የሕይወት እንጀራ አገልግሎት

ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

መላእክት

This entry is part 22 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ሀ. የመላእክት አፈጣጠር  መጽሐፍ እንደሚናገረው፥ እግዚአብሔር ሰውን ከመፍጠሩ አስቀድሞ ለቁጥር የሚያዳግቱ ሠራዊተ መላእክት ፈጥሯል። መላእክት ልክ እንደ ሰው ሕልውና ያላቸው ከመሆናቸውም በላይ፥ ታላቅ እውቀትና የግብረ ገብ ኃላፊነት ችሎታ አላቸው። “መልአክ” ማለት ልዩ በሆነ አገባሱና አገላለጡ መልእክተኛ ማለት ነው። ቃሉ አንዳንዴ ለሌሎች መልእክተኞች ማለት በራእይ 2-3 የተጠቀሱትን የሰባት የእስያ አብያተ ክርስቲያን መልእክተኞች ላመሳሰሉት መጠሪያ ሊሆንም ይችላል (ራእይ 1፣ 20፤ 2፡1፥ 8፥ 12፥ 18፤ 3፡1፥ 7፥ 14)። አንዳንዴም ለሰብአዊ መልእክተኞች መጠሪያነት አገልግሏል (ሉቃስ 7፡24፤ ያዕ. 2፡25)። የሞቱ ሰዎችን መንፈስ ላመጥቀሻም ውሏል (ማቴ. 18፡10፤ ሐዋ. 12፡15)። እዚህ ላይ ከፍተኛ ግንዛቤኝ የሚሻው ዐቢይ ጉዳይ፥ ሰዎች ሲሞቱ ወደ መላእክትነት ይለወጣሉ ወይም ከሰዎች የተለየ መንፈስ ይሆናሉ ማለት አለመሆኑ ነው። “መልእክተኛ” የሚለው ቃል በጣም ሰፊ አሳብ ይዟል። በዚህ ሁኔታ “መላእክትን የሚለው ቃል የእግዚአብሔርን መልአክ ለማመልከትም፥ ማለት ክርስቶስ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ሰመላእክት መልክ ከእግዚአብሔር ወደ ሰው የተላከ መሆኑን ለመግለጫነት አገልግሷል (ዘፍጥ. 16፡1-13፤ 21፡17-19፤ 22፡11-16)።  ቃሉ ሰውን ወይም እግዚአብሔርን በግልጥ ለማመልከቻነት በማይውልበት ጊዜ፥ ግብረ ገባዊ ኃላፊነት ላሰባቸውና፥ በዚህም አኳያ እግዚአብሔርን ለሚያገለግሉ ማለት ልዩ ሁኔታ ላላቸው ሰዎች መጠሪያነት ያገለግላል። መላእክት እንደ ሰው ሁሉ ለዘላለም የሚኖሩና ከሌሎች ፍጡራን የሚሰዩ ናቸው። እግዚአብሔር በዘመናት ባለው ዕቅድ ውስጥ ጎላ ያለ ስፍራ የሚይዙ ሲሆኑ፥ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ከመቶ ጊዜ በላይ፥ አዲስ ኪዳን ውስጥ ደግሞ ይበልጥ በተደጋጋሚ ተጠቅሰዋል።  መላእክት እጅግ ከቁጥር በላይ ሆነው በአንድ ጊዜ የተፈጠሩ ናቸው (ዕብ. 2፡22፤ ራእይ 5፡11)። ጥበብ፥ ፈቃድና ስሜት ያለው አንድ ፍጡር የሚኖሩት ባሕርያት ሁሉ አሏቸው። ከዚህም የተነሣ ለእግዚአብሔር አምልኮ የማቅረብ ችሎታ አላቸው (መዝ. 148 ፡2)። ስላ አገልግሎታቸውና ሥነ- ምግባራዊ ምርጫቸውም ኃላፊነት አለባቸው።  2204 በመንፈሳዊ ሥርዓት የተፈጠሩ እንጂ፥ ሰብአዊ አካል ያላቸው አይደሉም (1ኛ ቆሮ. 15፡44)። አንዳንዴ ግን በአካል ሊገለጡና እንደ ሰው ሊታዩ ይችላሉ (ማቴ. 28፡3፤ ራእይ 15፡6፤ 18፡1)። በመዋለድ አይባዙም፥ አካላዊ ሞትም አይሞቱም። ከሰው ጋር የሚመሳሰሉበት ነገር ቢኖርም፥ ዓበይት በሆኑ ነገሮች የተለዩ ናቸው።  ለ. ያልወደቁት መላእክት  በአጠቃላይ መላእክት፥(1) ያልወደቁ መላእክት፥ (2) የወደቁ መላእክት ተብለው በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ይመደባሉ። ያልወደቁት መላእክት በዘመናቸው ሁሉ የተቀደሱ ስለሆኑ ቅዱሳን መላእክት” ተብለው ይጠራሉ (ማቴ. 25፡31)። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በአጠቃላይ ስለ መላእክት ሲጠቀስ በዓይነ ሕሊና የሚታዩት ያልወደቁ መላእክት ናቸው። የወደቁ መላእክት የሚባሉት ደግሞ ቅድስናቸውን ያልጠበቁት ናቸው።  ያልወደቁ መላእክት በሚከተለው አኳኋን በልዩ ክፍል የሚመደቡ ሲሆን፥ ከእነርሱም አንዳንዶቹ በስም ተጠቅሰዋል።  1. የቅዱሳን መላእክት ሁሉ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሲሆን፥ የስሙም ትርጉም ንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው” ማለት ነው (ዳን. 10፡21፤ 12፡1፤ 1ኛ ተሰ. 4፡16፤ ይሁዳ 9፤ ራእይ 12፡7-10)።  2. ከዋና ዋናዎቹ የእግዚአብሔር መልእክተኞች አንዱ ቅዱስ ገብርኤል ሲሆን፥ የስም ትርጉም ተግዚአብሔር ጀግና” ቀሚል አው። ለዳንኤል የተላኩ ታላላቅ መልእክትን (ዳን. 8፡16፤ 9፡21)፥ ለዘካርያስ (ሉቃስ 1፡18-19)፤ እና ለቅድስት ድንግል ማርያም (ሉቃስ 1፡26-38) የተላለፉትን ጭምር በታማኝነት አድርሷል።  3. ተስዙዎቹ መላእክት የየራሳቸው ስም ባይሰጣቸውም፥ የተመረጡ ተብለው ይጠራሉ (1ኛ ጢሞ. 5፡21)። ይህ አሳብ የሚገርም ነጥብ አለው። ይህም መላእክት በመለኮታዊ አጠራር የተመረጡ መባላቸው፥ ዳግም ተወልደው የዳኑ ሰዎችም የተመረጡ ተብለው ከተጠሩበት አጠራር ጋር መመሳሰሉ አስደናቂ ነው።  4 . “ኃይላትና ሥልጣናት” የሚለው መጠሪያ የወደቁትንም ሆኝ ያልወደቁን መላእክት ለመጥሪያነት የሚያገለግል ይመስላል (ሉቃስ 21፡26፤ ሮሜ 8፡38፤ ኤፌ. 1፡21፤ 3፡10፤ ቈላ. 1፡16፤ 2፡10፥ 15፤ 1ኛ ጴጥ. 3፡22)። ይህም በመሆኑ ሰዎችን ለመቆጣጠር ወይም ለመያዝ በቅዱሳኑና በወደቁት መላእክት መካከል የማያቋርጥ ጦርነት ይካሄዳል።  5 . አንዳንድ መላእክት ኪሩቤል በመባል የሚታወቁ ሊሆኝ፥እነርሱም የእግዚአብሔርን ቅድስና ከማንኛውም ዓይነት የኃጢአት ርኩሰት የሚከላከሉ ሕያው ፍጡራን ናቸው(ዘፍጥ. 3፡24፤ ዘጸ. 25፡18፥ 20፤ ሕዝ. 1፡1-18)። የወደቁት መላእክት አለቃ ሰይጣንም በመጀመሪያ ቅዱስ ሆኖ ለዚህ ዓላማ ነበር የተፈጠረው (ሕዝ. 28፡14)። በብሉይ ኪዳን፥ መገናኛው ድንኳን እንዲሁም ቤተ መቅደስ ቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ የታቦቱን የሥርየት መክደኛ የሚጠብቁት የኪሩቤል ምስሎች ከወርቅ የተሠሩ ነበሩ።  6. ሱራፌል በመባል የሚጠሩት መላእክት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱት አንዴ ብቻ፥ ኢሳይያስ 6፡2-7 ውስጥ ነው። እነርሱም ስድስት ክንፎች ያሏቸው፥ እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑ፥ በእግዚአብሔር ወደ ምድር የሚላኩና በተለይ የእርሱን ክብር የሚጠብቁ ናቸው።  7. “የእግዚአብሔር መልአክ” የሚለው ቃል የክርስቶስን በመልከ መልክ መለጥ ለማመልከት ብሉይ ኪዳን ውስጥ በተደጋጋሚ ተጠቅሷል። ስሙም የሚገባው ለእግዚአብሔር ብቻ ሲሆን፥ ያገለገለውም ከመለኮት ስምድር መገለጥ ጋር ነው። በመሆኑም በምንም ሁኔታ የሠራዊተ መላእክት መጠሪያ ሊሆን አይገባም (ዘፍጥ. 18፡1-19፡29፤ 22፡11፥ 12፤ 31፡11-13፤ 32፡24-32፤ 48፡15፥ 16፤ ኢያሱ 5፡13-15፤ መሳ. 13፡19-22፤ 2ኛ ነገሥት 19፡35፤ 1ኛ ዜና 21፡12-30፤ መዝ. 34፡7)። የእግዚአብሔር መልአክ በሆነው ክርስቶስና በሌሉች መላእክት መካከል ያለው እጅግ ከፍተኛ ልዩነት፥ ጳውሎስ ወደ ዕብራውያን ባስተላለፈው መልእክት ውስጥ ተገልጧል(ዕብ. 1፡4-14)።  ሐ. የወደቁ መላእክት  ያልወደቁ መላእክት እንዳሉ ሁሉ፥ ስፍር ቁጥር የሌላቸውና የመጀመሪያ ክብራቸውን ትተው የወደቁ መላእክት መኖራቸውም ተገልጧል። ሲፈጠር ቅዱስ በነበረውና በኋላ ግን በትዕቢቱ ከከፍታ ቦታ በወደቀው መልአክ፥ በሰይጣን የተመሩት እነዚህ ለቁጥር የሚያዳግቱ መላእክት ከዳተኞች፥ በእግዚአብሔር ላይ ያመፁ፥ እንዲሁም በተፈጥሯቸውም ሆነ በስፍራቸው ኃጢአተኞች ሆኑ።  የወደቁ መላእክት በሁለት ይመደባሉ። እነርሱም፦ (1) ነጻ የሆኑና (2) በእስራት ያሉ ናቸው። ከወደቁት መላእክት ሰይጣን ብቻ ነው በተለይ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚጠቀሰው። ሰይጣን በወደቀ ጊዜ ብዙ ከእርሱ ያነሱ ታናናሽ መላእክትን አስከትሎ እንደነበር ለመገመት ይቻላል (ዮሐ. 8፡44)። ከእነርሱም አንዳንዶቻቸው እስከ ታላቁ የፍርድ ቀን ድረስ ታስረው ለፍርድ ተጠብቀዋል (1ኛ ቆሮ. 6፡3፤ 2ኛ ጴጥ. 2:4፤ ይሁዳ 6)። ሌሎቹ ደግሞ ለጊዘው ነጻ የሆኑና አጋንንት ወይም መናፍስት እየተባሉ በአዲስ ኪዳን በተደጋጋሚ የሚጠቀሱት ናቸው (ማር. 5፡9 15፤ ሉቃስ 8፡30፤ 1ኛ ጢሞ. 4፡1)። በድርጊቱ ሁሉ ተሳታፊ ሆነው ሰይጣንን ስለሚያገለግሉት፥ የመጨረሻ ዕጣውም ተሳታፊዎች ይሆናሉ (ማቴ. 25፡41፤ ራእይ 20፡10)።  መ. የቅዱሳን መላእክት አገልግሎት  መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ መላእክት በሰፊው የተጠቀሰው አገልግሎታቸው ነው። ቀዳሚው አገልግሎታቸው እግዚአብሔርን ማምለክ ሲሆን፥ ራእይ 4፡8 ውስጥ የአንዳንዶቹ አገልግሎት፥ “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም” ተብሏል። ይህ በሌላም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ተጠቅሷል (መዝ. 103፡20፤ ኢሳ. 6፡3)። በአጠቃላይ ቅዱሳን መላእክት በተለያዩ ብዙ መንገዶች እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ መሆናቸው ቀጥሎ ባሉት ተግባራታቸው በመጠኑ ተገልጧል።  1. በፍጥረት መጀመሪያ(ኢዮብ. 38፡7)፥ ሕግ በሚሰጥበት ጊዜ(ሐዋ. 7፡53፤ ገላ. 3፡19፤ ዕብ. 2፡2፤ ራእይ 22፡16)፥ ክርስቶስ ሲወለድ (ሉቃስ 2፡13)፥ ሲፈተን (ማቴ. 4፡11)፥ በአትክልቱ ስፍራ(ሉቃስ 22:43)፥ በትንሣኤ (ማቴ. 28፡2)፥ በዕርገት ጊዜ(ሐዋ. 1፡10) የነበሩ ሲሆን፥ በክርስቶስ ዳግም ምጽአት ጊዜም አብረውት ይገለጣሉ (ማቴ. 24፡31፤ 25፡31፤ 2ኛ ተሰ. 1፡7)።  2. ቅዱሳን መላእክት የድነት ወራሾች የሆኑትን የሚያገለግሉ መናፍስት ናቸው (ዕብ. 1፡14፤ መዝ. 34፡7፤ 91፡11)። ከመላእክት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ወይም ኅብረት እንዲኖረን ባይነገረንም፥ የሁልጊዜ በጎ አገልግሎታቸውን ልንረዳ ይገባል።  3. መላእክት በምድር ላይ ያሉ ነገሮችን የሚመለከቱና ምስክሮች ናቸው (መዝ. 103፡20፤ ሉቃስ 12፡8፥ 9፤ 15፡10፤ 1ኛ ቆሮ. 11፡10፤ 1ኛ ጢሞ. 3፡16፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡12፤ ራእይ 14፡10)።  4. አልዓዛር ሲምት ወደ አብርሃም እቅፍ የተወሰደው በመላእክት ነበር(ሉቃስ 16፡22)።  5. መልእክት በታሪክ አተረዘሩት እገልግሎቶቻቸው በተጨማሪ፥ ጌታችን ወደ ምድር ሲመለስ አብረውት ይመጣሉ፥ በአዲሲቷ ኢየሩሳሌምም ለዘለም ይታያሉ(ዕብ. 12፡22-24፤ ራእይ 19፡14፤ 21፡12)። ቅዱሳን መላእክት በሺህ ዓመቱ መንግሥት መጨረሻ፥ ማለት በአዲሱ ዘላለማዊ መንግሥት መጀመሪያ፥ ፍርድና ሽልማት ሳይጠብቃቸው አይቀርም። የወደቁት መላእክት ደግሞ በዚሁ ጊዜ ከመሪያቸው ጋር በአንድነት ይፈረድባቸውና ወደ እሳት ባሕር ይጣላሉ።  6. በመላው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጠው የቅዱሳን መላእክት አገልግሎት ትምህርት እጅግ ጠቃሚ ነው። በታሪክ የተገለጠውንና እግዚአብሔር ለፍጡራኑ ያለውን ሰጎ ፈቃድና ልዑላዊ

መላእክት Read More »

