የሰው ውድቀት

ኃጢአት ለምን ከእግዚአብሔር ዕቅድ ውስጥ ገባ? የሚለው ጥያቄ ሰው ሊመልሰው የማይችለው ነው። በምን አኳኋን ኃጢአት በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ እንደገባ ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ዘፍጥረት 3 ላይ ተገልጧል። ይህ ምዕራፍ የይዘቱን ታሪካዊነት ተረት፥ እውነተኛ ተረት፥ አፈ ታሪክ፥ የተቀደሰ አፈ ታሪክ፥ ወዘተ. እያሉ የሚክዱ ብዙ ነቃፊዎች አሱት። ይሁን እንጂ ታሪካዊ ያልሆነ “እውነተኛ” ባሕርይ አጥብቀው ይይዛሉ (መጨረሻው ውሸት የሆነ ታሪክ)። እንዲህ ያለውን የተዛባ ሥነ-መለኮታዊ አመለካከት የሚያሳይ አንድ ምሳሌ እነሆ፡- 

ጠንካራ ወግ አጥባቂዎች ካልሆንን በዘፍጥረት 3 ላይ የተጻፈውን ታሪክ “እውነተኛ አፈታሪክ” ነው እንላለን። ይህም ማለት ኤደን ካርታ ላይ ባይገኘም እንዲሁም የአዳም እውቀት ከሰው ልጅ የታሪክ ቀመር ወይም መዘክር ጋር ባይጣጣምም፥ ምዕራፉ ልክ በሰው ልጅ የታሪክ ጅማሬ ወቅት እንደነበረው ዛሬ ያለውን የሰው ልጅ የኑሮ ልምድ ስፋት ያሳያል ማለት ነው። በቀላል ቋንቋ ለመናገር፥ እኛ የወደቅን ፍጡሮች ነን፤ የአዳምና የሔዋን ታሪክም የኔና የእናንተ ታሪክ ነው። 

ይህ አባባል በዚህ መልኩ ይቅረብ እንጂ፥ የታሪኩን መዋቅር፥ ዝርዝር ሁኔታውንና ተከታታይ ጥቅሶቹን ልብ ብሉ ያጤነ፥ ታሪኩ እውነታ እንዳለው ይረዳል። (ማቴ. 19፡3-6 እና ሮሜ 5፡12-21፤ እንደዚሁም ሉቃስ 3፡38 እና ይሁዳ 14 አዳም ማለት የሰው ዘር ማለት ሳይሆን፥ እንድ ግለሰብ መሆኑን ነው የሚያመለክቱት።) 

ፈተናው 

አዳምና ሔዋን የተፈተኑበት ሁኔታ ታላቅ ትርጉም ያለው ሲሆን፥ ባንጻሩም ቀላል ነው። ቀላልነቱም በኤደን ገነት ካሉት እጅግ ብዙ ፍሬዎች መካከል አንዱን ብቻ ከመከልከላቸው አንጻር ሲታይ ነው። ክፉን ነገር በሙከራ እንዳያውቁ መከልከላቸው የእግዚአብሔር በረከት እንጂ፣ የሕይወታቸው ጉድለት አይደለም። በሌላ አቅጣጫ ስንመለከተው ግን እገዳው የሞት ወይም የሕይወት ጐዳይ ነውና ታላቅ ጠቀሜታ ነበረው። ትእዛዙን ማክበር፥ ወይም መጣስ፥ ለእግዚአብሔር ፈቃድ መዛትን ወይም አለመገዛትን የሚያሳይ ነበር። (እርግጥ አዳምና ሔዋን ሌላም ኅላፊነት ነበረባቸው። ለምሳሌ፡- የኤደን ገነትን መንከባከብ፡፡) በኋላ ግልጥ እንደሚታየው ክፉውንና መልካሙን የምታስታውቀው ዛፍ እውነተኛ ዛፍና እግዚአብሔር ይህንኑ እውቀት እንድታስተላልፍ መሳሪያ ያደረጋት ነበረች። 

የፈተናው ሂደት 

የሰይጣን ጥቃት በማባበል የተጀመረው በዘፍጥረት 3፡1 ነው። እግዚአብሐር አንዳች ነገር እስካልነፈጋቸው ድረስ ለነሱ መልካም አለመሆኑን ሔዋን እንድታምን ማድረግ ነበር የሰይጣን ሙከራ። ቁጥር 2 ላይ እንደተገለጠው የሷ መልስም እግዚአብሔር ሁሉን እንደፈቀደላቸውና አንድ ነገር መከልከሉ ቀላልና የማይጎዳቸው መሆኑን የሚገልጥ ነበር። የሰይጣን ስራ ሔዋን በእግዚአብሔር ቅር እንድትሰኝ ማድረግ ነበርና “እግዚአብሔር መልካም ቢሆን” ሲል ይጀምርና “አንዳችም ነገር አይከለከላችሁም ነበር። ነገር ግን የዚህን ዛፍ ፍሬ እንዳትበሉ ከልከሏልና መልካም ሊሆን አይችልም። በተቃራኒው የእኔ ዕቅድ እግዚአብሔር የከለከላችሁን ሁሉ እንድታደርጉ ይፈቅድላችኋል” የሚል ነበር ማታለያው። 

