የሕይወት እንጀራ

መዝሙረ ዳዊት

መዝሙር 76-150

መዝሙር 76-100  መዝሙረ ዳዊትን በማንበብ በመንፈሳዊ ሕይወትህ እንደተባረክህ አምናለሁ። ባለፈው ሳምንት እንዳደረግነው፥ በዚህ ሳምንት መዝሙራት ምንም ማብራሪያ አንሰጥም። መዝሙራትን ሁሉ ስለ ማንበብህ እርግጠኛ ሁን። መዝሙራት የተጻፉት ለልባችን ለመናገር እንደሆነ አስታውስ። ስሜታችንን ለመቀስቀስ የተጻፉ ናቸው። መዝሙራትን በምታነብበት ጊዜ ጸሐፊው በግጥም ለመግለጥ የፈለገው ነገር በስሜትህ እንዲሠርጽ ፍቀድ።  የውይይት ጥያቄ፥ ባለፈው ሳምንት ስለ መዝሙራት የተመለከትነውን መግቢያ ከልስ።  የውይይት ጥያቄ፥ መዝሙር 76-100 አንብብ። ሀ) እነዚያ መዝሙራት እያንዳንዳቸው በየትኛው የመዝሙራት ዓይነት ውስጥ እንደሚመደቡ ጥቀስ። ለ) ጸሐፊው በመዝሙሩ ለመግለጽ የፈለገው ስሜት ምን ነበር? ሐ) እያንዳንዱ መዝሙር እግዚአብሔርን በተሻለ ሁኔታ ለመረዳትና በሙላት ለማምለክ እንዴት ይረዳናል? መ) አንድ መዝሙር ምረጥና በልብህ ውስጥ ያለውን ስሜት እንዴት እንደሚገልጥ አስረዳ። ሠ) ሌላ መዝሙር ምረጥና ስለ ራስህ ሕይወት የምታደርገውን ጸሎት እንዴት እንደሚገልጥ አስረዳ። ረ) በሚከተሉት መንገዶች ሊያገለግሉ የሚችሉ መዝሙራትን ዝርዝር አዘጋጅ፡-  1) በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እግዚአብሔርን በኅብረት ለማምለክ፣  2) በግል የጥሞና ጊዜህ እግዚአብሔርን ለማምለክ፣  3) ራስህንም ሆነ ሌላውን ሰው በብቸኝነት ጊዜ ለማበረታታት፣  4) በስደት ላይ የሚገኝ ሌላ ሰው ለማበረታታት፣  5) በጣም የታመመ ወይም ወደ ሞት የተቃረበ ሰው ለመርዳት።  ለእግዚአብሔር የሚቀርብ አምልኮ የሚገልጥ ሌላ መዝሙር ምረጥ። በዚህ መዝሙር ስለ እግዚአብሔር ባሕርያት የተዘረዘሩትን ነገሮች ሁሉ ጻፍ። ስለ እነዚህ ባሕርያት እግዚአብሔርን በጸሎትና በመዝሙር ለ15 ደቂቃዎች ያህል አምልከው።  መዝሙር 101-125 የውይይት ጥያቄ፥ መዝሙር 101-125 አንብብ። ሀ) ከእነዚህ መዝሙራት እያንዳንዳቸው በየትኛው የመዝሙራት ዓይነት ውስጥ እንደሚመደቡ ጥቀስ። ለ) ጸሐፊው በመዝሙሩ ለመግለጽ የፈለገው ስሜት ምን ነበር? ሐ) እያንዳንዱ መዝሙር እግዚአብሔርን በተሻለ ሁኔታ ለመረዳትና በሙላት ለማምለክ እንዴት ይረዳናል? መ) አንድ መዝሙር ምረጥና በልብህ ውስጥ ያለውን ስሜት እንዴት እንደሚገልጥ አስረዳ። ሠ) ሌላ መዝሙር ምረጥና ስለ ራስህ ሕይወት የምታደርገውን ጸሎት እንዴት እንደሚገልጥ አስረዳ። ረ) በሚከተሉት መንገዶች ሊያገለግሉ የሚችሉ መዝሙራትን ዝርዝር አዘጋጅ፡-  1) በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እግዚአብሔርን በኅብረት ለማምለክ፣  2) በግል የጥሞና ጊዜህ እግዚአብሔርን ለማምለክ፣  3) ራስህንም ሆነ ሌላውን ሰው በብቸኝነት ጊዜ ለማበረታታት፣  4) በስደት ላይ የሚገኝ ሌላ ሰው ለማበረታታት፣  5) በጣም የታመመ ወይም ወደ ሞት የተቃረበ ሰው ለመርዳት።  ለእግዚአብሔር የሚቀርብ አምልኮ የሚገልጥ ሌላ መዝሙር ምረጥ። በዚህ መዝሙር ስለ እግዚአብሔር ባሕርያት የተዘረዘሩትን ነገሮች ሁሉ ጻፍ። ስለ እነዚህ ባሕርያት እግዚአብሔርን በጸሎትና በመዝሙር ለ15 ደቂቃዎች ያህል አምልከው።  