ቃል ኪዳኖቹ

This entry is part 21 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

የሰው ልጅ ታሪክ ዘላለማዊው የእግዚአብሔር ዓላማ አፈጻጸም ታሪክ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጣል። የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ዕቅድ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጠ ሲሆን፥ እርሱም ክቡር የሆኑ ቃል ኪዳኖቹን መሠረት ያደረገ ነው። ቢያንስ ስምንት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ኪዳኖች በቃሉ ተመዝግበው ይገኛሉ። እነርሱም እግዚአብሔር ስለ ዓለም ካለው ዕቅድና ዓላማ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ዓበይት እውነታዎች ያካትታሉ። ከእነዚህ ቃል ኪዳኖች ብዙዎቹ መፈጸማቸው በማይቀርና በአዋጅ መልካ የቀረቡ መለኮታዊ ዓላማዎች ናቸው። የሥነ-መለኮት ጠበብት ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ኪዳኖች በተጨማሪ ከሰው ድነት ጋር የሚገናኙ ሦስት ሥነ-መለኮታዊ ቃል ኪዳኖችን አቅርበዋል።  ሀ. ሥነ-መለኮታዊዎቹ ቃል ኪዳኖች  የሥነ-መለኮት ሊቃውንት የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ ዓላማ በሚገልጡበት ጊዜ፥ ዘላለማዊ ዓላማው የመረጣቸውን ማለት፥ ከዘላለም በፊት ለድነት የወሰናቸውን ማዳን ነው የሚል ፅንሰ አሳብ አቅርበዋል። ይህን ትምህርታቸውን ሲያስፋፉ መሠረታዊ የሆኑ ሦስት ሥነ-መለኮታዊ ቃል ኪዳኖችን ያብራራሉ።  1. ከአዳም ጋር የተደረገው የሥራ ቃል ኪዳን። አዳም በቃል ኪዳኑ መሠረት እግዚአብሔርን ቢታዘዝ፥ ሰሙንፈሳዊ ሁኔታው የሚጠበቅ ከመሆኑም ባሻገር፥ ዘላለማዊ ሕይወትም ያገኝ ነበር። ቃል ኪዳኑ መልካምና ክፉ እውቀት ስለምትሰጠው ዛፍ በተነገረውና “ከእርሱ በላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና” (ዘፍጥ. 2:17) ተብሎ በተሰጠ ማስጠንቀቂያ የተደገፈ ነበር። ከዛፉ ባይበላ ኖሮ ባልሞተም ነበር፤ ደግሞም እንደ ቅዱሳን መላእክት ለእርሱም ተሰጥቶ የነበረው ሰፍራ ይጸናለት ነበር ተብሎ ይገመታል። ይህ ቃል ኪዳን ሙሉ በሙሉ የተመሠረተው በግምት ላይ በመሆኑና መጽሐፍ ቅዱስ በቃል ኪዳንነት ያልተጠቀሰ በመሆኝ፥ እንዲሁም በቂ መሠረት እንደሌለው ስለታወቀ ሰብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ዘንድ ተቀባይነት የለውም።  2. ሌላው ቃል ኪዳን ማመቤዠት ቃል ኪዳን” ተብሎ የሚጠራ ሲሆን፥ እርሱም የሰውን ድነት የሚመለከት ሆኖ በእግዚአብሔር እብና በእግዚአብሔር ወልድ መካክል አላለም ጀምሮ ያተደረገ ቃል ኪዳን ነው ተብሏል። ይህ ቃል ኪዳን የእግዚአብሔር ልጅ ለሚያምኑበት የድነት ቤዛ እንደሚሆንና እግዚአብሔር አብም መሥዋዕቱን እንደሚቀበልለት ተስፋ የተሰጠበት ነው።  ቃል ኪዳኑ ቀደም ሲል ከተጠቀሰው የሥራ ቃል ኪዳን ይበልጥ የመጽሐፍ ቅዱስ ድጋፍ አለው። ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ እንደሚያውጀው፥ የእግዚአብሔር የማዳን ዕቅድ ዘላለማዊ ነው። በዚህ ዕቅድ መሠረትም ክርስቶስ የኃጢአት መሥዋዕት ሆኖ እንደሚሞትና እግዚአብሔርም በክርስቶስ የሚያምኑትን ለማዳን መሥዋዕቱን በቂ አድርጎ እንደሚቀበል በመታወቁ ነው። ይህም የዓለም ሳይፈጠር በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን” (ኤፌ. 1፡4) ተብሎ በተጻፈው ቃል ተረጋግጧል። በክርስቶስ ያለንን ቦታ በማስመልከት ደግሞ፥ “እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ፥ አስቀድመን የተወሰንን በክርስቶስ ደግሞ ርስትን ተቀበልን (ኤፌ. 4፡11) ተብሏል።  ከእነዚህና ከሌሎችም ጥቅሶች በግልጥ የምንረዳው፥ በማዳን ረገድ የእግዚአብሔር ዓላማ ዘላለማዊ መሆኑን ነው። በእግዚአብሔር አብና እግዚአብሔር ወልድ መካከል የተደረገው ግልጥ ቃል ኪዳን የሚያመለክተው የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ዓላማ ሰዎችን ማዳን መሆኑን ነው።  3. ሌላው አቀራረብ የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ የማዳን ዓላማ እንደ የጸጋቃል ኪዳን” መመልከት ይገባል የሚለው ነው። በዚህ አመለካከት መሠረት ክርስቶስ የቃል ኪዳኑ መካከለኛና እምነታቸውን በእርሱ ለሚያደርጉ ሁሉ ወኪሳቸው እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል። ሰዎች ለዚህ ቃል ኪዳን ብቁ የሚሆኑት፥ ክርስቶስን አዳኛቸው አድርገው እምነታቸውን በእርሱ ላይ ሲያደርጉ ነው። ይህ ቃል ኪዳን ከዘላለማዊ የድነት ዕቅድ በተወሰደ ግምት ላይ የተመሠረተ ሲሆንዎ፥ የእግዚአብሔርን የማዳን ባለጠግነት ያጎላዋል። በመሆኑም የመቤዥት ቃል ኪዳንና የጸጋ ቃል ኪዳን የተወሰነ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት አላቸው። የሥራ ቃል ኪዳን የመጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ድጋፍ የሌለው ከመሆኑ የተነሣ፥ ሰብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም።  ነገር ግን ከፍተኛ ችግር የተነሣበት ሁኔታ አለ። ይኸውም የሥነ-መለኮታዊ ቃል ኪዳኖች ደጋፊ የሆኑ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ የእግዚአብሔርን የማዳን ዕቅድ እርሱ ለሰው ታሪክ ያለው የመጀመሪያ ዓላማ ያደርጉታል። ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ለእስራኤል፥ ለቤተ ክርስቲያንና ለአሕዛብ ያለውን ዕቅድ ልዩ ሁኔታዎች ቸል ወደ ማለት ያዘነብላሉ። የእግዚአብሔር የማዳን ዕቅድ የዘላለማዊ ዓላማው ዋና ክፍል ቢሆንም አጠቃላይ ዕቅዱ ግን አይደለም። የተሻለው አመለካከት እግዚአብሔር በታሪክ ያለው ዕቅድ ክብሩን መግለጥ ነው የሚለው ይሆናል። ይህን የሚያደርገው ሰዎችን በማዳን ብቻ ሳይሆን፥ ዓላማውን በማከናወንና ከእስራኤል፥ ከቤተ ክርስቲያንና ካሕዝቦች ጋር በሚያደርገው ግንኙነት ራሱን በመግለጥ ጭምር ነው። በመሆኑም ታሪክን እግዚአብሔር በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ያለውን ዋና ዋና ዓላማዎች በሚገልጡትና የማዳን ዕቅዱን ባካተቱት ስምንት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ኪዳኖች በኩል መመልከቱ ይመረጣል። በሥነ-መለኮታዊ ቃል ኪዳኖች ላይ የሚያተኩሩ ወገኖች “የቃል ኪዳን ሥነ-መለኮታውያን” ተብለው ሲጠሩ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ኪዳኖች የሚደግፉ ግን “ሥፍረ-ዘመናውያን” ይባላሉ፤ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ኪዳኖች በየሥፍረ-ዘመናቱ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ በየደረጃው የታዩትን ልዩነቶች ስለሚገልጡ ነው።  ለ. መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ኪዳኖች  መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቃለሉት የእግዚአብሔር ቃል ኪዳኖች በሁለት የሚመደቡ ሲሆን፥ እነርሱም ቅድመ ሁኔታዊና ከቅድመ ሁኔታ ነጻ የሆኑ ናቸው። ቅድመ ሁኔታዊ ቃል ኪዳን፥ ቃል ኪዳኑ ከሚመለከታቸው ሰዎች በኩል ለሚወሰድ እርምጃ እግዚአብሔር የሚሰጠው አጸፋ ነው። ቅድመ ሁኔታዊ ቃል ኪዳን፥ ሰዎች የሚጠበቅባቸውን ካደረጉ፥ እግዚአብሔር የራሱን ድርሻ እንደሚያደርግ ፍጹም እርግጠኛነት ዋስትና ይሰጣል። ሰው የሚጠበቅበትን ባያደርግ ግን፥ እግዚአብሔር ቃል ኪዳኑን ደፈጽም ዘንድ አይገደድም።  ከቅድመ ሁኔታ ነጻ የሆነው ቃል ኪዳን ምናልባት አንዳንድ ከሰው የሚፈልጉ ሁኔታዎችን ጨምሮ የተወሰኑ የእግዚአብሔር ዓላማዎች አዋጅ ሲሆን፥ የዚህ ቃል ኪዳን ተስፋዎች ያለ ጥርጥር በእግዚአብሔር ጊዜና አሠራር ይፈጸማሉ። ከስምንቱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ኪዳኖች፥ ኤደን ገነት ውስጥ የተደረገውና የሙሴ ቃል ኪዳኖች ነበሩ ቅድመ ሁኔታ የነበራቸው። ይሁን እንጂ ቅድመ ሁኔታዊ ሳልሆኑ ቃል ኪዳኖችም ሲሆን የተወሰኑ ግለሰቦችን ሰሚመለከት ቅድመ ሁኔታዊ ነገር አለ። ከቅድመ ሁኔታ ነፃ የሆነ ቃል ኪዳን ከቅድመ ሁኔታዊ ቃል ኪዳን የሚለየው፥ የመጨረሻ አፈጻጸሙ በእግዚአብሔር ተስፋ የተሰጠበት፥ እንዲሁም በርሱ ኃይልና ሉዓላዊነት ላይ የተመሠረተ በመሆኑ ነው።  1. ቅኤደን ቃል ኪዳን” እግዚአብሔር ከሰው ጋር የገባው የመጀመሪያ ቃል ኪዳን ነበር (ዘፍጥ. 1፡26-31፤ 2፡16-17)። ያም ቅድመ ሁኔታዊ ሆኖ በአዳም ታማኝ መሆን ወይም አለመሆን ምክንያት ሕይወትና በረከት ወይም ሞትና እርግማን የሚመጡ መሆናቸውን የሚገልጥ ነበር። የኤደን ቃል ኪዳን የሚያጠቃልለው፥ አዳም የሰው ዘር ሁሉ አባት የመሆኑን ኃላፊነት፥ ምድርን የመግዛት፥ እንስሳትን የማዘዝ፥ የአትክልቱን ስፍራ የመጠበቅና መልካሙንና ክፉውን ከምታስታውቀው ዛፍ ፍሬ አለመብላትን ነበር። አዳምና ሔዋን ከተከለከለው ዛፍ ፍሬ በመብላታቸው፥ ያለመታዘዝ ቅጣት የሆነው ሞት ተፈረደባቸው። ወዲያውኑ መንፈሳዊ ሞት ሞቱ፥ ከዚያ ለመዳን ዳግም ልደት አስፈለጋቸው። ቆይተውም አካላዊ ሞት ሞቱ። የእነርሱ ኃጢአት የሰውን ዘር ሁሉ ተመሳሳይ በሆነ ኃጢአትና ሞት ውስጥ ጣለው።  2. ኅዳማዊው ቃል ኪዳን” ከውድቀት በኋላ ከሰው ጋር የተደረገ ነበር(ዘፍጥ. 3፡16-19)። ይህ ቃል ኪዳን ከቅድመ ሁኔታዎች ነጻ የሆነና ከኃጢአቱ የተነሣ የሰው ዕጣ በሕይወቱ ዘመን ምን መምሰል እንዳለበት እግዚአብሔር ያወጀበት ነው። ምንም ዓይነት ይግባኝ ወይም የሰው ኃላፊነት አልነበረበትም።  ቃል ኪዳኑ በአጠቃላይ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሰውን ሕይወት የሚለውጡ ጠቃሚ ሁኔታዎችን የሚያዘጋጅ ነበር። በዚህ ቃል ኪዳን የምንመለከተው ነገር፥ በእባብ የተመሰለው ሰይጣን መረገሙ (ዘፍጥ. 3፡14፤ ሮሜ 16፡20፤ 2ኛ ቆሮ. 11፡3፥ 14፤ ራእይ 12፡9)፤ እና አዳኝ የሚመጣ የመሆኑ ተስፋ (ዘፍጥ. 3፡15) ሲሆን፥ ተስፋው በመጨረሻ በክርስቶስ ተፈጽሟል። በዚያ ጊዜ ሴት በወሊድ ወቅት በብዙ ምጥና ጣር እንድትሠቃይ የተፈረደባት ከመሆኑም ባሻገር፥ ወንድ ራስ መሆኑን አውቃ እንድትገዛለት ተወስኖባታል (ዘፍጥ. 1፡26-27፤ 1ኛ ቆሮ. 11፡7-9፤ ኤፌ. 5፡22-25፤ 1ኛ ጢሞ. 2:11-14)። ከዚያ ወዲህ ሰው ሰፊቱ ወዝ እንጀራ እንዲበላ (ዘፍጥ. 2፡15፤ 3፡17-19)፥ በድካም እንዲኖርና በመጨረሻም እንዲሞት ተፈረደበት (ዘፍጥ. 3፡19፤ ኤፌ. 2፡5)። ከዚህ ጊዜ በኋላ ሰውም በአጠቃላይ በአዳማዊ ቃል ኪዳን ሥር መተዳደሩን ቀጠለ።  3. ኖኀዊው ቃል ኪዳንስኖጎና ከልጆቹ ጋር ተደረገ(ዘፍጥ. 9፡1-18)። ይህ ቃል ኪዳን ከአዳማዊው ቃል ኪዳን የተወሰኑ ሁኔታዎችን የሚደግም ቢሆንም፥ ኃጢአትን ለመግታት ይቻል ዘንድ አዲስ የሰብአዊ መንግሥት ሥርዓትን አምጥቷል። እንደ አዳማዊው ቃል ኪዳን ከቅድመ ሁኔታዎች ነጻ ስለሆነም ከኖኅ ቀጥሎ ላለው የሰው ዘር የእግዚአብሔርን ዓላማ

ቃል ኪዳኖቹ Read More »

