የሕይወት እንጀራ

ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

እግዚአብሔር ወልድ፡- ለቅዱሳኑ መምጣቱ

This entry is part 12 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ሀ. ያልተፈጸመ ትንቢት  በዚህ ምዕራፍ የተመረጠው አስተምህሮ እጅግ ጠቃሚ ከሆኑት ያልተፈጸመ ትንቢት ጉዳዮች አንዱ ነው። የዚህ ጽሑፍ አንባቢ ሊረዳው የሚገባ ነገር፥ ትንቢት እግዚአብሔር አስቀድሞ የተናገረውና በጽሑፍ የሰፈረ ታሪክ መሆኑን ነው። ስለዚህ እንደ ማንኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይታመናል። መጽሐፍ ቅዱስ ሲጻፍ አንድ አራተኛ የሚሆነው ከፍሉ በትንቢት መልክ ነበር። ብዙው ትንቢት ተፈጽሟል፥ እያንዳንዱ ፍጻሜ ልክ በትንቢት እንደተነገረው ነው። ከልደቱ ብዙ ዓመታት በፊት እንደተተነበየው ክርስቶስ የመጣው ከይሁዳ ነገድ፡ከአብርሃም ልጅ፥ ከዳዊት ልጅ፥ ቤተልሔም ውስጥ ከአንዲት ድንግል በመወሰድ ነበር። በተመሳሳይ ሁኔታ፥ የአሟሟቱ ዝርዝር መዝሙረ ዳዊት ውስጥ ከሺህ ዓመታት በፊት በተተነበየው መሠረት በትክክል ተፈጽሟል።  የእግዚአብሔር ቃል በአሁኑ ጊዜ ያልተፈጸሙ ብዙ ትንቢቶች አሉት። ስለሆነም ትንቢቶቹ በአሁኑ ጊዜ እንዳሉት እንደ ሌሎቹ የእግዚአብሔር ሥራዎች ሁሉ ያለጥርጥር እንደሚፈጸሙ ማመኑ ተገቢና እግዚአብሔርንም በእምነት ማክበር ነው።  ኢየሱስ ክርስቶስ ልክ ወደ ሰማይ በሄደበት አኳኋን፥ “ይህ…ኢየሱስ” በዕረገበት አካሉና በደመናት ታጅቦ (ሐዋ. 1፡11) የሚመለስ መሆኑ በትንቢት ቃሎች በሚገባና በስፋት ተገልጧል። በታላላቅ የክርስትና እምነት መግለጫዎች ውስጥም ታክሏል። ይህ እውን ቢሆንም፥ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት አስተምህሮ ልዩ ጥንቃቄ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው።  ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ትንቢትን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ጋር በተዛመደ አኳኋን ሲመለከቱ፥ ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያኑ መምጣቱን (የአማኞች ወደ ሰማይ መነጠቅ) እና ግልጥ ከሆነው ዳግም ምጽአት (መንግሥቱን ለመመሥረት እና ለሺህ ዓመታት ለመግዛት ከቅዱሳኑ ጋር ከመምጣቱ) ይለያዩታል። በነዚህ ሁለት ክንውኖች መካከል ብዙ ዋና ዋና ክስተቶች ይታያሉ፤ የዓለም አቀፊቱ ቤተ ክርስቲያን ብቅ ማለት፥ በአምባገነን መሪ የሚተዳደር ዓለም አቀፍ መንግሥት መመሥረት፥ እና እጅግ አሠቃቂ ጦርነቶች መቀስቀሳቸው የሚጠቀሱ ናቸው። እርሱ መንግሥቱን ሊያቆም እስኪመጣ ጦርነቶቹ ይካሄዳሉ። ትንቢቶች ቃል በቃል ከተተረጎሙ የሚኖረው ቅደም ተከተል በመጀመሪያ ከርስቶስ ለቤተ ክርስቲያኑ የመምጣቱ ክንውን ነው።  ምንም እንኳን ከቤተ ክርስቲያን መነጠቅ በኋላ የፍጻሜው ዘመን ክንውኖች በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን ትንቢቶች ቢጠቀሱ፥ ክርስቶስ መጀመሪያ ለቤተ ክርስቲያኑ የመምጣቱ እውነት መጀመሪያ ብሉይ ኪዳን ውስጥ አልተገለጠም፤ የአዲስ ኪዳን ትንቢት ነው፡፡ ለ. ስለ መነጠቅ የተነገሩ ትንቢቶች  ክርስቶስ ከፍጻሜው ዘመን ክንውኖች በፊት ለቅዱሳኑ የመምጣቱን መገለጥ፥ በመሰቀሉ ዕለት ዋዜማ በላይኛው ክፍል ውስጥ ለደቀ መዛሙርቱ ነግሯቸዋል። ዮሐንስ 14:2-3 ውስጥ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ብሏቸዋል፡- “በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ፤ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ”።  ደቀ መዛሙርቱ ያን ትንቢት ለመስማት ፈጽሞ የተዘጋጁ አልነበሩም። ማቴዎስ 24፡26-31 ውስጥ ክርስቶስ መንግሥቱን ለመመሥረት ዳግም በክብር ስለመምጣቱ ተነግሯቸዋል። እስከዚያች ሰዓት ድረስ ከርስቶስ መጀመሪያ ወደ ሰማይ እንደሚወስዳቸውና በመጨረሻው ዘመን ከሚፈጸሙ ክፉ ነገሮች እንደሚጠብቃቸው ደቀ መዛሙርቱ አልተገነዘቡም ነበር። ዮሐንስ 14 ውስጥ እንደተጠቀሰው ክርስቶስ ስፍራ ሊያዘጋጅላቸው የሚሄድበት የአብ መኖሪያ በሰማይ መሆኑ ግልጥ ነው። ስፍራ ካዘጋጀ በኋላ ሊወስዳቸው እንደሚመለስ ተስፋ ሰጥቷቸዋል። ዓላማው ደቀ መዛሙርቱን ከምድር ወደ አባቱ ቤት መውሰድ ነው። ይህን ተስፋ ሐዋርያው ጳውሎስ በዝርዝር ገልጿል።  ጳውሎስ በቅዱሳን ትንሣኤና ክርስቶስ በምድር ላሉት ቅዱሳን በመምጣቱ መካከል ስላለው ጉዳይ የተሰሎንቄ ሰዎች ለነበራቸው ጥያቄ መልስ ሲጽፍ የዚህን ታላቅ ክንውን ዝርዝር ገልጧል (1ኛ ተሰ. 4፡13-18)። ከ16-17 ባሉት ቁጥሮች እንዲህ ብሏል፡- “በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤ ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፥ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን”።  የክርስቶስ ለቅዱሳኑ መምጣት ሁኔታዎች ቅደም ተከተል የሚጀምረው ክርስቶስ ከዙፋኑ ተነሥቶ ከምድር በላይ ወዳለው አየር ሲወርድ ነው። ሲመጣ ድምፅ ይሰጣል። ያም ድምፅ የትእዛዝ ድምፅ” ነው። ይህ ሁኔታ በመላእክት አለቃ ሰሚካኤል የድል ድምፅና የእግዚአብሔር መለኮት ይታጀባል። ሙታን ክርስቲያኖች የክርስቶስን ድምፅ በመታዘዝ ( ዮሐ. 5፡28-29) ከመቃብር ይነሣሉ። ሰiኛ ተሰሎንቄ 4፡14 ላይ እንደተጠቀሰው የሙታኑ ነፍሳት ክርስቶስን ያጅቡታል። ምክንያቱም ቃሉ እንዲሁም በኢየሱስ ያንቀላፉትን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ያመጣቸዋል” ይላልና። እነዚህ ነፍሳት ጌታን አጅበው ከመጡ በኋላ መቃብር ውስጥ ከነበረውና ከሚያርገው አካላቸው ጋር ይገናኛሉ። በክርስቶስ ያንቀላፉት (የሞቱት) ከተነሣ በኋላ፥ በሕይወት ያሉት ክርስቲያኖች “ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና ይነጠቃሉ”። በዚህ ሁኔታ ቤተ ክርስቲያን ከምድር ትወሰድና፥ በአብ ዘንድ በመኖር ዮሐንስ 14 ውስጥ የተጠቀሰውን ተስፋ ትፈጽማለች።  ተጨማሪ ዝርዝር 1ኛ ቆሮንቶስ 15፡51-58 ውስጥ ተሰጥቷል። ጌታ ለቤተ ክርስቲያኑ የሚመጣበት ሁኔታም “ምስጢር” ተብሏል። ይህ ማለት፥ እውነታው በብሉይ የተሸሽገና በአዲስ ኪዳን የተገለጠ ነው ለማለት ነው (ሮሜ 16፡25-26፤ ቈላ. 1፡26)። ክርስቶስ መንግሥቱን በምድር ለመመሥረት የመምጣቱ እውነት በብሉይ ኪዳን የተገለጠ ሲሆን፥ ንጥቀት ግን በአዲስ ኪዳን ብቻ ነው የተገለጠው። ጳውሎስ 1ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ 15 ውስጥ ክንውኑ ወዲያውኑ “ሰቅፅበተ ዓይን” እንደሚሆን ገልጧል። የሙታኑ አካል የማይበሰብስ፥ የማያረጅና የማይሞት ይሆናል (1ኛ ቆሮ. 15፡53)።  አዲሱ አካላችን ኃጢአት አልባ እንደሚሆን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ያስረዳል (ኤፌ. 5፡27፤ ፈልጵ. 3፡20-21)። በመቃብርም ሆነ በሕይወት ያሉት አካላት ለመንግሥተ ሰማያት የሚስማሙ አይደሉም። ለዚህ ነው ጳውሎስ “እኛ ሁላችንም እንለወጣለን” (1ኛ ቆሮ. 15፡51) ያለው። ከቤተ ክርስቲያን (አማኞች) ትንሣኤና መነጠቅ ጋር ሲነጻጸር፥ ከጰንጠቆስጤ ዕለት በፊት የሞቱ፥ ወይም ከመነጠቅ ክንውን በኋላ የሚሞቱ ቅዱሳን ትንሣኤና ንጥቀት ክርስቶስ መንግሥቱን ሊመሠርት እስኪመባ ይዘገያል (ዳን. 12፡1-2፤ ራእይ 20፡4)። ኃጢአተኞች ግን እስከ ክርስቶስ የሺህ ዓመታት አገዛዝ ፍጻሜ ድረስ አይነሡም (ራእይ 20፡5-6፥ 12-13)።  ሐ. ክርስቶስ ለቅዱሳኑ መምጣቱ እና ከቅዱሳኑ ጋር መምጣቱ ሲነጻጸሩ።  መነጠቁ የሚከናወነው ከፍጻሜው ጊዜ ቀድሞ ነው የሚለው አስተምህሮ፥ ቅድመ ፍዳ አመለካከት ይባላል። ከዚህ ጋር የሚነጻጸረው ሌላ አመለካከት ደግሞ ድኅረ ፍዳ ዘመን የተሰኘው ሲሆን፥ የክርስቶስን ለቅዱሳኑና ከቅዱሳኑ ጋር መምጣት እንደ አንድ ክንውን የሚያይ ነው። ከነዚህ ሁለት አመለካከቶች የቱ ነው ትክክል ለሚለው ጥያቄ መልስ የሚሆነው፥ ትንቢትን በትክክል የመተርጎሙ ውጤት ይሆናል።  በሁለቱ ክንውኖች መካከል አንዳንድ ልዩነቶች ይታያሉ።  1, ክርስቶስ ቅዱሳኑን በሰማይ ወዳለ አባቱ ቤት ለመውሰድ የመምጣቱ ሂደት፥ ከምድር ወደ ሰማይ የሚደረግ እንቅስቃሴ ሲሆን፥ ከቅዱሳኑ ጋር የመምጣቱ ክንውን ግን ከሰማይ ወደ ምድር የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው። ይህም ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተገልጦ መንግሥቱን የሚመሠርትበት ጊዜ ይሆናል።  2. በሕይወት ያሉ ቅዱሳን በሙሉ በመነጠቅ ጊዜ ቀሚለወጡ ሲሆን፥ ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት ጋር በተያያዘ ሁኔታ ግን ቅዱሳን አይለወጡም።  3. በመነጠቅ ጊዜ ቅዱሳን ወደ ሰማይ የሚሄዱ ሲሆን፥ በዳግም ምጽአቱ ግን ሳይለወጡ በምድር ላይ ይኖራሉ።  4. በመነጠቅ ጊዜ ዓለም የማይለወጥና የማይፈረድበት ሆኖ በኃጢአቱ ይቀጥላል፥ በዳግም ምጽአት ግን ይፈረድበታል፥ ጽድቅም በምድር ላይ ይመሠረታል።  5. ቤተ ክርስቲያን የምትጠቀሙ ከሚመጣው የቁጣ ቀን ለመሳኝ ሲሆን፥ ዳግም ምጽአቱ ግን በክርስቶስ በማመን በመከራው ጊዜ ሁሉ ታግሠው የቆዩትን ለማዳን ነው።  6. መነጠቅ ሳይታሰብና በቅፅበት ሊሆን እንደሚችል የተገለጠ ሲግ፥ ዳግም ምጽአቱ ግን ብዙ ምልክቶችና ድርጊቶችን ተከትሎ የሚፈጸም ይሆናል።  7. መነጠቅ በአዲስ ኪዳን ብቻ የተገለጠ እውነት ሲሆን፥ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ግን በቅድሚያ ሊከናወኑ ካሉ ምልክቶችና ሁኔታዎች ጋር በብሉይም በአዲስም የተጠቀሰ እውነት ነው።  8. መነጠቅ የዳኑትን ብቻ የሚመለከት ሲሆን፥ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ግን ሁለቱንም ማለት የዳኑትንና ያልዳኑትን ይመለከታል።  9. በመነጠቀ ጊዜ ሰይጣን ስለማይታሰር በቀጣዮቹ ጊዜያት ከበፊቱ ይልቅ ይበረታል። በዳግም ምጽእት ግን ይታሰራል። ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርግ ይጠበቃል፥ ይከለከላል።  10. መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ስተመሠረተችበት ወቅትና ስመነጠቋ መካከል ይህ እንዲከናወን የግድ መፈጸም ያለበት ትንቢት የለም። ንጥቀት ቅፅበታዊ ነገር ነው። ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት ቀደም ብሎ ግን መፈጸም የሚገባቸው ብዙ ምልክቶች አሉ።  11. ክርስቶስ መንግሥቱን ለመመሥረት ወደ ምድር በሚመጣበትና ከቅዱሳን መነጠቅ ጋር በተያያዘ ሁኔታ፥ የሕያዋን ቅዱሳን በዚያው ጊዜ መለውጥ በብሉይም ሆን በአዲስ ኪዳን

እግዚአብሔር ወልድ፡- ለቅዱሳኑ መምጣቱ Read More »

