የሕይወት እንጀራ

ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች

ጳውሎስ ለክርስቶስ እንዴት ልንኖር እንደሚገባ ያስተምራል (ፊልጵ. 1፡27-2፡18)

ክርስቶስን የግል አዳኝ አድርጎ ማመኑ አስፈላጊ ነው። ይህ ወደ ሲዖል እንዳንገባና የእግዚአብሔር ልጆች እንድንሆን ያስችለናል። ነገር ግን እግዚአብሔር በሚያድነን ጊዜ ከዚህ የበለጠ ብዙ ይጠብቅብናል። ለእኛ ያለውን ታላቅ ፍቅር በሚያንጸባርቅ መልኩ እንድንኖርለት ይሻል። ምንም እንኳ እግዚአብሔር ከእኛ የሚፈልገው ምስጋናችንን ብቻ ነው ብንልም፥ አዲስ ኪዳን ግን እርሱን በሚያስከብር መንገድ እንድንኖርም ያስተምራል። ጳውሎስም ለተጠራችሁለት የክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ተመላለሱ […]

ጳውሎስ ለክርስቶስ እንዴት ልንኖር እንደሚገባ ያስተምራል (ፊልጵ. 1፡27-2፡18) Read More »

በጳውሎስ እስራት ወንጌል መስፋፋቱ (ፊልጵ. 1፡12–26)

መከራ በሚደርስብን ጊዜ ትክክለኛ አቋም መያዝ አስቸጋሪ ነው። በቀላሉ ተስፋ መቁረጥ ይቻላል። ታላቁ የወንጌል አገልጋይ ከአራት ዓመታት በላይ ወኅኒ ቤት ውስጥ ቆይቷል። በዚህ ጊዜ ለጳውሎስ እግዚአብሔር ተሳስቶ ይሆን? ብሎ ማሰብ ቀላል ነበር። የፊልጵስዩስ አማኞችም የቤተ ክርስቲያናቸው መሥራችና ወዳጃቸው የሆነው ሰው በመታሠሩ ተጨንቀው ነበር። ጳውሎስ በወኅኒ ቤት ውስጥ ቢሆንም፥ እግዚአብሔር ታላቅ አምላክ በመሆኑ ክፉውን ነገር ወደ

በጳውሎስ እስራት ወንጌል መስፋፋቱ (ፊልጵ. 1፡12–26) Read More »

ምስጋናና ጸሎት (ፊል. 1፡1-10)

ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ፥ ሁለት ዐበይት እውነቶችን ለማስተላለፍ ይፈልጋል። በመጀመሪያ፥ የፊልጵስዩስ አማኞች በማንኛውም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ቢሆኑ በክርስቶስ ደስ መሰኘትን እንዲማሩ ይፈልጋል። እሥራት፥ ስደት፥ ድህነት፥ ሞትም እንኳን ቢያጋጥማቸው ደስታቸውን ማጣት አይኖርባቸውም። በሚጎዱን ነገሮች አንደሰትም። አፍቃሪው አምላካችን ሁኔታዎችን በመቆጣጠር ላይ በመሆኑ ደስ ልንሰኝ እንችላለን። ሁለተኛ፥ ጳውሎስ የፊልጵስዩስ አማኞች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንድነትን ለመፍጠር እንዲጥሩ ይፈልጋል።

ምስጋናና ጸሎት (ፊል. 1፡1-10) Read More »

የፊልጵስዩስ መልእክት ዓላማ፣ ልዩ ባሕሪያት፣ መዋቅርና አስተዋጽኦ

የፊልጵስዩስ መልእክት ዓላማ የፊልጵስዩስ ቤተ ክርስቲያን በአፍሮዲጡ መታመም ላይ የነበራትን ስጋት አስመልክቶ መረጃ መስጠት። የጳውሎስ ደብዳቤ የመጣው በሮምና ፊልጵስዩስ መካከል ተከታታይ መልእክቶች ከተላለፉ በኋላ ነበር። በፊልጵስዩስ የነበሩ ክርስቲያኖች ስለ ጳውሎስ መታሠር በሰሙ ጊዜ፥ ሁኔታውን ይከታተል ዘንድ አፍሮዲጡን ወደ እርሱ ላኩት። መጠነኛ ገንዘብም ሰደዱለት (ፊልጵ. 4፡10-18)። አፍሮዲጡ የጳውሎስን የተጎሳቆለ አኗኗር ከተመለከተ በኋላ ተጨማሪ ገንዘብ ይልኩለት ዘንድ

የፊልጵስዩስ መልእክት ዓላማ፣ ልዩ ባሕሪያት፣ መዋቅርና አስተዋጽኦ Read More »

የፊልጵስዩስን መልእክት ማን ጸፈው፣ ለማን ተጻፈ፣ መቼና የት ተጻፈ

የፊልጵስዩስ መልእክት ጸሐፊ ጳውሎስ ይህንን መልእክት ለፊልጵስዩስ ሰዎች ያቀረበው ራሱንና የአገልግሎት ተባባሪው የነበረውን ጢምቴዎስን በማስተዋወቅ ነው። መልእክቱን የጻፈው ጢሞቴዎስ ነበር። ነገር ግን ጢሞቴዎስ ከጳውሎስ ጋር አብሮ ስለነበረና መጀመሪያ ወንጌሉን ለፊልጵስዩስ ሰዎች ከጳውሎስ ጋር አብሮ ስላደረሳ፥ ጳውሎስ ሰላምታውን ሊያካትትለት ፈለገ። ጳውሎስ በሌሎች መልእክቶቹ ውስጥ ከሚያሳየው ሁኔታ በተለየ መልኩ ሐዋርያነቱን አለመግለጹ አስገራሚ ነው። ጳውሎስ በዚህ መልእክት ውስጥ

የፊልጵስዩስን መልእክት ማን ጸፈው፣ ለማን ተጻፈ፣ መቼና የት ተጻፈ Read More »

የፊልጵስዩስ መልእክት መግቢያ

ወንጌላዊ ተገኘወርቅ ከነበረበት ስፍራ ወደ ሌላ አካባቢ ሄዶ ወንጌልን እንዲሰብክ ተልኮ ነበር። በዚሁ ስፍራ ለ10 ዓመታት ሲያገለግል እግዚአብሔር በሚገባ ባረከው። ከ20 የሚበዙ አብያተ ክርስቲያናት ተመሠረቱ። ይሁንና፥ ብዙም ጎልቶ ሳይታይ የቆየው ተቃውሞ ይበልጥ እየተጠናከረ መጣ። አንድ ቀን ተገኘወርቅ በነበረባት ከተማ ውስጥ የሚገኝ አንድ ሱቅ ተዘረፈ። በዚህም ጊዜ ጠላቶቹ ተገኘወርቅ ዝርፊያውን ሲፈጽም መመልከታቸውን ተናገሩ። በመሆኑም፥ ተገኘወርቅ በፖሊስ

የፊልጵስዩስ መልእክት መግቢያ Read More »