የሕይወት እንጀራ

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች

ታማኝነት- መጋቢው (1ኛ ቆሮ. 4፡1-6)

በምዕራፍ 3፥ ጳውሎስ የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያንን ሦስት ምስሎች አሳይቶአል። አሁን ደግሞ የአገልጋይን ሦስት ምስሎች ያቀርባል። እነርሱም መጋቢ (ቁ. 1-6)፥ መጫወቻ (ቁ. 7-13)። እና አባት (ቁ 14-21) ናቸው። አንባቢያኑ የአንድን ክርስቲያን አገልግሎት እግዚአብሔር እንዴት እንደሚመዝን ና እንደሚገመግም እንዲገባቸው ፈለገ። ቁጥር 6 የጳውሎስን ዓላማ ይገልጻል። «ስለ አንዱ በአንዱ ላይ አንዳችሁም እንዳይታበዩ።»  ሰዎችን ና አገልግሎታቸውን በምንገመግበት ጊዜ ጽንፎችን […]

ታማኝነት- መጋቢው (1ኛ ቆሮ. 4፡1-6) Read More »

ቤተ መቅደሱ – ጥራት (1ኛ ቆሮ. 3፡9-23)

የዚህ ምንባብ ተለምዶአዊ ገለጻ የክርስቲያን ሕይወትን ስለሚያንጽ ነገር ማውሳቱ ነው። ሁላችንም በክርስቶስ ላይ እናንጻለን፥ ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች መልካም የሆኑ ቁሳቁሶችን፥ ሌሎች ደግሞ መናኛ ቁሳቁሶችን ለእነጻው ይጠቀማሉ። የምትጠቀመው ቁሳቁስ የምታገኘውን ዋጋ ይወስናል።  ይህ የዚህ ምንባብ ትክክለኛው ተዛምዶ ቢሆንም፥ መሠረታዊው ትርጓሜ ግን አይደለም። ጳውሎስ ያወሳ የነበረው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሆነችውን የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ስለማነጽ ነው። (ከ

ቤተ መቅደሱ – ጥራት (1ኛ ቆሮ. 3፡9-23) Read More »

ማሣው -ብዛት (1ኛ ቆሮ. 3፡5-9)

ጳውሎስ የእርሻ ምሳሌዎችን ይወድድ ነበር እናም ብዙ ጊዜ በደብዳቤዎቹ ይጠቀምባቸዋል። «እናንተ የእግዚአብሔር እርሻዎች ናችሁ» ማለት፥ «እናንተ የእግዚአብሔር የተዘጋጀ ማሣ ናችሁ፥ የእግዚአብሔር የአትክልት ስፍራ ናችሁ» ማለት ነው። በዘሪው ምሳሌ ላይ፥ ኢየሱስ የሰውን ልብ ከመሬት፥ ዘሩን ደግሞ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር አነጻጽሮታል (ማቴ. 13፡1-9፥ 18-23)። ጳውሎስ ይህን ግላዊ ምሳሌ ወስዶ የጋራ አደረገው፥ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ፍሬ ማፍራት የሚገባት

ማሣው -ብዛት (1ኛ ቆሮ. 3፡5-9) Read More »

ቤተሰብ -በብስለት ማደግ (1ኛ ቆሮ. 3፡1-4)

ብሪታኒያዊው የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪ ዶክተር ጂ. ካምቤል ሞርጋን እራት ወንድ ልጆች ነበሯቸው፤ አራቱም ወንጌል አገልጋዮች ሆኑ። አንዱ ሰው ከልጅ ልጆቻቸው እንዱን እርሱም የወንጌል እገልጋይ ይሆን እንደሆነ ሲጠይቀው፥ «የለም፥ እኔ ለኑሮዩ ለመሥራት ነው ዕቅዴ» በማለት መለሰለት።  አንድ መጋቢ ማድረግ የሚጠበቅበት ምንድን ነው? «የወንጌል አገልግሉት ሥራ በእርግጥ ምንድን ነው»? ይህን ካላወቅን የወንጌል አገልጋዩን ሥራ ከቶውንም መገምገም አንችልም።

ቤተሰብ -በብስለት ማደግ (1ኛ ቆሮ. 3፡1-4) Read More »

ወንጌል በመንፈስ አማካኝነት በቃሉ በኩል ተገልጧል (1ኛ ቆሮ. 2፡10-16)

ደኅንነታችን በመለኮት የተጠቃለሉትን ሦስቱንም አካላት ይመለከታል (1ኛ ጴጥ. 1፡2፤ ኤፌ 1፡3-14)። የአብ የጸጋ ምርጫ፥ የወልድ የፍቅር መሥዋዕት፥ እና የመንፈስ ቅዱስ የመውቀስ እና የማደስ አገልግሎት ሳይኖር ልትድን አትችልም። «በእግዚአብሔር አምናለሁ» ማለቱ በቂ አይደለም። ምን ዓይነት እግዚአብሔር ነው? የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ «አምላክ እና አባት» (ኤፌ. 18) ካልሆነ በቀር ደኅንነት ሊኖር አይችልም።  ይህ የደኅንነታችን አሀዱ ሥሉሳዊ ገጽታ የደኅንነታችንን

ወንጌል በመንፈስ አማካኝነት በቃሉ በኩል ተገልጧል (1ኛ ቆሮ. 2፡10-16) Read More »

ወንጌል የአብ ዘላለማዊ ዕቅድ ክፍል ነው (1ኛ ቆሮ. 2፡6-9)

