የግል ፀሎት ምንድን ነው?
አንተ ግን ስትጸልይ፣ ወደ እልፍኝህ ግባ፣ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፣ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሀል፡፡ ማቴዎስ 6፡6 ኢየሱስ ‹‹በስውር ላለው አባታችሁ ፀልዩ›› እንጂ ‹‹በስውር ስፍራ ወዳለው አባታችሁ ህልምን አልሙ፡፡›› አላለም፡፡ ፀሎት ፈቃድን ማስገዛት ይጠይቃል፡፡ ወደ እልፍኛችን ከገባንና በራችንን ከዘጋን በኋላ ልናደርግ የሚቸግረን ትልቁ ነገር ቢኖር መፀለይ ነው፡፡ አእምሮአችንን ለፀሎታችን ልንጠቀምበት በምንችለው ሁኔታ ማዘጋጀት […]