1ኛ የጴጥሮስ መልእክት

ለሽማግሌዎችና ለጎልማሶች የተሰጠ ምክር (1ኛ ጴጥ. 5፡1-14)

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መልካም ግንኙነት ሊኖር ይገባል። ጴጥሮስ ከሚያሳድዱን ዓለማውያን፥ ከቤተሰብ አባላትና ከሌሎች አማኞች ጋር ስለሚኖረን ግንኙነት አስተምሯል። አሁን ደግሞ የእግዚአብሔር ሕዝብ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ምን ዓይነት ግንኙነት ሊኖረው እንደሚገባ ያስተምራል። ጴጥሮስ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በሆኑት ሽማግሌዎች ይጀምራል። በተለይ በስደት ጊዜ የሽማግሌዎች ቀዳማይ ኃላፊነት ምንድን ነው? ሽማግሌዎች የእግዚአብሔር መንጋ እረኞች እንደ መሆናቸው መጠን በቤተ ክርስቲያን […]

ለሽማግሌዎችና ለጎልማሶች የተሰጠ ምክር (1ኛ ጴጥ. 5፡1-14) Read More »

ለእግዚአብሔር መኖር እና ክርስቲያን በመሆን የሚደርስ መከራ (1ኛ ጴጥ. 4፡1-19)

ክርስቲያኖች የተቀደሰ ሕይወት መምራት ይኖርባቸዋል (1ኛ ጴጥ. 4፡1-6)። በመከራ ውስጥ በማለፍ ክርስቶስ ድልን ተቀዳጅቷል። እግዚአብሔር ክርስቶስን በማክበር ከሁሉም በላይ ሥልጣን ሰጥቶታል። ክርስቲያኖች መከራ በሚቀበሉበት ጊዜ የክርስቶስን ምሳሌነት ቢከተሉ ድል ነሺዎች ይሆናሉ። ብንሠቃይም፥ በኃጢአት ተፈጥሮአችን ላይ ድልን እንቀዳጃለን። መከራ ክርስቲያኖች በክርስቶስ ላይ እንዲደገፉ ይረዳቸዋል። ከዘላለም ዘመን አንጻር አስፈላጊው ነገር ምን እንደሆነ ለይተው እንዲያውቁ ያግዛቸዋል። በሕይወታችን ውስጥ

ለእግዚአብሔር መኖር እና ክርስቲያን በመሆን የሚደርስ መከራ (1ኛ ጴጥ. 4፡1-19) Read More »

የእግዚአብሔር ሕዝብ ቤተሰባዊ ግንኙነት እና መልካም በማድረግ መከራን መቀበል (1ኛ ጴጥ. 3፡1-22)

፩. የእግዚአብሔር ሕዝብ ቤተሰባዊ ግንኙነት (1ኛ ጴጥ. 3፡1-7) እግዚአብሔር እንደሚፈልገን ለመኖር እና የሚደርስብንን ስደትና መከራ ለማሸነፍ የምንችለው ጤናማ ቤተሰባዊ ግንኙነት ካለን ብቻ ነው። ይህም ግንኙነት ከእግዚአብሔር አካል፥ ከወላጆች፥ ከልጆች፥ ከወንድሞችና ከእኅቶች ጋር የሚደረገውን ቤተሰባዊ ግንኙነት ይመለከታል። ሚስቶች ለባሎቻቸው መገዛት አለባቸው (1ኛ ጴጥ. 3፡1-6)። ጴጥሮስ ሚስቶች ለባሎቻቸው መገዛት እንዳለባቸው ያስተምራቸዋል። ባሎቻቸው ክርስቲያኖች ባይሆኑም እንኳን መታዘዝ አለባቸው፡፡

የእግዚአብሔር ሕዝብ ቤተሰባዊ ግንኙነት እና መልካም በማድረግ መከራን መቀበል (1ኛ ጴጥ. 3፡1-22) Read More »

ለአለቆችና ለጌቶች መታዘዝ (1ኛ ጴጥ. 2፡13-25)