መዝሙር 126-150  የውይይት ጥያቄ፥ መዝሙር 126-150 አንብብ። ሀ) ከእነዚህ መዝሙራት እያንዳንዳቸው በየትኛው የመዝሙራት ዓይነት ውስጥ እንደሚመደቡ ጥቀስ። ለ) ጸሐፊው በመዝሙሩ ለመግለጽ የፈለገው ስሜት ምን ነበር? ሐ) እያንዳንዱ መዝሙር እግዚአብሔርን በተሻለ ሁኔታ ለመረዳትና በሙላት ለማምለክ እንዴት ይረዳናል? መ) አንድ መዝሙር ምረጥና በልብህ ውስጥ ያለውን ስሜት እንዴት እንደሚገልጥ አስረዳ። ሠ) ሌላ መዝሙር ምረጥና ስለ ራስህ ሕይወት የምታደርገውን ጸሎት እንዴት እንደሚገልጥ አስረዳ። ረ) በሚከተሉት መንገዶች ሊያገለግሉ የሚችሉ መዝሙራትን ዝርዝር አዘጋጅ፡-  1) በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እግዚአብሔርን በኅብረት ለማምለክ፣  2) በግል የጥሞና ጊዜህ እግዚአብሔርን ለማምለክ፣  3) ራስህንም ሆነ ሌላውን ሰው በብቸኝነት ጊዜ ለማበረታታት፣  4) በስደት ላይ የሚገኝ ሌላ ሰው ለማበረታታት፣  5) በጣም የታመመ ወይም ወደ ሞት የተቃረበ ሰው ለመርዳት።  ለእግዚአብሔር የሚቀርብ አምልኮ የሚገልጥ ሌላ መዝሙር ምረጥ። በዚህ መዝሙር ስለ እግዚአብሔር ባሕርያት የተዘረዘሩትን ነገሮች ሁሉ ጻፍ። ስለ እነዚህ ባሕርያት እግዚአብሔርን በጸሎትና በመዝሙር ለ15 ደቂቃዎች ያህል አምልከው።  (ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ.አይ.ኤም ከታተመውና የብሉይ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ እግዚአብሔር አገልግሎታቸውን ይባርክ፡፡)

መዝሙር 76-150 Read More »

መዝሙረ ዳዊት 1-75

መዝሙረ ዳዊት 1-25  የውይይት ጥያቄ፥ መዝሙር 1-25 አንብብ። ሀ) እነዚህ መዝሙራት እያንዳንዳቸው በየትኛው የመዝሙራት ዓይነት ውስጥ እንደሚመደቡ ጥቀስ። (ምሳሌ፡- የግል ምስጋና፥ ሰቆቃ፥ ጥበብ ወዘተ)። ለ) እያንዳንዱ መዝሙር እግዚአብሔርን በተሻለ ሁኔታ ለመረዳትና በሙላት እርሱን ለማምለክ እንዴት ይረዳናል? ሐ) አንድ መዝሙር ምረጥና በልብ ውስጥ ያለውን ስሜት እንዴት እንደሚገልጥ ተናገር። መ) ሌላ መዝሙር ምረጥና ያ መዝሙር ለራስህ ሕይወት የምታደርገውን ጸሎት እንዴት እንደሚገልጥ ተናገር። ሠ) በሚከተሉት መንገዶች አገልግሎት ላይ ሊውሉ የሚችሉትን መዝሙራት ዝርዝር አዘጋጅ፡-  1) በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እግዚአብሔርን በጋራ ለማምለክ  2) በግል የጥሞና ጊዚህ እግዚአብሔርን ለማምለክ፥  3) እራስህንም ሆነ ሌላን ሰው በብቸኝነት ጊዜ ለማበረታታት፡  4) በስደት ላይ የሚገኝን ሰው ለማበረታታት፥  5) በጣም የታመመ ወይም ለመሞት የተቀረበ ሰው ለመርዳት የሚያስችል።  ለእግዚአብሔር የሚቀርብ አምልኮን የሚገልጥ ሌላ መዝሙር ምረጥ። በዚህ መዝሙር ስለ እግዚአብሔር ባሕርያት የተዘረዘሩትን ነገሮች ሁሉ ጻፍ። ስለ እነዚህ ባሕርያት በጸሎትና በመዝሙር እግዚአብሔርን ለ15 ደቂቃዎች ያህል አምልከው።  መዝሙራት የተጻፉት ለልባችን እንዲናገሩ መሆኑን አስታውስ። ስሜታችንን ለመቀስቀስ የተጻፉ ናቸው። መዝሙራትን በምታነብበት ጊዜ ጸሐፊው በግጥም ለመግለጥ የፈለገው ነገር በስሜትህ እንዲሠርፅ አድርግ።  መዝሙር 26 – 50  የውይይት ጥያቄ፥ መዝሙር 26-50 አንብብ። ሀ) እነዚህ መዝሙራት እያንዳንዳችው በየትኛው የመዝሙራት ዓይነት ውስጥ እንደሚመደቡ ጥቀስ። ለ) ጸሐፊው በመዝሙሩ ለመግለጽ የፈለገው ስሜት ምን ነበር? ሐ) እያንዳንዱ መዝሙር እግዚአብሔርን በተሻለ ሁኔታ ለመረዳትና በሙላት እርሱን ለማምለክ እንዴት ይረዳናል? መ) አንድ መዝሙር ምረጥና በልብህ ውስጥ ያለውን ስሜት እንዴት እንደሚገልጥ አስረዳ። ሠ) ሌላ መዝሙር ምረጥና ይህ መዝሙር ለራስህ ሕይወት የምታደርገውን ጸሎት እንዴት እንደሚገልጥ አስረዳ። ረ) በሚከተሉት መንገዶች ሊያገለግሉ የሚችሉ መዝሙራትን ዝርዝር አዘጋጀ፡-  1) በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እግዚአብሔርን በኅብረት ለማምለክ፣  2) በግል የጥሞና ጊዜህ እግዚአብሔርን ለማምለክ፣  3) ራስህንም ሆነ ሌላውን ሰው በብቸኝነት ጊዜ ለማበረታታት፣  4) በስደት ላይ የሚገኝ ሌላ ሰው ለማበረታታት፣  5) በጣም የታመመ ወይም ወደ ሞት የተቃረበ ሰው ለመርዳት።  