጀት መጀመር ማለት የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃሎች የምንረዳበትና በመተማመን የምንናገርበት ጽኑ መሠረት የለንም ማለት ነው። የውይይት ጥያቄ፥ ሕዝቅኤል 40-48 አንብብ። ሀ) ስለ ወደፊቱ ቤተ መቅደስ የሰጡትን የተስፋ ቃላት ግለጽ? ለ) የእግዚአብሔር ክብር ምን ይሆናል? ሐ) በእዚህ ምዕራፎች የተጠቀሰው ልዑል ማን ነው? ) የከነዓን ምድር ምን ትሆናለች ሠ) በዚያን ጊዜ የሚቀርቡ መሥዕዋቶች ምን ዓይነት ይሆናሉ?  1. አዲሱ ቤተ መቅደስ (ሕዝቅኤል 40-42) በእነዚህ ሦስት ምዕራፎች ቤተ መቅደስ ምን እንደሚመስል ዝርዝር መግለጫዎች ተሰጥተዋል። ምሁራንና የሕንጻ ባለሙያዎች (አርክቴክቶች) ቤተ መቅደስ ምን እንደሚመስል ለማበጀት ቢሞክሩም፥ የተሰጠው የወርድና የስፋት መጠን ዝርዝር በቂ ስላይደለ አልተቻለም። ሆኖም ግን በተሰጠው መረጃ ብቻ ቤተ መቅደሱ ከሰሎሞን ቤተ መቅደስ እንኳ እንደሚበልጥ እናውቃለን። የሰሎሞን ቤተ መቅደስ ከጥንቱ ዘመን ሰባት ታላላቅ ሕንጻዎች አንዱ እንደነበር የሚታወስ ነው። እንደዚህ ዓይነት ቤተ መቅደስ ተሠርቶ ስለማይታወቅ ይህ ቤተ መቅደስ በኢየሱስ ክርስቶስ 1000 ዓመት መንግሥት ጊዜ የሚሠራው እንደሆነ ብዙ ምሁራን ያምናሉ። ሕዝቅኤል ስለ ቤተ መቅደሱ ገለጣ የሚሰጠው ከውጭው ግድግዳ ጀምሮ ነው። የምሥራቁ መግቢያ ወደ ቤተ መቅደሱ ውጫዊ ክፍልና ወደ ሌሎች የቤተ መቅደስ መውጫዎች የሚመራ ነው። ሕዝቅኤል በውጫዊው የቤተ መቅደስ ክፍል ስላሉትና ካህናት ስለሚጠቀሙባቸው ክፍሎች ይገልጣል። የቤተ መቅደሱን እውነተኛ ቅርጽም ጭምር ይገልጣል።  2. የጌታ ክብር ወደ ቤተ መቅደሱ ይመለሳል (ሕዝቅኤል 43፡1-12)  ሕዝቅኤል ቤተ መቅደሱን በሚመለከትበት ጊዜ አስደናቂ ነገር አየ። የጌታ የክብር ደመና ወደ ቤተ መቅደሱ ሲመለስና በመገናኛው ድንኳንና በቤተ መቅደሱ እንደነበረው ዓይነት ሲሞላው ተመለከተ። እንደሚታወሰው ከዚህ በፊት ሕዝቅኤል የእግዚአብሔር ክብር ቤተ መቅደሱንና የኢየሩሳሌምን ከተማ ትቶ ሲሄድ ስለተመለከተ ይህ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው (ሕዝቅኤል 10-11)። እግዚአብሔር ወደ ሕዝቡ ወደ እስራኤልና ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ እንደገና ይመለሳል። እግዚአብሔር እንደገና ከሕዝቡ ጋር ይኖራል።  3. በቤተ መቅደሱ ውስጥ የነበረው መሠዊያ (ሕዝቅኤል 43፡13-27)  4. የእስራኤል የወደፊት መሪዎች (ሕዝቅኤል 44) ትዝ እንደሚልህ፥ ሕዝቅኤልና ሌሎች የትንቢት መጻሕፍት ለኢየሩሳሌም መደምሰስና ለእግዚአብሔር ሕዝብ መማረክ በዋናነት ጥፋተኞች ያደረጉት መሪዎችን እንደነበሩ የሚታወስ ነው። ነገሥታት፥ ካህናትና ነቢያት በሙሉ ብልሹዎች ስለነበሩ ሕዝቡን ከእግዚአብሔር አራቁአቸው (ለምሳሌ፡- ሕዝቅኤል 34)። ሕዝቅኤል ተገቢ የሆኑ የፖለቲካና መንፈሳዊ መሪዎች የሚነሡበትን ጊዜ አሻግሮ ተመለከተ። ትኲረቱ በሁለት ዓይነት መሪዎች ላይ ነበር። የመጀመሪያው፥ የፖለቲካ መሪ «አለቃ» ተብሏል። ሕዝቅኤል መሢሑን በሚመለከተው በዚህ ትንቢት ላይ ብዙም አላተኰረም። ሁለተኛ፥ የሃይማኖታዊ መሪዎች የሆኑት ካህናትና ሌዋውያን ነበሩ። ሕዝቅኤል ራሱ ካህን ነበር። ስለዚህ ለሙሴና ለአሮን በተሰጡት ትንቢቶች ፍጻሜ መሠረት ትኵረቱን እውነተኛ መንፈሳዊ መሪዎች በሚኖሩባቸው ቀናት ላይ አድርጎአል። እነዚህ መሪዎች የሚኖሩት ሕግን በመጠበቅና በመፈጸም ስለሚሆን ሕዝቡን ወደ እውነተኛ አምልኮ ይመራሉ።  5. የእስራኤል ምድር መከፋፈል (ሕዝቅኤል 45-48) ሕዝቅኤል ወደፊት ምድሪቱ ስለምትከፋፈልበት ሁኔታ በዝርዝር ይገልጣል። የአለቃው ንብረት ባለበት በምድሪቱ ማዕከላዊ ስፍራ ቤተ መቅደሱ ይሠራል። በዚያ ሰፊ ምድር ለካህናትና ለሌዋውያን ስፍራ ይሰጣቸዋል። የቀረው የከነዓን ምድር ለአሥራ ሁለቱ ነገዶች በእኩልነት ይከፋፈላል።  ሕዝቅኤል ስለሚቀርቡት የተለያዩ መሥዋዕቶችም ይገልጻል። የብሉይ ኪዳን ዋና ዋና መሥዋዕቶች በዚህ ክፍል አለመጠቀሳቸውን መገንዘብ ጠቃሚ ነው። አንዳንድ የተቀደሱ ቀናት በተለይ ከሁሉ የሚበልጠው ቤተ መቅደሱ የሚነጻበት የማስተስርያ ቀን እንኳ አልተጠቀሰም፡፡ የአይሁድ ምሁራን ይህ ለምን እንደሆነ አያውቁም። ብዙ ክርስቲያኖች እነዚህ ለውጦች በመሢሑ ዘመን ሰዎች ሁሉ በጌታ ስለሚዋጁ ለኃጢአት የሚቀርቡ መሥዋዕቶችና የቤተ መቅደሱ መንጻት የማያስፈለግ መሆኑን የሚያንጸባርቁ ናቸው ይላሉ። እንዲሁም ሕዝቅኤል ከቤተ መቅደሱ ስለሚፈስስ ወንዝ ይገልጻል። ወደ ሙት ባሕር በመፍሰስ ሕይወትን ይሰጠዋል። በወንዙም ሳር ላይ ዓመቱን ሙሉ ፍሬ የሚያፈሩና ለሕዝብ ፈውስና መብል የሚሰጡ ዛፎች ይኖራሉ። (በራእይ 22 ያለውን ተመሳሳይ ወንዝ ተመልከት።) በኢየሩሳሌም ወንዝ ፈጽሞ አልነበረም። ውኃ የእግዚአብሔር በረከት ምልክት ተደርጎ ይቆጠር ነበር። ምናልባት ይህ የእግዚአብሔር መንፈሳዊና ሥጋዊ በረከት ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ለሕዝቡ ሁሉ እንደሚደርስ የሚያሳይ ምልክት ይሆናል። ሕዝቅኤል ትንቢቱን የሚደመድመው ለኢየሩሳሌም አዲስ ስም በመስጠት ነው። የከተማይቱ ስም «ያህዌ ማህ» ወይም

ሕዝቅኤል 40-48 Read More »

ሕዝቅኤል 33-39

የውይይት ጥያቄ፣ እግዚአብሔር ያለፈውንና አሁን ያለውን እንደሚያውቅ ሁሉ፥ የወደፊቱንም ነገር እንደሚያውቅና እንደሚቆጣጠር መረዳት አበራታች የሚሆነው ለምንድን ነው? እንደ እኛ በጊዜ ለማይወሰነው እግዚአብሔር፥ የወደፊቱ ሁኔታ የአሁኑን ያህል ግልጽ ነው። እግዚአብሔር ቀድም የሆነውንና አሁን በመፈጸም ላይ ያለውን ብቻ ሳይሆን፥ ወደ ፊት ምን እንደሚሆንም በትክክል ያውቃል። በሕዝቅኤል 33-48 ስለ ወደፊት የተነገሩ በርካታ ትንቢቶችን እናገኛለን። አንዳንዶቹ ለእስራኤል ሕዝብ እንደማስጠንቀቂያ ነበር የተሰጡት። ሌሎች ደግሞ በምርኮ የነበሩትን አይሁድ ለማበረታታት ነበር። እዚህ ምዕራፎች በቀጥታ እኛን የሚመለከቱ ትንቢቶችን የያዙ ባይሆኑም እንኳ እግዚአብሔር ነገሮችን ሁሉ እንዲሁም ወደ ፊት የሚፈጸሙ ሁኔታዎችን ሳይቀር እንደሚቆጣጠር በማወቅ እንድንበረታታ የተሰጡ ናቸው። እግዚአብሔር የማይቆጣጠረው አንዳችም ነገር አይደርስብንም። ዓላማውን ለመፈጸም ነገሮችን ሁሉ ይጠቀምባቸዋል። እነዚህ ምዕራፎች ስለ መጨረሻዎቹ የሚናገሩ በርካታ ትንቢቶችን ስለያዙ፥ ምሁራን ትርጕማቸውን በሚመለከት ብዙ ጊዜ ይወዛገባሉ። አንድ ሰው በትንቢተ ሕዝቅኤል መጨረሻ የሚገኙትን ትንቢቶች የሚረዳው እግዚአብሔር ስለመጨረሻው ዘመን ያለውን ዓላማና በእርሱም ውስጥ እስራኤል ያላትን ስፍራ መረዳት በሚችልበት መንገድ ነው። የውይይት ጥያቄ፥ ሕዝቅኤል 33-39 አንብብ። ሀ) ሕዝቅኤል በጠባቂነቱ በነበረበት ኃላፊነት እግዚአብሔር ምን ማስጠንቀቂያ ሰጠው? ለ) ሕዝቅኤል በምርኮ የነበሩትን አይሁድን ለማበረታታት የፈለገባቸውን መንገዶች ዝርዝር። ሐ) እነዚህ ጥቅሶችስ ለኢየሩሳሌም ውድቀት የሚሰጧቸው ምክንያቶች ምንድን ናቸው? መ) ሕዝቅኤል ያየው ራእይና ትርጕም ምንድን ነው? ሠ) የጎግና ማጎግ ሕዝቦች ምን ያደርጋሉ? 1. ሕዝቅኤል፥ የእስራኤል ጉበኛ ወይም ጠባቂ (ሕዝቅኤል 33፡1-20) ሕዝቅኤል የነቢይነት ሥራውን በጀመረ ጊዜ፥ እግዚአብሔር በባቢሎናውያን አማካይነት ሊመጣ ስላለው አደጋና ስለ እነርሱ ንስሐ የመግባት አስፈላጊነት በመንገር፥ የሚያስጠነቅቅቅ ጉበኛ ወይም ጠባቂ መሆን እንደሚገባው አስጠንቅቆት ነበር። በሕዝቅኤል 33 በጉበኛነቱ ያለበትን ኃላፊነት በመንገር እንደገና ያስጠነቅቀዋል። ሕዝቡ ንስሐ እንዲገቡ ማስገደድ የሕዝቅኤል ኃላፊነት አልነበረም። ሕዝቅኤል ቢያስጠነቅቃቸውና እነርሱ ከክፋታቸው አንመለስም ቢሉ፥ ጥፋቱ መስማት እንቢ ያሉት የሕዝቡ እንጂ የሕዝቅኤል አልነበረም። ሕዝቅኤል ግን ዝም ቢልና ሕዝቡን ስለ ኃጢአታቸው ሳያስጠነቅቅ እንዲሁም ንስሐ እንዲገቡ ባያበረታታ፥ እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን በኃላፊነት ይጠይቀዋል። የእግዚአብሔር ፍላጎት ኃጢአተኛው እንዲሞት ሳይሆን፥ ንስሐ እንዲገባና እንዲድን ነው። የውይይት ጥያቄ፥ ሕዝቅኤል በጉበኛነት የነበረበት ኃላፊነት ዛሪም እኛ ላላመኑ ሰዎች ወንጌልን ለማድረስ ካለን ኃላፊነት ጋር የሚመሳሰለው እንዴት ነው?  2. የኢየሩሳሌምን ውድቀት የሚመለከት ገለጻ (ሕዝቅኤል 33፡21-33) ከተማይቱ በወደቀች ጊዜ ከሞት ያመለጠ አንድ ሰው ወደ ሕዝቅኤል መጣና ኢየሩሳሌም እንደወደቀች ነገረው። በዚያን ጊዜ ሕዝቅኤል መልእክቱን በግልጽ ለሕዝብ መናገር ይጀምር ዘንድ እግዚአብሔር ፈቀደለት። ሕዝቅኤል የተናገራቸው ትንቢቶች በሙሉ ስለተፈጸሙ እውነተኛ የእግዚአብሔር ነቢይ መሆኑ ታወቀ። ከዚህ በኋላ የሕዝቅኤል መልእክት ከፍርድ ወደ ማጽናናት ተቀየረ። በኢየሩሳሌም የነበሩ ሰዎች ከውድቀት በኋላ ንስሐ ያልገቡ ይመስላሉ። አንድ ብቸኛ ሰው የነበረው አብርሃም ታላቅ ሕዝብ ከሆነ፥ ከአንድ በላይ የሆንን እኛ ሕዝቡንና መንግሥታችንን እንደገና ለመመሥረት እንችላለን ብለው ነበር። እግዚአብሔር ይባርካቸው ዘንድ ከኃጢአታቸው ንስሐ መግባት እንደነበረባቸው አሁንም አልተገነዘቡም ነበር። እንዲሁም ሕዝቅኤል መልእክቱን መስማት ይፈልጉ የነበሩትንና ልባቸውን ያልለወጡትን ምርኮኞች ገሥጾአል። በአፋቸው እግዚአብሔርን እንከተላለን ቢሉም፥ በልባቸው ግን ኃጢአት ነበር፤ ቃላቸውም በተግባር አይተረጉምም ነበር። የውይይት ጥያቄ፥ ዛሬም በቤተ ክርስቲያን የሰዎች ቃልና ተግባር በአንድ ላይ አብሮ አይሄዱም፤ እንዲህ ዓይነቱ ተመሳሳይ ችግር የሚከሠተው እንዴት ነው? መግለፃዎችን ስጥ።  3. የእረኛውና የበጎች ምሳሌ (ሕዝቅኤል 34) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችንና የሕዝቡን ግንኙነት ለመግለጽ ካገለገሉ ማነጻጸሪያዎች እጅግ የተለመደው የእረኛና የበጎች ምሳሌ ነው። ይህ ምዕራፍ መሪዎቹ ኃላፊነታቸውን ካልተገነዘቡና መልካም እረኛ ካልሆኑ የሚመጣባቸውን ፍርድ የሚገልጽ ስለሆነ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በጥንቃቄ ሊያነብቡት የሚገባ እጅግ ጠቃሚ ክፍል ነው። የእስራኤል መሪዎች የእግዚአብሔር መንጋ የሆኑት የእስራኤላውያን እረኞች ነበሩ። እነዚህ መሪዎች ግን ለመንጋው እንክብካቤ ከማድረግ ይልቅ የራሳቸውን የስግብግብነት ዓላማ ያራምዱ ነበር። ለራሳቸው ሕይወት ቁሳዊ ጥቅማ ጥቅሞችን በማሳደድ፥ ለሕዝቡ ተገቢውን እንክብካቤ አያደርጉም ነበር። ስለዚህ የመንጋው ጠላቶች መንጋውን እንዲያጠፉ በር ከፍተው ነበር። በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር ፈረደባቸውና በባቢሎን ምርኮ የአመራር ስፍራቸውን አሳጣቸው። ዳሩ ግን እግዚአብሔር አንድ ቀን ለመንጋው ሰላምና ደኅንነት በሚያመጣ መንገድ፥ የእግዚአብሔርን መንጋ የሚመራ፥ እንደ ዳዊት ያለ አንድ መሪ እንደሚያስነሣ ተስፋ ሰጥቶ ነበር፤ ያም እረኛ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው (ዮሐንስ 10 ተመልከት)። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) በጥንቷ እስራኤል የነበረው የእረኞች ችግር ዛሬ በመጥፎ መሪዎቻቸው ምክንያት ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን ከሚያጋጥሟቸው ችግሮች ጋር የሚመሳሰለው እንዴት ነው? ለ) መልካም እረኛ የሆነውን ኢየሱስን ከቤተ ክርስቲያን መሪዎች ጋር አወዳድር። የእግዚአብሔር መንጋ የሆኑትን የቤተ ክርስቲያን አባሎች በመምራት ረገድ ያላቸው ተመሳሳይነት እንዴት ነው?  4. በኤዶም ላይ የተነገረ ትንቢት (ሕዝቅኤል 35) ኤዶም የእስራኤልንና የይሁዳን ምድር ለመውሰድ በመፈለግ እስራኤልን በማጥፋት ድርጊት ስለተባበረች እግዚአብሔር እንደሚያጠፋት ለሁለተኛ ጊዜ ተናገረ።  5. ስለ እስራኤል ተራሮች የተነገረ ትንቢት (ሕዝቅኤል 36) የእስራኤል ተራሮች እግዚአብሔር ለአይሁድ ሊሰጣቸው ቃል የገባላቸውን የተስፋይቱን ምድር የሚወክሉ ናቸው። ሌሎች መንግሥታትና ሕዝቦች በኢየሩሳሌም ውድቀትና ጥፋት ተደስተው ነበር። አብዛኛው ሕዝብ በምርኮ ተወስዶ ስለነበር በእስራኤል አብዛኛዎቹ አይሁድ ይኖሩባቸው የነበሩት ተራራማ ስፍራዎች ሰው የማይኖርባቸው ሆነው ነበር። እግዚአብሔር ግን አንድ ቀን አይሁድ ከምርኮ እንደሚመለሱና እነዚህ ተራራማ ስፍራዎች በሰዎች የተሞሉ ፍሬያማ እንደሚሆኑ ተናገረ። እንዲያውም ምድሪቱ ከፊት ይልቅ እጅግ በተሻለ ደረጃ ላይ እንደምትሆን ተስፋ ሰጠ። አይሁድ በኃጢአት ድርጊታቸው በራሳቸው ላይ ባመጡት ጥፋት የእግዚአብሔርን ስም ያሰደቡ ቢሆኑም እንኳ እግዚአብሔር አንድ ቀን ቅዱስ መሆኑን በመግለጽ ራሱን ለእስራኤል እንደሚያሳይ ተስፋ ሰጠ። ከተበተኑበት ስፍራ ሁሉ እንደገና እንደሚሰበስባቸው ተናገረ። ከኃጢአታቸውና ከክፉ መንገዳቸው ሁሉ እንደሚያነጻቸውና ሕጉን በልባቸው ላይ በመጻፍ ለእርሱ በፍጹምነት እንዲታዘዙ እንደሚያደርግ ቃል ገባላቸው። እነዚህ የተስፋ ቃሎች አይሁድ በዘሩባቤል፥ በዕዝራና በነህምያ መሪነት በተመለሱ ጊዜ በከፊል የተፈጸሙ ቢሆኑም፥ ሙሉ በሙሉ የሚፈጸሙት ግን አይሁድ በሙሉ ወደ ተስፋይቱ ምድር ተመልሰው፥ በኢየሱስ ክርስቶስ መሪነትና በበረከቱ በሚጥለቀለቁበት በመጨረሻው ዘመን ይመስላል። የውይይት ጥያቄ፣ ሀ) ከእነዚህ የተስፋ ቃሉች አንዳንዶቹ ዛሬ በክርስቲያኖች ወይም በመንግሥተ ሰማያት የሚፈጸሙት እንዴት ነው?) ከእነዚህ የተስፋ ቃሎች አብዛኛዎቹ ለክርስቲያኖች ቃል በቃል ሳይሆን ለአይሁድ ብቻ መፈጸም ያለባቸው የሚመስሉት እንዴት ነው?  6. የደረቁ አጥንቶች የሞሉበት ሸለቆ ራእይ (ሕዝቅኤል 37) በትንቢተ ሕዝቅኤል ውስጥ በሚገባ ከታወቁት ክፍሎች አንዱ የደረቁ አጥንቶች ስለሞሉበት ሸለቆ የተሰጠው ራእይ የሚገኝበት ክፍል ነው። አጥንቶቹ ሕያዋን ፍጥረታት ሆነው ሊቆሙ በሚችሉበት አኳኋን እግዚአብሔር ሠራ። እነዚህ የደረቁ አጥንቶች ከእስራኤልና ከይሁዳ የሆኑትን አይሁድ የሚወክሉ ነበሩ (ሕዝቅኤል 37፡11)። በምርኮ ላይ ለነበሩ አይሁድ ምንም ተስፋ የሌለና የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝቦችም የሞተ ያህል በመሰሉበት ጊዜ፥ አንድ ቀን እግዚአብሔር የሕይወትን እስትንፋስ እንደሚዘራባቸውና ወደ ከነዓን እንደሚመልሳቸው ቃል ገባላቸው። እንዲሁም እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን፡- አንዱ እስራኤል ሌላው ይሁዳ ተብሎ የሚጠራ ሁለት በትር እንዲወስድና አንድ ላይ እንዲያስራቸው ነገረው። ይህም አንድ ቀን የተከፋፈሉት የእስራኤልና የይሁዳ መንግሥታት አንድ እንደሚሆኑ የሚያመለክት ነበር። በዚያን ጊዜ በእስራኤል ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር አገልጋይ ተብሎ የሚጠራው መሢሑ-ዳዊት ይነግሣል። እግዚአብሔር ዘላለማዊ ቃል ኪዳንን ከእነርሱ ጋር በመመሥረት በመካከላቸው ለዘላለም ይኖራል። እነዚህ ትንቢቶች ደግሞ የተፈጸሙት በከፊል ነበር። ከሰባ ዓመታት ምርኮ በኋላ ከአይሁድ አንዳንዶቹ ወደ ምድራቸው የተመለሱ ቢሆንም ድሮ የነበራቸውን ክብር ግን አላገኙም። በ70 ዓ.ም. ደግሞ አይሁድ እንደገና ተበተኑ። ከዚያ በኋላ ወደገዛ ምድራቸው መመለስ የጀመሩት በ1948 ዓ.ም. ነበር። አብዛኛዎቹ አይሁድ ግን እስካሁን ድረስ በአሕዛብ መካከል ተበትነው ይኖራሉ። ስለዚህ መሢሑ ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ቀን አንድ ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ አይሁድን በመሰብሰብ በላያቸው ይነግሣል። እነዚህ የተስፋ ቃሎች ሙሉ በሙሉ የሚፈጸሙት ያኔ ብቻ ነው። 7. በጎግ ላይ የተነገረ ትንቢት (ሕዝቅኤል 38-39) ሕዝቅኤል ስለ መጪው ጊዜ ከተናገራቸው ትንቢቶች መካከል አስደሳች ያልሆኑም ነበሩባቸው። ነቢዩ ከእስራኤል በስተሰሜን እጅግ ርቆ ስለሚገኘው ስለ ጎግ ምድር በተናገረው ትንቢት ውስጥ ወደገዛ ምድራቸው እንደገና በተሰበሰቡ አይሁድ ላይ ጎግ ጦርነት እንደሚከፍት ይገልጣል።

