በፔንታቱክ ውስጥ የሚገኙ የሥነ ጽሑፍ ዓይነቶች
ፔንታቱክ በአንድ ጸሐፊ (ሙሴ) የተጻፈ የቅዱሳት መጻሕፍት አንድ ክፍል ቢሆንም፥ በውስጡ አራት የተለያዩ የሥነ-ጽሑፍ ዓይነቶች ይገኛሉ፡፡ አንድ የተወሰነ ክፍል ወስደን ለመተርጎም በምናጠናበት ጊዜ ሰሚገባ እንተረጉመው ዘንድ የሥነ-ጽሑፍ ዓይነት ወስነን በዚያው መልክ መተርጎም ይገባናል። በፔንታቱክ ውስጥ አራት ዋና ዋና የሥነ-ጽሑፍ ዓይነቶች ይገኛሉ። ፩. የታሪክ ጽሑፎች፡- በብሉይ ኪዳን ውስጥ በብዛት የምናገኘው የሥነ -ጽሑፍ ዓይነት የታሪክ ጽሑፍ ወይም ትረካ ነው። መጽሐፍ ቅዱሳችንን በአጠቃላይ በሚመለከትም ይህ እውነት ነው። የብሉይ ኪዳንን ሥነ ጽሑፍ ስንመለከት ከመቶ አርባው እጅ (40%) ትረካ ነው። በታሪክ ጽሑፎች ውስጥ የቅዱሳት መጻሕፍት ጸሐፊው ማንኛውም ሰው በሚረዳው በቀላል ቋንቋ ታሪኩን ይተርካል። የሚናገረውም ምን እንደተፈጸመ ነው። ይህም ሆኖ መጽሐፍ ቅዱስን ልዩ የሚያደርገው የሚናገረው ታሪክ ተራ ያለመሆኑ ነው። ታሪኮቹ የተጻፉት በድሮ ጊዜ ምን እንደተፈጸመ ሊነግሩን ብቻ አይደለም። የውይይት ጥያቄ፥ ሮሜ 15፡4 እና 1ኛ ቆሮ. 10፡11 አንብብ። የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ዛሬ ለእኛ ያላቸው ዓላማ ምንድን ነው? እንዳንድ ምሁራን የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክን «የድነት (ደኅንነት) ታሪክ» ብለው ይጠሩታል። ሌሎች ደግሞ «የእግዚአብሔር ታሪክ» ይሉታል። የታሪክ ጽሑፎች ዋና ዓላማ እግዚአብሔር በፍጥረት ውስጥና በሕዝቡ መካከል ሲሠራ ማሳየት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ዳር እስከ ዳር የምናየው አንድ ዋና ዓላማ እግዚአብሔር በታሪክ ውስጥ በተለያዩ ሰዎች ሕይወትና በልዩ ነገድ ውስጥ ሲሠራ ድነትን (ደኅንነትን) እየገለጠ መሆኑን ነው፤ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ከዚህ በፊት ስለተፈጸሙት እውነተኛ ታሪካዊ ክስተቶች ቢሆንም ጸሐፊው ስለ እነርሱ በሚጽፍበት ጊዜ ሁለት ዓላማዎችን ይዞ ነበር። የመጀመሪያው፥ ባለፈው ጊዜ ምን እንደተፈጸመ በትክክል መናገር ሲሆን፥ ሁለተኛው ደግሞ፥ የእግዚአብሔር ሰዎች ባለፉት ጊዜያት ከኖሩት ሰዎች አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ምሳሌነት በመማር እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሕይወት እንዴት መኖር እንደሚችሉ ለማሳየት ነው። ለምሳሌ፡- ሳምሶን በአሉታዊ ምሳሌነቱ ትምህርት ልናገኝበት ለምንችለው ታሪክ አንድ ጥሩ ምሳሌ ነው (መሳ. 13-16)። ክርስቲያኖች እንደመሆናችን፥ ሳምሶን በፍትወተ ሥጋ ኃጢአት በመውደቁ ሕይወቱን እንዴት እንዳጠፋ በመመልከት። ሕይወታችንና አገልግሎታችን እንዳይበላሽ በፍትወተ ሥጋ ኃጢአት እንዳንወድቅ መጠንቀቅ እንዳለብን እንማራለን። የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) አንዳንድ ክርስቲያን መሪዎች ሳምሶን በወደቀበትአኳኋን የሚወድቁት እንዴት ነው? ለ) ከሳምሶን ሕይወት መጥፎ ምሳሌነት ምን ሊማሩ ይገባ ነበር? ከታሪኮች በጎ ምሳሌነትም ልንማር ይገባናል። ለምሳሌ፥ አብርሃም ይስሐቅን ለመሠዋት ከፈቀደበት ታሪክ እግዚአብሔር ከማንኛውም ነገር ይልቅ ከቤተሰባችንም በላይ እንዴት እርሱን መውደድ እንዳለብን እንደሚፈልግ እንማራለን (ዘፍ. 22)። የብሉይ ኪዳንን ታሪካዊ ክፍሉች የምንተረጉምባችው በርካታ መመሪያዎች አሉ። ከዚህ በታች የተሰጡት እግዚአብሔር ከታሪክ ውስጥ ምን ሊያስተምረን እንደሚፈልግ ለመረዳት እንድንችል ሁል ጊዜ በአእምሮአችን ውስጥ ልንጠብቃችው ከሚገቡን ነገሮች ጥቂቶቹ ናቸው። የብሉይና የአዲስ ኪዳን ታሪኮችን መረዳት የሚገባን በሦስት የተለያዩ ደረጃዎች ነው። በመጀመሪያ፥ እያንዳንዱ ታሪክ ከፍተኛ ደረጃ አለው። ታሪኩ በዚህ ደረጃው ስለ እግዚአብሔር ሰፊ ነገር ያስተምረናል። በዚህ ደረጃ ጸሐፊው ሊነግረን የሚፈልገው፥ እግዚአብሔር በአንድ ሕዝብ ወይም በግለሰቦች ሕይወት ውስጥ ሊሠራ ያለውን ዓለም አቀፋዊ ዕቅድ ነው። አብዛኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ስለ እግዚአብሔር አካላዊ ሕልውና፥ ዓለምን ስለ መፍጠሩ፥ ስለ ሰው ልጅ ክፋትና በእግዚአብሔር ስለ መቤዠት አስፈላጊነት አንዳንድ ነገሮችን ያስተምረናል። ይህ ከፍተኛ ደረጃ እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ለማስተካከል ስለ ሚሰጠው መሢሕም ይናገራል። የውይይት ጥያቄ፥ አንድ የብሉይ ኪዳን ታሪክ ምረጥ። ይህ የመረጥከው ታሪክ (ስለ እግዚአብሔር ባሕርይና ዓላማ፥ ከሰው ልጅ ጋር አብሮ ስለ መሥራቱ፥ ለስው ልጅ ኃጢአተኛነት ወይም እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ለመዋጀት ስላለው ዕቅድ ምን ያስተምረናል? ሁለተኛው፥ የታሪኩ መካከለኛ ክፍል ነው። ይህ ደረጃ ማዕከላዊ የሚያደርገው በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕዝብ የነበሩትን እስራኤልን ነው። በአዲስ ኪዳን ይህ ደረጃ የሚያተኩረው በኢየሱስና በቤተ ክርስቲያን ጅማሬ ላይ ነው። የብሉይ ኪዳን ታሪክ የሚያተኩረው በእስራኤል ሕዝብ አካባቢ ነው። የእስራኤል ሕዝብ በአብርሃምና