2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች

2ኛ ቆሮ. 13:1-14

ሐዋርያው በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የመጨረሻ ሐሳቡን ይዘረዝራል። ይህ የጥናታችን መደምደሚያ ይሆናል፡፡ እግዚአብሔር በእነዚህ በሁለት መጽሐፎች ማለት በ1ኛና በ2ኛ ቆሮንቶስ ያስተማረን ብዙ ነገሮች አሉ። እነዚህን ራሳችን በሥራ ላይ እያዋልናቸው ለሌሎችም እንድናካፍል እግዚአብሔር ጸጋውን ይስጠን።  ይህ የጥናታችን የመጨረሻው ነው። በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ያሉት ሃሳቦች በፊት የተጠቀሱ ናቸው። ዋናው የምዕራፉ ነጥብ ሐዋርያው ለሦስተኛ ጊዜ ሊጎበኛቸው ሲሄድ ሁሉም ንስሐ …

2ኛ ቆሮ. 13:1-14 Read More »

2ኛ ቆሮ. 12:11-21

ጥያቄ 15. በቁጥር 11 ላይ «እናንተ እኔን ልታመሰግኑ ይገባ ነበርና» ሲል ምን ማለቱ ነው?  ጥያቄ 16. በቁጥር 13 «ይህን በደሌን ይቅር በሉኝ» ሲል ምን ማለቱ ነው? በደሉ ምን ነበር?  ጥያቄ 17. በቁጥር 16 ላይ «ነገር ግን ሸንጋይ ሆኜ በተንኮል ያዝኋችሁ» ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ አብራራ።  ጥያቁ 18. ከቁጥር 19 እስከ ቁጥር 21 ሐዋርያው ወደ ቆሮንቶስ …

2ኛ ቆሮ. 12:11-21 Read More »

2ኛ ቆሮ. 12:1-10

ጥያቄ 11. ከቁጥር 1-7 ባለው ክፍል ውስጥ ሐዋርያው ጳውሎስ የሚናገረው ስለማን ነው?  ጥያቄ 12. ከቁጥር 7-10 ባለው ክፍል ውስጥ ሐዋርያው በደረሰበት ችግር ምክንያት ምን ተማረ? እኛስ ከሐዋርያው ጳውሎስ ስለዚህ ዓይነት ነገር ምን ልንማር ይገባናል?  በዚህ ክፍል ውስጥ ሐዋርያው ጳውሎስ የሚናገረው ስለ ራሱ ነው፡፡ ሐሰተኛቹ አስተማሪዎች ስለራሳቸው ራእይ ብዙ በመናገር ራሳቸውን ከፍ ከፍ ሳያደርጉ አይቀሩም። ጳውሎስ …

2ኛ ቆሮ. 12:1-10 Read More »

2ኛ ቆሮ. 11:22-33

ጥያቄ 5. «ማንም በሚደፍርበት እኔ ደግሞ እደፍርበታለሁ» ሲል ምን ማለቱ ነው?  ጥያቄ 6. ከቁጥር 22-29 ድረስ በሦስት ዓይነት መንገዶች ሐዋርያው ትምክህቱን ይገልፃል፤ እነዚህ ሦስት መንገዶች ምንድናቸው?  በዚህ ክፍል ውስጥ ሐዋርያው ስለራሱ ትውልድና ስለአገልግሎቱ በመዘርዘር ትምክህት የሚገባ ቢሆን እርሱ የሚመካበት እንዳለው ይናገራል። የሚመካባቸው ሦስት ነገሮች አሉ፤ እነርሱም፡- እስራኤላዊነቱ፥ በክርስቶስ ወንጌል ምክንያት ብዙ መከራን መቀበሉና ስለራሱ ሳይሆን …

2ኛ ቆሮ. 11:22-33 Read More »

2ኛ ቆሮ. 11:16-21

ጥያቄ 1. በቁጥር 1 ላይ በሞኝነቴ ታገሡኝ ይላል፤ አሁን ደግሞ በቁጥር 16 ላይ “ለማንም ሞኝ የሆንሁ አይምሰለው” ሲል በሁለቱ መካከል አስታራቂ ሃሳብ ስጥ።  ጥያቄ 2. ሐዋርያው ደብዳቤዎቹን ይጽፍ የነበረው በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ነው፤ በቁጥር 17 ላይ ያለውን ንግግር ከዚህ ጋር አስታርቅ።  ጥያቄ 3. በቁጥር 20 የቆሮንቶስ ሰዎች ከሐሰተኛ አስተማሪዎች የተቀበሏቸውን ግፎች ይዘረዝራል፤ ምን ምን ናቸው?  …

2ኛ ቆሮ. 11:16-21 Read More »