ሕዝቅኤል 33-39 Read More »

ሕዝቅኤል 33-39

የውይይት ጥያቄ፣ እግዚአብሔር ያለፈውንና አሁን ያለውን እንደሚያውቅ ሁሉ፥ የወደፊቱንም ነገር እንደሚያውቅና እንደሚቆጣጠር መረዳት አበራታች የሚሆነው ለምንድን ነው? እንደ እኛ በጊዜ ለማይወሰነው እግዚአብሔር፥ የወደፊቱ ሁኔታ የአሁኑን ያህል ግልጽ ነው። እግዚአብሔር ቀድም የሆነውንና አሁን በመፈጸም ላይ ያለውን ብቻ ሳይሆን፥ ወደ ፊት ምን እንደሚሆንም በትክክል ያውቃል። በሕዝቅኤል 33-48 ስለ ወደፊት የተነገሩ በርካታ ትንቢቶችን እናገኛለን። አንዳንዶቹ ለእስራኤል ሕዝብ እንደማስጠንቀቂያ ነበር የተሰጡት። ሌሎች ደግሞ በምርኮ የነበሩትን አይሁድ ለማበረታታት ነበር። እዚህ ምዕራፎች በቀጥታ እኛን የሚመለከቱ ትንቢቶችን የያዙ ባይሆኑም እንኳ እግዚአብሔር ነገሮችን ሁሉ እንዲሁም ወደ ፊት የሚፈጸሙ ሁኔታዎችን ሳይቀር እንደሚቆጣጠር በማወቅ እንድንበረታታ የተሰጡ ናቸው። እግዚአብሔር የማይቆጣጠረው አንዳችም ነገር አይደርስብንም። ዓላማውን ለመፈጸም ነገሮችን ሁሉ ይጠቀምባቸዋል። እነዚህ ምዕራፎች ስለ መጨረሻዎቹ የሚናገሩ በርካታ ትንቢቶችን ስለያዙ፥ ምሁራን ትርጕማቸውን በሚመለከት ብዙ ጊዜ ይወዛገባሉ። አንድ ሰው በትንቢተ ሕዝቅኤል መጨረሻ የሚገኙትን ትንቢቶች የሚረዳው እግዚአብሔር ስለመጨረሻው ዘመን ያለውን ዓላማና በእርሱም ውስጥ እስራኤል ያላትን ስፍራ መረዳት በሚችልበት መንገድ ነው። የውይይት ጥያቄ፥ ሕዝቅኤል 33-39 አንብብ። ሀ) ሕዝቅኤል በጠባቂነቱ በነበረበት ኃላፊነት እግዚአብሔር ምን ማስጠንቀቂያ ሰጠው? ለ) ሕዝቅኤል በምርኮ የነበሩትን አይሁድን ለማበረታታት የፈለገባቸውን መንገዶች ዝርዝር። ሐ) እነዚህ ጥቅሶችስ ለኢየሩሳሌም ውድቀት የሚሰጧቸው ምክንያቶች ምንድን ናቸው? መ) ሕዝቅኤል ያየው ራእይና ትርጕም ምንድን ነው? ሠ) የጎግና ማጎግ ሕዝቦች ምን ያደርጋሉ? 1. ሕዝቅኤል፥ የእስራኤል ጉበኛ ወይም ጠባቂ (ሕዝቅኤል 33፡1-20) ሕዝቅኤል የነቢይነት ሥራውን በጀመረ ጊዜ፥ እግዚአብሔር በባቢሎናውያን አማካይነት ሊመጣ ስላለው አደጋና ስለ እነርሱ ንስሐ የመግባት አስፈላጊነት በመንገር፥ የሚያስጠነቅቅቅ ጉበኛ ወይም ጠባቂ መሆን እንደሚገባው አስጠንቅቆት ነበር። በሕዝቅኤል 33 በጉበኛነቱ ያለበትን ኃላፊነት በመንገር እንደገና ያስጠነቅቀዋል። ሕዝቡ ንስሐ እንዲገቡ ማስገደድ የሕዝቅኤል ኃላፊነት አልነበረም። ሕዝቅኤል ቢያስጠነቅቃቸውና እነርሱ ከክፋታቸው አንመለስም ቢሉ፥ ጥፋቱ መስማት እንቢ ያሉት የሕዝቡ እንጂ የሕዝቅኤል አልነበረም። ሕዝቅኤል ግን ዝም ቢልና ሕዝቡን ስለ ኃጢአታቸው ሳያስጠነቅቅ እንዲሁም ንስሐ እንዲገቡ ባያበረታታ፥ እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን በኃላፊነት ይጠይቀዋል። የእግዚአብሔር ፍላጎት ኃጢአተኛው እንዲሞት ሳይሆን፥ ንስሐ እንዲገባና እንዲድን ነው። የውይይት ጥያቄ፥ ሕዝቅኤል በጉበኛነት የነበረበት ኃላፊነት ዛሪም እኛ ላላመኑ ሰዎች ወንጌልን ለማድረስ ካለን ኃላፊነት ጋር የሚመሳሰለው እንዴት ነው?  2. የኢየሩሳሌምን ውድቀት የሚመለከት ገለጻ (ሕዝቅኤል 33፡21-33) ከተማይቱ በወደቀች ጊዜ ከሞት ያመለጠ አንድ ሰው ወደ ሕዝቅኤል መጣና ኢየሩሳሌም እንደወደቀች ነገረው። በዚያን ጊዜ ሕዝቅኤል መልእክቱን በግልጽ ለሕዝብ መናገር ይጀምር ዘንድ እግዚአብሔር ፈቀደለት። ሕዝቅኤል የተናገራቸው ትንቢቶች በሙሉ ስለተፈጸሙ እውነተኛ የእግዚአብሔር ነቢይ መሆኑ ታወቀ። ከዚህ በኋላ የሕዝቅኤል መልእክት ከፍርድ ወደ ማጽናናት ተቀየረ። በኢየሩሳሌም የነበሩ ሰዎች ከውድቀት በኋላ ንስሐ ያልገቡ ይመስላሉ። አንድ ብቸኛ ሰው የነበረው አብርሃም ታላቅ ሕዝብ ከሆነ፥ ከአንድ በላይ የሆንን እኛ ሕዝቡንና መንግሥታችንን እንደገና ለመመሥረት እንችላለን ብለው ነበር። እግዚአብሔር ይባርካቸው ዘንድ ከኃጢአታቸው ንስሐ መግባት እንደነበረባቸው አሁንም አልተገነዘቡም ነበር። እንዲሁም ሕዝቅኤል መልእክቱን መስማት ይፈልጉ የነበሩትንና ልባቸውን ያልለወጡትን ምርኮኞች ገሥጾአል። በአፋቸው እግዚአብሔርን እንከተላለን ቢሉም፥ በልባቸው ግን ኃጢአት ነበር፤ ቃላቸውም በተግባር አይተረጉምም ነበር። የውይይት ጥያቄ፥ ዛሬም በቤተ ክርስቲያን የሰዎች ቃልና ተግባር በአንድ ላይ አብሮ አይሄዱም፤ እንዲህ ዓይነቱ ተመሳሳይ ችግር የሚከሠተው እንዴት ነው? መግለፃዎችን ስጥ።  3. የእረኛውና የበጎች ምሳሌ (ሕዝቅኤል 34) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችንና የሕዝቡን ግንኙነት ለመግለጽ ካገለገሉ ማነጻጸሪያዎች እጅግ የተለመደው የእረኛና የበጎች ምሳሌ ነው። ይህ ምዕራፍ መሪዎቹ ኃላፊነታቸውን ካልተገነዘቡና መልካም እረኛ ካልሆኑ የሚመጣባቸውን ፍርድ የሚገልጽ ስለሆነ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በጥንቃቄ ሊያነብቡት የሚገባ እጅግ ጠቃሚ ክፍል ነው። የእስራኤል መሪዎች የእግዚአብሔር መንጋ የሆኑት የእስራኤላውያን እረኞች ነበሩ። እነዚህ መሪዎች ግን ለመንጋው እንክብካቤ ከማድረግ ይልቅ የራሳቸውን የስግብግብነት ዓላማ ያራምዱ ነበር። ለራሳቸው ሕይወት ቁሳዊ ጥቅማ ጥቅሞችን በማሳደድ፥ ለሕዝቡ ተገቢውን እንክብካቤ አያደርጉም ነበር። ስለዚህ የመንጋው ጠላቶች መንጋውን እንዲያጠፉ በር ከፍተው ነበር። በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር ፈረደባቸውና በባቢሎን ምርኮ የአመራር ስፍራቸውን አሳጣቸው። ዳሩ ግን እግዚአብሔር አንድ ቀን ለመንጋው ሰላምና ደኅንነት በሚያመጣ መንገድ፥ የእግዚአብሔርን መንጋ የሚመራ፥ እንደ ዳዊት ያለ አንድ መሪ እንደሚያስነሣ ተስፋ ሰጥቶ ነበር፤ ያም እረኛ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው (ዮሐንስ 10 ተመልከት)። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) በጥንቷ እስራኤል የነበረው የእረኞች ችግር ዛሬ በመጥፎ መሪዎቻቸው ምክንያት ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን ከሚያጋጥሟቸው ችግሮች ጋር የሚመሳሰለው እንዴት ነው? ለ) መልካም እረኛ የሆነውን ኢየሱስን ከቤተ ክርስቲያን መሪዎች ጋር አወዳድር። የእግዚአብሔር መንጋ የሆኑትን የቤተ ክርስቲያን አባሎች በመምራት ረገድ ያላቸው ተመሳሳይነት እንዴት ነው?  4. በኤዶም ላይ የተነገረ ትንቢት (ሕዝቅኤል 35) ኤዶም የእስራኤልንና የይሁዳን ምድር ለመውሰድ በመፈለግ እስራኤልን በማጥፋት ድርጊት ስለተባበረች እግዚአብሔር እንደሚያጠፋት ለሁለተኛ ጊዜ ተናገረ።  5. ስለ እስራኤል ተራሮች የተነገረ ትንቢት (ሕዝቅኤል 36) የእስራኤል ተራሮች እግዚአብሔር ለአይሁድ ሊሰጣቸው ቃል የገባላቸውን የተስፋይቱን ምድር የሚወክሉ ናቸው። ሌሎች መንግሥታትና ሕዝቦች በኢየሩሳሌም ውድቀትና ጥፋት ተደስተው ነበር። አብዛኛው ሕዝብ በምርኮ ተወስዶ ስለነበር በእስራኤል አብዛኛዎቹ አይሁድ ይኖሩባቸው የነበሩት ተራራማ ስፍራዎች ሰው የማይኖርባቸው ሆነው ነበር። እግዚአብሔር ግን አንድ ቀን አይሁድ ከምርኮ እንደሚመለሱና እነዚህ ተራራማ ስፍራዎች በሰዎች የተሞሉ ፍሬያማ እንደሚሆኑ ተናገረ። እንዲያውም ምድሪቱ ከፊት ይልቅ እጅግ በተሻለ ደረጃ ላይ እንደምትሆን ተስፋ ሰጠ። አይሁድ በኃጢአት ድርጊታቸው በራሳቸው ላይ ባመጡት ጥፋት የእግዚአብሔርን ስም ያሰደቡ ቢሆኑም እንኳ እግዚአብሔር አንድ ቀን ቅዱስ መሆኑን በመግለጽ ራሱን ለእስራኤል እንደሚያሳይ ተስፋ ሰጠ። ከተበተኑበት ስፍራ ሁሉ እንደገና እንደሚሰበስባቸው ተናገረ። ከኃጢአታቸውና ከክፉ መንገዳቸው ሁሉ እንደሚያነጻቸውና ሕጉን በልባቸው ላይ በመጻፍ ለእርሱ በፍጹምነት እንዲታዘዙ እንደሚያደርግ ቃል ገባላቸው። እነዚህ የተስፋ ቃሎች አይሁድ በዘሩባቤል፥ በዕዝራና በነህምያ መሪነት በተመለሱ ጊዜ በከፊል የተፈጸሙ ቢሆኑም፥ ሙሉ በሙሉ የሚፈጸሙት ግን አይሁድ በሙሉ ወደ ተስፋይቱ ምድር ተመልሰው፥ በኢየሱስ ክርስቶስ መሪነትና በበረከቱ በሚጥለቀለቁበት በመጨረሻው ዘመን ይመስላል። የውይይት ጥያቄ፣ ሀ) ከእነዚህ የተስፋ ቃሉች አንዳንዶቹ ዛሬ በክርስቲያኖች ወይም በመንግሥተ ሰማያት የሚፈጸሙት እንዴት ነው?) ከእነዚህ የተስፋ ቃሎች አብዛኛዎቹ ለክርስቲያኖች ቃል በቃል ሳይሆን ለአይሁድ ብቻ መፈጸም ያለባቸው የሚመስሉት እንዴት ነው?  6. የደረቁ አጥንቶች የሞሉበት ሸለቆ ራእይ (ሕዝቅኤል 37) በትንቢተ ሕዝቅኤል ውስጥ በሚገባ ከታወቁት ክፍሎች አንዱ የደረቁ አጥንቶች ስለሞሉበት ሸለቆ የተሰጠው ራእይ የሚገኝበት ክፍል ነው። አጥንቶቹ ሕያዋን ፍጥረታት ሆነው ሊቆሙ በሚችሉበት አኳኋን እግዚአብሔር ሠራ። እነዚህ የደረቁ አጥንቶች ከእስራኤልና ከይሁዳ የሆኑትን አይሁድ የሚወክሉ ነበሩ (ሕዝቅኤል 37፡11)። በምርኮ ላይ ለነበሩ አይሁድ ምንም ተስፋ የሌለና የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝቦችም የሞተ ያህል በመሰሉበት ጊዜ፥ አንድ ቀን እግዚአብሔር የሕይወትን እስትንፋስ እንደሚዘራባቸውና ወደ ከነዓን እንደሚመልሳቸው ቃል ገባላቸው። እንዲሁም እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን፡- አንዱ እስራኤል ሌላው ይሁዳ ተብሎ የሚጠራ ሁለት በትር እንዲወስድና አንድ ላይ እንዲያስራቸው ነገረው። ይህም አንድ ቀን የተከፋፈሉት የእስራኤልና የይሁዳ መንግሥታት አንድ እንደሚሆኑ የሚያመለክት ነበር። በዚያን ጊዜ በእስራኤል ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር አገልጋይ ተብሎ የሚጠራው መሢሑ-ዳዊት ይነግሣል። እግዚአብሔር ዘላለማዊ ቃል ኪዳንን ከእነርሱ ጋር በመመሥረት በመካከላቸው ለዘላለም ይኖራል። እነዚህ ትንቢቶች ደግሞ የተፈጸሙት በከፊል ነበር። ከሰባ ዓመታት ምርኮ በኋላ ከአይሁድ አንዳንዶቹ ወደ ምድራቸው የተመለሱ ቢሆንም ድሮ የነበራቸውን ክብር ግን አላገኙም። በ70 ዓ.ም. ደግሞ አይሁድ እንደገና ተበተኑ። ከዚያ በኋላ ወደገዛ ምድራቸው መመለስ የጀመሩት በ1948 ዓ.ም. ነበር። አብዛኛዎቹ አይሁድ ግን እስካሁን ድረስ በአሕዛብ መካከል ተበትነው ይኖራሉ። ስለዚህ መሢሑ ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ቀን አንድ ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ አይሁድን በመሰብሰብ በላያቸው ይነግሣል። እነዚህ የተስፋ ቃሎች ሙሉ በሙሉ የሚፈጸሙት ያኔ ብቻ ነው። 7. በጎግ ላይ የተነገረ ትንቢት (ሕዝቅኤል 38-39) ሕዝቅኤል ስለ መጪው ጊዜ ከተናገራቸው ትንቢቶች መካከል አስደሳች ያልሆኑም ነበሩባቸው። ነቢዩ ከእስራኤል በስተሰሜን እጅግ ርቆ ስለሚገኘው ስለ ጎግ ምድር በተናገረው ትንቢት ውስጥ ወደገዛ ምድራቸው እንደገና በተሰበሰቡ አይሁድ ላይ ጎግ ጦርነት እንደሚከፍት ይገልጣል።