በዘሮቹ እንዴት እንደተጀመረ በዘፍጥረት እናነባለን። ከዘጸአት ጀምሮ እስከ 2ኛ ዜና ባለው ክፍል ደግሞ እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ የተስፋይቱን ምድር እንዴት እንደሰጣቸው፥ በዳዊት በኩል የተሳካላቸው ሕዝብ አድርጎ እንዴት እንደለወጣችው፥ ሕዝቡ እንዴት በኃጢአት እንደወደቁና እግዚአብሔር እንደቀጣቸው እንመለከታለን። አብዛኛውን ጊዜ የብሉይ ኪዳን ታሪኮች እግዚአብሔር ከእስራኤል ሕዝብ ጋር እንዴት ይሠራ እንደነበረ ያመለክታሉ። ስለዚህ አንድን ታሪክ በምናጠናበት ጊዜ እግዚአብሔር ስለ እስራኤል ሕዝብ ምን እንደሚል መገመት አለብን። የውይይት ጥያቄ፥ ሌላ የብሉይ ኪዳን ታሪክ ምረጥ። ያ ታሪክ በእስራኤል ሕዝብ አጠቃላይ ታሪክ ላይ ምን የሚጨምረው ነገር አለ? ሦስተኛው፥ የእስራኤልን ሕዝብ ታሪክ የተሟላ የሚያደርጉት የግለሰቦች ታሪኮች አሉ። የአብርሃም፥ የሙሴ፥ የዳዊት፥ ወዘተ ታሪኮች ተጽፈው ይገኛሉ። ከእነዚህ ታሪኮች በርካታ መንፈሳዊ እውነቶችን እንማራለን። እያንዳንዱ የግለሰብ ታሪክ የመጽሐፍ ቅዱስ ትረካ የተመሠረተበት ነው። ጸሐፊው የእያንዳንዱን ግለሰብ ታሪክ ሲጽፍ ትልቅ ዓላማ ነበረው። ሊነግረን የፈለገው የእስራኤልን ሕዝብ ታሪክ ቢሆንም፥ የእያንዳንዱ ግለሰብ ታሪክ የሚጫወተው ትልቅ ሚና አለው፤ ነገር ግን ከዚህም በላይ ጸሐፊው ሊነግረን የፈለገው ስለ እግዚአብሔርና ከሰዎች ጋር ስላለው ግንኙነት ነው። ስለ እግዚአብሔር ማስተማር ስለ እስራኤል ማስተማር ስለ ግለሰቦች ማስተማር የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች በትምህርት ቤት እንደምናጠናቸው ዓይነት የጥንት ሰዎች ታሪክ ብቻ አይደሉም። ይልቁንም እግዚአብሔርን ለመግለጥና ለሰዎች በሰዎች በኩል ምን እንዳደረገ የሚነግሩን ናቸው። የመጽሐፍ ቅዱስ ትኩረት በእግዚአብሔር ላይ እንጂ ሰዎች ባደረጉት ነገር ላይ አይደለም። በብሉይ ኪዳን የታሪክ ጽሑፎች ውስጥ የቃላትን ተምሳሌታዊ ትርጉም መፈለግ የለብንም። ታሪኩን ልክ ተጽፎ እንዳለ በቀጥታ ለመረዳት መሞከር ያሻል። ይህም ማለት ድርጊቱ በተፈጸመበት ታሪካዊ መሠረት ልንረዳው ያስፈልጋል ማለት ነው። ለመረዳት የማንችላቸው ባሕላዊ ነገሮች ካሉ ለመረዳት መሞከር አለብን። አንድን ታሪክ ከመተርጎማችን በፊት ባሕላዊ ነገሮችን ስለ መረዳት አስፈላጊነት ጥሩ ምሳሌ የሚሆንን ቦዔዝ በምሽት መጎናጸፊያውን በሩት ላይ ስለማኖሩ የሚናገረው ታሪክ ነው። በአይሁድ ባሕል ይህ አንድ ሰው የማግባት መግለጫ ነው (ሩት 3፡9)። እነዚህን የተለያዩ ባሕላዊ ተግባሮች ለመረዳት ካልቻልን፥ በታሪኩ ውስጥ ልንረዳቸው የማንችላቸው በርካታ ነገሮች ይኖሩና የእግዚአብሔርን ሥራና