ሥፍረ-ዘመናት

This entry is part 20 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ሀ. የሥፍሩ-ዘመናት ትርጉም  መጽሐፍ ቅዱስ በሚጠናበት ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል መገለጥ ሥርዓትን በተከተስ መንገድ በተጎለጡ ወቅቶች መመደቡን መረዳት ይገባል። እነዚህ ጊዜያት የተለዩ በመሆናቸው በየምድባቸው ለይቶ ማወቁ የመለኮታዊ ዓላማ አሠራርን ሰመረዳትና ትክክለኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ለማወቅ ወሳኝ ነው። እነዚህ የእግዚአብሔር የመለኮታዊ ዓላማና አሠራር ጊዜያት “ሥፍረዘመናት” ተብለው ይታወቃሉ። በመሆኑም በእግዚኦብሔር አሠራር ውስጥ ዘመናት የተለያየ ስፍራ ስላላቸውና፥ የሚስኩትም በእርሱ የሥራ ዘመን በመሆኑ ተከታታይ ሥፍረ-ዘመናት ተለይተው ይታያሉ።  ሥፍረዘመን ማለት ለየት ባሉ ዘመናት እግዚአብሔር ሰዎችን የመራበትና የሕይወት መመሪያ የሰጠባቸው የጊዚ ክልል ማለት ነው። በእያንዳንዱ ዘመን ውስጥ ሰዎች የእግዚአብሔር መመሪያን መከተል ተስኗቸው ወድቀዋል። ስለዚህ ከውድቀታቸው የተነሣ እያንዳንዱ ሥፍረ-ዘመን በእግዚአብሔር ፍርድ መገለጥ ያጠቃለሳል። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ሥፍረ- ዘመን” እና “ዘመን አንድ አይደሉም። ነገር ግን እያንዳንዱ ዘመን የራሱ የሆነ ሥፍረ-ዘመን ኦለው። ዘመናት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሰዋል (ኤፌ. 2፡7፤ 3፡5፡9፤ ዕብ. 1፡2)። ዘመናት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተለይተዋል (ዮሐ. 1፡17ን፤ ከማቴ. 5፡21-22፤ 2ኛ ቆሮ. 3፡11፤ እና ከዕብ. 7፡11-12 ጋር አስተያዩ)።  ከሌላ ከማንኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ አጠናን ዘዴ ይበልጥ የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክቶች ለመረዳት የሚጠቅመውና ሰሚገባም የሚገልጠው፥ የእግዚአብሔርን አሠራር ሥፍረ-ዘመናት ማወቅና መረዳት ነው። (* አውግስጢኖስ (354-430 ዓ.ም.) እንዲህ አለ፡- “በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሱ ዘመናትን በትክክል መለየት ከቻልኝ፥ የመጽሐፍ ቅዱስን የተያየዘና ወጥ መሆንን በደንብ እንረዳለን።”) የእግዚአብሔርን ሥፍረዘመናትና፥ ከእነርሱም ውስጥ የተገለጡትን መለኮታዊ ዓላማዎች ውጤቶች በቅድሚያ መረዳት ራሱ የመጽሐፍ ቅዱስን ጠቃሚ እውቀት የመረዳት መጀመሪያ ከመሆኑም ባሻገር፥ ለመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ያለንን ፍላጎት ይቀሰቅሳል። የሰውና የእግዚአብሔር ግንኙነት በየዘመናቱ ሁሉ አንድ ዓይነት አይደለም። በኃጢአት የተበከለውን ሰው በመለኮታዊ ሚዛን ውስጥ አስገብቶ መፈተን አስፈላጊ ነው። ይህ ደግሞ በከፊል በየዘመናቱ የሚታይ የእግዚአብሔር ዓላማ ነው። የፈተናውም ውጤት የሚያሳየው፥ ሰው በማያጠያይቅ ደረጃ ፍጹም በሆነ የውድቀትና የኃጢአተኛነት ሕይወት ውስጥ መሆኑን ያረጋግጣል። በመጨረሻም ሰው ሁሉ የልቡ ምኞትና አሳብ ስንፍናና ቅድስና እንደጎደለው በየዘመናቱ የተረጋገጠ መሆኑ የሚያስደንቅ እውነት ነው።  እያንዳንዱ ሥፍራ-ዘመን የሚጀምረው ሰው አዲስ መብትና ኃላፊነት ውስጥ በመግባቱ ነው። ሥፍራ- ዘመኑ የሚያበቃው ደግሞ፥ ሰው የተሰጠውን ልዩ መብትና ኃላፊነት መወጣት ተስኖት በእግዚአብሔር ጻድቅ ፍርድ ሥር ሲሆን ነው። በየዘመናቱ ሁሉ ለሰው ዘር የሚሰጡ የተለያዩ አመራሮችና ኃላፊነቶች እንደየዘመናቱ ቢለያዩም፥ ዘላለማዊው የእግዚአብሔር የቅድስና ባሕርይ ግን እይላውጥም።  ከዚህ ጋር በተያያዘ ሁኔታ፥ ማንኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ፥ የእግዚአብሔር ቃል መጀመሪያም ሆነ በሁለተኛ ደረጃ የተነገረው ለማን መሆኑን መረዳት ይኖርበታል።  የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሰው ሁሉ ሰቀጥታ ላለበት ዘመን የሚመለከተውን ብቻ መጠቀምና መከተል ይገባዋል። እነዚህን የቃሉን መመሪያዎች ሙሉ በሙሉ እንዲፈጽም ይጠበቅበታል። በሁለተኛ ደረጃ መታየት ያለበት ደግሞ፥ ማንኛውም ክርስቲያን በሌሉች ዘመናት የተሰጡትን ሕጎችና መመሪያዎችን እንደ መንፈሳዊ ትምህርት ሊወስዳቸው ይችላል። በሌሎች ዘመናት ሰዎች እንዲመሩበት ጌታ የሚፈልገው ዓይነት ኑሮን ይኖር ዘንድ እግዚአብሔር አልመረጠውም። መገንዘብ ያለብን መጽሐፍ ቅዱስ የሁሉም ዘመናት ስለሆነ፥ ለሁሉም ዘመን የሚሆን መንፈሳዊ ትምህርት ያለው መሆኑን ነው። ለምሳሌ በዚህ ዘመን ያለ አማኝ፥ አዳም ወይም አብርሃም ወይም እስራኤላውያን በሕግ ይመሩ እንደነበረ የእግዚአብሔር ፈቃድና አሠራር በነበረበት ዘመን ሁኔታ ውስጥ አይደለም፤ ወይም ንጉሡ (ኢየሱስ) መጥቶ መንግሥቱን ምድር ላይ በሚመሠርትበት ወቅት የሚኖሩ ሰዎች ሊኖራቸው የሚገባን ልዩ ሕይወት እንዲኖርም አልተፈጠረም።  የእግዚአብሔር ልጅ ለዕለታዊ ሕይወቱ አጠቃላይ መመሪያ ለማግኘት የሚችለው ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው። ነገር ግን የተለያዩ ዘመናት መመሪያዎችና ሕጎች በጣም የተለያዩና አንዳንዴም የሚቃረኑ ይሆናሉ። በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር የጸጋ ልጅ በቀጥታ እርሱን የሚመለከቱ የቃል ክፍሎች ለይቶ ቢያውቅ፥ የእግዚአብሔር ፈቃድና የእግዚአብሔር ክብር ምን እንደሆነ ተረድቶ በዚያው ለመመላለስ ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን አጠቃላይ ምዕክርነት በምናይበት ጊዜ፥ አንድ አማኝ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ተረድቶ እርሱንም ለመፈጸም ይችል ዘንድ ሰቀጥታ የማይመለከተውን ክፍል ማወቁ የሚመለከተውን የማወቅ ያህል አስፈላጊና ጠቃሚ ነው። ስለዚህ አንድ አማኝ የሥፍረ ዘመናትን በቂ እውቀት ሳያገኝ በአሁኑ ዘመን የእግዚአብሔር ዓላማና ፈቃድ ምን እንደ ሆነ ተረድቶና አስተውሎ ራሱን ከሁኔታዎች ጋር ለማገናዘብ እይችልም። ይህ እውቀት ብቻ ነው በሕግ ይሆን የነበረውን ያለፈ ዘመንና፥ ገና ምንም ማድረግ የማይቻለውን መጪ ዘመን በማሰብ ልባችን እንዳይዝል የሚያደርገው።  መጽሐፍ ቅዱስ ወደተለያዩ ቋንቋዎች በሚተረጎምበት ጊዜ፥ የዘመናት ትክክለኛ መግለጫ የሆኑ እንዳንድ ቃላት እገባብ ትክክል ያለመሆኑ ችግር አለ። ለምሳሌ በግሪክ ቋንቋ “አዮን” የሚለው ቃል በአማርኛ “ዓለም” ተብሎ ተተርጉሟል። የቃሉ ትክክለኛ ትርጉም ግን “ዘመን” ወይም “ሥፍረ-ዘመን” ማለት ነው። ማቴዎስ ወንጌል 13፡49 ውስጥ የተጠቀሰው “በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል” የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው፥ የቁሳዊውን ዓለም መጨረሻ (ኢሳ. 66 ፡22፤ 2ኛ ጴጥ. 3፡7፤ ራእይ 20፡11) ሳይሆን፥ ያለንበትን ዘመን መጨረሻ ነው። በመቃረብ ላይ ያለው የዓለም መጨረሻ ሳይሆን፥ የዘመኑ መጨረሻ ነው። በመጽሐፍ ቅዱሳችን መሠረት ሰባት ታላላቅ ሥፍረ-ዘመናት ያሉ ሲሆን፥ እኛ አሁን ያለንበት፥ የስድስተኛው ሥፍረ-ዘመን መዳረሻ ነው። የሺህ ዓመቱ መንግሥት ዘመን ገና ሊመጣ ነው (ራእይ 20፡4፥ 6)።  በመሠረቱ አንድ ሥፍረ-ዘመን ከሌላው የሚለየው፥ በአዲስ መለኮታዊ አሠራርና በምሪት መጀመሩና በእነዚህም ላይ በሚሰጠው መለኮታዊ ፍርድ በመጠናቀቁ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙዎች የሚረዷቸው ሰባት ሥፍረ-ዘመናት፡-(1). የንጽሕና ሥፍረ ዘመን፥ (2) የሕሊና ሥፍረ-ዘመን (3) የሰብአዊ መንግሥት ሥፍረ-ዘመን፥ (4) የተስፋ ሥፍረ-ዘመን፥ (5) የሕግ ሥፍረ-ዘመን፥ (6) የጸጋ ሥፍረ-ዘመን፥ (7) የሺህ ዓመት መንግሥት ሥፍረ-ዘመን ናቸው።  ዕባቱ ሥፍራ-ዘመናት ሰሚጠኑበት ጊዜ ትምህርቱን ለመረዳት የሚያግዙ አንዳንድ መመሪያዎች ያስፈልጋሉ። አንደኛው፥ የሥፍረ-ዘመናት ትምህርት የሚባለው ሲሆን፥ ይህ ትምህርት መጽሐፍ ቅዱስን የሚገነዘበው፥ ቃል በቃል በሆነ አተረጓጎም ላይ በመመሥረት ነው። ዘመናትንና በውስጣቸው የሚገኙትን ሥፍረ-ዘመናት በደንብ ለይተው ሳያውቁና ሳይረዱ፥ መጽሐፍ ቅዱስን በትክክል ለመረዳትና ለመተርጎም እይቻልም። ሁለተኛው መመሪያ፥ ተከታታይ መገለጥን የሚያሳይ ነው። ይህ በሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ዘንድ በተጨባጭ ታይቷል። መገለጥ በየደረጃው የሚሰጥ መሆኑን የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎችም ተረድተዋል። ሦስተኛው መመሪያ፥ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያብራሩ ሰዎች ሁሉ፥ ተከታዩ መገለጥ ቀዳሚውን ራእይ በመጠኑም ቢሆን የሚተካው መሆኑን ማወቅ ያጎባቸዋል የሚለው ነው። ምክንያቱም የመጀመሪያው መገለጥ በተሰጠበት ወቅት የነበረው ሁኔታ ሊለወጥ፥ ሊቀር ወይም ሌላ የሕይወት መመሪያና ደንብ ሊሰጥ ስለሚችል ነው። ለምሳሌ፥ በሰንበት ቀን እንጨት ሲለቅም በመገኘቱ ወደ ሙሴ ሰፍርድ የመጣው እስራኤላዊ በድንጋይ ተወግሮ እንዲገደል እግዚአብሔር ሙሴን እዞታል (ዘኁል. 15፡32-36)። ዛሬ ይህን ሕግ አንጠቀምበትም። ማድረግም አይገባም። ምክንያቱም በቃሉ መሠረት እኛ የምንኖረው፥ ፍጹም ልዩ በሆነ ሌላ ሥፍረ-ዘመን ውስጥ ነው።  መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተለይተው የተመለከቱት ሰባት ሥፍረ-ዘመናት ቢሆኑም፥ ሦስቱ ግን ከሌሎቹ ይበልጥ ጠቃሚ ሆነው እናገኛቸዋለን። እነርሱም የሕግ ዘመን (ከሙሴ ጊዜ ጀምሮ እስራኤላውያን በብሉይ ኪዳን ዘመን የተመሩበት)፤ የጸጋ ዘመን (የአሁኑ ዘመን)፤ ወደፊት የሚመጣው እና የሺህ ዓመቱ መንግሥት ዘመን ናቸው።  ለ, የንጽሕና ሥፍረ-ዘመን፡- የነጻነት ዘመን  ይህ ዘመን ከሰው መፈጠር (ዘፍጥ. 1፡26፥ 27) ጀምሮ እስከ ዘፍጥረት ምዕራፍ 3 ቁጥር 6 ድረስ ይሄዳል። በዚህ ዘመን ስው ፍሬያማ እንዲሆን፥ ምድርን በሙሉ እንዲገዛ፥ በእንስሳት ላይ እንዲሠለጥን፥ አትክልትና ፍሬ እንዲመገብና የዔደን ገነትን የአትክልት ስፍራ እንዲጠብቅ ኃላፊነት ተሰጥቶት ነበር (ዘፍጥ. 1፡28-29፤ 2፥ 15)።  ሰው የተከለከው አንድ ነገር፥ ይኸውም መልካምና ክፉን ለመለየት እውቀት ከምትሰጥ የዛፍ ፍሬ እንዳይበላ ነበር (ዘፍጥ. 2፡17)። ምንም እንኳ ሰው የከበረ ስፍራ፥ ፍጹም አካል፥ አእምሮና ባሕርይ፥ እንዲሁም ሕይወትን የሚያረኩ ነገሮች ተስተካክለው ቢሰጡት፥ ሔዋን ተፈትና ተሸነፈችና ከተከለከለው ዛፍ ፍሬ በላች፤ አዳምም አብሮአት ሰመብላት ያለመታዘዝዋ ተባባሪ ሆነ (ዘፍጥ. 3፡1-6)። ከዚህም የተነሣ ውጤቱ ሰማያዊ ፍርድ፥ መንፈሳዊ ሞት፥ የኃጢአት እውቀት፥ እግዚአብሔርን መፍራትና የኅብረት መበላሸት ሆነ።  በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ እንኳ እግዚአብሔር የጸጋውን መመሪያ፥ የአዳኝን ተስፋ (ዘፍጥ. 3፡15) ሰመስጠት መዳንን የሚያሳይ የቁርበት ልብስ አለበሳቸው (ዘፍጥ. 3፡21)። ከገነት ተባረሩ፤ የግል ሕይወታቸውን ከዚያ ውጪ እንዲመሩ ተፈረደባቸው (ዘፍጥ. 3፡23-24)። በእነርሱ ላይ በተሰጠው ሰዚህ የእግዚአብሔር ፍርድ የመጀመሪያው

ሥፍረ-ዘመናት Read More »

