ኦሪት ዘጸአት

ዘጸአት 25-40

ከዘጸአት 25-40 ባሉት ክፍሎች ሦስት ዋና ዋና ነገሮች ቀርበዋል። 1) እግዚአብሔርን የማምለኪያ ስፍራ የሆነው የመገናኛው ድንኳን እንዴት መሠራት እንዳለበት የሚናገረው መመሪያ ሰፊውን ክፍል ይዟል። ቀጥሎም የእስራኤል ሕዝብ የተሰጣቸውን ትእዛዝ ተቀብለው እግዚአብሔር የሚኖርበትን የመገናኛ ድንኳን እንዴት እንደሠሩ ይናገራል። 2) በሁለተኛ ደረጃ የካህናትና የሊቀ ካህኑ አልባሳት እንዴት እንደተሠሩ የሚናገር ክፍል እናገኛለን። 3) ሕዝቡ በእግዚአብሔር ላይ በማመፅ የጥጃን […]

ዘጸአት 25-40 Read More »

ዘጸአት 19-24

ምናልባት ከእስራኤል ሕዝብ ታሪክ ከሁሉም ላቅ ያለ ስፍራ ሊሰጠው የሚገባው ሕዝቡ በሲና ተራራ የቆዩበት የአንድ ዓመት ጊዜ ነው። እግዚአብሔር ራሱን በታላቅ ክብር ለሕዝቡ የገለጠው በዚያ ነበር። እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ግንኙነት የሚያደርግበትን የሥነ-ምግባርና የመንፈሳዊ ሕይወት መሠረት የሰጣቸው በዚያ ነበር። በእግዚአብሔር ሕዝብና በዓለም ሕዝብ መካከል የሚገኙ ዋና ዋና ልዩነቶች የተገለጡት በዚያ ነበር። ክርስቲያኖች ለሆንን ሁሉ ከእነዚህ መመሪያዎች

ዘጸአት 19-24 Read More »

ዘጸአት 13-18

አንድ ሰው የመንፈሳዊ ሕይወት ጉዞውን በመልካም ሁኔታ ጀመረ ማለት ያለማቋረጥ በእምነት ይጓዛል ማለት አይደለም። እግዚአብሔር አይሁዳውያንን ከግብፅ ባርነት በታላቅ ኃይል አወጣቸው። አይሁድ በታላቅ ደስታ ከምርኮኛነት ተላቀቁ፡፡ ነገር ግን ብዙም ሳይቆዩ መጠራጠር፥ ማጉረምረም ማማረር ጀመሩ። ከዚህም አልፈው ወደ ግብፅ ለመመለስ ከጀሉ። መንፈሳዊ አረማመዳቸው ልክ እንደ እኛው የድልና የሽንፈት ጊዜያትን ያካተተ ነበር። የእስራኤል ሕዝብ በምድረ በዳ ያሳለፉት

ዘጸአት 13-18 Read More »

የእግዚአብሔር ሕዝብ ነጻነት (ዘጸ. 5-12) 

በዚያን ጊዜ ግብፅ በምድር ላይ ካሉ መንግሥታት ሁሉ በላይ የሆነ ኃያል መንግሥት ነበር። ነገር ግን የሰዎች ሁሉ ፈጣሪ ከሆነው ከእግዚአብሔር የሚበልጥ ታላቅነት ነበረውን? እነዚህ ምዕራፎች እግዚአብሔርን ወክሎ በሚናገረው በሙሴና በግብፅ መሪ በነበረው በፈርዖን መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ ያመለክታሉ። ምናልባት ሙሴ ከዚህ የግብፅ ንጉሥ ጋር በቂ ትውውቅ ያለውና አብረው ያደጉም ሳይሆኑ አይቀሩም። (ማስታወሻ፡- ፈርዖን የሚለው ቃል የአንድ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ነጻነት (ዘጸ. 5-12)  Read More »