ለእግዚአብሔር የሚቀርብ አምልኮ የሚገልጥ ሌላ መዝሙር ምረጥ። በዚህ መዝሙር ስለ እግዚአብሔር ባሕርያት የተዘረዘሩትን ነገሮች ሁሉ ጻፍ። ስለ እነዚህ ባሕርያት እግዚአብሔርን በጸሎትና በመዝሙር ለ15 ደቂቃዎች ያህል አምልከው። መዝሙራት የተጻፉት ለልባችን ለመናገር እንደሆነ አስታውስ። ስሜታችንን ለመቀስቀስ የተጻፉ ናቸው። መዝሙራትን በምታነብበት ጊዜ ጸሐፊው በግጥም ለመግለጥ የፈለገው ነገር በስሜትህ እንዲሠርጽ ፍቀድ።  መዝሙር 51-75  የውይይት ጥያቄ፥ መዝሙር 51-75 አንብብ። ሀ) እነዚህ መዝሙራት እያንዳንዳቸው በየትኛው የመዝሙራት ዓይነት እንደሚመደቡ ዘርዝር። ለ) ጸሐፊው በመዝሙሩ ለመግለጽ የፈለገው ስሜት ምን ነበር? ሐ) እያንዳንዱ መዝሙር እግዚአብሔርን በተሻለ ሁኔታ ለመርዳትና በሙላት ለማምለክ እንዴት ይረዳናል? መ) አንድ መዝሙር ምረጥና በልብህ ውስጥ ያለውን ስሜት እንዴት እንደሚገልጥ አስረዳ። ሠ) ሌላ መዝሙር ምረጥና ለራስህ ሕይወት የምታደርገውን ጸሎት እንዴት እንደሚገልጥ አስረዳ። ረ) በሚከተሉት መንገዶች ሊያገለግሉ የሚችሉ መዝሙራትን ዝርዝር አዘጋጅ፡-  1) በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እግዚአብሔርን በኅብረት ለማምላክ፥  2) በግል የጥሞና ጊዜህ እግዚአብሔርን ለማምለክ፥  3) ራስህንም ሆነ ሌላውን ሰው በብቸኝነት ወቅት ለማበረታታት፥  4) በስደት ላይ የሚገኝን ሰው ለማበረታታት፥  5) በጽኑ የታመመ ወይም ሊሞት የተቃረበ ሰውን ለመርዳት።  ለእግዚአብሔር የሚቀርብ አምልኮ የሚገልጥ ሌላ መዝሙር ምረጥ። በዚህ መዝሙር ስለ እግዚአብሔር ባሕርያት የተዘረዘሩትን ነገሮች ሁሉ ጻፍ። ስለ እነዚህ ባሕርያት እግዚአብሔርን በጸሎትና በመዝሙር ለ15 ደቂቃዎች ያህል አምልከው። መዝሙራት የተጻፉት ለልባችን ለመናገር እንደሆነ አስታውስ። ስሜታችንን ለመቀስቀስ የተጻፉ ናቸው። መዝሙራትን በምታነብበት ጊዜ ጸሐፊው በግጥም ለመግለጥ የፈለገው ነገር በስሜትህ እንዲሠርጽ ፍቀድ።  (ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ.አይ.ኤም ከታተመውና የብሉይ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ እግዚአብሔር አገልግሎታቸውን ይባርክ፡፡)

መዝሙረ ዳዊት 1-75 Read More »

የመዝሙረ ዳዊት ዓላማ እና ልዩ የሚያደርጉት ነገሮች

የመዝሙረ ዳዊት ዓላማ  እያንዳንዱ መዝሙር የተለያየ ዓላማ ያለው ቢሆንም እንኳ መዝሙረ ዳዊት የመዝሙር መጽሐፍ እንዲሆን ተደርጎ መሰብሰቡን ማስታወስ ጠቃሚ ነው፡፡ አይሁድ ከምርኮ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው ቤተ መቅደሱን እንደገና ከገነቡ በኋላ (በ520 ዓ.ዓ.) እነዚህ መዝሙራት በአይሁድ የአምልኮ ፕሮግራም ውስጥ ተካትተው ነበር። አይሁድ በቤተ መቅደስና በምኲራቦቻቸው እግዚአብሔርን በሚያመልኩበት ጊዜም ይጠቀሙባቸው ነበር። እነዚህ መዝሙራት በጥንት ቤተ ክርስቲያን የአምልኮ ጊዜ ያገለግሉ ነበር።  መዝሙረ ዳዊት በመሠረቱ ወደ እግዚአብሔር የሚደረግ ጸሎትና ለእግዚአብሔር የሚቀርብ ምስጋና ያለበት መጽሐፍ ነው። የመጽሐፉ ትኲረት ሁልጊዜ ከእግዚአብሔርና ከልጆቹ ጋር ባለው ግንኙነት ላይ ነው፡፡ በየመዝሙራቱ ላይ የተጻፉ ርእሶች  እንደ ቀድሞው የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ባለ፥ በአብዛኛው መጽሐፍ ቅዱስ ትርጕም፥ ውስጥ ለአብዛኛዎቹ መዝሙራት የተሰጡ አርእስት አሉ። ሆኖም እነዚህ ርእሶች መዝሙራቱ በመጀመሪያ በተጻፉበት ወቅት ስለ መሰጠታቸው፤ ምሁራን ይከራከራሉ። ከ150 መዝሙራት