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የመሙላት ተግባሩ

This entry is part 19 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ህ. የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ሲብራራ  ከመንፈስ ቅዱስ የማዳን ተግባራት፥ ማለት ዳግም ከመወለድ፥ በእማኝ ውስጥ ከማደር፥ ኮማተም እና ከማጥመቅ ሥራ ጋር ሲነጻጸር፥ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ከከርስቲያን ልምምድ፥ ኃያል እና አገልግሎት ጋር ነው የሚገናኘው። ከድነት ጋር የተያያዘው የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ለአንዴና ለዘላለም የሚከናወን ሲሆን፥ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ግን የሚደጋገም ልምምድ መሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ጊዜ ተገልጧል።  የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ከጰንጠቆስጤ ዕለት በፊት በጣም ውሱን በሆነ ደረጃ በአንዳንድ ግለሰቦች ላይ ታይቷል (ዘፀ. 28፡3፤ 31፡3፣ 35፡31፤ ሉቃስ 1፡15፥ 41፥ 67፤ 4፡1)። የእግዚአብሔር መንፈስ ሰግለሰቦች ላይ መውረዱና የአገልግሎት ኃይል የሞላበት ሁኔታ መኖሩ የሚያጠራጥር አይደለም። በአጠቃላይ ሲታይ ግን ካጳንጠቆስጤ ዕለት በፊት በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉት ጥቂት ናቸው። የመንፈስ ቅዱስ ሥራም እግዚአብሔር በልዑል ዓላማው መሠረት በግለሰቦች አማካይነት ከሚያከናውነው አንዳንድ ልዩ ሥራዎች ጋር የተያያዘ ይመስላል። የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ከጰንጠቆስጤ ዕለት በፊት ሕይወቱን ለጌታ ለሰጠ ሰው ሁሉ ክፍት የነበረ መሆኑን የሚያመለክት ነገር የለም።  ከጰንጠቆስጤ ዕለት ወዲህ ያለው ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በአማኞች ሁሉ የሚሠራበት እዲስ ዘመን ሆኗል። በዚህ ዘመን አማኝ ሁሉ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ካምሆኑም በላይ፥ ቅድመ ሁኔታዎችን ካሟላ ሰመንፈስ ቅዱስ ሊሞላ ይችላል። ይህን እውነት አዲስ ኪዳን ውስጥ ያሉ አያሌ መግለጫዎች ያረጋግጣሉ (ሐዋ. 2፡4፤ 4፡8፥ 31፤ 6፡3፥ 5፤ 7፡55፤ 9፡17፤ 11፡24፤ 13፡9፥ 52፤ ኤፌ. 5 ፡18)።  የመንፈስ ቅዱስ ሙላት፥ መንፈስ ቅዱስ በአማኝ ልብና ሕይወት ውስጥ ሊሠራ የሚፈልገውን ያለመከልከል ሲሠራ በእማኝ ሕይወት ውስጥ የሚከሰት ሁኔታ ነው ማለት ይቻላል። ድርጊቱ መንፈስ ቅዱስን ይበልጥ የመቀበል ሳይሆን፥ የእግዚአብሔር መንፈሰ ራሱ አማኙን ይሰልጥ የራሱ ማድረጉ ነው። የመንፈስ ቅዱስ ሙላት በዚህ ዘመን ከጰንጠቆስጤ ዕለት በፊት እንደነበረው በተወሰኑ ሰዎች ላይ ለልዩ ሥራ መከናወን የሚሆን ሳይሆን፥ አማኞች ሁሉ ሊያገኙት የሚቻላቸውና በእርሱ ለሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር የቀረበ የክርስቲያን ልምምድ ነው። ክርስቲያን ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ እንዲሞላ ታዟል (ኤፌ. 5፡18)፤ በመንፈስ ቅዱስ አለመሞላት ግን ከፊል አለመታዘዝ ነው።  ክርስቲያን ባሕርይና ዕለታዊ ሕይወቱ ውስጥ በግልጥ የሚታይ ልዩነት አለ። ጥቂቶች መንፈስ የሞላሳቸው ሆነው ይታወቃሉ። የዚህ ጸጋ ተጠቃሚዎች ቁጥር ጥቂት የመሆኑ ምክንያት፥ ከእግዚአብሔር ልግስና ማነስ ሳይሆን፥ ሰዎች ራሳቸውን ሳያዘጋጁና የእግዚአብሔር መንፈስ ሕይወታቸውን እንዲሞላው ሳይፈቅዱ መቅረታቸው ነው።  በመንፈስ ቅዱስ መሞላት ከመንፈሳዊ እድገት ጋር ሊነጻጸር ይገባል። ድነትን ካገኘ አጭር ጊዚው የሆነ አዲስ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ሊሞላና የመንፈስ ቅዱስ ኃያልም በሕይወቱ ሊገለጥ ይችላል። በክርስትና ሕይወት መብሰል፥ በእውቀት ማደግ፥ በመንፈስ ቅዱስ የመሞላት የማያቋርጥ ልምምድ እና መንፈሳዊ ነገሮችን በመለየት ማደግ ነው። ይህ የሚገኘው፥ እስከ ሕይወት ፍጻሜ በሚያድግ መንፈሳዊ ልምምድ ይሆናል። አዲስ የተወለደ ሕፃን ሙሉ ጤናማ ሊሆን እንደሚችል፥ አዲስ ክርስቲያንም በመንፈስ ቅዱስ ይሞላ ይሆናል። ነገር ግን ልክ አዲስ እንደተወለደ ሕፃን አዲሱን ክርስቲያንም ወደ እድገት የሚያደርሰው በሕይወቱ የሚያገኘው ልምምድ ነው። ለዚህ ነው ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባቦች ስለ መንፈሳዊ እድገት አበክረው የሚናገሩት። የስንዴ ቡቃያ እስከ መከር ያድጋል (ማቴ. 13፡30)። እግዚአብሔር መንፈሳዊ ስጦታዎች ባሏቸው ሰዎች አማካይነት ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ይሠራል። ይህን የሚያደርገው፥ ቅዱሳኑን ለአገልግሎት ብቁ ለማድረግ፥ በእምነት በእውቀትና በመንፈሳዊ ሁኔታ ለማሳደግ እንዲሁም የክርስቶስ አካል የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን ለመቀደስ ነው (ኤፌ. 4፡11-16)። ጴጥሮስ አዲስ የተወለዱ ሕፃናት ለእድገታቸው መንፈሳዊ ወተት እንደሚያሻቸው ይናገራል (1ኛ ጴጥ. 2:2)። “በጌታችንና በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ” (2ኛ ጴጥ. 3፡18) በማለትም ክርስቲያኖችን ይመክራል።  በመንፈስ ቅዱስ ሙላትና በመንፈሳዊ እድገት መካከል ግልጥ የሆነ ግንኙነት አለ። በዚሁ መሠረት በመንፈስ ቅዱስ ካልተሞላ ከርስቲያን ይልቅ የተሞላው በፍጥነት በመንፈስ ያድጋል። በመንፈስ ቅዱስ መሞላትና ውጤቱ የሆነው መንፈሳዊ እድገት፥ እግዚአብሔር ለሕይወቱ ያለውን ፈቃድ ለማግኘት፥ የእርሱንም እቅድ በመፈጸም ረገድ በክርስቲያን ሕይወት የሚከናወኑ ሁለት ዋና ዋና ነገሮች ናቸው (ኤፌ. 2፡10)።  በዚህ መሠረት የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ለማንኛውም አማኝ የሚደረግ ነው። ይህ የሚሆነው ግን አማኙ ሕይወቱን ሙሉ በሙሉ ውስጡ ለሚኖረው መንፈስ ቅዱስ ሲያስገዛ ይሆናል። ይህ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ ግለሰቡን ይቆጣጠረዋል፥ ኃይልም ይሰጠዋል። የመንፈስ ቅዱስ ሙላት የሚገለጥባቸው ሁኔታዎችና የሚሰጠው መለኮታዊ ኃይል ደረጃም ያላያዩ ይሆናል። በመንፈስ ቅዱስ የመሞላት ማዕከላዊ አሳብ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለ ምንም መከልከል በአማኙ ውስጥና በርሱ በኩል ይሠራል የሚል ነው። እግዚአብሔር ለዚያ ሰው ያለው ፍጹም ፈቃድ እንዲህ ይከናወናል።  የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ፅንሰ አሳብ አዲስ ኪዳን ውስጥ በርከት ባሉ ጥቅሶች ተመልክቷል። እጅግ በላቀ ሁኔታ የታየው፥ ሉቃስ 4፡1 ውስጥ “መንፈስ ቅዱስ ሞልቶበት፥ በተባለው በኢየሱስ ነው። መጥምቁ ዮሐንስ እናቱ ማኅፀን ውስጥ እንዳለ በመንፈስ ቅዱስ በመሞላቱ በሌሎች ያልተላመደ ልምምድ በረው (ሉቃስ 1፡15)። እናቱ ኤልሳቤጥና አባቱ ዘካርያሰም ለጊዜው በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው ነበር (ሉቃስ 1፡41፥ 67)። ይህን የመሰለው የመንፈስ ቅዱስ ሙላት፥ ለጥቂት ሰዎች ብቻ የሚደረግና ሰብሉይ ኪዳን በተደረገው አኳኋን የሚከናወን የልዑል እግዚአብሔር እሠራር ነው።  በጰንጠቆስጤ ዕለት ግን በዚያ የነበሩት ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተዋል። ሰጥንታዊቱ ቤተ ክርስቲያን፥ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማድረግ የፈለጉ ሁሉ፥ በጴጥሮስ እንደሆነው (ሐዋ. 4:8) በተደጋጋሚ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተዋል። ለእግዚአብሔር ኃይልና ብርታት የጸለዩ ክርስቲያኖች (ሐዋ. 4፡31)፥ ጳውሎስም ከተለወጠ በኋላ (ሐዋ. 9፡17) እንዲሁ ተሞልቷል። አንዳንዶች፥ ማለት የመጀመሪያዎቹ ዲያቆናት፥ (ሐዋ. 6፡3)። ሰማዕቱ እስጢፋኖስ (ሐዋ. 7:55) እና በርናባስ (ሐዋ. 11፡24) በተከታታይ በመንፈስ ቅዱስ እንደተሞሉ ተናግሯል። ጳውሎስ በተደጋጋሚ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቷል (ሐዋ. 13፡9)፤ ሌሎች ደቀ መዛሙርትም እንዲሁ (ሐዋ. 13: 52)። በእያንዳንዱ ሁኔታ በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉት ራሳቸውን ለእግዚአብሔር የሰጡ ክርስቲያኖች ብቻ ናቸው።  የብሉይ ኪዳን አማኞች በአንዳንድ ሁኔታዎች ተግሣጽ ቢሰጣቸውም በመንፈስ ቅዱስ እንዲሞሉ ሰፍጹም አልታዘዙም። የእግዚአብሔር ሥራ መከናወኑን አስመልክቶ ዘሩባቤል በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፡(ዘካ. 4፡6) ተብሏል። በዚህ ዘመን ክርስቲያን ሁሉ ኤፌሶን 5፡18 ውስጥ እንደተመለከተው በመንፈስ ቅዱስ እንዲሞላ ታዟል። “መንፈስ ቅዱስ ይሙላባችሁ እንጂ፥ በወይን ጠጅ አትስከሩ፥ ይህ ማባከን ነውና።” ድነት በእምነት እንጂ በሥራ እንደማይገኝ፥ በመንፈስ ቅዱስ መሞላትም በሰብአዊ ጥረት የሚሆን አይደለም። ያ የሚሆነው፥ አንድ ሰው እግዚአብሔር በሕይወቱ ይህን የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ይሠራ ዘንድ ሲፈቅድ ነው። ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምንረዳው፥ አንድ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ሳይሞላ ድነትን ሊያገኝ ይችላል። በዚህ መሠረት የመንፈስ ቅዱስ ሙላት የድነት አንዱ አካል አይደለም ማለት ነው። የመንፈስ ቅዱስ ሙላት አንድ አማኝ በዳነ ጊዜ ለአንዴና ለዘላለም በሕይውቱ ከተከናውነው ሥራ ጋር ሊገናዘብ ይችላል። አንድ ሰው ድነትን ሲያገኝ በመንፈስ ቅዱስ ሊሞላ ቢችል እንኳን፥ ክንውኑ ሕይወቱን ከሰጠ ክርስቲያን ውስጥ በተደጋጋሚ የሚፈጸም ነው። በመሆኑም ይህ ተደጋጋሚ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት የክርስቲያኖች የዘወትር ልምምድ ሊሆን ይገባል።  በመንፈስ ቅዱስ መሞላት በተደጋጋሚ መፈጸም ያለበት መሆኑ ኤፌሶን 5፡18 ውስጥ “መንፈስ ይሙሳሳችሁ” በሚለው ቃል ተገልጧል። ቃሉ “ሁልጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ” የሚል ቀጥተኛ ፍቺ ነው ያለው። ይህ ቃል ምንባቡ ውስጥ ሰውነትንና አእምሮን ከሚጎዳ ስካር ጋር ተነጻጽሯል። ስለዚህ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት አንድ ጊዜ ለዘላለም የሚሆን ነገር አይደለም። በተደጋጋሚ የሚከናወን ነገር ሆኖ ሳለ፥ አልፎ አልፎ እንደሚሰማው ሁለተኛ የጸጋ ሥራ መባሉ ግን ተገቢ አይደለም። ለመጀመሪያ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ የመሞላት ልምምድ ያለ ጥርጥር ለክርስቲያን አስደናቂ ሁኔታ ነው። የክርስትና ልምምድንም ወደ አዲስ ከፍታ የሚያወጣ የመሠረት ድንጋይ ሊሆንም ይችላል። ያም ሆነ ይህ ክርስቲያን ለማያቋርጥ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት በእግዚአብሔር ነው የሚተማመነው፤ በትላንትናው መንፈሳዊ ኃይል የሚኖር ክርስቲያን የለም።  በመንፈስ ቅዱስ ከመሞላት ምንነት በመነሣት በክርስቲያኖች መንፈሳዊ ልምምድና በእግዚአብሔር ዓላማ እንዲሁም ፍላጎት መጣጣም መካከል ሰፊ ልዩነት የሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ ከመሞላት ወይም ካለመሞላት የተነሣ ነው ብሎ ለመደምደም ይቻላል። የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈጸም የሚፈልግ አማኝ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ እንዲሆን ከእግዚአብሔር ወደተሰጠው መብት መግባትና ሕይወቱንም ለእግዚአብሔር መንፈስ ሙሉ በሙሉ ማስረከብ

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የመሙላት ተግባሩ Read More »

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፡- የማጥመቅ ተግባሩ

This entry is part 18 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ሀ. የመንፈስ ቅዱስ ማጥመቅ ትርጉም  የመንፈስ ቅዱስ ማጥመቅ አስተምህሮ ከሌሎቹ አስተምህሮዎች ይልቅ ግራ የሚያጋባ ይመስላል። ይህ ችግር በአብዛኛው የሚከሰተው፥ የመንፈስ ቅዱስ የማጥመቅ ተግባር የሚጀምረው ከሌሎቹ ታሳሳቅ የመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች፥ ማለት ከዳግም ልደት፥ መንፈስ ቅዱስ በአማኙ ውስጥ ከማደሩ እና ከማተሙ ተግባር ጋር በአንድ ላይ በመሆኑ ነው። በአንዳንድ ሁኔታዎችም የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና መሞላት ተግባር በአንድ ጊዜ ሆኖ ያውቃል። ይህ ሁኔታ አንዳንድ ተንታኞች ሁለቱም ክንውኖች ተመሳሳይ ናቸው እንዲሉ አድርጓቸዋል። ይሁን እንጂ አንድ ሰው ከመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ጋር የተዛመዱ የመጽሐፍ ክፍሎችን በጥንቃቄ ሲመረምር፥ በአተረጓጎም የሚፈጠረው አለመግባባት ይፈታል። የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን በሚመለከት አዲስ ኪዳን ውስጥ በአጠቃላይ አሥራ አንድ ግልጥ ጥቅሶች አሉ (ማቴ. 3፡11፤ ማር. 1፡8፤ ሉቃስ 3፡16፤ ዮሐ. 1፡33፤ ሐዋ. 1፡5፤ 11፡16፤ ሮሜ 6፡3-4፤ 1ኛ ቆሮ. 12፡13፤ ገላ. 3፡27፤ ኤፌ. 4፡5፤ ቆላ. 2፡12)።  ለ. የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ከጰንጠቆስጤ ዕለት በፊት  አራቱ ወንጌላትና በሐዋርያት ሥራ 1፡5 ውስጥ ያሉት ጥቅሶች ሲመረመሩ፥ በእያንዳንዱ ሁኔታ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ከዚያ በቀደሙ ጊዜያት ያልሆነና የወደፊት ከንውን መሆኑ ግልጥ ይሆናል። ስለ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ብሉይ ኪዳን ውስጥ የተጠቀሰ ነገር የለም። አራቱ ወንጌላት ናቸው ከሐዋርያት ሥራ 1፡5 ጋር በአንድ ላይ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ጎና ሊሆን የሚገባው ነገር እንደነበር የገለጡት። ወንጌላት ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ በኩል የሚያከናውነው ተግባር ሆኖ ነው የቀረበው። ለምሳሌ ማቴዎስ 3፡11 ውስጥ መጥምቁ ዮሐንስ “እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል” በማለት ስለ ክርስቶስ ተንብዮአል። በእሳት የማጥመቁ ጉዳይ በኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ወቅት ስለሚኖረው ፍርድ የሚያመለክት ይመስላል። ይህ ጉዳይ ሉቃስ 3፡16 ውስጥ እንጂ ማርቆስ 1፡8 ወይም ዮሐንስ 1፡33 ውስጥ አልተጠቀሰም። አንዳንድ ተንታኞች ይህን ሁኔታ በሐዋርያት ሥራና በመልእክቶች ከተጠቀሰው የመንፈስ ጥምቀት የተለየ አድርገው ነው የተገነዘቡት። የተሻለው አመለካከት ግን የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት በመላው አዲስ ኪዳን ተመሣሣይ መሆኑን መገንዘቡ ነው። በየትኛውም ሁኔታ ይሁን ጥምቀቱ የሚከናወነው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ነው። ይህም ክርስቶስ ራሱ የርሱን በዮሐንስ እጅ መጠመቅ ከአማኞች ወደፊት በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ ጋር ባነጻጸረበት ሥፍራ ተገልጧል። ይህም ከእርገቱ በኋላ የሚፈጸም ነበር። ክርስቶስ እንዲህ ብሏል፡- ዮሐንስ በውኃ አጥምቆ ነበርና፤ እናንተ ግን ከጥቂት ቀናት በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ” (ሐዋ. 1፡5)።  ሐ. በዚህ ዘመን ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ተጠምቀዋል  የመንፈስ ቅዱስን የማጥመቅ ሁኔታና ጊዜ በተመለከተ ከሚፈጠረው ግራ መጋበት የተነሣ ማንኛውም ክርስቲያን ድነትን ባገኘ ወቅት በመንፈስ ቅዱስ መጠመቁን ብዙዎች አይገነዘቡትም። ይህ እውነት በመንፈስ ቅዱስ የመጠመቅ ጉዳይ ማዕከላዊ ጥቅስ በሆነው በ1ኛ ቆሮንቶስ 12፡13 ውስጥ “አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን፥ ባሪያዎችም ብንሆን፥ እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናል። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል” ተብሏል። ጥቅሱ የሚያመለክተው በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አማካይነት ከዚሁ መንፈስ ጋር ወደ እዲስ ግንኙነት የመግባታችንን እውነት ነው።  “እኛ ሁላችን” የሚለው አገላሰጥ የሚያመለክተው ሁሉንም ሰዎች ሳይሆን፥ ክርስቲያኖችን መሆኑን በሚገባ መገንዘብ አስፈላጊ ነው። ይህም ክርስቲያኖች ለሆኑ ሁሉ የሚሆን እንጂ ከመካከላቸው ለተወሰኑ ቡድኖች ብቻ አለመሆኑ መታወቅ አለበት። እውነቱ ክርስቲያን ሁሉ ከዳነበት ቅጽበት ጀምሮ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ወደ ክርስቶስ አካል መጠመቁ ነው። በዚሁ መሠረት ኤፌሶን 4፡5 ላይ “አንድ ጌታ፥ አንድ ሃይማኖት፥ አንዲት ጥምቀት” ይላል። የውኃ ጥምቀት ሥርዓት የተለያየ ቢሆንም፥ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አንድ ብቻ ነው። የዚህ አገልግሎት ሁለንተናዊነት እንደሚያመለክተው ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ለመጠመቅ ጥረት እንዲያደርግ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድም ጊዜ አልተጠየቀም፤ ከመንፈስ ቅዱስ እንዲሞላ ነው የተመከረው (ኤፌ. 5፡18)።  መ. በመንፈስ ቅዱስ በመጠመቅ ወደ ክርስቶስ አካል መጨመር  በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አማካይነት ሁለት ዋና ዋና ውጤቶች ይገኛሉ። የመጀመሪያው አማኙ መጠመቁ ወይም ወደ ክርስቶስ አካል መጨመሩ ሲሆን፥ ከዚሁ ጋር የተያያዘውና ሁለተኛው ደግሞ አማኙ ወደ ክርስቶስ ውስጥ መጠመቁ ነው። እነዚህ በአንድ ላይ የሚፈጸሙ ሁለት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀቶች እጅግ ዋናዎቹ ናቸው።  በዚህ ዘመን አንድ አማኝ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የእውነተኛ እማኞች ሕያው ሕብረት ወደሆነው የክርስቶስ አካል ይጨመራል። በዚህ ደረጃ የጥምቀት መሠረታዊ ትርጉም መጨመር፥ መገናኘት፥ እንዲሁም አዲስና ዘላለማዊ ግንኙነት መስጠት የሚለውን ይይዛል። በዚህ መሠረት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት በተለያዩ ዘመናት ከተለያዩ ሕዝቦች የመጡ አማኞችኝ ሁሉ ወደ አንድ የክርስቶስ አካል እንዲጨመሩና አዲስና ዘላለማዊ ኅብረትን የሚካፈሉ ያደርጋቸዋል።  በዚህ ሁኔታ በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አማካይነት የሚፈጠረውና አዳዲስ አባላት በተጨመሩ ቁጥር የሚያድገው የእማኞች አካል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተደጋጋሚ ተጠቅሷል (ሐዋ. 2፡47፤ 1ኛ ቆሮ. 6፡15፤ 12፡12-14፤ ኤፌ. 2፡16፤ 4:4-5፥ 16፤ 5፡30-32፤ ቆላ. 1፡24፤ 2፡19)። የዚህ አካል ራስና ክንውኖቹን ሁሉ የሚመራ ክርስቶስ ነው (1ኛ ቆሮ. 11፡3፤ ኤፌ. 1፡22-23፤ 5፡23-24፤ ቆላ. 1፡18)። በዚህ ሁኔታ በክርስቶስ የተፈጠረውንና የሚመራውን አካል ክርስቶስ ራሱ ያሳድገዋል፥ ይጠነቀቅለታል (ኤፌ. 5፡29፤ ፊልጵ. 4፡13፤ ቆላ. 2፡19)። ከከርስቶስ ተግባራት አንዱ ይህን አካል በክብር ለመገለጡ ዕለት ለማቅረብ መቀደስ ነው (ኤፌ. 5፡25-27)።  እማኝም እንደ ክርስቶስ አካል አባልነቱ በዚህ አካል ውስጥ የሚያከናውናቸው ልዩ ልዩ ስጦታዎች ወይም ሥራዎች አሉ (ሮሜ 12፡3-8፤ 1ኛ ቆሮ. 12፡27-28፤ ኤፌ. 4፡7-16)። በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ወደ ክርስቶስ አካል መጨመር፥ ዘር፥ ባሕል ወይም ማንነት የሌለበትን አካል ሕብረት ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን፥ አማኙ የራሱ የተለየ ሥራና ሥፍራ ያለው የመሆን ዋስትና ይሰጠዋል። በአቅሙና በስጦታው መሠረት በአካሉ ውስጥ እግዚአብሔርን እንዲያገለግልም ዕድል ያስገኝለታል። አካሉ በአጠቃላይ “የተጋጠመና የተያያዘ” (ኤፌ. 4፡16) ነው። እባላቱ የተለያዩ ቢሆኑም፥ እካሉ ግን በሚገባ የተያያዘና የተደራጀ ነው።  ሠ. መንፈስ ቅዱስ ወደ ክርስቶስ ውስጥ ማጥመቁ  በመንፈስ የተጠመቀ አማኝ፡የክርስቶስ አካል ከሆኑት አማኞች ጋር ካለው አንድነት ተጨማሪ፥ በክርስቶስ ያለ በመባሉ አዲስ ሥፍራ አለው። ይህ ሁኔታ ዮሐንስ 14፡20 ውስጥ ክርስቶስ በመሰቀሉ ዋዜማ ምሽት “እኔ በአባቴ እንዳለሁ፥ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ፥ እኔም በእናንተ እንዳለሁ፥ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ” በማላት በተናገረው ቃል ተተንብዮ ነበር። “እናንተም በእኔ” የሚለው አነጋገር ሊመጣ ያለውን የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ነበር የተነበየው።  አማኝ በክርስቶስ ውስጥ በመሆኑ ክርስቶስ በሞቱ፥ በትንሣኤውና በክብሩ ከፈጸመው ክንውን ጋር ይዛመዳል። ይህ ሮሜ 6፡1-4 ውስጥ አማኝ ወደ ክርስቶስ እካልነትና ወደ ሞቱ የተጠመቀ መሆኑን በሚያስገነዝበው ቃል ተረጋግጧል። በሞቱ ከተዛመደ ከክርስቶስ ጋር ተቀብሮ አብሮት ተነሥቷል። ብዙ ጊዜ ይህ ድርጊት የውኃ ጥምቀት ሥርዓትን የሚወክል ተደርጎ ይወሰዳል። ይህ ነገር በማንኛውም እኳኋን የመንፈስ ቅዱስን ሥራ የሚጨምር መሆኑና ያለ እርሱ የጥምቀቱ ሥርዓት ትርጉም የለሽ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። ቆላስይስ 2፡12 ውስጥ ተመሣሣይ ምንባብ አለ። በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አማካይነት ከክርስቶስ ጋር መመሳሰላችን፥ እግዚአብሔር ሰጊዜ ውስጥና ሰዘላለም ለአማኙ ለሚያደርገው ሁሉ ዋና መሠረት ነው።  አንድ እማኝ ክርስቶስ ውስጥ ከመሆኑ የተነሣ፥ አካል የሆነችው ቤተ ክርስቲያን ራሷ ከሆነው ክርስቶስ የምትጋራው ሕይወት ተካፋይ ነው። ክርስቶስ ራሷ ከሆነው ቤተ ክርስቲያን ጋር ያለው ግንኙነት፥ ልክ ሰብአዊ አእምሮ አካልን እንደሚመራ፥ እርሱም ልዑላዊ በሆነ መንገድ መምራቱ ነው።  ረ. የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ከመንፈሳዊ ልምምድ ጋር ሲዛመድ  ማንኛውም ክርስቲያን ድነትን ባገኘ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ተጠምቋል ከሚለው እውነት የምንረዳው ነገር፥ ጥምቀት በእምነት ልንቀበለው የሚገሳ የእግዚአብሔር ሥራ መሆኑን ነው። ምንም እንኳን የኋላ መንፈሳዊ ልምምድ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን የሚያረጋግጥ ቢሆን፥ ጥምቀት በራሱ ልምምድ አይደለም። ጥምቀት ለሁሉም አማኝ የሚሆንና በክርስቶስ ካለን ሥፍራ ጋር የሚዛመድ ስለሆነ፥ በቅጽበት የሚከናወን የእግዚአብሔር ሥራ እንጂ፥ ከዳግም ልደት በኋላ ይመጣል ተብሎ የሚጠበቅ አይደለም።  ብዙ ስሕተት የሚፈጠረው፥ ክርስቲያኖች በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን የልሳን በመናገር የተገለጠውን ዓይነት የመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ ሊፈልጉ ይገባል ከሚለው አመለካከት ነው። ሐዋርያት ሥራ ውስጥ በሦስት ሁኔታዎች (ምዕራፎች 2፥ 10 እና 19) ክርስቲያኖች በመንፈስ ቅዱስ ሲጠመቁ በልሣን መናገራቸው ተገልጧል።