እግዚአብሔር ወልድ፡- ዕርገቱና የክህነት አገልግሎቱ

This entry is part 11 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ሀ. የክርስቶስ ዕርገት እውነትነት  በክርስቶስ መከበር ቅደም ተከተል ትንሣኤው የመጀመሪያው ሲሆን፥ ዕርገቱ ደግሞ ቀጣይ ዋና ነገር ነው። ይህ ማርቆስ 16፡19፤ ሉቃስ 24፡50፥51፤ የሐዋርያት ሥራ 1፡9-11 ውስጥ ተመዝግቧል።  ክርስቶስ በትክክለኛው ሁኔታ ከማረጉ በፊት ወደ ሰማይ ወጥቶ ነበር? የሚል ጥያቄ ይነሣል። ይህንም በተመለከተ ክርስቶስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ፥ “እኔ ወደ አባቴና ወደ እባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁም በርጋለሁ” ሲል ለመግደላዊት ማርያም የተናገረው ይጠቀሳል (ዮሐ. 20፡17)። በብሉይ ኪዳን ዘመን ካህኑ ከመሥዋዕት በኋላ ደም ይዞ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የሚገባበት ሁኔታ በምሳሌነት ቀርቧል (ዕብ. 9፡12፥ 23-24)። የደሙ መሥዋዕት ተግባራዊ በሆነ ሁኔታ የተከናወነው መስቀሉ ላይ ነው። መስቀሉ ላይ የተከናወነው ሥራ ጥቅሞች ለአማኞች መዋላቸው ዛሬም ይቀጥላል (ዮሐ. 1፡7 )። ምንም እንኳ ቃሉ የተለያዩ ፍቺዎች ቢሰጡትም፥ አብዛኛዎቹ የወንጌል አማኞች ዮሐንስ 20፡17 ውስጥ የተጠቀሰውንና “ዐርጋለሁ” የሚለውን ቃል የወደፊት ጊዘ ገሳጭ አድርገው ይገነዘቡታል።  1103 ሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ አንድ ውስጥ እንደተጠቀሰው፥ የክርስቶስ ዕርገት በእርግጠኛነት መከናወኑን በተመለከተም ጥያቄ ተነሥቷል። ክርስቶስ በመፀነስና በመወለድ ወደ ምድር መምጣቱ እውነት እንደሆነ ሁሉ፥ ወደ ሰማይ የማረጉን እውነትነት ምንባቡ በሚገባ ይደግፋል። የክርስቶስን ዕርገት ለመግለጥ ሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 1 ውስጥ አራት የግሪክ ቃላት ጥቅም ላይ ውለዋል። “ከፍ ከፍ አለ” (ቁ.9)፥ “ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው፡” (ቁ.9)፥ “ሲሄድ” (ቁ. 30)፥ “ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው” (ቁ. 1)። እነዚህ አራት ገለጣዎች ጠቃሚ ናቸው፤ ምክንያቱም ቁጥር 11 ውስጥ ዳግም ምጽአቱ ልክ እንደ ዕርገቱ፥ ማለትም በዓይኖቻቸው እያዩት በአካል ደመናት እንደተቀበሉት ሁሉ፥ ሲመለስም ሁሉ እያየው በአካል እንደሚመለስ ተተንብዮአል (ሐዋ. 1:9-11)። ይህ ክፍል የሚያመለክተው ክርስቶስ የሚመጣው ቤተ ክርስቲያኑን ለመውሰድ ሳይሆን፥ መንግሥቱን ለመመሥረት መሆኑን ነው።  ለ. ክርስቶስ ሰማይ የመግባቱ ማረጋገጫ  ክርስቶስ ከምድር ወደ ሰማይ ማረጉ ብቻ ሳይሆን፥ እዚያ መድረሱም በተደጋጋሚ መገለጡ የዕርገቱን እውነተኛነት ያረጋግጣል። የከርስቶስን በሰማያዊ ሥፍራ መሆን አያሌ ምንባቦች ያሳያሉ (ሐዋ. 2፡33-36፤ 3፡21፤ 7፡55-56፤ 9፡3-6፤ 22፡6-8፤ 26፡13-15፤ ሮሜ 8፡34፤ ኤፌ. 1፡20-22፣ 4፡8-10፤ ፊልጵ. 2:6-11፤ 3፡20፤ 1ኛ ተሰ. 1፡10፣ 4፡16፤ 1ኛ ጢሞ. 3፡16፤ ዕብ. 1፡3፥ 13፣ 2-7፤ 4፡14፤ 6፡20፤ 7፡26፤ 8፡1፤ 9፡24፤ 10፡12-13፤ 12፡2፤ 1ኛ ዮሐ. 2፡1፤ ራእይ 1፡7፥ 13-18፤ 5፡5-12፤ 6፡9-17፤ 7:9-17፤ 14፡1-5፤ 19፡11-16)።  ሐ. የዕርገቱ ትርጉም  የክርስቶስ ዕርገት የምድራዊ አገልግሎቱን መጠናቀቅ ያስረዳል። ክርስቶስ ወደ ምድር በመምጣት ቤተልሔም ውስጥ እንደተወለደ ሁሉ፥ አሁን ደግሞ ወደ አባቱ ተመልሷል። ዕርገቱ በተጨማሪ የሚያስገነዝበው፥ ከትንሣኤው በኋላ ቀድሞ ወደነበረ ገናና ክብሩ መመለሱን ነው። ወደ ሰማይ ማረጉ፥ ምድራዊ ሥራውን ማጠናቀቁንና በአባቱ ቀኝ ወዳለው አዲስ ተግባር መግባቱን ያስገነዝባል።  ክርስቶስ በሰማያትና በምድር ሁሉ ላይ ጌትነቱን እንደጨበጠ አሁን ባለበት ሰማያዊ ስፍራ ሆኖ እውን ሊሆን ያለውን የፍጻሜ ድሉንና ዳግም ምጽአቱን ይጠብቃል። በአብ ቀኝ እንደተቀመጠም በተደጋጋሚ ተገልጧል (መዝ. 110፡1፤ ማቴ. 22 :44፤ ማር. 12፡36፤ 16፡19፤ ሉቃስ 20፡42-43፤ 22፡69፤ ሮሜ 8፡34፤ ኤፌ. 1፡20፤ ቈላ. 3፡1፤ ዕብ. 1፡3-13፤ 8፡1፤ 10፡12፤ 12፡2፤ 1ኛ ጴጥ. 3፡22)። በሰማያት የተቀመጠበት ዙፋን የአብ ነው፤ ይህን ምድራዊ ከሆነው የዳዊት ዙፋን ጋር አንድ በማድረግ ልናየው አይገባም። ምድር የክርስቶስ ዙፋን ማረፊያና የእግሩም መረገጫ ለመሆን በመጠባበቅ ላይ ናት (ማቴ. 25፡31)። የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደመሆኑ አሁን ያለው ስፍራ የክብርና የሥልጣን ነው።  መ. ክርስቶስ በአሁኑ ጊዜ በሰማይ የሚያከናውነው ተግባር  በአብ ቀኝ ተቀምጦ ባለው ክብሩ ከቤተ ክርስቲያን ጋር የሚያገናኙትንና በተምሳሌትነት የተጠቀሱ ሰባት ተግባራትን ያከናውናል፡- 1. እንደ የመጨረሻው አዳም እና የአዲሱ ፍጥረት ራስ፥ 2. አካሉ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ራስ በመሆን፥ 3. እንደ በጎቹ (የመንጋው) መልካም እረኛ፥ 4. ለቅርንጫፎቹ እንደ እውነተኛ የወይን ግንድ5. እንደ ሕንጻ ለምትቆጠረው ቤተ ክርስቲያን በማዕዘን ድንጋይነት፥ 6. የንጉሥ ካህናት ስብስብ ለሆነች ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ካህን በመሆን፥ 7. እንደ ሙሽሪት ለምትጠብቀው (ቤተ ክርስቲያን) እንደ ሙሽራዋ። እነዚህ ሁሉ ተምሳሌቶች ክርስቶስ በአሁኑ ጊዜ የሚያከናውናቸውን ተግባራት በሚገባ ይገልጣሉ። ይሁን እንጂ ዋናው አገልግሎቱ ቤተ ክርስቲያንን በመወከል በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት እንደ ሊቀ ካህን መቅረብ ነው።  በሊቀ ካህንነት አገልግሎቱ ውስጥ አራት ጠቃሚ እውነቶች ተገልጠዋል።  1. ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በላይ ሳለች እውነተኛይቱ ድንኳን ሊቀ ካህን በመሆን፥ በዓለም ላሉትና የራሱ ለሆኑት እንደ ሊቀ ካህን ሆኖ ሊያገለግል ወደ ሰማይ ገብቷል (ዕብ. 8፡1-2)። ወደ ሰማይ በዕረገ ጊዜ የሰማይ አባቱ የተቀበለው መሆኑ አንድ እውነትን ያሳያል፤ ይህም ምድራዊ እገልግሎቱ በአባቱ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ መሆኑን ነው። በአብ ቀኝ መቀመጡም በዓለም የሚያከናውነው ተግባር መጠናቀቁን ያመለክታል።  በራሱ ሳይሆን በአባቱ ዙፋን መቀመጡ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በቋሚነትና ባለማቋረጥ የሚያስገነዝበን፥ በመጀመሪያ ምጽአቱ ወቅት መንግሥቱን ምድር ላይ አለመመሥረቱን ነው። መንግሥቱን በምድር መመሥረቱ ወደፊት የሚጠበቅ” ሲሆን፥ ያኔ መለኮታዊ ፈቃዱ በሰማይ እንደሆነ በምድርም ይሆናል።ያኔ የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፥ ከዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል” (ራእይ 11፡15) የተባለው ይፈጸማል። ንጉሥ የሆነው ልጅ ያኔ መንግሥትን ከአባቱ ይለምናል፥ አባቱም አሕዛብን ለርስቱ፥ የምድርንም ዳርቻ ስግዛቱ ይሰጠዋል (መዝ. 2፡8)።  ይህን መንግሥቱኝ አሁን በምድር እንዳልመሠረተ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ያመለክታል (ማቴ. 25፡31-46)። ሆኖም ሰማያዊ ዜጋ የሚሆኑ ሕዝቦችን ከአይሁድና ከአሕዛብም አሁን በምድር እየጠራ ነው። ይህ ሕዝብም እካሉና ሙሽራው የሆነች ሴት ክርስቲያን ናት። የአሁኑ ጊዜ ዕቅድ ሲያበቃ፥ ወደ ምድር ይመለስና “የወደቀችውን የዳዊትን ድንኳን እንደገና እሠራታለሁ” የሚለውን ትንቢት ይፈጽማል (ሐዋ. 15፡16፥ እንዲሁም ከቁጥር 13 እስከ 18 ያለውን ይመልከቱ)። ምንም እንኳን እርሱ እንደ መልከ ጼዴቅ ንጉሥና ካህን ቢሆን (ዕብ. 5፡10፤ 7፡1)፥ በአሁኑ ጊዜ እንደ ንጉሥ ሳይሆን እንደ ካህን ነው በማገልገል ላይ ያለው። ዳግም ሊመጣና የነገሥታት ንጉሥ ሊሆን ያለው ወደ ሰማይ ዐርጓል። “ከሁሉ በላይ ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው። እርስዋም አካሉና ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላቱ ናት” (ኤፌ. 1፡22-23)።  2. ክርስቶስ ሊቀ ካዘናችን እንደመህን የመንፈሳዊ ስጦታዎች ሁሉ ለጋሽ ነው። አዲስ ኪዳን እንደሚነግረን፥ መንፈሳዊ ስጦታ ለአማኝ የሚሰጥና በመለኮታዊ ኃይል የሚታገዝ ችሎታ ሲሆን፥ የሚሰጠውም አማኙ ውስጥ በሚያድረው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ነው። ይህም መንፈስ ቅዱስ በውስጡ ያደረበትን ሰው ተጠቅሞ መለኮታዊ ሥራዎችን ለማከናወን የሚሠራው ሥራ ነው። ይህ ሙሉ በሙሉ በመንፈስ ቅዱስ የሚከናወን ስለሆነ፥ በምንም ሁኔታ በመንፈስ ቅዱስ የተረዳ የሰዎች ሥራ ሊባል አይገባም።  መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተለያዩ ስጦታዎች ቢጠቀሱም (ሮሜ 12፡3-8፤ 1ኛ ቆሮ. 12፡4-11)፡በምንም አኳኋን ሁለት ነፍሳት ተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ሊኖሩ ስላማይችሉ የስጦታዎቹ መለያየት ያዚያኑ ያህል በርካታ ስጦታዎች እንዲኖሩ ያደርጋል። ይሁን እንጂ ስጦታዎቹና ኃይላቸው በግብር የሚታዩት የአማኙ ሕይወት ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር ሲሰጥ ነው (ሮሜ 12፡1-2፥ 6-8)። እያንዳንዱ አማኝ መንፈሳዊ ስጦታ ተሰጥቶታል። በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ እማኝ እግዚአብሔር የሚከበርበትን ሥራ በተመለከተ እምብዛም ማደፋፈር አያሻውም፤ ማድረግንም፥ ፈቃዱንም ሰሰውዬው ውስጥ የሚያኖረው መንፈስ ቅዱስ ነው (ፊልጵ. 2፡13)።  የዐረገው ጌታ አንዳንድ ሰዎችን እንደ ስጦታ ሰጥቷል። ኤፌሶን 4፡7-11 ውስጥ “ለሰዎችም ስጦታን ሰጠ” በማለት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ የሆኑትን ይዘረዝራል። እነዚህንም በየአጥቢያው አድርጓል። ጌታ ይህን ተግባር ብቃትና እርግጠኛነት አጎደሰው የሰዎች አሠራር አልተወም (1ኛ ቆሮ. 12፡11፥ 18)።  3. የፀረገው ክርስቶስ እንደ ዘላለማዊ ሊቀ ካህን የራሱ ለህኑት እየማለደ ይኖራል። ይህን አገልግሉቱን የጀመረው ገና በዓለም ሳለ ሲሆን (ዮሐ. 17፡1-26)። እገልግሎቱም ለዳኑት እንጂ ላልዳኑ ሰዎች አይደለም (ዮሐ. 17፡9)። ይህ ተግባር የርሱ የሆኑት በዓለም እስካሉ ድረስ በሰማይ ይቀጥላል። የመማለድ ተግባሩ በምድር ያሉ ቅዱሳንን ደካማነት፥ አጋር የለሽነትና፥ አለመብሰል ይመሰክታል። እነዚህ ነገሮች ቅዱሳኑ በምንም አኳኋን በደለኞች የሚሆኑባቸው አይደሉም። የቅዱሳኑን ድካም የሚረዳ፥ የጠላታቸውን ኃይልና ዓላማ የሚያውቅ ይህ ጌታ እረኛቸውና የነፍሳቸው ሊቀ ጳጳስ ነው። ለጴጥሮስ ያደርግለት የነበረ ጥበቃ የዚህ እውነት መገለጫ ነበር (ሉቃስ 22፡31-32)።  የክርስቶስ ካህናዊ ምልጃ

እግዚአብሔር ወልድ፡- ዕርገቱና የክህነት አገልግሎቱ Read More »