መካከል 116ቱ በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ርእሶች አሏቸው። ርእሶቹ ከሚከተሉት አንዱን ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ነገሮችን የሚገልጹ ናቸው:-  1. ጸሐፊው ማን እንደነበር፥  2. ምን ዓይነት መዝሙር እንደሆነ (ለምሳሌ፡- ኃዘን፥ ምስጋና ወዘተ)፥  3. በምን ዓይነት የሙዚቃ መሣሪያ ይዘመር እንደነበር፥  4. በአምልኮ ጊዜ ውስጥ እንዴት አገልግሎት ላይ መዋል እንዳለበት፥  5. መዝሙራቱን ለማዘጋጀት ጸሐፊውን ያነሣሣው ታሪካዊ ድርጊት።  መዝሙረ ዳዊትን ልዩ የሚያደርጉት ነገሮች፡-  1. ከአብዛኛዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በተለየ ሁኔታ ይህ መጽሐፍ የተጻፈው ለልባችንና ለስሜታችን ይናገር ዘንድ ነው። ጸሐፊው ያለፈበትን፥ ለእግዚአብሔር የነበረውን ከፍተኛ ፍቅርና ውዳሴ እንድንለማመድ የተጻፈ ነው። በኃጢአት ወይም በጠላቶቹ በሚሸነፍበት ጊዜ ተሰምቶት የነበረውን የተስፋ መቍረጥ ስሜት እንድንለማመድ በሚያደርግ መንገድ የተጻፈ ነው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር እንዴት ይቅር እንዳለው ወይም በጠላቶቹ ላይ ድልን እንደሰጠው በምናነብበት ጊዜ ልባችን ይነቃቃል።  2. አብዛኛውን የዚህን መጽሐፍ ክፍል ለመረዳት የሚያስችል መሠረታዊ ነገር እግዚአብሔር ጻድቃንን እንደሚባርክና ኃጢአተኞችን ደግሞ እንደሚቀጣ የሚናገረው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ነው። ከመጽሐፈ ኢዮብ ጥናታችን እንደተረዳነው እግዚአብሔር የሚያከብሩትንና የሚታዘዙትን እንደሚባርክ የማይታዘዙትን ደግሞ እንደሚቀጣ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስተምራል። ነገር ግን አይሁድ ይህንን ትምህርት ከመጠን በላይ በማስፋት፥ አንድ ሰው ባለጠጋ ከሆነ ይህ ጻድቅ የመሆኑና እግዚአብሔር በእርሱ ደስ የመሰኘቱ ምልክት እንደሆነ፥ መከራና ሥቃይ ከደረሰበት ደግሞ የእግዚአብሔር የፍርድ ምልክት እንደሆነ ይመስላቸው ነበር። የበረከቱ ወይም የመከራው መጠን ሰውዬው ምን ያህል ጻድቅ ወይም ኃጢኣተኛ መሆኑን የሚያሳይ ይመስላቸው ነበር። መጽሐፈ ኢዮብ የተጻፈው ይህንን አሳብ ለመቃወም ነበር።  በብሉይ ኪዳን ውስጥ ስለ መንግሥተ ሰማያትና ስለ ገሃነም የሚያስተምር ግልጽ ነገር አልነበረም። እግዚአብሔር ይህንን በግልጽ ያሳየው በአዲስ ኪዳን ዘመን ነው። ስለዚህ እግዚኣብሔር በረከቱንና ፍርዱን የሚገልጸው ሰው በሕይወት እያለ ብቻ ሳይሆን፥ ከሞተ በኋላም ሊገልጽ እንዳለው አይሁድ አልተረዱም ነበር። ስለዚህ አይሁድ ሰው በሕይወት እያለ እግዚአብሔር ጻድቅ ፍርዱን ወዲያውኑ በመስጠት ጻድቁን እንደሚባርከና ኃጢአተኛውን የሚቀጣ ይመስላቸው ነበር፡፡  አይሁድ እግዚአብሔር ኃጢአተኛ ሰውን ወዲያውኑ እንዲቀጣ የነበራቸው ፍላጎት በተለይ የሚታየው ጸሐፊዎቹ እግዚአብሔር ክፉዎችን እንዲደመስሥ በሚለምኑበት ክፍል ነው (መዝሙር [28]፡ 4፤ [137]፡9)። ኢየሱስ ጠላትን መውደድ እንደሚገባ (ማቴዎስ 5:43-48) ካስተማረው የሚቃረኑ ስለሚመስሉ እዚህን መዝሙራት መረዳት ለክርስቲያኖች አስቸጋሪ ነው። ዳሩ ግን በእነዚህ ሙዝሙራት ውስጥ የጸሐፊዎቹ ትኵረት በእግዚአብሔር ጻድቅ ፈራጅነት ላይ ነበር። እግዚአብሔር የራሱንና የልጆቹ ጠላቶች የነበሩትን በመቅጣት፥ ቅን ፍርዱን እንዳያሳይ ታማኝ የሆኑ ሰዎችንም እንዲባርክ ይፈልጉ ነበር።  