መላእክት
ሀ. የመላእክት አፈጣጠር መጽሐፍ እንደሚናገረው፥ እግዚአብሔር ሰውን ከመፍጠሩ አስቀድሞ ለቁጥር የሚያዳግቱ ሠራዊተ መላእክት ፈጥሯል። መላእክት ልክ እንደ ሰው ሕልውና ያላቸው ከመሆናቸውም በላይ፥ ታላቅ እውቀትና የግብረ ገብ ኃላፊነት ችሎታ አላቸው። “መልአክ” ማለት ልዩ በሆነ አገባሱና አገላለጡ መልእክተኛ ማለት ነው። ቃሉ አንዳንዴ ለሌሎች መልእክተኞች ማለት በራእይ 2-3 የተጠቀሱትን የሰባት የእስያ አብያተ ክርስቲያን መልእክተኞች ላመሳሰሉት መጠሪያ ሊሆንም ይችላል […]