የአንደኛ ጴጥሮስ መልእክት የመጨረሻው ዐቢይ ክፍል የእግዚአብሔር ምርጥ ሕዝብ መሆናችንን በሚያንጸባርቅ መልኩ ከዓለም የተለየ ሕይወት ልንኖር የምንችልባቸውን የተለያየ የሕይወት ክፍሎች ይመረምራል። ሀ. ክርስቲያኖች ለመንግሥት መሪዎች መገዛት አለባቸው (1ኛ ጴጥ. 2፡13-17)። ሁሉም የመንግሥት ባለሥልጣናት እግዚአብሔርን ቢያከብሩም ባያከብሩም እግዚአብሔርን ቢያምኑም ባያምኑም፥ በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው። ስለሆነም አማኞች መሪዎቻቸውን ማክበርና መታዘዝ ይኖርባቸዋል። ይህም ማለት ቀረጥን እንዲከፍሉ በሚጠየቁበት ጊዜ ከማጭበርበር

ለአለቆችና ለጌቶች መታዘዝ (1ኛ ጴጥ. 2፡13-25) Read More »

የእግዚአብሔር ምርጥ ሕዝብ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ሕያዋን ድንጋዮች ናቸው (1ኛ ጴጥ. 2፡4-12)።

በስደትና መከራ ጊዜ ክርስቲያኖች ከሚዘነጓቸው ነገሮች አንዱ ክርስቲያናዊ ማንነታቸውን ነው። ክርስቲያኖች ብዙውን ጊዜ የተረገጡ፥ የተጨቆኑና ማኅበረሰቡ እንደ ከንቱ ነገር የሚቆጥራቸው ናቸው። «ደደቦች ናችሁ» የሚለው ቃል ብዙውን ጊዜ በክርስቲያኖች ጆሮ ያቃጭላል። ሰይጣን ብዙውን ጊዜ በዚህ ሰዓት ወደ እኛ በመቅረብ ክርስቶስን በመከተላችንና እንደ ሌሎች ሰዎች ባለመሆናችን የሞኝነት ውሳኔ እንደ ወሰንን እንድናስብ በማግባባት ይፈትነናል። እንዲሁም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን

የእግዚአብሔር ምርጥ ሕዝብ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ሕያዋን ድንጋዮች ናቸው (1ኛ ጴጥ. 2፡4-12)። Read More »

ድነት (ደኅንነት) ወደ ተቀደሰ አኗኗር ሊመራን ይገባል (1ኛ ጴጥ. 1፡13-2፡3)

ብዙውን ጊዜ በመጀመሪያ የድነት (ደኅንነት) ተግባር ላይ አጽንኦት እንሰጣለን። አንድ ሰው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በክርስቶስ በሚያምንበት ጊዜ ደስ እንሰኛለን። በመሠረቱ ይህ ትክከለኛ እርምጃ ነው። ይህ ታላቅ መዳን በመሆኑ፥ ሰማያት ሁሉ ከእኛ ጋር ይደሰታሉ (ሉቃ. 15፡10)። ነገር ግን ጴጥሮስ ድነት (ደኅንነት) ከዘላለማዊ ፍርድ ብቻ መዳን ሳይሆን፥ የአዲስ ሕይወት መነሻ እንደሆነ ይናገራል። አሁንም ጴጥሮስ በደኅንነታችን ታላቅነት ላይ

ድነት (ደኅንነት) ወደ ተቀደሰ አኗኗር ሊመራን ይገባል (1ኛ ጴጥ. 1፡13-2፡3) Read More »

ከስደት ባሻገር ድነታችን (ደኅንነታችን) ትልቅ ሽልማት ያስገኝልናል (1ኛ ጴጥ. 1፡1-12)