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፡- የማጥመቅ ተግባሩ Read More »

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፡- በሰው ውስጥ ማደሩና ማተሙ

This entry is part 17 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ሀ. የአሁኑ ዘመን አዲስ ገጽታው  በብሉይ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ ከሰዎች ጋር የኖረና የአዲስ ሕይወታቸው ምንጭ፥ የመንፈሳዊ ድላቸው መገኛ የነበረ ቢሆንም፥ የዚያን ጊዜ አማኞች ሁሉ መንፈስ ቅዱስ በውስጣቸው ያደረ መሆኑን የሚገልጥ ማረጋገጫ የለም። ይህን አስተምህሮ በተመለከተ ብሉይ ኪዳን የሚጠቅሰው ነገር የለም። ኢየሱስ ክርስቶስም በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበረውን ሁኔታ ሰአሁኑ ዘመን ካለው ጋር በማነጻጸር የተለያ ትምህርቱን ሲጠቅስ “ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውስጣችሁም ስለሚሆን” ብሏል (ዮሐ. 14፡17)። መንፈስ ቅዱስ በእያንዳንዱ አማኝ ውስጥ የማደሩ ጉዳይ የዚህ ዘመን ልዩ ገጽታ ሲሆን፥ በሺህ ዓመት መንግሥት ዘመንም የሚሆን ነው። በሌላ በማንኛውም ጊዜ አይገኝም።  ለ. የመንፈስ ቅዱስ በአማኞች ሁሉ ውስጥ ማደር  ክርስቲያኖች በመንፈሳዊ ኃይልና የመንፈስን ፍሬ በማፍራት ረገድ በጣም የሚለያዩ ቢሆንም፥ እያንዳንዱ ክርስቲያን ከጰንጠቆስጤ ዕለት ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ እንደሚያድርሰት መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል። መንፈስ ቅዱስ በሰው ውስጥ ሳያድር የመዘግየቱ ሁኔታ ምሳሌ ሐዋርያት ሥራ ውስጥ ታይቷል (8፡14-17፤ 19፡1-6)። እነዚህ ሁኔታዎች ችካካል ከሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የሽግግር ባሕርይ የተነሣ የተፈጠሩ ናቸው። መንፈስ ቅዱስ ሰዎች ውስጥ የማደሩ እውነት፥ የመጽሐፍ ቅዱስን ሥልጣን የሚቀበል ሰው ጥያቄ በማይሆንበት ሁኔታ በብዙ ስፍራ ተጠቅሷል (ዮሐ. 7፡37-39፤ ሐዋ. 11፡17፤ ሮሜ 5፡5፤ 8፡9፥ 11፤ 1ኛ ቆሮ. 2፡12፤ 6፡19-20፤ 12፡13፤ 2ኛ ቆሮ. 5፡5፤ ገላ. 3፡2፤ 4፡6፤ 1ኛ ዮሐ. 3፡24፤ 4፡13)። እነዚህ ጥቅሶች ከጳንጤቆስጤ ዕለት በፊት፥ ማለት በብሉይ ኪዳን አሠራር፥ መንፈስ ቅዱስ በጥቂት ሰዎች ብቻ ያድር የነበረ መሆኑን በግልጥ ያስረዳሉ። ከጰንጠቆስጤ ዕለት በኋላ ግን ትክክለኛው የመንፈስ ቅዱስ አሠራር በአማኝ ውስጥ ማደር ነው።  መንፈስ ቅዱስ በክርስቲያኖች ሁሉ የሚያድር መሆኑ ሮሜ 8፡9 ውስጥ የከርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለምን” ሰሚለው ቃል ተደግፏል። በተመሳሳይ ሁኔታ ይሁዳ 19 ውስጥ እንደተገለጠው፥ የማያምኑ ሰዎች (“መንፈስ የሌላቸው” ተብለዋል። ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጭ የሚኖሩና በቁጣው ሥር ያሉ (የሚቀጡ) ክርስቲያኖች እንኳ አካላቸው የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ነው። 1ኛ ቆሮንቶስ 6፡19 ውስጥ እንደተጠቀሰው፥ ሥጋዊ የሆኑ የቆሮንቶስ ሰዎች አካላቸው የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ስለሆነ፥ እግዚአብሔርን የሚያሳዝን ኃጢአት እንዳይፈጽሙ አስጠንቅቋቸዋል።  መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ስጦታ እንደሆነም በተደጋጋሚ ተገልጿል። የስጦታ መሠረታዊ እውነት ከተቀባዩ ምንም አጻፋ አለመፈለጉ ነው (ዮሐ. 7፡37-39፤ ሐዋ, 11፡17፤ ሮሜ 5፡5፤ 1ኛ ቆሮ. 2፡12፤ 2ኛ ቆሮ. 5፡5)። በተመሳሳይ ሁኔታ ከጌታ ጋር ለመጓዝ የሚሹ ክርስቲያኖች ለሚጠበቅባቸው የሕይወት ከፍተኛው ደረጃ፥ አስፈላጊውን መለኮታዊ ችሉታ ይሰጣቸው ዘንድ መንፈስ ቅዱስ በውስጣቸው ማደሩ ተገቢ ነው። ካህናትና ነገሥታት ተቀብተው ለተቀደሰ ሥራ እንደሚለዩ፥ ክርስቲያንም ድነቱን በሚቀበል ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ይቀባና በውስጡ በሚኖረው መንፈስ ቅዱስ አማካይነት ወደ ፊት ከክርስቶስ ጋር ለሚኖረው አዲስ ሕይወት ይለያል (2ኛ ቆሮ. 1፡21፤ 1ኛ ዮሐ. 2፡20፥ 27)። መቀባት ድነትን በመቀበያ ጊዜ የሚከናወንና ለሁሉም አማኝ የሚሰጥ ሲሆን፥ መንፈስ ቅዱስ በአማኙ ውስጥ የማደሩ እውነት ከሚያሳየው አስተምህሮም ጋር ይመሳሰላል። አንድ አማኝ ከዳነ በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ይቀባል፥ ይህም የጸጋ ሁለተኛ ክፍል ነው፥ ወይም ከመንፈስ ቅዱስ ሙላት በኋላ ብቻ የሚከናወን ነው የሚለው ትምህርት መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም።  ሐ. መንፈስ ቅዱስ በአማኙ ውስጥ ስለ ማደሩ በሚሰጠው አስተምህሮ ውስጥ የሚታዩ ችግሮች  መንፈስ ቅዱስ በእያንዳንዱ አማኝ ውስጥ የማደሩ እውነት፥ ከአንዳንድ አከራካሪ ጥቅሶች የተነሣ አጠያያቂ ይሆናል። በብሉይ ኪዳንና በወንጌል ውስጥ ባሉ ሦስት ጥቅሶች (1ኛ ሳሙ. 16፡14፤ መዝ. 51፡11፤ ሉቃስ 11፡13) መሠረትነት አንዳንድ ሰዎች መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ሰው በአንዳንድ ሁኔታዎች የእግዚአብሔርን መንፈስ ያጣል ብለው አምነዋል። ዳዊት በሳዖል እንደተደረገበት ሁሉ (1ኛ ሳሙ. 16፡14) ከእርሱም የእግዚአብሔር መንፈስ እንዳይወሰድበት የጸለየው ጸሎት (መዝ. 51፡11)፥ በብሉይ ኪዳን እሠራር ላይ የተመሠረተ ነው። በዚያ ወቅት መንፈስ ቅዱስ በሁሉም ውስጥ ማደሩ የተለመደ አልነበረም። በመሆኑም በጌታ ሉዓላዊነት የተሰጠ መንፈስ በዚሁ ሉዓላዊነት ሊወሰድ ይችል ነበር።  ሐዋርያት ሥራ ውስጥ ያሉ ሦስት ጥቅሶችም መንፈስ ቅዱስ በሁሉም ሰው ማደሩን አስመልክቶ የሚከሰትን አንድ ችግር የሚጠቁሙ ይመስላሉ። (1) ሐዋርያት ሥራ 5፡32 ውስጥ መንፈስ ቅዱስ “እግዚአብሔር ለሚታዘዙት የሰጠው” ተብሏል። እዚህ ላይ መታዘዝ የተባለው ለወንጌል መታዘዝ ነው፥ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚመለከተው በከፊል በማይታዘዙት እንኳን መንፈስ ቅዱስ ያድርባቸዋል። (2) ሰማርያ ውስጥ ፊሊጶስ ወንጌል የሰበከላቸው ሰዎች መንፈስ ቅዱስ ሳይቀበሉ የመዘግየታቸው ምክንያት፥ ይህን አዲስ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ኢየሩሳሌም ከነበሩ ሐዋርያት ተግባር ጋር ለማያያዝ ታስቦ ነበር። ለዚህ ነበር ሐዋርያቱ መጥተው እጃቸውን እስኪጭኑባቸው ድረስ ሰዎቹ በመንፈስ ቅዱስ ያልተሞሉት (ሐዋ. 8፡17)። ይህ ከቆርነሌዎስ መዳን ሁኔታ ጋር ሲነጻጸር በተለመደው መንገድ የሆነ አልነበረም። እርሱ መንፈስ ቅዱስን የተቀበለው እጅ ሳይጫንበት ነው። (3) ሐዋርያት ሥራ 19፡1-6 ውስጥ የተወቀሰው ሁኔታ በመጥምቁ ዮሐንስ ስብከት እንጂ፥ ፈጽሞ በኢየሱስ ያሳመኑትን ሰዎች የሚመለከት ነው የሚመስለው። ሰዎቹ ጳውሎስ እጅ በጫነባቸው ጊዜ ነው መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉት።  ይህ ሁኔታም ያልተለመደና ከዚያ ወዲህ ያልተደገመ ነው። 1ኛ ዮሐንስ 2:20 ውስጥ ቅዱሱ ቅባት” የተባለውና 1ኛ ዮሐንስ 2፡27 ውስጥ የተጠቀሰው ቃል በትክክል ከተተረጎመ። መንፈስ ቅዱስ አማኙ ውስጥ መጀመሪያ ከማደሩ ጋር እንጂ፥ በኋላ ከሚሆን የመንፈስ ቅዱስ አሠራርጋር የሚዛመድ አይደለም።  አዲስ ኪዳን ውስጥ የተጠቀሰው ማንኛውም የመንፈስ ቅዱስ መቀባት፥ ከጰንጠቆስጤ ዕለት በኋላም ሆነ በፊት፥ ሰው በጌታ እንዳመነ የሚሆን የመጀመሪያ ጊዜ ክንውን ነው (ሉቃስ 4፡18፤ ሐዋ. 4፡27፤ 10፡38፤ 2ኛ ቆሮ. 1፡21፤ 1ኛ ዮሐ. 2፡20፡27)። ስለዚህ ይህን አስተምህሮ የተመለከቱ ችግሮች የሚወገዱት። ችግሮቹ የሚነሡባቸውን ጥቅሶች በጥንቃቄ በማጥናት ነው።  መ. የመንፈስ ቅዱስ ሰሰው ውስጥ ማደር ከሌሎች አገልግሎቶች ጋር ሲነጻጸር  አንድ አማኝ አዲስ ልደት በሚያገኝበት ወቅት አንዳንድ የመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች ወዲያውኑ በሕይወቱ ስለሚከናወኑ፥ እነዚህን የተለያዩ ክንውኖች በጥንቃቄ መለየት ይገባል። ሁለቱም በአንድ ጊዜ የሚከናወኑ ቢሆኑም፥ የመንፈስ ቅዱስ በአማኙ ውስጥ ማደርና በመንፈስ ቅዱስ ዳግም መወለድ አንድ አይደሉም። በተመሳሳይ ሁኔታ ዳግም ልደትና የመንፈስ ቅዱስ በአማኙ ውስጥ ማደር በመንፈስ ቅዱስ ከመጠመቅ ጋር አንድ አይደሉም። በመንፈስ ቅዱስ የመጠመቁ ጉዳይ ወደፊት የምንገልጠው ይሆናል። የመንፈስ ቅዱስ በሰው ውስጥ ማደር በመንፈስ ቅዱስ ከመሞላት ይለያል። ይህም ልዩነት ክርስቲያኖች ሁሉ መንፈስ ቅዱስ ሊያድርባቸው ሲችል፥ በመንፈስ ቅዱስ የሚሞሉት ሁሉም አለመሆናቸው ነው። የመንፈስ ቅዱስ በአንድ ሰው ውስጥ ማደር ለአንዴና ለዘላለም የሚከናወን ሲሆን፥ በመንፈስ ቅዱስ መሞላት ግን ብዙ ጊዜ በክርስቲያን ልምምድ የሚፈጸም ነው። የመንፈስ ቅዱስ በአንድ ሰው ማደር ግን፥ በመንፈስ ቅዱስ ከመቀባትና ከመታተም ጋር ተመሳሳይ ነው።  የመንፈስ ቅዱስ በሰው ውስጥ ማደር ወይም መቀባት የዚህ ዘመን ክንውን ነው (ዮሐ. 14፡17፤ ሮሜ 7፡6፤ 8፡9፤ 1ኛ ቆሮ. 6፡19-20፤ 2ኛ ቆሮ. 1፡21፤ 3፡6፤ 1ኛ ዮሐ. 2፡20፥27)። መንፈስ ቅዱስ በውስጡ ከማደሩ የተነሣ አማኝ ይቀደሳል፥ ወይም ለእግዚአብሔር ይለያል። በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበረው የቅባት ዘይት በአሁኑ ዘመን ያለው በመንፈስ ቅዱስ የመቀባት ምሳሌ ነው። ዘይት ከሰባቱ የመንፈስ ምሳሌዎች አንዱ ነው።  1. በዘይት የተቀባ ነገር ሁሉ ወዲያውኑ የተቀደሰ ይሆናል (ዘፀ. 40፡9-15)። በተመሳሳይ ሁኔታ በዚህ ዘመንም መንፈስ ቅዱስ ሰውን ይቀድሳል (ሮሜ 15፡16፤ 1ኛ ቆሮ. 6፡11፤ 2ኛ ተሰ. 2:13፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡2)።  2. ነቢዩ በዘይት ተቀድሶ ነበር (1ኛ ነገ, 9፡16)። እንዲሁም ክርስቶስ በመንፈስ ነቢይ ነው (ኢሳ. 61፡1፤ ሉቃስ 4፡18)። አማኝም በመንፈስ ምስክር ነው(ሐዋ. 1፡8)።  3. ካህን በዘይት ይቀደስ ነበር(ዘፀ. 40፡15)፤ ክርስቶስም እንዲሁ በመሥዋዕቱ በመንፈስ ተቀድሷል (ዕብ. 9፡14)። እማኝም በመንፈስ ይቀደሳል (ሮሜ 8፡26፤ 12፡1፤ ኤፌ. 5፡18-20)።  4. ንጉሡ ዘይት ተቀድሷል (1ኛ ሳሙ. 16፡12-13)። ክርስቶስም እንዲሁ በመንፈስ (መዝ. 45፡7) እና አማኝም በመንፈስ ይነግሣል።  5. በዘይት መቀባት ለፈውስ ነበር (ሉቃስ 10፡34)፤ ይህም በመንፈስ ቅዱስ በሚገኝ ድነት አማካይነት የነፍስ ፈውስ የሚገኝ መሆኑን ያመለክታል።  6. ዘይቱ ፊት እንዲያበራ ያደርጋል፤ እንደ ደስታ ዘይት ነው (መዝ. 45፡7)፤ ለዚህም ንጹሕ