መዝሙረ ዳዊት የሚያስተምረው በዚህ ሕይወት እግዚአብሔር ድቃንን ለመባረክና ኃጥአንን ለመቅጣት ዝንባሌ ያለው መሆኑን ነው፤ ነገር ግን ይህ ሁሉንም ሰው በሁሉም ጉዳይ የሚመለከት አንደሆነ ጨርሶ አልተነገረም። ስለዚህ እነዚህን ዝንባሌዎች ማለትም ጻድቅ ሰው ክፋት እንደማይደርስበት ወይም ኃጢአተኞች ወዲያውኑ እንደሚፈረድባቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደተሰጡ የተስፋ ቃሎች አድርገን መውሰድ የለብንም። በተለየ ሁኔታ ውስጥ እግዚአብሔር አንድን ሰው ማበልጸጉ ወይም ነፃ ማውጣቱ ምን ማድረግ እንደሚችል የሚያሳይ ምስክር እንጂ ሁልጊዜ የሚያደርገው ነገር ነው ማለት አይደለም። እነዚህን መዝሙራት እንዴት እንደምንተረጕማቸውና ከሕይወት ጋር እንደምናዛምዳቸው መጠንቀቅ አለብን። ይህም እነዚህን መዝሙራት በተሳሳተ መንገድ በመተርጐም፥ እግዚአብሔር ሁልጊዜ ከማናቸውም ጉዳት እንደሚጠብቀን አድርገን እንዳናስብ ያደርገናል። ከመጽሐፍ ቅዱሳችን በግልጽ እንደምንመለከተው፥ እግዚአብሔር ብዙውን ጊዜ መከራ እንድንቀበል ይፈቅዳል። በምድር ላይ የምንጠብቃችወ ሥጋዊ የሆኑ በረከቶችን ሳናገኝ እንድንሞት እንኳ ሊያደርግ ይችላል። ክርስቲያኖች እንደመሆናችን ስለ በረከትና ቅጣት የተነገረው ይህ መንፈሳዊ እውነት በዘላለማዊ መንግሥት ውስጥ ተግባራዊ እንደሚሆን እናውቃለን። እግዚአብሔር ታማኝ የሆኑትን ሰዎች ይባርካችዋል። (ማቴዎስ 9፡20-21፣ 1ኛ ቆሮንቶስ 3፡12-15)። ክፉችን ደግሞ ይቀጣል (ራዕይ 20፡13-15)። ይህ እውነት ግን በምድር ላይ እያለን ሁልጊዜ  አይታይም።  የውይይት ጥያቄ፦ ጻድቃን መከራ እንዲቀበሉና እንዲጐሳቈሉ እግዚአብሔር እንደሚፈቅድ፥ ክፉና ኃጢአተኞች የሆኑትን ሰዎች ወዲያውኑ እንደማይቀጣ የሚለው እውነታ ከብዙ ክርስቲያኖች አስተሳሰብ የሚለየው እንዴት ነው?  3. ከመዝሙራት ውስጥ ዘጠኙ የሚናገሩት ስለ እስራኤል ነገሥታት ነው። ከእነዚህ አብዛኛዎቹ በዳዊት የተጻፉ ወይም ስለ ዳዊትና ስለ ልጆቹ የተጻፉ ናቸው። መዝሙሮቹ በመጀመሪያ የሚናገሩት ፍጹም የሆነ የእስራኤል ንጉሥ ምሳሌ ስለሆነው ስለ ዳዊት ነው። አንዳንዶቹ ደግሞ በእግዚአብሔር ምሪት፥ ዋናውና ከዳዊት ዘር ስለሆነው ፍጹም ንጉሥ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ይናገራሉ። ከእነዚህ መዝሙራት ውስጥ ብዙዎቹ ሁለት ትርጕም አላቸው ለማለት እንችላለን። በመጀመሪያ ደረጃ፥ ስለ ዳዊት ወይም ስለ ሌሎቹ የእስራኤል ነገሥታት ይናገራሉ። በሁለተኛ ደረጃ፥ ደግሞ ስለ ኢየሱስ ይናገራሉ።  የውይይት ጥያቄ፥ የሚከተሉትን ስለ ኢየሱስ የተነገሩ ትንቢቶች ከፍጻሜያቸው ጋር አወዳድር። በመዝሙራት ውስጥ የሚገኘው እያንዳንዱ ትንቢት በኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት እንደተፈጸመ ዘርዝር።  ሀ. መዝሙር 2፡7- ዕብራውያን 1፡5  ለ. መዝሙር (16)፡9-10 – ሐዋርያት ሥራ 2፡31-32  ሐ. መዝሙር (22)፡1 – ማቴዎስ 27፡46  መ. መዝሙር 40፡6-8 – ዕብራውያን 10፡9  ሠ. መዝሙር (41)፡9 – ዮሐንስ 13፡18  ረ. መዝሙር(45)፡6 – ዕብራውያን 1፡8  ሰ. መዝሙር(110)፡1 – ማቴዎስ 22፡43-45  ሸ. መዝሙር(110)፡4 – ዕብራውያን 7:17  ቀ. መዝሙር(118)፡22-23 – ማቴዎስ 21፡42  አዲስ ኪዳን ከሌላ ከማንኛውም የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ይልቅ ከፍተኛ ደረጃ የጠቀሰው ከመዝሙረ ዳዊት ነው።  የውይይት ጥያቄ፥ ደምቀው የቀረቡትን ቃሎች ከመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ተመልከት። ከዚያም በመዝሙረ ዳዊት በቀረቡበት አኳኋን ተርጒማቸው። እግዚአብሔር ከእነዚህ ተምሳሌቶች አንዱን እንዴት በሕይወትህ እንደፈጸመ አሳይ፡-  ሀ. እግዚአብሔር ዓለታችን ነው።  ለ. እግዚአብሔር አምባችን ነው።  