ቅድስና
ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ በደኅንነታችን ውስጥ ስለምናገኛቸው በረከተች ስናጠና ነበርን። በዳንንበት ጊዜ ስላገኘናቸው ብዙ የደኅንነት በረከቶች አጥንተናል። ዳግም በዳንንበት ወቅት፣ እግዚአብሔር በዳግም ልደት አዲስ ሕይወትን ሰጥቶናል። በደኅንነታችን ወቅት በውስጣችን ሊኖር ካመጣው ከክርስቶስ ጋር ኅብረት በምናደርግበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር እኛን ከክርስቶስ ጋር አንድ አድርጎ ያየናል። እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ይቅር በማለት ደኅንነትን ባገኘንበት ወቅት፣ ወዲያው መጽደቃችንን አስታውቆልናል። እንደ ልጆቹ […]