እግዚአብሔር ወልድ፡ትንሣኤው

This entry is part 10 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ሀ. ትንሣኤ በብሉይ ኪዳን  የሰዎችን ሁሉ ትንሣኤና የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ የሚያመለክት አስተምህሮ ብሉይ ኪዳን ውስጥ አለ። አስተምህሮው ቀደም ሲል ምናልባት በአብርሃም ዘመን ይኖር እንደነበር በሚገመተው ከኢዮብ ጊዜ ጀምሮ ነበር፤ ኢዮብ ሰእምነት መግለጫው እንዲህ ብሏል። “እኔን የሚቤዠኝ ሕያው እንደሆነ፥ ሰመጨረሻም ዘመን በምድር ላይ እንዲቆም፥ ይህ ቁርበቴም ከጠፋ በኋላ፥ በዚያን ጊዜ ከሥጋዬ ተለይቼ እግዚአብሔርን እንዳይ አውቃለሁ፥ እኔ ራሴ አየዋለሁ፥ ዓይኖቼም ይመልከቱታል፥ ከእኔም ሌላ አይደለም። ልቤ በመናፈቅ ዝሎአል” (ኢዮብ 19፡25-27)። ኢዮብ በዚህ ቃሉ የሚያረጋግጠው የራሱን ትንሣኤ ብቻ ሳይሆን፥ አዳኝ የሆነ ጌታው ሕያው እንደሆነና ሰኋላም በምድር ላይ የሚቆም መሆኑን ጭምር ነው። ሰዎች ሁሉ በዘመን ፍጻሜ የሚነሡ የመሆኑ ትምህርት ዮሐንስ 5፡28-29 እና ራእይ 20፡4-6፥ 12-13 ውስጥ ይገኛል።  ብሉይ ኪዳን ውስጥ የተለያዩ ትንቢቶች ስለ ሰው አካል ትንሣኤ ይናገራሉ (ኢዮብ 14፡13-15፤ መዝ. 16፡9-10፤ 17፡15፤ 49፡15፤ ኢሳ. 26፡19፤ ዳን. 12፡2፤ ሆሴዕ 13፡14፤ ዕብ. 11፡17-19)። የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ መዝሙረኛው ዳዊት፥ “ስለዚህ ልቤን ደስ አለው፥ ምላሴም ሐሴት አደረገች፤ ሥጋዬ ደግሞ በተስፋ ታድራለች፤ ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፥ ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም” (መዝ. 16፡9-10) ባለው ክፍል በግልጥ ተነግሯል። ዳዊት በዚህ ክፍል የሚገልጠው፥ በተስፋ ስለሚጠብቀው የግል ትንሣኤው ብቻ ሳይሆን “ቅዱስህን” ብሎ የሚጠራው ኢየሱስም  መበስበስን እንደማያይ ያረጋግጣል። ይህ የዳዊት ቃል የክርስቶስን ትንሣኤ በሚያመለክትበት ሁኔታ ሰጴጥሮስ ስብከት ውስጥ (ሐዋ. 2፡24-31)፥ እንዲሁም በጳውሎስ ስብከት ውስጥ (ሐዋ. 13፡34-37) ተጠቅሷል።  የክርስቶስ ትንሣኤ መዝሙረ ዳዊት 22፡22 ውስጥም ክርስቶስ ራሱ ከሞቱ በኋላ ስሙን “ለወንድሞቹ” የሚገልጥ መሆኑን ባስገነዘበበት ሥፍራም ተመልክቷል። ክርስቶስ ከፍ ከፍ ብሎ የማዕዘን ራስ እንደሚሆን መዝሙረ ዳዊት 118፡22-24 ውስጥ የተገለጠው፥ በሐዋርያት ሥራ 4፡10-11 ላይ የኢየሱስን ትንሣኤ በማጉላትና በማብራራት ተጠቅሷል። የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ብሉይ ኪዳን ውስጥ በመልከ ጼዴቅ ተምሳሌትነት የተተነበየ ይመስላል (ዘፍጥ. 14፡18፤ ዕብ. 7፡15-17፥ 23-25)። በተመሳሳይ ሁኔታ ዘሌዋውያን 14፡4-7 ውስጥ ስለ ለምጻሙ ሰው ክሚቀርቡት ሁለት ወፎች ውስጥ የሚለቀቀው ወፍ እና የመከሩ በኩራት (ዘሌ. 23፡10-11) ተምሳሌቶች ክርስቶስ የትንሣኤ በኩራት እንደሆነ ያመለክታሉ። ያቆጠቆጠችው የአሮን በትርም (ዘኁ. 17፡8) ስለ ትንሣኤ ታመለክታለች። ስለዚህ የሰው ሁሉና የክርስቶስ ትንሣኤ ብሉይ ኪዳን ውስጥ በሚገባ ተረጋግጧል።  ለ. ክርስቶስ ስለራሱ ትንሣኤ፥ የተናገራቸው ትንቢቶች  ክርስቶስ በወንጌሎች ውስጥ ስለ ሞቱና ትንሣኤው በተደጋጋሚ አስቀድሞ ተናግሯል (ማቴ. 16፡21፤ 17፡23፤ 20፡17-19፤ 26፡12፥ 28-29፥ 31-32፤ ማር. 9፡30-32፤ 14 ፡28፤ ሉቃስ 9፡22፤ 18፡31-34፤ ዮሐ. 2፡19-22፤ 10፡17-18)። ትንቢቶቹ በጣም የተደጋገሙ፥ ግልጥ እና ክርስቶስ የራሱን ሞት እራሱ የተነበየ ለመሆኑ በማያጠያይቅ ሁኔታ በብዙ ተዛማጅ ሁኔታዎች የተገለጡ ናቸው። የእነዚህ ትንቢቶች መፈጸምም ትክክለኛነታቸውን ያረጋግጣል።  ሐ. የክርስቶስ ትንሣኤ ማረጋገጫዎች  አዲስ ኪዳን የክርስቶስን ትንሣኤ እስመልክቶ እጅግ ብዙ ማረጋገጫዎችን ያቀርባል። ክርስቶስ ከትንሣኤው በኋላ ቢያንስ ለአሥራ ሰባት ጊዜ ታይቷል። እነዚህም፡(1) ለማርያም መግደላዊት (ዮሐ. 20፡11-17፤ ማር. 16፡9-11)፥ (2) ለሴቶች (ማቴ. 28፡9-10)፥ (3) ለጴጥሮስ (ሉቃስ 24፡34፤ 1ኛ ቆሮ. 15፡5)፥ (4) በኤማሁስ መንገድ ላይ ለደቀ መዛሙርቱ (ማር. 16፡12-13፤ ሉቃስ 24፡13-35)፥ (5) ለአሥሩ ደቀ መዛሙርት (እዚህ ላይ “አሥራ አንዱ” ይላል፥ ግን አሥር ናቸው።) ምክንያቱም ቶማስ በወቅቱ በቦታው አልነበረም (ማር. 16፡14፤ ሉቃስ 24፡36-43፤ ዮሐ. 20፡19-24)፥ (6) ከትንሣኤው ከአንድ ሳምንት በኋላ ለአሥራ አንዱ ደቀ መዛሙርት (ዮሐ. 20፡26-29)፥ (7) በገሊላ ባሕር አጠገብ ለሰባቱ ደቀ መዛሙርት (ዮሐ. 21፡1-23)፥ (8) ለአምስት መቶ ሰዎች (1ኛ ቆሮ. 15፡6)፥ (9) ለያዕቆብና ለጌታ ወንድም ለዮሐንስ (1ኛ ቆሮ. 15፡7)፥ (10) በገሊላ ተራራ ላይ ለአሥራ አንዱ ደቀ መዛሙርት (ማቴ. 28፡16-20፤ 1ኛ ቆሮ. 15፡7) ፥ (11) በደብረ ዘይት ተራራ በዕርገቱ ወቅት ለደቀ መዛሙርቱ (ሉቃስ 24፡44-53፤ ሐዋ. 1፡3-9)፥ (12) ሰማዕቱ እስጢፋኖስ ከመሰዋቱ በፊት ሰአባቱ ቀኝ ሆኖ (ሐዋ. 7፡55-56)። (13) ደማስቆ መንገድ ላይ ለጳውሎስ (ሐዋ. 9፡3-6፤ 22፡6-11፤ 26፡13-18፤ 1ኛ ቆሮ. 15፡8)። (14) በዐረቢያ ምድር ለጳውሎስ (ሐዋ. 20፡24፤ 26፡17፤ ገላ. 1፡12፥ 17) 15) ቤተ መቅደስ ውስጥ ለጳውሎስ (ሐዋ. 22፡17-21፤ 9፡26-30፤ ገሳ. 1፡18)፡(16) ቂሳሪያ እስር ቤት ለጳውሎስ (ሐዋ. 23፡11)፥ (17) ለሐዋርያው ዮሐንስ (ራእይ 1፡12-20)።  እነዚህ በብዙ የተለያዩ ሁኔታዎች የተፈጸሙ መታየቶች እና በዙሪያቸው ያሉ ማረጋገጫዎች ሁሉ ክርስቶስ ከሞት የተነሣ መሆኑን የሚመሰክሩ ብርቱ የታሪክ ማረጋገጫዎች ናቸው።  መታየቱን አስመልክቶ ከቀረቡት ማረጋገጫዎች አያሌ ተጨማሪ ማስረጃዎች ለመጥቀስ ይቻላል። ክርስቶስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ መቃብሩ ባዶ ነበር (ማቴ. 28፡6፤ ማር. 16፡6፤ ሉቃስ 24፡3፥ 6፥ 12፤ ዮሐ. 20፡2፥ 5-8)። የክርስቶስ ትንሣኤ ምስክሮች ድልሎችና በቀላሉ የሚታለሉ እለመሆናቸው እርግጥ ነው። እንደውም ማረጋገጫዎችን ለመገንዘብ የዘገዩ ነበሩ (ዮሐ. 20፡9፥ 11-15፥ 25)። የትንሣኤውን እውነት ከጨበጡ በኋላ ግን፥ በክርስቶስ ላላቸው እምነት ለመሞት ዝግጁ ሆኑ። ከትንሣኤው በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ለውጥ ታይቶባቸዋል። ኀዘናቸው በደስታና በእምነት ተተክቷል።  ከክርቶስ ትንሣኤ በኋላ በደቀ መዛሙርቱ ስለተከናወነው የመንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ ኃይል፥ ስላወጁት የምሥራች ቃል ኃይል እና ያን ይደግፉ የነበሩትን የማረጋገጫ ተአምራት የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ይመሰክራል። የጰንጠቆስጤ ዕለት ሌላው ጠቃሚ ማረጋገጫ ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ እውነት ባይሆን ኖሮ በዚህ ዕለት ሦስት ሺህ ሰዎችን ለማሳመን እይቻልም ነበር። ይህ የትንሣኤ ቃል አፈ ታሪክ ብቻ ቢሆን ኑሮም እነዚያ ሰዎች ማስረጃውን የመመርመርና የማረጋገጥ ዕድል ነበራቸው።  ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን የምታከብረው የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን፥ ከምትፈጽመው ሥርዓቶች ደግሞ የጌታ እራትና ይቀርብ የነበረው መባ ሌሎቹ ታሪካዊ ማረጋገጫዎች ናቸው (ሐዋ. 20፡7፤ 1ኛ ቆሮ. 16፡2)። ክርስቶስ ከሞት ባይነሣ ኖሮ። ሐዋርያቱ የተሰደዱና የተገደሉባት ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ጸንታ የመኖሯ እውነት ያለ በቂ መግለጫ ይቀር ነበር። የክርስቶስ አካላዊ ትንሣኤ ነው አካሉ የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን ለሰማያዊ ሥራዋ ብቁ የሚያደርጋት።  መ. የክርስቶስ ትንሣኤ ምክንያቶች  ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ ቢያንስ ሰባት ዋና ዋና ምክንያቶችን ለመጥቀስ ይቻላል።  1. የክርስቶስ ትንሣኤ አማንነቱ የሚመነጭበመሪን(ሐዋ. 2፡24)።  2. ለዳዊት የተሰጠን ቃል ኪዳን ለመፈጸም (2ኛ ሳሙ. 7፡12-16፤ መዝ. 89፡20-37፤ ኢሳ. 9፡6-7፤ ሉቃስ 1፡31-33፤ ሐዋ. 2፡25-31)።  3. የትንሣኤ ሕይወትን ለመስጠት (ዮሐ. 10፡10-11፤ 11፡25-26፤ ኤፌ. 2፡6፤ ቆላ. 3፡1-4፤ 1ኛ ዮሐ. 5፡11-12)።  4. የትንሣኤ ኃይል ምንጭ ለመሆን (ማቴ. 28፡18፤ ኤፌ. 1፡19-21፤ ፊል. 4፡13)።  5. የቤተ ክርስቲያን ራስ ለመሆን(ኤፌ. 1፡20-23)።  6. ጽድቃችን ስለተከናወነልን(ሮሜ 4፡25)።  7. የትንሣኤ በኩርዕመናን(1ኛ ቆሮ. 15፡20-23) ነው።  ሠ. የክርስቶስ ትንሣኤ ጠቃሚነት  የክርስቶስ ትንሣኤ ከታሪካዊነቱ የተነሣ የመለኮታዊነቱ ዋና ማረጋገጫ ነው። ትንሣኤው በሞትና በኃጢአት ላይ ታላቅ ድል እንደመሆኑ፥ ኤፌሶን 1፡19-21 ላይ እንደተጠቀሰው የዘመናችን መለኮታዊ ኃይል መለኪያም ነው። ትንሣኤ እንዲህ ያለ ጠቃሚ አስተምህሮ በመሆኑ፥ በዘመናችንም የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ለኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ መታሰቢያነት ተለይቷል። ይህ ሰንበት እስራኤላውያን እንዲያከብሩት ከታዘዙበት የሰባተኛው ቀን የሰንበት ሕግ ይልቃል። ስለዚህ ትንሣኤ ለክርስትና እምነት የማዕዘን ድንጋይ ነው። ጳውሎስ 1ኛ ቆሮ. 15፡17 ውስጥ “ክርስቶስ ካልተነሣማ እምነታችን ከንቱ ነው፤ ገና በኃጢአታችሁ ናችሁ” እንዳለው ትንሣኤውን በእርግጠኛነት እንናገራለን፥ ክርስቶስ ከሞት ስለተነሣ እምነታችን እርግጠኛ፥ ድል አድራጊነቱን እውነት፥ የክርስትና እምነታችንን ደግሞ ፍጹም ያደርገዋል። ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

እግዚአብሔር ወልድ፡ትንሣኤው Read More »

እግዚአብሔር ወልድ፡የምትክነት ሞቱ

This entry is part 9 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ኢየሱስ ክርስቶስ የሞተው ለዓለም ሁሉ ኃጢአት መሥዋዕትነት መሆኑ በመጽሐፍ ቅዱስ ተገልጧል። በዚሁ መሠረት መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስን ሲያስተዋውቅ፡- የዓለምን ሁሉ ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” (ዮሐ. 1፡29) ብሏል። ኢየሱስ የሞተው ለሌሎች መሥዋዕትነትና ምትክነት ነው። “ምትክ” የሚለው ቃል በግልጥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባይሆንም፥ ኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢአተኞች ምትክ የመሆኑ እውነት ግን በመጽሐፍ ቅዱስ በሚገባ ተረጋግጧል። ክርስቶስ በምትክነት ሞቱ የማይለካውን እግዚአብሔር በኃጢአተኞች ላይ ያለውን የጽድቅ ፍርድ ተሸከመ። የዚህ የምትክነት ጸጋ ውጤት ግልጥና፥ የተከናወነም ነው። አዳኝ የሆነው ክርስቶስ የእግዚአብሔርን ቁጣ ሊያበርድ በሚችል ሁኔታ በኃጢአተኞች ሳይ የነበረውን መለኮታዊ ፍርድ ተሸክሟል። ሰዎች ይህን የእግዚአብሔር ማዳን ተቀብለው የምሥራቹን እንዲያምኑ፥ ክርስቶስ ስለ ኃጢአታቸው መሞቱን እንዲገነዘቡ እና እርሱ የግል አዳኛቸው መሆኑን እንዲቀበሉ ተጠይቀዋል።  “ምትክነት” የሚለው ቃል፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት አማካይነት የተፈጸመውን ሥራ በከፊል ብቻ ይገልጣል። በመሠረቱ ይህን ሥራ የሚገልጥ አጠቃላይ ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጥቅም ላይ አልዋለም። “ሥርየት” የሚለው ቃል ትምህርተ-መለኮት ውስጥ ብዙ ጊዜ አጠቃላይ ገላጭ ሆኖ አገልግሏል። ይሁን እንጂ በብሉይ ኪዳንም ሆነ አዲስ ኪዳን ውስጥ የተጠቀሰ ተመሳሳይ ቃል የሰውም። ብሉይ ኪዳን ውስጥ የሥርየት ጽንሰ አሳብ ያገለገሰው ኃጢአተኛ በሚያቀርበው መሥዋዕት አማካይነት ኃጢአት ለጊዜው የመሸፈኑን ተግባር ለመግለጥ ነበር። ይህ ድርጊት ለጊዜያዊ ይቅርታ መሠረት ሆኗል። “ይህም በፊት የተደረገውን ኃጢአት በእግዚአብሔር ችሎታ ስለመተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው” (ሮሜ 3፡25)። እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ዘመን ኃጢአትን ይቅር በማለት ፍጹም በሆነ ጽድቅ ይሠራ ነበር። ኃጢአትን ለጊዜው መሸፈን ብቻ ሳይሆን፥ ለዘላለም የሚያስወግደውንና እንደ መሥዋዕት በግ የሚሆነውን የልጁን መምጣትም አስቀድሞ አቅዷል (ዮሐ. 1፣ 29)።  ሀ. የልጁ ሞት የሚያከናውናቸው ነገሮች  የኢየሱስ ክርስቶስን ሞት ሙሉ ዋጋ ለማገናዘብ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በርከት ያሉ ጠቃሚ እውነቶች ተጎልጠዋል።  1. የክርስቶስ ምታ እግዚአብሔር ለኃጢአተኞች ያለውን ፍቅር ያረጋግጣል (ዮሐ. 3፡16፤ ሮሜ 5፡8፤ 1ኛ ዮሐ. 3፡16፤ 4፡9)። አማኝ በእግዚአብሔር የመወደዱ እውነት፥ አማኝን የማያምን ሰው በማይችለው ላቅ ያለ ሥነ-ምግባራዊ ኑሮ መኖር የሚጠበቅበት ያደርገዋል (2ኛ ቆሮ. 5፡15፤ 1ኛ ጴጥ. 2፡11-25)።  2. የክርስቶስ ምታ፥ ኃጢአተኛውን ከኩነኔ ለመቤዠት የእግዚአብሔር ጻድቅ ፍርድለሚጠይቀው የቤዛነት ዋጋ የተከፈለ ነው ተብሏል። ኃጢአተኛውን ከእግዚአብሔር ጻድቅ ፍርድ ለማዳን የተከፈለ የቤዛነት ዋጋ ነው (ማቴ. 20፡28፤ ማር. 30፡45፤ 1ኛ ጢሞ. 2፡6)። የክርስቶስ ሞት ስለ ኃጢአተኛ የተከፈለ ተገቢ ቅጣት ነበር (ሮሜ 4፡25፤ 2ኛ ቆሮ. 5፡21፤ ገላ. 1፡4፤ ዕብ. 9፡28)።  ክርስቶስ ዕዳችንን በመክፈል ነጻ አወጣን። ይህን አሳብ ለመግለጥ ሦስት ጠቃሚ የግሪክ ቃላት አዲስ ኪዳን ውስጥ ተጠቅሰዋል።  (ሀ) “አጎራዞ፥ “ከበያ መግዛት” ማለት ይሆናል። (“አጎራ ማለት “ገበያ” ነው)። ሰው በኃጢአቱ ሳቢያ ከሞት ፍርድ በታች እንደሆነ ተቆጥሯል (ዮሐ. 3፡18-19፤ ሮሜ 6፡23)፥ ማለት “ለኃጢአት የተሸጠ” ባሪያ (ሮሜ 3፡14) ሆኗል። ነገር ግን የመቤዥት ተግባር በሆነውና የኢየሱስ ክርስቶስ ደም አማካይነት ተገዝቷል (1ኛ ቆሮ. 6፡20፤ 7፡23፤ 2ኛ ጴጥ. 2፡1፤ ራዕይ 5:9፤ 14፡3-4)።  (ለ) “ኤክሳጎራዞ”፥ “ጎዝቶ ከገበያ ማውጣት” ማለት ሲሆን፥ አሳቡ መግዛት ብቻ ሳይሆን፥ ከግብይት ማውጣትንም ያካትታል (ገላ. 3፡13፤ 4፡5፤ ኤፌ. 5፡16፤ ቆላ. 4፡5)፤ አባባሉ ነጻ የማውጣቱ ተግባር ለዘላለም መሆኑንን ያመለክታል።  (ሐ) “ሉትሮ፥ “መፍታት” ወይም “በነጻ መልቀቅ” (ሉቃስ 24፡21 ፤ ቲቶ 2፡14፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡18) ማለት ነው። ይህ ቃል ባሪያን ነጻ ማድረግን ያመለክታል (ሉቃስ 21:28፤ ሮሜ 3፡24፤ 8፡23፤ 1ኛ ቆሮ. 1፡30፤ ኤፌ. 1፡7፥ 14፤ 4፡30፤ ቆላ. 1፡14፤ ዕብ. 9፡15፤ 11፡35)። በዚሁ መሠረት መቤዥት የሚለው አሳብ፥ መግዛትን፥ ከግብይት ማውጣትን እና የተቤዠውን ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት፥ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ሥራ ፍጹም ነጻ ማውጣትን ይጨምራል።  የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ለኃጢአት የቀረበ መሥዋዕት ነው። መሥዋዕቱ በብሉይ ኪዳን ዘመን ይቀርብ እንደነበረውና ኃጢአትን ለጊዜው እንደሚሸፍነው፥ እንዲሁም የጽድቅን ፍርድ ያዘገይ እንደነበረው የእንስሳት መሥዋዕት ዓይነት አልነበረም። ክርስቶስ በመሥዋዕትነቱ ኃጢአታችንን ለዘላለም ተሸክሟል (ኢሳ. 53፡7-12፤ ዮሐ. 1፡29፤ 1ኛ ቆሮ. 5፡7፤ ኤፌ. 5 ፡2፤ ዕብ. 9፡22፥ 26፤ 10፡14)።  3. የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት፥ ኃጢአተኞች ለተላለፉት ሕግ ጋን ለመክፈል የታዛዥነት ተግባር ነው። ይህ መታዘዝ ኃጢአተኛ በበደሉ ምክንያት ይቀበሰው የነበረውን የእግዚአብሔር ፍጹም ፍርድ ያሟላል። ሄላስቴሪዮን” የሚለው የግሪክ ቃል ሲሆን፥ ማስተሥረያውን (ዕብ. 9፡5) ማለትም ቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ የነበረና በታቦቱ ውስጥ የነበረውን ሕግ የሸፈነ ኪዳንን የሚያመለክት ነው። ሰሥርየት ዕለት (ዘሌዋ. 16፡14) ማስተሥረያው ላይ ከመሠዊያው የተወሰደ ደም ይረጭበታል፤ ይህ ክንውን የፍርድን ዙፋን ወደ ምህረት ዙፋንነት ይቀይረዋል (ዕብ. 9፡11-15)። በተመሳሳይ ሁኔታ የእግዚአብሔር ዙፋን በኢየሱስ ክርስቶስ የማስተሥረይ ሥራ የጸጋ ዙፋን ይሆናል (ዕብ. 4፡14-16)።  የዚህ ቃል ተመሳሳይ የሆነውና ሂላስሞስ የሚለው የግሪክ ቃል የማስተሥረይን ተግባር ይገልጣል (1ኛ ዮሐ. 2፡2፤ 4፡10)። ትርጉሙ ክርስቶስ በመስቀል ሞቱ አማካይነት እግዚአብሔር ከሰው ኃጢእት የሚጠይቀውን ዋጋ (ሞት) ፍጹም በሆነ መንገድ አርክቷል ማለት ነው። ሮሜ 3፡25-26 ውስጥ እንደተገለጠው፥ እግዚአብሔር ኃጢአትን ይቅር በማለቱ ጳድቅ ተብሏል። ይህ በመስቀሉ ፊት የሚደረግ ይቅርታ፥ በመጨረሻ ጊዜ ክርስቶስ በሞቱ የጽድቅን ጥያቄ ሙሉ በሙሉ የሚያረካ የመሆኑ መሠረት ነበር። በዚህ ሁሉ እግዚአብሔር ኃጢአተኛን በመቅጣት የሚረካ ሆኖ አልታየም። ይልቁንም የፍቅር አምላክ ስለሆነ ኃጢአተኛውን ይቅር በማለት ደስ የሚሰኝ መሆኑ ተገልጧል። የሥርየትና የመቤዥት ተግባር፥ በክርስቶስ ለሚያምን ሰው ሁሉ ዕዳው ሙሉ ለሙሉ እንደተከፈለለት፥ ከኃጢአት ባርነት ነጻ መውጣቱ እና ኃጢአተኛ ይደርስበት የነበረ የእግዚአብሔር ቁጣ ሙሉ ለሙሉ የቀረለት መሆኑን ያረጋግጣል።  4. የክርስቶስ ምት ኃጢአተኛውን የዋጀና ሥርየት ያመጣለት ብቻ ሳይሆን፥ እግዚአብሔርን ያረካና ዓለም ከእርሱ ጋር የታረቀበት መሠረትም ነው። ካታላሶ፡የሚለውና “ማስታረቅ” የሚል ትርጉም ያለው የግሪክ ቃል ሰውን ሙሉ በሙሉ መለወጥ ከእግዚአብሔር ጋር ማገናኘት የሚል አሳብ አለው። ይህ ማስታረቅ የሚል ቃል አዲስ ኪዳን ውስጥ ብዙ ቦታ ተጠቅሷል (ሮሜ 5፡10-11፤ 11፡15፤ 1ኛ ቆሮ. 7፡11፤ 2ኛ ቆሮ. 5፡18-20፤ ኤፌ. 2፡16፤ ቆላ. 1፡20-21)። መታረቅ በሚለው ቃል ውስጥ ያለው ፅንሰ-አሳብ፥ እግዚአብሔር ይለወጣል ማለት ሳይሆን፥ በክርስቶስ ነጻ የማድረግ ሥራ አማካይነት ከሰው ጋር ያለው ግንኙነት ይቀየራል ማለት ነው። ሰው ነው ይቅር የተባለ፥ የጸደቀ እና ከእግዚአብሔር ጋር ሊታረቅ በሚችልበት ደረጃ በመንፈስ ካፍ ያስ። አሳቡ የሚገልጠው እግዚአብሔር ከኃጢአተኛ ጋር መታረቁን ማለትም ከኃጢአተኝነት ጋር መስማማቱ ሳይሆን፥ ኃጢአተኛው ከእግዚአብሔር ቅዱስ ባሕርይ ጋር እንዲስተካከል መደረጉን ነው። እግዚአብሔር ዓለምን በሞላ ነጻ እንዳደረገና ለኃጢአት ሁሉ ሥርየትን እንደሰጠ፥ እርቅም እንዲሁ የተሰጠ ነው፤ ሆኖም ዓለም ሁሉ ይህን እልተጠቀመበትም (2ኛ ቆሮ. 5፡19፤ 2ኛ ጴጥ. 2፡1፤ 1ኛ ዮሐ. 2 ፡1-2)። ይህ የእግዚአብሔር መቤዥት አስደናቂ ስጦታ ከሁሉ የላቀ ዋጋ ያለው ነው። ሥርየትና የማስታረቅ ሥራም እንዲሁ ናቸው፤ ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን፥ እግዚአብሔር በዚህ ስጦታው አማካይነት ከዓለም ጋር ይታረቃል(2ኛ ቆሮ. 5፡18-19፤ ኤፌ. 2፡16)።  5. በክርስቶስ ምት የሰውን ልጅ ከውድቀቱ የሚያመጣ የኃጢአት ዕዳ ተከፍሏል። በዚሁ መሠረት እግዚአብሔር የሥርየት ዋጋን በመከፈል ሰውን ከራሱ ጋር አስታርቋል። ከእንግዲህ ወዲህ ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ግል አዳኙ የሚያምን ሰው ሁሉ እግዚአብሔር እንዳይቀበለው የሚያደርግ አንዳች እንቅፋት የለበትም (ሮሜ 3፡26)። ዓለማት ተሰብስበው ከሚያከናውኑት ነገር ሁሉ ይልቅ እግዚአብሔርን ያረካ የክርስቶስ ሞት ነው። በመሆኑም ይህ እርካታ የእግዚአብሔር ቅድስና ከኃጢአተኞች የሚፈልገውን ዋጋ በመክፈል ፍቅርና ኃይሉን እንዲለግስ አድርጎታል።  6. ክርስቶስ በሞቱ የኃጢአተኞችን ቅጣት ሰመሸከም የእነሱ ምትክ ሆኗል (ዘሌዋ. 16፡21፤ ኢሳ. 53፡6፤ ማቴ. 20፡28፤ ሉቃስ 22 ፡37፤ ዮሐ. 10፡11፤ ሮሜ 5፡6-8፤ 1ኛ ጴጥ. 3፡18)። ይህ እውነት ለድነት ወደ እግዚአብሔር ለሚቀርቡ ሁሉ የዋስትና መሠረት ነውዬ ማንኛውም ሰው ከእግዚአብሔር ጋር በሚኖረው ግንኙነት ኃጢአትን አስመልክቶ ያለውን ጥያቄ ሁሉ የሚፈታ እውነትም ነው። ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ሞቷል የሚለው አጠቃላይ እምነት በቂ አይደለም። ክርስቶስ ኃጢአቴን ተሸክሟል የሚል የግል እምነት ያስፈልጋል፤ ይህም ዕረፍት ደስታና እርካታን ያስገኛል (ሮሜ 15፡13፤