ሕዝቅኤል 33-39 Read More »

ሕዝቅኤል 25-32

የውይይት ጥያቄ፥ መዝሙር (115)፡ 1-3 (135)፡5-6 አንብብ። ሀ) እግዚአብሔር በነገሮች ሁሉ ላይ የበላይ ተቁጣጣሪ ስለ መሆን እነዚህ ቍጥሮች ምን ያስተምሩናል? ለ) እነዚህን ትምህርቶች ማስታወሱ ለምን አስፈለገ? አብዛኛው ትንቢተ ሕዝቅኤል የእግዚአብሔር ሕዝብ ስለሆኑት አይሁድ ኃጢአትና በእነርሱ ላይ ስለሚመጣው ፍርድ የሚናገር ቢሆንም እንደ አብዛኛዎቹ የትንቢት መጻሕፍት፥ እግዚአብሔር በአሕዛብ ላይ ስለሚያመጣው ፍርድም ይናገራል። ይህ ከመንፈሳዊ መመሪያ ጋር የሚስማማ ነው። የእግዚአብሔር ፍርድ ወይም ቅጣት የሚጀምረው የእግዚአብሔር ቤተሰብ ከሆኑት ከልጆቹ ነው (1ኛ ጴጥሮስ 4፡17)። ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ በሚያምኑ ሁሉ ላይም ይደርሳል። እግዚአብሔር አይሁድን ለመቅጣት አሕዛብን ቢጠቀምም እንኳ እነርሱም የእግዚአብሔር ቁጣና ፍርድ እንዳለባቸው በማሳሰብ ያስጠነቅቃቸዋል። በምድር ላይ የምንኖረው ኑሮ እግዚአብሔርን ከማያውቁ ሰዎች ጋርና በእነርሱም ቍጥጥር ሥር ቢሆንም፥ የምናመልከው አምላክ ግን በክፉ ሰዎች ወይም በክፉ መንግሥታት ዕቅድ ቍጥጥር ሥር አለመሆኑን ማስታወስ በጣም አስፈላጊ ነው። ይልቁንም የእኛ አምላክ እግዚአብሔር ሰዎችን ሁሉ ስለሚቁጣጠር ወደዱም ጠሉም ፈቃዱን ይፈጽማሉ። የውይይት ጥያቄ፥ ሕዝቅኤል 25-32 አንብብ። ሀ) ሕዝቅኤል ትንቢት የተናገረባቸውን የተለያዩ ሕዝቦች ስም ዘርዝር። ለ) በእነዚህ ሕዝቦች ላይ የተነገሩትን ዐበይት ትንቢቶች ዘርዝር። ሐ) እነዚህ ሕዝቦች የት እንደሚገኙ ለማወቅ፥ በመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ የሚገኝ “ካርታ ተመልከት።  1. በአሞን ላይ የተነገረ ትንቢት (ሕዝቅኤል 25፡1-7) በአሁኑ ጊዜ የዮርዳኖስ ክፍል አካል የሆነችው የጥንቷ አሞን የእስራኤል የቀድሞ ጠላት ነበረች። ባቢሎናውያን ኢየሩሳሌምን ባጠፉ ጊዜ፥ አሞናውያን ሁኔታውን በደስታ ከመመልከት ሌላ፥ ኢየሩሳሌምን በማጥፋት ረገድም ተባባሪ ሆነዋል። ስለዚህ እግዚአብሔር አሞናውያንን እንደሚያጠፋ ተናገረ። በአሁኑ ጊዜ አሞናውያን የሚባል ሕዝብ የለም። ዳሩ ግን እግዚአብሔር የተናገረው ትንቢት በመፈጸሙ አካባቢው ዛሬ የዐረብ ከብት አርቢዎች የቀንድ ከብቶቻቸውን፥ በጎቻቸውንና ግመሎቻቸውን የሚያሰመሩበት ስፍራ ሆኗል።  2. በሞዓብ ላይ የተነገረ ትንቢት (ሕዝቅኤል 25፡8-11) ሴይር በመባል የምትታወቀው ሞዓብ ከአሞን በስተደቡብ የምትገኝ ነበረች። እግዚአብሔር ዓብን ስለ ኃጢአቷ እንደሚቀጣት ተናገረ።  3. በኤዶም ላይ የተነገረ ትንቢት (ሕዝቅኤል 25፡12-14)  ኤዶም በደቡብ ሞዓብ የምትገኝ አገር ስትሆን፥ የይሁዳ የረጅም ጊዜ ጠላት ነበረች። እስራኤላውያን ወደ ኤዶም እንደሚመጡና እንደሚያሸንፏቸው እግዚአብሔር ተስፋ ሰጠ።  4. በፍልስጥኤም ላይ የተነገረ ትንቢት (ሕዝቅኤል 25፡15-17) በእስራኤልና በይሁዳ በስተምዕራብ ይገኙ የነበሩት ፍልስጥኤማውያን ለረጅም ዘመናት የአይሁድ ጠላቶች ነበሩ። የፍልስጥኤም ጦር ብዙ ጊዜ ይሁዳን ለመውጋትና ለመውረር ከሚዘምት ጦር ጋር ይተባበር ነበር። ስለዚህ እግዚአብሔር ፍልስጥኤማውያንን እንደሚቀጣቸው አስቀድሞ ተናገረ። እነዚህ ሦስት መንግሥታት ወዲያውኑ በባቢሎናውያን ተደመሰሱ። ቆይቶ ደግሞ ኤዶምና ፍልስጥኤም በእስራኤል ቍጥጥር ሥር ዋሉ። የውይይት ጥያቄ፥ በእዚህ ሕዝቦች ላይ የተነገረውን ትንቢቶ የእያንዳንዱ ትንቢት የመጨረሻ ክፍል ተመልከት። አሕዛብ ከእግዚአብሔር ዘንድ በመጣባቸው ቅጣት ምክንያት ምን ይገነዘባሉ? 5. በጢሮስ ላይ የተነገረ ትንቢት (ሕዝቅኤል 26-28፡19) ከማንኛውም የትንቢት መጽሐፍ ይልቅ በጢሮስ ላይ የተነገረውን ትንቢት የያዘው ትንቢተ ሕዝቅኤል ነው። የአሁኒቷ ሊባኖስ ጢሮስ አንዳንድ ጊዜ የይሁዳ ጠላቶች ተባባሪ ስትሆን፥ በሌላ ጊዜ ደግሞ ራሷን የቻለች ጠላት ነበረች። ኢየሩሳሌም ስትደመሰስ የመካከለኛው ምሥራቅ ንግድ ብቸኛ የበላይ ተቆጣጣሪ እንደምትሆን በማሰብ ደስ ተሰኘች። ይህ ሕዝብ በሜዲተራኒያን ባሕር ላይ በመርከብ በሚካሄድ ንግድ ገናና ስምን፥ ሥልጣንንና ኃይልን ያተረፈ ነበረ። ጢሮስ ለጠላት ወረራ አመቺ እንዳትሆን የዋና ከተማዋ ምሽግ በባሕር ዳርቻ ባለ ደሴት ላይ የተሠራ ነበር። ስለዚህ ሕዝቡ ማንም ሊያጠፋው እንደማይችል በመገመት ታበየ፤ ተኲራራም። እግዚአብሔር ጢሮስን ሙሉ በሙሉ እንደሚያጠፋ ተናገረ። ይህም በሁለት ደረጃዎች ተፈጸመ። በመጀመሪያ፥ ናቡከደነፆር በየብስ በእርሱ ምድር ላይ ወደምትገኘው ወደ ዋናዋ ከተማ በመምጣት አጠፋት። በደሴት ላይ ተመሥርታ የነበረችውን ከተማ ለመውጋት ግን አልቻለም ነበር። በሁለተኛ ደረጃ፥ በ331 ዓ.ዓ. ታላቁ እስክንድር የጥንቷን የጢሮስ ከተማ ፍርስራሽ ወደ ባሕሩ በመጣል፥ ከርእሰ ምድሩ አንሥቶ በደሴት ላይ እስከምትገኘዋ ከተማ የሚደርስ መንገድ ሠራ። እግዚአብሔር እንደተናገረው፥ በደሴት ላይ የነበረችዋን ከተማ ለማጥፋት ቻለ። በርእሰ ምድሩ ላይ የነበረችው የጥንቷ ዋና ከተማም ሆነች፤ በደሴት ላይ የምትገኘዋ ከተማ እንደገና ሊሠሩ አልቻሉም። የአሁኒቱ የጢሮስ ከተማ ከቀድሞዋ ጢሮስ የምትመሳሰል ብትሆንም፥ የጥንቷ ከተማ ግን አይደለችም። የእግዚአብሔር ቃል ሙሉ በሙሉ ለመፈጸም ብዙ መቶ ዓመታት የወሰደ ቢሆንም እንኳ አንድም ሳይቀር ተፈጸሞአል። የውይይት ጥያቄ፦ ሀ) ስለ እግዚአብሔር ቃል ትክክለኛነት ይህ ምን ያስተምረናል? ለ) ያልተፈጸሙ የእግዚአብሔር የተስፋ ቃሎች እንደሚፈጸሙ ይህ ምን ዋስትና ይሰጠናል? ሐ ካልተፈጸሙ ትንቢት (የእግዚአብሔር የተስፋ ቃሎች) አንዳንዶቹን ዘርዝር። ሕዝቅኤል 28 በጢሮስ ንጉሥ ላይ የተነገረ ትንቢት ነው። ሕዝቅኤል 28፡12-17 በምሁራን መካከል ከፍተኛ ውዝግብ ያስነሣ ክፍል ነው። አንዳንዶች እነዚህ ቊጥሮች የሚናገሩት በትዕቢቱ ምክንያት በራሱ ላይ የእግዚአብሔርን ፍርድ ስላመጣው ስለ ጢሮስ ንጉሥ ብቻ ነው ይላሉ። ሌሎች ግን እነዚህ ጥቅሶች የሚናገሩት በተለይ የእግዚአብሔር ጠላት ስለሆነው ስለ ሰይጣን ነው ብለው ያምናሉ። ሕዝቅኤል የጢሮስን ንጉሥ ትዕቢት በሥዕላዊ መግለጫነት በመጠቀም የሰይጣንን ውድቀት መግለጡ ነው ብለው ያስተምራሉ። እርግጠኞች ለመሆን ባንችልም እንኳ እነዚህ ቊጥሮች የሚገልጡት ከሥጋ ለባሹ የጢሮስ ንጉሥ የሚልቅ ፍጡርን ይመስላል። ይህ ፍጡር ከጢሮስ ንጉሥ ኃይልና ዝንባሌ በስተኋላ የነበረውና ከጢሮስ ንጉሥ ጋር ተመሳሳይ የሆነው ሰይጣን ነበር። ይህ ትንቢት ስለ ሰይጣን የተነገረ ከሆነ የሚከተሉትን ነገሮች አስተውል፡- ሀ. ሰይጣን እግዚአብሔር ከፈጠራቸው ታላላቅ ፍጥረታት አንዱና ከሁሉም ይልቅ የተዋበ ፍጡር ነበር። በዚያን ዘመን ከነበሩት እጅግ የከበሩ ድንጋዮች ሁሉ ጋር ተወዳድሯል። ሕዝቅኤል በራእዮቹ እንዳያቸው አራት እንስሳት፥ የእግዚአብሔርን ዙፋን እንደሚጋርዱ መላእክት ዓይነት እርሱም እንደ እርሱ ኪሩቤል ነበር (ሕዝቅኤል 13)፤ በእግዚአብሔርም ፊት ይኖር ነበር።  ለ. የሰይጣን ውድቀት የትዕቢቱ ውጤት ነበር። ትዕቢት ሰይጣንን ከመንግሥተ ሰማያት ተባርሮ እንዲወጣና ለመጨረሻም ጥፋት ዳረገው። ** ማስታወሻ፡- ስለ ሰይጣን ውድቀት በኢሳይያስ 14፡12-15 የተነጋገርንበትን ማብራሪያ ተመልከት። የውይይት ጥያቄ፥ እግዚአብሔር ትዕቢትን ስለ መጥላቱ እዚህ ጥቅሶች የሚያስተምሩት ምንድን ነው? 6. በሲዶና ላይ የተነገረ ትንቢት (ሕዝቅኤል 28፡20-26) ሲዶና ከጢሮስ በስተሰሜን 40 ኪሎ ማትር ያህል ርቃ የምትገኝ የወደብ ከተማ ስትሆን፥ ብዙ ጊዜ ከጢሮስ ጋር ትተባበር ነበር። በጢሮስ ኃጢአት ስለተባበረች እግዚአብሔር በሲዶና ላይ ሊፈርድ ቃል ገብቶ ነበር። አይሁድ ደግሞ ወደ ከነዓን እንደሚመለሱና በዚያ በሰላም እንደሚኖሩ ተስፋ ሰጥቷል።  7. በግብፅ ላይ የተነገረ ትንቢት (ሕዝቅኤል 29-32) ግብፅ ከይሁዳ በስተደቡብ የምትገኝ ታላቅ አገር ነበረች። ንጉሥ ኢዮስያስን የገደለችና ልጁን በምርኮ የወሰደችው ግብፅ እንደነበረች የሚታወስ ነው። በውጊያው እንደምትረዳ ቃል በመግባት፥ ይሁዳ በባቢሎን ላይ እንድታምፅ ያበረታታች ግብፅ ነበረች። ዳሩ ግን ግብፅ ጦርነቱ በተጀመረ ጊዜ ይሁዳን ለመርዳት ሳትፈቅድ ቀረች። ይህም ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም ጥፋት ምክንያት ነበር። ስለዚህ ናቡከደነፆር ግብፅን እንደሚያሸንፍ እግዚአብሔር ተናገረ። ግብፅ የቀድሞ ክብሯንና ኃይሏን አጣች። እንደ አይሁድ ሁሉ ግብፃውያንም በአሕዛብ መካከል ተበተኑ። በዘመናቸው ታላቅ እንደነበሩትና እንደወደቁት አምራውያን ታላቁ የግብፅ መንግሥትም ይወድቃል። የሕዝቡ ምልክት ወይም ተወካይ የሆነው ፈርዖንም ሊሸነፍና ከእርሱ በፊት የተሸነፉት ሌሎች ነገሥታትና አሕዛብ በሙሉ ወደ አሉበት ሙታን መንደር ሊሄድ ግድ ነበር። ** ማስታወሻ፡- ስለ ግብፅ የተነገሩት እነዚህ ትንቢቶች ከ587-571 ዓ.ዓ. ባለው በ15 ዓመታት ጊዜ የተሰጡ ነበሩ። የመጨረሻ የሕዝቅኤል ትንቢት ስለ ግብፅ የሚናገር ነበር። ስለ ግብፅ የተነገረው ትንቢት የሚገኘው በጊዜ ቅደም ተከተል መሠረት አይደለም። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) ከእነዚህ ምዕራፎች ልንማራቸው የምንችል ትምህርቶችን ዘርዝር። ለ) ስለ እግዚአብሔርና ከሕዝቦች ጋር ስላለው ግንኙነት ምን ልንማር እንችላለን? (ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ.አይ.ኤም ከታተመውና የብሉይ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ እግዚአብሔር አገልግሎታቸውን ይባርክ፡፡) የመመዘኛ ጥያቄዎችን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ (መስፈንጠሪያ) ይጫኑ፡፡