ሐ. እግዚአብሔር እረኛችን ነው።  መ. እግዚአብሔር ጋሻችን ነው።  ሠ. እግዚአብሔር መሸሽጊያችን ነው።  ረ. እግዚአብሔር የደኅንነታችን ቀንድ ነው።  (ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ.አይ.ኤም ከታተመውና የብሉይ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ እግዚአብሔር አገልግሎታቸውን ይባርክ፡፡) የመመዘኛ ጥያቄዎችን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ (መስፈንጠሪያ) ይጫኑ፡፡

የመዝሙረ ዳዊት ዓላማ እና ልዩ የሚያደርጉት ነገሮች Read More »

የመዝሙረ ዳዊት መግቢያ

ከቤተ ክርስቲያን የጥንት ጽሑፎች መካከል አንዱ የሆነው «ዌስትሚኒስተር ሾርተር ካታኪዝም» የተሰኘው አጭር የክርስትና ትምሕርት መጽሐፍ “የሰው ልጅ ዋና ፍጻሜ (ዓላማ) ምንድን ነው?” በሚል ጥያቄ ይጀምራል።  የውይይት ጥያቄ፥ ይህን ጥያቄ እንዴት ትመልሰዋለህ?  ይህንን ጥያቄ በተለያየ መንገድ ለመመለስ ብንችልም፥ የክርስትና ትምህርት መጽሐፍ (ካታኪዝም) ጸሐፊዎች ግን በዚህ መልኩ መልሰውታል፡- «የሰው ልጅ ዋና ዓላማ እግዚአብሔርን ማክበርና በእርሱ ደስ ተሰኝቶ መኖር ነው።» እግዚአብሔርን ከምናከብርባቸው ዐበይት መንገዶች አንዱ እርሱን ማምለክ ነው። እግዚአብሔር፥ እርሱን በሚያከብር መንገድ እናመልከው ዘንድ ካዘጋጀልን እጅግ ጠቃሚ  መሣሪያዎች አንዱ መዝሙረ ዳዊት ነው። መዝሙረ ዳዊት በችግር ላይ በምንሆንበት ጊዜ እንዴት ወደ እግዚአብሔር መጸለይ እንዳለብን ያስተምረናል። እግዚአብሔርን እንዴት እንደምናመልክም ያስተምረናል። የመዝሙረ ዳዊትን መጽሐፍ ለኅብረት አምልኮአችንም ሆነ በግል የጸሎት ጊዜያችን መጠቀም አለብን።  መዝሙረ ዳዊት እጅግ ተወዳጅና ተነባቢ ከሆኑት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አንዱ ነው። ከየትኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት በላይ  መዝሙረ ዳዊት የልባችንን ስሜቶች በግልጽ ያንጸባርቃል። በመዝሙረ ጻዊት ውስጥ ፍርሃት፥ ጥላቻ፥ ፍቅር፥ አምልኮ፥ ምስጋና ደስታ ወዘተ የመሳሰሉ ሰው የሚያዘወትራቸው ስሜቶች ሁሉ ተገልጸዋል፤ ስለዚህ ሰው የየትኛውም ነገድ አባል ይሁን እነዚህ መዝሙሮች ስሜቱንና አስተሳሰቡን ሊገልጹለት ይችላሉ።  የውይይት ጥያቄ፦ ሀ) ለአንተ እጅግ ተወዳጅ የሆነው የመዝሙረ ዳዊት ክፍል የቱ ነው? ለ) ይህን ከፍል የምትወደው ለምንድን ነው?  ሐ) በዚያ መዝሙር ውስጥ ከሁሉም በላቀ ሁኔታ የተገለጸው ስሜት የትኛው ነው?  መዝሙረ ዳዊት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካለ ከማንኛውም መጽሐፍ የተለየ ነው። እስራኤላውያን እግዚአብሔርን በሚያመልኩበት ጊዜ ወደሚዘምሩት መዝሙራት የተለወጡ በርካታ ግጥሞችና ቅኔዎች ያሉበት መጽሐፍ ነው። ብዙ የተለያዩ ጸሐፊዎች ያዘጋጁት መዝሙረ ዳዊት አሁን ያለበትን መልክ ለመያዝ አንድ ሺህ ዓመታት ወስዶበታል። እያንዳንዱ የመዝሙረ ዳዊት ክፍል ራሱን የቻለ በመሆኑ፥ መጽሐፉን አጣምሮ የሚይዝ አንድ መሪ አሳብ ወይም ዓላማ የለውም። ይልቁንም የተለያዩ መዝሙሮች ያሉበት አንድ ትልቅ የመዝሙር መጽሐፍ አድርገን ልንቆጥረው ይገባናል።  የመዝሙረ ዳዊት ርእስ  የውይይት ጥያቄ፥ ይህ መጽሐፍ በአማርኛ መዝሙረ ዳዊት ለምን ተባለ?  ብዙውን ጊዜ ስለ መዝሙረ ዳዊት ጸሐፊ ስናስብ ወደ አእምሮአችን የሚመጣው ዳዊት ነው። አብዛኛው የመዝሙረ ዳዊት ክፍል በዳዊት እንደተጻፈ የተረጋገጠ ቢሆንም፥ በሌሎች ጸሐፊዎች የተጻፉ በርካታ መዝሙራትም አሉ፤ ስለዚህ ይህንን መጽሐፍ «መዝሙረ ዳዊት» ብለን መሠየም ትክክል አይደለም። «መዝሙራት» ወይም አይሁድ እንደሠየሙት «የምስጋና መዝሙራት» ሊባል ይገባል። ብዙዎቹ መዝሙራት የተጻፉት እግዚአብሔርን ለማመስገን እንደሆነ ይህ ርእስ ይገልጻል።  