እግዚአብሔር ወልድ፡የምትክነት ሞቱ Read More »

እግዚአብሔር ወልድ፡- ሠግዎቱ

This entry is part 8 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

የክርስቶስን ሥጋ መልበስ በምናጤንበት ጊዜ ሁለት ዐበይት እውነቶችን ልብ ልንል ይገባል፡- 1) ክርስቶስ ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰው ሆኗል፥ 2) ሥጋ ሲለብስ፥ ምንም እንኳን ክብሩን ቢተው፥ በምንም ሁኔታ መለኮትነቱን አልጣስም። ሥጋ በለበሰ ጊዜ መሠረታዊ የመስኮትነት ባሕርያቱን እንደያዞ ነው። ሙሉ መለኮትነቱና ፍጹም ሰብአዊነቱ ለመስቀል ላይ ሥራው አስፈላጊ ነበሩ። ሰው ባይሆን ኑሮ እይሞትም፥ እግዚአብሔር ባይሆን ኑሮ ደግሞ፥ ሞቱ ዘላለማዊ ዋጋ አይኖረውም ነበር።  ሐዋርያው ዮሐንስ (ዮሐ. 1፡1) ከእግዚአብሔር ጋር አንድ የሆነውና ለዘላለም እግዚአብሔር የሆነው ክርስቶስ ሥጋ ሆኖ በእኛ ዘንድ እንዳደረ ይገልጣል (ዮሐ. 1፡14)። ጳውሎስም በእግዚአብሔር መልክ የነበረው ክርስቶስ፥ የሰውን ምሳሌ መያዙን ያስገነዝባል (ፊልጵ. 2፡6-7)። “አምላክ በሥጋ ተገለጠ’” (1ኛ ጢሞ. 3፡16)፤ የእግዚአብሔር ሙሉ ክብር መገለጥ ነጻብራቅ የሆነው ክርስቶስ፥ የባሕርዩ ምሳሌ ነው (ዕብ. 1፡3)። ሉቃስም የክርስቶስን መፀነስና መወለድ ታሪካዊ እውነት ሰፋ ባለ ዝርዝር አቅርቧል (ሉቃስ 1፡26-38፤ 2፡5-7)።  መጽሐፍ ቅዱስ አያሌ ማነጻጸሪያዎችን አቅርቧል። ክርስቶስ ፍጹም አምላክ እና ፍጹም ሰው ሆኖ መገለጡ ግን ከሁሉ ይልቃል። ይህን የመሰሉ የማነጻጻሪያ ጎለጣዎች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ናቸው። ደክሞት ነበር (ዮሐ. 4:6)፥ ነገር ግን ደካሞችን ሊያሳርፋቸው ወደ ራሱ ጠራቸው (ማቴ. 11፡28)። ተርቦ ነበር (ማቴ. 4፡2)፥ ነገር ግን ራሱ “የሕይወት እንጀራ ነው” (ዮሐ. 6፡35)። ተጠምቷል (ዮሐ. 19፡28)፥ ነገር ግን ራሱ የሕይወት ውኃ ነው” (ዮሐ. 7፡37)። ተሠቃየ (ሉቃስ 22፡44)፥ ነገር ግን ሰዎችን ከማንኛውም በሽታ ፈወሰ፥ ማንኛውንም ሕመም አስወገደ። “አደገ፥ በመንፈስም ጠነከረ” (ሉቃስ 2፡40)፥ ነገር ግን ከዘላለም በፊት ነበር (ዮሐ. 8፡58)። ተፈትኗል (ማቴ. 4፡1)፥ ሆኖም አምላክ በመሆኑ፥ ኃጢአትን አላደረገም። በእውቀት የተወሰነ ነበር (ሉቃስ 2፡52)፥ ነገር ግን ራሱ የእግዚአብሔር ጥበብ ነበር። ለጥቂት ጊዜ ሥጋን በመልበሱ ራሱን ዝቅ በማድረጉና በማዋረዱ ከመላእክት ትንሽ ማነሱን ይናገራል (ዕብ. 2፡6-7 )፤ “አባቴ ከእኔ ይበልጣል” (ዮሐ. 14፡28) ይልና “እኔን ያየ አብን አይቷል” (ዮሐ. 14 :9) እና “እኔና አባቴ አንድ ነን” (ዮሐ. 10፡30)፥ በማለት ንጽጽሩን ራሱ ያቀርበዋል። ጸልይዋል (ሉቃስ 6፡12)፥ ነገር ግን ራሱ ለጸሎት መልስ ይሰጣል (ሐዋ. 10፡31)። በመቃብር አጠገብ አለቀሰ ( ዮሐ. 11፡35)፥ ነገር ግን ራሱ ሙታንን ከመቃብር እንዲነሡ ይጣራል (ዮሐ. 11፡43)። “የሰውን ልጅ ሰዎች ማን ይሉታል?” በማለት ጠየቀ (ማቴ. 16፡13)፥ ነገር ግን ““ስለ ሰው ማንም እንዲመሰክርለት አልፈለገም፤ በሰው ውስጥ ያለውን ያውቅ ነበርና” (ዮሐ. 2፡25)። “አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ?” አለ (ማር. 15፡34)፥ ነገር ግን እርሱ የጮኸለት አምላክ በዚያን ሰዓት “ዓለሙን ሁሉ ከራሱ ጋር የሚያስታርቅ ነበር” (2ኛ ቆሮ. 5፡19)። ሞተ፤ ዳሩ ግን የዘላለም ሕይወት ነው። እርሱ ለእግዚአብሔር ምቹ የሆነ ሰው፥ ለሰው ምቹ የሆነ አምላክ ነው።  ከዚህ ሁሉ ለመረዳት የሚቻለው፥ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አንዳንድ ጊዜ ፍጹም ሰው ሆኖ የሚሠራ ሲሆን፥ በሌላ ጊዜ ደግሞ ፍጹም አምላክ በሆነ ሁኔታ ሲሠራ መታየቱን ነው። መለኮታዊ ሕላዌው ሰው በመሆኑ ምክንያት ከቶ ውሱን አልሆነም። መለኮታዊነቱን በምንም ዓይነት ለሰብአዊ ፍላጐቱ መገልገያነት አልተጠቀመበትም። ሰብአዊ ርሃቡን ለማርካት ድንጋዩን ወደ ዳቦነት ሊለውጠው ይችል ነበር፤ እርሱ ግን አሳደረገውም።  ሀ. ክርስቶስ ሰው የመሆኑ እውነት  1. ክርስቶስ ሰው የመሆን እውነት የታቀደውና የታለመው ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ነበር (ኤፌ. 1፡4-7፤ 3፡11፤ ራእይ 13፡8)። የእግዚአብሔር በግ የመባሉ ምሥጢር፥ ደም ለማፍሰስና መሥዋዕት ለመሆን አካለ ሥጋን በቅድመ ሁኔታነት የሚፈልግ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው።  2. በብሉይ ኪዳን ስለ ክርስቶስ ሥጋ መልበስ የተነገረው ምሳሌና ትንቢት፥ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን አስቀድሞ ለማሳወቅ ነበር።  3. የክርስቶስ ሰው የመሆን እውነት የተረጋገጠው፥ እንደማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር ተፀንሶ በመወለዱ ነው (ሉቃስ 1፡31-35)።  4. ምድራዊሕይወቱሰው መሆኑን አሳይቶአል። ይኽውም፡-  (ሀ.) በሰብአዊ ስሞቹ፥ “የሰው ልጅ”፥ “ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ”፥ “የዳዊት ልጅ” የሚሉትና የመሳሰሉት፥ በሰብአዊ ትውልዱ፤  (ሰ.) በሰብአዊ ውልደቱ፥“የወገብ ፍሬ”፥ “የበኩር ልጅዋ”፥ “የዚህ ሰው ዘር”፥ “የዳዊት ዘር”፥ “የአብርሃም ዘር”፥ “ከሴት የተወለደ”፥ “ከይሁዳ የወጣ መባሉ፤  (ሐ.) ሰብአዊ አካል፥ ነፍስና መንፈስ ያለው ስለመሆኑ (ማቴ. 26፡38, ዮሐ. 13፡21፤ 1ኛ ዮሐ.4፡2፡9) እና  (መ.) ራሱ ወዶ በወሰደው ሰብአዊ ውሱንነት።  5. የክርስቶስ ሰው መሆን በሞቱና በትንሣኤው ታይቷል። በመስቀል ላይ የሞተውም ሥጋ በሆነ አካሉ ሲሆን፥ መቃብርን አሸንፎ በትንሣኤው ክብር የተነሣውም በአካሉ ነበር።  6. የክርስቶስ ሰው የመሆን እውነት ወደ ሰማይ በማረጉ ታይቷል። አሁን ደግሞ በከበረ ሰውነቱ የራሱ የሆኑትን በማገልገል ላይ ነው።  7. ዳግም በሚመለስበት ጊዜም ያው “አንዱ ኢየሱስ” ወደ ሰማይ ባረዝት ነገር ግን በከበረ አካሉ)፥ በተሠግዎ ይመለሳል።  ለ. የተሠግዎው ምክንያቶች  1. የመጣው እግዚአብሔርን ለሰው ለማሳየት ነው(ማቴ. 11፡27፤ ዮሐ. 1፡18፤ 14:9፤ ሮሜ 5፡8፤ 1ኛ ዮሐ. 3፡16)። ሥጋ በመልበሱ ሰው ከአእምሮው በላይ የሆነውን እግዚአብሔርን እንዲረዳ አደረገ።  2. ሰውን ለመግለጥ መጣ። ኢየሱስ እግዚአብሔር የሚፈልገው ሰው ምሳሌ በመሆኑ፥ ለሚያምኑ ሁሉ አርአያ ነው (1ኛ ጴጥ. 2፡21)። ለማያምኑ ግን ከቶ ምሳሌ አይደለም። ምክንያቱም እግዚአብሔር በአሁኑ ዘመን የሚፈልገው ያልዳኑትን ለማሻሻል ሳይሆን፥ ስማዳን ነው።  3. ለኃጢአት መሥዋዕት ሊሆን መጣ፤ በመሆኑም ስለ ሰብአዊ አካሉ እና ይህ አካሉም ለኃጢአት ይቅርታ የተዘጋጀ በመሆኑ፥ እግዚአብሔርን ሲያመሰግን ታይቷል (ዕብ. 10፡1-10)።  4. የዲያብሎስን ሥራ ያፈርስ ዘንድ ሥጋ ለብሶ መጣ (ዮሐ. 12፡31፤ 16፡11፤ ቆላ. 2፡13-15፤ ዕብ. 2፡14፤ 1ኛ ዮሐ. 3፡8)።  5. ወደ ዓለም የመጣው፥ ይቅር ባይና ለእግዚአብሔር ታማኝ ሊቀ ካህን ይሆን ዘንድ ነው(ዕብ. 2፡16-17፤ 8፡1፣ 9፡11-12፥24)።  6. ሥጋ ለብሶ የመጣው፥ እግዚአብሔር ከዳዊት ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን ይፈጽም ዘንድ ነው (2ኛ ሳሙ. 7፡16፤ ሉቃስ 1፡31-33፤ ሐዋ. 2፡30-31፥36፤ ሮሜ 15፡8)። በዚሁ መሠረት በከበረ ሥጋው ይገለጣል፥ “የነገሥታት ንጉሥ፥ የጌቶችም ጌታን በመሆን ይነግሣል። በአባቱ በዳዊት ዙፋን ይቀመጣል (ሉቃስ 1፡32፤ ራእይ 19፡16)።  7. ሥጋለብሶ አዲስ የተፈጠረችው ቤተ ክርስቲያን ራስን(ኤፌ. 1፡22)።  የእግዚአብሔር ልጅ ሥጋ ሲለብስ ሰብአዊ አካልን ብቻ ሳይሆን፥ ሰብአዊ ነፍስና መንፈስንም ወስዷል። በዚህ ሁኔታ ቁሳዊውንና መንፈሳዊውን ሰብአዊነት ተሳበሰ። ሁለንተናዊ ሰው በመሆንም በቅርብና በቋሚነት የሰብአዊው ቤተሰብ አባል ሆኖ፥ “የኋለኛው አዳም” (1ኛ ቆሮ. 15፡45) ተባለ። “ክቡር ሥጋው” ተብሏልም (ፊልጵ. 3፡21)። ይህ አሁን ሕያው እውነት ነው።  ይህ ዘላለማዊ ልጅ፥ ያህዌ እምላክ፥ የማርያም ልጅ፥ የናዝሬት ወጣት፥ የይሁዳ መምህርና ፈዋሽ፥ የቢታንያ እንግዳ፥ የቀራንዮ በግ ነበር። አሁን የሰዎች አዳኝ፥ ወደፊት ደግሞ የክብር ንጉሥ፥ ሊቀካህን፥ የሚመጣው ሙሽራና ጌታ ይሆናል። ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

እግዚአብሔር ወልድ፡- ሠግዎቱ Read More »