ሕዝቅኤል 25-32 Read More »

ሕዝቅኤል 18-24

የውይይት ጥያቄ፥ ሕዝቅኤል 18፡2 አንብብ። ሀ) እስራኤላውያን ይጠቅሱት የነበሩት ምሳሌያዊ አነጋገር ምንድን ነው? ለ) የዚህ ምሳሌያዊ አነጋገር ትርጉም ምን ይመስልሃል? ሐ) ይህ ምሳሌ በከፊል እውነት የሚሆነው መቼ ነው? መ) ይህ ምሳሌ ውሸት የሚሆነው መቼ ነው? ኤርምያስና ሕዝቅኤል በነበሩበት ዘመን ምሳሌያዊ አነጋገሮች በእስራኤል አገር የተለመዱ ነበሩ። ከምሳሌያዊ አነጋገሮች አንዱ፡«አባቶች ጮርቃ የወይን ፍሬ በሉ፥ የልጆችም ጥርሶች ጠረሱ» የሚል ነበር። የዚህ ምሳሌያዊ አነጋገር ትርጕም፥ ልጆች የወላጆቻቸውን ክፉ ድርጊት ውጤት ያጭዳሉ ማለት ነው። ይህ አነጋገር ብዙ ጊዜ እውነት ነው (ዘጸአት 20፡5 ተመልከት)። ለምሳሌ አንዲት ሴት በሴሰኝነቷ ምክንያት የኤድስ በሽታ ቢይዛትና ብታረግዝ፥ የኃጢአትዋ ውጤት የሆነውን የኤድስ በሽታ ምንም ወደማያውቀው ሕፃን ልጇ ታስተላልፋለች። ወይም ሱስ የሚያሲዙ ዕፆችን የሚወዱ ወላጆች ልጆቻቸው አካለ ስንኩላን ሆነው እንዲወለዱ ምክንያት ይሆናሉ። ከእዚህ ሁለት ምሳሌዎች እንደተረዳነው፥ የወላጆች ኃጢአት ምንም በማያውቁና በኃጢአታቸው ባልተባበሩ ልጆቻቸው ላይ ክፉ ውጤቶችን ያመጣል። አይሁድ ግን ምሳሌያዊ አነጋገሩን የተጠቀሙበት በዚህ መንገድ አልነበረም። በእግዚአብሔር ፊት ንጹሐን ብንሆንም እንኳ አሁን የተለያዩ መከራዎችን የምንቀበለውና በባቢሎናውያን ወረራና ብዝበዛ እንድንቀጣ የተፈረደብን ወላጆቻችን በሠሩት ኃጢአት ምክንያት ነው የሚል ነበር። ዕጣ-ፈንታቸውም የራሳቸው ምርጫና ድርጊት ውጤት ሳይሆን፥ የወላጆቻቸው ምርጫ እንደነበር በመናገር ራሳቸውን ነፃ የማውጣት ሙከራ ያደርጉ ነበር። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) ዛሬም ቢሆን የተለያዩ ሰዎች የዚህ ተመሳሳይ የሆነ አመለካከት የሚያደርጉትና ክርስቲያን ወላጆች ያሏቸው ልጆች ሳይቀሩ እንኳ እንዲህ የሚያስቡት እንዴት ነው? ላ) ይህ አስተሳሰብ ስሕተት የሆነው ለምንድን ነው? ሰዎች ስለ እግዚአብሔር ያላቸውን ይህን የተሳሳተ አስተሳሰብ ለመከላከል፥ እግዚአብሔር የሦስት ትውልድ ሕዝቦች ምን እንደደረሰባቸው በምዕራፍ 18 ለሕዝቅኤል ይገልጥለታል። በመጀመሪያው ትውልድ፥ ሰውዩው እግዚአብሔርን ይወድ ነበር፥ በእግዚአብሔር ያምን ነበር፤ እግዚአብሔርን ያመልክና ይታዘዝ ነበር። ይህ የሚያረጋግጠው ሰውዬው በእግዚአብሔር ላይ የነበረው እምነት እውነተኛ መሆኑንና ሰውየውም ጻድቅ ስለነበር እግዚአብሔር የዘላለምን ሕይወት እንደሰጠው ነው። በሁለተኛው ትውልድ፥ የጻድቁ ሰውዩ ልጅ ግን እንደ አባቱ አልነበረም። ይልቁንም ክፉና ኃጢአተኛ ነበር። በግሉ እግዚአብሔርን አላመነም ነበር። ለእግዚአብሔር የሚታዘዝ ሕይወትም አልነበረውም። ስለዚህ ምንም እንኳ አባቱ ጻድቅ ቢሆንም፥ ክፉው ልጅ በራሱ ምርጫዎች ባደረጋቸው ነገሮች ምክንያት ጻድቅ አልነበረም። እግዚአብሔርም በመንፈሳዊ ሞት ይቀጣዋል። «ኃጢአትን የምትሠራ ነፍስ እርስዋ ትሞታለች።» በሦስተኛው ትውልድ፥ የክፉው ሰውዩ ልጅ አባቱ የሚያደርገውን ክፋት አየ። ነገር ግን የአባቱን ፈለግ አልተከተለም። ይልቁንም አያቱ እንዳደረገው በእግዚአብሔር አመነ። ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ሕይወት መኖሩን ቀጠለ። ስለዚህ እግዚአብሔር በአባቱ ኃጢአት ምክንያት አይቀጣውም፤ ስለ እምነቱና ስለ ታዛዥነቱ የዘላለምን ሕይወት ይሰጠዋል። ክፉ የሆንና ከኃጢአቱ ንስሐ የገባው ሰውስ ምን ይሆናል? እግዚአብሔር ኃጢአተኛ በኃጢአቱ እንዲሞት ይፈቅዳልን? አይፈቅድም! የእግዚአብሔር ፍላጎት ሰው ሁሉ በሕይወት እንዲኖር ነው። ስለዚህ አንድ ክፉ ሰው ስለ እግዚአብሔር የነበረውን አስተሳሰብ ቢለውጥና ቢያምን፥ በመታዘዝም የእምነቱን እውነተኛነት ቢያረጋግጥ እግዚአብሔር ያንን ሰው ይቅር ይለዋል፤ የዘላለምንም ሕይወት ይሰጠዋል። እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ሊያስጠነቅቅ የፈለገው፡- ችግር የደረሰባቸው በወላጆቻቸው ኃጢአት ሳይሆን በራሳቸው ኃጢአት ምክንያት መሆኑን ነው። ስለዚህ ንስሐ መግባት ነበረባቸው። ንስሐ ቢገቡ እግዚአብሔር ይፈውሳቸው፥ አዲስ ልብና አዲስ መንፈስ ይሰጣቸው ነበር።  የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) ይህ ነገር ስለ እግዚአብሔር ባሕርይ ምን ይነግረናል? ለ) ከሁሉ የላቀ ኃጢአተኛ የሆነውን ሰው እንኳ እግዚአብሔር ይቅር እንደሚለው በመተማመን እንድንመሰክር ይህ እንዴት ያበረታታናል?  የውይይት ጥያቄ፥ ሕዝቅኤል 18-24 አንብብ። ሀ) የሕዝቅኤል 18 ዐቢይ ትምህርት ምንድን ነው? ለ) በምዕራፍ 20 እንደተገለጠው፥ የእስራኤልን ሕዝብ የዓመፃ ታሪክ በተከታታይ አሳይ። ሐ) ስለ እስራኤል የወደፊት ሁኔታ የተሰጠው ተስፋ ምንድን ነው? መ) ሁለቱ አመንዝራ እኅትማማች እነማን ናቸው? የሚያመለክቱትስ ምንድን ነው? ሠ) እግዚአብሔር ስለ ሚስቱ ለሕዝቅኤል የሰጠው ትእዛዝ ምን ነበር? ይህ የትንቢተ ሕዝቅኤል ክፍል ሕዝቅኤል በምርኮ ለነበሩ አይሁድ የተነበያቸውን በርካታ ትንቢቶች ይዟል።  1. እግዚአብሔር ጥፋት የሌለባቸውን ሰዎች አይቀጣም፤ ነገር ግን ጻድቃንን ይባርካቸዋል፤ ክፉዎችንም ይቀጣል (ሕዝቅኤል 18)።  2. ስለ እስራኤል መሪዎች የቀረበ ሙሾ (ሕዝቅኤል 19) ሕዝቅኤል የአንበሳዪቱንና የደቦልዋን ሥዕላዊ መግለጫ በመጠቀም የእስራኤልን መሪዎች ውድቀት ያብራራል። አንበሳም የነገሥታት እናት የሆነችው የይሁዳ ወይም የኢየሩሳሌም ምሳሌያዊ ምልክት ሳይሆን አይቀርም። የመጀመሪያው ደቦል ወደ ግብፅ በምርኮ የተወሰደው ኢዮአካዝ ነው። ሁለተኛው ደቦል ደግሞ ከሕዝቅኤል ጋር ወደ ባቢሎን በምርኮ የተወሰደው ኢዮአኪን ወይም ኢየሩሳሌም በተደመሰሰች ጊዜ ወደ ባቢሎን የተወሰደው ሴዴቅያስ ነው።  3. የዓመፀኛይቱ እስራኤል ታሪክ (ሕዝቅኤል 20) በምርኮ ይኖሩ የነበሩ የአይሁድ መሪዎች የሆኑ ሽማግሌዎች እግዚአብሔር ለእነርሱ መልእክት ይኖረው እንደሆነ ለመጠየቅ ወደ ሕዝቅኤል በወጡ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ስለ እስራኤል ክፋት የሚገልጽ የታሪክ ትምህርት ሰጣቸው። እስራኤላውያን እግዚአብሔር ከግብፅ ነፃ ካወጣቸው ቀን ጀምሮ እስከ ሕዝቅኤል ዘመን ድረስ በተደጋጋሚ ቢያምፁበትም የፍርድ እጆቹን ከመዘርጋት ለረጅም ጊዜ ተቆጥቦ ቆይቷል። ይህንን ያደረገው ስሙ ወይም ክብሩ በአሕዛብ ዘንድ እንዳይጐድፍ ነበር (ሕዝቅኤል 20፡9፡ 14፥ 22)። አሁን ግን የእግዚአብሔር ቍጣና ፍርድ የሚገለጥበት፥ ኢየሩሳሌም የምትደመሰሰበትና ሕዝቡ የሚበተኑበት ጊዜ እንደደረሰ ተረጋገጦ ነበር። ይሁን እንጂ ፍርድ የሚያገለግለው አይሁድን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ሳይሆን፥ አንድ ቀን የእስራኤል ሕዝብ ዓመፅ እንዲያበቃና እስራኤላውያን ከየተበተኑባቸው አገሮች ተሰብስበው እግዚአብሔርን በኢየሩሳሌም እንዲያገለግሉት ለማጥራት ነበር። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) እግዚአብሔር «… ስለ ስሜ ስል በሠራሁላችሁ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃላችሁ» ሲል ምን ማለቱ ነው? ለ) እግዚአብሔር ዛሬ «ስለ ስሙ» ብሎ የሚያደርገው ነገር ምን አለ? 4. ባቢሎን የእግዚአብሔር የፍርድ ሰይፍ ነበረች (ሕዝቅኤል 21) የውይይት ጥያቄ፥ ሕዝቅኤል 22፡30 አንብብ። ሀ) እግዚአብሔር ከይሁዳ ያጣውና በዚህም ምክንያት ፍርድ ያመጣበት ነገር ምን ነበር? ለ) ይህ እውነት ዛሬም ለቤተ ክርስቲያን ሊሠራ የሚችለው እንዴት ነው? 5. የኢየሩሳሌም ኃጢአቶች ባጭሩ (ሕዝቅኤል 22)  6. የሁለቱ አመንዝራ እኅትማማች ምሳሌ (ሕዝቅኤል 23) እግዚአብሔር የእስራኤልን ኃጢአት ግልጽ በሆነ መንገድ ለማወዳደር እስራኤልንና ይሁዳን በሁለት አመንዝራ እኅትማማች ምሳሌነት ያወዳድራል። እነዚህ ሁለት እኅትማማች ከልዩ ልዩ አሕዛብ ጋር በመተባበራቸውና ሐሰተኞች አማልክትን በማምለካቸው አመንዝራዎች ነበሩ። ይህ ምዕራፍ በምንዝርና ላይ ያተኮረው እስራኤል ከልዩ ልዩ አሕዛብ ጋር በነበራት ስምምነት ምክንያት ነው። የመጀመሪያዪቱ አመንዝራ እኅት ኦሖላ ስትባል ትርጒሙም «ድንኳኔ» ማለት ነው። ይህ የሚወክለው ሰማርያን ወይም እስራኤል ተብለው የሚጠሩት አሥሩን የሰሜን ነገዶች ነው። ሁለተኛዋ ደግሞ እሖሊባ ስትባል ትርጒሙ «ድንኳኔ በእርሷ ዘንድ ነው» የሚል ነው። ይህም ኢየሩሳሌምን ወይም የደቡቡን የይሁዳ መንግሥት ይወክላል። ሰማርያ በእግዚአብሔር ከመታመን ይልቅ ከአሦር ጋር ስምምነት በማድረጓ ተገቢ ያልሆነ ነገር በእርሷ ላይ በመፈጸም ወደ ምርኮ ይወስዷት ዘንድ እግዚአብሔር ለአሦራውያን አሳልፎ ሰጣት። ኢየሩሳሌም በሰማርያ ላይ ከደረሰው ነገር መማር ሲገባት ከእርስዋ የበለጠ ክፉና ኃጢአተኛ ሆነች። ከባቢሎናውያን ወይም ከከለዳውያን ጋር ስምምነት አደረገች፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ባቢሎናውያን ኢየሩሳሌምን እንደሚከዷት፥ ተገቢ ያልሆነ ነገር እንደሚፈጽሙባትና ወደ ምርኮ እንደሚወስዷት ተናገረ። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) እግዚአብሔር ሕዝቡ ከአሕዛብ መንግሥታት ጋር ስምምነት እንዲያደርጉ የማይፈልገው ለምን ይመስልሃል? ለ) ሥጋዊ ምንዝርና ከመንፈሳዊ ምንዝርና ጋር የሚመሳሰለው እንዴት ነው? ሐ) ዛሬ ክርስቲያን መንፈሳዊ ምንዝርናን ሊፈጽም የሚችለው እንዴት ነው? 7. የማብሰያ ድስት ምሳሌ (ሕዝቅኤል 24፡1-14) በዚህ ምሳሌ፥ በእሳት ላይ የተጣደው ድስት የኢየሩሳሌም ምሳሌ ሲሆን፥ ሥጋው ወደ ባቢሎን ምርኮ ገና ያልተወሰዱት አይሁድ ናቸው። እሳቱ ደግሞ ባቢሎንን ይወክላል። ሕዝቅኤል ይህንን መልእክት የጻፈው ኢየሩሳሌም በመጨረሻ የምትወረርበት ጊዜ ሊጀምር በተቃረበበት በ588 ዓ.ዓ. ነበር።  8. የሕዝቅኤል ሚስት መሞት ምልክት (ሕዝቅኤል 24፡15-27) እግዚአብሔር የሕዝቅኤልን ሚስት ሞት ሳይቀር ሊመጣ ስላለው ኃዘንና ስለ ኢየሩሳሌም ሕዝብ ሞት ለምርኮኞቹ እንደ ምልክት ተጠቅሞበታል። ሚስቱ እንደምትሞት በመንገር ሕዝቅኤልን አስጠነቀቀው። እርሷም በሚቀጥለው ቀን ሞተች። ሕዝቅኤል ማንኛውም ሰው የሚወደው ሰው በሚሞትበት ጊዜ የሚያሳየውን ኃዘን እንዲያዝን አልፈቀደለትም ነበር። ጮኾ እንዲያለቅስ፥ መጐናጸፊያውን እንዲያወልቅ፥ በራሱ ላይ አመድና ትቢያ እንዲነሰንስ፥ ወይም ለሞተ ሰው የሚያዝኑና የሚያለቅሱ ሰዎች የሚበሉትን የእዝን እንጀራ እንኳ