የመዝሙረ ዳዊት ጸሐፊ  ስለ መዝሙረ ዳዊት ጸሐፊ በምንናገርበት ጊዜ፥ መዝሙረ ዳዊት በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ከሚገኙ ከሌሎች መጻሕፍት ሁሉ የተለየ መሆኑን እንመለከታለን። የአንድ ጸሐፊ የሥራ ውጤት ከመሆን ይልቅ በመቶ ዓመታት ልዩነት የኖሩ የብዙ ጸሐፊዎች የሥራ ውጤት ነው። ስለ መዝሙረ ዳዊት ዝግጅት በምንነጋገርበት ጊዜ ሁለት ጥያቄዎችን መጠየቅ ያስፈልገናል፡- በመጀመሪያ፥ በመጽሐፉ ውስጥ ያሉትን መዝሙራት በተናጠል የጻፋቸው ማን ነው? የሚል ሲሆን፤ ሁለተኛው፥ ደግሞ መዝሙራቱን በሙሉ ሰብስቦ በአንድ መጽሐፍ የጠረዛቸው ማን ነው? የሚል ይሆናል። መዝሙረ ዳዊትን አቀነባብሮ ያዘጋጀው ማን ነው?  በመዝሙረ ዳዊት ውስጥ ከምናገኛቸው 150 መዝሙራት መካከል 100ዎቹ መዝሙራት በማን እንደተጻፉ ይናገራሉ። ይህ ማለት የ50 መዝሙራት ጸሐፊ ማን እንደነበረ አናውቅም ማለት ነው፡፡ ከ 150 መዝሙራት መካከል 73 መዝሙራት የተጻፉት በዳዊት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ከሌሉቹ ጸሐፊዎች ሁሉ ይልቅ ብዙ መዝሙራትን የጻፈው ዳዊት ነው ማለት ነው። ነገር ግን ሙሴ (መዝሙር 90)፥ ሰሎሞን (መዝሙር 72፤127)፣ አሳፍ (መዝሙር 50)፥ ኤማን (መዝሙር 88)፣ ኤታን (መዝሙር 89) እንዲሁም የቆሬ ልጆች (መዝሙር 42፣ 44-49) የመዝሙር ጸሐፊዎች ነበሩ።  እርግጠኞች ለመሆን ባንችልም እንኳ መዝሙረ ዳዊት አሁን ባለበት መልኩ ተሰብስቦ የተደራጀው በ400 ዓ.ዓ. ይመስላል። የመዝሙረ ዳዊት የመጀመሪያ ዋና ክፍል የተሰበሰበው በዳዊት ዘመን ሳይሆን አይቀርም። ዳዊት የመዝሙራት ዋና ጸሐፊ ነው (1ኛ ዜና 15-16)። ከዚህ የላቀው የዳዊት አስተዋጽኦ፥ መዝሙራት በአይሁድ የአምልኮ ሥርዓት እንዲለመዱ ማስጀመሩ ነበር (1ኛ ዜና 6፡31)። ከዳዊት ጊዜ ጀምሮ አይሁድ ከምርኮ እስከተመለሱበት እስከ 539 ዓ.ዓ. ድረስ የተለያዩ ግለሰቦች እግዚአብሔርን የማምለኪያ መዝሙራት መጻፍ ቀጥለው እንደነበር ጥርጥር የለውም። አንድ ያልታወቀ ሰው እስከዚያ ጊዜ ድረስ የነበሩትን መዝሙራት ሁሉ ሰብስቦ በልዩ ቅደም ተከተል እስካስቀመጠበት እስከ 400 ዓ.ዓ. ድረስ መሰብሰባቸውን ቀጥለው ነበር። ከዚያ በኋላ ይህ መጽሐፍ «መዝሙር» በመባል ታወቀ።  የመዝሙረ ዳዊት ቅንብር (አስተዋጽኦ)  መዝሙረ ዳዊት 150 ልዩ ልዩ መዝሙራትን ይዟል። ሆኖም ግን የተለያዩ ትርጕሞች እነዚህ 150 መዝሙራት የትኞቹ እንደሆነና አከፋፈላቸውንም በሚመለከት ይለያያሉ። የእንግሊዝኛው መጽሐፍ ቅዱስ የዕብራይስጡን መጽሐፍ ቅዱስ አከፋፈል ይከተላል፡፡ የእንግሊዝኛው መጽሐፍ ቅዱስ አከፋፈል በአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ በቅንፍ ውስጥ የሚገኘው ነው፡፡ የቀድሞው የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጕም የምዕራፍ አከፋፈሉን የወሰደው ከግሪኩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጒም ነው። በግሪኩ መጽሐፍ ቅዱስ (እንዲሁም አማርኛ) መዝሙር 9እና 10 እንዲሁም መዝሙር 114 እና 115 እንደ አንድ መዝሙር ተዋሕደው ቀርበዋል፤ ዳሩ ግን ቀድሞ አንድ መዝሙር የነበሩት 116 እና 147 እያንዳንዳቸው ለሁለት መዝሙራት ተከፍለዋል። በግሪኩ መጽሐፍ ቅዱስ በድምሩ 150 መዝሙራት ለማድረግ በተጨማሪ አንድ ሌላ መዝሙር አክለዋል።  ከጥንት ጀምሮ መዝሙረ ዳዊት በአምስት ትናንሽ መጽሐፍት ተከፍሏል፡፡ 1ኛ መጽሐፍ፡- መዝሙር 1-41 (በአብዛኛው የዳዊት መዝሙራት ናቸው)።  