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፡- በሰው ውስጥ ማደሩና ማተሙ Read More »

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፡- የዳግም ልደት ሥራ

This entry is part 16 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

የክርስትና እምነት ሕይወት ከዳግም ልደት የሚጀምር ስለሆነ፥ ከድኅነት ጋር በተዛመደ መልኩ ሲታይ ዳግም ልደት መሠረታዊ ከሆኑት አስተምህሮዎች አንዱ ነው። ስለዚህ ስለ መንፈስ ቅዱስ ሥራ ተገቢ መረዳትና ከአጠቃላዩ የክርስትና ሕይወት ጋር ያለውን ድንቅ ግንኙነት መገንዘቡ፥ ውጤት ላለው የወንጌል ሥራና ለመንፈሳዊ ብስለት ጠቃሚ ነው።  ሀ. የዳግም ልደት ትርጉም  “ዳግም ልደት” የሚለው ቃል ጽንሰ አሳብ አዲስ ሕይወት፥ አዲስ ልደት፥ መንፈሳዊ ትንሣኤ፥ አዲስ ፍጡር፥ ባጠቃላይ አማኞች እንደ እግዚአብሔር ልጅነታቸው የሚያገኙትን ከሁሉ የላቀ ወይም ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ሕይወትን ለመግለጫነት በሥነ-መለኮት ሰዎች የተመረጠ ነው። ይህ ቃል በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ብዙ ጊዜ ትክክለኛ ትርጉሙን አላገኘም። ትክክለኛ ግንዛቤ ቢያገኝ ግን ትርጉሙ እንድ ሰው በክርስቶስ ባመነ ጊዜ ወደ ዘላለም ሕይወት፥ ማለት በቅጽበት ከመንፈሳዊ ሞት ወደ መንፈሳዊ ሕይወት ተሸጋገረ ማለት ነው።  ለ. በመንፈስ ቅዱስ ዳግም መወለድ  ዳግም ልደት ከመሠረቱ የእግዚአብሔር ሥራ የመሆኑ እውነት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ቦታ ላይ ተጠቅሷል (ዮሐ. 1፡13፤ 3፡3-7፤ 5፡21፤ ሮሜ 6፡13፤ 2ኛ ቆሮ. 5፡17፤ ኤፌ. 2፡5፥ 10፤ 4፡24፤ ቲቶ 3፡5፤ ያዕ. 1፡18፤ 1ኛ ጴጥ. 2፡9)። በዮሐንስ 1፡13 መሠረት ዳግም ልደት ያገኘ ሰው፥ ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።”። ዳግም ልደት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ቦታ ላይ ከመንፈሳዊ ትንሣኤ ጋር ተነጻጽሯል (ዮሐ. 5፡21፤ ሮሜ 6፡13፤ ኤፌ. 2፡5)። የእግዚአብሔር የመፍጠር ሥራም ስለሆነ ከተፈጥሮ ጋር ተነጻጽሯል (2ኛ ቆሮ. 5፡17፤ ኤፌ. 2፡10፤ 4፡24)።  ለአማኝ ዳግም ልደትን በመስጠቱ ተግባር ሦስቱም የሥላሴ አካላት ይሳተፋሉ። ያዕቆብ 1፡17-18 ውስጥ አብ ከዳግም ልደት ተግባር ጋር ተዛምዷል። ኢየሱስም በዚህ ተግባር መሣተፉ በተደጋጋሚ ተገልጧል (ዮሐ. 5፡21፤ 2ኛ ቆሮ. 5፡18፤ 1ኛ ዮሐ. 5፡12)። ይሁን እንጂ ሦስቱም አካላት የተሣተፉባቸው ሌሎች የእግዚአብሔር ሥራዎች ቢኖሩም፥ በዮሐንስ 3፡3-7 እና ቲቶ 3፡5 ውስጥ መንፈስ ቅዱስ እንደ ዳግም ልደት ሰጭ ሆኖ ተገልጧል። መንፈስ ቅዱስ በዳግም ልደት ውስጥ ባለው ተግባር መሠረት በክርስቶስ መጸነስ ሁኔታ ተሳትፏል። በክርስቶስ ልደት እግዚአብሔር አብ የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ሲሆን፥ የወልድ ሕይወት በክርስቶስ ሆኖ በመንፈስ ቅዱስ ተፀነሠ።  ሐ. በዳግም ልደት የተገኘ የዘላለም ሕይወት  የዳግም ልደት ዋና አሳብ፥ በመንፈስ ሞቶ የነበረ አማኝ አሁን የዘላለም ሕይወት ማግኘቱ ነው። ይህን አሳብ ለማገናዘብ ሦስት መግለጫዎች ተጠቅሰዋል። አንዱ ዳግም የመወለድ አሳብ ነው። ክርስቶስ ከኒቆዲሞስ ጋር በሚነጋገርበት ጊዜ “ዳግም ልትወለድ ይገባል” ወይም አንዳንዴ እንደሚተረጎመው “ከላይ ልትወሰድ ይገባል” ብሎታል። ዮሐንስ 1፡13 ውስጥ እንደተጠቀሰው ዳግም ልደት ከሰብዓዊ ልደት ጋር በመነጻጸር ተገልጧል። ሁለተኛውና መንፈሳዊ ትንሣኤን የሚመለከተው እሳብ፥ በክርስቶስ ያመነ ሰው ከሙታን ተለይቶ በሕይወት እንደሚኖር…” (ሮሜ 6፡13) ያስረዳል። ኤፌሶን 2፡5 ውስጥ በበደላችን ሙታን እንኳን በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን” ይላል። ቀጥታ አባባሉ “ከክርስቶስ ጋር ሕያው አደረገን” ማለት ነው። ሦስተኛው አሳብ አዲስ ፍጥረትን የሚያመለክት ሲሆን፥ አማኞች “ለእውነትም በሚሆን ጽድቅና ቅድስና በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ” (ኤፌ. 4፡24) ተብለዋል። 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡17 ውስጥ አሳቡ ይበልጥ ግልጥ ተደርጓል። “ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፥ አሮጌው ነገር አልፎአል፥ እነሆ ሁሉም አዲስ ሆኖአል”። ከላይ የተጠቀሱት ሦስት ምሳሌዎች በክርስቶስ በማመን ስለሚገኘው አዲስ ሕይወት ነው የሚናገሩት።  ከአዲስ ልደት፥ ከመንፈሳዊ ትንሣኤና መፈጠር ሁኔታ በግልጥ የምንረዳው ነገር፥ ዳግም መወሰድ በማንኛውም ሰው መልካም ሥራ የማይገኝ መሆኑን ነው። የሰው በጎ ፈቃድ ሥራ ወይም የማንኛውም የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት አይደለም። ማለትም እንደ ጥምቀት የመሳሰሉ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓቶች ውጤትም አይደለም። ሙሉ ለሙሉ እግዚአብሔር ለሰው እምነት የሚመልሰው ፍጹም መለኮታዊ አጸፋ ነው።  በመሆኑም ዳግም ልደት ቀጥሎ ካሉት ልምምዶች ሊለይ ይገባል። ዳግም ልደት ቅጽበታዊ ክንውንና ከድኅነት የማይለይ ነው። በትክክለኛው መንገድ ድኅነትን ያገኘ ሰው ተከታታይ መንፈሳዊ ልምምድ ይኖረዋል። ይህ ልምምድ ግን የዳግም ልደት ማረጋገጫ እንጂ ራሱ ዳግም ልደት አይደለም። ለነገሩ አዲሱን ልደት በመለማመድ ላይ ነን በማለት ለመናገር እንችላለን፤ የዚህ አባባላችን ትክክለኛ ትርጉም ግን የአዲስ ልደትን ውጤቶች በመለማመድ ላይ መሆናችንን ነው የሚያመላክተው።  መ. የዳግም ልደት ውጤት  ዳግም ልደት በብዙ ሁኔታው ድኅነታችን የተገነባበት መሠረት ነው። በክርስቶስ የሆነ አዲስ ሕይወት ካልተገኘ፥ መንፈስ ቅዱስን፥ ጽድቅን ወይም ሌሎች ተከታታይ ውጤቶችን የማግኛ መንገድ የለም። በዳግም ልደት ወዲያውኑ እውን የሚሆኑ አንዳንድ ነገሮች ግን አሉ።  አንድ እማኝ ክርስቶስን በእምነት ሲቀበል፥ አዲስ ልደትን ያገኛል፤ በዚያም አማካይነት አዲስ ፍጡር ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ “እዲሱ ሰው” (ኤፌ. 4:24) የሚለው ይህን ነው። አዲሱ ሰው፥ ለአዲሱ እኛነታችን ይጠቅመን ዘንድ “እንድንለብሰው> የተነገረን ነው። በክርስቶስ የሚያምን እንድ እማኝ ከሚኖረው አዲስ ባሕርይ የተነሣ ድንቅ የሆነ ለውጥ በሕይወቱ ይሆናል። ይህን ለውጥ ያገኘ አማኝ ስለ እግዚአብሔር ያለው እመለካካትና፥ ኃጢአትን ላለማድረግ ያለው ጽናት ከቀድሞው የተለየና የበረታ ነው። ዳግም የተወለደ ሰው አዲስ ተፈጥሮ በእግዚአብሔር ባሕርይ አምሳል የተለወጠ ሲሆን፥ ይህ ተፈጥሮ አዳም ከመውደቁ በፊት ከነበረው ተፈጥሮ ለየት ያለ ነው። አዲሱ ተፈጥሮ መለኮታዊ ባሕርይ ዕላላው የእግዚአብሔር የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ይሻል። ያለመንፈስ ቅዱስ እርዳታ የራሱን ፍላጎት ለመፈጸም ኃይል ባይኖረውም፥ ለሕይወት እዲስ አቅጣጫን፥ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈጸም ደግሞ አዲስ ምኞትን ይሰጣል።  ዳግም ልደት የሂደት ልምምድ ሳይሆን ቅጽበታዊ ነው። ቢሆንም ዳግም የተወለደ ሰው የሚቀበለው አዲስ ሕይወት አንዳንድ ልምምድን ለመለማመድ የሚረዳ ብርታትን ይሰጠዋል። አዲሱ አማኝ ቀድሞ ዐይነ ሥውር ነበር። አሁን ግን ያያል። ቀድሞ ሙት ነበር፥ አሁን ግን ለመንፈሳዊ ነገሮች ሕያው ነው። ቀድሞ ከእግዚአብሔር የተለየና አንድነት የሌለው ነበር። አሁን ግን የአንድነት መሠረት ስላለው የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ያገኛል። አማኝ ራሱን ለጌታ በሰጠ መጠን የጌታን ድንቅ ስጦታዎች ይላማመዳል። ይህ ልምምድ ጌታ በአንድ ራሱን የሰጠ ሰው ሕይወት የሚያደርገው ድንቅና ሉዓላዊ ሥራ መግለጫ ነው።  የዘላለም ሕይወት የማግኘቱ ሌላ ጠቃሚ ነገር፥ የዘላለም ዋስትና መሠረትነቱ ነው። አንዳንዶች፥ ሰው ከእምነቱ ቢያፈነግጥ ድኅነቱንና የዘላለም ሕይወትን ያጣል ብለው ቢያስተምሩም፥ የዘላለም ሕይወትና የአዲስ ልደት ባሕርይ ራሱ ይህን የእግዚአብሔርን ሥራ የመሻር ሁኔታ ይከለክላል። ድኅነት በመጀመሪያ የሰው ሳይሆን የእግዚአብሔር ሥራ ነው፤ በሰው ሥራ ብቁዕነት የሚገኝም አይደለም። እምነት አስፈላጊ ቢሆንም ድኅነት የሚያስገኝ መልካም ሥራ ሆኖ ሊቆጠር አይገባም። እምነት እግዚአብሔር በአማኙ ሕይወት እንዲሠራ በር ይከፍታል። ተፈጥሯዊ ልደት ወደነበረበት እንደማይመለስ፥ መንፈሳዊ ልደትም እንዲሁ ነው። አንዴ ከተከናወነ እግዚአብሔር ሁልጊዜ ሰማያዊ አባቱ እንደሆነ ለአማኙ ያረጋግጥለታል።  የትንሣኤ ክንውን ወደነበረበት አይመለስም። በተመሳሳይ ሁኔታም በእግዚአብሔር አሠራር ወደ አዲስ ሕይወት ስለተሸጋገርን ይህን ሕይወት መቀየር አይቻልም። አዲስ ልደት ልክ እንደ ፍጥረት አሠራር አንዴ ከተከናወነ ለዘላለም የሚቀጥል መሆኑ ሌላው ማረጋገጫ ነው። ሰው ከተፈጠረ በኋላ ራሱን ወዳልተፈጠረበት ሁኔታ መመለስ እይችልም። እንዲሁም የዘላለም ዋስትና አስተምህሮ በሚከተሉት ትምህርት ጥያቄዎች ላይ የተመሠረተ ነው፡- ድኅነት የእግዚአብሔር ወይስ የሰው ሥራ፥ ሙሉ በሙሉ በጸጋ ላይ ወይስ በሰው ሥራ ላይ የተመሠረተ ነው? ምንም እንኳን በክርስቶስ አዲስ የሆነ ሰው እንደ እግዚአብሔር ልጅነቱ መሆን እንደሚገባው ሊሆን ባይችል፥ ልክ በሰብዓዊ ቤተሰብ የአንድ ሰው ልጅ ባደረገው ጥፋት ልጅነቱ እንደማይሻር፥ እማኝም ያገኘውን የዘላለም ሕይወት አያጣም። አሁን ያለን የዘላለም ሕይወት በመንፈሳዊ ልምምድ የተገለጠው በከፊል ብቻ መሆኑም እውነት ነው። የዘላለም ሕይወት ደስታ ፍጹም የሚሆነው፥ እግዚአብሔር ባለበት በሰማይ ነው። ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፡- የዳግም ልደት ሥራ Read More »