የዚህ አሳብ መንደርደሪያ ነጥብ፥ የምክንያት አደራደር ቅደም ተከተልን የተከተለ ነበር። መነሻው፣ ወይም ዋናው ነጥብ እገዳ መልካም አይደለም የሚል ነው። ቀጣዩ ነጥብ የእግዚአብሔር ዕቅድ እገዳን ይደግፋል የሚል ሲሆን ከዚህ በመነሳት ድምዳሜው የእግዚአብሔር ዕቅድ መልካም አይደለም፤ በተቃራኒው እገዳ የሌለው የሰይጣን ዕቅድ መልካም ነበር የሚል ሆነ። 

ሔዋንም ልትፈጽመው ስለወሰነችው ስሕተት ራሷን በራሷ ትክክለኛ ለማድረግ ምክንያቶቿን በሕሊናዋ ደረደረች። የተከለከለውን ፍሬ በመመልከት፥ ለምግብነት መልካም ነው ብላ አሰበች። ደግሞም እግዚአብሔር ጣፋጭና የተለያየ ምግብ ለሷ የማዘጋጁት ኀላፊነት እንደጣለባት በማስታወስ ይህን መልካም ፍሬ መመገብ በምን አኳኋን ስሕተት አይሆንም ብላ አመነች። ስለ ፍሬውም ማማርና የእውቀት ምንጭነት የተለመደ ምክንያቷን አቀረበች። እግዚአብሔር ያን ፍሬ እንዳይብሉ የመከልከሉ እውነት ከአእምሮዋ ጠፋ። ድርጊቱን መልካም ለማስመሰል በምታደርገው ጥረት የተነሳ እእምሮዋ በምክንያቶች የተሞላ ስለነበር እሷና አዳም የእግዚአብሔርን ፈቃድ በግልጥ በመጣስ ከፍሬው በሉ። 

የኃጢአታቸው ውጤቶች 

በዚህ ኃጢአት የተነሳ ቀጥሎ ያሉት ሁኔታዎች ተከሰቱ፣

1. እባብ በደረቱ እንዲሄድ ተፈረደበት (ዘፍጥ. 3፡14)። 

2. ሰይጣን ከሴቲቱ ከሚወለደው ዘር ጋር ጠላትነት እንዲኖረውና ክርስቶስን የሚያሳምም፥ ግን ሊያጠፋ የማይችል ቁስል (በተረከዙኝ እንዲሰጠው ተፈቀደለት (ቁ. 15)። እርሱ ግን ሕይወቱን የሚያጠፋ ቁስል (በራሱ) እንዲደርሰበት ተፈረደበት (“ራሱን” የሚለውን ቃል “ተረከዙን ከሚለው ጋር ያነጻጽሩ)። [በ1962 ዓ.ም. ታትሞ የወጣው የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ እሳቡ የሑዋንን ዘር “ሰኮና” ይቀጠቅጠዋል በሚል የተተረጎመ ሲሆን፥ በ1988 ዓ.ም. ተስሎ በታተመው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ግን እሳሱ ተረከዙን ይክሰዋል በሚል ተጽፏል። ]

3. ሔዋንና ሴቶች ሁሉ በፅንስ ጊዜ በጭንቅ እንዲወልዱና ለባሎቻቸውም ተገዢ እንዲሆኑ ተወሰነባቸው (ቁ. 16)። 

4. አዳምና ሰዎች ሁሉ በመሬት መረገም ምከንያት አድካሚ የሆነ ሥራ እንዲሠሩ ተወሰነባቸው (ቁ. 17-19)። 

5. የሰው ዘር ከእግዚአብሔር ጋር የነበረው ኅብረት ተቋረጠ፤ መንፈሳዊና ሥጋዊ ሞትም መጣ፤ ከኤደንም በረከት ተከለከለ። የአዳምና የሔዋን ኃጢአት የታሪክን አቅጣጫና የእነርሱን ዘር ሕይወት ሁሉ ቀየረ (ሮሜ 5፡12-21ን እንደገና ያንብቡ)።

ምንጭ፡- “የመጽሐፍ ቅዱስ ሥርዓተ ትምህርት ጥናት”፣ በዶክተር ቻርልስ ሲ. ራይሪ ተጽፎ፣ በሲሳይ ደሳለኝ የተተረጎመ እና በየላፕስሊ/ብሩክስ ፋውንዴሽን የታተመ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.