ደኅንነት የተገዛው በልጁ ሲሆን የታቀደው ግን በአብ ነው። ስለ «ቀላል ወንጌል» የሚናገሩ ሰዎች ትክክልም ስሕተትም ናቸው። አዎን፥ የወንጌል መልእክት ያልተማረ ሃይማኖት የለሽ ሰው እውቆት፥ አምኖ እስከሚድን ቀላል ነው። ነገር ግን በጣም የመጠቀ የሥነ መለኮት አዋቂ እንኳ እስከማይዘልቅበት ድረስ በጣም የጠለቀ ነው።  በጣም የረቀቀውን አእምሮ እንኳ የሚቋቋም «የእግዚአብሔር ጥበብ» በወንጌል ውስጥ ይገኛል። ይሁንና፥ ይህ ጥበብ ለጠፉ

ወንጌል የአብ ዘላለማዊ ዕቅድ ክፍል ነው (1ኛ ቆሮ. 2፡6-9) Read More »

ወንጌል የኢየሱስ ክርስቶስን ሞት ማዕከል ያደርጋል (1ኛ ቆሮ. 2፡1-5)

ባለቤቴ መኪናችንን እየነዳች አጠገቧ ተቀምጬ ወደ ቺካጎ እየሄድን ሳለ እንድ እሳታሚ እንድገመግመው የሰጠኝን የአንድ ደራሲ መጽሐፍ እነብብ ነበር። አልፎ አልፎ የማጉተምተም ከዚያም ማጉረምረም እይሉት ማቃሰት የሚመስል ድምፅ አሰማ ነበር፤ በመጨረሻም ራሴን ነቀነቅሁና፥ «ኦ፥ ፍጹም! ይህን አላምንም!» አልኩኝ።  «መጽሐፉን ያልወደድህ መሰለኝ፥ የሆነ ችግር አለው?» አለችኝ።  «አሳምሮ ነዋ!» አልኳት። «ሁሉም ነገር የተበላሸ ነው ማለት ይቻላል፤ ምክንያቱም ይህ

ወንጌል የኢየሱስ ክርስቶስን ሞት ማዕከል ያደርጋል (1ኛ ቆሮ. 2፡1-5) Read More »

እግዚአብሔርን ለማክበር የተጠራችሁ (1ኛ ቆሮ. 1፡26-31)

ቆሮንቶሳውያን በትዕቢት «የመነፋት» አዝማሚያ ነበራቸው (4፡6፥18-19፤ 5፡2)። ነገር ግን የእግዚአብሔር የጸጋ ወንጌል ራስን በትምክህት ለመሙላት ምንም ስፍራ አይሰጥም። መልካችን፥ ማኅበራዊ አቋማችን፥ ደረጃችን፥ የተፈጥሮ ቅርሳችን፥ ወይም የገንዘብ ዓቅማችን የእግዚአብሔርን አድናቆት ወይም አክብሮት አያተርፍልንም። ጳውሎስ ለማንም ሳይሆን ለብዙዎች እንደ ጻፈ ልብ በል። በአዲስ ኪዳን «ከፍተኛ ማኅበራዊ አቋም» ያላቸውን ጥቂት አማኞች እናገኛለን፤ ሆኖም ግን እንዲህ ዓይነቶቹ ብዙ አይደሉም።

እግዚአብሔርን ለማክበር የተጠራችሁ (1ኛ ቆሮ. 1፡26-31) Read More »

ወደ ኅብረት የተጠራችሁ (1ኛ ቆሮ. 1፡10–25)

ጳውሎስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የነበረውን የርኩሰት ችግር ከጠቀሰ በኋላ ወደ ክፍፍሉ ጉዳይ ተመለሰ። ክፍፍል በእግዚአብሔር ሰዎች መካከል ሁልጊዜ የነበረ ችግር ነው። ስለሆነም ሁሉም የአዲስ ኪዳን መልእክቶች ማለት ይቻላል ይህን ርእስ በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ይነኩታል ወይም ይጠቅሱታል። አሥራ ሁለቱ ሐዋርያትም እንኳ እርስ በርስ ሁልጊዜ የተስማሙበት ወቅት አልነበረም።  ከምንወዳቸው ቅዱሳን በከፍታ መኖር፥  ይህ በእርግጥም ነው ክብር! 

ወደ ኅብረት የተጠራችሁ (1ኛ ቆሮ. 1፡10–25) Read More »

ቅዱሳን ለመሆን እንደተጠሩ (1ኛ ቆሮ. 1፡1-9)

«ለኢየሱስ፥ እሺ! ለቤተ ክርስቲያን፥ እምቢ!»  በ1960ዎቹ ይህ መፈክር በወጣቶች ዘንድ ተወዳጅ የነበረበትን ጊዜ ታስታውሳለህን? በወቅቱ የነበረችው ቤተ ክርስቲያን በከፋ ችግር ውስጥ ስለነበረች፥ ይህን አባባል በ 56 ዓ.ም በቆሮንቶስ የነበሩት ያለ ጥርጥር በቅንነት በተጠቀሙት ነበር። የሚያሳዝነው፥ ችግሮቹ በቤተ ክርስቲያኒቱ ቤተሰቦች መካከል የቀሩ ሳይሆኑ፥ በውጭ ባሉ በማያምኑትም ዘንድ የታወቁ መሆናቸው ነበር።  በመጀመሪያ ደረጃ በቆሮንቶስ የነበረችው ቤተክርስቲያን የረከሰች

ቅዱሳን ለመሆን እንደተጠሩ (1ኛ ቆሮ. 1፡1-9) Read More »