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፡- መውረዱ

This entry is part 15 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

የመንፈስ ቅዱስ በጳንጠቆስጤ ዕለት ወደ ዓለም መምጣት መታየት ያለበት ከዚያ ሰፊት በነበሩት ሥፍረዘመናት ከነበረው ሥራ ጋር በተያያዘ መልኩ ነው። መንፈስ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን ዘመን በሁሉም ስፍራ የሚገኝ አምላካዊ ባሕርይ ሆኖ በዓለም ነበር። ቢሆንም ሰጰንጠቆስጤ ዕለት ወደ ዓለም የሚመጣ መሆኑ ተነግሯል። በዘመናችንም በዓለም ይኖራል። አንድ ቀን ግን ልክ እንደ ጰንጠቆስጤ ዕለት አመጣጡ ከዓለም ይለያል። ይህ የሚሆነው በቤተ ክርስቲያን መነጠቅ ጊዜ ነው። ይህን ስለ መንፈስ ቅዱስ የሚነገር እውነት ለመረዳት ይቻል ዘንድ፥ መንፈስ ቅዱስ ከዓለም ጋር ያለው ግንኙነት የተለያዩ ሁኔታዎች ሊታዩ ይገባል።  ሀ, መንፈስ ቅዱስ ሰብሉይ ኪዳን  ከክርስቶስ ልደት በፊት በነበረው ረጅም ዘመን መንፈስ ቅዱስ በሁሉም ስፍራ መገኘት በሆነው ሳሕርዩ በዓለም ነበር። በመለኮታዊ ፈቃዱ መሠረትም በእግዚአብሔር ሰዎች ውስጥና አማካይነት ሠርቷል (ዘፍጥ. 41፡38፤ ዘጸ. 31፡3፤ 35፡31፤ ዘኁል. 27፡18፤ ኢዮብ 33፡4፤ መዝ. 139፡7፤ ሐጌ 2፡4-5፤ ዘካ. 4፡6)። በብሉይ ኪዳን ዓለም ሲፈጠር የእግዚአብሔር መንፈስ አብሮ ፈጥሯል። ለቅዱሳንና ለነቢያት የመለኮታዊውን እውነት የመግለጥ ድርሻ ነበረው። ለተጻፉ የእግዚአብሔር ቃላት ምሪትን ሰጥቷል፥ ኃጢአትን ከዓለም በመከልከል አገልግሏል፥ አማኞች ለአገልግሎትና ታአምራትን ለመሥራት አስችሏቸዋል። እነዚህ ሁሉ ክንውኖች የሚያመላክቱት መንፈስ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን ዘመን በጣም ይሠራ የነበረ መሆኑን ነው። ይሁን እንጂ በዚያ ዘመን በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ ስለማደሩ ምንም ማስረጃ የለም። የዮሐንስ ወንጌል 14፡17 የሚያመለክተው፥ “ከእነርሱ” በማለት ከሰዎች ጋር እንደነበር እንጂ፥ በ“ውስጣቸው” እንደነበር አይደለም። ካጰንጠቆስጤ ዕለት በፊት የመንፈስ ቅዱስ የማተም ወይም የማጥመቅ ሥራ አልተጠቀሰም። ካለፉት ዘመናት፥ ከጰንጠቆስጤ ዕለት በኋላ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ የሳቀ ነው።  ለ. መንፈስ ቅዱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በነበረበት ዘመን  ሥጋ የለበሰና የሚሠራ፥ የሥላሴ ሁለተኛ አካል በዓለም መገኘቱ፥ የመንፈስ ቅዱስን ሥራ ለየት የሚያደርገው መሆኑን መገመት ተገቢ ነው። እውነት ሆኖም እናገኘዋለን።  1. ከክርስቶስ በተገናኘ ሁኔታ ሲታይ፥ እግዚአብሔር ሰው ሆኖ ለድንግሊቱ ማኅፀን ውስጥ የተፀነሰበትን ኃይል ያመነጨው መንፈስ ቅዱስ ነበር። ክርስቶስ በሚጠመቅበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በእርግብ አምሳል ሲወርድበት ታይቷል። ክርስቶስ ራሱን ለእግዚአብሔር የሰጠው በዘላለማዊ መንፈስ ብቻ መሆኑም ተገልጧል (ዕብ. 9፡14)።  2. ክርስቶስ ምድራዊ አገልግሎት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ከሰው ጋር የነበረው ግንኙነት እየሰፋ የሚመጣ ነበር። ክርስቶስ፥ ቢጠይቁ መንፈስ ቅዱስን ሊቀበሉ እንደሚችሉ ለደቀ መዛሙርቱ መጀመሪያ አረጋገጠላቸው (ሉቃስ 11፡13)። ምንም እንኳን ቀደም ሲል መንፈስ ቅዱስ እንደ ልዑል እግዚአብሔር ፈቃድ በሰዎች ላይ ቢወርድም፥ በሰዎች ልብ የመኖሩ ነገር ግን በሰዎች ጥያቄ የሚከናወን አልነበረም። የእግዚአብሔር ቃል እንደሚያስረዳውም ይህን መብት ጌታ ከመናገሩ በፊት ማንም አልተጠቀመበትም። ክርስቶስ በአገልግሎቱ መጨረሻና በሞቱ ዋዜማ እንዲህ ብሏል “እኔም አብን እለምናለሁ፥ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፥ እርሱም የእውነት መንፈስ ነው” (ዮሐ. 14፡16-17)። በተመሳሳይ ሁኔታ ከትንሣኤው በኋላ ተነፈሰባቸውና “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ” አላቸው (ዮሐ. 20፡22)። ይሁን እንጂ ለጊዜው መንፈስ ቅዱስን ቢቀበሉም፥ ከላይ በሚወርድ ኃይል እስኪሞሉ ድረስ ኢየሩሳሌም ውስጥ መቆየት ነበረባቸው (ሉቃስ 24፡49፤ ሐዋ. 1፡4)።  ሐ. በጰንጠቆስጤ ዕለት የመንፈስ ቅዱስ መውረድ  በአብ (ዮሐ. 14፡16-17፥ 26) እና በወልድ (ዮሐ. 16፡7) በተሰጠው ተስፋ መሠረት፥ በሁሉም ሥፍራ በመገኘት ባሕርይው ሁልጊዜ በዓለም የነበረው መንፈስ ቅዱስ በጳንጠቆስጤ ዕለት ወደ ዓለም መጣ። የዚህ የተደጋጋመ የሚመስል አሳብ ኃይል ገሀድ የሆነው፥ መንፈስ ቅዱስ በጰንጠቆስጤ ዕለት የመጣው በሰው ልብ ለማደር መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ ነው። እግዚአብሔር አብ፥ ምንም እንኳን በሁሉም ሥፍራ ያለ (ኤፌ. 4፡6) ቢሆን፥ በሰማያት የምትኖር አባታችን” በሚለው መሠረት መኖሪያው በሰማያት ነው (ማቴ. 6፡9)። በተመሳሳይ እግዚአብሔር ወልድ፥ በሁሉም ሥፍራ የሚገኝ ቢሆን (ማቴ. 18፡20፤ ቈላ. 1፡27)፥ አሁን መኖሪያው በእግዚአብሔር ቀኝ ነው (ዕብ. 1፡3፤ 10፡12)። መንፈስ ቅዱስም እንዲሁ ምንም እንኳን በሁሉም ሥፍራ የሚገኝ ቢሆን፥ ማደሪያው በምድር ነው። ማደሪያው በምድር ነው የሚባለው ስጳንጠቆስጤ ዕላት አመጣጡ መሠረት ነው። መኖሪያውን ከሰማይ ወደ ምድር ለውጧል። ደቀ መዛሙርቱ እንዲጠባበቁ የተነገራቸው ይህን የመንፈስ ቅዱስ መምጣት ነበር። መንፈስ ቅዱስ ባይመጣ ኑሮ የዚህ አዲስ የጸጋ ዘመን አገልግሎት ሊጀመር አይችልም ነበር።  የአሁኑ ዘመን የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በሚቀጥሉት ምዕራፎች ይቀርባል። ዮሐንስ 16፡7-11 ውስጥ እንደተገለጠው፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ከሁሉ በፊት ዓለምን የማገልገል ተልዕኮ አለው። የመጣው ዓለምን ስለ ኃጢአት፥ ስለ ጽድቅ፥ ስለ ፍርድ ለመውቀስ ነው። አንድን ሰው ክርስቶስን እንዲቀበል በአእምሮ የማዘጋጀት ልዩ ሥራ የመንፈስ ቅዱስ ነው። ሰይጣን የዘጋውን የማያምኑ ሰዎች አእምሮ የማብራት የጸጋ ሥራ በሦስት ታላላቅ አስተምህሮዎች መሠረት ይከናወናል።  1. ያላመነ ሰው፥ በርሱና በድኀነት መካከል የሚገኝኃጢአት ኢየሱስ ክርስቶስን እንደግል አዳኙ አድርጎ አለማመን መሆኑን እንዲገነዘብ ይደረጋል። ጥያቄው የርሱ ብቁ ሆኖ መገኘት፥ ስሜቱ ወይም ሌላ ሁኔታ አይደለም። ያለማመን ኃጢአት ድኅነትን እንዳያገኝ ያደርገዋል (ዮሐ. 3፡18)።  2. ላላመነ ሰው ስለ እግዚአብሔር ጻድቅነት ይነገረዋል። ክርስቶስ በምድር በተመላለሰ ጊዜ የእግዚአብሔር ጽድቅ መግለጫ ነበር፤ እርሱ ሲሄድ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ጽድቅ ለዓለም ይገልጥ ዘንድ ተላከ። እግዚአብሔር ጻድቅ እንደመሆኑ፥ ማንኛውም ሰው ሊያደርገው ከሚችለው በላይ የሆነን የጽድቅን ሥራ ይጠይቃል። ይህ ሁኔታ ምንም ዓይነት የሰው ሥራ ለሰው ልጅ ድኅነት መሠረት የመሆኑን ነገር ውድቅ ያደርገዋል። ከሁሉም ይልቅ በክርስቶስ በማመን የሚገኝ ጽድቅ መኖሩን መንፈስ ቅዱስ ይገልጣል። አንድ ሰው በክርስቶስ በማመኑ፥ በእግዚአብሔር ከኃጢአት ፍርድ ነጻ እና ጻድቅ ይባላል። ይህ የሚሆነው፥ ጻድቅ በሆነው ክርስቶስና በመስቀል ላይ በፈጸመው ሥራ ብቻ በመታመኑ ነው (ሮሜ 1፡16-17፤ 3፡22፤ 4፡5)።  3. የዚህ ዓለም ገዢ ሰይጣን በመስቀል ላይ የተፈረደሰትና የለም ቅጣት የተጣለበት የመሆን እውነት ተገልጧል። ይህ የሚያስገነዝበው፥ የመስቀል ላይ ሥራ የተፈጸመ፥ ፍርድ የተሰጠ፥ ሰይጣን ድል የሆነ እና፥ በክርስቶስ ለሚያምኑ ሁሉ ድኅነት የተዘጋጀላቸው መሆኑን ነው። አንድ ሰው ድኅነት እንዲያገኝ እነዚህን ሁሉ ሙሉ በሙሉ ይረዳ ዘንድ አስፈላጊ አይደለም። መንፈስ ቅዱስ ነው እውነቱን በሙላት ገልጦ በአእምሮ ዝግጅት ክርስቶስን በአካልነቱና በሥራው እንዲቀበል የሚያደርገው።  ባለፉት ዘመናትም፥ በብሉይ ኪዳን እንኳን ሰው ያለመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ሊያምንና ሊድን አለመቻሉን የሚያመለክቱ የተወሰኑ ሁኔታዎች አሉ። በአሁኑ ዘመን ግን፥ ከክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ በኋላ እውነቶቹ ይበልጥ ግልጥ ሆነዋል። መንፈስ ቅዱስ ወደ ዓለም የመምጣቱና የመኖሩ አንዱ ዋና ምክንያት እነዚህን ሁኔታዎች ለማያምኑ ሰዎች ለመግለጥ ነው።  መንፈስ ቅዱስ በጰንጠቆስጤ ዕለት ወደ ዓለም በመምጣት ተልዕኮው በብዙ አዳዲስ መንገዶች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዲከናወን እደረገ። ይህ በሚቀጥሉት ምዕራፎች የምንመለከተው ጉዳይ ይሆናል። መንፈስ ቅዱስ ለሚያምን ሰው ሁሉ አዲስ ልደት የሚሰጥ መሆኑ ተገልጧል (ዮሐ . 3፡3-7፥ 36)። በእያንዳንዱ አማኝ ውስጥ ይኖራል (ዮሐ. 7፡37-39፤ ሐዋ. 11፡15-17፤ ሮሜ 5፡5፤ 8፡9-11፤ 1ኛ ቆሮ. 6፡19-20)። መንፈስ ቅዱስ በአማኝ ውስጥ እንደመኖሩ መጠን ለመዳን ቀን ያትናል (ኤፌ. 4፡30)። እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ልጅ ወደ ክርስቶስ አካልነት የተጠመቀው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ነው (1ኛ ቆሮ. 12፡13)። እነዚህ ሁሉ አገልግሎቶች በዚህ ዘመን ላሉ እውነተኛ አማኞች ሁሉ ይሰጣሉ። ከነዚህ ከአማኙ ድኅነት ጋር የተያየዙት ሥራዎች በተጨማሪ፥ የመንፈስ ቅዱስ ሙላትና በርሱም ምሪት መሥራት ይኖራል። እነዚህ ታላላቅ የመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች በዚህ ዘመን ላለ አማኝ የአገልግሎቶች ሁሉ በር የሚከፍቱለት ለድኅነት ብቻ ሳይሆን፥ አጥጋቢ የክርስትና ሕይወት ለመኖር ቁልፍ በመሆንም ጭምር ነው።  እግዚአብሔር ለዚህ ዘመን ያለው ዓላማ በቤተ ክርስቲያን መነጠቅ ሲያበቃ፥ መንፈስ ቅዱስም ወደ ዓለም የመጣበትን ልዩ ተልዕኮ ያበቃና በጳንጠቆስጤ ዕላት በመጣበት አኳኋን ከዓለም ይወሰዳል። ኢየሱስ ክርስቶስ ሥራውን ለማከናወን ወደ ምድር እንደመጣና ከዚያም ሥራውን አጠናቆ ወደ አባቱ እንደሄደ፡መንፈስ ቅዱስም ለዚህ ዘመን ያለውን ሥራ ይሠራ ዘንድ ከላይ ወረደ። አሁን ሥራውን በማከናወን ላይ ነው፤ በንጥቀት ጊዜ ደግሞ ሥራውን አጠናቆ ይመለሳል። ይሁን እንጂ ልክ እንደ ክርስቶስ፥ መንፈስ ቅዱስም በሁሉም ሥፍራ በመገኘት ሳሕርይው መሠረት፥ ከቤተ ክርስቲያን መነጠቅ በኋላም ከጴንጠቆስጤ በፊት በነበረው አኳኋን ሥራውን ይቀጥላል።  በዚህ መሠረት

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፡- መውረዱ Read More »

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አካልነቱ

This entry is part 14 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

ሀ. የአካልነቱ አስፈላጊነት  መንፈስ ቅዱስን በተመለከተ ሰሚሰጥ ትምህርት ውስጥ እበይት ከሆኑት እውነቶች መካከል በማንነቱ ሳይ ልዩ ትኩረት ሊደረግ ይገባል። ይህ የሚያስፈልግበት ምክንያት በአሁኑ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ የሚሰማውን እንጂ (ዮሐ. 16፡13፤ ሐዋ. 13፡2) ከራሱ ወይም ስለ ራሱ የማይናገር መሆኑና ወደ ዓለም የመጣውም ክርስቶስን ሊያከብር በመሆኑ ነው (ዮሐ. 16፡14)። ከዚህ ጋር ሲነጻጸር አብም ሆነ ወልድ ከራሳቸው እንደሚናገሩ አድርጎ ነው መጽሐፍ ቅዱስ የሚያቀርበው። ይህ ሲሆን አብና ወልድን የሚያቀርባቸው በልዑላዊ ሥልጣንና እኔ በሚለው ተውላጠ ስም ብቻ ሳይሆን፥ እርስ በርሳቸው ቀጥተኛ መስተጋብር፥ ኅብረትና መስማማት እንዳላቸው በማረጋገጥ ነው። ከራሱና ስለ ራሱ አለመናገሩ ስለ መንፈስ ቅዱስ ማንነት ያላን መረዳት ውሱን ያደርገዋል። በዚሁ መሠረት በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የመንፈስ ቅዱስ አካልነት ለብዙ መቶ ዓመታት እንደቀላል ነገር የታየ ጉዳይ ነበር። በ325 ዓ.ም. በኒቅያ የእምነት መግለጫ አብና ወልድ በዝርዝር በተገለጡ ጊዜ ነው መንፈስ ቅዱስም እንደ አካል እውቅና ያገኘው።  በትክክለኛው አስተምህሮ በኋላ እንደተገለጠው፥ መጽሐፍ ቅዱሳዊው እውነት እግዚእብሔር በሦስት አካል ይገለጣል የሚል ነው። ይሄውም አብ፥ ወልድ፥ መንፈስ ቅዱስ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ተቀባይነት አግኝቷል። መንፈስ ቅዱስ እንደ አብና እንደወልድ አካል መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ያስተምራል። ከዚህ የሥላሴ አስተምህሮ ጥናት የምንረዳው፥ ሦስቱ አካላት አንድ አምላክ እንጂ ሦስት አማልክት አለመሆናቸውን ነው።  ለ. ቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የተገለጠው የመንፈስ ቅዱስ አካልነት  1. መንፈስ ቅዱስ አካል ያለው ብቻ ሊሠራ የሚችለውን እንደሚሠራ ተገልጿል።  (ሀ) ዓለምን ይወቅሳል፡- “እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት፥ ስለ ጽድቅም፥ ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሳል” (ዮሐ. 16፡8)።  (ለ) ያስተምራል፡- “እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል” (ዮሐ. 14፡26፤ ህ. 9፡20፤ ዮሐ. 16፡13-15፤ 1ኛ ዮሐ. 2፡27)።  (ሐ) ይናገራል፡- “ልጆችም ስለሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባት ብሉ የሚጮህ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ” (ገላ. 4፡6)።  (መ) ይማልዳል፡- “ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል” (ሮሜ 8፣ 26)።  (ሠ) ይመራል፡- “በመንፈስ ብትመሩ” (ገላ. 5፡18፤ ሐዋ. 8፡29፤ 10፡19፤ 13፡2፤ 16፡6-7፤ 20፡23፤ ሮሜ 8፡14)።  (ረ) ምዕመናንን ለአገልግሎት ይሾማል፡- “መንፈስ ቅዱስ በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ አለ” (ሐዋ. 13፡2፤ 20፡28)።  (ሰ) መንፈስ ቅዱስ ራሱ ለአገልግሎት ይላካል፡(ዮሐ. 15፡26)።  ሸ መንፈስ ቅዱስ ያገለግላል፥ ዳግም ልደትንም ይሰጣል፡- (ዮሐ. 3፡6)፤ ያትማል (ኤፌ. 4፡30)፤ ያጠምቃል (1ኛ ቆሮ. 12፡13)፤ ይሞላል (ኤፌ. 5 ፡18)።  2. እካል እንደመሆኑ መጠን በሌሉች ተጽዕኖ ይነካል።  (ሀ) አብ ወደ ዓለም ይልከዋል (ዮሐ. 14፡16፥ 26)። ወልድም ይልከዋል (ዮሐ. 16፡7)።  (ለ) ሰዎች ያስቆጡታል (ኢሳ. 63፡10)፥ ያሳዝኑታል (ኤፌ. 4፡30)፥ ያጠፉታል (ማዳፈን)፥ (1ኛ ተሰ. 5፡19)፥ ይሰድቡታል (ማቴ. 12፡31)፥ ይዋሹታል (ሐዋ. 5፡3)፥ ያክፋፉታል (ዕብ. 10፡29)፥ ቃል ይናገሩበታል (ማቴ. 12፡32)።  3. መንፈስ ቅዱስን በተመለከተ መጽሐፉ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ አባባሎች ሁሉ አካልነቱን ያመለክታሉ።  (ሀ) “ሌላው አጽናኝ” ተብሏል። ይህም የክርስቶስን ያህል አካልነት ያለው መሆኑን ያመለክታል (ዮሐ. 14፡16-17፥ 26፤ 16፡7፤ 1ኛ ዮሐ. 2፡1-2)።  (ለ) እግዚአብሔር መንፈስ እንደተባለ፥ መንፈስ ቅዱስም እንደአካል በዚሁ ስም ተጠርቷል (ዮሐ. 4፡24)።  (ሐ) ለመንፈስ ቅዱስ መጠሪያነት ያገለገሉ ተውላጠ ስሞች አካልነቱን ያመለክታሉ። በግሪክ “መንፈስ” የሚለው ቃል ጾታ የማይለይ ስም ሲሆን፥ በጾታ ለማይለይ አካል መጥሪያነት ያገለግላል። ይህ ጾታ የማይለይ ተውላጠ ስም በአንዳንድ ሁኔታዎች ተጠቅሷል (ሮሜ 8፡16፥ 26)። ብዙ ጊዜ ግን የተባዕታይ ጾታ ተውላጠ ስም የመንፈስ ቅዱስን አካልነት በሚገልጥ መልኩ አገልግሏል (ዮሐ. 14፡16-17፤ 16፡7-15)።  ሐ. መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር አካል እንደመሆኑ ከአብና ከወልድ ጋር እኩል ነው  1 እግዚአብሔር ተብሎ ይጠራል። ኢሳይያስ 6፡8-9 ውስጥ ያለውን ክፍል ከሐዋርያት ሥራ 28፡25-26፥ ኤርምያስ 31፡31-34ን ከዕብራውያን 10፡15-17 ጋር በማነጻጸር ይህን እውነት ለመረዳት ይቻላል። (2ኛ ቆሮ. 3፡18 እና ሐዋ. 5፡3-4 ውስጥ ይህን ቃል ልብ ይበሉ፡- “መንፈስ ቅዱስን ታታልልና ከመሬቱም ሽያጭ ታስቀር ዘንድ ሰይጣን በልብህ ሰለምን ሞላ? እግዚአብሔር እንጂ ሰውን አልዋሸህም።” ምንም እንኳን መንፈስ ቅዱስን ባታልሉት ላይ እግዚአብሔር ጠበቅ ያለ ፍርዱን ቢያወርድባቸውም (ሐዋ. 5፡3)፥ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ስም እንዳይምሉ ቢከለከሉና መንፈስ ቅዱስ በመባል ቢጠራም፥ ከአብና ከወልድ ይበልጥ ቅዱስ ነው ማለት አይደለም። ፍጹም ቅድስና የሥላሴ ዋና ባሕርይ ነው።  2. መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ባሕርያት አሉት(ዘፍጥ. 1፡2፤ ኢዮብ 26፡13፤ 1ኛ ቆሮ. 2፡9-11፤ ዕብ. 9፡14)።  3. የእግዚአብሔርን ሥራዎች ያከናውናል(ኢዮ. 33፡4፤ መዝ. 104:30፤ ሉቃስ 12፡11-12፤ ሐዋ. 1፡5፤ 20፡28፤ 1ኛ ቆሮ. 6፡11፤ 2፡8-11፤ 2ኛ ጴጥ. 1፡21)።  4. ከላይ እንደተጠቀሰው መንፈስ ቅዱስን ለማመልከት ያገለገሉት ሰብዓዊ ተውላጠ ስምች ማንነቱን ያረጋግጣሉ።  5. መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተጠቀሰው፥ መንፈስ ቅዱስ ሊታመንበት የሚገባ አካል ሆኖ ቀርቧል (መዝ. 51፡11፤ ማቴ. 28፡19፤ ሐዋ. 10፡19-21)። የሚታመንበት አካል እንደመሆኑ፥ ሊታዘዙትም የሚገባው ነው። በክርስቶስ ያመነ ሰው፥ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በሕብረት ስለሚጓዝ፥ ኃይሉን፥ መሪነቱን፥ ትምህርቱን፥ እና ሙሳቱን (ብቃቱን) በመለማመድ፥ የመንፈስ ቅዱስን አካልነት በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን ታላቅ የአስተምህሮ እውነት ይረዳል።  ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አካልነቱ Read More »

