ሮሜ 5፡1-21
ኃጢአተኛው በእግዚአብሔር ከጸደቀ በኋላ የሚቀበላቸው በረከቶች (ሮሜ 5፡1-11) የውይይት ጥያቄ፡– ሮሜ 5፡1-11 አንብብ። እግዚአብሔር በክርስቶስ ለሚያምኑ ሰዎች የሚሰጣቸውን የተለያዩ በረከቶች ዘርዝር። አብርሃም በእምነቱ ምክንያት ተስፋ የተገባለትን ልጅ አግኝቷል። እኛስ ክርስቶስን ብቸኛ የድነት (የደኅንነት) መንገድ እንደሆነ ስናምን ምን እናገኛለን? ጳውሎስ ብዙ ልንደርስባቸው የምንችልባቸውን በረከቶችን ዘርዝሯል። ሀ. ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም ይኖረናል። ከእንግዲህ ከእግዚአብሔር ጋር እየተዋጋን ከፍርዱ ሥር […]