የሕይወት እንጀራ

መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ

የመጽሐፈ ኢያሱ ዋና ትምህርቶች

የውይይት ጥያቄ፥ ከመጽሐፈ ኢያሱ ጥናት ከሕይወትህ ጋር ልታዛምድና በቤተ ክርስቲያንህ ላሉ ሰዎች ልታስተምር የምትችላቸውን መንፈሳዊ ትምህርቶች ዘርዝር። የከነዓንን ምድር ለአብርሃምና ለዘሩ ለመስጠት ቃል ኪዳን የገባው እግዚአብሔር የሰጠውን የተስፋ ቃል ኪዳን ፈጸመ፤ (ዘፍ. 12፡7፤ 15፡7፥ 18-21)። እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን በከነዓን ምድር በሚኖሩ ሰዎች ላይ ድልንና የከነዓንን ምድር ርስት አድርጎ ሰጣቸው። እኛ አይሁድ ስላልሆንን እነርሱ ለከነዓን ምድር የነበራቸውን […]

የመጽሐፈ ኢያሱ ዋና ትምህርቶች Read More »

ኢያሱ 13-24

ክርስቲያን በሕይወቱ ከሚያጋጥሙት አደገኛ ነገሮች አንዱ ሰላምና በረከትን በሚያገኝ ጊዜ እግዚአብሔርን መርሳት ነው። ሙሴ ስለዚህ ጉዳይ በዘዳ. 8፡7-20 ባለው ክፍል እስራኤላውያንን አስጠንቅቆአቸዋል። የከነዓን ምድር በሙሉ ለእስራኤላውያን (ለአሥራ ሁለቱም ነገዶች) ከተከፋፈለ በኋላ እያንዳንዱ ሰው በተሰጠው ምድር አርፎ ሲኖር ሕዝቡ በዕለታዊ ተግባራቸው እየተጠመዱ በመፈተናቸው እግዚአብሔርን የመርሳት ከፍተኛ ዝንባሌ ታይቶባቸው ነበር፤ ስለዚህ ኢያሱ ሕዝቡን ሁሉ ወደ ሴኬም ጠራና

ኢያሱ 13-24 Read More »

ኢያሱ 1-12

የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) ብዙ ክርስቲያኖች በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ሽንፈት የሚደርስባቸው ለምንድን ነው? ለ) ብዙ ክርስቲያኖች ያለማቋረጥ በኃጢአት የሚወድቁትና ጨርሶ ድል የማያገኙ የሚመስሉት ለምንድን ነው? ሐ) እግዚአብሔር ከእኛ የሚፈልገው ይህን ይመስልሃልን? ግለጥ። እግዚአብሔር ለሕዝቡ ድልን ለመስጠት ቃል ገብቷል። ጳውሎስ ለሮሜ ክርስቲያኖች ሲጽፍ፦ «በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን» ብሉአል (ሮሜ 8፡37)። በተጨማሪ 1ኛ ቆሮ. 15፡57፤ 1ኛ

ኢያሱ 1-12 Read More »

የመጽሐፈ ኢያሱ ዋና ዓላማ

መጽሐፉ የተሰየመው፥ በመጽሐፉ ውስጥ በሚገኘው ዋና ተዋናይ በኢያሱ ቢሆንም፥ ትኩረቱ ግን በእርሱ ላይ ሳይሆን በእግዚአብሔር ላይ ነው። የእግዚአብሔር ሕዝብ መሪ የሆነውና የእስራኤልን ጦር በመምራት ድልን ያስገኘው እግዚአብሔር ነው። ኢያሱ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ሥር ያለ ሰብአዊ መሪ በመሆኑ ትእዛዙን በቀጥታ ይፈጽም ነበር። ከሌሎች መጻሕፍት (መጽሐፈ መሳፍንት፥ ሳሙኤልና ነገሥት) ጋር በአንድነት ሆኖ የመጽሐፈ ኢያሱ ዋና ዓላማ እግዚአብሔር በታሪክ

የመጽሐፈ ኢያሱ ዋና ዓላማ Read More »

የመጽሐፈ ኢያሱ መግቢያ

የውይይት ጥያቄ፥ መዝ. (91)፡1-16 አንብብ። ሀ) በጠላቶቻችን ላይ ስለምንቀዳጀው ድል በዚህ ስፍራ የተሰጡ ተስፋዎች ምንድን ናቸው? ለ) እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ድል የሰጠህን አንዳንድ ጠላቶች ጥቀስ። ሐ) እግዚአብሔር፥ ቤተ ክርስቲያንህ በእነርሱ ላይ ድል እንድትጎናጸፍ ያደረጋትን አንዳንድ ችግሮችንና ጠላቶችን ጥቀስ። መጽሐፈ ኢያሱ በእግዚአብሔር ሕዝብ ጠላቶች ላይ ስለተገኘ ድል የሚናገር መጽሐፍ ነው። ዛሬም እኛ ድልን እንዴት እንደምናገኝ የሚያስተምረን

የመጽሐፈ ኢያሱ መግቢያ Read More »

ታሪካዊ መጻሕፍትን እንዴት እንደምንተረጉማቸው?

ብዙ ክርስቲያኖች የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪካዊ መጻሕፍት እንዴት እንደሚተረጉሙና በተለይም ከሕይወታቸው ጋር እንዴት እንደሚያዛምዱ ባለማወቅ ይቸገራሉ። ከእኛ ባሕል ጨርሶ ልዩ በሆነ ባሕል ውስጥ ብዙ ያልተለመዱ ስሞች፥ ቦታዎችና ክስተቶች ይኖራሉ። ስለዚህ ብዙ ጊዜ በቀላሉ ከሕይወታችን ጋር ልናዛምዳቸው የምንችላቸውን ታሪኮች የመምረጥና የቀረውን የመጽሐፍ ቅዱስ የሥነ መለኮት ትምህርት ቸል የማለት ዝንባሌ ይታይብናል። እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስን እንዲጽፉ ሰዎችን ሲመራ፥ ከሁሉም

ታሪካዊ መጻሕፍትን እንዴት እንደምንተረጉማቸው? Read More »

የታሪካዊ መጻሕፍት መግቢያ

በዚህ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት መክፈቻ ጥናታችን እስካሁን ድረስ የመጀመሪያውን ክፍል ፔንታቱክን ተመልክተናል። ፔንታቱክ፡- ዘፍጥረት፥ ዘጸአት፥ ዘሌዋውያን ዘኁልቁና ዘዳግም የሚባሉ አምስት መጻሕፍትን ይዞአል። ከታሪካቸው አንጻር፥ እነዚህ መጻሕፍት የሚናገሩት ከፍጥረት መጀመሪያ ጀምሮ እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመግባት እስከተዘጋጁበት ጊዜ ድረስ ያለውን ሁኔታ ነው። የፍጥረት መጀመሪያ መቼ እንደነበር ምንም የምናውቀው ነገር ባይኖርም፥ የፔንታቱክ ታሪክ ግን በ1400 ዓ.ዓ. ገደማ

የታሪካዊ መጻሕፍት መግቢያ Read More »