ሕዝቅኤል 18-24 Read More »

ሕዝቅኤል 13-17

ለቤተ ክርስቲያን ከመንግሥትና ከሌሎች ሃይማኖቶች ከሚመጣባት ስደት ይልቅ እጅግ አደገኛው ነገር በውስጥዋ የሚነሱ የሐሰተኞች አስተማሪዎች ጉዳይ ነው። ራሳቸውን የእግዚአብሔር ልጆች አድርገው ስለሚያቀርቡ ወይም ስለሚያስመስሉ ሐሰተኞች አስተማሪዎችን እውነተኛ ፈሪሀ- እግዚአብሔር ከሞላባቸው መሪዎች መለየት ብዙ ጊዜ አስቸጋሪ ነው። ብዙ ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል የሚለውጡት በጣም መጠነኛ በሆነ መንገድ ስለሆነና በእግዚአብሔርም ስም እንደሚናገሩ ስለሚያስመስሉ ብዙ ሕዝብን ወደ ክፋት ሊያስኮበልሉ የሚችሉ ናቸው። የውይይት ጥያቄ፥ ይህ ነገር በቤተ ክርስቲያንህ ወይም በሌላ ሰው ቤተ ክርስቲያን ሲፈጸም ያየኸው እንዴት ነው? ሐሰተኞች ነቢያት የእውነተኞች ነቢያት ቀንደኛ ጠላቶች ነበሩ። ኤርምያስ ከእነርሱ ጋር እንዴት ግብግብ መግጠም እንደነበረበት ተመልክተናል። ሕዝቅኤልም እንደዚሁ ግብግብ መግጠም ነበረበት። ስለዚህ እግዚአብሔር በሐሰተኞች ነቢያት ላይ እንደሚፈርድ ተናገረ። የውይይት ጥያቄ፥ ሕዝቅኤል 13-17 አንብብ። ሀ) በዚህ ክፍል ውስጥ ያሉትን ዐበይት ትንቢቶች ጥቀስ። ለ) ትንቢትን ለማስተላለፍ ያገለገሉትን የተለያዩ የአነጋገር ዘይቤዎች ዘርዝር። 1. በሐሰተኞች ነቢያት ላይ የተነገሩ ትንቢቶች (ሕዝቅኤል 13)፡- ሐሰተኞች ነቢያት መንፈሳዊ ቅጥሮቻቸውን ለመጠገን ከሰዎች ጋር ከመሥራት ይልቅ ለራሳቸው ጥቅም ይሠሩ ነበር። የተሳሳተ መረጃ በመስጠት፥ ሰዎች ንስሐ ለመግባትና ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ ባላቸው ችሎታ ላይ እንቅፋት ያኖራሉ። መንፈሳዊ ለመምሰል በሚያደርጉት ሙከራ፥ በውጭ ሲታይ ያማረ ሆኖ ውስጡ ግን በቆሻሻ እንደተሞላ ኖራ እንደተቀባ ግድግዳ ነበሩ። የጦርነቱ ዝናብ በእነርሱ ላይ በመጣ ጊዜ፥ መልካም ይመስሉ የነበሩ የሐሰት መልእክቶቻቸው ታጥበው ይወሰዱና ክፋታቸው በሙሉ በሕዝቡ ሁሉ ዘንድ የታወቀ ይሆን ነበር። እግዚአብሔር በአሁኑ ጊዜ ያሉትን ሐሰተኞች ነቢያት በመጨረሻ እንደሚያጠፋቸው ሁሉ፥ የዚያ ዘመን ሐሰተኞች ነቢያትንም እንደሚያጠፉ ቃል ገብቶ ነበር። የሚያሳዝነው አብዛኛዎቹ እስራኤላውያን የሐሰተኞች ነቢያትን መልእክት መከተላቸው ሲሆን፥ ዛሬም ብዙ ክርስቲያኖች የሐሰት ትምህርት አስተማሪዎችን ይከተላሉ።  2. በጣዖት አምላኪዎች ላይ የተነገረ ትንቢት (ሕዝቅኤል 14፡1-11)፡- የጣዖት አምልኮ በብዙ የተለያዩ መልኮች ይገለጻል። ዛፍን ወይም ድንጋይን ወይም አንድ ሌላ ጣዖትን ማምለክ ብቻ ሳይሆን፥ ስለ እግዚአብሔር ወይም ስለ ሃይማኖት የሚቀርብ ማንኛውም የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው። ስለ እግዚአብሔር የተሳሳተ አስተሳሰብ ካለን ጣዖትን እያመለክን ነው ማለት ነው። አይሁድ ጣዖታትን በግልጽ ማምለክ ብቻ ሳይሆን፥ በልባቸው ውስጥ ጣዖታትን አኑረው ነበር (14፡3)። ሕዝቅኤል ጣዖት አምላኪዎችን ንስሐ እንዲገቡ ያስጠነቅቃቸዋል። ከጣዖት አምልኮ ፊታቸውን ከመለሱ፥ እግዚአብሔር ለጸሎታቸው መልስ እንደሚሰጥ ቃል ገባላቸው። 3. በይሁዳ ላይ የመጣው ፍርድ የሚያመልጡት ዓይነት አይደለም (ሕዝቅኤል 14፡12-23)፡- በይሁዳ ላይ የፍርድ ቀን መጥቶ ነበር፡፡ ይህም ፍርድ ለማምለጥ የሚቻል አልነበረም። ለሕዝቡ ጸሎት እንዳያደርግ እግዚአብሔር ኤርምያስን እንደከለከለው ተመልከተናል፡፡ አሁን በትንቢተ ሕዝቅኤል እግዚአብሔር ስለ ጽድቃቸው የታወቁ ሦስት ሰዎችን በመጥቀስ የጻድቅ ሰው ጸሎት እንኳ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ስለነበሩ አይሁዳውያን ነፃ መውጣትን ወይም ከጥፋት ማምለጥን እንደማያስገኝላቸው ያስረዳል። የኖኅ ጽድቅ በዚያ ክፉ ዘመን ከጥፋት ውኃ ያመልጥ ዘንድ ረድቶታል። ዳንኤልም በጽድቁ ምክንያት ከአንበሶች ጉድጓድ አምልጧል። ይህም በወቅቱ በባቢሎን ውስጥ ይኖር ስለነበረውና በአይሁድ መካከል በጽድቁ ስለታወቀው ነቢይ የሚናገር ይመስላል። ኢዮብ እጅግ ቢፈተንም እግዚአብሔርን አልሰደበም። እነዚህ ሦስት ሰዎች በወቅቱ በኢየሩሳሌም ውስጥ ቢኖሩ እንኳ ለአይሁድ ዕርዳታ ለማድረግ አይችሉም። የራሳቸውን ሕይወት ለማዳን ቢችሉም፥ ከተማይቱንና የቀረውን ሕዝብ ለማዳን ስለማይችሉ፥ አይሁድን ባለማመናቸው ምክንያት እግዚአብሔር እንደሚያጠፋቸው ተናገረ። በዱር እንስሳ፥ በሰይፍ፥ በመቅሠፍት፥ በራብ አለቁ። የእግዚአብሔርን ታማኝነት ለማረጋገጥ ጥቂቶቹ ብቻ በሕይወት ቀሩ። የውይይት ጥያቄ፥ የአንድ ሰው ጽድቅ ለሌላው ሰው ደኅንነትን ለማስገኘት ስላለው ብቃት ይህ ክፍል ምን ያስተምረናል? 4. ኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር የማትጠቅም ወይን (ሕዝቅኤል 15)፡- በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በእግዚአብሔርና በሕዝቡ መካከል ስላሉ ግንኙነቶች ከሚገልጡ ዐበይት ምሳሌዎች አንዱ ስለ ወይን ተክል የቀረበ ምሳሌ ነው (ለምሳሌ፡- ዮሐንስ 15)። እግዚአብሔር ወይን የተከለው ፍሬ እንዲያፈራ ቢሆንም፥ በወይን የተመሰለችው ይሁዳ ግን ፍሬ አልሰጠችም ነበር። ከንቱና የማትጠቅም ሆና ነበር። የወይን ግንድ ለልብስ መስቀያ ወይም ለማገዶ እስከማያገለግል ድረስ ደካማ እንደሆነ ሁሉ፥ ይሁዳም ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር የማትጠቅም ከንቱ ሆና ነበር። ስለዚህ ልትጠፋ ይገባት ነበር። ከባቢሎን ጋር ከሚደረግ አንድ የጦርነት እሳት ልታመልጥ ትችል ይሆናል (597 ዓ.ዓ.)፤ ነገር ግን ሌላ እሳት ፍጹም ያጠፋታል (586 ዓ.ዓ.)።  5. የአመንዝራዪቱ የኢየሩሳሌም ምሳሌ (ሕዝቅኤል 16)፡- አይሁድ ከአባቶቻቸው በወረሱት ነገር ታብየው ነበር። የአብርሃም ልጆች ነበሩ፤ ከተማቸውም የዳዊት ከተማ ነበረች። እግዚአብሔር ግን እውነተኛውን ርስታቸውን በሥራቸው አሳያቸው። ኢየሩሳሌም ከከነዓናዊ አባትና ከኬጢያዊት እናት እንደተወለደችና እንዳልተፈለገች ልጅ ተደርጋ እንደተገለጸች እንመለከታለን። ከብዙ ጊዜ በፊት ኢየሩሳሌም የአሞራውያንና የኬጢያውያን ምድር ነበረች። ዳዊት በወረራ የያዛት ነበረች። ኢየሩሳሌም ልክ ተወልዶ ወደ ውጭ ከተጣለ ልጅ ጋር ተመስላ ቀርባለች። እግዚአብሔር ግን በምሕረቱ ወደዳት፤ መረጣት፤ አጠባት፤ ምግብና ልብስ ሰጥቶ እንድታድግ ተንከባከባት። ልክ እንደ ልዕልት እግዚአብሔር በረከቱን አትረፍርፎ ሰጣት። አንድ ባል ለሚስቱ ቃል ኪዳን እንደሚገባ፥ እግዚአብሔር ከኢየሩሳሌም ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። ባይወልዳትም እንኳ ልጁ አድርጎ የወሰዳት ኢየሩሳሌም ግን ባደገች ጊዜ በእግዚአብሔር ላይ ዓመፀች። ጣዖታትን በማምለክና ከአሕዛብ መንግሥት ጋር ቃል ኪዳን በማድረግ አመንዝራ ሆነች። በዚህ ክፍል ውስጥ ሰዶም ተብላ እንደተጠራችው እንደ እኅቷ ሰማርያ ሆነች። ስለዚህ እግዚአብሔር ሰማርያን (እስራኤል) እንደቀጣ ሁሉ፥ አመንዝራዋን ኢየሩሳሌምንም ይቀጣል። እግዚአብሔር የተናገረው ፍጹም እንደሚያጠፋት ሳይሆን፥ አንድ ቀን ከኢየሩሳሌም ጋር የዘላለም ቃል ኪዳን በማድረግ ኃጢአቷን ፍጹም ይቅር እንደሚል ነው። በዚያን ጊዜ ኢየሩሳሌምና ይሁዳ ለእግዚአብሔር ታማኞች ይሆናሉ። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) ቤተ ክርስቲያን ዛሬ በእግዚአብሔር ፊት አመንዝራ ልትሆን የምትችለው እንዴት ነው? መግለጫዎችን ዘርዝር። ለ) ቤተ ክርስቲያንህ ንጽሕት የክርስቶስ ሙሽሪት ትሆን ዘንድ እንዴት ማድረግ ትችላለህ? 6. የሁለቱ ንስሮችና የዝግባው ዛፍ ምሳሌ (ሕዝቅኤል 17)፡- በዚህ ምሳሌ ውስጥ ታላቁ ንስር ባቢሎን፥ ሁለተኛው ንስር ግብፅ፥ ሊባኖስ ኢየሩሳሌም ሲሆን፥ የዝግባው ዛፍ ደግሞ በዳዊት የዘር ግንድ ውስጥ የነበሩትን ነገሥታት የሚያመለክት ነበር። ባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ የዛፉን ቀንበጥ ቀንጥቦ ወደ ባቢሎን ወሰደው። ይህ በምርኮ የተወሰደውን ንጉሥ ኢዮአኪንን የሚያመለክት ነበር። ሁለተኛው ዛፍ ንጉሥ ሴዴቅያስ ነበር። እርሱ በሥልጣን ያደገ ንጉሥ ሲሆን ቅርንጫፎቹ ተስፋፍተው ሁለተኛው ንስር ወደሆነው ወደ ግብፅ ለእርዳታ እጆቹን ዘረጋ። ይህ ንጉሥ ሴዴቅያስ ከባቢሎን ጋር ያደረገውን ስምምነት በመጣስ የተደረገ ነበር። ስለዚህ እግዚአብሔር ንጉሥ ሴዴቅያስን የምሥራቅ ነፋስ በተባሉት በባቢሎን ኃይላት ሊያጠፋው ወሰነ። ዳሩ ግን አንድ ቀን እግዚአብሔር ከዳዊት ቤት የሆነ ሌላ ቅርንጫፍ ያስነሣል። ታላቅ ዛፍ ከመሆኑ የተነሣ ብዙ ሰዎች በቅርንጫፎቹ ሥር ያርፋሉ። ከማንኛቸውም ዛፎች ሁሉ የሚበልጥ ነው፤ ይህም ማለት ከአሕዛብ መንግሥታት ሁሉ በላይ ነው ማለት ነው። የመጨረሻው ዛፍ ስለ መሢሑ የተነገረ ትንቢት ነው። መሢሑ የዳዊት ልጅና የዓለም ሁሉ ንጉሥ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። የውይይት ጥያቄ፥ በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ የተካተቱትን ጠቃሚ መንፈሳዊ እውነቶች ዘርዝር። (ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ.አይ.ኤም ከታተመውና የብሉይ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ እግዚአብሔር አገልግሎታቸውን ይባርክ፡፡) የመመዘኛ ጥያቄዎችን ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ (መስፈንጠሪያ) ይጫኑ፡፡