እግዚአብሔር ወልድ፡ መለኮታዊነቱና ዘላለማዊነቱ

This entry is part 7 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

መጽሐፍ ቅዱስ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ፍጹም ሰውና ፍጹም መለኮት አድርጎ ያቀርበዋል። በዚህ መሠረት እንደ ማንኛውም ሰው ነው፥ አይደለም። በዮሐንስ 1፡14፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 3፡ 16 እና ዕብራውያን 2፡14-17 መሠረት፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰው የተወለደ፥ በሰዎች መካከል የኖረ፥ የተሠቃየ እና የሞተ መሆኑ ተገልጧል። ኢየሱስ ክርስቶስ ከዘላለም በፊት የነበረ በመሆኑ፥ እንደ ሰው አለመሆኑን፥ በሰብአዊነቱ ኃጢአትን የማያውቅ መሆኑን፥ ሞቱ ለዓለም ሁሉ ኃጢአት መሥዋዕት መሆኑን፥ ከሙታን ተለይቶ በመነሣትና ወደ ሰማይ በማረግ መለኮታዊ ኃይሉን የገለጠ መሆኑን በማስገንዘብ ረገድም መጽሐፍ ቅዱስ ግልጥ ነው።  በሰብአዊነቱ ጅማሬ ነበረው፤ ከመንፈስ ቅዱስ ተፀንሶ ከድንግል ማርያም ተወልዷል። በመለኮታዊነቱ ግን ከዘላለም በፊት የነበረ በመሆኑ ጅማሬ የለውም። ኢሳይያስ 9፡6 ውስጥ “ሕፃን ተወልዶልናል፤ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል” የሚል ትንቢት ተነግሮ ነበር። በተወለደ ሕፃንና በተሰጠ ልጅ መካከል ያለው ልዩነት ግልጥ ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ ገላትያ 4፡4 ውስጥ እንዲህ ተብሏል፡- “… የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን፥ ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ”። ዘላለማዊው የእግዚአብሔር ልጅ ሥጋ በመልበስ “ ከሴት ተወሰደ።  ክርስቶስ ከመወለዱ በፊት ነባሪ ነው፥ የሚለው ገለጣ ከመወለዱ በፊት መኖሩን በቀላሉ ያረጋግጣል። የፍጥረታት ሁሉ በኩር ሆኖ ብቻ ይኖር ነበር፥ የሚለው አስተሳሰብ (በአራተኛው ክፍለ ዘመን የነበረ አርዮሳዊ ኑፋቄን፥ የጊዜያችን ትምህርት አይደለም። ስለዚህ የቀዳሚ ነባሪነቱና የዘላለማዊነቱ ማረጋገጫዎች ጣምራ ናቸው። ክርስቶስ እግዚአብሔር ከሆን ዘላለማዊ መሆኑ፥ ዘላለማዊ ከሆነ እግዚአብሔርነቱ እርግጥ ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮትነትና ዘላለማዊነት የሚደጋገፉ ናቸው።  የኢየሱስ ዘላለማዊነትና መለኮትነት በሁለት መንገድ ተገልጧል፡- (1) ቀጥተኛ ገለጣ (2) በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጠ።  ሀ. የእግዚአብሔርን ልጅ ዘላለማዊነትና መለኮትነት ቀጥተኛ ገለጣ  የኢየሱስ ክርስቶስ ዘላለማዊነትና መለኮትነት እጅግ ሰፊ በሆነው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በተመዘገበው ቃል ተረጋግጧል። ይህም ከሴሳው የሥላሴ አካል ከአብ ጋር አቻነቱን፥ ፍጹምነቱንና ዘላለማዊነቱን ያረጋግጣል። ይህ እውነት ክርስቶስ ሥጋ በመልበሱ ሳቢያ አልተዛባም።  መጽሐፍ ቅዱስ ዮሐንስ 1፡ 1-2 ውስጥ የመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። “ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነው አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም” ይላል። በትንቢተ ሚክያስ 5፡2 ሲገለጥ ደግሞ  “አንቺ ቤተልሔም ኤፍራታ ሆይ! አንቺ ከይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፥ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤል ላይ ገዢ የሚሆን ይወጣልኛል” ተብሏል። ኢሳይያስ 7፡ 14 ውስጥ ደግሞ፥ ከድንግል መወለዱን አረጋግጦ እማኑኤል የሚል ስም ይሰጠዋል፤ ትርጉሙም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር” ማለት ነው። በኢሳይያስ 9፡6-7 መሠረት፥ ኢየሱስ እንደ ሕፃን ቢወለድም፥ እንደ ወንድ ልጅም የተሰጠ ነው። ይህ ብቻም አይደለም፥ “ኃያል አምላክ” ተብሏል። ክርስቶስ ራሱ ዮሐንስ 8፡58 ውስጥ ሲገልጥ፥ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ” ብሏል።  ይህ አገላለጥ፥ መለኮታዊነትንና ዘላለማዊነትን እንደሚያመለክት አይሁድ ተገንዝበዋል (ዘጸ. 3፡ 14፤ ኢሳ. 43፡13)። ዮሐንስ 17፡5 ውስጥ እንደተጠቀሰው ደግሞ፥ ክርስቶስ በጸሎቱ፥ “አሁንም አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አክብረኝ” ብሏል (ይህን ቃል ከዮሐ. 13፡3 ጋር ያነጻጽሩት)። ፊልጵስዩስ 2፡6-7 ውስጥ ክርስቶስ ሥጋ ከመልበሱ በፊት “በእግዚአብሔር መልክ” እንደነበር ተገልጧል።  ከሁሉም ግልጥ የሆነው ማስገንዘቢያ የሚገኘው፥ ቆላስይስ 1፡15-19 ውስጥ ነው። በዚያ ስፍራ ክርስቶስ ከፍጥረት በፊት እንደነበር፥ ራሱ ፈጣሪ እንደሆነ እናየማይታየው አምላክ ምሳሌ እንደሆነ ተገልጧል። 1ኛ ጢሞቴዎስ 3፡ 16 ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ “በሥጋ የተገለጠ አምላክ” ተብሏል። ዕብራውያን 1፡2-3 ውስጥም ወልድ ፈጣሪ እና የተገለጠ የእግዚአብሔር አምሳል መሆኑ እንደገና ተገልጧል። ዘላለማዊነቱም ዕብራውያን 13፡ 8 ውስጥ ተረጋግጧል (ይህን ማረጋገጫ ከኤፌሶን 1፡4፤ ራእይ 1፡8 ጋር ያነጻጽሩት)። ክርስቶስ ዘላለማዊ እና አምላክ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ አበክሮ ይገልጣል። ጥቂት ከሃዲ የአምልኮ ክፍሎች ሲቀሩ፥ መጽሐፍ ቅዱስ እጅግ ሥልጣን ያለው መሆኑን የሚቀበሉ የጊዜያችን ምሁራን ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘላለማዊና መለኮታዊ መሆኑን ያረጋግጣሉ።  ለ. የእግዚአብሔርን ልጅ ዘላለማዊነት የሚያመለክቱ ሁኔታዎች  የእግዚአብሔር ቃል፥ የኢየሱስ ክርስቶስን ከዘላለም በፊት ኗሪነትና ዘላለማዊነት በተከታታይና ባለማቋረጥ ያመለክታል። የዚህ እውነት ግልጥ ማረጋገጫ ከሆኑት አንዳንዶቹን ለመጥቀስ ይቻላል።  1. ተፈጥሮ በክርስቶስ እንደተከናወነ ተገልጧል(ዮሐ. 1፡ 3፤ ቆላ. 1፡16፤ ዕብ. 1፡ 10)። ስለዚህ ከፍጥረታት ሁሉ ይቀድማል።  2. የእግዚአብሔር መልአክ መታየቱ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ተመዝግቧል፤ የያዌ መልእክ ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ሌላ ሊሆን አይቻልም። አንዳንድ ጊዜ እንደ መልአክ ከዚያም አልፎ እንደ ሰው ቢታይም፥ የማያሳስት የመለኮትነት መገለጫ አለው። ለአጋር ተገልጧል፥ (ዘፍጥ. 16፡7)፥ ለአብርሃም (ዘፍጥ. 18፡ 1፤ 22 ፡ 11-12፤ በተጨማሪ ዮሐ. 8፡58ን ልብ ይብሉ)፥ ለያዕቆብ (ዘፍጥ. 48፡ 15-16፥ እንዲሁም ዘፍጥ. 31፡11-13፤ 32፡24-32)፥ ለሙሴ፥ (ዘጸ. 3፡2፥14)፥ ለኢያሱ፥ (ኢያ. 5፡13-14)፥ እና ለማኑሄ፥ (መሳ. 13፡ 19-22)። የራሱ ለሆኑ የሚዋጋና የሚጠብቃቸው እርሱ ነው (2ኛ ነገሥት 19፡35፤ 1ኛ ዜና 21፡ 15-16፤ መዝ. 34፡7፤ ዘካ. 14፡ 1-4)።  3. የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መጠሪያዎችና ማዕረጎች ዘላለማዊነቱን ያመለክታሉ። እርሱ በትክክል እንደ ስሙ ነው። “የእግዚአብሔር ልጅ”፥ “አንድያ ልጅ”፥ “የመጀመሪያውና የመጨረሻው ፥ “አልፋና ኦሜጋ”፥ “ጌታ”፡ (“የሁሉ ጌታ”፥ “የክብር ጌታ”፥ “ክርስቶስ”፥ “ድንቅ”፥ “መካር”፥ “ኃያል አምላክ”፥ “የዘላለም | አባት”፥ “እግዚአብሔር ከኛ ጋር”፥ “ታላቅ አምላካችን” እና “ለዘላለም የተባረከ አምላክ።  እነዚህ መጠሪያዎች ኢየሱስን በብሉይ ኪዳን ከተገለጠው ያህዌ- አምላክ ጋር ያዛምዱታል (ማቴ. 1፡23፥ ይህን ካኢሳ. 7፡ 14 ጋር ያነጻጽሩት፥ ማቴ. 4፡7ትን ደግሞ ከዘዳ. 6፡ 16 ጋር፥ ማር. 5፡ 19ን ከመዝ. 66፡ 16 ጋር እና ማቴ. 22፡42-45ትን ከመዝ. 110፡1 ጋር ያነጻጽሩ)።  አዲስ ኪዳን ውስጥ የተጠቀሱት የእግዚአብሔር ልጅ ስሞች ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ መጠሪያዎች ጋር ተዛምደዋል። ይህም ከአካላቱ ጋር ያለውን አቻነት ያመለክታል (ማቴ. 28፡19፤ ዮሐ. 14፡1፤ 17፡3፤ ሐዋ. 2፡ 38፤ 1ኛ ቆሮ. 1፡3፤ 2ኛ ቆሮ 13፡ 14፤ ኤፌ. 6፡23፤ ራዕ. 20፡6፤ 22፡3)። በማያሻማ ሁኔታም እግዚአብሔር ተብሏል (ዮሐ. 1፡ 1፤ ሮሜ. 9፡5፤ ቲቶ 2፡ 13፤ ዕብ. 1፡8)።  4. የእግዚአብሔር ልጅ ከዘላለም በፊት ኗሪነቱና ዘላለማዊነቱ፥ የእግዚአብሔር ባሕርያት ያሉት መሆኑን በሚያስገነዝቡት እውነቶች ውስጥ ተመልክቷል። ሕይወት (ዮሐ. 1፡4)። ኗሪ (ዮሐ. 5፡26)፥ የማይለወጥ ወይም የማይሻር (ዕብ. 13፡8)፥ እውነት (ዮሐ. 14፡6)፥ ፍቅር (1ኛ ዮሐ. 3፡ 16)፥ ቅድስና (ዕብ. 7፡26)፥ ዘላለማዊነት (ቆላ. 1፡17፤ ዕብ. 1፡ 1 1 )፥ በሁሉም ስፍራ መገኘት (ማቴ. 28፡20)፥ ሁሉን አዋቂነት (1ኛ ቆሮ. 4 ፡ 5፤ ቆላ. 2፡3) እና ሁሉን ቻይነት(ማቴ. 28፡ 18፤ ራእይ 1፡8)።  5. በተመሳሳይ ሁኔታ ከዘላለም በፊት ኗሪነቱና ዘላለማዊነቱ፥ እንደ እግዚአብሔር በመመሰኩ እውነት ውስጥ ተገልጧል (ዮሐ. 20፡28፤ ሐዋ. 7:59-60፤ ዕብ. 1፡6)። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር እንደመሆኑ፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ኗሪ ነው።  የእግዚአብሔር ልጅ መለኮትነትና ዘላለማዊነት ጉዳይ፥ ከክርስቶስ ከሰብአዊ ልደት ወይም ሥጋ መልበስ ጋር በቅርብ መያያዝ አለበት። ይህ ነው የሚቀጥለው ምዕራፍ መነጋገሪያችን። ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

እግዚአብሔር ወልድ፡ መለኮታዊነቱና ዘላለማዊነቱ Read More »