በታሪኩ ውስጥ በተመለከትነው መንገድ አንድን ነገር የፈጸመበትን ምክንያት ምን እንደሆነ ሳንረዳ እንቀራለን። ታሪኩን ለማሟላት አንዳንድ ነገሮችን በመገመት የራሳችንን አስተሳሰብ እንዳንጨምር መጠንቀቅ አለብን። አንዳንድ ጊዜ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ዋናውን ትምህርት በቀጥታ አያስተምሩም። እንደ አንዳዶቹ የመጽሐፍ ቅዱስ የማስተሪያ ክፍሎች፥ (ለምሳሌ፡- ሮሜ) እግዚአብሔር እንድናውቅ የሚፈልገውን ነገር በቀጥታ አይናገሩም። ይልቁንም በታሪኩ ውስጥ ያለውን ትምህርት የምናገኘው በተዘዋዋሪ መንገድ ነው። ብዙውን ጊዜ ታሪኮቹ በሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የሚገኙ ቀጥተኛ ትምህርቶችን ይገልጻሉ። ለምሳሌ፡- በዳዊትና በቤርሳቤህ ታሪክ ውስጥ ዝሙት ስሕተት እንደሆነ በቀጥታ አልተናገረም። ይህ ዘጸ. 20፡14 ላይ በቀጥታ ተነግሯል። ይህ ታሪክ ግን በተዘዋዋሪ መንገድ እግዚአብሔር ዝሙትን እንደሚጠላ ያስተምራል። እያንዳንዱን ታሪክ ለሥነ- ምግባር ወይም ለማስተማሪያነት ከመፈፈለግ ይልቅ አንድ ታሪክ የሌላ ትልቅ ታሪክ ክፍል አካል መሆኑንና ዋናው ትኩረቱም የትልቁን ታሪክ ዋና ትምህርት ማግኘት እንጂ ትንሹ ታሪክ ላይ እንዳልሆነ ልናስታውስ ያስፈልገናል። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች እያንዳንዳቸው መንፈሳዊ መመሪያን ለማስተማር የተመረጡ ናቸው። የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ በርካታ ታሪኮች ነበሩ። አንድን ታሪክ በተለይ የመረጡበት ምክንያት ምንድን ነው? ምክንያቱም እነዚያ ታሪኮች የሥነ ምግባር ወይም መንፈሳዊ ትምህርት ለማስተማር የተመረጡ ነበሩ፤ ስለዚህ አንድ ታሪክ በባሕላዊ መልኩ አንድ ጊዜ በግልጽ ከተረዳነው በኋላ ከታሪኩ የሚገኘውን ዋና መንፈሳዊ ትምህርት መፈለግ አለብን። ይህ ትምህርት ብዙ ጊዜ የሚገኘው በታሪኩ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ባደረጉት ምርጫ ወይም በፈጸሙት ተግባር ነው። ታሪኩን በመረዳት ሂደት ውስጥ ራሳችንን በውስጡ በማስገባት በዚያን ጊዜ የምንኖር ብንሆን ኖሮ ምን ይሰማን ወይም ምን እናደርግ ነበር? ብሎ መጠየቅ ብዙ ጊዜ በጣም ጠቃሚ ነው። በትረካው ጽሑፍ ውስጥ ጸሐፊው የተፈጸመውን ነገር በትክክል የሚገልጽ መሆኑን መገንዘብ መልካም ነው። እርሱ ይህ ጥሩ ነው ላይል ይችላል። ለምሳሌ፡- በዘፍ. 38 ይሁዳ ሴተኛ አዳሪ ናት ብሎ ከገመታት ሴት ጋር እንደ አመነዘረ እናነባለን። ይህ ስሕተት
በፔንታቱክ ውስጥ የሚገኙ የሥነ ጽሑፍ ዓይነቶች Read More »