ሕዝቅኤል 13-17 Read More »

ሕዝቅኤል 4-12

ምክንያታዊ የሚመስሉና በሌሎች ሰዎች ዘንድ ተቀባይነት የሚኖራቸውን ነገሮች ማድረግ ቀላል ነው። ዳሩ ግን ሰዎች እንግዳ አድርገው የሚቆጥሩትንና በእኛ ላይ እንዲሳለቁ የሚያደርጋቸውን ነገር ማድረግ የበለጠ አስቸጋሪ ነው። ይሁን እንጂ ክርስቲያኖች እንደ መሆናችን መጠን ሌሉች ሰዎች እንዲያፌዙብንና እንዲስቁብን የሚጋብዝ ነገር ቢሆንም እንኳ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ለመኖር መወሰን አለብን። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) ክርስቲያኖች ከሚያደርጓቸውና ክርስቲያን ያልሆኑ ሰዎች እንግዳና አስቂኝ አድርገው ከሚያስቧቸው ነገሮች አንዳንዶቹ ምንድን ናቸው? ለ) ብዙ ክርስቲያኖች ክርስቲያን ያልሆኑ ሰዎች እንዳይስቁባቸውና እንዳያፌዙባቸው በመፍራት ባሕርያቸውን የሚለውጡት ወይም የሚደብቁት ለምንድን ነው? ከማንኛውም ሌላ ነቢይ ይበልጥ ሕዝቅኤል ትንቢቶቹን ባልተለመዱ መንገዶች አቅርቧል። እነዚህ አቀራረቦች ለእኛ እንግዳ ናቸው። ዳሩ ቀን እግዚአብሔር እነዚህ መልእክቶች እንግዳ በሆነ መንገድ እንዲቀርቡ ያደረገው ሰዎች ለሕዝቅኤልና ለመልእክቱ ልዩ ትኩረት እንዲሰጡ ለማበረታታት እንደነበር ጥርጥር የለውም። እነዚህን ነገሮች ማድረ ፈጽሞ ያልተለመዱ ተግባራትን መፈጸም ቢሆንም ሕዝቅኤል እግዚአብሔርን ለመታዘዝ ፈቃደኛ ነበር። የውይይት ጥያቄ፥ ሕዝቅኤል 4-12 አንብብ። ሀ) ሕዝቅኤል ያደረጋቸውን የተለያዩ ተምሳሌታዊ ተግባራት ዘርዝር። የእያንዳንዱ ተምሳሌ ተግባር ትርጕም ምን ይመስልሃል? ለ) ሕዝቅኤል በዚህ ክፍል የተናገራቸውን ትንቢቶች በአጭሩ አቅርብ። 1. በጡብ አማካይነት የተካሄደው ተምሳሌታዊ ድርጊት (ሕዝቅኤል 4፡1-3)፡- የኢየሩሳሌም ከተማን ሥዕል በጡብ ላይ እንዲስል እግዚአብሔር ለሕዝቅኤል ነገረው። በዚያ የጡብ ሥዕል ዙሪያ የከተማይቱን መከበብ የሚያሳዩ ትንንሽ ነገሮች እንዲያስቀምጥ ታዝዞ ነበር። ቀጥሉ ሕዝቅኤል የብረት ምጣድ ወስዶ በእርሱና በጡብ በሠራት ከተማ መካከል ምጣዱን ማስቀመጥ ነበረበት። ይህ ሁሉ የኢየሩሳሌም ከተማ በባቢሎን ጦር እንደምትወረርና እንደምትያዝ፣ ልክ የብረት ምጣዱ እንደማይሰበር ሁሉ ወረራውንም ሊሰብር ወይ ሊያሸንፍ የሚችል አንዳችም ነገር እንደሌለ የሚያመለክት ነበር፡፡ ሕዝቅኤል እግዚአብሔርን ወክሉ በኢየሩሳሌም ላይ የሚመጣው ጦርነት ከጌታ እንደሆነ ለማሳየት ከተማይቱን በዚያ መልኩ መክበብ ነበረበት። 2. በጐድኑ የመተኛቱና በድርቅ ጊዜ ምግብ የመብላቱ ተምሳሌታዊ ድርጊት (ሕዝቅኤል 4፡4-17)፡- ሕዝቅኤል በአንድ ጐድኑ ለ390 ቀናት፥ በሌላው ጐድኑ ደግሞ ለ40 ቀናት ተኛ። ሕዝቅኤል በአንድ ጐድኑ 390 ቀናት በመተኛት የእስራኤልን ሕዝብ ኃጢአትና ዓመፅ ርዝመት በተምሳሌታዊ ድርጊት አሳየ። ለ40 ቀናት በአንድ ጐድኑ በመተኛት ደግሞ የይሁዳን ኃጢአትና ዓመፅ አሳየ። የቍጥሮቹን ተምሳሌታዊ ድርጊቶች በሚመለከት ምሁራን የተለያየ አስተሳሰብ አላቸው። 390 ቀናት የጣዖት አምልኮ በእስራኤል መንግሥት ውስጥ ከተጀመረበት ከሰሎሞን ጊዜ አንሥቶ ኢየሩሳሌም እስከተደመሰሰችበት ጊዜ ድረስ ያለውን የ390 ዓመታት ርዝመት የሚያሳይ ሊሆን ይችላል። 40 ቀናት ደግሞ ክፉና ኃጢአተኛ ንጉሥ የነበረው ምናሴ ንስሐ ከመግባቱ በፊት የነበሩትን 40 የዓመፅ ዓመታት የሚያሳይ ነው ሊባል ይችላል። ጥቂት ምግብ እንዲበላና ጥቂት ውኃ እንዲጠጣ እግዚአብሔር ለሕዝቅኤል የነገረው ኢየሩሳሌም በወረራ በምትያዝበት ጊዜ በከተማው ውስጥ ራብ እንደሚኖርና በቂ ምግብና ውኃ እንደማይገኝ ለማሳየት ነበር። እንዲሁም ምግቡን ለማብሰል የሰውን እዳሪ እንደማገዶ እንዲጠቀም እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን አዝዞት ነበር። ይህ ግን ሕዝቅኤልን በሃይማኖታዊ ሥርዓት ርኩስ የሚያደርገው ነገር ስለነበር አጕረመረመ። ስለዚህ የከብት እበት እንዲጠቀም እግዚአብሔር ፈቀደለት። ይህም የሚያሳየው፡- ኢየሩሳሌም በወረራ በምትያዝበት ጊዜ ሁኔታዎች እጅግ የከፉ ከመሆናቸው የተነሣ ለማገዶነት የሚያገለግል እንጨትም ሆነ የማንኛውም እንስሳ እበት እንደማይገኝና ስለዚህም ሰዎች የራሳቸውን እዳሪ ለማገዶነት ለመጠቀም እንደሚገደዱ ነው።  3. የሕዝቅኤል ጠጕር ተምሳሌታዊ ድርጊት (ሕዝቅኤል 5)፡- በአይሁድ ዘንድ ጠጕርን መላጨት ትልቅ ሐፍረት ነበር። ስለዚህ ብዙ ጊዜ ረጃጅም ጠጕርና ጢም ነበራቸው። ዳሩ ግን ሰዎች ወደ ምርኮ በሚወሰዱበት ጊዜ በማራኪዎቻቸው አማካይነት ራሳቸው ሙልጭ ተደርጎ ይላጭ ነበር። ስለዚህ ምርኮን በተምሳሌታዊ መግለጫነት ለማስረዳት፥ ጠጕሩንና ጢሙን እንዲላጭ እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን አዘዘው። ጠጕሩንም በትክክል ሦስት ቦታ እንዲከፍል አዘዘው። የጠጕሩን ሢሶ በሠራው የሸክላ ከተማ ቅርጽ ውስጥ እንዲያቃጥል አዘዘው። ይህ የሚያመለክተው:- የኢየሩሳሌም ከተማ በምትያዝበት ጊዜ በሚፈጠረው ራብ፥ ችግርና መቅሠፍት ምክንያት የሕዝቡ ሲሶ በኢየሩሳሌም ከተማ ውስጥ እንደሚሞት ነበር። ሕዝቅኤል ሁለተኛውን የጠጕሩን ሲሶ ደግሞ በሰይፍ እንዲቈራርጠው ታዝዞ ነበር። ይህ ደግሞ የሚያመለክተው ከኢየሩሳሌም ሕዝብ ሲሶው ከከተማው ውጭ ከባቢሎናውያን ጋር በሚደረግ ጦርነት እንደሚሞት ነበር። የመጨረሻውን የጠጒሩን ሲሶ በነፋስ ላይ እንዲበትነው ታዝዞ ነበር። ይህም የኢየሩሳሌም ሕዝብ በአሕዛብ መካከል እንደ ጠጕር እንደሚበተኑ የሚያሳይ ነበር። ዳሩ ግን ሕዝቅኤል ከጠጕሩ ጥቂቱን ደግሞ በመጐናጸፊያው ውስጥ ሸሽጎ እንዲያስቀምጥ ታዝዞ ነበር። ይህም እግዚአብሔር በጸጋው ሁልጊዜ እንዳይጠፉ የሚጠብቃቸው ቀሬታዎት እንዳሉት የሚያሳይ ነበር። እነርሱም ከጠቅላላ የአይሁድ ሕዝብ ብዛት ጋር ሲነጻጸር በቍጥር ጥቂት ናቸው።  4. በእስራኤል ተራሮች ላይ የተነገረ ትንቢት ሕዝቅኤል 6)፡- በዚያን ዘመን፥ ብዙውን ጊዜ አይሁድ የሐሰት አማልክትን ወይም ጣዖታትን በኮረብታዎችና በተራራዎች ላይ ያመልኩ ነበር። ስለዚህ እግዚአብሔር የጣዖት ማምለኪያ ስፍራዎችና ጣዖት አምላኪዎች እንደሚደመሰሱ ተናገረ። የጣዖታቱ መደምሰስ ብቻ ሳይሆን ሊያመልካቸው የሚችል ማንም አይኖርም። ከንቱና የማይጠቅሙ ሆነው በእግዚአብሔር ይሸነፋሉ። 5. የኢየሩሳሌምና በእርስዋም የሚቀሩ ሰዎች ጥፋት እርግጠኛ ስለ መሆኑ የተሰጠ ትንቢት (ሕዝቅኤል 7)፡- ሕዝቅኤል እንደገና ሕዝቡ የጦርነት ሰለባ በመሆን በችግር፥ በራብና በመቅሠፍት፥ በአሕዛብ መካከል በመበተን፥ በተለያዩ መንገዶች እንደሚቀጡ ተነበየ። 6. በቤተ መቅደስ ውስጥ ስለሚፈጸም የጣዖት አምልኮ የተሰጠ ራእይ (ሕዝቅኤል 8-9)፡- እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን በራእይ ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ መለሰው። በዚያም በቤተ መቅደስ ውስጥ የሚፈጸም የተለያየ የጣዖት አምልኮን አሳየው። ይህም በሕዝቡ ላይ የሚመጣው የእግዚአብሔር ፍርድ እርግጠኛ እንዲሆን ያደረገው ጸያፍ ተግባር ነበር። ሀ. ቀናተኛነትን ያነሣሣ የነበረው ጣዖት (የተቀረጸ ምስል)፡- ይህ የተቀረጸ ምስል የሚገኘው በቤተ መቅደሱ ውጫዊ ክፍል ነበር። ይህ ጣዖት ኢዮስያስ ከሠላሳ ዓመታት በፊት ያስወገደው ዓይነት፥ የከነዓናውያን የልምላሜ አምላክ የነበረችው የአስታሮት ምስል ሳይሆን አይቀርም (2ኛ ነገሥት 23፡6)።  ለ. የተንቀሳቃሾችና የርኩሳን አራዊት የሌሎችም አማልክት ምስሎች፡- እዚህ በቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍል ግድግዳ ላይ የተሳሉ ነበሩ። እነዚህ ከግብፃውያን የጣዖት አምልኮ የተቀዱ ሳይሆኑ አይቀሩም። በእነዚህ ጣዖታት ወይም የተቀረጹ ምስሎች ፊት ለፊት ሐሰተኞች አማልክትን በሥውር ያመልኩ የነበሩ ሰባዎቹ ሽማግሌዎች ነበሩ። እነርሱም የይሁዳ የፖለቲካ መሪዎች ነበሩ።  ሐ. ተሙዝ የተባለው ጣዖት፡- ይህ የባቢሎናውያን የወላድነት አምላክ ነበር። ይህንን ጣዖት በተለይ የሚያመልኩት ሴቶች ነበሩ። እነዚህ ሴቶች በየዓመቱ ዝናብ በሚያቆምበት ጊዜ ዕፀዋት እንደሚደርቁና በዝናም ወራት እንደገና እንደሚለመልሙ፥ ይህ ጣዖትም ሕይወትን የመስጠትና ወላድ የማድረግ ችሎታ አለው ብለው ያምኑ ነበር። ጣዖቱ የሚገኘው በቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍል ነበር። መ. ፀሐይ አምላኪዎች፡- በጥንት ዘመን ቤተ መቅደሶች የሚመለከቱት ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ ነበር። እነዚህ ሰዎች (ምናልባት ካህናት ሳይሆኑ አይቀሩም) በቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍል ነበሩ። እውነተኛውን አምልኮ ለሚገባው አምላክ ጀርባቸውን ሰጥተው ፀሐይን ያመልኩ ነበር።  እነዚህ ከላይ የተመለከትናቸው አራት ነገሮች በይሁዳ እውነተኛው አምላክ እንዲመለክበት በተሠራው ቤተ መቅደስ ውስጥ እንኳ የጣዖት አምልኮ ተስፋፍቶ እንደነበር የሚያስነዝቡ ጥቂት ምሳሌዎች ናቸው። እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ለመፍረድ የወሰነው በዚህ ምክንያት ነበር። እግዚአብሔር በጣዖት አምላኪዎች ላይ እንደሚፈርድ ለማሳየት ከሰሜን የመጡ ስድስት ቀሳፊ መላእክትን ለሕዝቅኤል አሳየው። መላእክቱን የጣዖት አምላኪዎችን እንዲያጠፉ ይመራቸው የነበረ አንድ በፍታ (ሐር) የለበሰ ሰውም ነበር። እነዚህ መላእክት የባቢሎንን ሠራዊት የሚያመለክቱ ነበሩ። እግዚአብሔር እርሱን የተከተሉትንና በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሚደረገው የጣዖት አምልኮ የሚያለቅሱትን ሰዎች ለይቶ አወጣ፡፡ በግምባራቸው ላይ «ታው» የሚል የዕብራውያን ምልክት አደረገ። የ «ታው» ቅርጽ ከመስቀል ቅርጽ ጋር ተመሳሳይ መሆኑ የሚያስገርም ነገር ነው። መላእክቱ በቤተ መቅደስ ውስጥ ጣዖትን ያመልኩ ከነበሩ ሰዎች ጀምረው በከተማው ውስጥ የሚገኙትን ጣዖት አምላኪዎችን በሙሉ ገደሉ። እንደገና እግዚአብሔር በጣዖት አምልኮ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ እንደነበረውና ኃጢአትን በመጥላት እርሱን በማይከተሉ ሁሉ ላይ እንደሚፈርድ የሚያሳይ ራእይ እንደሆነ ማስታወስ በጣም አስፈላጊ ነው። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) እግዚአብሔር የሐሰት አምልኮን ይጠላል ይቀጣልም ከሚለው አባባል ምን ትምህርት እንማራለን? ለ) የእግዚአብሔር ሕዝብ ለሐሰት አምልኮ ሊሰጡት ስለሚገባ ምላሽና በአምልኮአቸው ንጹሐን ሆነው ለመጽናት ስለሚያደርጉት ውሳኔ ምን እንማራለን 7. የእግዚአብሔር ክብር ቤተ መቅደሱን ለቆ መሄዱን የሚመለከት ራእይ (ሕዝቅኤል 10)፡- እግዚአብሔር እጅግ ታጋሽ ቢሆንም እንኳ ከኃጢአት ጋር