2ኛ ቆሮ. 11:7-15

ጥያቄ 14. በቁጥር 10 ላይ «ይህ ትምክሕት» ሲል ስለምንድነው የሚናገረው?  ጥያቄ 15. ቁጥር 12 ላይ «ምክንያትን ከሚፈልጉቱ ምክንያትን እቆርጥ ዘንድ» የሚለውን አብራራ።  ጥያቄ 16. በቁጥር 13 ላይ ዋናው የሐሰተኛ አስተማሪዎች ፀባይ ምንድነው ይላል?  ከቁጥር 7-9፡- ሐዋርያው ወንጌልን በመስበክ የወንጌል ተገልጋዮች ሊደግፉት የተገባ እንደሆነና ይህንን መብቱን ግን እንዳልተጠቀመበት አስቀድሞ በ1ኛ ቆሮ. 9:1-18 ዘርዝሮአል። አሁን ደግሞ በተጨማሪ …

2ኛ ቆሮ. 11:7-15 Read More »

2ኛ ቆሮ. 11፡1-6

ጥያቄ 10. በቁጥር 1 ላይ «በጥቂቱ ሞኝነቴ ብትታገሡኝ መልካም ይሆን ነበር» ሲል ምን ማለቱ ነው?  ጥያቄ 11. በቁጥር 3 ላይ ሐዋርያው እባብ ሔዋንን እንዳሳታት እናንተም በመታለል እንዳትወሰዱ በማለት ሥጋቱን ይገልጣል፤ ይህ ሥጋቱ የተመሠረተው እምን ላይ በር?  ጥያቄ 12. በቁጥር 5 ላይ ዋነኞች ሐዋርያት የሚላቸው እነማንን ነው?  ቁጥር 1፡- «በጥቂት ሞኝነቱ ብትታገሡኝ» ሲል ሞኝነት ያለው ስለ …

2ኛ ቆሮ. 11፡1-6 Read More »

2ኛ ቆሮ. 10፡13-18

ጥያቄ 5. “እስከ እናንተ እንኳ እንደሚደርስ እንደ ክፍላችን ልክ እንጂ ያለልክ አንመካም” ማለት ምን ማለት ነው?  ጥያቄ 6. በቁጥር 16 ላይ “በሌላው ክፍል ስለተዘጋጀው አንመካም» ማለት ምን ማለት ነው?  ቁጥር 13:- ሐዋርያው አገልግሎቱን ለሩጫ እሸቅድድም እንደተሰለፈ ሰው ይመስላል፡፡ በሩጫ ሕጋቸው ለእያንዳንዱ ሯጭ መሥመር ይደለደል ነበር። በመሥመሩ ብቻ መሮጥ ነበረበት እንጂ በሌላ ሰው መሥመር ውስጥ ሾልኮ …

2ኛ ቆሮ. 10፡13-18 Read More »

2ኛ ቆሮ. 10:7-12

ጥያቄ 1. ቁጥር 7ን አብራራ።  ጥያቄ 2. በቁጥር 12 ላይ ጳውሎስ ራሱን ከአንዳንዶች ጋር ማወዳደር አልደፍርም ሲል ምን ማለቱ ነው? ከእነርሱ አንሳለሁ ማለቱ ነው? አብራራ።  ቁጥር 7:- “በፊታችሁ ያለውን ተመልከቱ”። በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ሾልከው የገቡት ሐሰተኛ አስተማሪዎች ጳውሎስን ሐሰተኛ ነው በማለት ይናገሩ ነበር። ለእነርሱ መልስ ሲሰጥ «ማንም በእርግጥ የክርስቶስ ከሆነ እኔ ደግሞ በክርስቶስ እንደሆንሁ ያውቅ …

2ኛ ቆሮ. 10:7-12 Read More »

2ኛ ቆሮ. 10፡1-6

ጥያቄ 15. በቁጥር 2 ላይ “በዚያ እምነት ግን ከእናንተ ጋር ሆኜ እንዳልደፍር አለምናችኋለሁ” ሲል ምን ማለቱ እንዳሆነ ይህን ክፍል በጥንቃቄ በመመልከት አስረዳ።  ጥያቄ 16. በቁጥር 3 ላይ ሐዋርያው በሰው ልማድ እመላለሳለሁ ሲል ምን ማለቱ ነው?  ጥያቁ 17. በቁጥር 2 ላይ ሁለት ወገኖች ተጠቅሰዋል፤ ማንና ማን ናቸው?  ቁጥር 1:- ሐዋርያው ስለመስጠት ያለውን ትምህርት ጨርሶ ሌላ ርዕስ …

2ኛ ቆሮ. 10፡1-6 Read More »