2ኛ መጽሐፍ፡- መዝሙር 42-72 (በአብዛኛው የዳዊትና የቆሬ ልች መዝሙራት ናቸው)።  3ኛ መጽሐፍ፡- መዝሙር 73-89 (በአብዛኛው የአሳፍ መዝሙራት ናቸው)።  4ኛ መጽሐፍ፡- መዝሙር 90-106 (በአብዛኛው ጸሓፊያቸው የማይታወቅ መዝሙራት ናቸው)፡፡  5ኛ መጽሐፍ፡- 107-150 (በአብዛኛው የዳዊት መዝሙራት ናቸው)፡፡  እነዚህ አምስት መጻሕፍት እያንዳንዳቸው እግዚአብሔር ስለ ታላቅነቱ በማወደስ በምስጋና መዝሙር የሚጠቃለሉ ናቸው።  አንዳንድ ምሁራን 1ኛ መጽሐፍ በሰሎሞን ወይም በዳዊት (መዝሙር 72፡20)፣ 2ኛና 3ኛ መጻሕፍት በ710 ዓ.ዓ. በንጉሥ ሕዝቅያስ (2ኛ ዜና 29፡30)፥ 4ኛና 5ኛ መጻሕፍት በ430 ዓ.ዓ. በዕዝራ እንደተሰበሰቡ ያስባሉ። ሆኖም ይህን በሚመለከት የተጨበጠ ማረጋገጫ የለም።  ምናልባት ከ1ኛ-3ኛ ያሉት መጻሕፍት ከ4ኛና 5ኛ መጻሕፍት በፊት ሳይሆኑ አይቀሩም። እጅግ ጥንታዊ በሆኑ ረቂቅ ጽሑፎች ሁሉ ውስጥ ከ1ኛ-3ኛ ያሉት መጻሕፍት በአሁኑ ወቅት በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ባሉበት መልክ ተቀምጠው ነበር፤ ዳሩ ግን በ4ኛና በ5ኛ ውስጥ መጻሕፍት ውስጥ የበርካታ ልዩነቶች መኖር፥ ዘግይተው መሰብሰባቸውን የሚጠቁም ነው።  ብዙ ምሁራን በመዝሙረ ዳዊት ውስጥ አምስት መጻሕፍት መኖራችው፥ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት መሠረት የሆኑት የሙሴ መጻሕፍት አምስት መሆናቸውን የሚያንጸባርቅ ነው ብለው ያስባሉ።  በርካታ ምሁራን፥ መዝሙረ ዳዊትን በመጨረሻ ያቀናበረው ሰው፣ አሠራሩ ለአንድ ልዩ የሥነ-መለኮት ዓላማ እንደሆነ ያስባሉ። መዝሙራቱ ግልጽ የሆነ አንድ አካሄድ ስለሌላችው፥ ይህን የሥነ-መለኮት ትምህርት ዓላማ መወሰን አስቸጋሪ ነው። ቀጥሉ በአንድ ምሁር ግምት የመዝሙረ ዛዊት አጠናቃሪ የሆነ ሊቅ መዝሙረ ዳዊትን እንዴት እንዳቀናበረው እንመለከታለን፡-  1. የመዝሙረ ዳዊት መግቢያ (መዝሙር 1-2)  ሀ. መዝሙር 1 – እግዚአብሔር የጻድቅን ሰው ጽድቅ ያረጋግጣል  ለ. መዝሙር 2 – እግዚአብሔር የእስራኤልን ንጉሥ ይመርጣል፤ ይከላከልለታልም።  2. ዳዊት ከሳኦል ጋር ስለነበረው ግጭት የሚናገሩ መዝሙራት (መዝሙር 3-41)  3. ስለ ዳዊት ንጉሥነት የሚናገሩ መዝሙራት (መዝሙር 42-72)  4. ከአሦር ጋር ስለተደረገው ጦርነት የሚናገሩ መዝሙራት (መዝሙር 73-89)  5. ስለ ቤተ መቅደሱ መደምሰስና ስለ ምርኮ የሚናገሩ መዝሙራት (መዝሙር 90-106)  6. እግዚአብሔር እስራኤልን ከምርኮ በመመለስ እንደሚያድስ የሚናገሩ የምስጋና መዝሙራት (መዝሙር 107-145)  7. ለእግዚአብሔር ምስጋና የሚሰጡ የማጠቃለያ መዝሙራት (146-150)  ዋና ዋና የመዝሙራት ዓይነቶች  እጅግ በርካታ የመዝሙራት ወይም የግጥም ዓይነቶች ቢኖሩም እንኳ በሦስት ዋና ዋና ዓይነቶች ሊመደቡ ይችላሉ።  1. የምስጋና መዝሙራት፡- እነዚህ የምስጋና መዝሙራት የግል ወይም የቡድን ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አንዳንዶቹ መዝሙራት በእግዚአብሔር ላይ በማተኮር፣ ስለ ማንነቱ፣ ባሕሪያቱያመሰኙታል፡፡ ሌሎች መዝሙራት ደግሞ እግዚአብሔር ለግለሰብ ወይም ለቡድን ስላደረጋቸው፥ በተናጠል ስለሚታዩ ጉዳዮች እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ።  የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) እግዚአብሔርን ስለ ባሕርዩ ማመስገን የሚያስፈልገው ለምንድን ነው? ለ) ይህ በአምልኮ ውስጥ ሊኖር የሚገባ ዐቢይ ነገር የሆነው

የመዝሙረ ዳዊት መግቢያ Read More »