ወርቅነሽ ተወልዳ ያደገችው በሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ ሲሆን፥ ቤተሰቦቿ ጠንካራ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ነበሩ። አንድ ቀን አንድ ወንጌላዊ ወደ አካባቢያቸው መጥቶ ወርቅነሽ ከክርስቶስ ጋር የግል ግንኙነት ሊኖራት እንደሚገባ ነገራት። ከወንጌላዊው ጋር በምትወያይበት ጊዜ በክርስቲያን ቤተሰብ ውስጥ መወለዱ ወይም ክርስቶስ እንደ ሞተ ማመኗ ብቻ በቂ እንዳልሆነና ዳሩ ግን ክርስቶስ ድነትን (ደኅንነትን) የምታገኝበት ብቸኛው መንገድ እንደሆነ በማመን ልትከተለው እንደሚገባው

ከስደት ባሻገር ድነታችን (ደኅንነታችን) ትልቅ ሽልማት ያስገኝልናል (1ኛ ጴጥ. 1፡1-12) Read More »

የ1ኛ ጴጥሮስ መልእክት ዓላማ፣ ባሕሪያት፣ መዋቅር እና አስተዋጽኦ

የ1ኛ ጴጥሮስ መልእክት ዓላማ የውይይት ጥያቄ፡- 1ኛ ጴጥ. 5፡12 አንብብ። ጴጥሮስ የመልእክቱ ዓላማ ምንድን ነው ይላል? የ1ኛ ጴጥሮስ መልእክት የተጻፈው ለተለያዩ ዓላማዎች ነበር። የመጀመሪያው ዓላማ፡ አማኞች ምንም ዓይነት ስደት ወይም መከራ ቢደርስባቸው በእምነታቸው ጸንተው ይቆዩ ዘንድ ለማበረታታት (1ኛ ጴጥ. 1፡6፤ 2፡20፣ 4፡13፥ 19)። በክርስቲያኖች ላይ ስደት እየተጠናከረ መምጣቱን በመመልከቱ፥ ጴጥሮስ አዝማሚያው እየከፋ እንደሚሄድና ብዙ አማኞች

የ1ኛ ጴጥሮስ መልእክት ዓላማ፣ ባሕሪያት፣ መዋቅር እና አስተዋጽኦ Read More »

ጴጥሮስ መልእክቱን የጻፈው ለማን ነው፣ መቼ እና የት ተጻፈ?

ጴጥሮስ መልእክቱን የጻፈው ለማን ነው? ጴጥሮስ በመግቢያው ላይ፥ «ለጳንጦስና፥ ለገላትያ፥ በቀጰዶቂያም፥ በእስያም፥ በቢታንያም ለተበተኑት መጻተኞች» ይላል። እነዚህ አውራጃዎች የሚገኙት ከትንሹ እስያ (የአሁኗ ቱርክ) በስተ ሰሜን ነበር። መንፈስ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ እነዚህ አካባቢዎች እንዳይገባ ነግሮት ነበር (የሐዋ. 16፡6-8)። ምሁራን መንፈስ ቅዱስ ጳውሎስ ወደዚህ አካባቢ እንዳያገለግል የከለከለው ጴጥሮስ ቀደም ሲል ወይም ወደ በኋላ በዚህ አካባቢ የወንጌል አገልግሎት

ጴጥሮስ መልእክቱን የጻፈው ለማን ነው፣ መቼ እና የት ተጻፈ? Read More »

የአንደኛ ጴጥሮስ ጸሐፊ

የውይይት ጥያቄ፡- 1ኛ ጴጥሮስ 1፡1 አንብብ። ሀ) የዚህ መልእክት ጸሐፊ ማን ነው? ለ) እራሱን እንዴት ይገልጸዋል? ይህ ጳውሎስ ሁልጊዜ ራሱን ከሚገልጽበት ሁኔታ የሚለየው ወይም የሚመሳሰለው እንዴት ነው? ሐ) የዚህ መልእክት ተቀባዮች እነማን ናቸው። በዚህ መልእክት ውስጥ የተገለጸበት ሁኔታ ምን ይመስላል? የአንደኛ ጴጥሮስ መልእክት ጥንታዊ የደብዳቤ አጻጻፍ ስልት በመከተል የጸሐፊውን ማንነት በማስተዋወቅ ይጀምራል። እርሱም ጴጥሮስ መሆኑን

የአንደኛ ጴጥሮስ ጸሐፊ Read More »