እግዚአብሔር አብ

This entry is part 6 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ሀ. አብ የመጀመሪያው አካል  አብ፥ ወልድ፥ መንፈስ ቅዱስን በሚገልጠው የሥላሴ ትምህርት፥ የመጀመሪያው አብ ይባላል። አብ፥ ወልድም ሆነ መንፈስ ቅዱስ በተናጠል ሥሉስ አይደሉም። ሥላሴ ሦስቱንም አካላት ይይዛል። ምንም እንኳ የአብ፥ የወልድና የመንፈስ ቅዱስ አስተምህሮ በብሉይ ኪዳን ሲሰጥና ይህ ቃል ለሥላሴ መጠሪያነት ያገለገለ ቢሆን፥ አዲስ ኪዳን ነው ሙሉውን አስተምህሮ የሚገልጠውና የሚያብራራው። አብ እንደ መራጭ፥ አፍቃሪና ለጋስ ተገልጧል። ወልድ እንደ ሕማም ሰው ፥ ተቤዥ እና ዓለማትን እንደሚይዝ ተገልጿል። መንፈስ ቅዱስ ዳግም ልደት የሚሰጥ፥ በሰው የሚያድር፥ የሚያጠምቅ፥ ኃያል የሚሰጥ እና የሚቀድስ ሆኖ ነው የተገለጠው። የአዲስ ኪዳን መገለጥ ዋና ጉዳይ፥ ኢየሱስ ክርስቶስን መግለጥ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ እግዚአብሔር ልጅ ሲገለጥ፥ የእግዚአብሔር አብ እውነትም አብሮ ይገለጣል። አብ ልጁን የላከበትና የሾመበት፥ ወልድ ደግሞ መንፈስ ቅዱስን የላከበትና የሾመበት ቅደም ተከተል የማይዛባ ሲሆን፤ ይህ የሥነ-መለኮት ትምህርት ሊገለጥ የማይቻለውን የወልድንና የመንፈስ ቅዱስን መለኮትነት በምንም ሳያሳንስ አብን የመጀመሪያው አካል አድርጎ የሚሰይም ነው።  የእግዚአብሔርን አባትነት በሚመለከተው መገለጥ ውስጥ አራት የተለያዩ ሁኔታዎች ይታያሉ። (1) እግዚአብሔር አብ እንደ ፍጥረት ሁሉ አባት፥ (2) እግዚአብሔር አብ በቅርብ ግንኙነት፥(3) እግዚአብሔር አብ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባት፥(4) እግዚአብሔር አብ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነትና ጌትነት ለሚያምኑ ሁሉ አባት ነው።  ለ. ለፍጥረት ሁሉ አባትነት  ምንም እንኳን በመፍጠር ተግባር፥ እንዲሁም ቁሳዊዎቹን ዓለማትና በውስጣቸው ያሉትን በመደገፉ ረገድ፥ ሦስቱም አካላት ቢሣተፉ፥ የመጀመሪያው አካል፥ እግዚአብሔር አብ፥ በልዩ ሁኔታ የፍጥረታት ሁሉ አባት ነው። ኤፌሶን 3፡14-15 ውስጥ ጳውሎስ “ስለዚህ ምክንያት በሰማይና በምድር ያለ አባትነት ሁሉ ከሚሰየምበት ከአብ ፊት እንበረከካለሁ” ብሏል። እዚህ ላይ የተገለጠው የሥነ-ምግባራዊ ምርጫ ማድረግ ከሚችሉ ፍጡራን (መላእክትና ሰው) መካከል እግዚአብሔር አባት የሆነበት ቤተሰብን የሚያመለክት ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ የመጀመሪያው አካል ዕብራውያን 12፡9 ውስጥ “የመናፍስት አባት” ተብሏል። ይህ እንደገና ሥነ-ምግባራዊ ፍጡራንን ሁሉ ማለት፥ ሰውንና መላእክትን ይጨምራል።  ያዕቆብ 1፡17 ውስጥ በተገለጠው መሠረት የመጀመሪያው አካል፥“የብርሃናት አባት” ነው። ይህ ልዩ አገላለጥ፥ አካሉ የመንፈሳዊ ብርሃን ሁሉ ምንጭ መሆኑን የሚያመለክት ይመስላል። ኢዮብ 1፡6፤ 2፡1፤ 38፡7 ውስጥ መላእክት የእግዚአብሔር ልጆች ተብለዋል። ሉቃስ 3፡38 ውስጥ አዳም በፍጥረቱ የእግዚአብሔር ልጅ ተብሏል። ነቢዩ ሚልክያስ በመጽሐፉ ምዕራፍ 2:10 ውስጥ “ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን?” በማለት ይጠይቃል። ሐዋርያው ጳውሎስም አርዮስ ፋጎስ በተባለው ስፍራ ለአቴናውያን ባደረገው ንግግሩ፥ “እንግዲህ የእግዚአብሔር ዘመዶች* ከሆንን” በማለት ጠቅሷል (ሐዋ. 17፡29)። (በዚህ ስፍራ የተጠቀሰው “ጌኖስ” የሚለው ቃል “ዘር” ወይም “ልጅ” የሚለው ትርጉም አለው። የ1980ውና የ2001 ዓ.ም. የአማርኛ ትርጉሞች ሁለቱም “ልጆች” ብለው ተርጉመውታል። ይህም “ዘመዶች” ከሚለው ትርጉም ይልቅ ትክክለኛ ነው)። 1ኛ ቆሮንቶስ 8፡6 ውስጥ “ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ፥ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን” ተብሎ ተጽፏል።  በነዚህ ጽሑፎች መሠረት፥ የሥላሴ ቀዳሚ አካል እንደፈጣሪነቱ የፍጥረታት ሁሉ አባት መሆኑን እና አካል ያላቸው ፍጡራን ሁሉ መነሻ እርሱ መሆኑን ለማመን የሚያበቃ ማረጋገጫ አለ። በዚህ መንገድ ብቻ ነው የእግዚአብሔርን ሁለንተናዊ አባትነት ለማመልከት የሚቻለው። በዚህ ሁኔታ ፍጥረታት ሁሉ ሁለንተናዊና ተፈጥሯዊ ወንድማማችነትን (ዝምድና) ይጋራሉ። ይሁን እንጂ ይህ አባባል ለዘብተኛ ትምህርተ መለኮታውያን (liberal theologians)፥ ሁለንተናዊ ድነት ወይም እግዚአብሔር ለማንኛውም ሰው በመንፈስ አባት ይሆነዋል፥ የሚሉትን የተሳሳተ አስተምህሮ አይደግፈውም።  ሐ. በቅርብ ግንኙነት የሚመሠረት አባትነት  ብሉይ ኪዳን ውስጥ የአባትነትና የልጅነት ፅንሰ-አሳብ እግዚአብሔርን ከእስራኤል ጋር ለማዛመድ በብዙ አጋጣሚ ተጠቅሷል። ዘጸአት 4፡22 ውስጥ ሙሴ ፈርዖንን እንዲህ ብሎታል “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- እስራኤል የበኩር ልጄ ነው”። ይህ እግዚአብሔር ለእስራኤል ፈጣሪ ከመሆን በተጨማሪ ያለውን ግንኙነት ሲገልጥ፥ እስራኤላውያን ዳግመኛ ተወልደዋል ከማለት ደግሞ ጥቂት የሚያንስ ነው። ምክንያቱም፥ መንፈሳዊ ሕይወት የነበራቸው ሁሉም እስራኤላውያን አልነበሩም። ይህ ሁኔታ አባት ለልጁ እንደሚያደርገው፥ እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ያለውን መለኮታዊ ግንኙነት፥ ክብካቤና ርኅራኄ ያመለክታል።  እግዚአብሔር ለዳዊት ቤት ያለውን ፍቅር ለራሱ ለዳዊት ሲገልጥለት፥ በርሱና በዳዊት ልጅ በሰሎሞን መካከል የሚኖረው ግንኙነት የአባትና የልጅን ያህል እንደሚሆን እንዲህ በማለት አስታውቆታል፡- “እኔም አባት እሆነዋለሁ፥ እርሱም ልጅ ይሆነኛል” (2ኛ ሳሙ. 7፡14)። በአጠቃላይ እንደ አምላካቸው ለሚተማመኑበት ሁሉ እንደ አባት እንደሚጠነቀቅላቸው እግዚአብሔር ገልጧል። ይህ አባባል መዝሙረ ዳዊት 103፡13 ውስጥ “አባት ለልጆቹ እንደሚራራ፥ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል” ተብሏል።  መ. የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት  የእግዚአብሔርን አባትነት በተመለከተ እጅግ ጠቃሚውና ሰፊው መገለጥ፥ የመጀመሪያው አካል ከሁለተኛው አካል (አብ ከወልድ) ጋር ያለውን ግንኙነት ያጠቃልላል። የመጀመሪያው አካል የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት፥ ተብሏል (ኤፌሶን 1፡3)። የአዲስ ኪዳን ትምህርተ-መለኮታዊ አጠቃላይ መገለጥ እግዚአብሔር አብ ወይም የመጀመሪያው አካል፥ የሁለተኛው አካል የኢየሱስ ክርስቶስ አባት መሆኑን የሚያመለክተው ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ በአዲስ ኪዳን በተደጋጋሚ እንደ እግዚአብሔር ልጅ መገለጡ፥ እንዲሁም የእግዚአብሔር ባሕርያትና ሥራዎች በተከታታይ ለርሱ መሰጠታቸው የኢየሱስ ክርስቶስን መለኮትነት ያረጋግጣሉ። የሥላሴ ትምህርት ባጠቃላይ፥ ክርስቶስን እንደ ሁለተኛ አካልና ከአብ ጋር ደግሞ እንደ ልጁ ባለ ግንኙነት ይገልጠዋል።  የሥነ-መለኮት ምሁራን አብ እንዴት የሁለተኛው አካል፥ ማለት የወልድ አባት ሊሆን ይችላል? ለሚለው ጥያቄ ትክክለኛውን መልስ ለማግኘት፥ ከአንደኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ የበረታ ጥረት እድርገዋል። “አብ” እና “ወልድ” የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት፥ በአብና በወልድ መካከል ያለውን ልዩ የሆነ ግንኙነትን ሲሆን፥ ይህ፥ ግንኙነቱ በሰብአዊ አባትነትና ልጅነት መካከል እንዳለው የግንኙነት ዓይነት ነው ማለት እይደለም። ይህ ሁኔታ በተለይ የሚረጋገጥበት አሳብ አብና ወልድ ሁለቱም ዘላለማዊ መሆናቸውን በሚያሳየው እውነት ነው። በአራተኛው መቶ ክፍለ-ዘመን የተነሣው መናፍቅ፥ የአርዮስ የመጀመሪያ ስሕተት፥ ወልድ የፍጥረት ሁሉ በኩር ነው የሚለው ነበር። ጥንታዊቱ ቤተ ክርስቲያን ወልድ እንደ አብ ዘላለማዊ ነው ከሚለው መሠረተ አሳብ በመነሣት ይህን አስተምህሮ በኑፋቄነት አወገዘችው።  አንዳንድ የሥነ-መለኮት ምሁራን የወልድን ዘላለማዊነት ተቀብለው፥ ነገር ግን ሁለተኛው አካል እንደ ወልድ ተግባሩን የጀመረበትን ሁኔታ በጊዜ ውስጥ አንድ ነጥብ ላይ ማለት፥ በፍጥረት መጀመሪያ፥ ሥጋ በለበሰበት ወቅት ወይም የኋላ ኋላ ሁለተኛው አካል ልዩ ግንዛቤ ባገኘ ጊዜ፥ ማለትም በተጠመቀበት ወቅት በትንሣኤው ወይም በዕርገቱ ጊዜ ነው ለማለት ሞክረዋል። ይሁን እንጂ እነዚህ አማራጭ አመለካከቶች ሁሉ ስሕተት ናቸው። ምክንያቱም ወልድ ከዘመናት በፊት ጀምሮ ከአብ ጋር አንድነት ያለው መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ያመለክታል። በዚህ መሠረት ወልድ፥ “አንድያ ልጅ (ዮሐ. 3፡16) ሲሆን፥ ሥጋ በለበሰ ጊዜ እግዚአብሔር ለዓለም የሰጠው” ልጁ ነው። ወልድ ለዓለም የተሰጠው እንደ እግዚአብሔር ልጅነቱ እንጂ፥ ከመሰጠቱ በኋላ ልጅ ይሆን ዘንድ አይደለም። ኢሳይያስ 9፡6 ውስጥ “ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል” ተብሏል። ይህ አሳብ ቆላስያዕ 1፡15-16 ውስጥ ይበልጥ ግልጥ ተደርጓል። በዚህ ስፍራ ክርስቶስ፥ «የማይታይ አምላክ ምሳሌ፥ … ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኩር” እንደሆነ ተነግሯል። ክርስቶስ የፍጥረታት ሁሉ በኩር ከሆነ፥ ማለት ከማንኛውም ፍጥረት ሁሉ በፊት የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነ፥ የርሱ ልጅነት ከዘላለም በፊት መሆኑ ግልጥ ነው።  ስለዚህ የአብና የወልድ አንድነት ከዘላለማዊነት አንጻር ከቅድስት ሥላሴ ዘላለማዊ መለኮትነት ጋር የሚያያዝ ገጽታ ሲኖረው፤ በሌላ በኩል ወልድ ሥጋን ከለበሰበት ዘመን እንጻር ደግሞ የሚታይ ለየት ያለ የጊዜ ገጽታ አለው። የኒቅያው ጉባኤ (325 ዓ.ም.) በአራተኛው ክፍለ-ዘመን ለተነሣው የአርዮስ ኑፋቄያዊ አስተምህሮ በሰጠው የመልስ ድንጋጌ፥ ለወልድ፥ የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ፥ ከዓለማት መፈጠር በፊት የአብ የሆነ፥ ከእግዚአብሔር የወጣ እግዚአብሔር፥ ከብርሃን የሆነ ብርሃን፥ ከእውነተኛው አምላክ የወጣ እውነተኛ አምላክ፥ የተወለደ፥ ያልተፈጠረ፥ ከአብ ጋር አንድ የሆነ” ብሏል። በተመሳሳይ ሁኔታ አትናቴዎስ በተባለው ጳጳስ አማካይነት የተቀናበረው ድንጋጌ እንዲህ ይላል፡- “ወልድ ከአብ ብቻ የሆነ፥ የተወለደ እንጂ ያልተሠራ ወይም ያልተፈጠረ፥ ከዘላለም በፊት ከአብ የወጣ።  “አብ” እና “ወልድ” የሚሉት ቃላት ቀዳማዩንና ደህራዩን አካል ለመግለጥ በሚያገለግሉበት ጊዜ የሕይወትን፥ የባሕርይንና የልዩ መለያን አድነት ሊያስገነዝቡ በሚቻላቸው ከፍተኛ ሁኔታ ይገልጣሉ። ምንም እንኳን የጠበቀ የአባትና ልጅነት አንድነት ቢኖር፥ አብ ልጁን የመስጠቱና የመላኩ

እግዚአብሔር አብ Read More »

እግዚአብሔር ሥሉስ

This entry is part 5 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ሀ. በእግዚአብሔር ሕልውና ማመን  ከሰው የሚልቅና መለኮታዊ ሕልውና ያለው አካል መኖሩን ማመን በማንኛውም ባሕልና ሥልጣኔ ያለ ነው። ይህ የሆነበት ምክንያት፥ ባንድ ወገን፥ ሰው ስለ ዓለማችንና ስለ ሰብአዊ ልምምድ የሚገለጥ አንድ ነገር መኖር አለበት፥ ይህን ለመግለጥም፥ ያ ከሰው የሚልቅ አካል ይቻለዋል ብሎ ስለሚመራመር ነው። ሰው በተፈጥሮ አስተዋይነቱ እንዲሁም ሃይማኖታዊ ተፈጥሮው ከርሱ የሚልቅ ሕልውና ወዳለው አካል የመድረስ ፍላጎት አለው። ይህ ፍላጎቱ በትምህርተ መለኮት ለሁሉም የሚሆን ጸጋ በመባል ከሚታወቅ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ጋር በመያያዝ ሊገለጥ ይችላል። ይህ ከሰዎች ድነት ጋር ከተያያዘው የመንፈስ ቅዱስ ሥራ የተለየ ነው። እግዚአብሔር የለም የሚሉ ብዙ ሰዎች ዘመናዊ ክሥተት የሚመነጨው፥ ከተዛባ አስተሳሰብ እና በማንኛውም አቅጣጫ በሚደረግ ምርምር ዓለምን ለመግለጥ ይቻላል ከሚል አመለካከት ነው። እግዚአብሔር የለም የሚለውን ሰው መጽሐፍ ቅዱስ ሞኝ* ይለዋል(መዝ. 14፡1)። *እዚህ ላይ የተጠቀምነው የ1980ውን ትርጉም ነው። ምክንያቱም ዩናባል ለሚለው የዕብራይስጥ ቃል የተሻለ ትርጉም ይሰጣል ብለን ስለምናምን ነው።  በተለያዩ አገባቦች “ናባል” የሚለው ቃል ብሉይ ኪዳን ውስጥ 36 ጊዜ ጥቅም ላይ ውሏል። አምስት ጊዜ የአእምሮ ችግርን ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል። ነገር ግን በአብዛኛው “ናባል” በሕብረተሰብ ያለውን ሕግ ወይም የእግዚአብሔርን ሕግ በድፍረት የሚጥስ ሰው አስተሳሰብን ይገልጣል። ለምሳሌ “ናባል” ሴኬም ዲናን አስገድዶ መድፈሩን ለመግለጥ (ዘፍጥ. 34፡7)፥ አምኖን ትዕማርን አስገድዶ መድፈሩን (2ኛ ሳሙ. 13፡12-13)፥ ከጎረቤት ሚስት ጋር ማመንዘርን (ኤር. 29፡23) ለመግለጥ ጥቅም ላይ ውሏል። አካን ከኢያሪኮ ድል በኋላ የፈጸመው የምርኮ ዕቃዎች ስርቆት “ናባል’ ነበር (ኢያሱ 7፡15)። የኢዮብ ጓደኞች “ናባል” ተብለው ተጠርተዋል። ምክንያቱም አስተሳሰባቸውና ድምዳሜያቸው ከእግዚአብሔር አልነበረምና (ኢዮ. 42፡8)። የእስራኤል መሪዎችም እርኩሰትን ሲለማመዱ፥ ዓመጽን ሲያቅዱ፥ ሰዎችን ሲያስርቡ ናባል ተብለው ይጠሩ ነበር (ኢሳ. 32፡5-7)።  ሐሰተኛ ነቢያት አክአብና ሴዴቅያስ “ናባል” ነበሩ፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔርን እውነት አልተናገሩም (ኤር. 29፡23)። የእስራኤል ሕዝብ ናባል ነበር (ዘዳ. 32፡6፥ 15፥ ኤር. 14፡1)። ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ክብርና ታላቅነት እያወቀ ከእርሱ ይርቅ ነበር። ናባል የእግዚአብሔርን መኖር የሚክድና (መዝ. 14፡1፥ 53፡2)፥ በእግዚአብሔር በሚታመኑት ላይ የሚሳለቅ ነው (መዝ፡39፥9፥ ኢዮ. 2፡10)።   በተለምዶ ሰዎች ስለ ራሳቸው ሕልውናም ሆነ፥ በስሜት ሕዋሶቻቸው አማካይነት ሊረዱአቸው ስለሚችሉአቸው ቁሳዊ ነገሮች ሕልውና ማረጋገጫ አይጠይቁም። እግዚአብሔር በአካለ ሥጋ ባይታይም ሕልውናው የተረጋገጠ በመሆኑ፥ በአብዛኛው ሰዎች ስለ መኖሩ ምንም ማስረጃ አይጠይቁም። የእግዚአብሔርን ሕልውና መጠራጠር የሚመጣው፥ ሰው ራሱ ትክክለኛውን መንገድ ከመሳቱና መንፈሳዊ ዓይኑ በመታወሩ፥ እንዲሁም ከሰይጣናዊ ተጽዕኖ የተነሣ ነው። የእግዚአብሔር ሕልውና በተፈጥሮ አማካይነት በሚገባ ተገልጧል። ስለ ወንጌል ያልሰማው የማያምን ዓለም የፍርድ መሠረትም ይህን በተፈጥሮ የተገለጠ የእግዚአብሔር ሕልውና አለማመኑ ነው። በመሆኑም ሮሜ 1፡19-20 ውስጥ፥ “እግዚአብሔር ስለገለጠላቸው፥ ስለ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚቻለው በእነርሱ ዘንድ ግልጥ ነውና”፥ በሚለው ቃል መሠረት ይፈረድባቸዋል።  መጽሐፍ ቅዱስ ከመጻፉ በፊት በነቢያት በኩል የተላለፈውን እና በመጽሐፉ የተላለፈውን የእግዚአብሔር መገለጥ ዛሬ በተወሰነ ደረጃ አብዛኛው ሰው ያውቀዋል። ዓለም በጠቅላላው ሲታይ በመጽሐፍ ቅዱስ ስለተላለፈው መገለጥ መሃይም ቢሆንም፥ በመጠኑም ቢሆን ስለ እግዚአብሔር እንዲያሰላስል መገለጡ የዓለምን ሁሉ አሳብ ይዞታል። ስለዚህ በአንድ ሉዓላዊ በሆነ አካል ማመን መጽሐፍ ቅዱስ በቀጥታ ባልደረሳቸው ሰዎች ዘንድ እንኳ አለ።  ጥንታዊ የግሪክ ፈላስፋዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊውን መገለጥ ባያውቁትም፥ አንድ ሉዓላዊ አካል አለ በሚል አስተሳሰብ ላይ በመመሥረት ዓለማትን ለመግለጥ ሞክረው ነበር። በዚሁ መሠረት የተለያዩ የአስተሳሰብ ዘዴዎች ቀርበዋል። እነሱም፦  1. በብዙ አማልክት ማመን (Polytheism)፤  2. ኃይሎኮይዝም (Hylozoism) በእያንዳንዱ ተፈጥሮ ውስጥ የሚገኘው የሕይወት ሥርዓት ራሱ እግዚአብሔር ነው የሚል እምነት፤  3. ቁስ-አካላዊነት (Materialism)፥ ቁስ-አካል በራሱ የተፈጥሮ ሕግ መሠረት የሚሠራ ስለሆነ፥ ለማንኛውም እንቅስቃሴው ምንም አምላክ አያስፈልገውም። ይህ ትምህርት የአዝጋሚ ለውጥን (Evolution) አሳብ የሚደግፍ ነው፤  4. “ፖንቴይዝም” (Pantheism) የሚባለው ደግሞ እግዚአብሔር ስብእና የሌለውና ከተፈጥሮ ጋር አንድ የሆነ ነው፥ ስለዚህም እግዚአብሔር አብሮ ያለ፥ የቅርብና እኩያ እንጂ የበላይ የሆነ ወይም አእምሮን የሚያልፍ አይደለም ይላል። ስለ እግዚአብሔር ይህን የመሳሰሉ ብዙ አስተሳሰቦች አሉ።  ስለ እግዚአብሔር መኖር ከቃሉ ከሚገኘው መገለጥ ውጪ፡ከተፈጥሮ እውነት አንጻር ብቻ ሲታይ እንኳን የሚከተሉት አራት ዋና ዋና አሳቦች ወይም ምክንያቶች ሊስተዋሉ ይችላሉ። እነርሱም፡ 1. እግዚኣብሔር አለ ብሎ ሰው ሁሉ ስለሚያምን እግዚኣብሔር መኖር አለበት የሚለው አሳብ ነው። ይህ አስተሳሰብ “አንተሎጂካል ተሐስቦ” (Ontological argument) ይባላል።  2. የዓለማት አፈጣጠር ተሐስቦ (Cosmological argument) የተሰኘው አመለካከት፥ ማንኛውም ውጤት ምክንያት ወይም መነሻ ሊኖረው ይገባል፤ ስለሆነም ውጤት የሆኑት ዓለማት መነሻ የሆን ፈጣሪ ሊኖራቸው ይገባል ይላል። በዚህም አሳብ የተካተተው ሌላ አመለካከት በአጋጣሚ ሊመጡ የማይችሉት ዓልማት ሥርዓት ውስብስብነት ነው።  3. ማንኛውም ውጥን ወይም ዕቅድ ያለ አድራጊና ያለ ዓላማ ሊከናወን አይችልም የሚለው “ቴሌሎጂካል ተሐስቦ” (Teleological argument) አስተሳሰብ፥ ተፈጥሮ ባጠቃላይ በረቀቀ ሁኔታ የታቀደና አንዱ ከሌላው የተዛመደ እንደ መሆኑ እንድ ታላቅ ሠሪ ሊኖረው ይገባል ይላል። ነገሮች ሁሉ በአንድነትና በኅብረት የመሥራታቸው እውነት፥ እነሱን የሠራ ፈጣሪ ፍጹም ኃይልና ጥበብ ያለው መሆኑን ያመለክታል።  4. ሥነ-ሰብአዊ (Anthropological argument) አመለካከት፥ የሰው ተፈጥሮ በአምሳያው ከፈጠረው፥ ነገር ግን ከርሱ እጅግ ከሚልቀው ከእግዚአብሔር ባሕርይ ተለይቶ ሊገለጥ አይችልም ይላል። ከዚሁ ጋር ሰው አእምሮ (የማሰብ ችሎታ)፥ ስሜት (በስሜት የመገንዘብ ችሎታን)፥ ፈቃድ (ምርጫ የማድረግ ችሎታ) አለው። እንዲህ ያሉት ልዩ ችሎታዎች ተመሳሳይ ነገር ግን የላቀ ባሕርይ ወዳለውና ሰውን ወደፈጠረ አምላክ ያመለክታሉ።  የእግዚአብሔርን ሕልውና አስመልክቶ የተነሡ እነዚህ አስተሳሰቦች በቀላሉ የማይገመት ጠቀሜታ አላቸው። ሰውም እነዚህን አሳቦች ባለመቀበሉ የተፈረደበት መሆኑ ትክክል ቢሆንም (ሮሜ 1፡18-20)፥ ሰው በትክክል ከእግዚአብሔር ጋር እንዲገናኝ አልረዳውም፤ ወይም ያለ መጽሐፍ ቅዱስ እርዳታ በእግዚአብሔር እውነተኛ እምነት እንዲኖረው አልረዳም። የእግዚአብሔር ሙሉ መገለጥ የተሰጠው በመጽሐፍ ቅዱስ ነው። በመሆኑም ተፈጥሮ ውስጥ ያሉትን እውነታዎች እና በርሱም ላይ ተፈጥሮ ሊገልጣቸው የማይቻለው ብዙ እውነቶች ታክለዋል።  ለ. የሥላሴ መለኮታዊ አንድነት  ብሉይ ኪዳን በአጠቃላይ የእግዚአብሔርን ውሑድነት ወይም አንድነት ይገልጣል (ዘፀ. 20፡3፤ ዘዳ. 6፡4፤ ኢሳ. 44 ፡6)። ይህን እውነት አዲስ ኪዳንም ያስተምራል (ዮሐ. 10፡30፤ 14፡9፤ 17፡11፤ 22፡23፤ ቆላ. 1፡15)። ብሉይ ኪዳን፥ በይበልጥም አዲስ ኪዳን፥ እግዚአብሔር በሥሉስነት ማለት፥ እግዚአብሔር አብ፥ እግዚአብሔር ወልድ፥ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሆኖ እንደሚኖር ያስገነዝባሉ። ብዙ ሰዎች የሥላሴ ትምህርት ኤሎሂም በሚለውና የእግዚአብሔርን ሥሉስነት ያመለክታል ተብሎ በሚታመነው ስም ውስጥ ይጠቃለላል ይላሉ። ይህንንም የሚሉበት ምክንያት ኤሎሂም የሚለው ቃል የብዙ ቁጥር በመሆኑ ነው።  በዘፍጥረት መጀመሪያ ክፍሎች ስለ እግዚአብሔር መንፈስ የሚገልጥና እግዚአብሔርን በብዙ ቁጥር የሚያመለክት ተውላጠ ስም ይገኛል (ዘፍጥ. 1፡26፤ 3፡22፤ 11፡7)። የአብን፥ የወልድንና የመንፈስ ቅዱስን ባሕርይ በተመለከተ፥ ብዙ ጊዜ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ልዩነቶች አሉ። ኢሳይያስ 7፡14 ላይ ወልድን አማኑኤል “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር” በማለት ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ለየት አድርጎ ያቀርበዋል። ኢሳይያስ 9፡6 ላይ ደግሞ፥ ይሄው ወልድ “ኃያል አምላክ፥ የዘለአለም አባት፥ የሠላም አለቃ” ተብሏል።  መዝሙረ ዳዊት 2፡7 ውስጥ “እኔ” ተብሎ የተጠቀሰው እግዚአብሔር አብ፥ ዓሳማው ልጁን የዓለም ልዑል ገዢ ማድረግ መሆኑ ተገልጧል። አብና ወልድ እንደተለያዩ ሁሉ፥ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን መላኩ በተገለጠበት መዝሙረ ዳዊት 104፡30 ውስጥ፥ አብ ከመንፈስ ቅዱስ የሚለይ መሆኑ ተመልክቷል። በዚህ ላይ የሚታካሉት ሌሎች ማስረጃዎች፥ የእግዚአብሔርን ልጅ መገለጥ በሚያመለክተው ብሉይ ኪዳን ውስጥ “የያህዌህ መልአክን” መታየት የሚያሳዩት ታሪኮች ናቸው። የእግዚአብሔር መንፈስ፥ መንፈስ ቅዱስ መሆኑና እርሱም ከአብና ከወልድ የተለየ መሆኑ መገለጡም ከዚሁ ጋር የሚዳመር ነው።  ለነዚህ የብሉይ ኪዳን ማስረጃዎች እዲስ ኪዳን ተጨማሪ መገለጥ ይሰጣል። ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ የተፀነሰና የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ፥ ማለት ሥጋ የለበሰ አምላክ ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ሥርዓተ ጥምቀት ጊዜ፥ እግዚእብሔር አብ ከሰማይ ሲናገር፥ መንፈስ ቅዱስ በእርግብ አምሳል ወርዶ በላዩ ሲያርፍበት እና፥ ኢየሱስ እራሱ ሲጠመቅ፥ በሥላሴ ውስጥ ያለው ልዩነት ተገልጧል (ማቴ. 3፡16-17)። ይህ የሥላሴ ልዩነት ዮሐንስ