ሕዝቅኤል 4-12 Read More »

የእግዚአብሔር ራእይና የሕዝቅኤል ጥሪ (ሕዝቅኤል 1-3)

የውይይት ጥያቄ፥ 2ኛ ጴጥሮስ 3፡1-13 አንብብ። ሀ) ብዙ ሰዎች ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተናገረው ስላልተመለሰ ምን ብለው ያስባሉ? ለ) እስካሁን ያልተመለሰው ለምንድን ነው? እግዚአብሔር ምን እየጠበቀ ነው? ሐ) አንድ ቀን ምድርና ሰማይ ምን ይሆናሉ? መ) ክርስቲያኖች ያንን ታሪካዊ ድርጊት በሚመለከት መኖር ያለባቸው እንዴት ነው? እግዚአብሔር የምሕረትና የፍቅር አምላክ ነው። የደኅንነት ተስፋ ያገኙት በዚህ እውነት ምክንያት ብቻ መሆኑን ስለሚያውቁ ይህ እውነት ለክርስቲያኖች ታላቅ ማበረታቻ ነው። እግዚአብሔር የምሕረትና የፍቅር አምላክ ስለሆነ ሰዎች ንስሐ እንዲገቡና እንዳይጠፉ ብዙ ጊዜ ፍርዱን ያዘገያል። የሚያሳዝነው ግን ሰዎች የእግዚአብሔርን ፍቅር ያለ አግባብ በመተርጐም ባደረጉት ኃጢአት ምክንያት ወዲያውኑ ስለማይፈርድባቸው እግዚአብሔር ጨርሶ የማይፈርድ መሆኑን ማሰብ መጀመራቸው ነው። ስለዚህ የእግዚአብሔር ፍቅርና ምሕረት ሰዎችን ወደ ንስሐ ከመምራት ይልቅ ፍርድን ባለመፍራት በኃጢአት እንዲኖሩ አድርጎአቸዋል። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) ይህንን ዓይነት ተመሳሳይ ዝንባሌ በሰዎች ሕይወት ውስጥ ያየኸው እንዴት ነው?) ክርስቲያኖች እግዚአብሔር የፍቅርና የምሕረት አምላክ ብቻ ሳይሆን፥ የቁጣ፥ የጽድቅና የፍርድ አምላክ ጭምር መሆኑን ማስታወሳቸው የሚጠቅመው ለምንድን ነው? በሕዝቅኤል ዘመን በነበሩ አይሁድ ሕይወት የተፈጸመው ነገር ይህ ነበር። አይሁድ በኃጢአታቸው ምክንያት እንደሚፈረድባቸው ለብዙ ዘመናት በእግዚአብሔር ነቢያት በኩል ማስጠንቀቂያ ሲደርሳቸው ኖረዋል። እግዚአብሔር መሐሪ ስለሆነ ሕዝቡ ንስሐ እንዲገቡና እንዳይፈረድባቸው ሲል በሕዝቡ ላይ ወዲያውኑ አልፈረደም። ይህ ግን ከሕዝቡ በኩል ከፍተኛ ድፍረትን አስከተለ። በኃጢአታቸው ምክንያት ከቶ እንደማይፈረድባቸው ይመስላቸው ነበር። ከዚህ የተነሣ ኃጢአታቸው እጅግ እየተባባሰ ሄደ። ከኃጢአታቸው ንስሐ ለመግባት የነበራቸው ፈቃደኝነትም እየቀነሰ መጣ። ስለዚህ እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን ጠራና ራእይን ሰጠው። በዚህም ራእይ እግዚአብሔር ደካማ አምላክ ሳይሆን ሕዝቡን ስለ ኃጢአታቸው ሊቀጣ የተዘጋጀ ቅዱስ አምላክ እንደሆን ለሕዝቅኤል አሳይቷል። የእግዚአብሔር የምሕረት ዘመን አልቆ የፍርድ ዘመን ከመጀመሩ በፊት ከነበሩ የእግዚአብሔር ቃል አቀባዮች አንዱ ሕዝቅኤል ነበር። የውይይት ጥያቄ፥ ሕዝቅኤል 1-3 አንብብ። ሀ) ሕዝቅኤል ያየውን የእግዚአብሔር ራእይ ግለጽ። ለ. በዚህ ራእይ ውስጥ ያሉት አንዳንድ ምልክቶች ትርጕም ምን ይመስልሃል? እንደ ነቢዩ ኢሳይያስ ሁሉ፥ የሕዝቅኤል የነቢይነት ጥሪ የተጀመረው በእግዚአብሔር ራእይ ነበር። ኢሳይያስ ያየው ራእይ ያተኮረው በእግዚአብሔር ታላቅነትና ክብር ላይ ሲሆን፥ የሕዝቅኤል ራእይ ደግሞ በእግዚአብሔር ዙሪያ ባሉ ነገሮች ላይ ያተኮረ ነበር። ሕዝቅኤል በራእዩ አራት ዐበይት ነገሮችን አይቶአል። ሀ. አራቱ እንስሶች (ሕዝቅኤል 1፡4-9)፡- እነዚህ አራት እንስሶች ኪሩቤል ተብለው የሚጠሩ የእግዚአብሔር መላእክት ነበሩ (ሕዝቅኤል 10፡1)። የተሰጣቸው ኃላፊነት እግዚአብሔርንና ዙፋኑን ማጀብና ክብሩን መጠበቅ ነው። ስለ እነዚህ አራት ፍጥረታት የተሰጠው ገለጣ እጅግ ሰፊና ዝርዝር አሳብ የያዘ ነበር። (ቍጥር አራት የፍጹምነትና የምሉእነት መግለጫ ነው)። እነዚህ አራት ፍጥረታት እያንዳንዳቸው አራት ራሶችና አራት ክንፎች ነበሯቸው። የእያንዳንዳቸው አራት ራሶች የእግዚአብሔርን ፍጥረት ይወክሉ ነበር። አንዱ ራስ የፍጥረታት ሁሉ ገዥ የሆነውን ሰውን፥ ሌላው ከዱር እንስሳት ሁሉ ኃይለኛና ብርቱ የሆነውን አንበሳን፥ ሌላው ከአዕዋፋት ሁሉ ጠንካራና ኃይለኛ የሆነውን ንስርን ሲመስል የመጨረሻው ደግሞ ከቤት እንስሳት ሁሉ ኃይለኛ የሆነውን በሬን ይመስል ነበር። (ለተመሳሳይ ገለጻ ራእይ 4፡7 ተመልከት።) ለ. የሠረገላው አራት መንኰራኲሮች፡- እነዚህን መንኲራኲሮች ልዩ የሚያደርጋቸው ነገር አቅጣጫቸውን ሳይለውጡ በፈለጉት አቅጣጫ ለመዞር እንዲችሉ በመንኰራኵር ውስጥ ሌላ መንኰራኵር መኖሩ ነው። እነዚህ መንኲራኲሮች ዓይኖች ሞልተውባቸው ነበር። እነዚህ ሁለት እውነቶች በምሳሌ የሚገልጹት የእግዚአብሔር ዙፋንና ሕልውና በአንድ ጊዜ በሁሉ ቦታ መሆኑንና ሁሉንም ነገር ለማየት እንደሚችል ነበር።  ሐ. ከመንኰራኵሮቹ በላይ ያለው ሰፊ ስፍራ  መ. «የሰውን ልጅ የሚመስል» ወይም እግዚአብሔር ራሱ የተቀመጠበት ዙፋን፡- ሕዝቅኤል እግዚአብሔር ምን እንደሚመስል ላለመግለጥ ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጓል። መልኩንና የከበበውን የክብር ነጸብራቅን ብቻ በአጭሩ ይገልጻል። ሕዝቅኤል ላየው ለዚህ ታላቅ ራእይ የሰጠው ምላሽ በአምልኮና እግዚአብሔርን በመፍራት በግንባሩ መውደቅ ብቻ ነበር። ሕዝቅኤል እግዚአብሔርን ካየ በኋላ ከእግዚአብሔር ጥሪ ተቀበለ። እግዚአብሔርም እርሱን መስማትና ንስሐ መግባት አሻፈረኝ ወዳለ ዓመፀኛ ሕዝብ እንደሚልከው ለሕዝቅኤል ይነግረዋል። እነርሱን እንዳይመስልና እንዳይፈራቸውም ያስጠነቅቀዋል። ከዚያም ይበላው ዘንድ የመጽሐፍ ጥቅልል ሰጠው። የመጽሐፉ ጥቅልል የእግዚአብሔር ቃል ስለነበረ እንደ ማር ይጣፍጥ ነበር። የመጽሐፉ ጥቅልል ሕዝቅኤል ለሕዝቡ መናገር ያለበትን የትንቢት ቃላት የያዘ ነበር። ሕዝቅኤል በጥቅልሉ ላይ በነበረው ጽሑፍና ስለ ሕዝቡ ኃጢአተኛነት ባገኘው አዲስ ግንዛቤ በመንፈሱ ተቈጣ፤ ተማረረም። ከመጠን በላይ ከመመሰጡ የተነሣ ለማንም ሰው ሳይናገር ሰባት ቀን ተቀመጠ። የውይይት ጥያቄ፥ የእግዚአብሔርን ቃል በተገቢው መንገድ መረዳት በሕይወታችን ውስጥ ይህን የመሰለ ምላሽ መፍጠር ያለበት በምን መንገድ ነው? ከሰባት ቀናት በኋላ እግዚአብሔር እንደገና ለሕዝቅኤል ተናገረ፤ የሕዝቡ «ጠባቂ»ም አደረገው። ጠባቂ በአንዲት ከተማ ከፍተኛ ስፍራ ላይ በመቀመጥ የጠላትን መምጣት በከተማ ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች የሚናገር ነበር። ጠባቂ እንደ መሆኑ መጠን የሕዝቅኤል ኃላፊነት ከፍተኛ እንደሆነ እግዚአብሔር አስጠነቀቀው። የእግዚአብሔርን የተግሣጽና የፍርድ መልእክት ለክፉው ሰውና ከመንገዱ ለመመለስ ለሚያመነታው ወይም የመኮብለል አሳብ ለሚፈታተነው ጻድቅ ሰው ንስሐ እንዲገባ የሚያበረታታ ቃል መናገር ነበረበት። ሕዝቅኤል ይህን መልእክት ለማስተላለፍ ባይፈቅድ፥ ክፉው ወይም ከእግዚአብሔር ፊቱን የመለሰው ጻድቅ ሰው ስለ ራሱ ኃጢአት በጥፋተኛነት የሚጠየቅ ቢሆንና ሕዝቅኤልም ይህን ሰው ባለማስጠንቀቁ ተጠያቂ ይሆን ነበር። ሕዝቅኤል የማስጠንቀቂያ መልእክቱን መናገር የነበረበት በክፋት ለሚመላለሰው ሕዝብ ብቻ ሳይሆን፥ እያንዳንዱ ሰው በግል ለሚፈጽመው ማንኛውም ተግባር ተጠያቂ መሆኑን ጭምር ነበር። የውይይት ጥያቄ፦ ሀ) ይህ ትምህርት በአሁኑ ጊዜ ወንጌል ላለን ለእኛ ብርቱ ማስጠንቀቂያ የሚሆነው እንዴት ነው? ለ) ዛሬ ይህን ትምህርት በቤተ ክርስቲያንህ የሚገኙ ሰዎች የጥበቃ ኃላፊነት እንዳለባቸው ለማስተማር ልትጠቀምበት የምትችልባቸው መንገዶች ምንድን ናቸው? ኢየሩሳሌም ከስድስት ዓመት በኋላ በባቢሎን እጅ እስከወደቀችበት ጊዜ ድረስ፥ ሕዝቅኤል ለሕዝቡ የሚሆን ግልጽ ከእግዚአብሔር መልእክት ካልተቀበለ በቀር ለመናገር አልቻለም ነበር (ሕዝቅኤል 24፡27፤ 33፡22)። (ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ.አይ.ኤም ከታተመውና የብሉይ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ እግዚአብሔር አገልግሎታቸውን ይባርክ፡፡) የመመዘኛ ጥያቄዎችን ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ (መስፈንጠሪያ) ይጫኑ፡፡

የእግዚአብሔር ራእይና የሕዝቅኤል ጥሪ (ሕዝቅኤል 1-3) Read More »