እግዚአብሔር ወልድ፡- ከቅዱሳኑ ጋር ስለመምጣቱ

This entry is part 13 of 52 in the series ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች

በዚህ ምዕራፍ፥ ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ጋር እና ለቅዱሳኑ መምጣቱን የሚያመለክተው ትምህርት ለአንዳንዶች ግር ይላቸዋል፥ ስለዚህ ልዩነታቸውን ለማጤን ሁለቱን ክንውኖች በጣምራ ማጥናቱ ተጎቢ ይሆናል።  ሀ. ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት የሚቀድሙ ዓበይት ሁኔታዎች  ኋላ ከመጨረሻው ዘመን ትንቢት ጋር በተያያዘ መልኩ በምናደርገው ጥናት እንደምናገኘው፥ ቤተ ክርስቲያን መነጠቅና በክርስቶስ መንግሥቱን ለመመሥረት ዳግም መምጣት መካከል ያለው ጊዜ ግልጥ በሆኑ ሦስት ወቅቶች ተከፋፍሏል።  1. ዮዝግጅቱ ወቅት ክቅዱሳን መነጠቅ ቀጥሎ የሚመጣ ሲሆን፥ ያን ጊዜ ስምታንሠራራው ጥንታዊት የሮም መንግሥት ሥር አሥር መንግሥታት በኮንፌዴሬሽን አስተዳደር ይጠቃለላሉ። ከዚህ አስተዳደር ውስጥ መጀመሪያ ሦስቱን፥ ቍጥሉ ደግሞ አሥሩንም መንግሥታት የሚገዛ አምባገነን መሪ ይነሣል።  2. ይህ መሪ ከእስራኤል ጋር በሚያደርገው የሰባት ዓመት ቃል ኪዳን መሠረት በሜዲትራንያን ባሕር አካባቢ የሠላም ጊዜ ይሆናል(ዳን. 9:27)።  3. ቃል ኪዳን ከተደረገ ሦስት ዓመት ተኩል በኋላ እምባገነኑ መሪ ቃሉን ስለሚያፈርስ፥ በእስራኤልና በክርስቶስ በሚያምኑ ሁሉ ሳይ ስደት ይነሣል። ይህ መሪ የዓለም አምባገነን መሪ ይሆናል፥ ስግደት ለርሱ ብቻ እንዲሆን ከመሻቱ የተነሣ የዓለም ሃይማኖቶችን ሁሉ ያጠፋል። ከርሱ ፈቃድ በቀር መገብየት እንዳይኖርና፥ ያለርሱ ፈቃድ መሸጥ ወይም መግዛት እንዳይቻል ለማድረግ በዓለም ያለውን የንግድ እንቅስቃሴ ሁሉ ይቆጣጠራል።  ይህ የሦስት ዓመት ተኩል ጊዜ ታላቁ ፍዳ ይባላል (ዳን. 12፡1፤ ማቴ. 24፡21 ፤ ራእይ 7፡14)። በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ታላቅ ፍርድ ይወርዳል (ራእይ 6፡1-18፥ 24)። ታላቁ ፍዳ ወደ ታላቅ የዓለም ጦርነት ይሸጋገራል (ራእይ 16፡14-16)። ጦርነቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በሚደርስበት ጊዜ፥ ክርስቶስ ሰማዕት ያልሆኑ ቅዱሳንን ለመታደግ፥ በምድር ላይ ሊፈርድና የጽድቅ መንግሥቱን ሊመሠርት ይመጣል። ከብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ለመረዳት እንደሚቻለው፥ ይህ ታላቅ፥ የሁከት ሁኔታ ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት ይቀድማል። እነዚህ ክንውኖች ሳይፈጸሙ የክርስቶስን ዳግም ምጽአት ይሆናል ብሎ መጠባበቅ አይቻልም።  ለ. ከዳግም ምጽአቱ ጋር የሚዛመዱ ወሳኝ እውነታዎች  1. ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር ቀሚመለስ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል (ዘካ. 14፡4)፤ በእካል (ማቴ. 25፡31፤ ራእይ 19፡11-16)፤ በደመና እንደሚመለስ (ማቴ. 24፡30፤ ሐዋ. 1፡11፤ ራእይ 1፡7)። ስለዚህ የሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ሁሉ እንደሚገልጡት ይህ ሁኔታ ዓለም ሁሉ የሚያየውና የከበረ ዕለት ነው (ራእይ 1፡7)።  2. በኢየሱስ ክርስቶስ በራሱ እንደተገለጠውና ማቴዎስ 24፡26-29 ውስጥ እንደተመዘገበው፥ የርሱ መገለጥ የመብረቅ ብርሃን ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ እንደሚታይ ይሆናል። ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት ከዚያች ወራትም መከራ በመባል በሚታወቁት ጊዜያት፥ በሰማይ ሁከት ይሆናል፥ ፀሐይ ትጨልማለች፥ ጨረቃ ብርሃን አትሰጥም፥ ከዋክብት ከሰማያት ይወድቃሉ፥ ሰማያት ራሳቸው ይናወጣሉ። ራእይ 6፡12-17፤ 16፡1-21 ውስጥ ሁኔታው በበለጠ ዝርዝር ተብራርቷል። የክርስቶስ ዳግም ምጽአት በምድር በሚኖሩ ሁሉ የሚታይ ይሆናል (ማቴ. 24፡30፤ ራእይ 1፡7)። “የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፡” (ማቴ. 24፡30)። ምክንያቱም ብዙዎቹ ፍርድ የሚጠብቃቸው በዚህ ጌታ ያላመኑ ሕዝብ ናቸው።  3. ክርስቶስ በዳግም ምጽአቱ ወቅት በቅዱሳንና በመላእክት በድምቀት ይታጀባል። ሁኔታው ራእይ 19፡11-16 ውስጥ በዝርዝር ተገልጧል። ዮሐንስ እንዲህ ነው የጻፈው:- “  ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆም አምባላይ ፈረስ፥ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፤ በጽድቅም ይፈርዳል፤ ይዋጋልም። ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፤ በራሱ ላይም ብዙ ዘውዶች አሉ፤ ከእርሱ በስተቀር አንድ እንኳ የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው፤ በደምም የተረጨ ልብስ ተጎናጽፏል፤ ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ተብሏል። በሰማይም ያሉ ጭፍሮች ነጭና ጥሩ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ ለብሰው በአምባላዮች ፈረሶች ተቀምጠው ይከተሉት ነበር። አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሠይፍ ከአፉ ይወጣል፤ እርሱም ሰብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔር የብርቱ ቁጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል። በልብሱና በጭኑም የተጻፈበት የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ የሚል ስም አለው”።  የክርስቶስ በቅዱሳን ሁሉና በመላእክት የታጀበ መሆኑ፥ ሂደቱን ዝግ ያለና ብዙ ሰዓት የሚወስድ መሆኑን ያመለክታል። በዚህ ጊዜ ዓለም ሁሉ ክንውኑን ያይ ዘንድ መሬት ትሽከረከራለች። የዳግም ምጽአቱ ክንውን ክርስቶስ ወደ ሰማይ በዐረገበት በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ያበቃል (ዘካ. 14፡1-4፤ ሐዋ. 1፡9-12)። በዚያን ጊዜ የክርስቶስ እግሮች ደብረ ዘይት ተራራ ላይ ያርፋሉ፤ ተራራውም ሁለት ላይ ደካፈልና ከኢየሩሳሌም ወደ ምሥራቅ እስከ ዮርዳኖስ የሚዘልቅ ሸለቆ ይፈጠራል።  4. ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜ በመጀመሪያ በጦርነቱ የተሳተፈውን የዓለም ጦር ሥራት ይቀጣል (ራእይ 19፡15-21)። መንግሥቱንም እንደመሠረተ እስራኤልን ሰብስቦ ወደ ሺህ ዓመቱ መንግሥት ለመግባት ካላቸው ብቃት አንጻር ይፈርድባቸዋል (ሕዝ. 20፡34-38)። በተመሳሳይ ሁኔታ ‘አሕዛብን” ሰብስቦ ይፈርድባቸዋል (ማቴ. 25፡31-46)። ከዚህ ሁሉ በኋላ የጽድቅና የሰላም መንግሥቱን ምድር ላይ ይመሠርታል። ሰይጣን ይታሰርና ግልጥ የሆኑ ዓመፃዎች ሁሉ ፍርዳቸውን ያገኛሉ። ይህን አሳብ በሚቀጥሉት ምዕራፎች ላይ በስፋት እንመለከታለን።  ሐ. ዳግም ምጽአቱ ከመነጠቅ ጋር ሲነጻጸር  ባለፈው ምዕራፍ እንደታየው በክርስቶስ ለቅዱሳኑ መምጣትና፥ በቅዱሳኑ ታጅቦ መምጣት መካከል ብዙ ማነጻጸሪያዎች አሉ። ሁለቱን ክንውኖች፥ ማለት የክርስቶስን ለቅዱሳኑ መምጣትና ከቅዱሳኑ ጋር መምጣትን በዚህ አኳኋን ለመለየት ይቻል ይሆናል። ልዩነታቸውን በደንብ ለመገንዘብ የክርስቶስን ለቅዱሳኑ መምጣትና ከቅዱሳን ጋር መመለሱን በተመለከተ ከዚህ በታች ያለውን ሠንጠረዥ ይመልከቱ።  ለቅዱሳን መምጣቱ  (1) “በአንድነት ወደ እርሱ መሰብሰባችን”።  (2) እንደ ንጋት ኮከብ” ይመጣል (ራእይ 2፡28፤ 22 ፡16፤ 2ኛ ጴጥ. 1፡19)፡፡ (3) “የክርስቶስ ቀን” (1ኛ ቆሮ. 1፡8፤ 2ኛ ቆሮ. 1፡14፤ ፊልጵ. 1፡6፤ 10፤ 2፡16)፡፡ (4) ያላ ምልክት እንደ ሌባ በድንገት የሚመጣ ቀን ነው።  (5) ድንገተኛ፥ በማንኛውም ጊዜ ሊሆን የሚችል፡፡ (6) ስለ ኃጢአት አልተጠቀሰም፡፡ (7) እስራኤል አትለወጥም፡፡ (8) ቤተ ክርስቲያን ከምድር ትወሰዳለች፡፡ (9) መንግሥታት አይለወጡም (10) ፍጥረት አይለወጥም፡፡ (11) አስቀድሞ ያልተገለጠ “ምስጢር”፡፡ (12) ተስፋ ክርስቶስ ላይ ብቻ ይሆናል “ጌታ በደጅ ነው” (ፊልጵ 4፡5)፡፡ (13) ክርስቶስ እንደሙሽራ፣ እንደጌታ እና የቤተ ክርስቲያን ራስ ይገለጣል (ኤፌ 5፡25-27፤ ቲቶ 2፡13)፡፡ (14) አመጣጡን አለም አያየውም (15) ክርስቲያኖች ሊሸለሙ ካለው ነገር አንጻር ለብያኔ ይቀርባሉ፡፡ ከቅዱሳን ጋር መምጣቱ  (1) “የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት” (2ኛ 1 ተሰ. 2፡1)። (2) እንደ “ጽድቅ ፀሐይ” (ሚል. 4፡2)።  3) “የጌታ ቀን” (2ኛ ጴጥ. 3፡10)።  (4) መቃረቡ ይታያል (1ኛ ተሰ. 5፡4፤ ዕብ. 10፡25)።  (5) ስለ ቀኑ የተነገረው ትንቢት አስቀድሞ ይፈጸማል (2ኛ ተሰ 22፡23)፡፡ (6) ኃጢአት ይጠፋል፥ ሰይጣን ይፈረድበታል፥ የኃጢአት ሰው ይደመሰሳል (2ኛ ተሰ. 2፡8፤ ራእይ 19፡20፤ 20፡1-4)። ሊሆን የሚችል።  (7) ቃል ኪዳኗ ሁሉ ይፈጸማል (ኤር. 23፡5 -8፤ 30፡3-11፤ 31፡27-37)።  (8) ከክርስቶስ ጋር ትመለሳለች (1ኛ ተሰ. 4፡17፤ ይሁዳ 14-15፤ ራእይ 19፡14)።  (9) መንግሥታት ይፈርድባቸዋል (ማቴ. 25፡31-46)።   (10) ፍጥረት ከክፉ እሥራት ነጻ ይወጣል (ኢሳ. 35፤ 65፡17-25)።  (11) በብሉይና በአዲስ ኪዳን በአጠቃላይ ታይቷል (ዳን. 7፡13-14፤ ማቴ. 24፡27-30፤ 1ኛ ቆሮ. 15፡51-52)።  12) መንግሥቱ ትመጣለች (ማቴ. 6፡10)።  (13) ክርስቶስ እንደ ንጉሥ፥ መሢሕ እና የእስራኤል መድኅን ይገለጣል (ኢሳ. 7፡14፤ 9፡6-7፤ 11፡1-2)፡፡ (14) በታላቅ ሥልጣንና ክብር ይመጣል (ማቴ. 24፡27፥ 30፤ ራእይ 1፡7)።  (15) ነገሥታት ለርሱ ከሰጡት ምላሽ አንጻር ይበየንባቸዋል (2ኛ ቆሮ. 5፡10-11፤ ማቴ. 25፡31-46)።  ጠቃሚ ጥቅሶች  ዮሐ. 14፡1-3፤ 1ኛ ቆሮ. 15፡51-52፤ 1ኛ ተሰ. 4፡13-18፤ ፊሊጵ 3፡20-21፤ 2ቆሮ 5፡10፤  ዘዳ. 30፡1-10፤ መዝ. 72፤ የነቢያትን ትንቢቶች በሙሉ ያስተውሉ (ማቴ. 25፡1-46፤ ሐዋ. 1፡11፤ 115፡13-18፤ 2ኛ ተሰ 22፡112፤ 2ኛ ጴጥ. 2፡1-3፡8፤ ራእይ. 19፡11-20፡6)። ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ቅዱሳን ድንቅ ስራ የተመሰገነ ይሁን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ይህን ጽሁፍ መቀየርም ሆነ ለሽያጭ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

እግዚአብሔር ወልድ፡- ከቅዱሳኑ ጋር ስለመምጣቱ Read More »