እግዚአብሔር ሥሉስ Read More »

መጽሐፍ ቅዱስ እንደ መለኮታዊ መገለጥ

This entry is part 4 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ሀ. የመለኮታዊ መገለጥ ዓይነቶች  መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ሕልውና፥ ሥራዎቹንና ዕቅዶቹን ለመግለጫነት ነው የተጻፈው። ፍጹም ልዑል የሆነው አምላክ ራሱን ለፍጥረታቱ መግለጡ ተገቢ ሲሆን፥ ፍጥረትን የፈጠረበት ዓላማም ይሞላ ዘንድ ይህ አስፈላጊ ነበር። አእምሮ ያላቸው ፍጡራን በሙሉ ፈጣሪያቸውን ለማወቅ መሞከራቸው ትክክል ነው። የተፈጥሮ ከፍተኛ ደረጃ ሰው ከሆነ፥ ፈጣሪውን ለመገንዘብና ከርሱ ጋር አንድነት ለመፍጠር ከቻለ፥ ፈጣሪ ዓላማና ፍቃዱን እንዲህ ላለው ፍጡር በመግለጥ እንደሚገናኘው መገንዘብ ይቻላል። እግዚአብሔር በሦስት ዋና ዋና መንገዶች ራሱን ገልጧል።  1. የእግዚአብሔር መገለጥ በፍጥረት ውስጥ። የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ሥልጣንና ባሕርይ በፈጠራቸው ፍጥረታት አማካይነት ተገልጧል (ሮሜ. 1፡20)። ተፈጥሮአዊው ዓለም የእግዚአብሔር ሥራ እንደመሆኑ፥ እግዚአብሔር የማይወሰን ኃይልና ጥበብ ያለው መሆኑን፥ እንዲሁም ነባራዊውን ዓለም ጥበብ ለተሞላበት ዓላማ እንደፈጠረው ያረጋግጣል። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር በተፈጥሮ በኩል ያሳየው መገለጥ፥ የእግዚአብሔርን ፍቅር፥ ወይም ቅድስና በተመለከተ ጥርት ያለ መግለጫ ስለማናገኝለት የራሱ ገደብ አለው። እግዚአብሔር በፍጥረት አማካይነት ያሳየው መገለጥ፥ የማያምነው ዓለም እርሱን እንደፈጣሪው ባለማምለኩ እንዲፈርድበት ቢያስችለውም፥ ይህ መገለጥ ኃጢአተኞች ቅዱስ ከሆነው እግዚአብሔር ጋር የሚታረቁበትን የድነት መንገድ አያመለክትም።  2. በክርስቶስ የታየ የእግዚአብሔር መገለጥ። ታላቁ የእግዚአብሔር መገለጥ የተከናወነው ራሱ በወሰነው ጊዜ በተወለደው በክርስቶስ እና በክርስቶስ ሥራ ነው (ገላ. 4፡4)። የእግዚአብሔር ልጅ ሰው ሆኖ ወደ ዓለም የመጣው፥ ሰዎች ሊረዱት በሚቻላቸው አኳኋን እግዚአብሔርን ሊገልጥ ነው። ክርስቶስ ሥጋ ለብሶ በመወለዱ እጅግ ከባድ የሆነ የእግዚአብሔር እውነት፥ ውስኑ የሰው አእምሮ በሚረዳው ደረጃ ተገልጧል። ስለዚህ በክርስቶስ የተገለጠው፥ የእግዚአብሔር ኃይልና ጥበብ ብቻ ሳይሆን፥ በጎነቱ፥ ቅድስናው፥ ጸጋውና ፍቅሩ ጭምር ናቸው። ይህንም ክርስቶስ ራሱ ሲመሰክር፥ “እኔን ያየ አብን አይቶአል” በማለት አረጋግጧል (ዮሐ. 14፡9)። ስለሆነም ክርስቶስ ኢየሱስን ያየውና ያወቀው ሁሉ፥ እግዚአብሔር አብንም አይቶታል፥ አውቆታልም።  3. በተጻፈ ቃል አማካይነት የተሰጠ የእግዚአብሔር መገለጥ። በጽሑፍ የሰፈረው የእግዚአብሔር ቃል፥ በክርስቶስ በራሱና በሥራው ከታየው ይልቅ ግልጥ በሆነ ቃል እግዚአብሔርን ሊገልጠው ይችላል። ቀደም ብሎ የተጻፈ እንደመሆኑ መጠን፥ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ትንቢት ዓላማ ወይም ባለቤት እና እንደ ትንቢት ፍጻሜ የሚያስተዋውቀን መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ በዝርዝር ከመግለጥ አልፎም፥ እግዚአብሔር ለእስራኤል፥ ለመንግሥታትና ለቤተ ክርስቲያን ያለውን ፕሮግራም ያመለክታል። የሰው ዘር ታሪክንና የዓለማትን መታወቅ የመሳሰሉ ነገሮችንም ይመለከታል።  መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔርን ዋና ጉዳዩ አድርጎ ማቅረብ ብቻ ሳይሆን፥ የእግዚአብሔርን ዓላማም ይገልጣል። በጽሑፍ የሰፈረው መገለጥ አጠቃላይ ነው። እግዚአብሔርን በተመለከተ፥ በተፈጥሮ አማካይነት የተገለጡትን እውነቶች ሁሉ ለማስገንዘብ፥ የእግዚአብሔርን በክርስቶስ መገለጥ ብቸኛ ዘገባ ያቀርባል። እግዚአብሔር አብን፥ ወልድን፥ መንፈስ ቅዱስን መላእክትን፥ አጋንንትን፥ ሰውን፥ ኃጢአትን፥ ድነትን፥ ጸጋን፥ እና ክብርን በተመለከተ ያለውን መገለጥ በጥልቀት ይዘረዝራል። በዚህ መሠረት፥ መጽሐፍ ቅዱስ፥ በተፈጥሮ በከፊል የታየውን፥ ይበልጥ በሙላት በክርስቶስ የተገለጠውን እና በጽሑፍ በሰፈረው ቃል የተጠቃለለውን መለኮታዊ መገለጥ ከፍጻሜ እንዳደረሰ ሊቆጠር ይችል ይሆናል።  ለ. ልዩ መገለጥ  በመላው የሰው ልጅ ታሪክ እግዚአብሔር ልዩ ራእይ ወይም መገለጥን ሰጥቶአል። በኤደን ገነት ውስጥ ከሰው ጋር ፊት ለፊት ተነጋግሯል። በተመሳሳይ ሁኔታ ከነቢያት ጋር በብሉይ ኪዳን ወይም ከሐዋርያት ጋር በአዲስ ኪዳን የተናገረባቸው ብዙ ሁኔታዎች ተመዝግበዋል። ከነዚህ ልዩ መገለጦች ጥቂቱና በእስትንፋሰ-እግዚአብሔር የተሞላ ሥልጣን ያላቸው፥ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግበዋል።  መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉ ስድሳ ስድስት መጻሕፍት ሌላ ኣዲስ መጻሕፍትን ሊያስጨምር የሚችል ልዩ መገለጥ አይኖርም። ስለዚህ አዋልድ መጻሕፍት እስትንፋሰ እግዚአብሔርነት ስለሌላቸው፥ ከስድሳ ስድስቱ መጻሕፍት እኩል የሚታዩ አይደሉም።  ይሁን እንጂ፥ በአሁኑ ጊዜ በልዩ መገለጥ ፈንታ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ጎልቶ ይታወቃል። የእግዚአብሔር መንፈስ ለቃሉ አብርሆት ወይም ብርሃን እንደሚሰጥ፥ የአሁኑ ጊዜ መገለጥም የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮዎች ለግል ሕይወትና ሁኔታዎች ግልጥ የሚሆኑት በዚህ አኳኋን ነው። ከእስትንፋሰ-እግዚአብሔር ጋር በተጓዳኝ የምናየው ነገር፥ መንፈስ ቅዱስ ለአንድ ሰው የሚያስፈልጉት አጠቃላይ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ተግባራዊ የሚሆኑበትን መንገድ የመምራቱ ሥራ ነው። ሁለቱም፥ ማለት ምሪትና አብርሆት ትክክለኛዎቹ የእግዚአብሔር ሥራዎች ቢሆኑም፥ አንድ ሰው መጽሐፍ ቅዱስን ሙሉ በሙሉ ለመረዳቱ ወይም የእግዚአብሔርን ምሪት በትክክል ለመገንዘቡ ዋስትና አይሰጡም። ስለዚህ፥ አብርሆትና ምሪት የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ቢሆኑም፥ ለስሕተት በሚጋለጥ ሰብአዊ ፍጡር በኩል የሚመጡና ለእርሱ የሚያስፈልገውን ነገር ለመግለጥ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በተያያዘ መልክ ስለሚሰጡ፥ “በእስትንፋሰ-እግዚአብሔር” የተጻፈን የመጽሐፍ ቅዱስን ያህል ስሕተት ኣልባ ሊሆኑ አይችሉም።  1ኛ ቆሮንቶስ 2፡10 ውስጥ እንደተመለከተው፥ ቃሉን በሚገልጥልን በእግዚአብሔር መንፈስ አማካይነት ካልሆነ በስተቀር፥ እውነትን በሚገባ የምንረዳበት መንገድ የለም። የእግዚአብሔር ቃል እውነት፥ በእግዚአብሔር መንፈስ ሊገለጥልን ይገባል። መማር ያለብንም በመንፈስ ቅዱስ ነው (1ኛ ቆሮ. 2፡13)። 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡14 ውስጥ እንደተጠቀሰው፦ “ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፥ በመንፈስም የሚመረመር ስለሆነ ሊያውቀው አይችልም”። ስለዚህ ትክክለኛ ፍቺውን መረዳትን በተመለከተ፥ መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያን ላልሆነና ከመንፈስ ቅዱስ ለማይማር ሰው ስውር ነው። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን የሚማር ሰው፥ መንፈስ ቅዱስ እውነቱን ይገልጥለት ዘንድ ከእግዚአብሔር ጋር የቅርብ ግንኙነት ሊኖረው ይገባል።  ሐ. ትርጉም ወይም ፍቺ  አንድ በክርስቶስ አማኝ የሆነ ሰው፥ የእግዚአብሔርን ቃል መገለጥ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በሚያጠናበት ጊዜ፥ ትርጉምን ወይም ፍቺን በሚመለከት አንዳንድ ችግሮች ይገጥሙታል። በመሆኑም አንድ ሰው “የመጽሐፍ ቅዱስ አፈታት ዘዴ” (“ኸርማኒዩቲክስ” /hermeneutics) ተብሎ በሚጠራው የእግዚአብሔር ቃልን የማጥኛ ስልት ለመጠቀም ከፈለገ፥ የአተረጓጎም መሠረታዊ ደንቦችን ሊከተል ይገባል። ፍቺን ወይም መረዳትን በተመለከተ በመንፈስ ቅዱስ ላይ መደገፍ አስፈላጊነቱ ሳይዘነጋ፥ አንዳንድ መሠረታዊ የማጥኛ ስልቶች ስለሚያስፈልጉ በዝርዝር ልናያቸው ይገባል።  1. የመጽሐፍ ቅዱስ አጠቃላይ ዓላማ። መጽሐፍ ቅዱስ በሚተረጎምበት ወይም በሚፈታበት ጊዜ ራሱን በራሱ የማይቃረን መጽሐፍ ስለሆነ፥ እያንዳንዱ ጥቅስ ከአጠቃላዩ ይዘት ጋር መዛመድ አለበት።  2. እያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ የያዘው ልዩ መልእክት። የእግዚአብሔር ቃል ፍቺ ወይም ትርጉም ሥራ ሁልጊዜ የሚተረጎመውን መጽሐፍ ዓላማ ከግንዛቤ ማስገባት አለበት። በዚህ መሠረት፥ የመጽሐፈ መክብብ ጥናት ወይም አተረጓጎም፥ ከራእይ ወይም ከመዝሙረ ዳዊት ጥናት ይለያል። ለዚህ ነው አንድ ትርጉም ከሚተረጎመው መጽሐፍ ዓላማ መራቅ የለበትም የሚባለው።  3. ለማን ተጻፈ? መጽሐፍ ቅዱስ በእስትንፋሰ-እግዚአብሔር የተጻፈ ቢሆንም፥ ሁሉም በእኩልነት ሥራ ላይ የሚውል አይደለም። የእግዚአብሔርን ቃል በተሳሳተ አኳኋን ከመተርጎም የተነሣ ብዙ የሐሰት አስተምህሮዎች ተፈጥረዋል። ስለዚህ አንድ የንባብ ክፍል በሚጠናበት ጊዜ፥ ማን፥ ለማን፥ የሚሉ ጥያቄዎችን ማንሣት ተገቢ ነው። የተጻፈውን መልእክት ስንመለከት፥ የተጻፈላቸው የመጀመሪያዎቹ ተቀባዮች ሲሆኑ፥ ከዛ በኋላ የሚያነቡት ሁለተኛ ተጠቃሚዎች ወይም ከራሳቸው ጋር አዛማጆች ይሆናሉ። የመጀመሪያው ተግባር ጽሑፉ እስከተጻፈለት ግለሰብ ወይም ቡድን የሚደርስ ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ ለገላትያ ሰዎች የተላከው መልእክት ወይም በዳዊት የተጻፈው መዝሙር ሊሆን ይችላል። በመጽሐፍ ቅዱሳዊው የንባብ ክፍል ውስጥ ያለ እውነት፥ በመጀመሪያ ጽሑፉ ለተጻፈላቸው ሰዎች የሚሆን ሲሆን፥ በሁለተኛ ደረጃ ሌሎችን የሚያጠቃልል እውነት ይኖረዋል። ስለዚህ፥ የብሉይ ኪዳን ሕግ ለእስራኤል የተጻፈ ቢሆንም፥ በዚህ ስፍረ-ዘመን ያሉ ክርስቲያኖች ቃሉ የእግዚአብሔር ቅድስና መግለጫ እንደሆነ ተገንዝበው ያጠኑታል። በዚህ መሠረት አንዳንድ ልዩ ነገሮች ለኛ ሁኔታ የሚውሉና የሚጠቅሙ ሊሆኑ ይችላሉ።  4. ዐውደ-ንባቡ ወይም አገባቡ (context)። ማንኛውም ምንባብ በሚብራራበት ጊዜ ልብ ሊባሉ ከሚገባቸው ጠቃሚ ነገሮች አንዱ፥ የምንባቡን የቅርብ ዐውድ ወይም አገባብ ማጤን ነው። ይህ አሠራር ብዙ ጊዜ በገላጣው ውስጥ ሊባል ስለተፈለገው ነገር ፍንጭ ይሰጣል። ማንኛውንም ጥቅስ የሚቀድም ወይም የሚከተል ቃል እንዲሁም ዓረፍተ ነገር፥ አንባቢው ጥቅሱን እንዲገነዘብ ይረዳዋል።  5. በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ በሌላ ስፍራ የሚኖሩ ተመሳሳይ ትምህርቶች። መጽሐፍ ቅዱስ ራሱን በራሱ የሚቃረን ስላይደለ፥ ስለ አንድ ጥቅስ ትምህርተ-መለኮታዊ ገለጣ ሲሰጥ፥ በሌላ ስፍራ ካሉ ገለጣዎች ጋር መዋሐድ ወይም መጣጣም አለበት። ይህ ነው የቅንብራዊ ትምህርተ-መለኮት (Systematic Theology) ልዩ ተግባር። ይህ ቅንብራዊ ትምህርተ-መለኮት፥ መለኮታዊውን መገለጥ እንዳለ በመውሰድ፥ ከማንኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ጋር በማይቃረን ሁኔታ በትምህርትነት ሊያቀናብረው ይሞክራል። የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት ብዙ ጊዜ ይደጋገፋሉ። ለምሳሌ፥ መጽሐፈ ራእይ ስለ መልእክቱ ፍቺ በዳንኤል ወይም በሌሎቹ የብሉይ