የእግዚአብሔር ሕዝብ በባርነት ቀንበር ሥር መሆን እና እግዚአብሔር ሕዝቡን ከባርነት ለማውጣት መሪ መጥራቱ (ዘጸአት 1-4)

የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) በአሁኑ ጊዜ አንተም ሆንክ በኢትዮጵያ ያሉ ሌሎች ክርስቲያኖች የምትጋፈጧቸው የመንፈሳዊ ውጊያ ክፍል የሆኑ ነገሮችን ዘርዝር። ለ) ብዙ ክርስቲያኖች እየተሸነፉ ያሉት እንዴት ነው? ሐ) እግዚአብሔር ለአንተና ለቤተ ክርስቲያንህ በእነዚህ ነገሮች ላይ ድልን ሲሰጥ ያየኸው እንዴት ነው? ክርስቲያን በመንፈሳዊ ውጊያ ውስጥ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል። ይህ ውጊያ በመጨረሻ በእግዚአብሔርና በሰይጣን መካከል በከፍተኛ ደረጃ የሚጧጧፍ

የእግዚአብሔር ሕዝብ በባርነት ቀንበር ሥር መሆን እና እግዚአብሔር ሕዝቡን ከባርነት ለማውጣት መሪ መጥራቱ (ዘጸአት 1-4) Read More »

የኦሪት ዘጸአት አስተዋጽኦ እና ዓላማ

፩. የኦሪት ዘጸአት አስተዋጽኦ የውይይት ጥያቄ፥ ስለ ኦሪት ዘጸአት ከመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት አንብብ። እዚያ የሚገኘውን አስተዋጽኦ ገልብጥ። በሚቀጥሉት ገጾች የሚገኘውን አስተዋጽኦም አጥና። በአጠቃላይ የኦሪት ዘጸአት ታሪክ በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፡ እስራኤላውያን በግብፅ ምድር (ዘጸ. 1-12፡36) በዚህ የመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ሦስት ዋና ዋና ነገሮች ተጠቅሰዋል። በመጀመሪያ የምናየው፥ የሙሴን ታሪክ ሲሆን ስለ ልደቱ፥ በምድረ በዳ

የኦሪት ዘጸአት አስተዋጽኦ እና ዓላማ Read More »

በዘጸአት ጊዜ የነበረው የግብፅ ታሪክ

የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ በዓለም ከሚፈጸመው ታሪክ ጋር በቅርብ የተቆራኘ እንደሆነ ሁሉ፥ የእስራኤል ሕዝብ ታሪክም ከጥንቱ ዓለም ጋር የተቆራኘ ነበር። ይህ ደግሞ በተለይ በዚያን ጊዜ ከሁሉም በላይ ገናና የነበረችውን ግብፅን በሚመለከት የበለጠ እውነትነት አለው። የውይይት ጥያቄ፥ መዝ. 2፤ ኢሳ. 40፡ 15-25 አንብብ። ሀ) እነዚህ ቁጥሮች እግዚአብሔር በአሕዛብ ሁሉ ላይ ስላለው አገዛዝ ምን ያስተምሩናል? ለ) እነዚህ ቁጥሮች

በዘጸአት ጊዜ የነበረው የግብፅ ታሪክ Read More »

የኦሪት ዘጸአት መግቢያ

የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) ከሁሉም በላይ አስፈላጊ የሆነና በሕይወትህ የተፈጸመ መንፈሳዊ ክስተት ምንድን ነው? ለ) ይህ ለአንተ በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ሐ) ስለዚህ ጉዳይ እግዚአብሔርን በጸሎትና በመዝሙር ምን ያህል ጊዜ ታመሰግነዋለህ? ብዙዎቻችን በሕይወታችን የተፈጸመውና ከሁሉ በላይ አስፈላጊ የሆነው መንፈሳዊ ክስተት  ድነታችን (ደኅንነታችን) ነው በማለት ነው ለላይኛው ጥያቄ መልስ የምንሰጠው። ወደ ኋላ መለስ ብለን ስናስብ ጌታ

የኦሪት ዘጸአት መግቢያ Read More »