የትንቢተ ሕዝቅኤል ዓላማ እና የሥነ መለኮት ትምሕርት

የትንቢተ ሕዝቅኤል ዓላማ ሕዝቅኤል ይህን መጽሐፍ ለምን እንደ ጻፈው ለመረዳት፥ ሕዝቅኤል ያገለገለው ከኢየሩሳሌም ውድቀት ጥቂት ቀደም ብሎና ከውድቀቷ በኋላም ለጥቂት ጊዜያት መሆኑን ማስታወስ ጠቃሚ ነው። ሕዝቅኤል ይህን መጽሐፍ የጻፈባቸው ሦስት ዋና ዋና ዓላማዎች ነበሩ፡- 1. ሕዝቅኤል ጠባቂና የእግዚአብሔር ቃለ አቀባይ ስለነበር፥ ልባቸው ለደነደነባቸው አይሁድ የእግዚአብሔርን የማይለወጥ ፍርድ በመናገር የንስሐ ጥሪ ያቀርብ ነበር። ሕዝቅኤል የፍርዱን መልእክት በማስተላለፍ ሕዝቡ ንስሐ እንዲገቡ ጥሪ ከማድረግ ይልቅ ዝም ቢል ይቀለው እንደነበር እግዚአብሔር ያውቃል። ዳሩ ግን እግዚአብሔር ሕዝቡን ባያስጠነቅቅና ንስሐ ይገቡ ዘንድ ጥሪ ባያደርግላቸው፥ ለሕዝቡ መሞት ተጠያቂ እንደሚያደርገው በመግለጽ ሕዝቅኤልን አስጠነቀቀው። የትንቢተ ሕዝቅኤል የመጀመሪያ ክፍል (ከምዕራፍ 1-14) የሚያተኩረው በዚህ ዓላማ ላይ ነው። የውይይት ጥያቄ፥ ሕዝቅኤል 3፡16-21 አንብብ። ሀ) እግዚአብሔር ለሕዝቅኤል የሰጠው ማስጠንቀቂያ ምን ነበር? ለ) ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር ለሆንን ለእኛም ይህ ማስጠንቀቂያ እውነት የሚሆነው እንዴት ነው? ) የበለጠ እንመሰክር ዘንድ ይህ እውነት ሊያበረታታን የሚገባው እንዴት ነው? መ) ብዙ ክርስቲያኖች የማይመሰክሩት ለምንድን ነው? እነዚህ ቍጥሮችስ ወንጌልን ለሌሎች በማካፈል የበለጠ ግልጽ ለመሆን የሚረዷቸው እንዴት ነው? 2. ሕዝቅኤል በኢየሩሳሌም ውድቀት ደስተኞች በነበሩና ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት በተባበሩ አሕዛብ ላይ የእግዚአብሔርን የፍርድ መልእክት ተናግሮ ነበር (ሕዝ. 25-32)። እግዚአብሔር በገዛ ሕዝቡ ላይ ቢፈርድም፥ አሕዛብ እውነተኛና ቅን ከሆነው ከእግዚአብሔር ፍርድ ተምረው ንስሐ መግባት ነበረባቸው። ነገር ግን የእግዚአብሔርን ሕዝብ በማጥፋት ተባበሩ ደስም አላቸው። ስለዚህ እግዚአብሔር እንደሚቀጣቸው ተናገረ። እነዚህ ትንቢቶች ከኢየሩሳሌም ውድቀት በኋላ አሕዛብ በውድቀቷ በሚደሰቱበት ጊዜ ወዲያውኑ የተፈጸሙ ናቸው። 3. ሕዝቅኤል ከኢየሩሳሌም ውድቀት በኋላ የእግዚአብሔርን የማበረታቻ መልእክት የሚናገር ሰው ነበር (ሕዝቅኤል 33-48)። እግዚአብሔር ምርኮውን የተጠቀመበት ሕዝቡን ለማጥፋት ሳይሆን ለማጥራት ነበር። የእግዚአብሔር ፍላጎት የአይሁድ ሕዝብ ከእንግዲህ የእርሱን በረከት አንቀበልም ብለው ተስፋ እንዲቆርጡ አልነበረም። ስለዚህ ሕዝቅኤል ስለ አይሁድ እንደገና መመለስ፥ ከዳዊት ዘር ስለሆነው እውነተኛ እረኛ (ኢየሱስ) አይሁድ እንደገና አንድ ስለሚሆኑበት ሁኔታና ምድራቸው ከኃጢአት ሁሉ ነጽታ በእውነት እግዚአብሔርን እንደሚያመልኩ ይነግራቸዋል። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) ወንጌልስ እንደዚሁ ፍርድ እንደሚመጣና በረከት እንዳለ የሚያበረታቱ የተስፋ ቃሎች ጥምረት የሆነው እንዴት ነው? ለ) ባለፈው ወር በቤተ ክርስቲያንህ ስለ ሰማሃቸው መልእክቶች አስብ። ከእነዚህ መልእክቶች መካከል የፍርድ መልእክት የነበሩት ምን ያህሉ ናቸው? የማበረታቻ መልእክት የነበሩትስ? ሐ) የፍርድን መልእክት ማወጅ ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ሕዝብ ማበረታታትም የሚጠቅመው ለምንድን ነው? በትንቢተ ሕዝቅኤል ውስጥ የሚገኝ የሥነ መለኮት ትምህርት  ትንቢተ ሕዝቅኤል ለመረዳት አስቸጋሪ በመሆኑ ምክንያት ብዙ ክርስቲያኖች ባያጠኑትም ጠቃሚ በሆኑ የሥነ መለኮት ትምህርት እውነቶች የተሞላ ነው። ከዚህ በመቀጠል በትንቢተ ሕዝቅኤል ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ጠቃሚ ትምህርቶችን እንመለከታለን፡- 1. ሕዝቅኤል እግዚአብሔር የሕዝቡንና የቀሩትን አሕዛብ ታሪክ በሙሉ የሚቆጣጠር መሆኑን በማሳየት፥ የእግዚአብሔርን ታላቅነትና ሉዓላዊነት ያስተምራል። በትንቢተ ሕዝቅኤል ውስጥ ከምናገኛቸው እጅግ ጠቃሚና አስፈላጊ ሐረጎች አንዱ፡- «እኔም እግዚአብሔር እንደሆንሁ ያውቃሉ» የሚለው ነው (ለምሳሌ፡- ሕዝ. 35፡15)። ይህ ሐረግ በመጽሐፉ ውስጥ 70 ጊዜ ያህል ተጠቅሷል። ይህ ሐረግ በአይሁድ ላይ ስለመጣው የእግዚአብሔር ፍርድና የእርሱን ማንነት ተገንዝበው በንስሐ ወደርሱ ስለ መመለሳቸው አስፈላጊነት ለማሳየትና እንዲሁም እግዚአብሔር የሚቀጣቸውን አሕዛብ በሚመለከት አገልግሎአል። እግዚአብሔር በአሕዛብ ላይ ያለው የበላይ ተቆጣጣሪነትና እነርሱን መቅጣቱ ሉዓላዊ አምላክ መሆኑን ለእነርሱ በተለይም ለራሱ ሕዝብ ለማሳየት ነው። እግዚአብሔር ወደፊት እስራኤልን እንደሚባርክ የተናገራቸው ትንቢቶች መፈጸማቸው እንደማይቀርና እርሱም ታላቁ የእስራኤል አምላክ ያህዌ መሆንን ለሁሉም ለማሳወቅ ነበር። የውይይት ጥያቄ፣ ሕዝቅኤል 1ን አንብብ። ይህ ራእይ የእግዚአብሔርን ታላቅነት እንዴት ያሳያል? ትንቢተ ሕዝቅኤል የእግዚአብሔርን ታላቅነትና ኃይል የሚያሳይበት ሌላ መንገድ አለ፤ ይህም፡- ሕዝቅኤል በሚያያቸው ራእዮች አማካይነት ነው። እነዚህ ራእዮች በምልክቶች የተሞሉ ናቸው። ብዙዎቹ ዓይኖች እግዚአብሔር በሰዎች ልብ ውስጥ የተሰወሩትን ነገሮች ሳይቀር፥ የሚፈጸሙትን ነገሮች በሙሉ የማየት ችሎታ እንዳለው የሚያመለክቱ ናቸው። መንኰራኵሮቹ እግዚአብሔር በሁሉም ስፍራ የሚገኝ መሆኑን ያመለክታሉ። እርሱ በተስፋይቱ ምድር በሚገኘው ቤተ መቅደስ ውስጥ ብቻ የተወሰነ አይደለም፤ ነገር ግን በምርኮ ምድር ከሚኖሩ አይሁድ ጋር ሳይቀር፥ በሁሉም ቦታ ይገኛል። እግዚአብሔር ለሕዝቅኤል በሰጣቸው ራእዮች ውስጥ ያሉ ነገሮች በሙሉ የእግዚአብሔርን ታላቅነት የሚገልጹ ናቸው። እነዚህ ራእዮች እግዚአብሔር ሕያውና ኃያል መሆኑን ለማሳየት ለሕዝቅኤልና ለእስራኤል በሙሉ የተሰጡ ናቸው። እርሱ ሰው እንደሚያውቀው እንደማንኛውም ነገር አይደለም። በሰማይ የሚነግሥ ታላቅ ግርማ ያለው አምላክ ነው። እርሱ ነገሮችን ሁሉ ማለት ሕዝቡን፥ የቀሩትን አሕዛብ ሁሉና፥ የአሁኑን ዘመን ፍርድና እንዲሁም የወደፊቱን የአይሁድ መመለስና በረከት ይቈጣጠራል። ስለ ሕዝቡ ሆኖ ያለ ማቋረጥ ይሠራል። የውይይት ጥያቄ፥ ክርስቲያኖች ይህን እውነት ሊረዱትና ከሕይወታቸው ጋር ሊያዛምዱት የሚያስፈልገው ለምንድን ነው? ይህ እውነት እንዴት እንዳበረታታህ ለማስረዳት አንዳንድ መግለጫዎችን ስጥ። 2. የእግዚአብሔር ክብርና ቅድስና፡- ሕዝቅኤል በራእዩ የእግዚአብሔርን ቅድስና አየ። የእግዚአብሔር የተቀደሰ ሕልውና ምልክት የክብር ደመና ነበር። እንደሚታወሰው፥ በአይሁድ ታሪክ ውስጥ ሁሉ ይህ የክብር ደመና እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የመኖሩ ምልክት ነበር። አይሁድ ይህን የክብር ደመና «የሺክናህ ክብር» በማለት ይጠሩታል። ይህ የክብር ደመና እስራኤላውያን ግብፅን ለቅቀው ሲወጡ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገለጠ ሲሆን፥ ለ40 ዓመታት በምድረ በዳ መርቶአቸዋል (ዘጸአት 40፡34-38)። ይህ የክብር ደመና በመጀመሪያ የመገናኛውን ድንኳን፥ በኋላ ደግሞ ቤተ መቅደሱ በተሠራ ጊዜ ቤተ መቅደሱን ሞልቶታል (1ኛ ነገሥት 8፡10-10። በትንቢተ ሕዝቅኤል ይህ የክብር ደመና ከቤተ መቅደሱ ተነሥቶ ወደ ምሥራቅ በር በመንቀሳቀስ፥ በመጨረሻ ከተማውን ለቅቆ ሲሄድ እንመለከታለን (ሕዝቅኤል 3ና 10)። ይህ ክብር በመጨረሻ ዘመን መሢሑ እንደገና እስኪመጣ ድረስ ወደ ኢየሩሳሌም አይመለስም (ሕዝቅኤል 43፡1-12)። እግዚአብሔር እስራኤልን ቅዱስ ሕዝቡ እንዲሆኑ አድርጎ ሲመርጣቸው በመካከላቸው ለማደር ፈልጎ ነበር። ቤተ መቅደሱ የእግዚአብሔር ዙፋን በእስራኤላውያን መካከል የመኖሩ ምልክት ሲሆን፥ ደመናው ደግሞ የሕልውናው ምልክት ነበር። በመጨረሻ ግን የሕዝቡ ኃጢአት እግዚአብሔርን ከዚህ ቤተመቅደስ አስወጣው። እግዚአብሔር ሕዝቡ እንደገና እንዲቀደሱና እርሱም በመካከላቸው ያድር ዘንድ በምርኮ ሊቀጣቸው ወሰነ። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) በአዲስ ኪዳንና በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕልውና የሚገለጽበት መንገድ የሚለያየውና የሚመሳሰለው እንዴት ነው? ለ) በአዲስ ኪዳን የእግዚአብሔር ክብር ምንድን ነው? ሐ) እግዚአብሔር ዛሬም በመካከላችን ሊያድር የሚፈልገው እንዴት ነው? መ) ንጹሐንና እርሱ ሊያድርብን የምንችል ሰዎች እንሆን ዘንድ እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ የሚቀጣን እንዴት ነው? እግዚአብሔር በአዲስ ኪዳን በውጭ የሚታይ የቤተ መቅደስ ሕንጻን በማደሪያነት መጠቀመን አቁሟል። ሕልውናውንም በክብር ደመና ውስጥ አያሳይም። ይልቁንም የእግዚአብሔር ማደሪያ የእያንዳንዱ አማኝ ልብ ሆኖአል። አማኞች የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሆነዋል (1ኛ ቆሮ. 6፡19)። በተጨማሪ የአማኞች ማኅበረሰብ ደግሞ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ናቸው (1ኛ ቆር. 3፡16)። እግዚአብሔር ሕዝቡ ቅዱስ እንዲሆን ይፈልጋል። ስለዚህ ልጆቹ ቅድስናቸውን ይጠብቁ ዘንድ ብዙ ጊዜ ይቀጣቸዋል። 4. ሕዝቅኤል ዘጠና ጊዜ «የሰው ልጅ» ተብሎ ተጠርቷል። እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን የጠራበት ተወዳጅ ስም ይህ ነበር። ይህ ማዕረግ በትንቢተ ዳንኤል ውስጥ ያተኮረው በመሢሑ ታላቅነት ላይ ሲሆን (ዳንኤል 7፡13)። በትንቢተ ሕዝቅኤል ግን ከእግዚአብሔርና ከመልእክቱ ታላቅነት በተቃራኒ በሕዝቅኤል ድካም ወይም ሰብአዊነት ላይ ያተኩራል። ኢየሱስ ራሱን «የሰው ልጅ» ብሎ ሲጠራ ምን ማለቱ እንደሆነ ምሁራን ዘወትር ይደነቃሉ። በሰብአዊነቱ ላይ አተኩሮ ነበር ወይስ እርሱ በትንቢተ ዳንኤል ውስጥ የተጠቀሰው የሰው ልጅ ፍጻሜ መሆኑ ነው? ምናልባት መልሱ ሁለቱም ሊሆን ይችላል። ኢየሱስ ፍጹም ሰው ነበር። ልክ እንደ እኛ ሥጋና ደም የነበረው ሲሆን፥ ኃጢአት ግን አልነበረበትም። እንዲሁም ከወንጌላት በግልጽ እንደምንመለከተው፥ ኢየሱስ በትንቢተ ዳንኤል የተጠቀሰው መሢሕ መሆኑን ያውቅ ነበር (ለምሳሌ፡- ማቴዎስ 24፡29-31)። ይህ ሐረግ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ሊያስታውሱትና በሕይወታቸው ሊጠቀሙበት የሚያስፈልግ ነው። የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ብዙ ጊዜ ልዩና ታላቅ እንደሆኑና ከፍተኛ ሥልጣን አለን ብለው ያስባሉ። ይሁን እንጂ እኛ የሰው ልጆች ሰብአዊ ፍጡራን ብቻ እንደሆንን ልናስታውስ ያስፈልገናል። አገልግሎታችን ወይም ስብከታችን ስኬታማ ቢሆንም በእኛ ምክንያት አይደለም፤ ይልቁንም በእኛ ውስጥና በእኛም አማካይነት ሊሠራ በመረጠን

የትንቢተ ሕዝቅኤል ዓላማ እና የሥነ መለኮት ትምሕርት Read More »

ትንቢተ ሕዝቅኤል በርካታ የሆኑ ልዩ ገጽታዎች እና አስተዋጽኦ

ትንቢተ ሕዝቅኤል በርካታ የሆኑ ልዩ ገጽታዎች አሉት፡- 1. ሕዝቅኤል ከማንኛውም የብሉይ ኪዳን ትንቢት መጻሕፍት በላቀ ሁኔታ (ለምሳሌ፡- ሕዝቅኤል 15 እና 16) በርካታ ምልክቶችንና ምሳሌዎችን ይጠቀማል። ለምሳሌ ሕዝቅኤል ብዙ አገሮችን በሕይወት እንዳሉ ፍጥረታት አድርጎ ያቀርባል። ኢየሩሳሌምና ሰማርያ በአመንዝራ ሴቶች፥ የዳዊት ንጉሣዊ የዘር ግንድ በአንበሳ ዋሻና በወይን ተክል፥ ግብፅ በአዞ፥ ባቢሎን ደግሞ በንሥር ተመስለው ቀርበዋል። 2. ሕዝቅኤል የነቢይነት መልእክቱን ለማስተላለፍ በአሁኑ ጊዜ በየአብያተ ክርስቲያናታችን እንደምናቀርባቸው ተውኔቶች (ድራማዎች) በተግባር በማሳየት ያቀርብ ነበር (ለምሳሌ፡- ሕዝቅኤል 3፡22-26፤ 4፡1-3)። እነዚህ በገቢር የሚታዩ ትዕይንቶች የፍርድን ቃል እየሰሙ ንስሐ እንዳይገቡ ልባቸውን ያጠነከሩትን አይሁድ ለማስደንገጥ የቀረቡ ነበሩ።  3. ሕዝቅኤል ጠንከር ያለና የሚያስቈጣ ቋንቋ በመጠቀም፥ ሕዝቡን በእግዚአብሔር አመለካከት ኃጢአት ምን ያህል ክፉ እንደሆነ ለማስገንዘብ ሊያስደነግጣቸው ይሞክር ነበር (ለምሳሌ፡- ኢየሩሳሌምን አመንዝራይቱ እያለ ይጠራታል)።  4. አብዛኛዎቹ የትንቢት መጻሕፍት የተጻፉት በግጥምና ቅኔ የአጻጻፍ ስልት ሲሆን፥ የትንቢተ ሕዝቅኤል አብዛኛው ክፍል ግን የተጻፈው በስድ ንባብ አጻጻፍ ስልት ነው።  5. ሕዝቅኤል መልእክቶቹን የተቀበለው በራእይ አማካይነት ነበር (ለምሳሌ፡- ሕዝቅኤል 1-3)። ከሕዝቅኤል በፊት ብዙ ነቢያት መልእክታቸውን በራእይ ሲቀበሉ አናይም። ራእይ ካላቸው ደግሞ ራእያቸው እንግዳ በሆኑ ተምሳሌቶች የተሞላ አልነበረም። ከሕዝቅኤል ጀምሮ ግን ነቢያት በብዙ ምልክቶች የተሞሉ ራእዮችን የመቀበል ዝንባሌያቸው ጨምሯል። የዚህ ዓይነቱ ትንቢት «አፓካሊፕቲክ» ትንቢት በመባል ይታወቃል። በዚህ ዓይነት ትንቢት ውስጥ ጨርሶ ያልተለመዱና በከፍተኛ ደረጃ ተምሳሌታዊ የሆኑ ራእዮች ይኖራሉ። በመንፈስ የሚደረጉ ጕዞዎች፥ የመላእክት ጐብኝት፥ እግዚአብሔር በሚሰጠው ፍርድ ወዘተ በተፈጥሮ ላይ ላለው የበላይ ተቁጣጣሪነት የሚሰጥ ትኩረት ይታያል። ከእንደነዚህ ዓይነት የትንቢት መጻሕፍት የሚመደቡት ሌሎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ዳንኤልና ዘካርያስ፥ ከአዲስ ኪዳን ደግሞ የዮሐንስ ራእይ ናቸው።  የትንቢተ ሕዝቅኤል አስተዋጽኦ 1. የሕዝቅኤል ለነቢይነት መጠራት (ሕዝ. 1-3)  2. በኢየሩሳለምና በይሁዳ ላይ የተነገሩ ትንቢቶች (ሕዝ. 4-24)፥  3. በተለያዩ የአሕዛብ መንግሥታት ላይ የተነገሩ ትንቢቶች (ሕዝ. 2532)፥  4. ስለ ወደፊቱ የእስራኤል መመለስ የተነገሩ ትንቢቶች (ሕዝ. 33-48)። (ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ.አይ.ኤም ከታተመውና የብሉይ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ እግዚአብሔር አገልግሎታቸውን ይባርክ፡፡)

ትንቢተ ሕዝቅኤል በርካታ የሆኑ ልዩ ገጽታዎች እና አስተዋጽኦ Read More »