መጽሐፍ ቅዱስ እንደ መለኮታዊ መገለጥ Read More »

መጽሐፍ ቅዱስ፡- መልእክቱና ዓላማው

This entry is part 3 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ሀ. ኢየሱስ ክርስቶስ በመልእክትነት  ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የመጽሐፍ ቅዱስ ዋና መልእክት ነው። ስለሆነም የክርስቶስን ማንነትና የሥራውንም ፍጹምነት በሚመለከት በብዙ መንገዶች የቀረበውን መግለጫ በትክክል ለማወቅ የሚቻለው፥ መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን፡-  1. ኢየሱስ ክርስቶስ ፈጣሪ ነው። የኦሪት ዘፍጥረት የመጀመሪያ ምዕራፎች እግዚአብሔር ዓለምን እንደፈጠረ የመዘገቡልን ሲሆን፥ ይህንንም “ኤሎሂም” በሚል የዕብራይስጥ ቃል ይገልጣሉ። ቃሉም አብን፥ ወልድን እና መንፈስ ቅዱስን ያመለክታል። አንድ ሰው ሁሉም ነገር የተፈጠረው በክርስቶስ መሆኑን የሚረዳው አዲስ ኪዳን (ዮሐ. 1፡3) ላይ ሲደርስ ነው። ቆላስይስ 1፡16-17 ውስጥ፥ “የሚታዩትና የማይታዩትም ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ፥ በእርሱ፥ ተፈጥረዋልና፤ ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኩር ነው፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል እርሱ ከሁሉም በፊት ነው ሁሉም በርሱ ተጋጥሞአል” በማለት ክርስቶስ የሁሉም ነገር ፈጣሪ መሆኑን ይመሰክራል። ይህ ማለት ደግሞ፥ እግዚአብሔር አብ እና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በፍጥረት ሥራ ውስጥ ምንም ድርሻ አልነበራቸውም ማለት አይደለም። ነገር ግን በፍጥረት ሥራ ውስጥ ለክርስቶስ የዋና አድራጊነትን ስፍራ ይሰጠዋል። በዚህ መሠረት ዓለምና በዓለም ያሉት ሁሉ የክርስቶስን የእጅ ሥራ ፍጹምነት ይገልጣሉ።  2. ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ዓለም ልዑል ገዥ። ኢየሱስ ክርስቶስ ፈጣሪ ስለሆነ በዓለማት ሁሉ ላይ ሉዓላዊ ገዥ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ልዕልና የእግዚአብሔር አብ መሆኑን ይናገራል። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ሁሉ ይገዛ ዘንድ የእግዚአብሔር አብ ፈቃድና ዓላማ ነው (መዝ. 2፡8-9)። ምላስ ሁሉ ክርስቶስ ጌታ መሆኑን እንዲመሰክር፥ ጉልበትም ሁሉ ለክርስቶስ ክብር እንዲሰግድና፥ እንዲንበረከክ የእግዚአብሔር ዓላማ ነው (ኢሳ. 45፡23፤ ሮሜ 14፡11፤ ፊሊ. 2፡9-11)። የሰው ዘር ታሪክ በእግዚአብሔር ላይ የማመፅ መዘክር ቢሆንም እንኳ (መዝ. 2፡1-2)፥ ክርስቶስ በመላው ዓለም ላይ በፍጹም ልዑልነቱ የሚገለጥበትን ጊዜም በመጠበቅ ላይ ነው (መዝ. 110፡1)። ጊዜውም ክርስቶስ ኢየሱስ በሁሉም ነገር ላይ ፍጹም ጌታ የሚሆንበት፥ በኃጢኣት ላይ የሚፈርድበት እና ገዥነቱ የሚረጋገጥበት ይሆናል (ራእይ 19፡15-16)።  ዓላማውን በማከናወን ረገድ እግዚአብሔር የዓለም ነገሥታት በዙፋናቸው እንዲሆኑ ፈቅዷል። በየዘመናቱ ታላላቅ መንግሥታትና መሪዎቻቸው ተነሥተዋል፥ ወድቀዋል። ከእነዚህም ጥቂቶቹ ግብፅ፥ ሶርያ፥ ባቢሎን፥ ፋርስ፥ ግሪክ እና ሮም ይገኙባቸዋል። የመጨረሻው መንግሥት ግን ከሰማይ የሚመጣውና ክርስቶስ የሚገዛው ይሆናል (ዳን. 7፡13-14)።  ክርስቶስ ኢየሱስ የሕዝቦች ገዢ መሆን ብቻ ሳይሆን፥ የዳዊት ልጅ እንደመሆኑ በዳዊት ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ የእስራኤል ንጉሥ ይሆናል (ሉቃስ 1፡31-33)። ይህ የሚረጋገጠው፥ ጌታ ዳግም ተመልሶ የሺህ ዓመት መንግሥቱን ሲመሠርትና በመላው ዓለምና በእስራኤል ላይ ሲነግሥ ነው።  ሉዓላዊነቱም ራስ ከሆነላት ቤተ ክርስቲያን ጋር ባለው ኅብረት ይገለጣል (ኤፌ. 1፡22-23)። ክርስቶስ የዓለም፥ የእስራኤል እና የቤተ ክርስቲያንም ራስ (ኤፌ. 1፡20-21) እንደመሆኑ በሰው ሁሉ ላይ ልዑል ፈራጅ ነው (ዮሐ. 5፡27፤ ኢሳ. 9፡6-7፤ መዝ. 72፡1-2፥ 8፥ 11)።  3. ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ የሆነ ቃል፡፡ በተለይ በአዲስ ኪዳን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ የሆነ ቃል መሆን ተገልጧል። እግዚአብሔር በአካል የተገለጠበት እና ባሕርይው፥ እንዲሁም ማንነቱ የተገለጠበት መሆኑን ነው ይህ የሚያሳየው። የእግዚአብሔር ባሕርያት ሁሉ በክርስቶስ ተገልጠዋል፤ በተለይም ጥበቡ፥ ኃይሉ፥ ቅድስናው እና ፍቅሩ። ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ምንነት የተገለጠበት ቃል ነው (ዮሐ. 1፡ 1)። ከሌላ ከማንኛውም መለኮታዊ መገለጥ ይልቅ፥ ሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔርን በትክክል ሊያውቁት ይችላሉ። ዕብራውያን 1፡3 ውስጥ እንደተገለጠው፥ “እርሱም የክብሩ መንፀባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ ሁሉን በሥልጣኑ ቃል እየደገፈ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ፥ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ”። የእግዚአብሔር ዋና ዓላማ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ራሱን ለፍጥረታቱ መግለጥ ነው።  4. ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ አዳኝ። የመጽሐፍ ቅዱስ ዋናውና ታላቁ መልእክት፥ በሰው መፈጠርና በኃጢአት መውደቅ ጀምሮ በአዲስ ሰማይና አዲስ ምድር በሚያበቃው የሰው ዘር ታሪክ ክንዋኔ ውስጥ የሚገኘው የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የአዳኝነት ሥራ ነው። ክርስቶስ ሰይጣንን ድል የሚያደርግ የተስፋ ዘር ነበር (ዘፍ. 3፡15)። የዓለምን ኃጢአት የሚሸከም የያህዌ አገልጋይ መሆኑ በብሉይ ኪዳን ተመልክቷል (ኢሳ. 53፡4-6፤ ከዮሐ. 1፡29 ጋር ያመሳከሩት)። የኃጢአት መሥዋዕት ሆኖ የዓለምን ሁሉ የኃጢአት ፍርድ በመሽከም በመስቀል ላይ መሞት ነበረበት (1ኛ ቆሮ. 15፡3-4፤ 2ኛ ቆሮ. 5፡ 19-21፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡ 18-19፤ 1ኛ ዮሐ. 2፡2፤ ራእይ 1፡5)። በአዳኝነቱ የኃጢአታችን መሥዋዕት ብቻ ሳይሆን፥ ሊቀ-ካህናችንም ነው (ዕብ. 7፡25-27)።  በቅዱሳት መጻሕፍት ተደጋግሞ እንደተረጋገጠው፥ ከእግዚአብሔር ዋና ዋና ዓላማዎች አንዱ፥ ለጠፋው የሰው ዘር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድነትን መስጠት ነው። በዚሁ መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስ ከዘፍጥረት እስከ ራእይ በከፍተኛ ሁኔታ እንደብቸኛው አዳኝ ቀርቧል (ሐዋ. 4፡ 12)።  ለ. የሰው ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ  መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈበት ዋና ዓላማ እግዚአብሔርን ለማክበር ሲሆን፥ ይህን ከመፈጸሙ አንጻር የሰውንም ታሪክ ያቀርባል። በመጀመሪያዎቹ የኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፎች የሚገኘው የፍጥረት ታሪክ በአዳምና ሔዋን መፈጠር ተደምድሟል። መጽሐፍ ቅዱስ በአጠቃላይ የሚገልጠው፥ እግዚአብሔር ለሰው ዘር ያለውን ዓላማ ነው።  የሚቀጥሉት ምዕራፎች እንደሚገልጡት፥ እግዚአብሔር ለዓለም ሕዝቦች ያለው ሉዓላዊ ዓላማ በትውልዶች ታሪክ ውስጥ ተገልጧል። የአዳምና ሔዋን የቅርብ ትውልዶች በኖኅ ዘመን በጥፋት ውኃ ጠፉ። ዘፍጥረት 10 ውስጥ የኖኅ ትውልዶች ሦስቱን ዋና ዋና የሰው ዘር ክፍፍሎች እንደመሠረቱ ተመዝግቧል። የኖኅ ትውልዶች ከእግዚአብሔር መንገድ ተሰናከሉና በባቢሎን ግንብ ሥራ ወቅት ተቀጡ። ከዚያም እግዚአብሔር ራሱን በእስራኤል በኩል የሚገልጥበትን ዓላማ ለመፈጸም አብርሃምን መረጠ። ከኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 12 ጀምሮ ያለው የመጽሐፍ ቅዱስ ዋና መልእክት የእስራኤል መንግሥት መመሥረትና የዚያ ታሪክ ነው። የብሉይ ኪዳን አብዛኛው ክፍል የሚገልጠው፥ በዙሪያዋ ከነበሩ አሕዛብ ጋር ስትነጻጸር እጅግ ትንሽ ስለነበረችው እስራኤል ነው። በእግዚአብሔር ዓላማ ውስጥ፥ በብሉይ ኪዳን ለአብርሃም በአንተ ዘር የሰው ዘር ሁሉ ይባረካል ተብሎ የተነገረለት ተስፋ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት ሙሉ በሙሉ እውን በመሆን በአዲስ ኪዳን ተፈጽሟል።  ሌላ አዲስ የሰው ዘር ክፍፍል በአዲስ ኪዳን ውስጥ ይታያል። ይኸውም ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኛቸው ያመኑ አረማውያንና፥ አይሁድን የያዘችው የክርስቶስ አካል ቤተ ክርስቲያን ናት። አዲስ ኪዳን፥ በተለይም በሐዋርያት ሥራና በመልእክቶች አማካይነት እግዚኣብሔር ከቤተ ክርስቲያን ጋር ያለውን ግንኙነት ያስገነዝባል። የራእይ መጽሐፍ የዚህ ሁሉ ታላቅ ፍጻሜ ነው። በግብፅና በሶሪያ በመጀመር በባቢሎን፥ በሜዶንና ፋርስ፥ በግሪክ፥ በሮም እያሉ የቀጠሉት ታላላቅ ተከታታይ መንግሥታት ሂደት፥ በክርስቶስ ዳግም ምጽአት ጊዜ ከሰማይ በሚመጣው መንግሥት ይደመደማል። በሺህ ዓመቱ መንግሥት ዘመን የሚገኙት፥ አይሁድም ሆኑ አረማውያን፥ እስራኤል በመሢሕ ንጉሥዋ ሥር በምትይዘው መሬት ላይ ሆና እና የዓለም ሕዝቦች ባጠቃላይ የሺህ ዓመቱን መንግሥት በረከት ይጋራሉ።  መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስን ማዕከሉ የሚያደርግና የእግዚአብሔር ክብር በዓለም ታሪክ ጋር እንዴት እንደተገለጠ የሚያሳይ ሲሆን፥ በዚሁ መሠረት የእግዚአብሔር ዋና ዋና ሥራዎቹ በሕዝቦች ላይ ባለው የበላይነት፥ ለእስራኤል ባለው ታማኝነትና ለቤተ ክርስቲያን ባለው ጸጋ አማካይነት ተገልጧል። የዚህ ሁሉ መጨረሻ፥ ታሪክ በሚፈጸምበት፥ እንዲሁም ዘላለም በሚጀምርበት፥ በአዲሱ ሰማይና በአዲሱ ምድር፥ በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም ይሆናል።  ሐ. የመጽሐፍ ቅዱስ ዓላማ  በጽሑፍ በሰፈረው የእግዚአብሔር ቃል መሠረት፥ እግዚአብሔር ያደረገው ወይም የሚያደርገው ነገር፥ ከፍጥረት መጀመሪያ እስከ ዘላለም ያለው አንድ ታላቅ ዓላማ ተገልጧል። ይህ ታላቅ ዓላማ የእግዚአብሔር ክብር መገለጥ ነው። ለዚህ ዓላማ መላእክት ተፈጠሩ፥ ቁሳዊዎቹ ዓለማት ይህን ክብር ያንጸባርቁ ዘንድ ተፈጠሩ፥ እና ሰው በእግዚአብሔር መልክና አምሳል ተፈጠረ። በማይመረመረው የእግዚአብሔር ተግባራዊ ጥበብ ኃጢአት እንኳ ተፈቅዶ፥ ድነትም ተሰጥቷል። ይህ የሆነው የዚህን ታላቅ ዓላማ መፈጸም አስቀድሞ በማሰብ ነው።  እግዚአብሔር ክብሩን ለመግለጥ መፈለጉ ትክክልና ተገቢ ነው። ሰው ራሱን ገናና ለማድረግ የሚያስችለው አንዳች ነገር የለውም። ምክንያቱም ፍጹምነት በርሱ ዘንድ አለመኖሩ ነው። እግዚአብሔር ክብሩን ገለጠ ማለት፥ ለፍጥረታት ሁሉ የማይወሰን በረከትን የሚያመጣ እውነትን ገለጠ እና አሳየ ማለት ነው። እግዚአብሔር በሕልውናው ዘላለማዊና በፍጹምነቱ ምሉእ እንደመሆኑ፥ ፍጹም ክብር ይገባዋል። ፍጥረቶቹ የሚገባውን ክብር ቢነፍጉት ግን ድርጊታቸው ሕገወጥ ነው። እግዚአብሔር ክብሩን የሚገልጠው ለራሱ ሳይሆን፥ ለፍጥረታቱ ጥቅም ነው። እግዚአብሔር ራሱን ለፍጥረታቱ መግለጡ፥ ለፍቅርና አምልኮ

መጽሐፍ ቅዱስ፡- መልእክቱና ዓላማው Read More »